April 13, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ በሐዋሳው ውዝግብ እና ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ ሥራ ስለሚደረገው አስተዋፅኦ ይወያያል


  • የሐዋሳው ችግር አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ዝግጅት በአባላቱ የሐሳብ ልዩነት ሳቢያ  አልተጠናቀረም፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያዘው አቋም ዋናው የልዩነቱ ነጥብ ነው።    
  • የአቡነ ጳውሎስ - አባ ሰረቀ ኮርፖሬሽን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጀው የ‹ብጥብጥ አፋልጉኝ› እና የውንጀላ ዘመቻ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቢዛመትም አሳፋሪ ገመናው እያደር በመጋለጥ ላይ ነው።
  • ከትላንትና ጀምሮ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ስም ‹‹ለሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ  ይቀርባል›› የተባለ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚከስ የአቤቱታ ፊርማ ተሰባስቧል፤ ለፊርማ  ማሰባሰቢያው ቅስቀሳ ላይ የዋለው ምፀታዊ ስልት ‹‹ያልፈረመ ተሐድሶ ነው›› የሚል ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ አወጡት ከተባለው ባለአምስት ነጥብ የአቋም  መግለጫ አንዱ ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የታላቁን የሚሌኒየም ግድብ ግንባታን ይቃወማል›› የሚል እንደ ሆነ ተገልጧል። 
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት የአስተዳደር ሠራተኞች እና አገልጋዮች ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን  በዓመት ለማበርከት ወሰኑ፤ የአባ ሰረቀን ሰርጎ ገብ አጀንዳ ተቃውመዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 13/2011)፦  ማክሰኞ ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግፊት የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ፡- በሲዳማ ጌዲኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በተፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት፣ በሐዋሳ ሦስት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተከሠተው አስተዳደራዊ ብልሽት እንዲሁም ይህን ተከትሎ በተባባሰው ሁከት እና ውዝግብ ላይ እንደሚወያይ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አመለከቱ፡፡ ከዚህም ባሻገር አስቸኳይ ስብሰባው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት መተከል ዞን/ግልገል በለስ/ ጉባ ወረዳ ቧምዛ ቀበሌ በዓባይ ወንዝ ላይ እንደሚቆም ለተነገረው የታላቁ የሜሌኒየም ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚኖራት አስተዋጽዖ ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡


ማክሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (ኤፕሪል 12/2011) ከቀትር በፊት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች እና ቁጥጥሮች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ባካሄዱት ስብሰባ ለታላቁ ሜሌኒየም ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በዓመት ለመለገስ እንዲሁም ከወለድ ነጻ የሆነ ቦንድ በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስም ለመግዛትወስነዋል፡፡ ውሳኔው በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት እና 160 በሚደርሱ ገዳማት እና አድባራት የሚገኙ 17,000 ያህል የአስተዳደር ሠራተኞችን፣ አገልጋይ ካህናትን እና መምህራንን እንደሚያጠቃልል ተመልክቷል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በነገው ዕለት በሚያካሂደው አስቸኳይ ጉባኤ በዚሁ ኢትዮጵያዊ ጥረት ዙሪያ ለሚደረገው የዜጎች ሀገር አቀፍ ርብርብ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች፣ ድርጅቶች እና አህጉረ ስብከት በሚያበረክቱት ተደማሪ አስተዋጽዖ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ አጠቃላይ በሚኖራት ድጋፍ ዙሪያ በመምከር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል፡፡  

በገናናነቷ እና ታላቅነቷ ሀገር ዐባይ በተባለችው ኢትዮጵያ ሊሠራ ለሚችለው የመጨረሻው ታላቁ ግድብ ታሪካዊ ፍጻሜ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመክርበት በዚሁ አስቸኳይ ስብሰባ፣ በፍጽምናዋ ሃይማኖት ዐባይ በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች መካከል በሲዳማ ጌዲኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት በተከሠተው ሁከት ላይ የምእመናን ተወካዮች ለመጨረሻ ጊዜ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ሌላው የመወያያ አጀንዳ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ ፓትርያርኩ ከሓዋሳ ምእመናን ተወካዮች ጋራ መጋቢት 28 ቀን 2003 ዓ.ም ካደረጉት ውይይት በኋላ ከመጋቢት 8 - 14 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ቆይታ ያደረገው የአጣሪ ልኡክ ሪፖርት ተጠናቅቆ ይደርሳል ቢባልም በልኡኩ አባላት መካከል ተፈጥሯል በተባለው የሓሳብ ልዩነት ምክንያት የሪፖርቱ ዝግጅት መስተጓጎሉን ነው የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች የሚገልጹት፡፡

ምንጮቹ እንዳመለከቱት በሐዋሳ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል አባ ኀይለ ጊዮርጊስ፣ የቅድስት ሥላሴው አባ ናትናኤል እና የሞኖፖል ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባ ሲሳይ ከሓላፊነታቸው እንደሚነሡ፤ የገዳሙን ሰበካ ጉባኤ በቃለ ዐዋዲው መሠረት በማስመረጥ ሰበካ ጉባኤው በፈንታው ሰንበት ት/ቤቱን እንዲያደራጅ ስምምነት ተደርሶበታል፡፡ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪን የሚሾሙት ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ከዚህ በመለስ በኮሚቴው አባላት መካከል አለመስማማት የፈጠረው ከፍተኛ የልዩነት ነጥብ የችግሩ መንሥኤ ነው በሚል እየተፈረጀ ባለው በማኅበረ ቅዱሳን የሓዋሳ ማእከል ሚና እና ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ እንደ ምንጮቹ ማብራሪያ፣ የኮሚቴው አባላት የሆኑት ሦስቱ ብፁዓን አባቶች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደ ቆየው ማኅበሩ እንደ አካል ተጠርቶ ባልተጠየቀበት ሁኔታ፤ ከአጣሪ ኮሚቴው አባላት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ለመወያየት በማእከል እና በዋናው ማእከል ደረጃ ቢጠይቅም ውይይቱ ባልተካሄደበት ሁኔታ በጥፋተኝነት ለመፈረጅ እንደማይቻል መግባባት አለ፡፡ ከተቀሩት አምስት የኮሚቴው አባላት በተለይም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመንፈሳውያን ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከዚህ በፍጹም ተፃራሪ ሆነው ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ መቆማቸው ተመልክቷል፡፡

ብዙዎች የጉዳዩ ተከታታዮች የአስቸኳይ ስብሰባው አጠራር ከፈጠረባቸው ጥርጣሬ በመነሣት ስጋቶቻቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 10 ንኡስ አንቀጽ 1 ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት በተደነገገው ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ/አንቀጽ 5 ቁጥር 164/ በሚያዝዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ጉባኤያትን ያካሂዳል፡፡ የመጀመሪያው ጉባኤ በየዓመቱ ጥቅምት 12 ቀን ሲሆን ሁለተኛው ጉባኤ ትንሣኤ በዋለ በሃያ አምስተኛው ቀን/ በርክበ ካህናት/ የሚካሄደው ነው፡፡ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ቅዱስ ፓትርያርኩ ወይም ቋሚ ሲኖዶስ በሚያደርጉት ጥሪ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሊካሄድ ይችላል፡፡ ከጠቅላላው አባላት ከሦስት ሁለት እጁ የሚሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ምልዓተ ጉባኤ እንዲደረግ በጠየቁ ጊዜም ጥሪ ሊደረግና ስብሰባው ሊካሄድ ይችላል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚባለው ከአቅም በላይ የሆነ እክል ካላጋጠመ በቀር መላው አባላት የተገኙበት ጉባኤ ነው፡፡ ይሁንና በሕመም እና በልዩ ልዩ ከዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት አንዳንድ አባላት ባይገኙ፡- ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከአራት ሦስት እጅ የተገኙ ከሆነ፣ አስተዳደርን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከሦስት ሁለት እጅ የተገኙ ከሆነ ነው፡፡
በዚህ መሠረት አሁን ከሚገኙት 49 ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ በተባለው አስቸኳይነት ለስብሰባው ሊደርሱ የሚችሉት በአዲስ አበባ ከተማ እና በከተማዋ ዙሪያ ባሉት አህጉረ ስብከት የሚገኙት ብቻ ናቸው፡፡ ከእኒህም ውስጥ ኋላ ላይ ስምምነት ከመደረሱ በፊት አጀንዳዎቹ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ መጠራትን የግድ እንደማያደርጉ አቋም ይዘው በነበሩት የሲኖዶሱን አባላት ለልዩ ስብሰባው በጽሑፍ የመጥራት ሓላፊነት ባለባቸው በብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና በፓትርያርኩ መካከል በነበረው ልዩነት ምክንያት እንዲሁም ወቅቱ የሱባኤ ወዲያውም ደግሞ የሆሳዕና በዓል በመሆኑ ብዙዎቹ በተለይም የሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች በአስቸኳይ ስብሰባው ላይ ለመገኘት አዳጋች እንደሚሆንባቸው ስጋት አለ፡፡ ስለሆነም ከአጀንዳው አስተዳደራዊ ይዘት አኳያ እንደተባለው በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ካሉት አህጉረ ስብከት ካልሆነ በቀር ከጠቅላላው 49ኙ ሁለት እጅ የሆኑት ከ30 የማያንሱ ብፁዓን አባቶች እንኳ ተሟልተው ይገኛሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ይህም በአስቸኳይ ስብሰባው ውስንነቶች በመጠቀም ፓትርያርኩ ለተገኙት ብፁዓን አባቶች አቅርበው በማስወሰን ሕጋዊ መሠረት ሊሰጧቸው የፈለጓቸው አጀንዳዎች እንዳሉ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል - ታዛቢዎችን፡፡

ቆይተን እርግጡን የምናየው ቢሆንም በአንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ሳይቀር የሚነገረው፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን ከሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ፣ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት እና ደርበው ከሚመሩት የነገሌ ቦረና ሀገረ ስብከት ለማንሣት ወይም የሚነሡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲሁም በእኒህ አህጉረ ስብከት እና በሌሎችም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እንዲነሣሱ ለተደረጉት ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን በጠበጠን›› ክሦች ከፍተኛውን መድረክ በመስጠት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በማኅበሩ ላይ እያካሄዱ ለሚገኙት የ‹‹ብጥብጥ አፋልጉኝ›› የውንጀላ ዘመቻ ማሳረጊያ መስጠት የአስቸኳዩ ስብሰባ ዋና ግብ ሆነው እንደተቀመጡ ተገምቷል፡፡

ይሁንና በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 10 ንኡስ አንቀጽ 5/ሀ - ሐ እንደተመለከተው፡- ቅዱስ ሲኖዶስ በማናቸውም ስብሰባ ላይ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ሙሉ ድምፅን ከሚጠይቀው ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ጉዳዮች ካልሆነ በቀር አስተዳደርን በሚመለከቱ አጀንዳዎች ከተገኙት አባላት መካከል የሚያልፈው ሐሳብ ከግማሽ በላይ በሆነው ድምፅ የተደገፈው መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም በአሁኑ አስቸኳይ ስብሰባም ይሁን በእርሱ መረማመጃነት ለግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአቡነ ጳውሎስ - አባ ሰረቀ ጥምረት የሚንቀሳቀስበትን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚደረምስ እና በፀረ-ማኅበረ ቅዱሳን (ማኒያ) የተለከፈ አደገኛ ተንኮል ማስተዋል የተሳናቸውን ደጋፊዎች በቀላሉ አግኝቶ ይሳካለታል ተብሎ አይጠበቅም።

10 comments:

Anonymous said...

All (especially what is said on MK) is guess, as it is confirmed by the reporter - las paragraph. Uggghhh.

Anonymous said...

እባክዎትን ልብ ይግዙ ዛሬ እግዚአብሔር ቢታገስ ዝም ቢል ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ለእርስዎ የንስሀ ጊዜ ለመስጠት ነውና ይህን ጊዜ እተውለው ቢጠቀሙበት ይሻላል።በእጅዎ ላይ የብዙ ሰው ደም አለ። የቤተክርስቲያን አምላክ ምህረቱን ይላክልን

Anonymous said...

እንደምን ሰነበታችው ደጀ ሰላሞች አለማችን በምን አይነት ሁኔታ እንዳላች የአለም ምሲጥር ነው፡ ሆኖም በሀይማኖታችንና በአገራችን ላይ እየተሰራ ያለው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር እንዲያየውና እንዲፈርድ እያልኩኝ ግን የባሰ አታምጣ ስል ከአመት ወደ አመት ከመንግስት ወደመንግስትም በተሸጋገርን ቁጥር ነገሮች ሁሉ የባሰ ሲሆኑ ምክትል ፓትሪያርኩ ሲነሱ ብዙ ችግሮች እንደሚጨምሩ እፈራ ነበር፤ በዚህ ላይ ደሞ በእንደዚህ ያለ አቢይ ጾም ሰውና እጊአብሔር ተገናኝተው ይቅርታና ምህረት ለሰውም ለምድርም ምህረት እንዳይወርድ ምንም አይነት አጣዳፊ ጉዳይ ሳይኖር ሱባአኤንና ጸሎትን ማአስቶጋጎል ምን ይባላል፤ አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ሀጢአታቸውን እያሰቡ ከፈጣሪያቸው ለመገናኘት ባደረጉት ሱባኤ የለመደው ጠላት በመላእክት ተመስሎ ምንም ሱባኤያቸውን ቢያስተጌጉልም እግዚአብሒር ሀይማኖታቸውንና ድካማቸውን በብሩህ ገጹ እንደተቀበለ አሁንም እግዚአብሔር የንጹህኑን መከራ አይቶ እንደ አባታችን አዳም እንደፈረደ አሁንም ይፍረድ፡ ለዘለቄታዊ መፍትሄ አጥብቀን እንጸልይ፤ እናልቅስ የፈጣሪ መፍትሔ ይበልጣልና፡ እግዚአብሔር የቸርነቱን ስራ ይስራልን፡ አሜን!!!!

Anonymous said...

እኔ የምለው ይህ ነው አስቸኩዋዩ እኛ በላባችን ነው የምንገነባው ስም ቀይረው "የምጽዋት ግድብ" ሊያስብሉት:: ምነው በዐቢይ ጾም ሱባኤ ቀርቶ . . .

Gebre Z Cape said...

"ለፊርማ ማሰባሰቢያው ቅስቀሳ ላይ የዋለው ምፀታዊ ስልት ‹‹ያልፈረመ ተሐድሶ ነው›› የሚል ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ አወጡት ከተባለው ባለአምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አንዱ ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የታላቁን የሚሌኒየም ግድብ ግንባታን ይቃወማል›› የሚል እንደ ሆነ ተገልጧል። "

ነገ ደግሞ ምን እናነብ ይሆን?? ምንስ እንሰማ ይሆን????? አምላካችን በቸርነትህ ጎብኘን::

Anonymous said...

Aba Paulos Getachew Donin wede Awasa yehagere Sibiket halfi adirgew lemelak endetezegaju Getachew Doni erasu bemenager lay new. Yeawasa hizib yihinen aynet wisane mekawem alebet.

Anonymous said...

ትናንት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአዲስአበባ ሀገረስብከት ሰራተኞች ለ አባይ ግድብ ርዳታ እንደሚሰጡ መወሰናቸውን ገልጾልናል፡፡ ርዳታው ያገር ጉዳይ ነውና መልካም ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ፋና ሬዲዮ የአዲስአበባ ሃገረስብከት አብያተክርሰቲያናት በነፍስወከፍ የ100000(መቶ ሽህ) ብር ቦንድ እንዲገዙ ለመወሰን ሲኖዶሱ አሰቸኳይ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ነግሮናል፡፡ ይህም ጥሩ ነው ያገርጉዳይ ስለሆነ፡፡ ግን ሁለት ነገሮች ገርመውኛል
1. አንድ መነኩሴ አቡነ ጳውሎስ በሰበሰቡት የገቢ ማሰባሰቢያ ስብሰባ ላይ ለETV በሰጡት ቃለምልልስ (አስተያየት) የ 10000(አስር ሽህ ) ብር ቦንድ እንደገዙ ተናግረዋል፡፡ አንድ መነኩሴ እንዴት ይህንያህል ገንዘብ አጠራቀመ? ከየትስ አመጡት? አንድ መነኩሴ ይህን ያህል ገንዘብ እንደዋዛ ለቦንድ ግዥ ካዋለ እንደዋዛ ያጠራቀመው ሌላ ብዙ አስር ሽህዎች አሉት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትላልቆቹ ስንት ይኖራቸው ይሆን?....................
2. ለአባይ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ የሚጠራ የቤተክርስቲያን መሪ ምነው አሁን ቤተክርስቲያኗ ላለችበት አንገብጋቢ ጉዳይ ዝምታን መረጠ? በየገጠሩ ለተዘጉት አያሌ አብያተክርቲያናትና አድባራት እንዲሁም ለአብነት ትምህርት ቤቶች እንዴት ርዳታ ማሰባሰብ አቃተው? በርግጥ ከሰማዩ ቤት የምድሩ በልጦ ይሆን አባቶቻችን?

እግዚአብሔር ደህናቀን ያምጣ

Anonymous said...

የአዋሳ ጉዳይ አስገራሚ እየሆነ ነው ለመሆኑ ዶኒ አዋሳ በምን ሂሳብ
ነው የሚሄደው በክልል እንዳይባል እርሱ ኦሮሞ ነው እየተበሳበሰ ያለውን የእባ ጎርጎርዮስ ሀግረስብከት ለምን ሄዶ አያስተካክልም
ይህ የአቡነ ጎርጎርዮስ እቅድ ነው።

Melkamu said...

የቤተክርስትያን ሰዎች ለአገራቸው ግንባታ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውና ገንዘብ ማዋጣቸው ምሳሌያዊ ነው፡ በጣም የሚደገፍም ነው። በተለይ ጠላቶቻችንን የሚይሰፈስፈስብብንን ዓባያችን በሚመለከት ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ፡ የኢትዮጵያ ፍቅር ያለው ሁሉ ተመሳሳይ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይገባዋል።

ይህን በተመለከተ፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምክርቤት የሚባለው ወይም ተመሳሳይ የእስላም ድርጅቶች ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ይሆን? በሳኡዲ አራቢያ ሁለተኛው ኃብታም እንደሆነ የሚነገርላቸው ሸህ አላሙዲንስ ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ያበረክቱ ይሆን? ባጠቃላይ በግድቡ ላይ ያላቸው አመለካከት ምን ይመስል ይሆን?

ቸሩ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በቅርቡ ገልጦ ገላልጦ እንደሚያሳይን እርግጠኛ ነኝ።

Anonymous said...

ABETU AMLAKI YECHINI BETEKIRESTIAN BE MYTATEFEWI KALHI TEBIKATI,,,,,,,,,,,,,,

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)