May 22, 2011

የቅ/ሲኖዶስ አራተኛ ቀን ውሎ (ሪፖርታዥ)

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

  • ቅዱስ ሲኖዶስ ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመተግበሩ ተገለጸ፤ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልት ሳይነሣ ታለፈ
  • ዋነኛው ችግር በመምሪያው አሠራር ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት ነው፤
  • ሌሎች ያልተተገበሩ የሲኖዶሱ ውሳኔዎች “ወዘተርፈ እና ሌሎችም›› በሚል  ብቻ ከመወሳት በቀር በዝርዝር ቀርበው አለመገምገማቸው እያነጋገረ ነው፤
  • የሐዋሳው አጣሪ ኮሚቴ ጥናት እና የምእመናኑ አቤቱታ በሪፖርት ቀርቧል፤
  • በጨለማው ቡድን ኮሚሽን ተደርገው በስመ ‹ደኅንነት› የሚንቀሳቀሱ ጉልበተኞች የማዋከብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግር ጠንካራ አቋም ካላቸው ብፁዓን አባቶች ጋራ ግንኙነት ያላቸውን አገልጋዮች በስልክ ያስፈራራሉ፤ በአካል በመከታተል ያዋክባሉ፡፡ መንግሥት ዜጎች ለሃይማኖታቸው መጠበቅ ለመቆም ያላቸውን ሕገ መንግሥታዊ መብት ሊያስከብርላቸው ይገባል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 22/2011)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዳሜ ግንቦት 13፣ 2003 ዓ.ም አራተኛ ቀን ውሎው ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ በጥቅምት ምልአተ ጉባኤው ያስተላለፈው ውሳኔ በአግባቡ ተግባራዊ አለመሆኑን ገመገመ፤ ውሳኔው ተከብሮ እንዲሠራበት አሳስቧል፡፡

ያልተገባ ጥቅምን አማክለው የሚንቀሳቀሱ እና የቤተ ክርስቲያንን ዐውደ ምሕረት መነገጃ ያደረጉ ሕገ ወጥ ሰባክያን እና ዘማርያን ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔ ያሳለፈበትን የወርኀ ጥቅምቱን ቃለ ጉባኤ እና ቀደም ሲል የወጣውን የስብከተ ወንጌል ደንብ ምልአተ ጉባኤው በንባብ አድምጧል፡፡ የሕገ ወጥ ሰባክያንን እና ዘማርያንን ስምሪት ለመከላከል የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በሚያከናውነው ተግባር ላይ በፓትርያኩ ጽ/ቤት የሚደረገው አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የችግሩ ዋነኛ መንሥኤ መሆኑን ምልአተ ጉባኤው በደማቁ አሥምሮበታል፡፡


“ሀገረ ስብከት ቀርቶብኝ በመምሪያው የበላይ ሓላፊነቴ ተወስኜ ብሠራ እመርጣለሁ” በማለት አገልግሎቱ ከምንጊዜውም በበለጠ የሚሻውን የሙሉ ጊዜ ትኩረት ለምልአተ ጉባኤው ያስረዱት የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ “እኔ ሳግድ እርስዎ [ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ] ካልፈቀዱ ችግሩን በቀላሉ መከላከል ይቻላል” ብለዋል፡፡ ይህንና ሌሎች ተዛማጅ የስብከተ ወንጌል ችግሮችን የገመገመው ምልአተ ጉባኤው ለሁሉም አህጉረ ስብከት የተላለፈው የስብከተ ወንጌል ደንብ፣ በየካቲት ወር 2001 ዓ.ም እና በጥቅምቱ ምልአተ ጉባኤው በቋሚ ሲኖዶሱ የወጣው ውሳኔ ተከብሮ እንዲሠራበት፣ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሳያውቀው አንዳችም የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ  እንዳይኖር አሳስቧል፡፡ ከዚሁ አጀንዳ ጋራ በተያያዘ በቅርቡ ከነበሩበት የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሥር ወጥተው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት ሥር እንዲዋቀሩ የተደረጉት የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እና የልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ መጽሔት ኅትመቶች ዝግጅት ክፍሎች ቀድሞ ወደነበሩበት መዋቅር  እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶሱ ትእዛዝ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡

ከስብከተ ወንጌል ባሻገር ሌሎች ያልተተገበሩ የቀደሙ የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔዎች(የአቡነ ጳውሎስን ሐውልተ ስምዕ መነሣት ጨምሮ) በምልአተ ጉባኤው አባላት ይሁን በአጀንዳ አርቃቂው ኮሚቴ፣ በብፁዕ ዋና ጸሐፊው ይሁን የጥቅምቱ ጉባኤ የማስፈጸም አደራ በጣለባቸው ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ በዝርዝር ተወስተው አለመገምገማቸው ብዙዎች በጉባኤው ላይ የነበራቸውን ተስፋ ከወዲሁ ሊያመነምነው ጀምሯል፡፡ በአንዳንድ የስብሰባው ተከታታዮች ትዝብት፣ ፓትርያኩ የሲዳሞ ሀገረ ስብከትን እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ያለውን የሥራ ግንኙነት ችግሮች የተመለከቱ አጀንዳዎች እንዳይያዙ አስቀድመው ተቃውሟቸውን ያከረሩት ቆይቶ እነዚያኑ የተቃወሟቸውን አጀንዳዎች በመቀበል የምልአተ ጉባኤውን አባላት ቀልብ እና የውጤታማነት አስተሳሰብ በእኒሁ ጉዳዮች ዙሪያ በማሰባሰብ /በመወሰን/ ለሌሎቹ ጉዳዮች ልብ እንዳይኖራቸው የማድረግ የሥነ ልቡና ጨዋታ ነበር፤ በትንቱ የምልአተ ጉባኤው አያያዝ ይኸው አጀንዳን አጉኖ በማሳረፍ /ወጥሮ በማርገብ/ አካሄድ የመደራደር ስልታቸው የሠራላቸው ይመስላል፡፡ ይሁንና ታዛቢዎቹ አያሌ ምልከታ የነበራቸውና ያልተተገበሩት የሲኖዶሱ ሌሎች ውሳኔዎች “ስብከተ ወንጌል እና ወዘተርፈ›› በሚል ብቻ መወዘት እንደማይገባቸው የምልአተ ጉባኤውን ተሳታፊዎች ያሳስባሉ፡፡

የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የሥራ አፈጻጸም የገመገመው ምልአተ ጉባኤው ከቀትር በኋላ ውሎው በሐዋሳ ምእመናን በማስረጃ የቀረቡት የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ችግሮች እና ሁኔታውን ለማጣራት ለሁለት ጊዜያት የተላከው አጣሪ ኮሚቴ ያጠናቀረው ዘገባ በሪፖርት ቀርቦለት ተሰምቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ከተለመደው በተለየ አኳኋን ዛሬም (በእሑድ ሰንበት) ቀጥሎ በሚውለው ስብሰባው በቀረበው ሪፖርት እና በቀሪ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ታውቋል፡፡

15 comments:

Shema-israel said...

I could able to understand two things:
1) comparing to the passed meetings, our fathers have tried to learn of save secret matters until it will declar officially
2) Holy Spirit has been intervening their agenda not to extend for bad thing.

Conclusion:
More or less, it is good
May God maximize the synod unity

Anonymous said...

እግዚአብሔር ለምድ ከለበሱ የሃይማኖት መሪዎች ቤተ ልርስቲያናችንን ይጠብቅልን !!!!!!!

Anonymous said...

yehe gize yalf yihon??????????? ene enga bicha ferahuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuu!!!!!!!!!!

A.M said...

እኔና ጓደኞቼ ተነጋግርን ለሀይማኖታችን የህይወት መስዋእትነትን ለመከፈል ተዘጋጅተናል. ነገር ግን በነፍሳችን አንዳንሞት ኦርቶዶክሳውያኑ ሰለኛ የሚጸልዩልን ከሆነ እኛ ተዘጋጅተናል.ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ የመጀመርያውን ውጤት ታያላችሁ. እንዲህ በቤተክርስቲያናችን እየቀለዱ አይኖትም
A.M. from addis

Anonymous said...

Why is Dejeselam entirely focused on the '-ve' of our religion?.... why ... why... why?

Anonymous said...

tesfaye egeziabeher new. I gave up on z sinod. beresun gize betun endiyateda amelaken amnewalehu.

ርብቃ ከጀርመን said...

ይሄ ግዜ ያልፍይሆን ነውያልከው ወንድሜ ሰላም ደጀሰላሞች አወ ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋን ይሆናልና ለሚመጣው ነገርሁሉ በማስተዋልና ከመቸውም በበለጠሁኔታ አንድነታችንን በማጠንከር በፀሎትም ሆነ ትክክለኛ መረጃ በመስጠትም ሆነ በማካፈል ጠንካራ ከሆኑ አባቶችጎን በመሰለፍ እስከወዲየኛው አብረናቸው በመሆን የሚያስፈልገውን ግዴታችንን ለመወጣት የኛም ዝግጁነትና ያምላካችንም ቸርነት አይለየን ኢትግድፈነ ወይትመንነነ አምላከሰላም ተራድአነ በማለት በተስፋ ወደርሱ እንጩህ ቸርያሰማን አሜን

Anonymous said...

itariene musinawa le betekristian amlak hoy yebetekristiyanin tifatuan atasayegn
ines betam chenekegn tesfam alitay alegn isti amlak hoy ye giyazin sayhon ye elsan ayin sitegn kefetenaw yilik yanten hayil ayi zend

ብዐሩ ዘአትላንታ said...

ለሃይማኖት አባቶች የማይገዛና ምህረት የሌለዉ ጉልበተኛ ለመንግሥትም የሚያስፈራ መሆኑን ተረድቶ መንግሥት ለሰላም ሲል ወንጀለኞችን ካልገራ የወንጀሉ ተባባሪ ነዉ ለማለት ያስደፍራል። ቤተ ከክርስቲያንና ትጉህ አባቶች እንዲህ የሚለፉትኮ በስነ-ምግባር የታነጸ፣ሀገሩንና ባህሉን አክባሪ ትዉልድ ለማፍራት እንጂ የግል ጥቅም አስገድዷቸዉ እንዳልሆነ አላዉያን ነገሥታት ልብ ሊሉ ይገባል። በየ አደባባዩ እና በየሸንጎዉ ስለ ሰላም የሚለፍፉ ሁሉ ቤተ ክርስቲያናችንን የሚዳፈሩ ፖለቲከኞችን የሚያሰለጥኑ ተኩላዎችን እዲያስታግሱ ይመከራሉ። ለአላዉያን ነገሥታት የ አራት ኪሎዉ ቤተ መንግሥት ክብር እንደሆነ ሁሉ ቤተ ክርስቲያናችን ለእኛ የድኅነት ቤተ መንግሥታችን ናትና እርግጫዉ ይቁም። አባ ጳዉሎስ ትምክህት ያደረጉት እግዚአብሔርን ቢሆን ኖሮ በአገልግሎት አቻ ለሆኑ አባቶች ርህራሄና ክብር ይኖራቸዉ ነበር። ዘመዶቼ ያፈርኩበት ዘመን ቢኖር አሁን ነዉ። አንድ ገጠመኝ ላጫዉታችሁና ሐሳቤን ልቋጭ። በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ወዳጄ አንድ ዓይኑ ጠፍቶ ሳያዉቀዉ ለዓመታት እንደቆየ አስተዉላለሁ። በአንደኛዉ ዓይኑ መጥፋት እየደከመ የመጣ ዓይኑን ለመታከም ሐኪም ዘንድ ሂዶ ነበር ጨርሶዉኑ የአንደኛዉን ዓይን መጥፋት የተረዳዉ። ምናልባት አቡነ ጳዉሎስም ቤተ ክርስቲያን ጠላቶቿ በበዙበት ዘመን ሰሚ ጀሮ እና የሚያይ ዓይን ያጡት ታዉረዉ ወይ ደግሞ ደንቁረዉ እንዳይሆን ። ብዕሩ ዘአትላንታ

Anonymous said...

why are u always focused at the negative side of the holy synoid?... why?

Anonymous said...

ከሁሉ አስቀድሞ የምሰጠው አስተያየት የድፍረት ሆኖ እንዳይወሰድብኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ::

ባለፈው ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፋቸው ብዙ ወሳኝ ውሳኔዎች ነበሩ:: እነዚህ ውሳኔዎች ምን እንደደረሱ ለሁላችንም ግልጽ ነው:: ከላይ ከፓትሪያርኩ ጀምሮ እስከ የመጨረሻው አገልጋይ ዲያቆን ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ንብረት እየተቀባበሉ በሚዘርፉበት በአሁኑ ጊዜ በዚህ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንፈስ ቅዱስ ይገኛል ማለት ራስን ማታለል ነው:: ስለዚህ እንደተለመደው ውሳኔ አሳልፈው ይለያያሉ አማኙም ባዶ ተስፋ ይዞ ይቀራል በአንጻሩ ግን ምንም ለውጥ አይኖርም:: አዝናለሁ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም ግን ሃቁን ለመናገር ነው::

Anonymous said...

በአራተኛው አስተያየት ላይ ወንድሞቼ ሆይ ተቃዋሚዎቻችን ዘወትር የሚገፉን መንገድ ስለሆነ ጠንቀቅ እንበል አሁን እናንተ የምትሉትን ሃሳብ በስሜት ብዙ ሰው ይለዋል ግን ይሄንንማ የሚፈልጉት ወጥመድ መሆኑን ሲያስታውስ እናም እኛን በዚህ ወጥመድ ጥለው እነሱ ስራቸውን ሊሰሩ እኛን በነብስም በስጋም ሊገሉን እነሱም የተመኙትን ስጋ ሊያደልቡ መሆኑን ሲያስብ እና ይህ አካሄድም የኛ እንዳልሆነ ሲያስብ እራሱን እየገታ ነው እንጂ መፍትሄ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም ከጎናችሁ በሆንን ነበር ስለዚህ በማስተዋል እንጓዝ እንበርታ እንጸልኝ የምናመልከው አምላክ ሁሉን ሊለውጥ ቀን አለው እንታገስ ውሳኔችንማ ይሄ ከሆነና ፈራጆቹ እኛ ከሆንን ለምን እስከ ዛሬ ተቀለደብን ስላልገባን ነው ብላችሁ ነው አይዞችሁ በርቱ ጸኑ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን

Anonymous said...

My people; we are stressed with many problems.On one side religious issues and on the other managing life. We can't be focused. I am now doughting that the Government has tried to divert the attension of the people through Abune Pawulos and became sucessful. Why Abune Pawulos became such dictator? Do you think he will do this with out Government's support? From where did he got this confidence and did everything he wants against the rule? Many people are starving and sufering from inflation which absolutely is Government's fault. A liter OF oil is being sold 60-70 birr.Fuel price is increasing eavery time. A killo of Sugar which said to be cost 3-4 birr is being distributed by Government agent at over 16 birr.Is the Government became rent seeker? I think the main cause of the problem is the Government. It should be blamed for that and will also pay price for this wrong doings.

Anonymous said...

yesewyewun foto sayew...deretu lay yalewun meskel egna abatoch lay aychew alawkim:: Lemin yihon???

Alemayehu G./Woldia said...

መንፈሳዊ ወንድሞቼ በራሳቸው ህይወት ላይ ለመወሰን ያላችሁን ሀሳብ ያቀረባችሁትን ሀሰሳብ ተመልክቼ በጣም ባዝንም ያላችሁን ፍቅር ሳላደንቅ አላልፍም ሆኖመም እኛ በምድር ያለን ሰወች እስካለን ድረስ በሀይማኖታችን በመጽናት ለቤተክርስቲያናችን በመጻለይ ፍርዱን ለእግዚአብሔር መተው ይገባናል ስራውን እሱ በጥበቡ ያከናውናል፡፡ ሆዳም ሰው በሆዱ ይጠፋልና ትልቁ ነገር ጉዳዩን በማወቅ የድርሻችንን ለመወጣት መትጋት እንጂ ራስን ማጥፋት ለሰይጣን ትልቁን ግብ ማሳካት ስለሆነ ብታስቡበት

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)