May 21, 2011

ነፍስ ይማር (ርእሰ አንቀጽ)

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ            

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ 56 ዓመት ቁጥር 119፤ ሚያዝያ፣ 2003 ዓ.ም)፦ በአሁኑ ጊዜ የተከሠተውን የኑሮ ውድነት አስመልክቶ የኢ... መንግሥት ለመላው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ባደረገው የደመወዝ ማስተካከያ መሠረት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞችም ወጉ ደርሷቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ትልቁም፣ ትንሹም፤ የትላንቱም የዛሬውም፣ የሦስት ሰዓቱም የስድስት ሰዓቱም የዘጠኝ ሰዓቱም፣ ትጉሁም ሰነፉም እኩል የደመወዝ ማስተካከያ አግኝተው ከላይ እስከታች ረክተዋል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ተገፋም አልተገፋም ለጊዜው ዕድሜ ለኤ... መንግሥት ብለዋል፡፡ የደመወዝ ማስተካከያ ጥናቱን ላጸደቁት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ፣ ለወቅታዊው የቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና ለአጥኒው ክፍልም ምስጋናቸውን አልነፈጉም፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ዕትሙ ጥቆማ ያደረገው ዜና ቤተ ክርስቲያንም እደግ ተመንደግ ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራተኞች በመንፈሳዊው ትምህርት ብዙ መለኪያ ያላቸው ሲሆኑ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሚካሄደውም በእነሱ የተለያዩ የሞያ ዘርፎች ሲሆን ዝንተ ዓለም በወረቀት እና በአቅም እየተመካኘ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ጋራ እኩል ሳይቆጠሩና ከሀገሪቱ የሚገኘውን በረከት እኩል ሳይቋደሱ ዘመናትን አሳልፈዋል፡፡ በጎስቋላው ኑሯቸው ቤት የሚያከራያቸው እና የሚጋባቸውም እስከማጣት ድረስ ከማንኛውም ማኅበራዊ ኑሮ ሳይሳተፉ ከብዙኀኑ ኅብረተሰብ ተገልለው ይኖሩ እንደነበረ አገር ያወቀው፣ ፀሃይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ ለዘመናት የሥቃይ ኑሮን ሲገፈግፉ ሕይወታቸውን ጨርሰው ወደ ወዲያኛው ዓለም የተጓዙትንም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዘመን እንጂ ሰው ሊቆጥራቸው አይችልም፡፡

በዚህ ረገድ በአሁኑ ጊዜ ከላይ እስከ ታች ያለነው መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሠራተኞች ከሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ጋራ እኩል ከምንታሰብበት እና ከምንታይበት ጊዜ መድረሳችን ትልቅ ብፁዕነት ወይም ብቃት ነው፡፡ ድክመታችንን ሁሉ ታግሦ፣ ረዥም ዕድሜ ሰጥቶ ከዚህ ዘመን እንድንደርስና እንድናይ ላደረገ ቸር አምላክም ምስጋና ልናቀርብለት ይገባናል፡፡ እኛም እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች በየደረጃችን የአገሪቱ በረከት ተቋዳሾች እንድንሆን የደመወዝ ማስተካከያውን የፈቀደውን የኤ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት፣ ጥናቱን ያጸደቀውን አካልና አጥኒውን ክፍል ማመስገን ተገቢ ቢሆንም ወደ ሐቁ ስናመራ ግን የበለጠ ልናመሰግናቸውና ልንዘክራቸው የሚገባን የእግዚአብሔርን ወይም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብ በሰማዩም በምድሩም በሆነ ባልሆነው ሳያባክኑ በፈሪሃ እግዚአብሔር በጥንቃቄ ጠብቀው ያቆዩትንና የገቢ ምንጭ ፈጥረውልን ያለፉትን አባቶች ናቸው፡፡

የቀደሙት አባቶች ከዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ገቢ የሚያስገኙ ታሪካውያን መካናትንና ቅርሳ ቅርሶችን በጥንቃቄ በመያዝና በመጠበቅ፣ ሰበካ ጉባኤን በመላ ኢትዮጵያ በማቋቋም፣ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚሆኑ ታላላቅ ሕንጻዎችን በመሥራት የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ልትንቀሳቀስ የቻለችበትን መላ ምት ፈጥረው ወይም ለተውልድ የሚተላለፍ ሥራ ሠርተው ባያልፉ ኖሮ ማሻሻያም እንበለው ማስተካከያ ዛሬ የደመወዝ ጭማሪው ከየት ይገኝ ነበር? ከጸፍጸፈ ሰማይ ወይስ ከውቅያኖስ? ከሁሉም አይገኝም ነበር፡፡ በዚህ ረገድ የደመወዝ ማሻሻያውንም ሆነ ጭማሪውን ያስገኙልን በዐጸደ ሥጋ ወይም በሕይወተ ሥጋ ያሉት ሳይሆኑ በዐጸደ ነፍስ ወይም በሕይወተ ነፍስ ያሉት አባቶቻችን ናቸው ለማለት ያስደፍራ፤ በትክክልም ናቸው፡፡

ይህ ከሆነ ዘንድም ያለፉትን አባቶች ነፍስ የማስማር ብቃቱ ባይኖረንም አባባሉ የተለመደ ስለሆነ ሁላችንም ያለፉትን አባቶች ነፍስ ይማር ማለት ይገባናል፡፡ ያሉትንም አባቶች በእነሱ የማስተዋልና የቅድስና መንገድ እንዲመራቸውና የእነሱን አስተዋይ ልብ እንዲሰጣቸው ሌት ተቀን ሳናቋርጥ መጸለይ ይኖርብናል፡፡ የነገይቱን ቤተ ክርስቲያን ከአሁኑ በበለጠ (በተሻለ) መልኩ ማንቀሳቀስ ለአገልጋዮቿም ከአሁኑ የተሻለ ኑሮ መፍጠር የሚቻለው የአሁኖቹ አባቶች ሠርተውት በሚያልፉት ቀዋሚ ሥራ ነውና፡፡

ያም ሆነ ይህ መብት በተከበረ መጠን ግዴታም መከበር ስለአለበት ከእንግዲህ ወዲህ ትልቅ ትንሹ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች የሚበሉት ገንዘብ የእግዚአብሔር ገንዘብ መሆኑን በጥልቀት ተገንዝበው ‹‹በልአ ደይኖ ወመቅሰፍቶ›› የተባለው እንዳይፈጸምባቸው በሚበሉት መጠን መሥራት፣ በትጋትና በቅንነት ማገልገል አጥብቆ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱም ሁሉንም ሠራተኛ በሞያውና በሚበላው መጠን ወደ ሥራ ማሠማራት፣ አጥብቆ መከታተልና መቆጣጠር አለበት፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ሥራ ይጨመርልን ወይም በሞያችን መጠን ሥራ ይሰጠን እንጂ ደመወዝ ይጨመርልን ብለው የሚጽፉት ማመልከቻ መገታት አለበት፤ ይህም ማለት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከበከቱ ያልተቋደሰ ሠራተኛ ካለ መብቱን አይጠይቅ ማለት አይደለም፡፡


በተረፈ የደመወዝ ጭማሪውን የበረከት እና የጤና እንዲያደርግልን፣ በዓለ ትንሣኤው የሰላም፣ የፍቅር፣ የስምምነትና የደስታ በዓል እንዲሆንልን ዜና ቤተ ክርስቲያን ምኞቱን ይገልጻል፡፡

(መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ)

6 comments:

Focal point said...

የሚበሉት ገንዘብ የእግዚአብሔር ገንዘብ መሆኑን በጥልቀት ተገንዝበው ‹‹በልአ ደይኖ ወመቅሰፍቶ›› የተባለው እንዳይፈጸምባቸው በሚበሉት መጠን መሥራት፣ በትጋትና በቅንነት ማገልገል አጥብቆ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱም ሁሉንም ሠራተኛ በሞያውና በሚበላው መጠን ወደ ሥራ ማሠማራት፣ አጥብቆ መከታተልና መቆጣጠር አለበት፡፡

kal said...

Dejeselamoch seletigatachehu enameseginalen gin ebakachehun yetenantina ye sebseba wulo post adergulen egna bechinket lenalk newu newu weyinim bemafiya buden asgedajenet sebsebawu tekwuarete ende??????????????? ere tewu endih atechekinu!!!

Amlake kidusan cher yaseman

Anonymous said...

minew minew deje selam ..eytebekin eko new ye sinodosn siebseba ? minew chiger tefetro kehone ngerun minew zim alachu ...sibesebaw min derese..? zegebachihun lemin akomachew ? ere bakachu betam techenkalehu... beyibelet enanite mezegebachihun sitetew bizu asebku ...yehonewun yederesebachuhn neger nigerun biyans betselot enasbachihualen

Anonymous said...

አሁን ነፍስ ይማሩን ትታችሁ የሶስተኛውን ቀን ውሎ አሳውቁን እባካችሁ!!

Unknown said...

Dear Deje Selamaweyan,
We are working on the report. Please be patient.

Anonymous said...

እኔ እኚ ሰውዬ ሀውልት ስር ሄጄ እየሰገድኩ ሀውልቱን እና ሰውዬውን ላመልክ ተዘጋጅቻለው!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)