May 17, 2011

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ረቡዕ ይጀመራል (አርእስተ ዜና)


 (ደጀ ሰላም፤ ሜይ 17/ 2011)፦
  • ቋሚ ሲኖዶስ ፓትርያሪኩ በአጀንዳነት እንዲያዝላቸው ያቀረቡትን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጥያቄ አልተቀበለውም፤ በፓትርያሪኩ ከቀረቡት ዕጩዎች   መካከል እስከ ብር 150,000 እጅ መንሻ የሰጡ ይገኙበታል ተብሏል፤   የ18ቱ ታሳቢዎች ዝርዝር ደርሶናል::
  • የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመስፋፋቱ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የሚፈጸመው ሹመት አስፈላጊ ቢሆንም ከተሿሚዎች ተገቢነት፣   ለሹመቱ ከተደረገው ቅድመ ዝግጅት እና ወቅታዊነት አኳያ ሹመቱ   ተቃውሞ እየገጠመው ነው::
  • የሐዋሳ፣ ዲላ፣ ይርጋለም እና ነገሌ ቦረና ምእመናን ውሳኔ ባላገኘው አስተዳደራዊ ችግሮቻቸው እና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሆነው  በተሾሙት ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ላይ ‹‹የማጠቃለያ ነው›› ያሉትን  አቤቱታቸውን ዛሬ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አባላት ያሰማሉ፤ በአቡነ ፋኑኤል፣  በጋሻው ደሳለኝ እና ያሬድ አደመ ላይ የተጠናቀረው የ1፡17 ቪሲዲ የአቤቱታው ቀጥተኛ ማስረጃ አካል ነው::
  • አቡነ ጳውሎስ በተጭበረበረ ሰነድ መነሻነት ‹‹ሲኖዶሱን ለመቆጣጠር እና  የራሱን ፓትርያሪክ ለመሾም የ25 ዓመት ዕቅድ አውጥቷል›› ያሉትን  ማኅበረ ቅዱሳንን በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ለመክሰስ ተዘጋጅተው ነበር::
  • ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጸሐፊው ስም የሐሰት ሰነድ በማዘጋጀት ለፓትርያሪኩ የሰጠውን አካል/ግለሰብ በሕግ ይጠይቃል ተብሏል:: 
  • ሲኖዶሱ የመወሰን ብቻ ሳይሆን ውሳኔውን የማስፈጸም አቅም እና ንቃት  እንዲኖረው እየተጠየቀ ነው::
 ዝርዝር ዜናዎች እንደደረሱልን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል።

10 comments:

Egziabher Hoy Erdan said...

Wud Deje-Selamawuyan, yeBete-Krstiyanacenn woqtawi huneta leMemenan lemadres bemitadergut tiret hulu yeAmlakachin Erdata ayileyachihu, Egziabher yabertachihu. Egziabher Menfes-Kidus Abatochachinin anid hasab adrigo leBete-Krstiyan yemibejewun wusane endiwosinu, yetelat diablosin mikrun endiyakeshifilin, beBete-Krstiyan lay yatemedewun wetmed endisebabirilin hulachinim kelibachin ENITSELIY:: Selame Egziabher kehulachinim gar yihun:: Amen::

ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች መቸምለወጉ ሰላም አልኩዋችሁ እንጅ እንዲህ አንጀት የሚያቆስልና ጨጉዋራ የሚልጥ ዜናእየነገራችሁን ምንሰላም ይኖራል! ምነው እግዚአብሄር ስንቱንሮጦያልጠገበወጣትና ስንቱንየቤተክርስቲያን ሊቅ በግዜሲወስዳቸው(በሰውኛአመለካከት) እኒህን ጉድዝምአላቸው መቸምቢቸግረኝእንጅ የክርስቲያን ደንብስአይደለም ለሰውሞትንመመኘት እርሳቸውም ቢሆን ጤናቸው ባስጊሁኔታላይ እንዳለነው የሚወራው ጋንግሪን ይዞአቸው በ8000ሽ ብር በየግዜው መርፌ እየተወጉእድሜያቸውንእንደሚያራዝሙነውየሚወራው ታዲያ እኒህሰውየ ጉቦቢበሉ ምንይደንቀኛል እኔስብሆን የዚህንሰውየሞት ብመኝ አጠፋሁ!ለዚያውስ በሞታቸው ችግሩከተቃለለአይደል ጦሳቸው እንዲህ እንደዋዛ መቸየሚለቃትነውና ቤተክርስቲያንን!

Anonymous said...

yetewahedo lijoch bertu bizu bizuoch alen ayzoachihu Amlak kenatega yihun.

Anonymous said...

yestarday 300.000 __500.000 tuday 150.000 hone lemn mewashet asfelege ketenagerachihu ewnet tenageru sihon yihinn batilu melkam neber mannm ayantsim zare lemeshom yekerbutin bicha sayihon yekedemutim begenzeb yeteshomu nachew yasbilal hulum yigebachewal ayibalim yemigebachew yinoralu -yetemaru yinoralu-yeseru yinoralu siho sihon ega zim binl egziabher yinageral zemenu gizew wekitu kebad honoal malet new weyim yene amelekaket lik aydelem malet new gebena meshefen yasfelgal tselat yiskal tehadso menafkan temechachew hulet sinodos yeamara -yetgray -yeoromo yegonder -yeshewa -yegojam-yewelo -church tebale ahun yekerew yegurage new yasaznal yasafiral ahunim yemiyababs neger atasnebbun yemyatseb neger yishalal beterefe bertu

YeAwarew said...

Stay true to the cause. Keep it up! At least you are doing something instead of the majority of us who are just sitting on our "....", you know what. Talk is cheap, so you guys just keep on fightin', we are behind you !

May the Almighty God protect his Church, the true Fathers and the people in service, what more can we say...


Love & Peace

Anonymous said...

I can imagin from no comment since this News was posted that your Ethiopian readers might not be able to read it. Watch out!!
Tazabiw

admasu said...

እኛን ምን አድርጉ ትሉናላችሁ? የሲኖዶሱን ክብር ያስጠብቃሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት አባቶች ድምጻቸው ጠፋ። እንደ አቡነ አብርሃም ያሉትም ከሲኖዶሱ 12000 ማይልስ ርቀው ተቀምጠዋል።

man yazewal said...

ልክ ብልሃል አድማሱ ብዛት ያላቸው በአግር ውስጥ ያሉ ጳጳሳት ይህን ታላቅ ፍልሚያ በተደጋጋሚ ድል አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱ
ን እየተደበደቡም ቢሆን በራቸው እየተሰበረ እዚህ አድረሰዋታል።
ብዙዎቻችንን ኮርተንባቸዋል። ይሁን እንጂ በውጭ አገር በተለይም በሰሜን አሜሪካን ያሉ አባቶች የዛሬ ዓመት ግንቦት ላይ አልተገኙ
በዚህ ዓመት በጥቅምቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልተገኙም በዘንድሮውም ስብሰባ ላይ አልመጡም። ታዲያ እነዚህን ምን እንበላቸው። የሲኖዶስ አባላት ናቸው ወይስ ነጋዴዎች ጥቅምትና ግንቦት ለእነርሱ ሲል ባይመጣ ደስታቸው ወደር የለውም ነበረ።
ደግሞ እኮ የሚሰጡት መልስ ከሄድን ድጋሚ እንድንመጣ አያደር
ጉንም እንደሚሉ ይሰማሉ ማፈሪዎች። ምእመኑ ወደ አገሬ መቼ ልግባ ይለል እናንተ ግን ለራሳችሁ ድሎት እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ምንም ደንታ የሌላችሁ ከአባ ዛሬ በመከራዋ ሰዓት ከተቀሩት አባቶች ጋር አብራችሁ ሆናችሁ ተነጋግራችሁ ለቤተ ክርስቲያን መፍትሔ ካልሰጣችሁ በሃገረ ስብከታችሁ ያለውን ውጣ ውረድ ካላቀረባችሁ የእናንተ እዚህ መቀመጥ ለመሆኑ ትርጉሙ ምን ይሆን?

Anonymous said...

Where is the list. It seems Wushet... Awututna Eneyew....

Anonymous said...

"በአቡነ ፋኑኤል፣ በጋሻው ደሳለኝ እና ያሬድ አደመ ላይ የተጠናቀረው የ1፡17 ቪሲዲ የአቤቱታው ቀጥተኛ ማስረጃ አካል ነው::"

Is it asking to much, if you could specifically state about which "የ1፡17 ቪሲዲ" you are talking about.

You are doing a good job; but at the same time you are not delivering the facts as they must be; you tend to make them as if they are somebody's "private secrets".

This method of work has damaged our church. You must must fight evil by arming the Me'emenan with
all the fact.

It is not necessary for you to censure some of the information and leave Me'emenan with partial
information while you keep all the rest of what Me'emenan must know!

Have the courage and dignity to accept such criticism from people who have followed your blog from it's beginning!

Please give us the facts without
censure!

May God save our Tewahedo Faith and Church!

With appreciation for Deje Selam's dedication and sacrifice,

Eyassu Mussie

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)