May 25, 2011

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ
  • ዋና ዋና አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች አልተጠቀሱም፤ በዓባይ ግድብ ዙሪያ ያጠነጠነ መግለጫ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 25/2011)፦ ከግንቦት 10-16 2003 ዓ.ም የተካሔደው መደበኛ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን መግለጨው ቅ/ሲኖዶሱ የተወያየባቸውን እና ውሳኔ ያሳለፋቸውን ዋና ዋና ጉዳዮ ሳያነሳ አልፏቸዋል።


በቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ የተደመጠው ይኸው መግለጫ ቅ/ሲኖዶሱ “በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ዘርፍ ስለተከናወኑትና ወደፊትም መከናወን ስለሚገባቸው አጠቃላይ ጉዳዮች ይልቁንም የዓባይን ሚሊኒየም ግድብ ግንባታ ፕሮጄክት በተመለከተ በስፋትና በጥልቀት ተወያይቷል” ብሏል።

መግለጫው የዓባይን ጉዳይ በማስፋት ከቅዱስ መጽሐፍ በመጥቀስ ኢትዮጵያ እና ዓባይ የማይለያዩ መሆናቸውን፤ ወንዙ እስካሁን በታሪከ እና በተፈጥሮ ቅርስነቱ እንጂ በአገልግሎት ሰጪነቱ እንደማይታወቅ፣ አሁን ግን ሁሉም ይተባበር ዘንድ መንግሥት ጥሪ እንዳደረገ ገልጿል። ይህንን ጥሪ በኢትዮጵያዊነት ስሜት ቤተ ክርስቲያኒቱም ተቀብላለች ያለው መግለጫው “ለተልዕኮው መፋጠንና ለዓላመው መሳካት ግንባር ቀደም ሚና አላት” ብሏል።

በዚሁ መሠረት “ለዓባይ ሚሊኒየም ግድብ ግንባታ ፕሮጄክት ማከናወኛ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብር 21 587 244.00(ሃይ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ፣ ሁለት መቶ አርባ አራት)” መሰጠቱን ገልጿል። በማጠቃለያም መግለጫው ሲያትት “የኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያውያት ሕይወት ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት አለኝታ ስለሆነ፣ ከዚህ ተሳትፎ መለየት ራስን ከኢትዮጵያዊነት እንደማግለል ስለሚቆጠር ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ኢትዮጵያውያት እንዲተባበሩ” አሳስቧል።

በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ መርሐ ግብር ላይ የአጫብር እና ቆሜ ወረቦች ከመቅረባቸውም በላይ ስለ ዓባይ ግድብ ቅኔ ተበርክቷል። በእንደዚህ ዓይነቱ ትልቅ ጉባኤ ወቅት ቅኔያቸውን በማቅረብ የሚታወቁት የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ “እስከ አሁን ድረስ ሞት እና ሕማም ለሚገድባቸው ቅኔ ስንሰጥ ቆይተናል፤ አሁን ግን እስከ ምጽዓት ድረስ ለሚቆየው ለዓባይ እንቀኛለን” ማለታቸው ታዳሚውን አስደምሟል። በበዓላት ወቅት በተለይም ለቅዱስ ፓትርያርኩ የቅኔ ማዕከል እንደሚፈስላቸው ይታወቃል፡፡

26 comments:

Orthodoxawi said...

Shola bedifin newu ... negeru!

Gin yihun .... yihim kifu aydelem.

awudemihiret said...

አዬዬዬዬ እንዲህም አርጎ ቅኔ የለም።የወጭቱን ውስጥ ትታ ውጪውን የምታጠራ ቤት።

Anonymous said...

“ለዓባይ ሚሊኒየም ግድብ ግንባታ ፕሮጄክት ማከናወኛ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብር 21 587 244.00(ሃይ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ፣ ሁለት መቶ አርባ አራት)”
Imagine hundreds of thousands churches in small towns and rural areas are their wholly doors closed till now. Do you know that in some of these places, children’s of eight and nine years still waiting to baptize. It seems fun and playing bribe with poor people money, giving this chunk amount for the bridge!!! The mandatory objective of the church is preserving her followers. But thanks to Pop Poul....
I am very eager to see when will be our heaven father gave us beloved leaders of Ethiopia and the Church!
AMELAKE ETHIOPIA SILENATIHI BELEHI YEBETEKIRISTIANENE TIFATI ATASAYENE!
Amen

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ዛሪም የወንጌል ስባኪ ሳይሆኑ የፖለቲካ መድረክ ስባኪ መሆኑን በድጋሚ አረጋገጠ
በመግለጫው ስለቤተ ክርስቲያ ስለወንጌል ስብከት አንድም ቃል አልተሰማም

አባ መላኩምም ከወንጌል ስባኪነት ሕንጻዎችን ማስተዳደር (ገንዘብ መሰብሰብ) መርጦ ተሾመ

ይሕ ሕዝብ እስከመቸ ከንፈሩን አየመጠጠ ሊኖር ነው?

Anonymous said...

አረ፣ እኝ የኢዲያሚን አይነት ማዕረግ የደረደሩ ሰው አሁንስ አንገሸገሹኝ!

ምዕመን ተነቃነቅ!

እኔስ ቅጥል ብያለሁና ወስኛለሁ።

ጆሊ ዘ4 ኪሎ።

Anonymous said...

megilechaw bizum yemikefam ayidelem mechem besibeseba sirat yemineger ale yemayneger ale lebet kirstian selam sibal endihu bedefenaw yekereb yimeslal ayikefam bay negn
gin ene yemigeremegn le and menekusie yihen yahil yekibr sim mederder tikmu mindnew ? ere mekari yelem begonachew legnih sewye < abba > eko keminm belay talak sim new silaliteserabet enji gizie nefis behonebet wekit yihen hulu sim siderderu mewal erasu tsere limat yasegnal ....bene bekul abune abba bibalu yemigolachew yale ayimeslegnm lela alemawi sim eyederedru kemechenanek ...abba /abune / pawulos < yihen yemiteka sim yelem . egnam lijochachew abune abba /abatachn bilen sintera enjii docter minamn bilen sintera kiber yelenm ......yitasebebiet

Anonymous said...

ኤድያ

Orthodoxawi said...

Ayi Aba Paulos, "Guad Likemenber Mengistu Hailemariam, ye Ehdiri President, ye Esepa Maekelawi Committee Likemenber, ye Tor Hailoch Teklay Azaz ... bla bla " yemilewun astawesun.

Anonymous said...

ayyyy abune paulos,eskemechay bedehaw dem yitatebalu???miskenu amagne kahin atito kemisterate betechirstian tegelilual,abyate chirstianat tezegtew meimenu yalekisal,ersio tamagnu degmo lepoletica kuami tebeka honewal.ewnet yegetan chernet nikewit yihon libeo yedenedenew???AMLAK HOY EBAKIH SILEKEDEMUT BEFIKER SILAGELEGELUH KIDUSAN ABATOCHACHIN BILEH ENDE MUSE YALE TEBAKIN SITEN!!!,EMA DENGLE HOY EBAKISH BEBEDELACHIN BIZAT ENDAYTEWEN KELJISH ZEND MIHRETIN LEMIGNELIN!!!

frew said...

let us know the list of peoples elected for bishop, so that we can comment on them.
regards,

Anonymous said...

አንድ እናት ናቸው ይባላል, ዉሻ ሊጡን ያህሸታል እሳቸው አባጋ ይመላለሳሉ አባ መተው ቤቱን ዪባርካሉ, አባም በዛባቸውና ውሻውን አምስጭውና ሊባርክልሽ አሉ ይባላል. የአባታችን ጉዳይም እንደዛ ሆነ ጎበዝ አባቶችም ሰዎች ናቸው ዪሰለቻል ሰውየም አባትነት አጡ. እናም የቤታችን ጉዳይ የሃገር ጉዳይ መሰለ መንፈሳዊነት ትቶ ቦለቲካ መሸዋወድ, ስብሳባ አንዛዝቶ አሸማቆ, መንጋውን ረስቶ ከተቻለ ማስፈራራት አክሎ, እናም ችግሩ ፍትህ ማጣት ጋ የተገናኘ ነው. እንደ መንግስት የህዝብ መሆን ይገባዋል ለዛ ነው አባታችን ህዝቡን የረሱት ምን ያመጣል በሚል. እናም የበታችን ትግል አብሮ የሚታይ መሰለኝ. አምላከ ቅዱሳን ዪርዳን ለሳቸው ልቦና መንፈሳዊ ይስጥልን. ሁሉም በቻለው ይርዳ. ዝምታ ይቁም!!!

Anonymous said...

አንድ እናት ናቸው ይባላል, ዉሻ ሊጡን ያሸታል እሳቸው አባጋ ይመላለሳሉ አባ መጠው ቤቱን ዪባርካሉ, አባም በዛባቸውና ውሻውን አምጭውና ሊባርክልሽ አሉ ይባላል. የአባታችን ጉዳይም እንደዛ ሆነ ጎበዝ አባቶችም ሰዎች ናቸው ይሰለቻሉ, ሰውየም አባትነት አጡ እናም የቤታችን ጉዳይ የሃገር ጉዳይ መሰለ መንፈሳዊነት ትቶ ቦለቲካ, መሸዋወድ, ስብሳባ አንዛዝቶ, አሸማቆ, መንጋውን ረስቶ ከተቻለ ማስፈራራት አክሎ, እናም ችግሩ ፍትህ ማጣት ጋ የተገናኘ ነው እሱ ሲገኝ ሲባረክ አብሮ የሚመጣ አይነት.
መንግስት እንደ መንግስት የህዝብ መሆን ይገባዋል, ለዛ ነው አባታችን ህዝቡን የረሱት ምን ያመጣል በሚል. እናም የቤታችን ትግል አብሮ የሚታይ መሰለኝ. አምላከ ቅዱሳን ዪርዳን ለሳቸው ልቦና መንፈሳዊ ይስጥልን. ሁሉም በቻለው ይርዳ. ዝምታ ይቁም!!!

Anonymous said...

ለነገሩ የማንንም ሆድ ለመሙላት ከሚጠፋ ለልማት መዋሉ በእጅጉ ይሻላል። ቆይ እኔ የምለው ይህንን ያህል ብር መስጠት የምትችል ቤተ ክርስቲያን በየ ገጠሩ ያሉትና ጧፍ እንኳን የሌላቸው በሺ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት፣ በዝናብ የሚበላሹ ስንት ውድ መፃሕፍት፣ የዕለት ጉርስ የዓመት ጉርስ አጥተው ሊቃውንት የሚሰደዱባት እንዴት ሆነች??? ነው ወይስ ጠቅላይ ቤተ ክሕነት የሚያሰተዳድረው የአዲስ አበባን እና ከክልሎች ደግሞ የአክሱም ፅዮንን፣ የቁልቢ ገብርኤልን፣ የደብረ ሊባኖስን፣ የአዋሳ ገብርኤልን፣ የላሊበላን እና የፃድቃኔ ማርያምን አድባራት ብቻ ነው??? እንደዛ ከሆነ ለሌሎቹ አድባራት እና ገዳማት ለምን ሌላ ጠቅላይ ቤተ ክሕነት እና ሌላ እውነተኛ አባት አይመረጥም??? ሌላው በመግለጫው ላይ የገረመኝ ደግሞ ለአንድ ሱባዔ ያክል ቅዱስ ሲኖዶስ የተወያየው ስለ ዓባይ ብቻ ነወ??? ምናለበት እንደው በደምሳሳው እንኳን ከህዳሴው ግድብ በተጨማሪም በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገን ውሳኔዎችን አስተላልፈናል ቢባል!!!
ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ...

ዘካርያስ ጋሻው said...

“ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?”
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4 : 17

አባይን ለልማት ለማዋል መነሳት እና የወቅቱ የመወያያ አጀንዳ ማድረግ ተገቢና ወሳኝ ነው።
በዚህ ላይ ምንም ድርድር አያስፈልግም። ነገር ግን የኔ ጥያቄ እርስዎ(አቡነ ጳውሎስ )እና መሰሎቾ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ ወደ ጎን በመተውና ምንም ችግር እንደሌለ በማስመሰል እግዚአብሄርን ሳይሆን ሰውን ለማስደሰት ደፋ ቀና ስትሉ ይስተዋላል። የዚህ ምንጩ ደግሞ የእምነት ማጣትና የድፍረት ሃጢአት ነው። እምነት ቢኖሮትማ ለእውነት ከቆሙት ጥቂት አባቶች ጎን በመሰለፍ የወቅቱን የተሃድሶ መናፍቃን ሴራ ባከሸፉ ወይም ለማክሸፍ ከአባቶችና ከምእመናነ ጎን በተሰለፉ ነበር።እንደ አባትነቶም የአዋሳ ምእመናንን እንባ ባበሱም፥የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔም አክብረው ባስከበሩም...ይገርማል!

አሁን ባሉበት ሁኔታ ውሰጥ ሆነው እንኳን(የጤናዎት ጉዳይ አጅግ አሳሳቢ በሆነበት ሰአት ) እግዚአብሄርን በመፍራት በንስሃ ያለመመለሶ ድፍረትም ያስገርማል። መቼም ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣የማይበድል የለም፤ ግን የእርስዎና የመሰሎቾ በጣም በዛ። ይህን የወንጌል ቃል እስኪ ልብ ይበሉት!

“ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።…ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥ የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ።”
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3 : 9-15

የዳዊትን ታሪከ ያሰታውሳሉ ? በአንድ ወቅት ከቤርሳቤህ መድረሱ ባሻገር ኦርዮን እንዴት እንዳስገደለ። ዛሬ የእርስዎ ስራ እንደዛ ነው። እርሶ ቤተክርስቲያንን በዘረኝነት ፥ በሙስና እና በማን አለብኝነት ሲበድሉና የእግዚአብሄርን ትአዛዝ በድፍረት ሲጥሱ ኖረው ልክ ኦርዮን ላይ እንደደረሰው ግድያ የተሃድሶ መናፍቃን አራማጆችን በመደገፍና በማበረታታት በርካታ ምእመናንን ለተኩላ ዳርገዋል፤ እየዳረጉም ይገኛሉ። ታዲያ ዳዊት በእግዚአብሄር ቸርነት በንስሃ ተመልሷል፤ እርሶስ እስከመቼ በሃጢአት እየተንገላቱ ይኖራሉ ?

ዛሬ ለእርሶ እግዚአብሄር ለዳዊት ጥፋቱን ለመንገር አንደላከው ናታን ያሉ በርካታ አባቶችና ምእመናንን በየጊዜው ወደ እርስዎ ልኳል። ልክ እንደ ዳዊት እነርሱን ስሟቸውና ሞት ሳይቀድሞት በንስሃ ይመለሱ።
"እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም" መጽሐፈ ኢዮብ 33:14

በዙሪያዎም ዘመድና ወዳጅ መስለው የተሰበሰቡትንና በግብራቸው እንደነ ኤልዛቤል፣ ይሁዳ፣ አርዮስ፣ ንስጥሮሰ፣ ሉተርና የመሳሰሉትን የሚመስሉ አፅራረ የቤተክርስቲያን ሃይሎችን አስወግዱ። ይህን ሲያደርጉ ከእግዚአብሄር ዘንድ ለስጋዎም ለነፍሶም እረፍትን ያገኛሉ።

“ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።”
የዳዊት መዝሙር 18:12-13

ይፍቱኝ!

Anonymous said...

you will see more bad news soon. abba melaku got best job which fits to his ability. guys , you have cry and pray. i am sorry what can i say to your bad holiy father (abba pauls)

Anonymous said...

መጋቤ ምስጢር፦

በቦታው ተገኝተን ቅኔዎን ባንሰማውም--ይዘቱ ምንም ይኹን ምን--ለአባይ ያሉት ቅኔ እንደርስዎ ምኞት ዐባይ እስከምጽአት ሲወደስበት የሚኖር ሳይኾን፤ የኢሕአዲግን ነፍስ ሊወስድ የተላከውን መልአከ-ሞት (ሕዝባዊ ዐመፅ) ገዝቶ (አታልሎ) ለማቆም በዐባዮች (በሐባልያን = በዋሾች፣ በቀጣፎች) የተጠነሰሰውን "መንግሥታዊ" ሴራ ከማዳመቅ አያልፍም። ደረቁ ሐቅ ይኸው ነው። (ርስዎን ግን መንቀፋችን አይደለም።)

Anonymous said...

አቡነ ፓውሎስ ከመቼ ጀምሮ ነው ቀዳማዊ ፓትሪያክ እያሉ መጠራት የጀምሩት? ምን ለማለት ፈልገው ነው የገባችሁ ካላችሁ አስረዱኝ አስኪ?

Anonymous said...

ቅዱስ ሲኖዶሱን በአባይ ሸወዱት በጣም ያስገርማል፡፡
ከመለስ መኮረጂ ተጀመረ

Anonymous said...

Abbay has now officially become your idol. Sinodos declared the choice of abbay from Orthodox Churches. There are no fathers left for the EOTC. The same thing with the children too. You can find no one. The real Ethiopians are no more existing. All of us
alive now are shameless, money lovers, talk show only. In the church from top to bottom, in government from top to bottom, forget the rest and you can find no body real Ethiopian. Back home and diaspora all just whisle only. No guts. You were given the original religion, you messed it up. You were given the best country,you messed that too. Better die than living like this. You all know what is wrong and what is right, but choosing the wrong. Adam was told the right thing to do, but he chose the wrong one. The result is not new for you all. Because your belief in GOD is not 100% complete, you are sufuring. It is not even " ye senfich Kintat yahil" as said on the Holy Book on your hand. If it was at least that much, you could have done a lot. This is the reality you all know. Every body I mentioned above have zero, none, empty belief. Am I insulting you? No, but telling you what you are. Don't try to give explanation or any response, I am not hearing to you at all, I am giving duff ears to you. Better choose GOD and live forever. Who am I? Nobody, but from the original EOTC-Ethiopia.

Anonymous said...

Aba Paulos has educated at Yale University. May be durign his stay there, he had became themeber of secret society 'bone and hte skull. visit the below website and you may find some clue why this pope is so devilish in his deeds and support only the bad doers in the church and stand againest the good doers.
http://meetilluminatimembers.com/skull-and-bones/

ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች እንደምን ከረማችሁ በቃ አለቀተብሎዝምተባለ የቤተክርስቲያናችን ነገር ያሉንአባቶች አረትና አምስትብቻናቸው ማለትነው ሌሎቹስ ለኛና ለቤተክርስቲያን ምንመሆናቸውነው!እግዚያብሄር ይስጠውና መምህር አእምሮ ሁሌ ሲያገኘኝ አኝገቴላይ ከወርቅ ሀብል በቀር የክርስቲያንነቴን መለያየሆነውን ክር ስለማያይ አንች እንግዲህ ሚኒሻ ሞሆንሽነው ክርስቲያን ነኝ ብለሽ ማተብሽን ግን የምታፍሪበት ይለኝ ነበር ነገሩ ሁሌአይገባኝም ነበር አንድቀንግን ደምንማትፈልጎእንደሆነ ጠየኩት እርሱም ሲመልስልኝ ሚኒሻ ማለት ለጊዜያዊ ጦርነት የሚመለመል መደበኛወታደርያልሆነ ማለትነው አለኝ እናየኔምክርስትና እንደግዜየው ሁኔታነው ማለትነው ብየእንዳስተውል ስላደረገኝ ከዚያበሁላ ካንገቴ ማተብ አልተለየኝም አሁንም ማለት የፈለግሁት እኒህሁሉ አባቶች የስብሰባ አድማቂዎች ብቻ ነበሩ እንጅ ለቤተክርስቲያንና ለምእመኑ ብሎም ለሀይማኖታቸው የቆሙ የሀይማኖት አባቶች ለመሆናቸው እጠራጠራለሁ ነው ምክንያቱም በመረጃ የተጠናከረ የሀይማኖት ቅሰጣና ዝርፊያ የቤተክርስቲያን ቀኖና ሲጣስ እያዩድምጻቸውን አጥፍተው እቃቃ ፈረሰ ዳቦተቆረሰ ብለው ወደመጡበት መበታተናችው በጣም ስላሳዘነኝእናበጣም ስላሳፈረኝም ጭምርም ነው የማህበሩንስችግርቢሆን ማንይሙት አሁን እነዚያሁሉ አባቶች በየአጥቢያቸው ያሉትን ገዳማትንና የአብነት ትምህርተቤቶችን እንደሚታደግ ጠፍቶአቸውነው በኮሚቴላይ ኮሚቴ እየመረጡ የሚቀልዱብን ደግሞስ የቤተክርስቲያን ችግር እስካልተፈታና የባሰችግር እስካለድረስ ቀኑን ጨምረው ችግሩንለመፍታት ያልቻሉት ለምንድነው!በቤተክርሰቲያናችን ቀኑእንዳይጨመር እንዳይቀነስ የተደነገገ ህግካለ እንግዲያስመታደስና መለወጥያለበት እንዲህያለው የማያሰራ ህግነው ብየ አምናለሁ ካጠፈሁ ይቅርታእጠይቃለሁ ይሄንበተመለከተ እርምትምሆነ አስተያየት(ትምህርት) ለመቀበል ዝግጁነኝ ደጀሰላሞችአንድበሉን ምንማድረግነው ያለብነ ዝምብለን እንጠብቅ ወይስ ማድረግ ያለብን ነገር አለ ብዙዘበዘብኩ መሰል ውስጤ ስለቆሰለ ቢቸግረኝ ነው ይቅርታ ወላዲተአምላክ መሀር ወልድየ ተዘከር ኪዳንየ ብላ አስራት ሀገራን ታስብልን ቸርያሰማን አሜን

Orthodoxawi said...

Hi Dejeselam,

Today (May 28 ... Ginbot 20) your site was unaccessible for several hours and now it is flaky (comes and goes). I don't have problem with my internet as I am not in Ethiopia.

What happened?

We want you to be accessible all the time. You are our ears, eyes, noses ... when it comes to getting some info about our church.

Pls fix it if the problem is from your side.

Melkam Be'al (Ye Emebetachin).

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

It is my first time to hear "Kedamawi Patriarc". What does it mean. Would you plse explain it to me if you know the meaning.

Anonymous said...

gud new!!! cher yaseman malet leka melkam new wegenoch,degmo yekedemut yet hadew new ersachew kedamawi patriyark yehonut???KEABATOCHAY ALBELTIEMINA.........ende elyas yemilubetin kena lib amlak yadelelin.

Bro said...

ምእመኑ ተቸግሮ ገንዘብ የሚሰተው ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ነበር አንጅ ለ መንግስትበጀትአልነበረም ምናለ ለፈራረሰው የካህናት ማሰልተና ና ለተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናት ቢሆን ለቤተክርስቲያን ይህንያሀል ብር ተመድቦ ያውቃል?

Anonymous said...

ያደለው አባት የሚስጠው ቃለ ምዕዳን
ከፖለቲካ ከዘር የፀዳ ጥርት ያለ መንፈሳዊ የሆነ ቃለምዕዳን ይህ ነው


His Holiness Pope Shenouda III - Easter Message April 2011
Saturday, 23 April 2011 02:41 | Written by Administrator | | |
His Holiness Pope Shenouda III
Pope of Alexandria & Patriarch of the See of St. Mark
Easter Message April 2011
My beloved children in the lands of immigration, both clergy and laity. I congratulate you for the Glorious Feast of the Resurrection, wishing you all that the Lord returns it upon you with all
goodness and blessing.
The resurrection of the Lord Christ was distinguished with an amazing power. He is the only One who was victorious over death by Himself. In His resurrection, He crushed death, and arose with the power of His Divinity. Also, by His power, He came out of the closed tomb which had a great stone upon it, without anyone seeing Him. Also with the same power, He entered the upper room where the disciples were, while its doors were shut. ="mso-tab-count: 1;"> After He spent forty days with them speaking to them about matters pertaining to the Kingdom of God, He ascended to the heavens with a great power, which is against all the laws of gravitational force. Of course, it is the power of His Divinity.
Therefore, St. Paul the Apostle said about Him, in the Epistle to the Philippians 3:10 “that I may know Him and the power of His resurrection, and the fellowship of His sufferings...” This is why we also praised Him throughout the Holy Week, confessing His power and saying to Him: “To You is the power ... Thok te tee gom.”
Our Lord Jesus Christ, who arose with power, and ascended with power, also grants us power. The Church started its history with power, when the Holy Spirit descended upon the pure disciples. The Bible says: “And with great power the apostles gave witness to the resurrection of the Lord Jesus. And great grace was upon them all.”
This power remained in the life of the Church. With great power, St. George was able to tear the decree of the emperor. Even all the martyrs received death with power, and they did not fear it. Instead, they reiterated the expression “...having a desire to depart and be with Christ, which is far better.” (Philippians 1:23)
Therefore, my beloved children and brethren, always be powerful. I mean, that you have spiritual power by which you defeat Satan, all the power of the enemy, all the wars of the ego, and all evil desires.
And in your victory, do not attribute this to your own personal power, but to the power of God which works in you, now and always.
Lastly, be well and absolved from the Holy Spirit; and pray for me.
His Holiness Pope Shenouda III
Glorious Feast of Resurrection April 2011

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)