May 22, 2011

(ሰበር ዜና) - ጌታቸው ዶኒ ከሥራ አስኪያጅነቱ እንዲባረር ብዙኀኑ የሲኖዱሱ አባላት የደረሱበት ስምምነት በፓትርያሪኩ ተቃውሞ ገጠመው፤ የቅ/ሲኖዶስ 5ኛ ቀን ውሎ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ
  • የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪም ከሐላፊነታቸው ይነሣሉ
  • ፓትርያሪኩ እና አቡነ ጎርጎርዮስ በውሳኔው ባለመስማማት ጌታቸው ዶኒ ‹‹መናፍቅ›› መባሉን ተቃውመዋል
  • ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውጤት የሌለው ውኃ ወቀጣ ሆኗል፤ ከግለሰብ ይልቅ ለእግዚአብሔር እና ለቤተ ክርስቲያኑ መወገን አይሻልም ወይ;››(ብፁዕ አቡነ በርናባስ)
  • ‹‹እንዴት በተሐድሶ/ኑፋቄ መኖርን በተመለከተ ድርድር ውስጥ ይገባል;››(ብፁዕ አቡነ ኤልያስ)
  • የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በመላ ወይም በከፊል ወደ ሐዋሳ ወርደው፣ ጉባኤ ሠርተው ያዘነውን ምእመን ያጽናናሉ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 22/2011)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ ግንቦት 14፣ 2003 ዓ.ም አምስተኛ ቀን የዕለተ ሰንበት ውሎው በሲዳሞ ሀገረ ስብከትን የተከሠተውን ችግር አስመልክቶ በተያዘው አጀንዳ ዙሪያ የጋለ ክርክር የተሞላበትን ውይይት በማካሄድ ‹‹ሊቀ ካህናት›› ጌታቸው ዶኒ ያለአግባብ ከተሰጠው የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ እንዲባረር ወስኗል፡፡ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ‹‹በውሳኔው አላምንበትም›› ብለዋል፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ አቋም በልዩነት ተይዞ ጌታቸው ዶኒ ከሐላፊነቱ እንዲነሣ ምልአተ ጉባኤው ከቀትር በፊት የደረሰበትን ስምምነት አቡነ ጳውሎስ ከቀትር በኋላ በማፍረስ በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ተዘጋጅቶ በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹ስለማላምንበት አልፈርምም፤›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ በዚህ ሳቢያ ጉባኤው ወደ ቀጣዩ የሰንበት ት/ቤቶች እና የማኅበረ ቅዱሳን ግንኙነት አጀንዳ ከመሻገር ተገትቶ ከፓትርያሪኩ እና ሰልፋቸውን ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ካደረጉት አቡነ ጎርጎርዮስ ጋራ የጋለ ክርክር ሲያካሂድ አምሽቶ ማምሻውን ያለውጤት ተነሥቷል፡፡

የጉባኤው ምንጮች እንደተናገሩት የሐዋሳ ችግር አጣሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በጌታቸው ዶኒ ከሐላፊነት መባረር በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ተስማምተው ነበር፡፡ ከቀትር በኋላ ግን ጌታቸው ዶኒን በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ‹‹ሊቀ ካህናት›› በሚል ማዕርገ ቅስና የሰጧቸው ብፁዕ አቡነ ገብርኤል መሆናቸውን በማስታወስ ‹‹ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ መናፍቅ እንደሆነ በቀረበው ማስረጃ አላምንበትም›› በሚል ልዩነታቸውን አጠናክረው የቀረቡትን አቡነ ጳውሎስን በመደገፍ የአቋም ሽግሽግ አድርገዋል ተብሏል፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርት እና ሹመት ካፈራናቸው መካከል ጥቂቶች ያልተለወጡ እንደሌሉ ሁሉ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒም በወቅቱ ደኅና እንደነበሩና ዛሬ የተለወጡ መሆኑን ያስረዱት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ በበኩላቸው በጌታቸው ዶኒ የሃይማኖት ሕጸጽ እና ለሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የማይበቁ በመሆናቸው በመነሣታቸው እንደሚያምኑበት አስረድተዋል፡፡ የውይይቱን ሂደት ‹‹ውኃ ወቀጣ ሆኗል›› በሚል የጠዋቱ የምልአተ ጉባኤ በመከለሱ ማዘናቸውን የተናገሩት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ‹‹ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር፣ ከግለሰብ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መቆምና መወገን አይበልጥም ወይ;›› ብለዋል፡፡ እርሳቸውን በመከተልም ‹‹እንዴት በዚህ ጉዳይ ድርድር ውስጥ ይገባል; እንዴት መናፍቅ አይደለም ይባላል;›› በሚል አቋማቸውን በጠነከረ ስሜት የገለጹት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኤልያስ ናቸው፡፡ በቀደሙት አጀንዳዎች አቡነ ጳውሎስን ሲደግፉ የቆዩት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በውይይቱ ላይ ዝምታን መምረጣቸው ተገልጧል፡፡ አቡነ ገብርኤል ከሾሙት በሚል ዕርቅም የጠየቁ ነበሩ፤ ‹‹ጉዳዩ የሃይማኖት ልዩነት ነው፤ በዕርቅ የሚፈታ አይደለም›› በሚል ተመልሶላቸዋል፡፡ 
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከቀትር በኋላ በታየው የፓትርያሪኩ
 ግትርነት በማዘን ጉባኤውን ትተው መውጣቸው ተሰምቷል፡፡ ሁኔታው ‹‹ምልአተ ጉባኤውን በማሰላቸት በቀጣዩ አጀንዳ አቋሙ እንዲላላ አልያም ተስፋ እንዳይኖረው የማድረጉ ስልት ቀጣይ ገጽታ›› እንደ ሆነ ያመለከቱት ታዛቢዎች ሲኖዶሱ ወስኖበት ባለፈው አጀንዳ ላይ ከመቸከል ይልቅ የፓትርያሪኩ አቋም በልዩነት ብቻ ተይዞ ወደ ቀጣዩ አጀንዳ ቢሻገር መልካም እንደሚሆን መክረዋል፡፡ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎችም ጌታቸው ዶኒ ‹‹መናፍቅ ነው›› ከሚለው ጋራ ፓትርያሪኩ በትክክለኛው መንገድ ሥራ አስኪያጅ አድርገው እንዳልሾሙት በማጋለጥ ነገሩን በቀላሉ መሻገር ይቻል እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ከዚሁ ጋራ በተያያዘ ቀጣዩን ለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት የሚመጥነውን ሰው ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል መርጠው እንዲያሳውቁ፣ የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል ኀይለ ጊዮርጊስም ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ከፓትርያሪኩ በቀር ምልአተ ጉባኤው ተስማምቶበት ነበር፤ የገዳሙን አለቃ የሚሾሙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ናቸው፡፡ ከተቻለ መላው የምልአተ ጉባኤው አባላት አልያም ከፊሎቹ ወደ ሐዋሳ በማምራት ጉባኤ ሠርተው ለረጅም ጊዜያት ያዘነውን ምእመን እንዲያጽናኑም ከቀትር በፊት ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን እና በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ላይ በቀጣይ እንደሚወያይ የተጠበቀው ጉባኤው የሐዋሳውን ጉዳይ ሳይቋጭ ለነገ ተላልፏል፡፡ በአንዳንዶች አስተያየት የፓትርያሪኩ አቋም በትላንቱ የጉባኤ ውሎ ‹‹በወዘተርፈ›› የታለፈውን የሐውልቱን መነሣት እና ሌሎች ያልተፈጸሙ ውሳኔዎችን እንዲያነሡ ሳይገፋፋቸው እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

24 comments:

Anonymous said...

ስለጌታቸው ዶኒም ሆነ ስለሌሎች መናፍቃን መሆን ብዙ ብዙ ይወራል። ይሁን እንጂ መናፍቅ ይሁን ከሃዲ ቤተክርስቲያን አውግዛ ከአንድነት የምትለየው በያዘው ልቀቀው ወይም በመረጃ አለኝ ጋጋታ ሳይሆን በዚህ ጉዳይ ተጠርጣሪው በቤተክርስቲያን ጉባዔ ተጠርቶ እምነት ክህደቱ ተጠይቆ፤ ቢከራከር በመጽሐፍና በእምነት መሰረት ጥቅስ ከትርጉም ተሰጥቶት እንዲመለስ፤ እምቢ ቢል ከመንጋው በውግዘት እንዲለይ የማድረጉ ስራ የቆየ የአባቶች ወግ ነበር። ዛሬ ግን እገሌ የተባለውን ግለሰብ የኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት ህጸጽ እንዳለበት ስለማውቅና እያስተማረም ተሳስቶ ፤ማሳሳቱን ማስረጃ ስላለኝ ጉባዔ ላይ ይጠራልኝ ከማለት ይልቅ በየስብሰባው ላይ ክስና ውንጀላ እያንጋጉ አስፈንጥሮ ለመጣል የሚደረገው ሩጫ ከቤተክርስቲያን ቅንዓት የመነጨ ሳይሆን የግል ግብን በተገኘው አጋጣሚ ለማሳካት የሚደረግ ሰይጣናዊ ሴራ ነው። የጉባዔ ክርክር መጥራትና መናፍቅናንን ረትቶ መመለስ ወይም እምቢ ካሉ በውግዘት መለየት እኮ በበሰለ እውቀት የሚደረግ እንጂ በነጠላ ተሸፋፍኖ ከበሮ በመደለቅ አይደለም። እግዚአብሔር ለከሳሾችም፤ለተከሳሾችም አስተዋይ ልቦና ይስጥልን።

Orthodoxawi said...

እንደፈራሁት "ውኃ ወቀጣው" አልቀረልንም።
ብፁዓን አባቶች መቸም በአባ ጳውሎስ አቋም ተሰላችተው ቤተክርስቲያንን ለወሮበሎች አሳልፈው እንደማይሰጧት ሰስፋ አደርጋለሁ። አሁን አሁን እንደተለመደው ጨጓራዬን ከመምለጥ በተጨማሪ "መፍትሄው ምን ይሆን?" እያልኩ ሳሰላስል እውላለሁ።

የተሃድሶው ጉዳይ ከታች እስከላይ እንደተዳረሰ የእነ አቡነ ጎርጎሪዎስ አካሄድ አመላካች ነው። ተኩላው ለምድ ለብሶ ከገባ ቢቆይም አሁን ራሱን እየገለጠ ነው። ጠላትን ማዎቅ ትልቅ ድል ነውና ብፁዓን አበው በጀመራችሁት አካሄድ ቀጥሉበት። የነብሩን ጅራት ጨብጣችሁታል ከዚህ በኋላ ብትለቁት የኋለኛው ጥፋት ከፊቱ እጅግ የከፋ ይሆናል።

ከዚህ በኋላ ከመንግስት አካላት ጋርም ጠንከር ያለ ውይይት ማድረግ አለባችሁ። መንግስት አሸባሪነትን እዋጋለሁ ይለናል። ምነው ታዲያ የዚህን ሁሉ ብጥብጥ ፈታውራሪ አባ ጳውሎስን ዝም አሏቸው?

ለመንግስት ቅርብ የሆናችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች እስኪ ቀረቤታችሁን ተጠቀሙበት።

የሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ ነውና የምትችሉ ሁሉ ስለ ቤተክርስቲያን ጩሁ! ለምኑ! አልቅሱ!።
እግዚኦ መሀረነ በሉ!

eyob said...

plz our Fathers be strong!!!!!!!!!!!!!!!!!!
OHHHHHHH no Argument Abt Getachew Doney, he is MENAFIK!

Anonymous said...

dejeselamawyan yetebalew yetetereterew ewenet new malet new? yegermal


tadiwos

A3A said...

Because he himself is ,,,,,Now I can say that he promote # tehadeso # with in the church intentionally.

T/selase said...

ደግሞ ለታጣቂው ለጌታቸው ጥብቅና ያሳዝናል፣ አሁን መስጋት ለቀጣዩ አጀንዳ ነው፣ እስቲ የስብሰባውን መጨረሻውን እ/ር ያሳምረው::

Anonymous said...

Endeferon lbachewn yadenedenut Amlak beteamr betun liyatsed yihon?

ርብቃ ከጀርመን said...

አድህነነ እግዚኦ ኦ ዘአዳንካ ለሀገረ ነነዌ በትንብልና ትንብልና ሳህል! እኒህሰውየ ሊያጠፉን ነው የመጡብን እና ትልቅ እግዚኦታ መታወጅአለበት ሁሉም በያለበት በጸሎት አንድይሁን ታመዋል የጤነኛ መንፈሳዊ አባትስራ አይደለምናስራቸው ወላዲተአምላከ አስራትሀገርሽን አትርሻት መሀርወልድየ ተዘከርኪዳንየ ብለሽ ከዚህ ጥፋት በምልጃሽ ታደጊን ከማለት ውጭ ምንይባላል!

Mesi said...

Kedusan Abatochachen Embrhan kenant gar tehun Amen!

Anonymous said...

የመጀመሪያዉ አስተያየት ሰጭ አቶ ጌታቸዉ ዶኒ እኮ የራሱ የእምነት ድርጅት የመሰረተና በራሱ ጊዜ የተለየ ሰዉ ነዉ። አሁን ምን ይደረግለት ብለህ ነዉ ልባችንን የምታወልቀዉ? ራሱ ስለመሰረተዉ የኑፋቄ ድርጅት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አይተህ ስለዶኒ የምተከራከር ከሆነ አንተም ተበልተህ አልቀህ እንዳይሆን ፍራ - እኔ ፈርቸልሃለሁ። አካፋንስ አካፋ ካላሉት ቆይቶ ምናምንቴ ትምህርቱን ባዉደምሕረታችን ሲያስተምር ማን ሊሰማ ነዉ? ደግሞ የሚጠነቀቀዉ 'ወርቅ ያለዉ' እንጂ 'ድንጋይ ያለዉ' አይደለም። የበሰበሰ ዝናም አይፈራምና ሰዉየዉ አንዴ በክህደት አዙሪት ዉስጥ ስለገባ ሌላዉን ከመበከሉ በፊት መወገዙ ለቤተ ክርስቲያንም ለራሱም/ለቁንጥጫ/ የሚጠቅም ይመስለኛል።

Anonymous said...

The first commenter,
Do you think Getachew Doni will reveal his heresy in front of us, anymore? Don't you know that, tehadiso protestants are playing double standards while in Tewahido. Infact Muluwongels need their 'militiamen' like Doni to stay within EOTC. Both to weaken Tewahido and to spread their heresy.

Anonymous said...

ጌታቸው፡ዶኒ፡የእናት፡አባቱን፡ሃይማኖት፡ከመክ
ዳቱም፡ባሻገር፣በአሁኑ፡ወቅት፡ተዋሕዶን፡ከውስ
ጧ፡ገብተው፡ለማፍረስ፡ከሚታገሉት፡ፕሮተስታ
ንቶች፡አንደኛው፡መናፍቅ፡ነው።ለ"አባ፡ ሰ ረ ቀም፡በጻፈው፡ላይ፡እንዳመለከተው፡ተዋሕዶዎ
ች፡ነቅተው፡ሳያባርሩን።"እንጣላቸው!"ብሎ፡፡
በግልጽ፡አላማቸውን፡ጠቁሞ፡የል?የታጠቀው፡ሽ
ጉጥም፡ከዚህ፡አላማው፡ጋር፡የተሳሰረ፡የሰብከተ፡ሞ
ት፡መሣርያው፡አይደለምን?

ይህ፡ሰው፡የጣዖቱን፡ሐውልት፡ካቆሙት፡አንደኛ
ውና፡ዋና፡አንቀሳቃሽ፡እንደነበረ፡የራሱም፡ሰነዶ
ች፡ይመሰክራሉ!ጣኦቱ"የጌታቸውን፡መባረር፡ነ
ግ፡በኔ፡በማለት፤በዚህም፡ጭምር፡በመቃወሙ፡አ
ንገረምም!

የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ደፍረው፡ያስደፈሩትን፡
መናፍቃን፡ለማስወገድ፡በትጋት፡እንሥራ!

ጌታቸውና፡አለቃው፡የጥፋት፡ምልክት፣የአውሬው፡
አገልጋዮች፡ስለሆኑ፡በተጋድሎ፡የምትገኙት፡አባቶ
ች፣ይህን፡ተገንዝባችሁ፡እኒህን፡ሰርጎ፡ገቦች፡በቆራ
ጥነት፡አስወግዷቸው!!!

መላው፡ሕዝበ-ተዋሕዶ፡አብረናችሁ፡ቆመናል!!!

"አባ፡፡ጳውሎስ፡ይውረዱ!!!
ገታቸው፤ዶኒና፡"አባ"ሰ ረ ቀ፡ ይወገዱ!!!

መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡የተዋሕዶን፡ጠላቶች፡
በሙሉ፡ያስወግድልን!!!አሜን።


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

አባቶቼ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን የገጠማችሁ ፈተና ቀላል አይደለምና በርቱ ጸኑ ያለበለዚያ የበለጠው ከፊት አለ

ዘካርያስ ጋሻው said...

"የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።

አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።"
መዝሙር 78:8

ዮሀንስ ጋሻው said...

"ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።

ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።"
መፅሐፈ ምሳሌ 29 :1-2

Unknown said...

Mechem bihon betekiristianachin tekorkari yatach iyemeselen new.Tinante beNikia gubae ariyosin yeleye Igziabher Berasu tibeb yesu yalhonutin hulu kebutu indiyatsedalin hulachinim intseliy.Geta ignanim befetenawoch hulu indanwodk yitebiken amen.

123... said...

ለመጀመርያ አስተያየት ሰቺ
የ ቀደሙት አባቶች አኮ ጉባኤ ሰርተው አምነት ከደት የሚጠይቁት የካደውም አንደ አሁኑ ተሃድሶ ዘ ፕሮቴስታንት አይነት መስሎ አይሸፋፈንም ባደባባይ ክደቱን የሚናገርበት ዘመን ነበር። አሁን ዘመኑ መስሎ ግን ማፍረስ ነው የተያዘው በምሆኑም አንድ ሰው ከ በንግግር ከሚያወጣው ቃል በላይ ተግባሩ ጉባኤ ተሰርቶ ከሚናገረው የ አምነት ከደት ቃል በ አጅጉ የላቀ አና አሳማኝ ነው። ለ ጣኦት ተንበርክኮ ሲሰግድ የታየን ሰው ጉባኤ ፀራለታለህ ወይስ አውግዘህ ለይተህ ቀኖና ይሰጠው ትላለ? አንዳተ አባባል ጉባኤው ''ቅድም ጣኦቱ ጋር ስትሰግድ ያየሁህ አንተነህ ወይስ ሌላ?'' ብሎ አንድጠይቀው ነው የሚፈለገው? በትክክል መረጃ ሌለው ነገር ግን ባንዳንድ ምልክቶች በ ትምርቱ ሕፀፅ ላለበት ነው ጉባኤ የምአስፈልገው። ለ ንግግር ችግር በ ጉባኤ ይረጋገጣል ተግባር ግን ከላይ ለ ጣኦቱ አንደሰገደው ሰውዬ ያለ ጥያቄ ይጠየቅ ማለትህ ግር ያሰኛል። አባቶቻችንም ያረጉት የነበረው ይሄንኑ ነው።

Unknown said...

Amlake Kidusan Ebakeh temelketen!!!!!!!! bemehireteh Gobegnen Abetu endechereneteh enji endebedelachin ayihun amlk hoy ebakehin seyitan Des endayilewu belehe maren yihenin fetena astagselen!!!
yegnan yewegenochehin hatiyat atemelketebin . oh!!! amlakene Meharene Lepapasiene pawulos we Gorgoriose III .......
Ere minewu Abune Gorgorios degmo Basebachewu min metabachewu newu? beselam newu gin????????? newu weyenis Abune Pawulos Yehone engedih cheger agegntewubachewu eyassferarwuachewu selehone newu wey Zeway!!!!!!!! Ahun endewu Abune Gorgorios II betekemetubet wenber Abune Gorgorios III tekemtewu endih yihunu ere yihe bewunet amlak tetaltonal enji beselam ayimeslegnem becha Enamnalen amlakachin Sinesa kemanim zegyito yetenesa bimeslenim siders gin kemanim kedmo newuna abatochachinin atsenteh fetneh dereselin belene enechuh lela min yibalal.

Egzio maherene Keristose benetemariyam, bente melaekt ,beinte kidusan , bente semaetat meharene kiristos.

Anonymous said...

ዕዳ ገባን እኮ ጎበዝ! እስኪ የመጀመሪያውን አስተያየት ሰጭ ምን ትሉታላችሁ? እንዲህ አይነት ፌዝ ማን አስተማረህ እባክህ! አንተና መሰሎችህ እስከዛሬ ታነበንቡት እንደነበረው "ማስረጃ የላችሁም፣ ጥቅማችሁ ስለተነካ ነው ..." እያላችሁ ተመሳስላችሁ ለመኖር ታደርጉት የነበረው ጥረት እንገትህ ደርሶ በቃኝ እስክትል ድረስ በማስረጃ ተደግፎ ሲቀርብልህ አሁን ደግሞ የመጥፊያችሁ የጣር ድምጽ መሆኑ ነው? አትድከም አሁን እንኳ ጉድጓዳችሁ የተማሰ ይመስለኛል። በራሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ከድቶ ኑፋቄን የመረጠን ሰው በቤተክርስቲያን ላይ ተሹሞ እንዲደራደርና እንዲማር የምትሻ ለመሆኑ አንተ ራስህ ማን ነህ? መናፍቅ በቅድሚያ ከቤተክርስቲያን ተወግዞ በኋላ ግን እመለሳለሁ ካለ በአባቶች ትምህርት ተስተካክሎ፣ ከዚያም ቄደር ተጠምቆ ወደቤታችን ሲገባ እንጂ እንደምትለው አይነት የደፈጣ ውጊያማ በቅቶናል።

ለማንኛውም ቤታችን እስክትፀዳ ድረስ የእውነተኛ አባቶቻችንን ዕድሜ ያርዝምልን። የሰውዬው (የጳውሎስ) ዓላማ ገብቶናል። መሰሉን ወንበሩ ላይ ጥዶ እስኪሞት ድረስ አባቶቻችንን መፈታተኑ ይቀጥላል። ኃይለ እግዚአብሔር እንደሚያሸንፍ ግን ጥርጥር የለንም።

Anonymous said...

ወስብሃት ለ እግዚያብሄር፡
እኔ የምለው… ሰውየው ከተመደበ የሚመደበው ምእመናን ለማገልገል አይደለም እንዴ?! ታዲያ የሚገለገለው ም እመናን አልፈልግህም ካለው እንዴት አድርጎ ነው መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጠው? ወይ አባ ገብረመድህን… የቤተክርስቲያናችን እርግማን ሆኑኮ

Anonymous said...

Getachew done malet eko.... akaki benebere gize kebetekristianua sibarer ye edir betun adarash tekerayto aganinit alebin yemilu teketayochun asketilo Montarbo asgebitu yeakababiwin sew be menafik mezimur bemerebesh endihum aganint alebin yemilut wetatoch getachew lemin yewetal bemalet yeakaki medhani alemin yemekides ber bergicha bemekifet betekristianuanim hizbunim sirebish yeneber eko new..... yeakaki medhanialemin awde mihiret aganinit nen lemilu pentewoch bemestet bemaicrafon belu ahun esti eza pentewochu gar yemitzemirutin zemiru bemalet awdemhiretun bepente mezmur yemola eko new.... abet amilake yemibejewin yamita

21 said...

21

1. የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ አስተያየቱን ከመጥፎ አልወሰድኩትም እኔ:: ነገር ግን አንድ መላሽ እንደጠቀሱለት ጥንት በአባቶቻችን ዘመን የነበረው ኑፋቄ እና ያሁኑ ይለያያል ብሎ ማስገንዘቡ ደህና ይመስለኛል:: ከዚያ ባሻገር ግን የአዛኝ ቅቤ አንጓች እንዳይሆንብኝ በክርስትና ውስጥ ለሚኖር ሰው ሁል ጊዜ ስለሚወድቁት መጸለይ እንጂ እንዲወድቅ ማበረታታት አያስፈልግም ብዬ አምናለሁ::

2. መለስ ብለን ስናየው ደግሞ “እሾህን በእሾህ” ለማንኛውም ወገን አይጠቅምም ጎበዝ እስቲ አስተያየት ስትጽፉ ታናናሾቻችሁ ነንና ስድብ አታስተምሩን፤ ዘለፋ እንኳን ሲመጣባችሁ አስተማሪና መካሪ የሆነ ነገር ጻፉ እንጂ የስድብ አመላለስ አታስተምሩን እባካችሁ::

3. የተባሉት ግለሰብ ተወገዙ አልተወገዙ ያው ናቸው:: በእኛ አእምሮ የተወገዙ ናቸው ግን ስማቸው በሰሩት ሥራ መነሳቱ አይቀሬ ነው:: ይሁዳም ስሙ እኮ ከመጽሓፍ ቅዱስ አልተፋቀም፤ ግን ይሁዳን በጥሩ ምግባሩ የሚያነሳ የለም::

Kolo-temari said...

To Deje Selam and all comment givers,
I have been always wondering on your primitive writings,over the patirarch. I observe that you are foolishly ruding him; as the result you become zeroset.
Why don't you learn from his accompanies how they are convincing him?
Sorry, can I tell you how to overcome the agenda?
One Mewedis [praise] to him automatically welcomes you instead of insulting him 1000 times.

Anonymous said...

O Egzio ekeba lebetekrstiyanke kidist.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)