April 29, 2011

“የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” (Orthodox Photo Bank Service):- ማስታወቂያ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 29/2011)፦ በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎች የምናገኝበት ጠንካራ ድረ ገጽ ስለሌለን በዚህ ቴክኖሎጂ ዘመን ከሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሲነጻጸር ወደ ሁዋላ ቀርተናል ማለት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት እንዲቻል “ደጀ ሰላም” የጀመረችውን የድረ ገጽ ጡመራ እና የመረጃ ልውውጥ የበለጠ በማጠናከር ለመቀጠል እንድትችል አንባብያንን የሚከተሉትን ነገሮች ይልኩላት ዘንድ በትህትና ከጋበዘች፣  “የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” ((Orthodox Photo Bank Service) ብላ ከጀመረች ድፍን አንድ ዓመት ሞላት። “ፎቶ ባንክ” ያልነው ፎቶዎችና ቅዱሳት ሥዕላት የሚጠራቀሙበት “ግምጃ ቤት” ለማለት ነው።

መግነዙን በመቃብር ትቶ የመነሣቱ ምሥጢር!

(ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ):- ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በእውነት ተነሥቷል፡፡ ሲነሣም ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን የገነዙበትን ከተልባ እግር የተሠራ ንጹሕና ድርብ በፍታ የመግነዝ ጨርቅ (ከፈን) በመቃብር ትቶ ነው፡፡ መተዉ ብቻ ሳይሆን በፍታው በመቃብሩ ውስጥ በጣም በተሰናዳ መልኩ ተቀምጦ ነበር፡፡ ወንጌል ስለዚህ ነገር እንዲህ ትላለች ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ መቃብሩ በገባ ጊዜ ‹‹በራሱ ላይ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምቶ እንዳልነበረ አየ›› (ዮሐ20.7)::  ለመሆኑ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መግነዙን በመቃብር በዚህ መልኩ ትቶ የመነሣቱ ምሥጢር ምንድር ነው@ ይህን በሚገባ መረዳት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ ምክንያት የተቀመጠ አንድም ቃልና ፊደል እንዲሁም የተከናወነ ትንሽ ተግባር እንኳን እንደሌለ ያስረዳናልና በአትኩሮት እናንብበው!

April 27, 2011

በዓባይ ወንዝ ላይ ቤተ ክርስቲያን የነበራት ታሪካዊ ሚና ምን ነበር፤ አሁንስ ምን ዓይነት ሚና መጫወት ትችላለች???

(በፍቅር ለይኩን  ከደቡብ አፍሪካ):- የታሪክ መዛግብትና ሊቃውንት የሚነግሩን ታላላቅ የዓለማችን ሥልጣኔዎች መነሻ ወንዞች እንደሆኑ ነው። በዚህም በዓለማችን ታሪክ በግንባር ቀደምትነት ከመዘገባቸው ታላላቅ ሥልጣኔዎች (The Great World Civilizations) መካከል የሜሴፖታሚያ፣ የፋርስ፣ የባቢሎን፣ የግብጽ፣ የቻይና፣ የአሲሪያን፣ የግብጽና የእኛይቱ ኢትዮጵያ ሥልጣኔዎች መነሻ ወንዞች እንደሆኑ ልብ ይሏል። ለእነዚህ ግዙፍ ሥልጣኔዎች ከፍተኛውን ሚና ካበረከቱት ወንዞች መካከል የኤፍራጥስና የጤግሮስ፣ ያንጊቲዝና የቢጫ፣ አማዞንና ዓባይ/ናይል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

April 26, 2011

የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጅምር ከዳር ለማድረስ እንርዳ

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 25/2011)፦  ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጀመሯቸውን ፕሮጄክቶች ለመርዳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ የራት ግብዣ በአሜሪካ መዘጋጀቱን ይህንኑ በማስተባበር ላይ የሚገኝ አንድ ማኅበር አስታወቀ። “ዝክረ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ” የሚሰኘው ይኸው ማኅበር ዝግጅቱን ያስተዋወቀበትን ደብዳቤ ከዚህ በታች ያቀረብን ሲሆን እኛም በበኩላችን የእኒህን ታላቅ አባት ጅማሮዎች እውን በማድረግ ስማቸው ከመቃብር በላይ ይውል ዘንድ መርዳት አለብን ብለን እናምናለን። “መጥፎ ሥራ ላይ የተሰማሩትን መቃወም ብቻ ሳይሆን ደግ የሚሠሩትንም በመርዳት መበርታት አለብን” እንላለን። በተለይም በአሜሪካ የምትገኙ ክርስቲያኖች የተዘጋጀውን ካርድ በመግዛት፣ በቦታው መገኘት ባትችሉም እንኳን የሚገኙትን እና የሚሠሩትን ለማበረታታት ቲኬቱን በመግዛት የበኩላችሁን ማድረግ አለባችሁ። በሌሎች የዓለም ክፍሎች የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንም እንዲሁ። ዝርዝሩን ከዚህ በታች ተመልከቱ።

April 23, 2011

የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ


 «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡  መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡  «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡ «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡ አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡ ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡ ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡ አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የእርሰ ትምህርታችንም መሠረት ይኸው እንደሆነ ይታወሳል፤ ብለን ተስፋ አናደርጋለን፡፡  ዐምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

April 16, 2011

በዴር ሡልጣን ገዳም መንግሥታዊ ትእዛዝ የተሰጣቸው አቡነ ማቲያስ ከባለሥልጣናት እና ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ ነው


 • ሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ጥሪ ቀርቧል
አቡነ ማቲያስ
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 16/2011)፦  በዴር ሡልጣን ገዳም “የኮፕት መነኩሴ በቀዳም ስዑር ሻማ አብርቶ ይዞ ይለፍ” የሚል መንግሥታዊ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ ነው:: በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ እና ማኅበር አባላት ግብጻዊው የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መነኩሴ በበዓለ ትንሣኤ ዋዜማ (ቀዳም ሥዑር) ከጎልጎታ - የጌታ መቃብር ሻማ አብርቶ ይዞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ይዞታ በሆነው በዴር ሡልጣን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ገብቶ በመድኃኔ ዓለም እና አርባዕቱ እንስሳ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለውስጥ አልፎ ወደ ኮፕቲክ ገዳም እንዲገባ ፈቃድ እንዲሰጠው ካዘዙት የእስራኤል መንግሥት ባለሥልጣናት እና ትእዛዙን በግድ ለማስፈጸም ከሚዝቱት የብሉይ ከተማ ኢየሩሳሌም ፖሊሶች ጋራ እየተከራከሩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

April 15, 2011

የቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ እና የመ/ኮሌጅ ደቀመዛሙርት ደብዳቤ (ሪፖርታዥ)


 • ማኅበረ ቅዱሳን ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ጋራ ለመወያየት የኮሌጁን አስተዳደር ጠየቀ
 • “ፕሮቴስታንታዊውን የተሐድሶ ኑፋቄ ወጥመድ የሚያጋልጠው ሰነድ ሲም የተባለ የተሐድሶ ድርጅት በአጭር ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ለመውረስ የቴዎሎጂ ት/ቤቶችን ማእከል አድርጎ ለመንቀሳቀስ የያዘውን ዓላማ የሚያጋልጥ እንጂ ኮሌጁን እንደ ተቋም የሚወነጅል እንዳልሆነ በበለጠ ግልጽነት ሊሠራበት ይገባል፡፡” (ብዙኀን የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት)
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 15/2011)፦  ረቡዕ፣ ሚያዝያ አምስት ቀን 2003 ዓ.ም በአስቸኳይ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የምልአተ ጉባኤውን ሥልጣን እና ክብር የሚያስጠብቁ አንፀባራቂ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ከትናንት በስቲያ ማምሻውን ከተጠናቀቀ በኋላ ቁጥራቸው ከ40 ያላነሱ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በፓትርያርኩ ጽ/ቤት በመገኘት ባለስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ዝርዝሩ እነሆ።

“ደጀ ሰላም” እንድትዘጋ ለፓትርያርኩ ጥያቄ ቀረበ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 14/2011)፦  በቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመምሪያ ሓላፊዎች እና በመንፈሳዊ ኮሌጆች ደቀ መዛሙርት ላይ ያደርሳል ባሉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት መንግሥት “ደጀ ሰላም” ላይ ርምጃ እንዲወስድ የአቤቱታ ደብዳቤ ለቅ/ፓትርያረኩ ቀረበ። አቤቱታውን ትናንት ረቡዕ ለቅዱስነታቸው ያቀረቡት በቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚማሩ የተወሰኑ ደቀመዛሙርት ሲሆኑ የኮሌጁ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እንቅስቃሴውን ተቃውመዋል ተብሏል።

April 14, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ተጠናቀቀ


 • እነ ንቡረ እድ ኤልያስ በአጣሪ ኮሚቴው ስም ባቀረቡት ሪፖርት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከሐዋሳ እንዲነሡ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሓዋሳ ማእከል እንዲዘጋ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።
 • ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ጠንካራ ሥራ አስኪያጅ ከሁለት ረዳቶች ጋራ ተመድቦላቸው ባሉበት ሀገረ ስብከት ይቀጥላሉ፤
 • ሦስት የአጣሪ ኮሚቴው አባላት ማኅበረ ቅዱሳንን የቤተ ክርስቲያን ካልሆኑ አካላት ጋራ ደምረው ለመክሰስ ያደረጉትን ሙከራ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች ብፁዓን አባቶች ተቃወሙ፤
 • “በሓላፊነቴ የራሴ መረጃ አለኝ፤ ለምንድን ነው ማኅበሩን የችግር ምሕዋር ውስጥ የምትከቱት?” (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ)
 • በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ደቀ መዛሙርት ስም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የቀረበው የክስ አቤቱታ በኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ፣ ምክትል አካዳሚክ ዲን እና ሌሎች ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው
 • “ፕሮቴስታንታዊውን የተሐድሶ ኑፋቄ ወጥመድ የሚያጋልጠው ሰነድ ሲም የተባለ የተሐድሶ ድርጅት በአጭር ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ለመውረስ የቴዎሎጂ ት/ቤቶችን ማእከል አድርጎ ለመንቀሳቀስ የያዘውን ዓላማ የሚያጋልጥ እንጂ ኮሌጁን እንደ ተቋም የሚወነጅል እንዳልሆነ በበለጠ ግልጽነት ሊሠራበት ይገባል፡፡”(ብዙኀን የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት)
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 14/2011)፦  በአስቸኳይ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የምልአተ ጉባኤውን ሥልጣን እና ክብር የሚያስጠብቁ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ማምሻውን ተጠናቀቀ፡፡ ከሃያ ያላነሱ አባላት በተገኙበት ረቡዕ ጠዋት በተከፈተው አስቸኳይ ስብሰባ መጀመሪያ ላይ በዐባይ ወንዝ ላይ ለሚሠራው ለታላቁ ሚሌኒየም ግድብ ግንባታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የአንድ ወር ሙሉ ደመወዛቸውን ለማበርከት ተስማምተዋል፤ በዚህ ረገድ ምእመናን እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በቀጣይነት በተለያየ መልክ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ለማበረታት ተወስኗል፡፡

April 13, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ በሐዋሳው ውዝግብ እና ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ ሥራ ስለሚደረገው አስተዋፅኦ ይወያያል


 • የሐዋሳው ችግር አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ዝግጅት በአባላቱ የሐሳብ ልዩነት ሳቢያ  አልተጠናቀረም፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያዘው አቋም ዋናው የልዩነቱ ነጥብ ነው።    
 • የአቡነ ጳውሎስ - አባ ሰረቀ ኮርፖሬሽን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጀው የ‹ብጥብጥ አፋልጉኝ› እና የውንጀላ ዘመቻ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቢዛመትም አሳፋሪ ገመናው እያደር በመጋለጥ ላይ ነው።
 • ከትላንትና ጀምሮ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ስም ‹‹ለሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ  ይቀርባል›› የተባለ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚከስ የአቤቱታ ፊርማ ተሰባስቧል፤ ለፊርማ  ማሰባሰቢያው ቅስቀሳ ላይ የዋለው ምፀታዊ ስልት ‹‹ያልፈረመ ተሐድሶ ነው›› የሚል ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ አወጡት ከተባለው ባለአምስት ነጥብ የአቋም  መግለጫ አንዱ ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የታላቁን የሚሌኒየም ግድብ ግንባታን ይቃወማል›› የሚል እንደ ሆነ ተገልጧል። 
 • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት የአስተዳደር ሠራተኞች እና አገልጋዮች ለታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን  በዓመት ለማበርከት ወሰኑ፤ የአባ ሰረቀን ሰርጎ ገብ አጀንዳ ተቃውመዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 13/2011)፦  ማክሰኞ ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግፊት የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ፡- በሲዳማ ጌዲኦ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በተፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት፣ በሐዋሳ ሦስት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተከሠተው አስተዳደራዊ ብልሽት እንዲሁም ይህን ተከትሎ በተባባሰው ሁከት እና ውዝግብ ላይ እንደሚወያይ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አመለከቱ፡፡

“ሥላሴ አትበሉ፣ እግዚአብሔር አትበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ” (በጋሻው)


የንፍሮ ቀቃይ ልጅ?ሰው ባለማወቁ መሰደብ አለበት? ያውም በዐውደ ምሕረት ላይ? በዚህ መቼ በቃው። ሥላሴ፣ እግዚአብሔር ወደዛ ወደዛ አትበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ” ሲል ማንም ተርታ ምእመን ሊፈጽመው የማይችለውን የድፍረት ንግግር አቅርቧል። የሚገርሙት ከኋላ ተደርድረው የተቀመጡት ጉዶች ናቸው። ልብሳቸውን አሳምረው ነገረ ተዋሕዶ እንዲህ ሲዘነጠል እና ሲቃለል መስማታቸው። ምን ዓይነት ዘመን ነው? በዚህ የምድር ጉድ እንጭጭ መናፍቅ ጉዳይ ይህንን ያህል ጊዜ ማጥፋታችን በራሱ ትልቅ ጥፋት ነው። 

April 12, 2011

ሰበር ዜና፦ ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶስን ለአስቸኳይ ጉባኤ እየጠሩ ነው፤ ብዙዎች አባቶች አይገኙም(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 11/2011)፦  ዓመታዊው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ከሚካሄድበት ከግንቦት ርክበ ካህናት አስቀድሞ አስቸኳይ የተባለ ጉባኤ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተጠራ መሆኑ ታውቋል።  አጠራሩ ተገቢነት የለውም በሚል አባቶች  ተቃውመዋል ተብሏል። የሐዋሳውን ውዝግብ ለመፍታት በሚል እየተጠራ ባለው በዚህ ጉባኤ የተያዘው የሐዋሳ ችግር ጉዳይ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚችል እየታወቀ እና እየተጠበቀ በአቋራጭ የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተጠራው በዚሁ አጋጣሚ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተዘረጋባትን የተሐድሶ ወጥመድ ይፋ አድርጓል የተባለ “ሰነድ” ይፋ ሆነ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 5/2011፤ ጥር 29/2003 ዓ.ም)፦ ከ1920ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እና ትውፊት በመለወጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እና መዋቅሮች ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሠሩ የተሐድሶ ኑፋቄ ማኅበራት እና ድርጅቶች በተለዋዋጭ ስልቶች ሲማስኑ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ጥረታቸው ያሰቡትን ያህል ያልተራመደላቸው የተሐድሶ መናፍቃኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ‹‹ከውስጥ እያጠቁ ወደ ውጭ በመገስገስ እና ከውጭ ከበባውን አጠናክሮ ወደ ውስጥ በመግፋት›› ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አልያም ውጥንቅጧን አውጥቶ ለሁለት ለመክፈል ስልት ቀይሰው፣ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማእከል አድርገው በመንቀሳቀስ ላይ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ሰነድ ሰሞኑን ለደጀ ሰላም ደርሷል፡፡

April 11, 2011

ቋሚ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚያስጠብቅ እና ሕዝቡን የሚያረጋጋ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች ጠየቁ

 •   ቋሚ ሲኖዶስ ረቡዕ በዚህ ጉዳይ እንደሚነጋገር ይጠበቃል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 11/2011)፦ በጥቂቶች ማስፈራሪያ ተልእኮውን ሳያጠናቅቅ የተመለሰው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ መፍትሔ እንዲፈለግ አለመደረጉ የሐዋሳን ምእመን እና ውጤቱን በገለልተኛነት የሚጠባበቀውን የክልሉን መንግሥት በእጅጉ እንዳሳዘነ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች ገለጹ፡፡ “ጉዳዩን እንዲያጣራ የተላከው የጳጳሳት ኮሚቴ ለአምስት ቀናት ብቻ ቆይታ በማድረግ የማጣራት ሥራውን ሠርቶ በተከታዩ ሦስት ቀናት ውስጥ ምላሽ ታገኛላችሁ ቢልም ሀገረ ስብከቱ ያለ መሪ ባዶውን እንደሚገኝ” ተወካዮቹ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ ባሰሙት ባለአራት ገጽ የጽሑፍ ማሳሰቢያ ላይ አመልክተዋል፡፡

April 5, 2011

Axis Of Corruption & Tehadiso!!

ስለ እግዚአብሔር ክብር…


ሁሉም በአግባቡና በሥርዐት ይሁን፡፡  (1ኛ ቆሮ.14፥40)
(ወልደ ያሬድ አበ ማቱሳላ):- የአድዋ ድል መታሰቢያ ዕለት ነው፤ በጾም ወራት መንገድ ከመሔድም መጾም ይገባል ብዬ እኔ መንገደኛው ወደ መንፈሳዊ ጉባኤ ታደምሁ፡፡ ቀኑ ብሔራዊ በዓል በመሆኑ ሥራና ትምህርት ስለሌለ ጉባኤው በጊዜ እንዲጀመርና ብዙ ምእመናን እንዲታደሙ ምክንያት ሆኗል፡፡ ጉባኤው ከተጀመረ በመድረሴ የመጀመሪያው ትምህርት ወደ መጠናቀቁ ነበር፡፡ መርሐግብር መሪው ዐውደ ምሕረቱን እንደተረከቡና መዝሙር መዘመር እንደተጀመረ ግን ግራ የሚያጋባ ነገር ገጠመኝ፡፡

April 1, 2011

ውድ ደጀ ሰላማውያን፤ የፌስቡክ “ጓደኞቻችን” ቁጥር 5 ሺህ በመሙላቱ አዲስ ሰዎችን መጨመር አንችልም። ስለዚህ አዳዲሶችም ሆናችሁ የቀድሞ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ከዚህ በታች ያለውን "Like" የሚለውን ቃል በመጫን በዚያ እንድትከታተሉን በትህትና እንጠይቃለን።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)