April 12, 2011

ሰበር ዜና፦ ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶስን ለአስቸኳይ ጉባኤ እየጠሩ ነው፤ ብዙዎች አባቶች አይገኙም(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 11/2011)፦  ዓመታዊው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ከሚካሄድበት ከግንቦት ርክበ ካህናት አስቀድሞ አስቸኳይ የተባለ ጉባኤ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተጠራ መሆኑ ታውቋል።  አጠራሩ ተገቢነት የለውም በሚል አባቶች  ተቃውመዋል ተብሏል። የሐዋሳውን ውዝግብ ለመፍታት በሚል እየተጠራ ባለው በዚህ ጉባኤ የተያዘው የሐዋሳ ችግር ጉዳይ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚችል እየታወቀ እና እየተጠበቀ በአቋራጭ የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተጠራው በዚሁ አጋጣሚ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ነው።

እንደምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ ባለፉት ቀናት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በተጠሩ ስብሰባዎች ከስብሰባዎቹ ዓላማ ውጪ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ሰፊ ገለጻ ሲያደርጉ የሰነበቱት የአባ ሰረቀ ወ/ሳሙኤል ዓላማ እንዲሳካ እና ማኅበሩ ከአገልግሎቱ እንዲታቀብ ለማድረግ የታሰበ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ይህንን ዓላማቸውን ለማሳካት በአንዳንድ አካባቢዎች ለሚገኙ አባቶች በተላለፈ መልእክት “ማኅበረ ቅዱሳን አላሠራ አለን፣ እየበጠበጠን ነው የሚል ደብዳቤ ጻፉ” መባላቸው የታወቀ ሲሆን በርግጥም ይህ ደብዳቤ ተጽፎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከደረሰ ያንን መነሻ በማድረግ በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ አንድ ውሳኔ ለማሳለፍ የተፈለገ ይመስላል።

አባ ሰረቀ ወ/ሳሙኤል
ከነገ በስቲያ ረቡዕ ይደረጋል ተብሎ በተጠራው በዚህ ጉባኤ ላይ በሱባኤው እና በጥሪው አጭርነት ምክንያት ብዙዎቹ አባቶች ለመገኘት እንማይችሉ የታወቀ ሲሆን ምልዓተ ጉባዔ ሳይሞላ ሊካሄድ የሚችል ምን ዓይነት የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እንደሆነ ብዙዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው። ከዚህ ጉባኤ ጋር የተገናኙ ዝርዝር ጉዳዮችን እንደደረሰልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)