May 31, 2011

እውን ‹‹ተሐድሶ›› የለምን?

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

(በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ/ hibretyes@yahoo.com):- ሰሞኑን በተደጋጋሚ ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› የሚል ንግግር በመስማቴ ይህንን አጭር ማሳሰቢያ ለመጻፍ ተነሳሣው፡፡ በእርግጥ ንግግሩን ቀደም ሲልም ሰምቼው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን መደጋገሙ ሲበዛ በተለይም ግምት የሰጠዋቸው ሰዎች ነገሩን ተቀብለዉት ስመለከት ለካ የሚናቅ ሐሰት የለም አሰኘኝ!

አባ ሰረቀ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፤ ተሐድሶን መቃወምን ተቃውመዋል

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 31/2011)፦ አባ ሰረቀ የተባሉት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሐላፊ ዛሬ ይሰጡታል ተብሎ በሚጠበቀውና ለደጀ ሰላም በደረሰው ጽሑፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ “ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና በሚጻረር መልኩ በአገልጋይና በተገልጋይ መካከል ለዘመናት የቆየውን ጤናማ ግንኙነት በሚያሻክር አኳኋን አለስልጣኑ በመግባት የሚተገብረው ዐዋጅ ነው” አሉ።

May 29, 2011

(ሰበር ዜና) ብፁዕ አቡነ በርናባስ አረፉ

 • የብፁዕ አቡነ በርናባስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነገ ይፈጸማል
 •  "የትምህርት መጨረሻው መልካም ሥራ ነው፡፡" (ብፁዕ አቡነ በርናባስ)
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 29/2011)፦  ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2001 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ግድም በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ያረፉት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ሥርዐተ ቀብር ነገ ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ረፋድ ላይ ለበርካታ ዐሥርት ዓመታት ባገለገሉበት በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ይፈጸማል፡፡ 

ግንቦት 16 ቀን ከተፈጸመው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ ግንቦት 19 ቀን በሀገረ ስብከታቸው መኪና ወደ ባሕር ዳር ያመሩት ብፁዕነታቸው ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲደርሱ ድካም እንደሚሰማቸው በመግለጽ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና አድረው በበነጋው ጉዟቸውን ቀጥለው እንደ ነበር ተገልጧል፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ብፁዕነታቸው በባሕር ዳር መንበረ ጵጵስናቸው ቅዳሜ ግንቦት 20፣ ከቀኑ 8፡00 ላይ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ላይ ማረፋቸውን የስፍራው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው የሰነበተ ሕማም እንደሌለባቸው፣ ግንቦት 16 ቀን የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የመጨረሻ ቀን ውሎ ‹‹ሆዴን አሞኛል›› በማለታቸው ሳይሳተፉ መቅረታቸው ተጠቁሟል፡፡ ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን ወደ ሕክምና የተወሰዱት ብፁዕነታቸው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈራል ተጽፎላቸው የነበረ ቢሆንም ‹‹ግዴለም፤ እዚያው ቤቴ ውሰዱኝ፤ ባሕርዳር ስደርስ እታከመዋለሁ›› በማለታቸው መንገድ መግባታቸውን እኒሁ ምንጮች  ያስረዳሉ፡፡ ብፁዕነታቸውን በመንበረ ጵጵስናቸው ተቀብለው ያሳረፏቸው የምሥራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ‹‹አልለዮትም›› ብለው ብፁዕነታቸውን ይዘው ባሕርዳር ድረስ መጓዛቸው ተመልክቷል፡፡ የብፁዕ አቡነ በርናባስ ዕረፍት እንደተሰማ የክልሉ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከተወሰኑ የካቢኔ አባሎቻቸው ጋራ እሑድ ጠዋት በመገኘት ሐዘናቸውን መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡
ለቀብሩ ሥነ ሥርዐት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ከአምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ ዛሬ ተሲዓት በኋላ ወደ ባሕር ዳር አምርተዋል፡፡ በባሕርዳር አየር ማረፊያ ‹‹ከ30 በላይ በሆኑ መኪኖች አቀባበል ተደርጎላቸዋል››ም ተብሏል፡፡ 

በየዓመቱ ጥቅምት ወር በሚካሄደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አህጉረ ስብከታቸው ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚያደርገው ፈሰስ እና የራስ አገዝ ልማት ቀደምት በማድረግ የሚታወቁት ብፁዕነታቸው፣ ከግንቦት 10 - 16 ቀን 2003 ዓ.ም በተካሄደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ያለልምዳቸው ባሰሙት ጠንካራ ንግግር የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በፓትርያርኩ አላግባብ በተሾመው ጌታቸው ዶኒ ላይ የተደረሰበት ውሳኔ እንዳይረጋ አቡነ ጳውሎስ የጉባኤውን አመራር ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ያደረጉበትን አካሄድ ተቃውመዋል፤ ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውኃ ወቀጣ ሆኗል፤ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር፣ ከግለሰብ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መወገን አይሻልም ወይ?››
በአህጉረ ስብከታቸው በቆሙበት ዐውደ ምሕረት ሁሉ፣ ‹‹የትምህርት መጨረሻው መልካም ሥራ ነው፤›› በሚለው ተደጋጋሚ ምክራቸውም ይታወሳሉ - ብፁዕ አቡነ በርናባስ፡፡

ጥቅምት 18 ቀን 1983 ዓ.ም በአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አንብሮተ እድ ከተሾሙት አራት ኤጶስ ቆጶሳት(አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልስ፣ አቡነ መልከ ጼዴቅ) አንዱ የነበሩት ብፁዕነታቸው የዜማ እና የመጽሐፍ ዐዋቂ መምህር ነበሩ፡፡ በሐረር መድኃኔዓለም፣ በርእሰ አድባራት ቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል እና በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመሳሰሉት ታላላቅ አብያተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡  በማዕርገ ጵጵስናም በመጀመሪያ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ በመቀጠልም የምሥራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በመጨረሻም እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው የመሩት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አምላካችን ለብፁዕ አባታችን ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቶ ከማኅበረ መላእክት፣ ከማኅበረ ጻድቃን ይደምርልን፡፡ አሜን፡፡

May 25, 2011

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ
 • ዋና ዋና አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች አልተጠቀሱም፤ በዓባይ ግድብ ዙሪያ ያጠነጠነ መግለጫ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 25/2011)፦ ከግንቦት 10-16 2003 ዓ.ም የተካሔደው መደበኛ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን መግለጨው ቅ/ሲኖዶሱ የተወያየባቸውን እና ውሳኔ ያሳለፋቸውን ዋና ዋና ጉዳዮ ሳያነሳ አልፏቸዋል።

May 24, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ሰባተኛና የመጨረሻ ቀን ውሎ ርእሰ ጉዳዮች

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ
 (ደጀ ሰላም፤ ሜይ 24/2011)፦  
 •  ከግንቦት 10 - 16 ቀን 2003 ዓ.ም ለሰባት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ዛሬ ቀትር ላይ በማጠናቀቅ ከሰዓት በኋላ የዋና ጸሐፊውን ቃለ ጉባኤ በንባብ በማዳመጥ ተፈራርሟል፡፡ 
 • ፓትርያርኩ ነገ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት ሦስት ላይ ጋዜጣዊ ጉባኤ ጠርተዋል፡፡ ከጋዜጣዊ ጉባኤው ጋራ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተዋፅኦ በሚገለጽበት መድረክ ወረብ በአጫብር እና ቆሜ የያሬዳዊ ዜማ ይትበሃሎች ይቀርባል፤ ሊቃውንቱ ስለ ዐባይ እና ስለ ሕዳሴው ግድብ ቅኔ ያበረክታሉ፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመመሪያ እና የድርጅት ሐላፊዎች፣ የአ/አ ሀ/ስብከት ሠራተኞች፣ የአ/አ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ጸሐፊዎች የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ከሰዓት በኋላ ውይይት አርእስተ ዜና

 (ደጀ ሰላም፤ ሜይ 23/2011):-
 • ቅዱስ ሲኖዶስ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለውን ችግር የሚያጣራ ኮሚቴ ሠየመ፤
 • ኮሚቴው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳትን እና አራት ሊቃውንትን አካቷል፤  የውይይቱ አካሄድ እና የኮሚቴው አባላት ምርጫ መጠነኛ ድራማን አስተናግዷል፡፡
 • የኮሚቴው መቋቋም እና ለሥራው የተሰጠው ጊዜ በአዎንታዊነት የታየ ቢሆንም የሲኖዶሱ አባላት በስብሰባው አካሄድ መሰላቸታቸውን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡
 • ፓትርያሪኩ ከቀትር በኋላ (ከ8፡00  - 9፡00) የሕዳሴ ግድቡን መግለጫ ለመስጠት ታዳሚዎችን በጠሩበት ሁኔታ ሲኖዶሱ አጀንዳዎቹን ባለማጠናቀቁ ስብሰባውን እርሳቸው በሌሉበትም ቢሆን እንደሚቀጥል በመወሰኑ የተበሳጩት አቡነ ጳውሎስ በከሰዓት በኋላ የጉባኤው ውሎ በጌታቸው ዶኒ መነሣት ላይ ከቀትር በፊት የተላለፈውን ውሳኔ ዳግመኛ ወደ ኋላ ለመመለስ ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ተዘግቧል፤ ከፊሎቹ የሲኖዶሱ አባላት ያሳለፉትን ውሳኔ በማጽናት ጉባኤው እዚያው ላይ አብቅቶ እንዲነሣ ሲጠይቁ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በስብሰባው ላይ ተገኝተው እንዲታዘቡ ሐሳብ በማቅረብ ስብሰባው እንዳይበተን እና አጀንዳው በተፈለገው መልክ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ተሰምቷል፡፡፡
 • ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቀጣዩ ቋሚ ሲኖዶስ አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
 • የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ለመዘዋወር መጠየቃቸው ተሰምቷል፤ በጥያቄያቸው መነሻ ሐሳብና ምክንያት ላይ ጥርጣሬ ከገባቸው ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሣባቸው ይጠበቃል፡፡
 • ፓትርያሪኩ ልዩ ልዩ በሚል ርእስ ባስያዙት አጀንዳ ውስጥ በምልአተ ጉባኤው ሳይነሣ የታለፈውን የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ዳግመኛ እንዳያነሡ እየተሰጋ ነው፡፡
 • በመጪው ዓርብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  ግንባታ በቢልዮን የሚቆጠር ብር እንደምታበረክት ተመልክቷል፤ አስተዋፅኦዋቸውን ያላሳወቁ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን፣ አህጉረ ስብከት እና ድርጅቶች በሁለት ቀን ውስጥ እንዲያጠናቀቁ ታዝዘዋል፤ ከወለድ ነጻ የቦንድ ግዥ ባሻገር የወር ደመወዛቸውን ከሚሰጡ የአ/አ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከእያንዳንዳቸው በአማካይ ከብር መቶ ሺሕ ያላነሰ ገቢ ቢገኝም አስተዋፅኦው በጅምላ ውሳኔ እየተሰበሰበ ያለበት ሁኔታ የችግረኛውን ጓዳ ያላገነዘበ መሆኑ ቅሬታ እየቀረበበት ነው፡፡
 • ቅዱስ ሲኖዶስ ዝውውር የጠየቁ ሊቃነ ጳጳሳትን ምደባ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አስተዋፅኦን እና በልዩ ልዩ ርእስ በተያዙ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ካሳለፈ በኋላ  የርክበ ካህናት ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል፡፡
ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን!!!!!!!!!!!!!!!

May 23, 2011

አርእስተ ሰበር ዜና:- የቅ/ሲኖዶስ 6ኛ ቀን ውሎ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 23/2011):-
 • ጌታቸው ዶኒ አላግባብ ከተሾመበት ሥልጣኑ ተወገደ የሐዋሳ ደ/ም/ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪም ተነሥተዋል፤  የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎችም በቀጣይ በሊቀ ጳጳሱ ውሳኔ  እንደሚነሡ ይጠበቃል
 • ‹‹ሹመቱ ከሕግ ውጭ ነው፤ ሕግ ተላልፈዋል፤ ሕግ መከበር አለበት፤ ቤተ ክርስቲያን በሕግ የምትመራ ናትና፤›› (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ)
 • ፓትርያሪኩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎችን፣ ጸሐፊዎችንና ጋዜጠኞችን በመጥራት ለመስጠት ያቀዱት መግለጫ በሲኖዶሱ አባላት ታገደ
 • የመግለጫው ዋነኛ ዓላማ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዋፅኦ ለመግለጽ ነው ቢባልም የምልአተ ጉባኤው አባላት ባልወሰኑበት ሁኔታ ‹‹የሲኖዶሱን መጠናቀቅ በማስመልከት ነበር›› የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
 •  ምልአተ ጉባኤው ከቀትር በኋላ በሰንበት ት/ቤቶች እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ባለው ችግር ላይ መነጋገሩን ቀጥሏል::

May 22, 2011

(ሰበር ዜና) - ጌታቸው ዶኒ ከሥራ አስኪያጅነቱ እንዲባረር ብዙኀኑ የሲኖዱሱ አባላት የደረሱበት ስምምነት በፓትርያሪኩ ተቃውሞ ገጠመው፤ የቅ/ሲኖዶስ 5ኛ ቀን ውሎ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ
 • የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪም ከሐላፊነታቸው ይነሣሉ
 • ፓትርያሪኩ እና አቡነ ጎርጎርዮስ በውሳኔው ባለመስማማት ጌታቸው ዶኒ ‹‹መናፍቅ›› መባሉን ተቃውመዋል
 • ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውጤት የሌለው ውኃ ወቀጣ ሆኗል፤ ከግለሰብ ይልቅ ለእግዚአብሔር እና ለቤተ ክርስቲያኑ መወገን አይሻልም ወይ;››(ብፁዕ አቡነ በርናባስ)
 • ‹‹እንዴት በተሐድሶ/ኑፋቄ መኖርን በተመለከተ ድርድር ውስጥ ይገባል;››(ብፁዕ አቡነ ኤልያስ)
 • የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በመላ ወይም በከፊል ወደ ሐዋሳ ወርደው፣ ጉባኤ ሠርተው ያዘነውን ምእመን ያጽናናሉ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 22/2011)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ ግንቦት 14፣ 2003 ዓ.ም አምስተኛ ቀን የዕለተ ሰንበት ውሎው በሲዳሞ ሀገረ ስብከትን የተከሠተውን ችግር አስመልክቶ በተያዘው አጀንዳ ዙሪያ የጋለ ክርክር የተሞላበትን ውይይት በማካሄድ ‹‹ሊቀ ካህናት›› ጌታቸው ዶኒ ያለአግባብ ከተሰጠው የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ እንዲባረር ወስኗል፡፡ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ‹‹በውሳኔው አላምንበትም›› ብለዋል፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ አቋም በልዩነት ተይዞ ጌታቸው ዶኒ ከሐላፊነቱ እንዲነሣ ምልአተ ጉባኤው ከቀትር በፊት የደረሰበትን ስምምነት አቡነ ጳውሎስ ከቀትር በኋላ በማፍረስ በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ተዘጋጅቶ በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹ስለማላምንበት አልፈርምም፤›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ በዚህ ሳቢያ ጉባኤው ወደ ቀጣዩ የሰንበት ት/ቤቶች እና የማኅበረ ቅዱሳን ግንኙነት አጀንዳ ከመሻገር ተገትቶ ከፓትርያሪኩ እና ሰልፋቸውን ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ካደረጉት አቡነ ጎርጎርዮስ ጋራ የጋለ ክርክር ሲያካሂድ አምሽቶ ማምሻውን ያለውጤት ተነሥቷል፡፡

የቅ/ሲኖዶስ አራተኛ ቀን ውሎ (ሪፖርታዥ)

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

 • ቅዱስ ሲኖዶስ ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመተግበሩ ተገለጸ፤ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልት ሳይነሣ ታለፈ
 • ዋነኛው ችግር በመምሪያው አሠራር ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት ነው፤
 • ሌሎች ያልተተገበሩ የሲኖዶሱ ውሳኔዎች “ወዘተርፈ እና ሌሎችም›› በሚል  ብቻ ከመወሳት በቀር በዝርዝር ቀርበው አለመገምገማቸው እያነጋገረ ነው፤
 • የሐዋሳው አጣሪ ኮሚቴ ጥናት እና የምእመናኑ አቤቱታ በሪፖርት ቀርቧል፤
 • በጨለማው ቡድን ኮሚሽን ተደርገው በስመ ‹ደኅንነት› የሚንቀሳቀሱ ጉልበተኞች የማዋከብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግር ጠንካራ አቋም ካላቸው ብፁዓን አባቶች ጋራ ግንኙነት ያላቸውን አገልጋዮች በስልክ ያስፈራራሉ፤ በአካል በመከታተል ያዋክባሉ፡፡ መንግሥት ዜጎች ለሃይማኖታቸው መጠበቅ ለመቆም ያላቸውን ሕገ መንግሥታዊ መብት ሊያስከብርላቸው ይገባል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 22/2011)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዳሜ ግንቦት 13፣ 2003 ዓ.ም አራተኛ ቀን ውሎው ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ በጥቅምት ምልአተ ጉባኤው ያስተላለፈው ውሳኔ በአግባቡ ተግባራዊ አለመሆኑን ገመገመ፤ ውሳኔው ተከብሮ እንዲሠራበት አሳስቧል፡፡

ያልተገባ ጥቅምን አማክለው የሚንቀሳቀሱ እና የቤተ ክርስቲያንን ዐውደ ምሕረት መነገጃ ያደረጉ ሕገ ወጥ ሰባክያን እና ዘማርያን ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔ ያሳለፈበትን የወርኀ ጥቅምቱን ቃለ ጉባኤ እና ቀደም ሲል የወጣውን የስብከተ ወንጌል ደንብ ምልአተ ጉባኤው በንባብ አድምጧል፡፡ የሕገ ወጥ ሰባክያንን እና ዘማርያንን ስምሪት ለመከላከል የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በሚያከናውነው ተግባር ላይ በፓትርያኩ ጽ/ቤት የሚደረገው አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የችግሩ ዋነኛ መንሥኤ መሆኑን ምልአተ ጉባኤው በደማቁ አሥምሮበታል፡፡

May 21, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ሦስተኛ ቀን ውሎ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 21/2011)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በትላንት ግንቦት 12 ቀን 2003 ዓ.ም ግማሽ ቀን ውሎው ልማትን በተመለከተ፣ በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በየደረጃው በሁሉም የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት እና የአስተዳደር መዋቅሮች ተፈጻሚ ስለሚሆንበት ሁኔታ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ከወጣለት መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በርካታ ቤቶች እና ሕንጻዎች ፍትሐዊ ባልሆነ አፈጻጸም ያለጨረታ ለግለሰቦች በመሰጠታቸው፣ ሠራተኞች ከደንቡ ውጭ በመቀጠራቸው እና በመዛወራቸው በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ እየተመራ እርምት እንዲደረገበት ውሳኔ ስለተላለፈበት የቤቶች እና ሕንጻዎች ድርጅት ጉዳይ መወያየቱ ተሰምቷል፡፡

ነፍስ ይማር (ርእሰ አንቀጽ)

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ            

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ 56 ዓመት ቁጥር 119፤ ሚያዝያ፣ 2003 ዓ.ም)፦ በአሁኑ ጊዜ የተከሠተውን የኑሮ ውድነት አስመልክቶ የኢ... መንግሥት ለመላው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ባደረገው የደመወዝ ማስተካከያ መሠረት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞችም ወጉ ደርሷቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ትልቁም፣ ትንሹም፤ የትላንቱም የዛሬውም፣ የሦስት ሰዓቱም የስድስት ሰዓቱም የዘጠኝ ሰዓቱም፣ ትጉሁም ሰነፉም እኩል የደመወዝ ማስተካከያ አግኝተው ከላይ እስከታች ረክተዋል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ተገፋም አልተገፋም ለጊዜው ዕድሜ ለኤ... መንግሥት ብለዋል፡፡ የደመወዝ ማስተካከያ ጥናቱን ላጸደቁት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ፣ ለወቅታዊው የቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና ለአጥኒው ክፍልም ምስጋናቸውን አልነፈጉም፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ ባለፈው ዕትሙ ጥቆማ ያደረገው ዜና ቤተ ክርስቲያንም እደግ ተመንደግ ብለዋል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)