May 21, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ሦስተኛ ቀን ውሎ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 21/2011)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በትላንት ግንቦት 12 ቀን 2003 ዓ.ም ግማሽ ቀን ውሎው ልማትን በተመለከተ፣ በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በየደረጃው በሁሉም የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት እና የአስተዳደር መዋቅሮች ተፈጻሚ ስለሚሆንበት ሁኔታ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ከወጣለት መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በርካታ ቤቶች እና ሕንጻዎች ፍትሐዊ ባልሆነ አፈጻጸም ያለጨረታ ለግለሰቦች በመሰጠታቸው፣ ሠራተኞች ከደንቡ ውጭ በመቀጠራቸው እና በመዛወራቸው በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ እየተመራ እርምት እንዲደረገበት ውሳኔ ስለተላለፈበት የቤቶች እና ሕንጻዎች ድርጅት ጉዳይ መወያየቱ ተሰምቷል፡፡


የተወሰኑ ብፁዓን የስብሰባው ተሳታፊዎች ትንት ለተዘከረው የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ክብረ በዓል ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እና እቲሳ ደብረ ላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመውረዳቸው መለስተኛ በተባሉ አጀንዳዎች ላይ ብቻ በተቀሩት አባቶች ስብሰባው እንደተካሄደ የጉባኤው ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ትንት ባስተላለፍነው ዘገባችን በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ዓመታዊ የሥራ ክንውን ሪፖርት ውስጥ በዓመት ከተያዘው ዕቅድ በላይ በስምንት ወራት ውስጥ ብር 40 ሚዮን ወጭ መደረጉን የዘገብን ቢሆንም መጠኑ እስከ ብር 60 ሚዮን ብር እንደሚደርስ ለደጀ ሰላም የደረሱት የጉባኤው ምንጮች መረጃ ያስረዳ፡፡


ከተጀመረ አንሥቶ እስከ አሁን ሰባት አጀንዳዎችን ያየው ስብሰባው ዛሬም በመቀጠል ጉባኤው ዛሬም አንገብጋቢ በተባሉት አጀንዳዎች ላይ በመቀጠል የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሥራ አፈጻጸም፣ መንፈሳውያን ተቋማትን፣ ስብከተ ወንጌልን፣ ማእከላዊነትን ባልጠበቁ አሠራሮች፣ በሲዳሞ ሀገረ ስብከት ችግሮች፣ በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና በማኅበረ ቅዱሳን ግንኙነት ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

5 comments:

Mesi said...

Melkamun yaseman

kal said...

amlake kidusan cher nehina haylehi geltseh melkam zena aseman!!!

Orthodoxawi said...

እግዜር ይስጥልን ደጀሰላም::
የጉባኤው ውጤትም እንደ ከዚህ በፊቱ በአባ "ፓትርያርክ" ልበ ደንዳናነት እና እቡይነት ምክንያት "ውኃ ቢወቅጡት እምቦጭ" ከመሆን ያድነው::
እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያንን ከመናፍቃን እና ከእነ ሆድ (ስልጣን) አምላኩ ሴራ ይጠብቅልን::
እነርሱንም ቅን ልቡና ይስጥልን::
አሜን!

ይቅር ይለን ዘንድ ጸልዩ!!!

Anonymous said...

ስድሳ ሚሊዮን ምን አላት? ከ8.4 ቢሊየን ጋራ ሲነጻጸር ማለቴ ነው። ስለዚህ ገና ይግጣሉ ወዳጆቼ። ሐይ የሚላቸውም የለም።

ሐይ ባዮቹ፣ እረኞቹ ራሳቸው አኹን ተለውጠው ፍየሎች ከኾኑ ምን ይደረግ?

frehiwot said...

o!AMLAKIYE ETAREYENI MUSSINAHA LE EYERUSALEM!AMLAKE HOY YE EYERUSALEMIN TIFAT ATASAYEGN.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)