June 29, 2011

(ሰበር ዜና) - የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መነኮሳት አስተዳዳሪውን አባረሩ


 • To Read in PDF, Click HERE.
 • ፓትርያርኩ በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ልመና አስተዳዳሪውን በኀይል ለማስገባት ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰምቷል፤
 • በአሁኑ ሰዓት የገዳሙ የውስጥ ጥበቃ በመጠናከሩ “ይመጣል” ከተባለው የፖሊስ ኀይል ፍጥጫ እንዳይፈጠር ተሰግቷል፤
 • ለገዳሙ ገቢ ለማስገኘት የተሠራው አዲሱ ሁለገብ ሕንጻ ከተቀመጠለት ዲዛይን ውጭ እና ከተገመተው ዋጋ በላይ ያወጣ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 29/2011)፦ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት “የገዳሙን ት/ቤት እና ሁለገብ የአገልግሎት ሕንጻ ከገዳሙ አስተዳደር በመለየት ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋራ በዝብዘዋል” ሏቸውን አስተዳዳሪውን መልአከ ሰላም ተክለ ማርያም ዘውዴን አባረሩ።

June 28, 2011

“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሚና በአየር ንብረት ለውጥ” የተሰኘ ጥናታዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ


 • TO READ IN PDF CLICK HERE.
 • “ቤተ ክርስቲያን ከአየር ንብረት ለውጥ ፈንዶች (ካርቦን ንግድ) ተጠቃሚ ልትሆን ይገባል”፤
 • በዓመት እስከ ከ150,000 - 200,000 ሄ/ር ደን ይራቆታል፤ በመልሶ ማልማት የሚተካው ከ2000 ሄክታር አይበልጥም፤ ለብሔራዊ ፓርኮች መጀመርና ለመንግሥት ደኖች መከለል መሠረት ለሆኑት የቤተ ክርስቲያን ተፈጥሯዊ የደን ይዞታዎች መንግሥት የሕግ ከለላ እንዲሰጥ ተጠይቋል፤
 • በሐዲስ  ኪዳን  ውስጥ ብቻ ለ1733 የበሽታ ዐይነቶች ፈውስ ሊሰጡ የሚችሉ 4200 የሚደርሱ የዕፀዋት ዓይነቶች መጠቀሳቸውን ተወስቷል፡፡
 • ለቅብዐ ሜሮን የሚሆኑት ዕፀዋት ውጤቶች በአብዛኛው ከግብፅ እና ከሱዳን የሚመጡ ናቸው፤ በሀገር ውስጥ የማልማቱ ጅምር እንዳለ ተጠቁሟል
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 28/2011)፦ የአየር ንብረት ለውጥን አሉታዊ ተጽዕኖዎች በመቀነስ እና ለውጡን በመግራት ተስማሚ የአኗኗር ሁኔታን ለመፍጠር በሚደረገው ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ አጋር ልትሆን እንደምትችል ተመለከተ፡፡

June 26, 2011

ቃለ ምልልስ ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ጋር


“አዲስ ጉዳይ” መጽሔት 
ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ጋር ያደረገው ድንቅ ቃለ ምልልስ ስለ “ተሐድሶዎች” እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደቀኑት አደጋ::
(Click HERE to read in PDF).

June 25, 2011

ነጋድራስ ጋዜጣ ስለ ዘማሪ እስጢፋኖስ


 • Read in PDF.
 • ደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥቢያ ወጣቶች “በአስተሳሰባቸው ትክክል ናቸው” ብሏል፤
 • ከሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት ጋራ “በሃይማኖትም እንደማይገናኝ” መስክሯል፤
 • የቅኔ፣ የድጓ እና የመጻሕፍት ሊቃውንት በየበረሓው ወድቀው እኛ ግን በገንዘብ ከብረናል፤ በስምም ታውቀናል፤ መተዳደሪያችንም ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ሆኖም ተሐድሶ በሚል ስያሜ የቤተ ክርስቲያንን መሠረት ለመናድ መሞከር አሳዛኝ ገጽታ ነው፡፡” (ዘማሪ እስጢፋኖስ ለነጋድራስ ጋዜጣ)
(ነጋድራስ ጋዜጣ፤ ዐርብ፣ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ.ም)፤ ከኦርቶዶክስ ዘማርያን አንዱ የሆነው እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ)፣ “የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ለመለወጥ ከተሰለፉ ተሐድሷውያን ጋራ አለመሆኔ ይታወቅልኝ” ሲል ገለጠ፡፡

June 24, 2011

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ እየጠየቀ ነው


 • Read this News in PDF.
 • “እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን፡፡›› (እስጢፋኖስ ሣህሌ)
 • በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሰባክያንንና እና ዘማርያንን የመከላከሉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፤
 • በጋሻው ደሳለኝ “በቪሲዲ የተሰራጨብኝ ማስረጃ በአኒሜሽን የተቀናበረ ነው!!›› አለ
 • በቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዋዜማ በሜጋ - ሞያሌ መንገድ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ምርትነሽ ጥላሁን እና አሰግድ ሣህሉ በሕክምና ላይ ናቸው
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 24/2011)፦ በደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የአካላዊ ቅጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል አንዱ የነበረው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (በቅጽል ስሙ ቄሴ) የሕገ ወጥ ‹ሰባክያን› እና ‹ዘማርያን› አካል እና አባል በመሆን ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች የተጸጸተ መሆኑን በመግለጽ ካህናት እና ምእመናን ይቅርታ እንዲያደርጉለት እየጠየቀ ነው፡፡ “እኔ ከእነርሱ የተለየሁት ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ነው፤በዘማሪ ፈቃዱ አማረ የጋብቻ ሥነ ሥርዐት ዕለት ወጣቶቹ የወሰዱት ርምጃ ስለ ቅንዐተ ቤተ ክርስቲያን የፈጸሙት እንጂ በግል ጥላቻ ወይም በስሜታዊነት ተነሣስተው አለመሆኑን አምኜበታለሁ” ያለው ዘማሪ እስጢፋኖስ ከሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ ለረጅም ጊዜ አብሮ ስለቆየበት ሁኔታ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “ከዛሬ  ነገ የተሻለ ነገር አያለሁ በሚል ተስፋ በማድረግ ነበር” ብሏል፡፡

ሲኖዶሱ እየሠራ ነው፤ እኛስ? ለፓትርያርክ ጳውሎስ ፲፱ኛ በዐለ ሲመት የተበከረተ

 ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ ከፌስቡክ የተገኘ ሲሆን ፀሐፊው ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ ናቸው። መልካም ንባብ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ታሪከ-ጡመራ
በዓመት ፪ ጊዜ በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ለሕዝብ መገለጥ ያለባቸውን ያህል ሳይገለጡ በመቆየታቸው ብዙ ችግሮች በወረቀት ላይ እንጂ በተግባር ባለመፈታታቸው ሲደመሩ ቆይተዋል። ፈጣሪ ፈቀደና ደጀሰላምም ፋና ወጊ ሆና ስለውሳኔዎቹ መስማትና ሀሳቡን መከታተል ተጀመረ፤ በእርግጥ ጥቂት ውሳኔዎች በሬድዮኖች በጣም ጥቂቱ ዘገባ ደግሞ በጋዜጦች ሲቀርቡ ቆይተዋል። ከዚያ ወዲህ ምእመናን የትኛው ሀሳብ ለምን ተወሰነ? ይኼኛው ለምን ቀረ? ወዘተ እስከማለት ደርሰዋል። በዚህም ሁላችንም የየግላችንን ሀሳብ ተለዋውጠናል። የእስከዛሬውን ወጥ አድርገን ብንገመግመውስ ለነገውም ጭምር የሚጠቅም አይመስላችሁም?

June 16, 2011

"ቅዱስ ሲኖዶስ ሲባንን" (የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ርእሰ አንቀጽ)

To Read in PDF Click HERE.
(መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ 56 ዓመት ቁጥር 120፣ ግንቦት 2003 ዓ.ም)፦ የዘንድሮው ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ሲኖዶስ ጉባኤ በየፈርጁ ያሳለፋቸው ወቅታዊ ውሳኔዎች ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መጠበቅና መጠናከር የሚበጁ፤ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በተገቢው መንገድ ለመወጣት የሚያስችሉ ከላይ እስከ ታች ሰላምንና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ ተገቢ ውሳኔዎች ናቸው፡፡

ስለ ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዘገባ

To Read in PDF, click HERE.
(ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ)፦ በመቐለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ የሚሰጠው ትምህርት ‹‹የርዳታ ሰጭ ፈረንጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት›› እንጂ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሰጥ በሲኖዶሱ የተፈቀደው የትምህርት መርሐ ግብር ባለመሆኑ ጉዳዩን ቅድሚያ ሰጥተውና በሚገባ አጣርተው ለሐምሌው ጉባኤ ሪፖርት የሚያቀርቡ የምሁራን ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲመደቡ ከግንቦት 10 - 16 ቀን የተካሄደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መወሰኑን ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዘገበ፡፡

June 15, 2011

“ዐገቱኒ ከለባት (ውሾች ከበቡኝ)” - የተባለ አዲስ መጽሐፍ ታተመ


To Read in PDF, Click HERE.
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 15/2011)፦  ወጣቱ ትውልድ በሃይማኖቱ ተነቃቅቶ አምልኮተ እግዚአብሔርን እያጸና፣ የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት እየተማፀነና እየመሰከረ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮና ትውፊት ለመጠበቅ በሚተጋበት በአሁኑ ወቅት ወጣቱን የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ሰለባ ለማድረግ በኑፋቄው የውስጥ አቀንቃኞች የሚፈጸመው ደባ ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት ከመድፈርና በወጣቱ ላይ ከመሳለቅ ተለይቶ እንደማይታይ “ዐገቱኒ ከለባት - ውሾች ከበቡኝ” በሚል ርእስ በሊቀ ትጉሃን ወንደሰን ተገኝ ተዘጋጅቶ ለገበያ የዋለው ባለ 35 ገጽ መጽሐፍ አከል ጽሑፍ አሳሰበ፡፡

አትሌት ኃይሌ የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶንን ካሸነፈ ሽልማቱን ለገዳም እንደሚሰጥ ቃል ገባ

(ዘሪፖርተር ጋዜጣ/ Wednesday, 15 June 2011):- አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶን ካሸነፈ የሚያገኘውን ሽልማት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኘው ጥንታዊው የአቡነ መልከ ጸዴቅ ገዳም በስጦታ እንደሚያበረክት ቃል ገባ፡፡

June 11, 2011

Deje Selam Back to Service

Deje Selam "blocking" solved. 
The service is back to normal now. Our technical team diagnosed the problem hindering our availability. Please inform all readers in Ethiopia to start using the blog.

June 10, 2011

የማ/ቅዱሳንን ሕትመቶች የሚገመግሙ ሊቃውንት ተመደቡ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 9/2011)፦ በማ/ቅዱሳን እና ከበላዩ ባለው በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ መካከል ለዓመታት ለዘለቀው አለመግባባት በመምሪያው በኩል በምክንያትነት የሚቀርበውን “ማህበሩ ሕትመቶቹን ለመምሪያው አያሳይም” የሚለውን ሰበብ ለመዝጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ባደረገው እንቅስቃሴ ከሊቃውንት ጉባኤ ሦስት ሊቃውንትን መመደቡን በድጋሚ አስታወቀ።

June 9, 2011

Leave Voice Message to Deje Selam

ደጀ ሰላም:- በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዜናዎችን፣ አስተያየቶችን፣ ጥያቄዎችን፣ መልሶችን የምታወጣ የጡመራ-መድረክ ናት።  ግለሰቦች ለሚጽፏቸው ጽሑፎች “ደጀ ሰላም” ኃላፊነቱን አትወስድም። ደጀ ሰላም ራሷ ያዘጋጀቻቸውን ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ብላ ትጠቅሳለች። ላፊነቱን የምትወስደው ለነዚያ ጽሑፎች ብቻ ነው። ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን 
dejeselam@gmail.com/ Or call at (+1) 703 776-9824

ተስፋ ኪ/ምሕረት የተባለው ማኅበር ተፈረደበት፤

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
 • የወሰደውን ገንዘብ እንዲከፍል ተወሰነበት፤
 (ደጀ ሰላም፤ ጁን 9/2011)፦ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና ልማት ማኅበር የሚባለውና በቅርቡ በሐዋሳው የአብያተ ክርስቲያናት ብጥብጥ ስሙ ጎልቶ የሚጠራው ማኅበር ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን እረዳለሁ በሚል  ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የወሰደውንና በምንጥቅም ላይ እንዳዋለው ማስረጃ ያላቀረበበትን 73 ሺህ ብር እንዲከፍል፣ እንዲሁም ንብረቱ እንዲታገድ ሲል የሐዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።

የተወደዳችሁ የ ቪኦኤ አዘጋጆች

(ጸጋ ብሩክ ነኝ ከአሜሪካ):- የፕሮግራማችሁ የዘወትር ተከታታይ ነኝ:: ስለዝግጃትችሁ ሁለ ገብነት እና አስተማሪነት ሁሌም ቢሆን በልበ ሙሉነት የምመሰክረው ሃቅ ነው:: በ6/08/2011 ዝግጅታችሁ ላይ አለማየሁ ከተባሉ አድማጭ የተላከ መልዕክት ብላችሁ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ያስተላለፋችሁት መልዕክት ግን እጅጉን አሳዝኖኛል:: ደብዳቤው የያዘውን ጭፍን ወቀሳ እና ክስ፣ ጭብጥ የሌለው በማስረጃ  ያልተደገፈ አስተያየት ምንም ሳትመዝኑና የሚመለከተውን ወገን ለጥያቄ ወይንም ላስተያየት ሳታዘጋጁ የዚህ ማኅበር አባልና ደጋፊ የሆኑ አድማጮቻችሁን ከግምት ሳታስገቡ በማቅረባችሁ ምንም እንኳን የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም እጅግ  ስህተት እንደሰራችሁ ይሰማኛል::

June 8, 2011

በስምዐ ጽድቅ ኅትመት ላይ የተጣለው እገዳ ተነሣ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
 • “እገዳው በአጣሪ ኮሚቴው ሥራ ላይ እንቅፋት ሊፈጥር ይችል ይሆናል፡፡” (የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት)
 • እነ አባ ሰረቀ ደብዳቤው ከመዝገብ ቤት እንዳይወጣ ለማሳገድ ሞክረዋል::
 • የዋና ሓላፊው ሕገ ወጥ እግድ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስቆጥቷል፤ የጠቅ/ቤ/ክ ሓላፊዎችን አሳዝኗል
 • የአባ ሰረቀ እግድ በዋ/ሥ/አስኪያጁ መሻሩ ዋና ሓላፊው በሕገ ወጥ መግለጫቸው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እወስዳቸዋለሁ ያሏቸው አስተዳደራዊ ርምጃዎች ከድብቅ ዓላማቸው የሚመነጩ ከመሆናቸው ውጪ መሠረተ እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 8/2011)፦  በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በየ15 ቀኑ እና በየወሩ በሚያሳትማቸው የስምዐ ጽድቅ እና የሐመር መጽሔት ኅትመት ላይ በመምሪያው ዋና ሓላፊ በሕገ ወጥ መንገድ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሣቱን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ስምዐ ጽድቅ ታተመች

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 7/2011)፦ ከሥርዓት ውጪ በተደረገ ደብዳቤ እና የስልክ ልውውጥ ሕትመቷ ተስተጓጉሎ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጋዜጣ ስምዐ ጽድቅ በዛሬው ዕለት በሌላ ማተሚያ ቤት ታት መሠራጨ ጀምራለች። ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በመታተም በሕትመት ብዛት እና ረዥም ዓመታት በማሳለፍ ቀዳሚ የሆነው ይህ ጋዜጣ ለብዙ ጊዜያት ያለመታተም እንቅፋት ቢገጥማትም እንደ አሁኑ ከፍ ያለ ፈተና እንዳልደረሰት ምንጮች አስረድተዋል። ብዙዎች ምዕመናን “መምህራችን” የሚት ጋዜጣ መቋረ በደጀ ሰላም ከተዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱን የተረዳን ሲሆን ቤተ ክህነቱ አሁን በያዘው መልኩ የሚሔድ ከሆነ ምዕመናን የራሳቸውን መፍትሔ ወደ መፈለግ እና በደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንደታየው ዓይነት “ጉልበት ወደ መጠቀም” የመሰለ አላስፈላጊ መፍትሔ እንዳይዘዋወሩ አስግቷል።

June 6, 2011

ሰበር ዜና - የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ኅትመት ታገደ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
 •  እግዱ አባ ሰረቀ ለሜጋ ማተሚያ ኢንተርፕራይዝ የጻፉትን ደብዳቤ እና የብሮድካስት ባለሥልጣን ለኢንተርፕራይዙ ሰጥቶታል የተባለውን የቃል ትእዛዝ መነሻ ማድረጉ ተነግሯል
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 6/2011)፦ ከ1985 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በሕትመት ላይ የነበረው እና በማ/ቅዱሳን የሚታተመው ስምጸ ጽድቅ ጋዜጣ እንዳይታተም እገዳ እንደተጣለበት ምንጮቻችን አስታወቁ። የጋዜጣው አሳታሚ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት እና የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ጽ/ቤት አባላት ከመምሪያው ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ ተወያይተዋል፡፡

June 5, 2011

ሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን በደብረ አሚን ተ/ሃይማኖት የከረረ ተቃውሞ ገጠማቸው፤ የተጎሸሙም አሉ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
 • የደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምክሐ ደናግል ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በአሸናፊ ገብረ ማርያም፣ ዳግማዊ ደርቤ፣ እስጢፋኖስ ሣህሌ፣ ምርትነሽ ጥላሁን እና ሌሎች መሰሎቻቸው ላይ የአካላዊ ቅጣት ርምጃ በመውሰድ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን አባረሩ፤ ከተባረሩት ውስጥ የሕገ ወጦቹን ሥራ በማተም እና በማከፋፈል ተባባሪ የሆኑ ‹‹መዝሙር ቤት›› ባለቤቶች ይገኙባቸዋል፤ ወላዋይ አገልጋዮችም አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል
 • ወጣቶቹ ሕገ ወጦቹን የቀጡበት አኳኋን ጉዳዩ የሚመለከተው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፍተኛ አስተዳደር ሕገ ወጦቹን በተጨባጭ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ የምእመኑ ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን እንደሚያመለክት ተገልጧል
 • ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝም በማለታቸው ይህን ርምጃ ለመውሰድ ተገደናል፤ የተክለ ሃይማኖት ድል በዮሴፍም ይደገማል፤ ሕገ ወጦቹን ከአዲስ አበባ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በማጽዳት የሐዋሳን ምእመናን እምባ እናብሳለን፤ ሃይማኖታችንን መጠበቅ ብቻ ማእከል ያደረገው ርምጃችን ሕገ ወጦቹ ስሕተታቸውን አርመው የበደሉትን ምእመን ይፋዊ ይቅርታ እስኪጠይቁ አልያም ለይቶላቸው ወደ መናፍቃኑ ጎራ እስኪገቡ ድረስ ይቀጥላል!!››  (የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች)

June 4, 2011

የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› አመራሮች ላይ የእስር ቅጣት ወሰነባቸው

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 4/2011)፦ የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚያዝያ ወር ውስጥ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ባስነሡት ብጥብጥ በንጹሐን ምእመናን ላይ ከፍተኛ የድብደባ ወንጀል ፈጽመዋል ባላቸው አራት የ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› ማኅበር አመራር በሆኑ ተከሳሾች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሐሙስ፣ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ገዛኸኝ አበራ እና አየነው የተባሉት ግለሰቦች በ8 ዓመት፣ ተስፋዬ በ5 ዓመትና ጌታሁን የተባሉት ደግሞ በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

June 3, 2011

የወ/ሮ እጅጋየሁ ቃለ ምልልስ ከቁምነገር መጽሔት ጋር

Photo: Courtesy of Addis Journal.
To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክህነት አካባቢ እንደ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አወዛጋቢ ሴት የለም፡፡ ወ/ሮ እጅጋየሁ የዝነኛው ድምፃዊ የማህሙድ አህመድ የቀድሞ ባለቤት ናቸው፡፡ ከድምፃዊው ጋር የፍርድ ቤት የፍቺ ጣጣቸው ገና አልተቋጨም፡፡ ዝነኛውን ማህሙድ ሙዚቃ ቤትን ሽጠው ብሩን ተካፍለውታል፡፡ “ እሱ ነው ይሸጥ ያለው” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ወ/ ሮ እጅጋየሁ ከፓትሪያርኩ ጋር ስማቸው አብሮ ይነሳል፤ “ፈላጭ ቆራጭ እርሳቸው ናቸው” በሚል፡፡ ቁም ነገር መጽሔት ያተመው የሴትየዋ አስገራሚ ቃለምልልስ በከፊል ይህን ይመስላል፡፡

ጥያቄ፡- በነገራችን ላይ ወ/ሮ እጅጋየሁ እድሜሽ ስንት ነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- እግዜአብሄር ይመስገን 66ኛ ዓመቴን ጨርሻለሁ

German Radio About Holy Synod


German Radio About Abba Sereke Press Release


June 2, 2011

ስለ እግዚአብሔር የሚገዳቸው ብፁዕ አባት

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።


(ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ ፤ ተባባሪ ፕሮፌሰር):- ለተመረጡት ሞት እረፍት መሆኑን ባምንምና ብፁዕ አባታቻን አቡነ በርናባስም የእድሜ ባለጸጋ መሆናቸውን ባውቅም እረፍታቸውን ስሰማ ማዘኔ አልቀረም። በተለይ በዚህ ወቅት እንደዚህ አይነት ብፁዕ አባት አስፈላጊነቱ ግልጽ ስለሆነ። ብፁዕነታቸውን በአጭሩ ለማሰብ ነው አነሳሴ። 

ብፁዕ አባታችንን በአካል የማውቃቸው ከዛሬ አስራ አምስት ዓመት በፊት ከሁለት ዓመት በላይ በቆየሁባት የባህር ዳር ከተማ ነው።  በወቅቱ በከተማው በሚገኘው ሽምብጥ ሚካኤል ከነበረው የሰራተኞች ጉባኤ ጋር በተያያዘ እንዲሁም ለባህር ዳር ፓሊ ቴክኒክና ለባህር ዳር ፔዳ ተማሪዎች መሐል ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወርኃዊ ጉባኤ ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት ጋር በተያያዘ አገኛቸው ነበር። በወቅቱ የማኅበረ ቅዱሳን አባል መሆኔን መግለጽ ሳያስፈልገኝ ብፁዕነታቸው ስለ ማኅበሩ እንቅስቃሴ የነበራቸውን በጎ አመለካከት ግልጽ ነበር። ይህ የብፁዕነታቸው  አባታዊና መንፈሳዊ እይታ በወቅቱ የነበረውን ማኅበሩን በፓለቲካ የመጠርጠር  የአካባቢው የመንግሥት አካል ስጋት በሚያውቁት መጠን ለማስረዳት አስችሏቸው እንደነበር አውቃለሁ።

ተዋሕዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እነማን ናችሁ?

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
(ታምራት ፍስሃ):- ክብር የሚገባህ አምላካችን እግዚአብሄር ሆይ ፦ የለማት ሁሉ አስገኝ፣ የፍጥረታት ሁሉ ጌታ፤ እኔ ልጅህ እንዳልል የአባትነት ክብርን ያልሰጠሁህ፣ እኔ ባሪያህ እንዳልል የጌትነት ትእዛዝህን ያልፈፀምኩ ለምንም የማልጠቅም የወደቅሁ ሰው ስሆን አሁን ግን እንደ አዋቂ፣ ጥበብን ገንዘብ እንዳደረገ በደምህ ስለዋጃሃት ቤተ ክርስቲያን በድፍረት እናገር ዘንድ ራሴን አዘጋጅቻለሁና ማስተዋሉ አቅቶኝ ፍቅሩ ጎድሎኝ አንተን የሚያሳዝን ቃላትንና ረጋትን ብጠቀም ስለ ተወዳጇ እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ይቅርታህን እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ፡፡ አምላክ ሆይ አንተ በእውነት ምስጋና ይገባሃል፡፡

ከሐዋሳ የመጡ የጌታቸው ዶኒ ልዑካን ጳጳሳትን ሲሰድቡ ዋሉ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 1/2011)፦ ትናንት ከቀትር በፊት የአባ ሰረቀን ጋዜጣዊ መግለጫ ያስተናገደው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ሕንፃ በሌላው የስብከተ ወንጌል አዳራሹ ደግሞ ጌታቸው ዶኒ አላግባብ ከተሰጠው የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን በቅዱስ ሲኖዶስ መወገዱን ለመቃወም ነው በሚል የመጡ ቡድኖች ከአቡነ ጳውሎስ እና ከአራት ሊቃነ ጳጳሳት (ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ) ጋራ ያካሄዱትን ዛቻ እና ኀይለ ቃል የተመላበት ስብሰባ እያስተናገደ ነበር፡፡

Voice Messages to Deje SelamJune 1, 2011

ትዕቢት እና ዕብሪት (arrogance) የመላባቸው የአባ ሰረቀ መግለጫዎች

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 1/2011)፦
 • አባ ሰረቀ ትናንት የሰጡትን መግለጫ የማ/መምሪያው ሊቀ ጳጳስ ያውቁት እንደ ሆነ ሲጠየቁ ‹‹አይመለከታቸውም፤ ውሳኔዎችን የማስፈጸም አስተዳደራዊ ሥራ የእኛ ነው፤ እርሳቸው ለክብር ብቻ የተቀመጡ ናቸው›› ብለዋል፤ እርሳቸው ‹‹ወልደ ሳሙኤል›› የተባሉበትን የደብረ ዐባይ ቅዳሴ ሞያ የት እንዳሳዩት ባይታወቅም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የተዘጋ ቤተ ክርስቲያን ከማስከፈት ጀምሮ ሊቀ ማእምራን የተሰኙበት መዓርገ ዲቁና እና መዓርገ ቅስና ለእርሳቸው ‹‹ሥርዐቱን ያልጠበቀ›› ከመሆኑም በላይ ‹‹አሐዱ አብ ብለው የማይቀድሱበት፣ ነአኵቶ ብለው የማያመሰግኑበት ያለትምህርት ከሚገኘው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ›› ተለይቶ እንደማይታይ ተናግረዋል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)