May 24, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ከሰዓት በኋላ ውይይት አርእስተ ዜና

 (ደጀ ሰላም፤ ሜይ 23/2011):-
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለውን ችግር የሚያጣራ ኮሚቴ ሠየመ፤
  • ኮሚቴው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳትን እና አራት ሊቃውንትን አካቷል፤  የውይይቱ አካሄድ እና የኮሚቴው አባላት ምርጫ መጠነኛ ድራማን አስተናግዷል፡፡
  • የኮሚቴው መቋቋም እና ለሥራው የተሰጠው ጊዜ በአዎንታዊነት የታየ ቢሆንም የሲኖዶሱ አባላት በስብሰባው አካሄድ መሰላቸታቸውን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡
  • ፓትርያሪኩ ከቀትር በኋላ (ከ8፡00  - 9፡00) የሕዳሴ ግድቡን መግለጫ ለመስጠት ታዳሚዎችን በጠሩበት ሁኔታ ሲኖዶሱ አጀንዳዎቹን ባለማጠናቀቁ ስብሰባውን እርሳቸው በሌሉበትም ቢሆን እንደሚቀጥል በመወሰኑ የተበሳጩት አቡነ ጳውሎስ በከሰዓት በኋላ የጉባኤው ውሎ በጌታቸው ዶኒ መነሣት ላይ ከቀትር በፊት የተላለፈውን ውሳኔ ዳግመኛ ወደ ኋላ ለመመለስ ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ተዘግቧል፤ ከፊሎቹ የሲኖዶሱ አባላት ያሳለፉትን ውሳኔ በማጽናት ጉባኤው እዚያው ላይ አብቅቶ እንዲነሣ ሲጠይቁ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በስብሰባው ላይ ተገኝተው እንዲታዘቡ ሐሳብ በማቅረብ ስብሰባው እንዳይበተን እና አጀንዳው በተፈለገው መልክ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ተሰምቷል፡፡፡
  • ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቀጣዩ ቋሚ ሲኖዶስ አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
  • የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ለመዘዋወር መጠየቃቸው ተሰምቷል፤ በጥያቄያቸው መነሻ ሐሳብና ምክንያት ላይ ጥርጣሬ ከገባቸው ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሣባቸው ይጠበቃል፡፡
  • ፓትርያሪኩ ልዩ ልዩ በሚል ርእስ ባስያዙት አጀንዳ ውስጥ በምልአተ ጉባኤው ሳይነሣ የታለፈውን የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ዳግመኛ እንዳያነሡ እየተሰጋ ነው፡፡
  • በመጪው ዓርብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  ግንባታ በቢልዮን የሚቆጠር ብር እንደምታበረክት ተመልክቷል፤ አስተዋፅኦዋቸውን ያላሳወቁ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን፣ አህጉረ ስብከት እና ድርጅቶች በሁለት ቀን ውስጥ እንዲያጠናቀቁ ታዝዘዋል፤ ከወለድ ነጻ የቦንድ ግዥ ባሻገር የወር ደመወዛቸውን ከሚሰጡ የአ/አ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከእያንዳንዳቸው በአማካይ ከብር መቶ ሺሕ ያላነሰ ገቢ ቢገኝም አስተዋፅኦው በጅምላ ውሳኔ እየተሰበሰበ ያለበት ሁኔታ የችግረኛውን ጓዳ ያላገነዘበ መሆኑ ቅሬታ እየቀረበበት ነው፡፡
  • ቅዱስ ሲኖዶስ ዝውውር የጠየቁ ሊቃነ ጳጳሳትን ምደባ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አስተዋፅኦን እና በልዩ ልዩ ርእስ በተያዙ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ካሳለፈ በኋላ  የርክበ ካህናት ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል፡፡
ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን!!!!!!!!!!!!!!!

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)