June 29, 2012

አጀንዳችን አንድ ነው - ሃይማኖታችን እና ቤተ ክርስቲያናችን ብቻ!!!!!!

To Read, Print & share, click HERE (PDF).
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 13/ 2011)፦  ላለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናሳስብ እንደቆየነው ቤተ ክርስቲያናችንን ከፊት ከኋላ፣ ከግራ ከቀኝ እና ከውስጥ ጠፍንገው የያዟት ችግሮች የበለጠ እየተገለጡ፣ ፈተና የሆኑባት ግለሰቦችም የበለጠ እየታወቁ፣ በሕዝቡ ዘንድ ይፈጥሩ የነበሩትም ብዥታና ግርታ የበለጠ እየጠራ በመምጣት ላይ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጪም ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት ቢሆንም ከውስጥ ተቀምጠው፣ እንጀራዋን እየበሉ ተረካዛቸውን የሚያነሱባት ግን ፋታ የሚሰጧት አልሆኑም። እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና የተሰጣቸውን አደራ አራካሾች ሳናሰልስ ተግባራቸውን በመቃወምና ለምእመኑም ለማሳወቅ በመጣር ላይ እንገኛለን። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች የተንጠለጠሉበት ካስማ ደግሞ ሁለት ነው። አንደኛው ሙስና፣ ሁለተኛው ኑፋቄ። ደጀ ሰላምም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሰፈነውን ሙስና ትቃወማለች፣ ሰርገው የገቡትን መናፍቃን እና የሚዘሩትን ኑፋቄ ትጸየፋለች። ምን ማለታችን እንደሆነ እናብራራው።


በየትኛውም መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ውስጥ ይብዛም ይነሥም ሙስና መኖሩ ይታወቃል። በአገራችን ደረጃ ከተመለከትነው በየደራጀው ሙስና እንዳለ በዚህም ምክንያት ከሥልጣናቸው የተባረሩ ሰዎች መኖራቸውን በመገናኛ ብዙሃን እንሰማለን፣ እንመለከታለን፣ እናነባለን። የሙስናው አየር ከነፈሰባቸው ተቋማት መካከል ደግሞ ግንባር ቀደምነቱን ሊይዝ የሚገባው የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ነው። ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ የጻፍን በመሆኑ አንመለስበትም። በጠቅላላ ለማስቀመጥ ግን ያለ አግባብ በሥልጣን በመባለግ፣ እጅ መንሻ ወይም ጉቦ በመቀበል፣ ከምእመናን የተሰበሰውን ገንዘብ እና ቁሳቁስ ለግል ጥቅም በማዋል፣ የትኛውንም ጉዳይ ለማስፈጸምም ሆነ ተመሳሳይ ተግባር ለማከናወን ጉቦን እንደ መፍትሔ መጠቀም እጅግ በጣም ሰልጥኗል። ይህ ብልሹ አሠራር በጊዜው እንዳይገታ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ፍላጎትም ችሎታም የለውም።

ሙስና በምድራዊ ሕግ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊውም ሕግ የተጠላ እና የተከለከለ ቢሆንም ሃይማኖታዊውን ሕግ የሚያውቁ እና የመንፈስ ልዕልና ኖሯቸው ሌላውን በትምህርታቸው ተግሳጽ፣ በቃላቸው ምክር ሊያቀኑ የሚገባቸው ሰዎች እና ይህንን ልታደርግ ይገባት የነበረች ተቋም የዚህ መፈብረኪያ ስትሆን በሽታው መድሃኒት ሊያገኝ አይችልም። የበሽታ ማጥፊያ መድሃኒቶችን እንደሚላመዱ የበሽታ አምጪ ሕዋሶች፣ ቃለ እግዚአብሔር እና ኢትዮጵያዊ ሥነ ምግባርን በመጣስና በመደምሰስ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ በማጧጧፍ ላይ ናቸው።

ሠራተኛ መበደል፣ ንብረት ማባከን፣ ጉቦ መቀበል በዚህም ደግሞ የራስን ንብረት ማከማቸት ለካህን እና ለክህነት የማይገባ ድርጊት መፈጸም የአደባባይ ምሥጢር ሆኗል። ይህም ከርዕሰ ቤተ ክርስቲያኑ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ የሚታወቅ ቢሆንም እርሳቸውም የችግሩ አካል በመሆን ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ውድቀት አፋፍ ከመግፋት ውጪ ራሳቸውም ድርጊቱን ተጸይፈው ሌላውን ሊወቅሱ አልቻሉም። በዙሪያቸው በሰበሰቡት የቤተ ዘመድ ጉባኤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስነቅፉ እና ሲያዋርዱ ዓመታት አስቆጥረዋል። አሁንም ቀጥለዋል።

ይህም ሳያንስ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን በተሐድሶ የኑፋቄ ትምህርት ለማበላሸት ለሚፈልጉ ሰዎች ነገሮችን በማመቻቸት ችግሩን የበለጠ አስፈሪና አስቸጋሪ አድርገውታል። ገንዘብ ቢዘረፍ በገዘንዘብ ይተካል። ንብረት ቢወድም በንብረት ይካካሳል። እምነት ከተበላሸ ግን በምን ይስተካከላል?

ኢትዮጵያ ሕብረ-እምነት ያላት አገር መሆኗን እናምናለን። ኢትዮጵያ የአንድ እምነት ብቻ የሚል ጅል አስተሳሰብ የለንም። ሁሉም የየራሱን እምነት አክብሮ እስከኖረ ድረስ አንድ ሰው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት የተለየ አስተሳሰብ ስላራመደ ችግር ይገጥመው ዘንድ አንመኝም።፡ ለዚህም ነው ጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች በጅማ አካባቢ በፕሮቴስታንቶች ላይ ያደረሱትን አደጋ አምርረን የተቃወምነው። ነገ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ተመሳሳይ ችግር ቢደቀን አብረናቸው ከመቃወም ወደ ኋላ አንልም። ነገር ግን የሌላ እምነት፣ ቡድን እና ግለሰብ በእምነት መፈጸሚያ ቦታችን እና በመዋቅራችን በድብቅ ሰርጎ በመግባት የሚፈጽመውን ተንኮል አጥብቀን እንቃወማለን። ተሐድሷውያን ፍፁም የለየላቸው ፕሮቴስታንቶች ሆነው ሳለ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚፈጽሙትን ደባ አምርረን የምንቃወመው ያለ እምነታቸው እና ያለ ቤታቸው በመግባታቸው ነው። ጦማሪው ዳንኤል ክብረት በአንድ ጽሑፉ እንዳለው “ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው?” በቤታችንስ ማን አስገባቸው? እስካልወጡ ድረስም እንቅልፍ አይኖረንም እንላቸዋለን። ይህ ደግሞ የደጀ ሰላም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን አቋም እና እምነት ነው።

ቤተ ክርስቲያናችንን ፈተና የሆኗት እነዚህ ሁለት ቡድኖች (ሙሰኞች እና ተሐድሶዎች) ዓላማቸውን ለማስፈጸም የጋራ ግንባር በመፍጠር እንደሚሠሩ ከዕለት ዕለት ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ግልጽ ሆነ ያልነው ለእኛ ሳይሆን የችግሩን መኖር ይጠራጠሩ ለነበሩ አካላት ነው። ሙሰኞቹ ገንዘብ እስካገኙ ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመሸጥ አይመለሱም። ተሐድሶዎቹ ደግሞ ዓላማቸውን የሚያስፈጽምላቸው ሰው እስካገኙ ድረስ ገንዘብ ለመስጠት እና ለመተባበር ወደኋላ አይሉም። ለዚህም ነው ትናንት የተጣሉ ይመስሉን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ግን እጅግ የሚዋደዱ መስለው በሕብረት ቆመው የምናያቸው። እነዚህ ሁለት ቡድኖች ደግሞ ዓላማቸውን የሚያሰናክልባቸው የመሰላቸውን ማንኛውንም አካል ከማጥፋት ወደኋላ አይሉም። አላሉምም። ሁለቱም ወገኖች ዓላማቸውን ለማስፈጸሚያነት፣ የሚቃወማቸውን ለማጥቂያነት ለመጠቀም የሚፈልጉት መንግሥትን እና ያለውን አስተዳደራዊ መዋቅሩን ነው። መንግሥት ለእነዚህ ወገኖች በመጠቀሚያነት ይውላል የሚል እምነት ባይኖረንም ሙከራቸው ግን እንዳለ እርግጠኞች ነን። ይህ ደግሞ ጥንትም የነበረ እንጂ አዲስ የመጣ ዘዴ አይደለም።

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን አይሁድ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከከሰሱባቸው ክሶች መካከል አንደኛው ከሮማውያን ገዢዎቻቸው ጋር ለማጋጨት የተጠቀሙበት “ራሱን የአይሁድ ንጉሥ  ነኝ ይላል” የሚለው ፖለቲካዊ ክስ ነው። ንጉሥ በንጉስነቱ፣ ወንድ ልጅ በሚስቱ፣ እግዚአብሔር በመለኮቱ ሲመጡበት … እንደሚባለው ጌታን ከሮም ቤተ መንግሥት ጋር በማጋጨት ሊያሰቅሉት ሞክረዋል። ይህ በጌታችን ላይ የተደረገው ነገር በየዘመኑ በተለያየ መልክና ቅርጽ ሲፈጸም ኖሯል።

ሌላውን ትተን በተለያየ ዘመን በአገራችን እንኳን የነበረውን ሁኔታ ብንመለከት እበላ ባይ ደባትር በነገረ ሰሪነት ወደ ነገሥታቱ በመቅረብ ንፁሐን እና ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ላይ አደጋ ሲያደርሱ ኖረዋል። “እገሌ እና እገሌ በሥልጣንህ መጥተውብሃል” በሚለው ክፉ ወሬያቸው የብዙዎችን ደም አስፈስሰዋል። ብዙዎችንም በግዞት እንዲጣሉ፣ በእግር ብረት እንዲታሰሩ፣ በብቸኝነት እንዲንከራተቱ፣ አገር ጥለው እንዲሰደዱ አስደርገዋል። ለአብነት የደብረ ሊባኖሱን ቅዱሱን የአባ ፊሊጶስን ግዞት እና ግርፋት፣ የጋስጫውን የአባ ጊዮርጊስን ግዞት፣ የነአባ በጸሎተ ሚካኤልን መከራ መጥቀስ ይቻላል።

እነዚህ ነገሥታት በቅዱሳኑ ላይ መከራ ያጸኑባቸው በነገረ ሠሪዎቹ ተታለው እንጂ ራሳቸው ክፉዎች ነገሥታት ስለነበሩ አልነበረም። በሌሎች መልካም ተግባሮቻቸው የተመሰገኑ መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል። ይሁን እንጂ ቤተ ክህነቱን መጠጊያ የሚያደርጉ ተንኮለኞች በሚፈጽሟቸው በደሎች ብዙዎች የመከራው ቀንበር ይወድቅባቸዋል። በዚህ ዘመንም የኢሕአዴግ አባላት ነን፣ በመንግሥት ዘንድ ሞገስ አለን፣ ሥልጣን አለን፣ የአገር ልጅነት እና አምቻ ጋብቻ አለን የሚሉ ሰዎች ብዙ መልካም ሰዎች ላይ የመከራ ቀንበር በማስጫን ላይ ናቸው።

እነዚህ በክህነታቸው በቤተ ክህነት፣ በፓርቲ አባልነታቸው ከመንግሥት የተጠጉ ጥቅመኞች ቤተ ክርስቲያኒቱን እየጎዱ ነው፤ የመንግሥትንም ስም እያስጠፉ ነው። ራሳቸውን የመንግሥት  ብቸኛ ወገንና ልጅ፣ ሌላውን ባዳና የእንጀራ ልጅ አድርገው በማቅረብ በአንድ አገር ሁለት ዜጋ ያለ እያስመሰሉ ነው። የመንግሥት መንግሥትነቱ ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ነው። በሕግ ፊት ሁላችንም እኩል ነን። ይሁን እንጂ እነዚህ ሰዎች በሚፈጽሙት ወንጀል ተያቂ ባለመሆናቸው በብዙው ምእመን ዘንድ ከሕግ በላይ የሆኑ አስመስሏቸዋል።

በአገራችን ልማት እንዲመጣ እንመኛለን። አመጽን፣ ብጥብጥን፣ በእምነቶች መካከል ሊከሰት የሚችልን አለመቻቻል እንቃወማለን። ይህም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን ያለውን ሙስና እና ሰርጎ የገባ ተሐድሷዊ የመናፍቃን ተንኮልም እንቃወማለን። እነዚህን ሙሰኞች እና ተሐድሶዎች የምንቃወማቸው ባላቸው የፖለቲካ አቋም ሳይሆን በእምነታችን ላይ በሚፈጽሙት ወንጀል ነው። አጀንዳችን አንድ እና አንድ ነው፦ እነዚህን የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች መቃወም።

31 comments:

Desalew said...

good job! dejeselamawyan!!!. yeketlal gena!!!

Anonymous said...

Well said Deje Selam. Live by your words!

Anonymous said...

Tiru new Dejeselamawyan!!! Egnam kegonachihu nen alamachinim and ena and new Betewahido lemimeta kelid yelem!!!

Aregawi said...

EGZIABHER BETECHRSTIANACHN YITEBKILIN ENGAM AQAMACHN AND(1) NEW!

mebrud said...

በቤተክርስቲያን ዘይቤ፣ባማረ ቋንቋ የተከሸነና እጥር ምጥን ያለ ግልጽ መልዕክት።እግዚአብሔር ይስጥልን።

Anonymous said...

GOOD, GOOD. Let's stand together to fight corruption and "Tehadiso". The time is now. please make our action practical soon.

Anonymous said...

I am not convinced about this TEHADSO thing. Yene Gimet Segat Yalebachihu Yemeselgnal and you label people as TEHADSO. Tehadso is your SEGAT, i do not think it exit. If TEHADSO does exit we will know about it first-hand from the so called TEHADSOWOCH, because a believer has to witness his or her belief in one way or another.One very saddening thing you people are pushing people out of the church because of this labeling of yours, and i have seen many God fearing the children of the ortho church pushed out and end up in the protestant camp. The protestant church ofcourse welcome them with open arm. So I can`t help it i blame you for all of this
.

Anonymous said...

ደጀ ሰላም በርቱልን እግዚአብሔር ጥበቡን ይስጣችሁ፡፡ ላልሰሙ ላልተረዱና ላልገባቸው ወገኖችም መረጃ እናደርሳለን፡፡ መንገዱን ዘግቶብን ቆሟል መኪናው
ወይ አዲስ አልገዛን በሽታ የሌለው
ግፉን መቼ ይሆን መገላገያው
መድኃኔዓለም ሠላሙን ይስጠን፡፡

gammachiis said...

BEZZIHU KETTILU!!!!!

hiwot hailu said...

Selam le-enante yehune

God will helps us, one day every thing will get a solution.That is why he has been silent to teach them.Keep it up in Your work to show the activities happened in our religion to update us about sensitive issues.

ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች እንደምን ከረማችሁ አወ እውነት ነውቤተክርስቲያንን ከለላ አድርገው በውስጥም በውጭም ማለትም በሀገርውስጥም ከሀገር ውስጥም ባለችው ቤተክርስቲያናችን ላይ እያደረጉትያለው አለሰፋሪ ሙስናና አስነዋሪ የሆነውን የክህደት ትምህርት መቸምቢሆን አሜንብለን የማንቀበል መሆናችንን በያለንበት ሆነን ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋህዶልጆች ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ማሳወቅና አስፈላጊም ከሆነ የሚጠበቅብን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁመሆን አለብን ወላዲተአምላክ አስራት ሀገሩዋን በምልጃዋ ታስብልን ለናንተም ቃለሂወት ታሰማልን አሜን

Anonymous said...

Well Said Dejeselam! Yes Let us just focus on the TEHADESOS and Corruption rather than fighting eac other. Let us work towards unity in the church and be model to our country unity and strength according to the teaching and doing of our holy fathers!
Good Job!

Anonymous said...

May God help your efforts to clean His house.

fikre said...

betam tiru genzabae naw gene yhen melikete lhulum ydrsale?

Anonymous said...

hasabu tsiru new bet meleyayetna menekakefu beza alamaw altawekem melkam yemiyasbew man endehone leyito lemawek techegern yebizu abatoch name tsefa hulum menafik tebale dehinaw manew ? sebakiw zemariw kedashu menkusew kahinu diyakonu miemenu hulum leba menafik duerye tebale minew dehina sew yelem malet new ?

Anonymous said...

well said....

Anonymous said...

selam lenante yehune,
Dear dejeselam first I thank u for all the things ur doing in these time & for being here when everybody is on silence.

What I want to say is for all EOTC christians is " what r we doing beside reading & wrighting a comment?" " did we realy care for what is going on?"

what realy need to do is take action on is let everybody leasen our voice " not on only this site".
As all u know the time for the Genetal meeting of the Sinodious is coming so, beside sitting & witing the answer lets go out and demonstrate our feeling, let them know what we r."

Let everybody know that we r a generation of strong christians that realy care for their "EOTC Dogma, Kenona .. ."

Please Dejeselamwian think about it we have to let them know we r morethan a person that is sit infront of a pc and chat about it.

This the time we all need to take action. unless we do something in this May meeting I don't think anything is going to change.

"Ebakachu erasachen lay endiwetu atadrgachew"

Ante said...

Let us stand together with the help of God.Pray pray pray.......

woldermariam said...

betam tru asab new mengstem yehenen guday betegbiw hunet limleketew yigebal

Dn Haile Michael said...

In the name of the Father the Son the Holy Spirit One God Amen.
Dear all ,
You can bypass the blocking by writing 1)https://www.dejeselam.org
instead of http://www.dejeselam.org
2) just first write https://www.ninjacloak.org
then on the page write www.dejeselam.org
The "tehadisos " have understood that the laity are becoming aware of them & are changing their strategy to stay in the church. One strategy is seeming more responsible than any other for church issue. Let me cite one guy from Debre tsege Saint Urael Church of Addis Ababa . His name is "Memhir" Fitsum.Yesterday he preached in the morning after the Mass , his preaching was unrelated to what is read from Gospel & Psalm.He also preached in the after noon program of Sunday school.
One day he advocated the EBS television to the laity by saying"It is the enemy who is talking against us , there is no problem , follow the EBS program."
Dear the children of the church , let us work hard first informing their evil deeds to the laity. Then taking action against them will be easy.
Let us also work to making peace demonstration against Patriarch Pawlos's deed. "Like Kehinat" Getachew Doni is not our church member. Let him go out & do his business with "Mekaneyesus's".This is our church.We have right to know what is being done ,who is who ,.......Let us directly participate in church issues.
May God help us.
Your Brother in Christ
Diacon Haile Mechael
from Debre Tsege Saint Urael church Sunday School.

tewye said...

"እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም" (1ቆሮንቶስ 2፥12)
dejeselamawian go forth even up to death,we are with u in every ocassion(time)
we love ethoc dogma and kenona
so please go forth especialy selercting and awaring people about tehadso awyann

tewye said...

ወይዜኒ መኑ ተስፉየ(ተስፉየ ማነው) መዝ ፫፰፤፮-----አልፋና ኦሜጋ የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ,ድንግልን ተስፋ ያድረገ ለዘላለም ይኖራል ኣይሞትም
ተስፋውም ዘላለማዊ ነው
ende keledubn ykeledbachewal tehadso awyan motachin bet crstian west yhun wegenoch
bechibchabo yalefew alfaul zera gin mekom alebet,zemariachin kidusann mawedes yhun,yerasachewn taric bemot mekabr west yaskemtut
betam yebedelunn sewech bzerezrachew des balegn sewech yawkut zend
DINGLE MARIAM HOY EBAKSH ETHIOPIAN BARKE,BEMOTE ENA BEHIWET MEKAKEL SALEN DRESHILEN(YETESFACHIN MEGEMERIA ENA MECHERESHA ANCH NESH)
BE EGIZIABHAIR ENA BEKIDUSAN ANDHUM BE ENATU YEMEDEREGU BEDELOCH YKUMU,
EBAKACHIHU TEHADSO AWYAN TEWN 5 AMET YAHIL BESNE MELEKOT TEMRACHIHU YE ARYOSIN,NSTROSN AND MEKDENYOSN BESTAWECH ATBETNUBN

tewye said...

ተስፋ መቁረጥ ነግሶ
ቢበዛም አበሳ
አንተ ባለህበት
ይታዘዛል ባህሩ
ነውጡም ያጣል ኃይሉን
ጸጥ ይላል ማእበሉ
ደጀ ሰላም በርቱልን እግዚአብሔር ጥበቡን ይስጣችሁ፡፡ ላልሰሙ ላልተረዱና ላልገባቸው ወገኖችም መረጃ እናደርሳለን፡፡ መንገዱን ዘግቶብን ቆሟል መኪናው
ወይ አዲስ አልገዛን በሽታ የሌለው
ግፉን መቼ ይሆን መገላገያው
መድኃኔዓለም ሠላሙን ይስጠን፡፡
ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች እንደምን ከረማችሁ አወ እውነት ነውቤተክርስቲያንን ከለላ አድርገው በውስጥም በውጭም ማለትም በሀገርውስጥም ከሀገር ውስጥም ባለችው ቤተክርስቲያናችን ላይ እያደረጉትያለው አለሰፋሪ ሙስናና አስነዋሪ የሆነውን የክህደት ትምህርት መቸምቢሆን አሜንብለን የማንቀበል መሆናችንን በያለንበት ሆነን ሁላችንም የኦርቶዶክስ ተዋህዶልጆች ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ማሳወቅና አስፈላጊም ከሆነ የሚጠበቅብን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁመሆን አለብን ወላዲተአምላክ አስራት ሀገሩዋን በምልጃዋ ታስብልን ለናንተም ቃለሂወት ታሰማልን አሜን

ባልቻ said...

የአሳ ግማቱ .....ተብሏል ወሬ ይብቃ አሁን ሁልሽም ተዘጋጂ የወረቀት አንበሳ ሁሉ .....bloger ( ጦማሪ ) ምናምን ተብየዎችም ወሬ ይብቃ !

Alfo Ayichew said...

የአንጋፋው ይድነቃቸው አባት ነጋድራስ ተሰማ እሽቴ ከአጼ ሃይለ ስላሴ እጅ መኪና ይሽለማሉ፡: ከታች ያሉት ታዲያ ድክም ያለችዋን ይሰጧቸዋል። በዚህ የተበሳጩት ነጋድራስ ቀን ሲጠብቁ አንድ ቀን ንጉሱ ወደ ደብረ ዘይት መሄጃ ሰዓታቸውን ጠብቀው መኪናቸውን ይይዙና ከፊት ይቀድማሉ። ትንሽ እንደሄዱ የንጉሱ መኪና ብቅ አለ። የዚህን ጊዜ ቶሎ ብለው መኪናው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ውረዱና መኪናውን ግፉ ይሏቸዋል። እሳቸው ከውስጥ ፍሬኑን ይዘውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የንጉሱ መኪና ደረሰ። የንጉሱ ባለሟሎች እና ወታደሮች ወረዱ። መኪናዋ አትንቀሳቀስም። የዚህን ጊዜ ነጋድራስ ጮክ ብለው ግፉ ግፉ ግፉ ገና ነው። ንጉሱ ማነው ምንድነው በማለት ሲጠይቁ ነጋድራስ እንደሆኑና ግፉ ገና ነው እያሉ መሆኑን ነገሯቸው። ንጉሱ ነገሩ ገብቷቸው ይህን አሮጌ መኪና ሰጥታችሁ ነው የምታሰድቡኝ በሉ ቀይሩለት ብለው አዲስ ተሰጣቸው።
መንገዱን ዘግቶብን ቆሟል መኪናው
ወይ አዲስ አልገዛን በሽታ የሌለው
ግፉ በዝቶብናል መፈታተኛው
አንድ እንሁንበት እናስወግደው

Anonymous said...

በቤተክርስቲያን ዘይቤ፣ባማረ ቋንቋ የተከሸነና እጥር ምጥን ያለ ግልጽ መልዕክት።እግዚአብሔር ይስጥልን

Anonymous said...

ሙሰኞች እና ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያናችንን ፈተና የሆኗት እስካልወጡ እንቅልፍ አይኖረንም እንላቸዋለን!!!
NEVER AND NEVER WE WILL NOT GO TO SLEEP.

Anonymous said...

" ለዓይኖቼም መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ፥ ለጕንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም፥" psalm.131
Before the enemy of our church destroyed and clear from inside to out side!!!
"Some trust in chariots, and some in horses: but we will remember the name of the LORD our God
they are brought down and fallen: we are risen and stand upright." psalm 19.
the God's of our fathers be with us.amen

Anonymous said...

10፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው። ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል? ቁም፤

11፤ እስራኤል(ethiopians) በድሎአል፤ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።

12፤ ስለዚህም የእስራኤል ልጆች(the chidern of ethiopians) በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም፤ የተረገሙ ስለ ሆኑ በጠላቶቻቸው ፊት ይሸሻሉ፤ እርም የሆነውንም ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
13፤ ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው። እስራኤል ሆይ፥ እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም ብሎ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና እስከ ነገ ተቀደሱ መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ. Our holly God ! please do not destroy us just the sake of Our Holly fathers!!!

Anonymous said...

Dear Dejeselamoch and all,
It is true the Church is being stretched by the Tehadeso in one side and by the corrupted on the other side to tear and destroy her. These Yehuda and Areyos,the children of Satan/Devil, even if they try the max. force they have had, never can they demolish our Church/Christians. B/c the Lord Jesus Christ is the saver of us.However, some innocent Christians might be deeply hurt, even being converted and join the Protestsnts' camp. During such hard time we all must remember our church and our fathers' history, who as a result of their blood, the church passed many generation and reached today. So, we have the responsibility to protect our religion (Dogma & canon) and pass to the next generation as we received from our fore fathers. Let the Almighty God generosity and mercy as well as St. Mary's intersession be with all of us, Amen.

asbet dngl said...

በቤተክርስቲያን ዘይቤ፣ባማረ ቋንቋ የተከሸነና እጥር ምጥን ያለ ግልጽ መልዕክት።እግዚአብሔር ይስጥልንea

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)