June 28, 2012

ርዕሰ አንቀጽ፡- የሀገሪቱን ሰላም ለማስከበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላም ማስከበር

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 2/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከትችውን አስተዋጽዖ መዘርዘር ለቀባሪው እንደማርዳት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ሕግና ሥርዓትን አውጥታ፤ ካህናትና ምዕመናን በአንድነትና በመከባበር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓተ እምነት፤ ዶግማና ቀኖና እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ፤ በልማትና በማኅበራዊ ጉዳዮች በሕብረተሰቡ ዘንድ መረዳዳትና መቻቻል እንዲኖር አድርጋለች፣ በማድረግም ላይ ትገኛለች። ይህም ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል።

ስት ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሁሉ ተግባራት ለዘመናት ስታከናውን የቆየችው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረድ በመጠቀምና በማክበር ነው። ይህም አራር ለዘመናት ሳይፋለስ ቆይቷል። ይህንን ከሀገሪቱ ከ50% በላይ የሆነና በሚሊዮን የሚቆጠር ምዕመን ይዛ በሕግና በሥርዓት ባታስተዳድር ኖሮ የቤተ ክርስቲያንቱ ሰላም ብቻ ሳይሆን የሀገሪም ሰላም ሊደፈር እንደሚችል እሙን ነው። የቤተ ክርስቲያንመንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረድ ለማስጠበቅ እና በቤተ ክርስቲያንቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት የግ ከለላ በመስጠት በየጊዜው የነበሩት ነገታትና የመንግሥት  አካላት በቂም ባይሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የቤተ ክርስቲያቱን ዶግማና ቀኖና ለማፍረስና ብቷንና ንረቷን ለመዝረፍ እንዲያመ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረዷን መጣስ እየተለመደ መጥቷል። እነዚህን ሕገ ወጥ ተግባራት ለመከላከል የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂና ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በየደረጃው ያሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር አካላት የሚወስኗቸው ውሳኔዎችና አመራሮች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ብዙ እንቅፋቶች እያጋጠሟቸው ነው። ለዚህም እንደማሳያነት በቦሌ የቆመው የፓትያርኩ ሐልተ ስምዕ መፍረስና በሐዋሳ ሀገረ ስብከት በተፈጠሩ ችግሮች ላይ የተወሰኑት ውሳኔዎችን ለማስፈፀም ያለው ፈተና መግለፅ ይቻላል። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው፦

1.      የቤተ ክርስቲያንቱን ዶግማ፤ ቀኖና እና ትውት ለማስከበር እና የቤተ ክርስቲያንብት እና ንብረት ከውድመትና ከዝርፊያ ለመታደግ ጥረት በሚያደርጉ አባቶች ላይ እየተደረገ ያለው ዛቻ፤ ጫና እና ማስፈራሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚገኝ ጉዳይ እንጂ የሚቀንስ ሆኖ አለመገኘቱ፤ ይህም ጉዳይ መንግሥት  በሀገሪ የለም፤ ሕግና ሥርዓት አስከባሪ የለም፣ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ደንታ የለውም”’ እስከኪባል ድረስ አድርሶታል።

2.     ባለፈው ዓመት በተደረገው በብፁዓን አበው ላይ የደረሰው ድብደባ፤ አፈናና ዛቻ የፈፀሙት ግለሰቦች ለፍርድ አለመቅረብና ሕጋዊ ቅጣት አለማግኘት ምዕመኑ በመንግሥት  ላይ ያለውን ተስፋ እስከመጨረሻው እንዲሟጠጥ አድርጎታል።

3.     በዚህ ዓመትም በጥቅምት ወር በተደረገው ጉባኤ ላይም ቢሆን ብዙ ብፁዓን አባቶች የማስፈራሪያ ዛቻዎች በስልክ እና በአካል ተሰንዝረዋልአሁንም የቤተ ክርስቲያቱ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅ፤ ብቷ እና ንብረቷ እንዳይዘረፍ፤ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረድ እንዲጠበቅ በሚታገሉ አባቶች ላይ ከእነዚህ ቡድኖች የሚሰነዘረው ማስፈራሪያ ቢጨመ እንጂ አልቀነሰም። 
  
4.     በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወሰኑት ውሳኔዎችንም ለማስፈፀም አለመቻሉ በቤተ ክርስቲያቱ ውስጥ ነው በዝርፊያና የቤተ ክርስቲያን ሰላም በማደፍረስ ምዕመኑን ተፋ በማስቆረጥ ራ ላይ የተሰማሩት ቡድኖች ቤተ ክርስቲያኒቱ ብሎም በሀገሪ ሰላም እና ልማት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚጥሉ ማወቅ ማስረጃና ጥልቅ ምርምር አያሻውም።
5.     አሁንም ቢሆን መንግሥት በራሱ የሚያደርገውን አስተዳደራዊ በደል ምዕመኑ የሚታገሰውን ያህል በእምነቱ ሲመጣበት ሊታገስ እንደማይችልና የቤተ ክርስቲያ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅ፤ ብቷ እና ንብረቷ እንዳይዘረፍ፤ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረድ እንዲጠበቅ አስፈላጊውን መስዋዕትነት መክፈል እንደሚችል አውቆ መንግሥት ያስብበት ይገባል

6.     በፖለካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመ ለመሪዎች መባረ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ምዕመ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው ይገባል።

7.     ስለሆነም የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ የልጣን ተዋረድ እንዲጠበቅ እና በቤተ ክርስቲያንቱ የበላይ ጠባቂና ወሳኝ አካል በሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ እና በየደረጃው ባሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር አካላት የሚወሰኑት ውሳኔዎችና አመራሮች በእምነቱ ቀኖናዊ አራር መረት ተፈሚ እንዲሆኑና ከላይ ለተጠቀሱት ለእውነተኛ የቤተ ክርስቲያንቱ አካላት መንግሥት  አስፈላጊውን የግ ከለላ ሰጥ ይገባል እንላለን።

8.     መንግሥት የሀገሪቱን ሰላም ለማስከበር የቤተ ክርስቲያኗን ሰላም ማስከበር ይጠበቅበታል

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

55 comments:

Anonymous said...

Ewenet belachehole dej selamoche menegeste betekeresetiyanene metebeke hegen maskeber alebet!

Anonymous said...

Hayemanot Malet Mesekel New Selazi Mengest Yasebebete.....በፖለቲካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ ለመሪዎች መባረር ምክንያት እንደሆነው ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ምዕመኑ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው ይገባል።

Anonymous said...

በፖለቲካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ ለመሪዎች መባረር ምክንያት እንደሆነው ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ምዕመኑ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው ይገባል። Ayekerem

እህተ ሚካኤል said...

እስቲ ባለቤቱ ይርዳን እኛም ያቅማችንን እንጣር በጾም በጸሎቱ መበርታት ነው በየዘመኑ ቤተክርስቲያን ይበረታባታል የአሁኑ የከፋም ቢሆንም እንካን

Anonymous said...

yalitaye gin le mengistim hone le hager selam ye hone sew Pawulose

EPRDF should see it in detail

Anonymous said...

መንግሥት ከማን ያተርፋል ከቅዱስነታቸው ወይስ ከሕዝብ?
ለዘመናት መሰደብያ ምክንያት ሆነው ሳለ ዝምታው ለምን አያስብልም? መንግስት ከሚተችባቸው ጉዳዮች ዋናው እኮ አቡኑ ናቸው። እስኪ ምን አተረፋቹ? ስለ ጎደለባቹ ነገሮች ግን ያለ ጥናት ብዙ ማለት ይቻላል:: ደጀ ሰላማውያን ብንወያይበትስ?
ይቀይርልን አይደለም ያስብበት ዘንድ ግን ...

Anonymous said...

"ሆድ ለባሰዉ ገመድ ኣታዉሰዉ" መንግስት ግን ስንት ጠላት እያፈራ እንደሆነ ማስተዋል ተስኖታል!!! ራሴን ጨምሮ፣ በመንግስት ያለኝ አመለካከት እየተለወጠ ነዉ። መጀመሪያ በጣም ደጋፊ ነበርኩ፣ ከዚያ ለዘብተኛ ደጋፊ ሆንኩ፣ ኣሁን ግን ቡዝም ነኝ..... በአዉነት ነዉ የምላቹሁ መንግስት ራሱ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም የሚሸርበዉ ሴራና በደል(በ83 ያደረሰዉ ጭፍጨፋ፣ በ97 የቤተ ክርስቲያንን ስም ማጥፋት፣ በ2001 ደግሞ ጳጳሳትን ድብደባና ማስፈራራት)፣ ሌላዉስ ባገኘዉ አጋጣሚ መጎንተሉንና በተለይ ስለእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጽመዉ በደል ብዙህ በመሆኑን ለመግለጽ ያቅተኛል። በቅርቡ እንኳዕ በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኛ በኣል ሲደርስ መንግስት ካፌ አስከለከለ። እኔ ግን በጣም እየናደድኩ ነኝ።

Dadi said...

Hulachinim ye dirshachinin enweta !
Ke minim belay gin "let have information about our church and distribute the information !!!"
let ask Question for ourself, what is my contribution?! Where, when § how can i do it?! Is really i pray for my church?!
With z help of God, St.Mart and Saints we save our church !!!
Thanks deje selam for sharing the information.

merdekeos said...

ሥርዓት አለባ መስተዳድር ከተጀመረ ሰነበተ በሁለት አባቶች ውግዘት መንጋውን ለመበተን ተሞከረ አልሆነም መናፍቃን ተላኩ አልተሳካም በመጬረሻም አናቱ ተነቃነቀ ምንለመሆን እንደሆነ ባናውቅም አራሱን ለውድቀት ያዘጋጄ ዬመስላል የተነቃነቀ ጥርስ ይወልቃል ቢስበስቡ ይሻላል b

Natnael said...

Brothers and sisters, why we are accusing the government?
Had there any body who formally claimed the crimnals during the conditions performed?

If we had not approached the crimnals to "frdibet" what is wrong to the government?

I think we are thinking by our nostrils and lips unlike the government who aheading to develop the country.

May God give us wisdom to internilize conditions by our enlightened mind

Anonymous said...

ምን መንግስት መንግስት ትላላችሁ ወገን ማን ሆነና ነው የችግሩ መንሰኤ? ወታደር ”አባ” ጳውሎስን በመጠቀም ቤተክርስትያንን ለመናዲ የተነሳ እኮ እራሱ መንግስት ነው፡፡እኔ ለመንግስት የቅርብ ሚስጢር አዋቂ ከሚባሉት ሰዎች አንዱ ነኝ (እድለ ቢሱ እኔ በቤተክርስትያን ላይ የሚጎነጎነውን ሴራ እየሰማሁና እያየሁ እራሴን አቃጥየ መሞቴ ነው) በየሴክተሩ ላይ የተሰገሰጉ መናፍቃንና እስማኤላውያን ስራቸው ምን መሰላችሁ?ባገኙት አጋጣሚ ቤተክርስትያን እንዳልነበረች ለማድረግ እኮ ነው የሚጥሩት፡፡ እኔ ግን በጣም የሚገርመኝ ና የሚደንቀኝ የእኛ ዝምታ ነው……ምን እስከሚኮን ነው? ቤተክርስትያን እክጠፋ? ዋይ!!!!!! አሁንስ ዝምታ ወርቅ አይደለምምምምምምምምምምም!!!!!!!!

Anonymous said...

ሰላም ለእናንተ ይሁን ደጀ ሰላሞች!

ያነሳችሁት ሀሳብ መልካም ቢሆንም ጩኸታችን ዛሬ የተጀመረ አይደለምና መንግሥት ብሎጓንም ሆነ እንዲህ ለእምነታቸው የሚንገበገቡ አካላትን(ማህበረ ቅዱሳንን ጨምሮ) በአመጽ ቀስቃሽነት ከመፈረጅ የዘለለ በወንጀለኞች ላይ ርምጃ ለመውሰድ አንዳች ዝግጁነት እንደሌሌው ለዘመናት ተገንዝበናል፡፡ አሁን ድረስ የዚህ መንግሥት ደጋፊ ብሆንም እነኳ በእምነት ላይ ያለውን ለዘብተኝነት በተመለከተ ቁጥር አንድ ተቃዋሚው ሆኛለሁ፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ፡-

1.ቤተ ክርስቲያኗ በመናፍቃን ስም የማጥፋት ዘመቻ ለአገሪቱ ድህነት እሷን ተጠያቂ ሲያደርጉ፣ እምነቷን ትክክል አይደለም እያሉ ሲያንቋሽሹ፣ የቅዱሳኖቿን ክብር ሲያዋርዱ፣ የአምልኮ ቦታዎቿን በአደባባይ ሲያረክሱና የኔ ቢጤን ከመንገድ ዳር እየጎተቱ አቡነ እገሌ መናፍቅ ሆነ እያሉ(ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቁሮ ለፍርድ የሚቀርብ አባት ብናጣም) በምን አገባኝነት እየሰማ እንዳልሰማ ማለፉ፤

2.በእስልምና ተከታዮች አዋቂ ነን ባይነት በራሳችን መጽሐፍ ሳያምኑበት እኛኑ ለማስተማርና ለማንቋሸሽ የሚያደርጉትን ጥረት ሃይ ከማለት ይልቅ የልብ ልብ መስጠቱና በዚህም ሳቢያ ወደእንግደላችሁ ደረጃ ከፍ እንዲሉ አስተዋጽኦ ማድረጉ፤

3.”ፓትርያርክ” ተብየው ወደሥልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ከላይ እናንተ የገለፃችሁትን ጨምሮ እዚህ ላይ ሊፃፍ ቦታ የማይበቃውን ወንጀላቸውንና የምእመናንን ጩኸት ወደጎን በማለት እንደሃገር መሪ ከቤተክርስቲያኗ ጎን ከመሆን ይልቅ ለግለሰብ በመወገን(ፖለቲካዊ ትሥሥሩ እንዳየለበት ግልጽ ቢሆንም)ችላ ማለቱ .....ለጊዜው ይበቁኛል፡፡

ስለሆነም ከዚህ መንግሥት ፍትህ መጠበቅ ከዝንብ ማር የመጠበቅ ያህል ቢሆንም መጓዝ ያለብን ርምጃ ግን ያለ ይመስለኛል፡፡ እነዚህም፡

ሀ.መንግሥት ሕጋዊ አካሄድን አልተከተላችሁም የሚለውን ክፍተት ለመድፈን ቢቻል ለእምነታቸው የቆሙ የሲኖዶስ አባቶችን አስተባብሮ ፍትህ ያጡ ውሳኔዎችን በመረጃ አጠናቅሮ ለፍርድ ቤት ማቅረብ(ፍትህ እንደማያገኝ ከወዲሁ እርግጥ ቢሆንም)፣

ለ.ታዋቂ የመንግሥት ድረ-ገጾችን ልቀቁልንና ተጨባጭና ግልጽ የሆኑ መረጃዎችን በመላክ የአቤቱታው መጠን በጳውሎስ ግቢ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የህዝብን ትእግሥት በእጅጉ የተፈታተነ ብሎም የአገር ሥጋት ወደመሆን የቀረበ መሆኑን ለማስገንዘብ መሞከር፣

ሐ.በቤተ-ክርሥቲያናችን ላይ እየተካሄደ ያለውን ዝርፊያ በተጨባጭ ማስረጃ በማስደገፍ ወደፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለማቅረብ መሞከር መቅደም ያለባቸው ርምጃዎች ይመስሉኛል፡፡

በርካታ አንባብያን ማን በማን ላይ ይፈርዳል? ይህ መንግሥት በጳውሎስ ላይ እንዴት ርምጃ ይወስዳል? የሚል ጥያቄ ልታስቀድሙ እንደምትችሉ ቢገባኝም መሄድ ያለብንን ሕጋዊ አካሄድ ለመጓዛችን ከላይ የተገለፁት ርምጃዎች “ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር ዘብ ቆሚያለሁ ለሚለን መንግሥታችን” ምን ያህል ርቀት እንደተጓዝን ለመመርመር ያስችለዋል የሚል እምነት ስላለኝ ነው፡፡
የመጨረሻው ርምጃችን ግን አይደለም ለመንግሥት ለአገሪቱም ምጥ ነው፡፡ ከተዋህዶ ጋር የመሆንና ያለመሆን ጉዳይ ያኔ የሚታይ ይመስለኛል፡፡ ያን ጊዜ እንደ ግብፃውያን ግባችንን ለማሳካት “ፌስቡክን ለቀጠሮ ትዊተርን ለቅንጅት ዩ ቲዩብን ደግሞ ጉዳቸውን ለዓለም ማሳያነት” ተጠቅመን የተዋህዶን ድንበር እስክናስከብር ድረስ ከዲያብሎስ አገልጋዮች ጋር መዋጋት፡፡

ቢንያም
ባህርዳር

ዝምታ said...

መንግስት ቤተክርስቲያንን እየደፈረ እና እያስደፈረ ነው። በአደባባይ ቤተክርስቲያንን ከሚነቅፉት ሚንስትሮች ጀምሮ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ እጁን በማስገባት በጣም እየጎዳን ነው።አቡኑ እና ግብረ አበሮቻቸው ሙስናን እና ቤተሰባዊ አሰራርን በቤተክህነት እያስፋፉ ያሉት መንግስትን ከለላ በማድረግ ነው።መንግስት ከጥፋቶቹ መማር አለበት። ኢህአዴግ ወደስልጣን ሲመጣ ህዝቡን ለመያዝ እና መረጋጋትን ለመፍጠር ብሎ ያደረጋቸው ድርጊቶች በቤተክርስቲያን ላይ ጠባሳቸውን ጥለው አልፈዋል። አሁን ያ ዘመን አልፏል።ዛሬም መንግስት መረጋጋትን ይፈልጋል።ያንን ደግሞ ማምጣት የሚቻለው የህዝቡን ፍላጎት በማሟላት፤ቤተእምነቶች በራሳቸው ህግና ደንብ እንዲተባበሩ በመተው፤ለሀገሪቷ ሰላምና ዕድገት የበኩላቸው እንዲወጡ በማበረታታት እና በማሳተፍ ብቻ ነው። ለአቡኑ እና ለግብረ አበሮቻቸው ከለላ መስጠት ተሃድሶ እና ቤተሰባዊ አስራር በቤተክርስቲያን ላይ እንዲያንሰራፋ መፍቀድ ነው። ይህን ደግሞ የምንሸከምበት ትከሻ ሳስቷል። የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ተኩላዎችን ከቤተክርስቲያን እናፀዳለን።ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም የማንነት ጉዳይ እንጂ። የተለያየ የፖለቲካ አመላካከት እና ብሔር(ክርስቲያን ቦታ ባይሰጠውም እንኳ)ያለውን ማህረሰብ መስቀሉ አንድ ያደርጋቸዋል።ይህ ወቅታዊውን አመጽ ለመቀስቀስ ከሚደረገው ሙከራ ጋር መደመር የለበትም!!!ይህ ስለሃይማኖት ብቻ ነው።ቤተክርስቲያን መጠቀሚያ ማድረግ አንፈልግ።

Anonymous said...

I accept "Bahirdar's" comment

Anonymous said...

በስመአብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!
It has been a long time since the government started ignoring the church, and for sure it will continue as long as the demon abune Paulos is in position. But lets pray to the omnipotent GOD and definitely he will help us solve the problem of the church.

" Be the almighty GOD with us,protect our church from disintegration and bless our country!!"

Whether you believe or not said...

Whether you believe or not,

As to me, as one of the comment giver reflected his position, I am also one of the 'burntout layman' by the plan of protestants and Amaleqawians who are using the hand of governmental power to their private or denominational mission (against our indigenious church).
Hence, what you say was ok if and only if our church's enemies were limited in number. However, in one side-external invaders are on the spot like Eygpt, Eriterea, alqaydas and other neighbours; in other side the internal enemies spiced by the outsiders are moving here and there.
Therefore, if we shift our hands to the patriarch and his followers, we are going to mis the developmental objective of the church and the country because we are going to widen up the gate to the above subjects.

So, the solution could be effective if we legally hand the corruptors and denouncers of our dogmatic & traditions over the court. I think, if the problem is in the patriarch, lets try to solve by polite- convincing way and effective discussion (God will change in to Good Line). If he become solid, lets leave him until his death (almost less than 2 years).

Anonymous said...

ውድ ወገኖቼ አለመታደል ነው፡፡ እኛው ክርስቲያኖቹ እራሳችን እርስ በርስ ፍቅር አጣን፡፡ጎጥ እየለየን ተጨካከንን፡፡ እጎናችን ያለ ወገናችን ሲራብ፣ ሲጠማ፣ንብረቱን ሲቀማ፣ ከመኖሪያው ሲፈናቀል፣ ሲታሰርና ሲገደል፣ ቀሪዎቻችን ከማዘን ይልቅ ፌሽታ አደረግን እንባችንን ወደፈጣሪያችን ከማፍሰስ ይልቅ ተሳለቅን፤ይበለው ይበለው አልን፡፡ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ተጫውተው ያልጠገቡ፤ሮጠው ያልጨረሱ ህጻናት ልጆቻችን እጄታው "የተበላ" የት/ቤት ዩኒፎርም እንደለበሱ"ባንክ ሲዘርፉ" በጥይት ተደብድበው እሬሳቸው ጎዳና ላይ ሲጎተት "ተራ ወሬ" ብለን ዝም አልን፡፡ከሙሲሊም ወንድሞቻችን ጋር እንድንባላ በካድሬዎች የተደራጀ "አክራሪ ቡድን" ገዳማቶቻችንን እና አብያተ ክርስቲያናቶቻችንን አቃጠለ፤ በርካታ የተዋህዶ ልጆችን በሰይፍ አንገታቸውን ቀላ፡፡ የቤተ መቅደሶቻችን ምንጣፍ በተዋህዶ ልጆች ደም ታጠበ፡፡ ነገር ግን የተበደሉ ወገኖች ስለሆነው ሁሉ አድልዖ ለሌለበትና ሁሉን እኩል ለሚያይ እውነተኛው ፈራጅ አምርረው እንደ ልጅ እንባቸውን አፈሰሱ፡፡ላለፉት 19 ዓመታት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን "ብሶት በወለዳቸው" የትግራይ ወያኔዎች የመከራ ዘመን አሳልፈዋል፡፡ የፖለቲካውን እና የኢኮኖሚውን ስቃይ ተሸክመን አምላካችንን ተስፋ በማድረግ መጪውን ዘመን በትእግስት ዝም ብለን ጠበቅን፡፡የአሁኑ ዘመቻ ግን ይህን የመከራና የስቃይ ዘመን ለማሳለፍ የተሸሸግንባትን እና ብቸኛ መጽናኛ እና ተስፋችን ያለባትን ሃይማኖታችንን ማጥፋት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ አሳዛኙ ነገር የኢትዮጵያዊነት አሻራ እና የሃይማኖታችን መሰረት የተተከለባት የዋሁና ደጉ የትግራይ ህዝብ አብራክ ያፈራቸው የሃይማኖት እና የፖለቲካ ሰዎች መሆናቸው ነው፡፡ወገኖቼ ሰው በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ኑሮው ክስረት ሲያጋጥመውና ተስፋ ሲቆርጥ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል…

Unknown said...

Nageenyi siniif yaata'u daje salam mana amantaa teenyarrati qormaani yeroo yeroodhan ulfaachaa dhufee jira. yaa ta'u malee qormaata kana caalus waan dabarsiteef wanti dhufu hinjiru waan dhiiga Waaqayootin dhaabateef jechuudha.

Anonymous said...

አባቶች የምትለው እነ ማንን ነው፡፡ እንዚህ በሀሰትና በተጭበረበረ መንገድ ወይም አንገታቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ፣ ወይም ባልተመዘናና ባልተጣራ ማስረጃ፣ ወይም በቲፎዦ፣ ወይም በውዳሴ ከንቱ፣ ወይም በስግደትና በምልጃ፣ ወይም በመንደር ድጋፍ ወይም.. ወይም.. ወይም… በብዙ ማታለያ ተሸመው በኋላ ለሾሟቸው አባቶችና ወይም ሲኖዶስ ሳይቀር ፈተና በመሆን የቤተ ክርስቲያንን ሰላም የሚያውኩትን ነው? ወይስ ሥርዓተ ገዳም አክብረው፣ የቤተ ክርስቲያንን ዋና ትምህርት ተምረው የአገልግሎቷን መሠረት አውቄው ቀን በሥራ ሌሊት በፀሎት፣ ቀን በቅዳሴ፣ ሌት በሳታታ፣ ቀን በማስተማር ሌት በማስተማር በመጸለይ፣ የሚኖሩትን፡፡ አባቶች የምትለው ከሀገር ሀገር ዞረው በድንግል ስም ተማጽነው ዲጓን ጾመ ዲጓውን ሳታታ ቅዳሴውን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የግእዝ ቅኔውን፣ ተምረው አሠረ አበው ጠብቀው ግን ተረስተው ቤገጠሩ በሠላሳ ብር የተቀጠሩትን ነው፣ ወይስ ቅዳሴ እንደሙዚቃ አጥንተው ደብረ አባይ ምስክር ነን፣ ድጓው ተምሬው ነበር ለስብከት ስዞር ጠፍቶኝ ነው፣ እያሉ ከዚያም ከዚያም ሮተው ሳያሟሉ ሮጠው ወረቀት በመሰብሰብ፣ በሺ በሁለት ሺ ተቀጥረው ገዳም ፈተው ገዳም ዘግተው ፣ ከተማ ለከተማ ሲዞሩ ቆይተው ወደ ቅዱሲ ሲኖዶስ የገቡትን ነው፡፡ ብዙ ብል ደስ ይለኛል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የተከበረ የአበው ጉባኤ ነው አንዳንዶቹ ከጸሎት የበለጠ ከየግለሰቡ የሚሰበስቡትን ወሬ ይዘው ይገባሉ፡፡ አንዳንዶች ለጽዋ ማህበርና በነጋዴ ቡድኖች ያላቸውን የጥቅምና የተስፋ አጋርነት ለመሟገት ይዘው ይገባሉ፡፡ ሀገረስብከትን ያህል ተሰጥቷው ለመንደር ስብሰባ ጉዳይ አስፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ቡድኖች እና ነጋዴዎች አማራጭ መጠጊያና የጥፋታቸው መደበቂያ አድረገው ስለሚቆጥሩ፣ ለእነሱ ሕልውና ተቆርቋሪ በመሆን ጀብዱኛ ሆነው ለመቅረብ ይሞክራሉ፡፡ በእነሱ ምክንያት የተከበረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕብረትና አንድነት ይናጋል፡፡ ለእኔ አባቶች ማለት የሰላም መልእክተኛች፣ ጥፋት ሲኖር በፍቅር ለማረም የሚሞክሩ፣ የቤተ ክርስቲያኗን ሕልውና ለቡድና እና ለጽዋ ማህበር አሳልፈው የማይሰጡ፣ የቤተ ክርስቲያን የሥልጣን ተዋረድ እንዲጠበቅ፣ አዛዥና ታዛዥ እንዲከባበር፣ ማንም ከተሰጠው ጸጋና ሐላፊነት ወጥቶ በማያገባው እንዳይገባ የሚከላከሉ፣ በአግባ የሚያስተምሩ፣ ከገዳን የተጠሩ፣ አፋቸው የታረመ፣ የራሳቸውን ጥፋት አውቀው ሌላውን ጥፋት የማይደግሙ፣ የዚህን ጽሑፍ መልስ አይቸ ገና ብዙ እልሀለው ወዳጀ ደጀ ሰላም አንተም በመልክ ቢጠፉ በስም ይደግፉ እንዳትሆን እንደስምህ መልክህ ይመር፡፡

ሰናፍጭ አባላለሁ

ኃይለ ኢየሱስ said...

ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያፅና .ቤተ ክርስቲያን መጎዳት የጀመረችው ዛሬ አይደለም .... ሁላችንም በየደረጃው የሚደረገውን ኢ- ፍትሐዊ እንቅስቃሴ እና አስተዳደር እንታገል !

Aragaw E. said...

I also accept Binyam's suggestion.

Anonymous said...

It is foolish to expect weyane to care for the church. For weyane, the church is a den for neftegnoch, i.e. Amharas.

The weyane leadership hates the church much more than anything because of that evil characterization of the church. If you could, just uprise and take your destiny into your hands in order to free the church and give the place it deserves in the society. That could perhaps pave the way to create democracy in the country.

Anonymous said...

"ከሁሉም በላይ አሳዛኙ ነገር የኢትዮጵያዊነት አሻራ እና የሃይማኖታችን መሰረት የተተከለባት የዋሁና ደጉ የትግራይ ህዝብ አብራክ ያፈራቸው የሃይማኖት እና የፖለቲካ ሰዎች መሆናቸው ነው፡፡ወገኖቼ ሰው በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ኑሮው ክስረት ሲያጋጥመውና ተስፋ ሲቆርጥ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል…?"

ለሚለዉ መልሱማ አይኑን ጨፍኖ ወደሞት ይጓዛል፣ በሞቱ ነጻነትን ለማወጅ!!! ኢሕአዴጎችስ እንደዚያ አይደል ያደረጉት፣ ረስተዉት ነዉ እንጂ!!!

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰው። ምንድነው የምንጠብቀው ምን እስኪሆን። ለሀገራችንና ለክርስትናችን አንድ የለውጥ አብዬት ማቀጣጠል ያቅተናል ዝም ብሎ ወሬ ምን ይሰራል፡ ከአረቦቹ እናንሳለን እንዴ ሃገራችንንም ቤተክርስቲያናችንንም ነጻ ለማውጣት።

እግዚአብሔር የጌዲዬንን ልብ ይስጠን

Anonymous said...

dear write of this article, why you afraid to say the truth? you know the person, who is abused our church. he is the the Current "goldne race" leader. forget about the Holy synod, I hope one day, God of ethiopia, will clean his house one day. many great fathers lost their jobs and their lives because they spoke the truth. Like Alaka Ayalewe , Lekelekawent Menker Mokonne (from gondar ),extra.I never see a father who enjoys when his childrens' are suffering.

Anonymous said...

woye gerum minyeshalenal ebakachu, woyanene khager mabarere akaten

Anonymous said...

good

Anonymous said...

abetu endecherenetih enji enedebedelachin ayhun!

Anonymous said...

Dear Ethiopians
I can smell the anger and frustrations resonating in every mind of true christians and Ethiopians. A big revolution and civil disobedience is in evitable in the coming years.
I personally prefer to die than seeing our church confsicated by tehadeso people. It is now a matter of being with evil or the holy spirit, not just politics.

And you diasporas please do not march to white house when we do so
just pray to God.
the solution for Ethiopia is in the hands of God.

Anonymous said...

መንግስት ለአንድ ግለሰብ(አቡነ ጰውሎስ) ብሎ በብዙ ድካም እየገነባ ያለውን የሰላምና የልማት ጉዞ ፈተና ውስጥ መጣል የለበትም ስለዚህ አቡነ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሱ ያሉትን በደል ሊቃወምና ከህዝበ ምዕመናኑ ጎን ሊቆም ይገባል፡፡በአንድ አቡነ ጰውሎስ ምክንያት መንግስት መጠላት የለበትም፡፡መንግስት አቡነ ጳውሎስን በማንሳትና ምዕመኑ የሚፈልገውን ጥሩ አባት እስኪሾም ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑን ሊያግዝ ይገባል፡፡

Anonymous said...

ሰላም ደጀሰላሞች
ሀሳባችሁን ባልቃወምም ከመንግስት ግን ከዚህ የከፋ ነገር እጠብቃለሁ፡፡ ለምን ብትሉ መጀመሪያውኑ በንግስት የዚች ቤተክርሰቲያን ህልውና ስጋቱ ነው፡፡ ህልውናዋ መቸም ቢሆን ያስፈራዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መጀመሪያውን በመንግስት ማንፌስቶ የተቀመጠ ነው፡፡ እስቲ የአቶ ገብረመደህን አረኣያን ቃለ-ምልልስ ከ you-tube ፈልጋችሁ አዳምጡ፡፡ የመንግስት አጀንዳ(Being Communist) እምነት የሌለው ህዝብ መፍጠር ነው፡፡ ከመንግስት ምንም ባንጠብቅ ጥሩ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ግን መከራዋ መብዛቱ ቃሉ ይፈፀም ዘንድ መሆኑን ስንቶቻችን አስተውለን ይሆን?!
እግዚኣብሔር የትንቢት መፈፀሚያ ከመሆን ይጠብቀን!

bre said...

Dear my respected brothers and sisters
It is clear that this is the act of go’v. if not we will
See what is going to happen .if the go’v is free of this
Revolution we will see when he change this ‘patriarc’ if not
He will stood up beside him and continue to destroy the church.
Enate mariam atleyin kifatachin bibezam
AB from hawwasa

bre said...

Dear my respected brothers and sisters
It is clear that this is the act of go’v. if not we will
See what is going to happen .if the go’v is free of this
Revolution we will see when he change this ‘patriarc’ if not
He will stood up beside him and continue to destroy the church.
Enate mariam atleyin kifatachin bibezam
AB from hawwasa

Anonymous said...

ላሜዳ ከአዲስ አባባ
እኔ አረቦች ጋር የሚደረገውን ነገር እኛ ሀገር ማየት የምፈልግ ሰው አይደለሁም ።እኛ እኮ የኦርቶዶክስ ልጆች ነን ካልን ለምን በአመጻ እናምናለን። ቤተክርስትያናችንን ነጻ የሚያወጣት የኛ በመንግስት ላይ የምናካሂደው አመጽ አይደለም። እሱ ያለው ቀን እስራኤልን ባህረ ኤርትራን በእግዚሐብሔር ሀይል በበትር መቶ እና ከፍሎ ያሻገራቸውን እንደ ሙሴ አይነት ህዝቡን የሚመራ አባት እስኪሰጠን ድረስ እግዚሐብሔርን በጾም፣ በጸሎት፣ መጠየቅ እንጂ ለሌላው በር የሚከፍት አይነት ከድጡ ወደ ማጡ የሚያሸጋግር ያልተመዘነ ሀሳብ ይዞ ሌሎች ሀገሮች ስላደረጉት እኛም ማድረግ አለብን ማለት ተገቢ አይመስለኝም። ለቤተክርስትያን መቆርቆር እና መወሰን ለየቅል ናቸው። በዚህ ጊዜ ቤተክርስትያናችን ሙሉ ሰላም አላት ብለን ለመናገር ባንፈቅድም አንጻራዊ ሰላም እንዳለ ግን ማወቅ አለብን። የኛን በመንግስት ላይ መነሳት ስናስብ ሌሎች ደግሞ አጋጣሚውን ተጠቅመው በእኛ ላይ እንደማይነሱብን ማን ያረጋግጥልናል። ስለዚህ የቤተክርስትያናችንንም ሆነ የሀገርን ሰላም የሚሰጠው ፣ እስከ አሁኗ ሰዓት የጠበቀን እግዚሐብሔር ስለሆነ ፣ ነገም በሰላም የሚጠብቀን ክፉ እንዳንሰማ የሚያደርግ እሱ ስለሆነ ቀን በቀን ስለሰላመችን ብንጸልይ ዮናስን ከአሳ-አንበሪ ውስጥ የሰማው አምላክ እኛንም ይሰማናል ብዬ አምናለሁ።
«እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።» ዳዊት 127፡1
እግዚሀብሔር በመቅደሱ ሆነው ሀላፊነታቸውን ያልተወጡትን ዲያቆናት ፣ቀሳውስት ፣ ሰባኪያንን ፣ ጳጳሳትን ሁሉንም በወንበሩ ላይ ለአገልግሎት ያስቀመጣቸውን የሚጠይቅበት ጊዜ ይመጣል። ሰይፉን የሚያነሳበት ጊዜ ሩቅ አይደለም የእሱ ትዕግስት ማለቂያ ስለሌለው ከዛሬ ነገ ይመለሳሉ ፣ በሰሩት ስራ ተጸጽተው ንስሀ ገብተው ልጅነታቸውን ይመልሳሉ እያለ እንጂ የማናችንም ስራ ከሱ ለአፍታ ተደብቆ አለመሆኑን ልናውቅ ይገባናል። እንዲህ ቤተክርስትያናችን ላይ ፣ እምነታችን ላይ ፣ ምዕመናን ላይ እንዳላገጡብን የዘሯትን ሳያጭዱ አያልፉም።
ቤተክርስትያናችን ላይ ያለው ችግር ይጻፍ ቢባል አባይን እንደ ቀለም ብንጠቀምበት የሚበቃን አይመስለኝም። ሲኖዶስ ውስጥ ሰላማቸውን ያጡ አባት ተብዬዎች እየገቡ እንዴት ሰላምን በቀላሉ እናግኛት።

Abel Yonatan Biruk said...

ደጀ ሰላሞች ሐይማኖትንና መንግስትን ነጠጣጥሎ ማየት ያስፈልጋል የቤተክርስቲያንን ችግር ለእግዚአብሔር ስጡ ሁሉንም እሱ በጊዜው ያስተካክለዋልና ነገር ግን ሌላ ድብቅ አላማ ካላችሁ ግልፅ አውጡ እንጂ ተከታዮቹን ወደ አላስፈላጊ ነገር ውስጥ እንዲገባ አትገፋፉት

Abel Yonatan Biruk said...

ደጀሰላሞች እባካችሁ መንግስትንና ሐይማኖትን ነጣጥላችሁ ተመልከቱ ሁል ጊዜ የችግሮች ምንጭ መንግስት ነው አትበሉ የቤተክርስቲያን ችግርን ለእግዚአብሔር ስጡ ምክንያቱም ያለእርሱ ፈቃድ የሆነ የለምና ነው

እያንዳንዱ ነገር በጊዜውም ይስተካከላል ለእርሱም በፀሎት ጠይቁ

ከዚህ ውጭ ግን መንግስት ነው መንግስት ነው አያላቸሁ ምእመናኑን ወደ አላስፈላጊ ነገር መገፋፋት ደግ አይደለም ከአንድ የእግዚአብሔር ሰው ነኝ ከሚልም አይጠበቅም

አቤል ከሐዋሳ

Anonymous said...

አዋሣዎች በትላንትናው እለት በቅ/ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን የምህላውንጸሎት በማስቆም የተበላሸውን የአቡነ ጳውሎስን አስተዳደር እና ደጋፊያቸው የሆነውን ወያኔን መቃወም ጀምረዋል። ሌሎች ምን እንጠብቃልን፡
ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው።

Anonymous said...

God bless our country and mk

gammachiis said...

GIZEW FIKIRE NIWAY ENA ZINA(KIBIR) YESEWN LIJ YETEKOTATEREBET MEHONUN ANIRSA. lezih misikir yemisha aymesilegnim(be hiywetachew ke amanawit KIDIST BETEKIRISTIAN wuchi yehonutin hulu: ye arebun alem meriwoch, ye mi'irabun alem alemawinet, protestantism, liberalism, gilobalization,... aramajoch, ye 'tehadiso' akenkagnochin,... temelketu). yegna mengist degmo ke mannim belay bezzih teteki new. lezzih new ewnetin(tarikin) kebro TEWAHDON bematlalat, akrari isliminaw YEMIYADERSEWUNIM BEDEL wede ewunetegnochu yetewahedo lijoch masakek yemikelachew. ahunim, YE TEWAHIDO LIJOCH! ijachinin wede EGZI'ABHEER inji wede mengist mezergat ayggebanim: የመንግስት አጀንዳ እምነት የሌለው ህዝብ መፍጠር ነው፡፡ mengist ye BETEKIRISTIANIN li'ilina defro, be hizbu zend teseminetuan atifto,...yerasun siltan lemadeladel yemmimechutin sewoch BEBETEKIRISTIANUA keffitegna botawoch lay bemaskemet le 20 ametat yetesakallet sira sertual(hizbochua wede alemawinet, protestantizim ,...indikeyeru hunetawochin amechachtual, ke arebu alemim yemmifelligewun genzeb agigntual...). wedefitim zegoch benetsanet hassabachewun yemmigeltubetin mediawochin(eg. dejeselam), le kiddist betekiristuan hilliwuna tegtew yemmiseru abbatochin inna wettatochin(eg. mahibere kidusan)ilama kemadreg wedehuala indemayl mulu bemulu irgitegnoch nen. midirawuan birr, zinna,...halafi tefi nachew: YeKiristian Hageru BESEMAY NEWUNNA ye TEWAHEDO LIJOCH BERTU!!!. SELFU YE ASHENAFIW YE EGZI'ABHEER NEW! BICHACHIN AYDELLENIM, ALEMIN YASHENEFU KIDUSAN, DINGIL MARIAM KEGNA GAR NACHEWNNA WEDEHUALA ANNIY, WEDEFIT INNIBERTA! EWNETECHOCHU YEBETEKIRISTIAN AGELGAYOCH HOY BERTU, LETIYAKEACHIHU MELSACHIN IJJIG FETTAN NEW!!!

Anonymous said...

yes you are right

Anonymous said...

መንግሥት መንግሥት የምትሉት መንግሥት ምን አደረገ መንም እንኳ ተበድለዋል ለሚባሉት ሃይመኖቶች ያህል ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ ጠበቃ ባይሆንላትም በተከበረው ሲኖዶስ ግለሰቦች (ጳጳሳት) በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን በሰዎች መንፈስ ቅዱሱን ሲኖዶስ ሲረብሹ ገብቶ አበረደ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሷ ሥርዓትና በነፃነት ፓትርያርክ እንደትሾም አደረገ፣ ደርግ ደፈረውን ክብሯን አልደግምም ብሎ በትግል ጊዜ ያወገዙትን ፓትርያርክ አሞኛል አልችልም ብለው ሥልጣን ሲለቁ አልገደላቸው አላሠራቸው፣ በክብር በቦሌ ተሸኝተው ወጥተው አሁን በሌላ ሥራ ተጠምደዋል፡፡ የአሁኑ መንግሥት ደርግ በግፍ የወሰደባትን የቤተ ክርስቲያን ንብረት መለሰ፣ ስንት የወጣት ማኅበር እንደፈለገ ተቋቋመ፣እዳንዱ እንደውም መተዳዳሪያ እስኪያደርገው ድረስ አሁንም በቤተ ክርስቲያነኗ ስም ይነግዳል፡፡ እኛ የተከበረው የውዱስ ሲሆደስ እኔስሙንም ለመጥራት ብቃት የሌለኝ የክርስቲያኖች ምክር ቤት ትቂት ሁሉም ባይሆኑ አባላት ለራሳቸው ቤት ከመሥራት፣ ዘመዶቻቸውን ከማበልጸግ፣ መኪና ከማማረጥ፣ በአንዲት ሴት ጉዳይ ከመራበሽ፣ በአንድ ምንም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በማይነካ ሀውልት ከመጣላት ለምን ስለመናፍቃን አንድም አጀንዳ የላቸውም፣ ለምን ስለ ስብከተ ወንጌል አጀንዳ የላቸውም፣ ለምን ስለ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት አጀንዳ የላቸውም፣ ለምን ስለ ቤተ ክረስቲያን አንድነት አጀንዳ የላቸውም፣ ለምን ስለ ገዳማት አጀንዳ የላቸውም፣ ልምን ስለ ሕገ ቤተ ክርስያን አጀንዳ የላቸውም፣ ለምን ስለ ድኅነት አጀንዳ ላቸውም፣ ለምን ስለ ቤተ ክርስቲያን የወደፊት ራዕይ አጀንዳ የላቸውም ያው እንግዲህ ከ2000 ዓመት ምህረት ጀምሮ ምንሰማው ጠብ ነው፣ እጅግ አየሁ፣ ሐውልት፣ ሥልጣን፣ ሹመት (ያሉት ሳይሠሩ)፣ ልዩነት አድማ …

በቸርነቱ በምህረቱ ኢትዮጵያን ይባርክ፣ እኛንም ይማረን

Anonymous said...

በፖለቲካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ ለመሪዎች መባረር ምክንያት እንደሆነው ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ምዕመኑ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው ይገባል።

Anonymous said...

በፖለቲካው ረገድ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ በኢ-ፍትሐዊ አስተዳደሮች ላይ የተደረገው ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ ለመሪዎች መባረር ምክንያት እንደሆነው ሁሉ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው በደል ማቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ምዕመኑ ወደዚህ ዓይነት ቁጣ ሊራመድ እንደሚችል መንግሥት ሊረዳው ይገባል።

Peace for EOTC said...

አንዳንድ የመንግስት ደጋፊዎች እና ደጀ ሰላማዊ መካሪዎች ስለቤተክርስቲያን ነጻነት አታዉሩ።እግዚአብሔር ነፃ እስኪያወጣችሁ ድረስ መጾምና መጸለይ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ ይሉናል። ጾም እና ጸሎት ትልቁ መሳሪያችን ነዉ። አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳው ጌታ ነው።ይህንን በደንብ እንረዳለን። እህቶቹም ግን ድርሻ ነበራቸው። ወደ እርሱ ማልቀስ እና ድንጋዩን ማንከባለል!!! እኛም ድንጋዩን እናከባልል እያልን ነው። አልዓዛር ከሞት አይነሳ ይበስብስ የምትሉ ጸረተዋህዶዎች እና ጭፍን ደጋፊዎች የቤተክርስቲያን ትንሣዔ ናፍቆናል ተውን።ይህ ጥያቄ ከዓመታት በፊት የተጀመረ እንጂ ወቅታዊ አመጽ አይደለም። አትፍሩ በዚህ ታኮ የሰሜን አፍሪካው አመጽ አይቀሰቀስም። ህልም ተፈርቶም ሳይተኛ አይተደርም። ለመንግስት እና ደጋፊዎች የሚጠበቅባቸው ጥቂት ነው። እጃቸውን ከቤተክርስቲያን ላይ ያንሱ። ውሾቻችሁን እሰሩልን።

Anonymous said...

ብዙ መናገር ባልፈልግም ሁሉም ሥራ ሆዳሞች የሚሰሩት ነው። ስለዚህ ሆዳቸዉን አንድመትኑ፣ ካልሆነ ግን !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Z'yismanigus said...

peace for EOTC!

U said what I was thinking and this is the only way we can keep our church from the internal enemies.If we can through-away this "Maoist" government,we will have the opportunity to think of our church.The same is true for Abune Paulos.The fate for EPRDF is in danger if the old man is not in his throne.Am sure they don't want to see 'religious' father in his place.In both case we are beneficial!!I think it already started ("the face book revolution") which is called YEDIL QEN,we should show our solidarity,courage,in such cases not as a politician but as a religious person since our fathers(ex bereketachew yidresen ena Abune petros....) were not politician,just to keep their country,religion from enemies.What is the difference now??
May God keep Tewahdo!!!Amen

Anonymous said...

ሀገር ቀርቶ የከተማ ያህል እንኳ የሰፋ አስተሳሰብ የሌላቸው በሰፈር የተከፋፈሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት፣ ስለ ሀገር ልማትና ለሕዝብ ደኅንነት ከመጨነቅ ይልቅ ለሥለጣን ብቻ የሚቋምጡ ግለሰቦች በበዙበት ሀገር የምንከፍለው ደም የለንም፣ አሁን ብንከፍል ወይም ብናምጽ አባይን ለመገደብ ነው

Anonymous said...

We Shall demonstrate against woyane.Every body weak up please!

Anonymous said...

God is with us let`s do some thing!

Unknown said...

እግዚአብሄር ሆይ በደምህ የገነባሃትን ቤትህን አፅዳልን፡፡ ይህንን ከግራኝ አህመድ ያላነሰ ጥፋት በቤተክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለውን ፓትሪያርክ አንሳልን፡አሜን፡፡
ተክለስላሴ
ከአዋሳ

Anonymous said...

I would say let's pray on this matter. I belive there are numerous cases in our church adminstration needs fixing, but chaos would not be a solution. Perhaps Abune Merkorios was have been the right Patriaric for our church

mebrud said...

In the name of Father and of the Son and of the Holy sprit one GOD.
አንዳንዶቻችን እንዴት አንብበን፣እንዴት ነው የምንረዳው ጎበዝ? በእርግጥ ሁሉም በአንድ አይነት መረዳት በተመሳሳይ ፍላጎት፣በእኩል የሃይማኖት ፍቅርና ተቆርቋሪነት አስተያየቱን እንደማይጽፍ እሙን ነው።አስተያየቶቹ ሲደበላለቁ ማን በምን ፍላጎት እንደሚጽፍ ለመናገር ያስቸግራል።በየመሐሉ፣ የሆኑ የማይመቹ ወይም የሚቆረቁሩ አስተያየቶች እየተሰነቀሩ ነገሩን ወደየግል አመለካከት ለመዘወር ሲሞከር አንባቢ በጥርጣሬ ሊያነበው ይገባል።ቤተክርስቲያን ከየትኛውም ወገን ጋር የምትጋረው ጭንቀት እንዳለ ሁሉ የማትጋራው ፍላጎት ስላለ አጀንዳ ባይዛነቅ መልካም ይሆናል።
የቤተክርስያንን ችግር የፖለቲካ ማስመሰል አይገባም፤ የፖለቲካውንም የቤተክርስቲያ አድርጎ ማቅረብ ደስ አይልም። ከአባቶች (ከሲኖዶስ )አልፎ መንግስት ሊፈታው የሚገባ የቤተክርስቲያን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ።የምዕመናን ድርሻ ከጸሎት ባሻገር በጽሞና ሊመከርበት የሚገባ ነው ነገር ነው።
ሁሉም ስለቤተክርስቲያን ሥርዓት እቆረቆራለሁ ብሎ ሌላ ሥርዓት እንዳይቀይስ ያሰጋል።ሁሉም እንደፈለገ ተናጋሪ ከሆነ አድማጭምኮ ግራ ይጋብል።ውሉን አታጥፉብን።ልብ በሉ ሲኖዶስ እስከመቀጠል ያደረሰን ‘ሥርዓት አንገብግቦን ነው’ ብንል ‘ፊቴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ’ በማለትም ነው ተብሎ እማኝና መረጃ ሊጠቀስብን ይችላልና ውስጠ ወይራ አስተያየቶች ጭምር ሳንመረምር አጨብጭበን የምንቀበል ከሆነ የዋሆች ነን ማለት ነው።
ለሀገሪቱም ሰላምም ሆነ ለቤተክርስቲያኗ ጤነኛውን ተቋማዊ ጥያቄ ላይ የግል ወይ የቦርድ አስተያየት ባንደባልቅበት መልካም ነው።ድምጽ እንዲበዛ ከሆነ ችግርም አለበት። እግዚአብሔር በራሱ ልጆች ይሰራል።ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው ።መድኃኔዓለም ሲሰራ በኃይለኞች ላይ አይደመርም።
ማኅበረ ቅዱሳን ተቀባይነት የሚኖረው ለአሐቲ ቤተክርስቲያን ለዶግማዋ ለቀኖናዋና ለትውፊቷና ለአንድነቷ ባሳየው ተቆርቋሪነት ነው፤ የብዙዎቻችንን ቀልብ የገዛው ሳይቀላቅል ስለቀና ነውና አንቀላቅል።ሥጋችን ከመንፈሳዊነታችን ሲልቅ አጀንዳውን ከመንፈሳዊነት አውጥቶ ሥጋዊ መፍትሔ ላይ ይጥለዋል።በቋንቋው ስንጠቀም ራሱ ስሜትንና እውነትን ሳያጋጭ እንጠቀምበት ዘንድ ወሳኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።በተለይ እንደቤተክርስቲያን ልጅ ‘ደርግ” ና” ወያኔ” ዘይቤን ስንጠቀም ያሳቅቃልና ቢታሰብበት።ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን። ቆላ 4፡6 አንዲል ቃሉ።
ቁጭት ልክ ሆኖ የምንገልጽበት አገባብ በስሜት እንደመጣልን ወይም እንደመጣብን የሚያጽፈን ከሆነ አንባቢውን የሚያበሳጭ ስለሚሆን ደጀሰላም በEditing ተባበሪን።የቤተክርስቲያንን ለቅሶ ዓለም አያለቅስላትም።ካለቀሰም ለቢZነሱ ።ሃይማኖታዊን ጎትቶ ፖለቲካዊ፤ፓለቲካውን ጎትቶ ሃይማኖታዊ የማድረግ ነገር በሌሎች መካነ ድሮች እንደምናነበው ሊሆን ነው።እንዴትስ ነው የምንለየው?በአንድ ወቅት በደጀሰላም እንዳነበብኩት "በሲዖል በኩል ወደ ገነት" ዓይነት እንዳይሆን ወገኖቼ። የቤተክርስቲያንን ሐዘን ፖለቲከኛም፣ዘረኛም፣ጽንፈኛም፣መናፍቅም ሲያለቅሰው ከጸሎት ወደቀረርቶ ይሸጋገራል። የቤተክርስቲያንን ምስጋና መንገደኛው ሲነጥቀው ዜማውን ከያሬዳዊ ወደ ምድራዊ(አለ ወይ አትበሉኝና) ይወስዱታል። ቅኝቱም ይፈርሳል፣ዜማውንም ይሰብራል፣ንባቡንም ይዘነጥላል፣ቋንቋውም ይነትባል።ይኼ ደግሞ ያደክማል ። በግልጽነት አሰተያየት ለመጻፍም ያስጨንቃል።ለማንኛውም በቀረችን ሱባኤ በጸሎት እንጩኽ።ጸጥ እንዲያደርግልን።
Amen.

Anonymous said...

@mebrud.
u r true christian

Anonymous said...

ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥...። ቆላ 4፡6 አንዲል ቃሉ።

"ማኅበረ ቅዱሳን ተቀባይነት የሚኖረው ለአሐቲ ቤተክርስቲያን ለዶግማዋ ለቀኖናዋና ለትውፊቷና ለአንድነቷ ባሳየው ተቆርቋሪነት ነው፤ የብዙዎቻችንን ቀልብ የገዛው ሳይቀላቅል ስለቀና ነውና አንቀላቅል።" said Mebrud.

Had St. Paulos composed a falsified preaching like you posted the above? (your core message spiced by many yeasts)

Anonymous said...

@mebrud
Thank you for your comment. I also afraid not to cross the border btwn the religion and politics.

However, I always see those people are also actively involved in the politics while they are in the church's leadership - both inside and outside of Ethiopia.

I believe that we should not mix though I am not sure how it could be done. Any ways, I support your solution: አንቀላቅል

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)