May 19, 2011

የሐዋሳ ምእመናን “አንቀበልም” የሚሏቸው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ማን ናቸው?

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

ስለ እኒሁ ሰው የተዘጋጀውን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ 
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 19/2011)፦ የሐዋሳ ምእመናን “አንቀበልም” የሚሏቸው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ማን ናቸው? የራሳቸውን የእምነት ድርጅት አቋቁመው የነበሩ፣ በፊርማቸው ከፕሮቴስታንት እምነት የመግባት ፍላጎት እንዳለው የጻፉ፤ ሽጉጥ ታጥቀው የሚሄዱ፣ ባላቸው የፖለቲካ ቀረቤታ ብዙ ግፍ የሚያስፈጽሙ፣ ምእመናን ለአቤቱታ ወደ አባቶቻቸው ዘንድ ሲመጡ በጎን በፖሊስ ምእመናንን ያሳገቱ ወዘተ ወዘተ። ለማንኛውም እርሳቸውን በተመለከተ ያሉትን መረጃዎች በሙሉ ከዚህ በታች በሰፊው አቅርበናል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ሰው ወግነው ይህንን ሁሉ ምእመን ማሳዘን አለባቸውን?

                                                    
ቀን፡- 05/02/2002

ለአባ ሠረቀ ብርሃን
ለሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ ሐላፊ፤

          የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኹ፣ እንደሚታወቀው ባለፈው በተነጋገርነው መሠረት ጉዳዩን እየሄድኹበት እገኛለኹ፡፡

እንደሚታወቀው አንዳንድ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች የግል ማኅደሬን ለማበላሸት የፓትርያሪኩን ሕጋዊ ወኪልነቴን ለመሻር ደብዳቤ ጽፈውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ሐሳባቸውን አክሽፌባቸዋለኹ፡፡ በመኾኑም አቡነ ይስሐቅ እንድነሣ ሊያደርጉኝ ቢያስቡም በአቡነ ገሪማ ጸሐፊነት ደብዳቤው እንዲመለስልኝ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ጋዜጣ ላይ የጻፍኹት ራሴን ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ የፀረ ሰላም ኀይሎችን ምስጢር ነው ያወጣሁት፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን በእርስዎ በኩል ይጠበቅብዎታል፣ ምክንያቱም በርካታ ሰንበት ት/ቤቶችን በመምሪያው ሥር ማግኘት ስለምትችሉ፣ ቤተ ክርስቲያንን በወጣት ኀይል ነውና ማደስ የሚቻለው ጠንክረን መሥራት እንችላለን፡፡
እኛ ሣራ ወለደችን በመኾኑ እናታችንን ከኋላ ቀር አሠራር እና ባህል አላቀን፣ ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ ‹‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት›› ሥር ልንሰበስባቸው እንችላለን፡፡

የካናቴራ አልባሳት ማሠርያ ለማሠራት በጎ ፈቃደኞችን እየጠቆሙኝ ነው፡፡ ስለዚህ እኔም የማጥመቅ ሥራ በየቤቱ እየዞርኹኝ እያጠናከርኩኝ ነው፡፡ እርስዎም ይህን መንገድ በተሻለ መንገድ አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፤ ስለ ገንዘቡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ 170 ሺሕ የሚያወጣ ሐውልት በእኛ ደብር ስለምናሠራ ከዚያ ላይ በሚገኘው ገንዘብ ልናጠናክረው እንችላለን፡፡ በዙሪያው ያሉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች ይህን ሐሳባችንን ሊያደናቅፉ ቢችሉ እንኳን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፡፡
 
በመጨረሻም የሙሉ ወንጌል አማኞች ወላጅ ለሌላቸው ሕፃናት የገንዘብ እና የልብስ ድጋፍ ስለሚያደርጉልን ሕፃናትን መመዝገብ አለብን፡፡ በዚህ እኔ ባለሁበት ደብር አባ ገብረ ሥላሴ የተባሉት በስማቸው የመሠረቱት የሕፃናት ማሳደጊያ በርካታ ልጆች ስላሉ፣ በዚህ ማሳደጊያ ስም ልናገኝ እንችላለን፡፡ ስለዚህ በገንዘቡ በኩል በእንዲህ ዐይነት ኹኔታ ላይ ስለሆንን እርስዎ ወጣቱን በማነሣሣት ትልቅ ሥራ ሊሠሩ ይገባል፡፡ በተረፈ አዳዲስ ነገር ሲኖር በስልክ በመደዋወል እንጨርሰዋለን፡፡

                                      
 ‹‹ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋራ››
                                    
ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ
                                   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
                                   ክርስቲያን መንበረ ፓትርያሪክ ሕጋዊ
                                   ወኪል
 To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

12 comments:

Anonymous said...

Is this guy Monk or just a priest?

Zeegzine

Anonymous said...

He is a married priest, dressed like a monk, actually.

Mekonnen Aderaw said...

First of all, I apologize my readers for writing in English.

This man is far worse than Ahmad ibn Ibrahim al-Ghazi (Ahmed Gragn) for the today Ethiopian Orthodox Church. If all these are true, what are we waiting to see on our church? Are we waiting until he takes the arch of the covenant out? May God clear our shadow of fear! I don't know what to say, I am really confused! I believe that information is power and more and more information about such people in the church is very crucial. But my question is when are we going to utilize all information we already have to date? Now, I think we have sufficient information on lots of such aspects of our church that can definitely help to make a certain decision to save our church. Of course, we believe that God is the true savior for the church from all kinds of enemies. But we are the ones to serve as messengers of in the God’s process of providing mercy, virtue and wisdom. St. Paul taught Pheben and her son about what Christianity is meant for. But Pheben and her son did not say “bring st. Paul and hang him on our behalf as he was the one who told us about Christianity”. Once they knew the truth, they paid their life as a price for truth. So, whom are we waiting to stand for the church and pay all the necessary prices needed to save Her traditions, cannon and doctrine?

I strongly suggest someone who has the technical know-how to immediately open a separate forum to discuss on our responsibilities.

May the mercy of God be upon us and our church!

Weyra said...

ምነው ደጀ ሰላሞች? የጌታቸው ዶኒን ሹመት ከሐዋሳ ምእመናን "ማስደሰትና ማሳዘን" ጋር ብቻ አያያዛችሁትሳ? የጌታቸው ዶኒ ሹመትኮ ቤተ ክርስቲያንን የመሸጥ ጉዳይ ነው! አንድን ሀገረ ስብከት መናፍቅነቱን በራሱ የተናገረ መናፍቅ እንዲያስተዳድረው መሾም ማለት ሀገረ ስብከቱን በሙሉ መናፍቅ ማድረግ ማለት ነው:: እናም ነገሩን አታቃሉት፣ ፓትርያርክ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን የተሐድሶ/የፕሮቴስታንት ለማድረግ ሂደታቸውን በግልጽ አንድ ብለው የጀመሩበት ነው::

Anonymous said...

Wey Gud! wey Zemen! Abba 'awlos min nekachew yezihin sew gud mayet tesanachew. Ersachewim yaw honu malet new?

May God protect our church.

Anonymous said...

Can you post the video on you tube, so that those who don't have Facebook account can see it too?

ABEBE BEKELE said...

ሊቀ ካሕናት ብሎ ጌታቸውን ወልደ ዶኒን መጥራት ራሱ ይከብዳል። ሊቀ ካሕናት የሚለው ስያሜ አለመታደድ ሆኖ ማንም ሲጠራበት ያሳዝናል። ጌታቸው ማን ነው ለመሆኑ በቤተ ክርስቲን ውስጥ ሳይታወቅ እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ቻለ።የልጅነት ባሕሪው ምን ይመስላለ ለማሕበረ ቅዱሳን ያለው ጥላቻ እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለውን በተወሰነ ደረጃ መቃኝት ያስፈልጋል።
ጌታቸው ተወልዶ ያደገው መቂ ነው። ጨርሷ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የኖረና የኖረና ያደገ ሰው አለነበረም። በባሕሪው በጣም አስቸጋሪና ልጆችን የሚ ያደባድብ ብዙን ጊዜ ጎራ እየለየ በማደባደብ
በመጠጥ እዕምሮውን ያናወዘ ሰው ነው። በተለይ በመቂ ከተማ ያለውን ቤተ ክርስቲያን ተጠግቶ እንዴት ራሱ ዲቁናውን ይቀበል አይቀበል እስከ አሁን የሚታወቅ ነገር በውል የለም። በገጠር ያሉ ካሕናት አባቶችን በማስፈራራት % ለሃገረ ስብከቱ እንዲገባ አደርጋለሁ በማለት ብዙ ግፍ በአባቶች ላይ የፈጸመ ሲሆን በተለይም በታላቁ ሊቅ በንቡረ ዕድ ክፍለዮሐንስ የናዝሪት ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በነበሩ ሰዓት መሳዮቹን በማሰባሰብ ከፓትርያርኩ ጋር በማጣላት ከሥራ አሥኪጅነት እንዲነሱና በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 75% ያህል ደሞዛቸው ተቀንሶ በቅኔ መምህርነት ሥም እንዲቀመጡ ተደርጎል።
የጌታቸው ዶኒ በፓትርያርኩ መታወቅ የጀመረው 1997 ዓ/ም ላይ አዋሳ ደረሰው ሲመጡ በክልሉ ላይበነበረው የፓለቲካ ፓርቲ የምርጫ አስፈጻሚነት በመጠቀም በገጠር ያለውን ሕዝብ በማስፈራራት በከተማ ያለውንም ሕዝብ የአትክልትሕን ቦታ እንዳታጣ ከፈለክ ከመንግስት ጋር ጳትርያርኩ ቅርብ ስለሆኑ ጥያቄያችንን ለእሳቸው እናቅርብ በማለት ከበሬው በፈረስ ከተማን በሳይክል ኣጅቦ እንዲቀበላቸው አደረገ። በኢትዮጰያም ሆቴል ግብ ትልቅ ግብዥያ አብረዋቸው ከነበርት ጋር አደረገ በአዋሳ ቆይታቸው መንፈሳዊው አባት የያኔው መምሕር ኃይለ ሥላሴ የአሁኑ አቡነ ሉቃስ ከሚከባው በላይ አቀባበል እንዳላደረጉ እዚህ ግን ያለየጠበቀ በመደረጉ በማለት የቤተ ክህነቱ ንግግር አዋቂ ግጥም ገጥሞለት ነበረ።ጌታቸው ዴኒ በፖለቲካው አለም ገብቶበት እንደማያዋጣው እንደሚመታ አውቆ ወደ ቤተ ክርስቲያን የተጠጋ ሰው ነው።በኢሃዲግ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት እንዳለው አድርጎ ይናገራል።ተራ የሆኑ ካድሪዎችን ቶሎ በማቅረብ እነርሱን በማብላትና በማጠጣት የፈለገውን ሥራ ያሰራል። ጌታቸው ዶኒ ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት መርጌታን መኩሪያ ቤታቸው ሊገቡ ሲል እነዚህ አላማቸውን በዘነጉ ካድሪዎች ተይዘው ወደ ወሕኒ ቤት ሊወረወሩ ችለዋል።
ጌታቸው ዶኒ አስቀድሞ ስራውን ስለሚያውቅ ለሱ የሚመቹትን ወጣቶች በተለይም በአካባቢው ላይ በድብድብ በምግባር ብልቹነት የሚታወቀትን በማቅረብ የክፉ ድርጊቱ ደጋፊዎችና የእርሱ ተሞጋችና ጠባቂዎች ያደርጋቸዋል። ለዚህም ነነበረባቸው ቦታዎች ሁሉ ከመቂ ጀምሮ በእንጦጦጦና በአቃቂ በነበረበት ሰዓት ትይቷል። አላማውን ለማሳካት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሉ እንደሚቃወሙት ሰለሚያውቅ ወደ አንድ ደብር ከሄደ ለማፍረስና ለመበተን ያማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። እንደምሳሌ በመንበረ ስብሐት ቅድስ ሥላሴ በመጣ ጊዜ ሰንበት ትቤቱን አፍርሶ ወጣቶችን እንዲበተኑ አድርጎል። የሰንበት ት/ቤቱ ወጣቶች አሳሥሯል በዚያ ቤተ ክርስቲያን የነበሩ ወላጆችንም ቀንጅት ናቸው በማለት ቀራቢዎቹ በነበሩ ካድሪዎች ሊታሰሩና በወህኒ ቤት ወስጥ ሊከርሙ ችለዋል። ጥፋቱ እየበዛና የመንግስት ተወካይ አድርጎ ራሱን በማቅረቡ ቤተ ክርስቲያንን በማሰደቡ በአቡነ ሳሙኤል የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ እንዲነሳ ቢያደርጉትም አባ ጳውሎስ ግን መልሰው አቃቂ ሾሙት።
የመቂ ሕዝብ ዛሬ በቤተ ክርሲያን በሚፈጸመው አዝኖል። ጌታቸው እንኮን ለቤተ ክርስቲያን ለምንም የማይሆን ሰው ነው።

A3A said...

I think it is time to deend our church. keeping talking as usual is not a solution.

dejeselam. it is good to post such evidences. but we have to go further. we need to have a forum to discuss on What to do as a solution. we have been talaking for several years.

Action Action! were ayetekemem.

Anonymous said...

አባ ሰረቀ ማን ናቸው
ጎንደር መ/መ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህን ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡ አቡነ ጳውሎስ ስልጣን በያዙ ማግስትሰላማዊ ሰልፍ ዋና አዘጋጅ ሆኑ፡፡
ጎንደር የሚኖሩ ምንም የማያውቁ ትግሬ ካህናትን በመሰብሰብ እኛ ጎንደር የምንኖር ትግሬ ካህናት ተጨቁነን ኖረናል በማለት የሰላማዊውን ሰልፍ ዋና ዓላማ ‹‹ጭቁን ካህን›› ብለው እሳቸው በዋና መሪነት ሠላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡ በሰላም የሚኖሩ ትግሬና አማራ ነዋሪ አበጣብጠው ወደ አዲስ አበባ ከዚያም ወደ አሜሪካ፡፡ አባ ሠረቀ እባክዎት ይህን መበጥበጥ ይተው

Anonymous said...

Thank you keep letting know us about our beloved church. Aba Gebremedhin(Fake Patriaric)is trying to kill our church before he died.

Anonymous said...

Why don't you accuse him, legally?

Shimelish said...

if the evidence is not forged, please put him in to court.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)