May 11, 2011

"ባለጌ"

(ቀሲስ ፋሲል አስረስ በፌስቡክ ላይ ካሠፈሩት የተወሰደ):- የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ካስተማሩኝ መምህራን ውስጥ በተለየ መልኩ ከማልረሳቸው መምህራን የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአዲስ ኪዳን መምህር የሆኑት ደጉዓለም ካሳ አንዱ ናቸው :: ክፍል ውስጥ ለማስተማር  ቀድመው ነው የሚገኙት ማርፈድ ለተማሪም ሆነ ለአስተማሪ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም አላቸው :: አንድ ቀን ወደ ክፍል መግባት ከሚገባቸው ሰዓት አስር ደቂቃ ዘግይተው መጡ ሁላችንም ገርሞናል  ይሁንና ማንም ያንጎራጎረ አልነበረም : ደግሞም አስር ደቂቃ ምንም አይደል::
መምህር ደጉዓለም ካሳ

መምህሩ ይቅርታ ጠየቁ በማስከተልምባለጌይዞኝ ነው የዘገየሁት ቤተ ክርቲያናችንየራሷ ባልሆኑ ባለጌዎችስለተሞላች ስለቤተ ክርስቲያን ስለ ወንጌል ሲነግሯቸው አይሰሙም ብለው መደበኛ ትምህርቱን ቀጠሉ ንግግራቸው ሊገባኝ ስላልቻለ ጥያቄ አለኝ አልኩ  ፈሊጥ ተጠቅመው ማስተማር የዘወትር ችሎታቸው የሆነው / ደጉ መቸ ትምህርቱ ተጀመረና ጥያቄ ትላለህ አሉኝ ቤተ ክርስቲያናችንየራሷ ባልሆኑ ባለጌዎችስለተሞላች ሲሉ ስለሰማሁ የራሷ የሆኑ ባለጌ ልጅዎች አሏት ወይ ለማለት ነው አልኩ ፈገግ አሉና ለመሆኑ ባለጌ ማለት ምን ማለትነው ? ብለው ተማሪዉን ጠየቁ ከጎኔ ተቀምጠው የነበሩት አንድ አባት እንዴ መምህር ባለጌማ ባለጌ ነው ሲሉ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አልቻለም ነበር ::

/ ደጉ ሌሎቻችሁ ሞክሩ አሉ ጥሩ ሥነ ምግባር የሌለው መጥፎ ጋጠወጥ ወዘተ.....በማለት ሁሉም የእውቀቱን ሞከረ / ደጉ ግን ስለ ቋንቋ አመጣጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንሽ ካብራሩ በኋላ በቀድሞ ዘመን ይሰጥ የነበረውን ማዕረግ መነሻ አደረጉ የደብረ ሊባኖስ አስተዳዳሪ እጨጌ እንደሚባሉ የንጉሡ ባለቤት እቴጌ እንደሆኑና ለወቅቱ መንግሥት ቅርብ ነኝ የሚል ደግሞ ባለጌ እንደሚባልባለጌ “ማለት ባለ ጊዜ እንደሆነ ባለጊዜ /ባለጌ / እንደፈለገ እንደሚናገር ትልቁን የሚያዋርድ አቅሙን የማያውቅ እንደሆነና እጨጌ ፡እቴጌ: ባለጌ ወዘተ... ይባል እንደነበር ነገሩን ::  

ዛሬም ሃይማኖት የሌላቸው ለሃይማኖት መሪዎች ቅርበት ያላቸው /ባለጊዜዎች /ስለቤተ ክርስቲያን ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን ወኪሎች /ባለጊዜዎች/ መብዛታቸው ለምን ይሆን ? አርባ ዓመት የቤቴ ክርስቲያን ትምህርት ተምረው በወር አርባ ብር የተነፈጋቸው ዘመናቸውን ሙሉ መምህራንን በማፍራት ያሉ የአብነት መምህራን አስታዋሽ አጥተው ምንም የቤተ ክርቲያን ትምህርት የሌላቸው ቀድሰው የማያቆርቡ የቤተ ክርስቲያኗን ቢሮ እንጅ በመቅደሱ በር የማይታዩ አስቀድሰው የማያውቁ  ማስተማር የማይችሉ አንድ ቀን ተስቷቸው ጹመው የማያውቁ ፍጹም መንፈሳዊ የሚባል ነገር የማይታይባቸው ዓለማውያን /ባለጊዜዎች/ባለጌዎች/ የራሳቸውን ሥጋዊ ኑሮ መገንባት አንሷቸው ቤተ ክርስቲያኗን ለማጥፋት መሰለፍ ምን ይሉታል ?   በታሪክ በባለጌ የተሰሩ በርካታ ጥፋቶች ቢኖሩም የተመዘገበ ጥቂት በጎ ነገር የለም :: ባለጌ /ባለጊዜ ለወቅቱ ባለሥልጣን ቅርብ በመሆኑ ብቻ እንደፈለገ ሊናገር ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑን ጨለማ ሊል ይችላል መልካም ስም ስለሌለው መልካም ስም ባለበት መቆም አይችልምና መልካም የሆነውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ደንጋይ የለም  ባለጌ የተመካበትን ባለሥልጣን ጭምር ያሰድባል :: እስኪ የሽማግሌ ምርቃት ብየ ልፈጽም :
ከቶሎ አኩራፊ                           
ከበሽታ ተላላፊ                           
ከወዳጅ ሸረኛ
ከጓድኛ ምቀኛ
ከልጅ አመዳም
ከጥጃ ቀንዳም
ከቄስ ውሸታም
ከዳገት ሩጫ
ከአህያ ርግጫ
ከባለጌ ጡጫ    ይሰውረን አሜን

10 comments:

zegeye said...

amen

Anonymous said...

Amen !

Orthodoxawi said...

Amen! Amen!Amen!

Anonymous said...

ዛሬም ሃይማኖት የሌላቸው የሃይማኖት መሪዎች /ባለጊዜዎች /ስለቤተ ክርስቲያን ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን ወኪሎች /ባለጊዜዎች/ መብዛታቸው ለምን ይሆን ?g

Anonymous said...

ዛሬም ሃይማኖት የሌላቸው የሃይማኖት መሪዎች /ባለጊዜዎች /ስለቤተ ክርስቲያን ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን ወኪሎች /ባለጊዜዎች/ መብዛታቸው ለምን ይሆን ?g
ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በክህነቱ ስም ተሸፍነው
የራሳቸውን ጥቅም ያራምዳሉ :: አፋቸው ይቀላምዳል ውስጣቸው ተኩላ ነው: እንደነሱ ባሉ
ቄስ ወይም መነኩሴ ፊት አንገታቸውን ሲደፉ አባ እገሌ እንዴት ያለ ባህታዊ የበቁ እያሰኙ የምስኪን
ምእምን ኣይምሮ ማደንዘዣ ወሬ እንዲናፈስ ያረጋሉ
በመሰሎቻቸው ዘንድ ታላቅ ይምስሉ እንጅ በእነሱ
መከራ የተቀበሉትን አምላክ ይቁጠረው:: የምንኩስናው ልብስ ማስክ ነው:: እኔ እንደውም
የሚገርመኝ ካህን አታምንም ከካህን በላይ ምን ታምናለህ የሚሉት ፈሊጥ አላቸው
ታድያ ማስታወሻ ይዛችሁ ሰባት የተለያየ ሰው እንዲጠይቃቸው ብታረጉ ለሰባቱም ሰው ሰባት ውሸት ያወራሉ ምእምኑን ከፋፍለው የራሳቸውን
ተከታይ አብዝተው መንፈስ ቅዱስ የሌለበት በኢ/ኦ
ቤ/ክ ስም ሱቅ ይከፍታሉ:: ዋሸሁ? እውነተኛ መነኩሴ ከዋሻው ወቶ ቱሪስት አይሆንም- ህዝብ አይከፋፍልም+ አንደበቱ በውሸት አይዘላብድም ስለ
ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ህዝቦች ይገደዋል እንጅ ቆብ
ደፍቶ መስቀል ይዞ ባላታለለ ነበር:: አይ ቤ/ክ እንዲህ የማንም ወያላ ዱርየ በአባቶች ልብስ ተሸፍኖ
ህዝቡን ይጫወትበት:!!!!!!! ያሳዝናል ዘንድሮስ እግዚአብሔር ተዋሕዶን ቤ/ክ በቃሽ ይበላት

Anonymous said...

አሜን ወአሜን። ምርቃቱ መልካም ነውና። መልእክቱም እንጂ ማለፊያ ነው። ነገርግን፤ "ባለጌ" = "ባለጊዜ"?? እ.እ... ምናልባት ዛሬ የምንሰጠው ስሜት ሊኾን ይችላል። ያውም ከተስማማንበት። በቆየው አጠቃቀምም ኾነ በሥርወ-ቃሉ ተመርጕዘን የምናገኘው ፍች ግን ሌላ ነው። ዐይናማው ሊቅ ደስታ ተክለወልድ ባዘጋጁልን የዐማርኛ መዝገበ-ቃላት "ባለጌ" ማለት፦ "አግድሞ አደግ፣ ስድ፣ መረን፣ ያልተቀጣ፣ ያልተገሠጸ፣ ነውረኛ፣ ነውር ጌጡ፣ አያት ያሳደገው ልጅ።" ነው ይሉና፤ "ባለጌን ካሳደገው የገደለው ይጸድቃል። ባለጌ የጠገበ ለት ይርበው አይመስለውም።" የሚሉትን አባባል ይጠቅሳሉ። ይኸ አኹን ቃሉን ከምንጠቀምበት ኹናቴ ጋራ አንድ ነው። ሥርወ-ቃሉን ተከትሎ የሚሰጠውን ትርጕምም ቢኾን ሊቁ አልሳቱትም። "ባለጌ፤ (በዓለ፡ ጌ። በዓለ ምድር)፤ = ባለምድር፤ የምድር ጌታ።" ብለው ፈትተውታል። ቃሉ ከዐማርኛ እና ከጽርእ/ግሪክኛ ቃላት ተዳቅሎ የተገኘ "ፍርንዱስ" ቃል ነው። "ባለ" ዐማርኛ ሲኾን "ጌ" (γη = land, earth) ግሪክኛ ነው። በተገናኝ "ባለምድር" ምናልባትም "ባለርስት" ያሰኛል ማለት ነው (ይኸውም over against "ባለጕልት" ይመስላል)። ይኸንን አጕልቶ የሚያሳይ "ባለጌ አያዝንም እሱ ስለገበረ፤ ባልንጀራው እንጂ ስለቀረ።" የሚል አባባል አለን! እነ"እጨጌ" እና "እቴጌ"ም እንዲኹ "ፍርንዱስ" ቃላት እንደመኾናቸው በዚሁ ፈሊጥ ይፈታሉ። "እጨ-ጌ/ሐፄ-ጌ = ሕፁየ-ጌ" የምድር እጮኛ፣ "እቴ-ጌ"ም ሌላ ሌላውን ትተን በ"እግዝእተ-ጌ" ዘይቤ ብንኼድ "የምድር እመቤት" ይኾናል።

lemma kefy. said...

አዎ ትክክል ነው ቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ ባለጌዎች እየተራቡ ነው።እግዚአብሔር ይከልክልልን ።አሜን

ብዕሩ ዘ አትላንታ said...

ባለጌ አሉ ቀሲስ ፋሲል
"ባለጌ" የማንነት መገለጫ ሆኖ በባለቤትነት እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ ለከበረዉ ፍጡር መሰጠቱ ወይ ጉድ ቢያስብልም ተገቢ ነዉ ወደ ሚባልልት መድረሳችን አያስተዛዝበንም። ቀሲስ ፋሲል ዘገዩ ቢባልም ባለጌን ለማስታወስ ገና አልተጀመረም ማለት ይቀላል። "የአጥንት እዳ" ነግሶባቸዉ ወንዜነትን ከእምነት መቋጠሪያዉ ነጥለዉ ማየት የተሳናቸዉ የዘመናችን የሆድ እድርተኞች የቆሙበትን ለማመልከት አንድ መባሉ የተኛን ለመቀስቀስ መልካም ጅምር ነዉ ። እረ ጉድ! የሐሜት ጥምቡሳስ ለነረተዉ ፈትሎ ገምዶ አንስቶ ለሚጥለዉ የዘመናችን ወረኛ ለአንደበቱ መስፊያ ባይበጅለት ለቆሸሸ ማንነት ባለጌ ነህ ተብሎ ቢነገረዉ ስልቹ አይሆንም። ቤተ ክርስቲያን ክብሯ ፣ የክርስቶስ ሥጋና ደም በሚፈተትበት ፣ቅዱሳን ማንነትና የትመጣቸዉ በሚነገርበት አዉድ ላይ ቦለቲኻ ለሚደሰኩሩ፣ የወዳጃቸዉን ደም ያለ ዋንጫ ለሚቀዱ፣ ሥጋዉን ያለ ቢላዋ ለሚመትሩ ባለጌ መባል ስድብ ሳይሆን ሽልማት ነዉ። ቀሲስ ያቆሙ አይመስለኝም ግፉበት....ለቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ለሚሉ፣ እርቅና ሰላም ለሚናፍቁ፣ ከገንዘብ ይልቅ ሀገራቸዉንና ቤተ ክርስቲያንን ላስቀደሙ ወጣት የሃይማኖት አርበኞች ሀገር ስደት ላልበገራቸዉ ትዉልዶች ክፉ ስም ለሚለጠፉ "ባለጌ" መባል ሲያንሳቸዉ ነዉ እላለሁ ....

Teddy said...

Amen yisewren

Anonymous said...

ዛሬም ሃይማኖት የሌላቸው የሃይማኖት መሪዎች /ባለጊዜዎች /ስለቤተ ክርስቲያን ደንታ የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን ወኪሎች /ባለጊዜዎች/ መብዛታቸው ለምን ይሆን ?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)