April 26, 2011

የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጅምር ከዳር ለማድረስ እንርዳ

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 25/2011)፦  ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጀመሯቸውን ፕሮጄክቶች ለመርዳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ የራት ግብዣ በአሜሪካ መዘጋጀቱን ይህንኑ በማስተባበር ላይ የሚገኝ አንድ ማኅበር አስታወቀ። “ዝክረ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ” የሚሰኘው ይኸው ማኅበር ዝግጅቱን ያስተዋወቀበትን ደብዳቤ ከዚህ በታች ያቀረብን ሲሆን እኛም በበኩላችን የእኒህን ታላቅ አባት ጅማሮዎች እውን በማድረግ ስማቸው ከመቃብር በላይ ይውል ዘንድ መርዳት አለብን ብለን እናምናለን። “መጥፎ ሥራ ላይ የተሰማሩትን መቃወም ብቻ ሳይሆን ደግ የሚሠሩትንም በመርዳት መበርታት አለብን” እንላለን። በተለይም በአሜሪካ የምትገኙ ክርስቲያኖች የተዘጋጀውን ካርድ በመግዛት፣ በቦታው መገኘት ባትችሉም እንኳን የሚገኙትን እና የሚሠሩትን ለማበረታታት ቲኬቱን በመግዛት የበኩላችሁን ማድረግ አለባችሁ። በሌሎች የዓለም ክፍሎች የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንም እንዲሁ። ዝርዝሩን ከዚህ በታች ተመልከቱ።
 +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
  
            ወዳጅ ሊቀ ጳጳስና ብዙ ይሠራሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው ትጉህ ሐዋርያ፣ አንደበተ ርቱዕ ሰባኪ፣ መላ ዘመናቸውን ከስብከተ ወንጌል ሳይለዩ ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ወንጌልን ተጫምተው፣ ወንጌልን ተሸክመውና ወንጌልን ተመርኩዘው በቅድስት ቤተክርስቲያን የኖሩ በእውነት ስለ እውነት እግዚአብሔርን ያገለገሉ ታላቅ አባት ነበሩ።

              በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከምባታ ሃድያ ጉራጌና ስልጢ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነት አብዝተው የታገሉ ፤ የሊቃነ ጳጳሳት የመንፈስ ኩራት ፤ የጀርባ አጥንትና የቤተክርስቲያን መስካሪ ኮኮብ አባት በይበልጥም ቤተክርስቲያን በልማት ራሷን እንድትችል እና ከልመና እንድትላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይተጉ ነበር። ከብዙ ሥራዎቻቸው መካከል አንዱና ዋነኛው የነበረው ለነገይቷ ቤተክርስቲያናችንና አገራችን መልካም ዜጋን ለማፍራት በማሰብ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሕፃናትን በማሰባሰብ ዘመናዊውንና መንፈሳዊውንም ትምህርት ማስተማር ነበር። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነና ብፁዕነታቸው ሕፃናቱ ያሰቡት ቦታ ሳይደርሱ በድንገት ዐረፍተ ዘመን ገታቸው።   

               እነዚህ የነገ የአገርና ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑ ሕፃናትም እንደ አባትና እናት እየተንከባከቡ የሚያሳድጓቸውን መንፈሳዊ አባት ማጣታቸው ለእነርሱ ጥልቅ ሃዘን እና የመንፈስ ስብራት ነበር። ስለዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት አረጋውያንና መነኮሳት ለከፍተኛ ችግር ሊጋለጡ እንደሚቸሉ በመንገዘብ በሀገር ቤትና በውጭ ሀገር ባሉ የብፁዕነታቸው የመንፈስ ልጆችና ምዕመናን አሳሳቢነት "ዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ" የሚባል መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር በስማቸው ተመስርቶ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ እየሠራ ይገኛል። 
ብፁዕነታቸው በሕይወታቸው የመጨረሻ ቀናት ከተነሡት ፎቶ
           በብፁዕነታቸው ዕረፍት መላው ሕዝበ ክርስቲያን አዝኗል፤ ሆኖም በሕይወተ ሥጋ  ቢለየኑም  በአኅጉረ ስብከታቸውና በምሑር ገዳመ ኢየሱስ ጀምረውት የነበሩትንና ያቀዱትን ሥራዎቻቸውን ለማገዝ፣ አሳዳጊ የሌላቸውን ሕፃናት በማሳደግ ፣ትምህርት ቤቶቻቸውን በማጠናከርና፣ ገዳሙን በመንከባከብ የቤተክርስቲያን ልጅነታችንን ለመወጣት በአንድነት እንድንነሣ በትህትና እንሳስባለን።  

          በመሆኑም የተከበራችሁ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እና መምህራን፣ የሰበካ ጉባዔ ወይም የቦርድ አስተዳደር አባላት፣ መንፈሳዊ የአገልግሎትና የጽዋ ማኅበራት፣ ዘማርያንና ዘማርያት፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት ምእመናን ና ምእመናት እና የተለያዩ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችና ባለሃብቶች እንዲሁም በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጉዳዩን አንገብጋቢነትና አሳሳቢነት በመረዳት አቅማችሁ የፈቀደውን የገንዘብ፣ የዕውቀትና የቁሳቁስ አስተዋጽዖ በማድረግ እንድትተባበሩ በትህትና እንጠይቃለን። ለምታደርጉልንም አስተዋጽዖ ከወዲሁ ምስጋናችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እናቀርባለን። 

       በመሆኑም በዋሽንግተን ዲ.. ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የፊታችን ዳግም ትንሣኤ ማለትም እሁድ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.(May 1st, 2011 )ከቀኑ ፲፪ ሰዓት(6 PM) ጀምሮ የእራት ምሽት የተዘጋጀ መሆኑን እየገለጽን የዚህን የእራት ምሽት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ዝግጅት ሊረዳ የሚችል ማንኛውንም እርዳታ እንዲያደርጉልን ትብብርዎን በሕፃናቱ ስም እየጠየቅን     ይህንንም ዝግጅት በኢንተርኔት (Live Broadcast U-stream ) እና በፌስ ቡክ  በቀጥታ የምናስተላልፍ መሆኑን እየገልጽን እርዳታችሁንም  በዚሁ አጋጣሚ online መለገሥ እንደምቻልም እያሳወቅን እግዚአብሔር ሥራዎን ይባርክልዎ ዘንድ  የዘወትር ጸሎታችን መሆኑን እንገልፃለን። 

ለበለጠ መረጃ በድረ ገጻችንን www.zamt.org እንዲሁም በስልክ ቁጥር 202-656-ZAMT (9268) ያገኙናል፡፡
 
                                          ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
              አቶ ግርማ ማሞ
                  Signed
የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ማኀበር ሰብሳቢቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ክንፈ ሚካኤል 
Signed  
የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Zikre Abune Melke Tsedek Account Information
Bank Name: Bank of America
Account Name: Zikre Abune Melke Tsedek
Account Number: 226004656247
Routing Number: 054001204
Bank Address: 915 Rhode Island Ave. NE.
Washington,
DC 20018

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ
ምሑር ገዳመ ኢየሱስ
የባንክ ሂሳብ ቁጥር 393
ወልቂጤ፤ ኢትዮጵያ
+++++++++++++++++++++++++++
አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ድጎማ ማድረጊያ ቅጽ
1. ሙሉ ስም _________________________
2. አድራሻ _________________________
_________________________
ስልክ ____________________
ኢ-ሜል _____________________
3. የአከፋፈል አይነት
 በቼክ ……………………………. Make your checks payable to ZAMT
 በባንክ ክፍያ……………………..የባንክ ሒሳብ ቁጥር (Account #) 226004656247
(Routing #) 054001204
 በኢንተርኔት……………………… Pay online ; www.zamt.org
For credit card payments fill out the “English Version of Contribution form”
4. የፕሮጀክት አይነት
 ለሕጻናት ማሳደጊያ
 ለመነኮሳት መርጃ
 ቋሚ ገቢ ማስፈጸሚያ
5. ክፍያውን የሚፈጽሙበት ጊዜ ና መጠን
 በወር $________
 በሦስት ወር $________
 `በስድስት ወር $________
 በአመት $________
 የአንድ ጊዜ ክፍያ $________
ለበለጠ መረጃ ፤ ስልክ ቁጥር= 202 -656 - ZAMT(9268) ኢ-ሜይል = info@zamt.org
ድረ ገጽ = www.zamt.org
Send your mails to:
Zikre Abune Melke Tsedek (ZAMT
3010 Earl Pl. NE
Washington DC 20018
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡
Note: ZAMT will provide legal letter for the donations you make which will help you while filing for TAX return!

6 comments:

…አንቀጸ ሰላም said...

በጣም ጥሩና ሊቀጥል የሚገባው ነገር ነው፡፡ ከብዙ አባቶች ጥቂቶቹ እንደ ዕንቊ ፈርጥ የሚያበሩና በርካታ ሥራዎችን ጀምረው(እንዳይነዋወጥ በዓለት ላይ መሠረቱን ጥለው) ሳይጨርሱት እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፤ ከነዚህም አንዱ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ናቸው፡፡ ስለዚህ ወገኖች እንረዳዳ እና የጀመሩትን ሥራ ከዳ እናድርሰው፡፡ በተረፈ ግን፡-
. ዝገጅቱም በአዲስ አበባ(ኢትዮጵያ) የሚዘጋጅበት ሁኔታ ቢመቻች
. የፊታችን እሑድ(ዳግም ትንሣኤ) ቀኑ ሚያዝያ ፳፫(23) እንጂ ፳፬(24) አይደልምና ብታስተካክሉት

Desalew said...

degeselamawian betam enamesegnalen! mimenanim yeakimachinin enrda.

Anonymous said...

This is really great. I am in

Anonymous said...

bewitatinetih fetarihen asib! besterjina yemayawatawn sra lemin endejemere yemigerm abat new.
geta nebsun yimar

Unknown said...

በርቱ በጣም ደስ ይላል አባታችን በሕይወት ባይኖሩም ትልቅ ስራ ሰርተው ስማቸውን ከመቃብር በላይ አውለዋል ይህውም እናንተ የሳቸውን በጎ አላማ በመደገፍ፣ በመከተል አራአያነታቸውን አራአያ አድርጋችሁ እየሰራችሁ ያለው ስራ በእውነት ደስ የሚል የሚያፅናና እሳቸው ስለሌሉ አለመቋረጡ ይልቁንም እየተሰራ ያለ የመስላልና በርግጥም ባባቶች ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ የሚያሰኝ ነው እግዚያብሔር ይርዳችሁ ይርዳን እንተባበራለን፡፡

Anonymous said...

Awo melkam ena yemigermu abbat neberu. yejemeruachew serawoch bezu ena bego sihonu gen mot aykerea kedemachew. Lejnam titew headu. selezih yehe kidus tegbar
endayiquaret yechalinewin yahil bemadereg entebaber. wode ager bet senihedim serachewin gobijnet enadereg. beterefe nefsachewin yimar.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)