March 10, 2011

የዓድዋው ድል ታሪካዊ ፋይዳ

ፎቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ
‹‹ትልቁ አደጋ የተጋረጠበት የኢትዮጵያ ታሪክ ይመስለኛል›› (አቶ ሽመልስ ቦንሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር)
(ሔኖክ ያሬድ ለሪፖርተር ጋዜጣ):- ለኢትዮጵያውያን በተለይም ለጥቁሩ ዓለም ፈርጥ የኾነው በኢጣሊያ ላይ የተመዘገበው የዓድዋ ጦርነት ድል በያመቱ የካቲት 23 በመጣ ቁጥር በታላቅ ክብር ይዘከራል፡፡ ዘንድሮም ለ115ኛ ጊዜ ሲከበር ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ፣ ከአፍሪካ እስከ መዲናዋ ኢትዮጵያ ድረስ በልዩ ልዩ መልክ ተከብሯል፡፡ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣም ከ115 ዓመት በፊት የዘገበውን አካትቶ ያቀረበው መሰናዶም ነበር፡፡ በኢትዮጵያም ከተለምዷዊ አከባበር በተለየ መልኩ በዓድዋና በአዲስ አበባ ዐውደ ጥናቶች ተዘጋጅተው ነበር፡፡

የካቲት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት የተዘጋጀውና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ጨምሮ ሌሎች በተጋበዙበት መሰናዶ የድሉ ታሪካዊ ፋይዳ ተተንትኖ ነበር፡፡

የዓድዋው ድል ኢትዮጵያዊ ማንነት ተጠብቆ እንዲኖር በማድረግ በኩል የላቀ ተግባር ተከናውኖበታል፡፡ ይሁን እንጂ በአሁን ዘመን ለታሪክ እየተሰጠ ያለው ቦታና ይዘት እንዲሁም ሀገራዊ ዕውቀት አደጋ ላይ መውደቁ በዕለቱ በተለያዩ ምሁራን ተንፀባርቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት አቶ ሽመልስ ቦንሳ እንደተናገሩት፣ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በተለይም ከ19ኛው ክፍለ ዘመን፤ ፈረንጆች በብዛት መግባት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶችና ሐሳቦች በአደጋ ላይ ነበሩ፡፡ በተለይም ከግሎባላይዜሽን መምጣት ጋር ተያይዞ እነዚሁ ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶችን በውጫዊ ዕውቀቶች የመተካት ነገር መፈጠሩ ትልቅ አደጋ ነው፡፡

አቶ ሽመልስ አጽንዖት ሲሰጡበትም እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹በተለይ ትልቁ አደጋ የተጋረጠበት የኢትዮጵያ ታሪክ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ በብዙ ቦታ መማር ያቆምን ይመስለኛል፡፡ እና የኢትዮጵያ ታሪክን እንደገና መማር ካልጀመርን፣ የኢትዮጵያ ታሪክ በኢትዮጵያውያን ሲጻፍና ኢትዮጵያውያን በሚያዩት ዓይን እንደገና ተጽፎ መማር ስንጀምር፣ ምናልባትም እያጣነው ያለውን ማንነት ልናገኝ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ታሪክ በፈረንጆች ተጽፏልና፡፡››

የታሪክ ምሁሩ፣ ‹‹ችግሩ ፈረንጆች ስለጻፉት ሳይሆን ታሪካችን በፈረንጆች ዓይንና መነጽር መታየቱ ነው፡፡ በራሳችን ዓይን ማየት የምንጀምርበት፣ በራሳችን መንገድ መጻፍ የምንጀምርበት ጊዜ ከመቼውም በበለጠ አሁን ነው፤›› በማለትም ያክላሉ፡፡ ‹‹ታሪክ አይጠቅምም›› የሚል ነገር ሲወራ መሰማቱ ደግሞ ትልቅ አደጋ መሆኑና ፖለቲካዊም ፋይዳ እንዳለው ይህም ሰዎች ታሪክን በሁለት መንገድ ከሚመለከቱበት አንፃር እንዲህ ፈክረውታል፡፡

‹‹በገጠር ውስጥ ሰዎች ሲተኙ የሚደገፉበት ብርኩማ አለ፡፡ እኛ ታሪክን በዚያ መንገድ እንደመተኛ አድርገን አናየውም፤ ማየትም የለብንም፡፡ ማለት ተመችቶን ያንን ትራስ ተደግፈን እንድናንቀላፋም አይደለም፡፡ እኛ የምንፈልገው ይኸ በፊዚክስ ትምህርት ትልቅ ከባድ ዕቃ ለማንሣት የምትገባ ነገር አለች፡፡ ታሪክ እንደዚያ ማለት ነች፤ ወደፊት የሚያስፈነጥር፣ መሣርያ አድርገን መመልከት እንጂ ሁልጊዜ ስለታሪክ ብቻ እያወራን ወደኋላ እንድንመለስ አይደለም፡፡ ማስፈንጠርያችን ነውና፡፡ ወደፊት የሚሮጥ ሰው ወደ ኋላ ትንሽ ይሔዳልና በዚያ መንገድ ማየት አለብን፡፡››

አቶ ሽመልስ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነው›› የሚለውን አገላለጽም ተቀባይነት የሌለው ነው ይላሉ፡፡

‹‹ብዙ ሲነገሩን የነበሩ፣ እንደ ዕውቀትም የተሰጡንን ነገሮች እንደገና መጠየቅ አለብን፡፡ አንደኛው መጠየቅና መመርመር ያለብን ስለኢትዮጵያ ታሪክ እንደ መግለጫ የሚሰጠው፣ የጦርነት ታሪክ የሚለው ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት አይደለም፤ የመስዋዕት ታሪክ ነው ብዬ እመለከተዋለሁ፡፡››

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓድዋ ድል የነበራትን ሚና አስመልክቶ ጥናት ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር አቶ መንግሥቱ ጎበዜ እንዳሉት፣ የአሁን ትውልድ እንዳባቶቻችን ተመሳሳይ ታሪክ ባንሠራ እንኳ ታሪክና ቅርስን መጠበቅ ከእኛ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ እንደሚባለው፣ ‹‹ታሪኩን የማያውቅ ልጅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ በማያውቅ ልጅ ይመስላልና፡፡››

ሁልጊዜ ያባቶቻችንን ታሪክ እየተረክን ከመኖር ይበልጥ እኛም ታሪክ መሥራት አለብንም ብለዋል፡፡

አንዱ ተናጋሪም (በሕክምና ዓለም ውስጥ ያሉ ናቸው) ንግግራቸውን ሲጀምሩ፣ ታዳሚውን፣ ‹‹እስቲ የግብረ ገብ (ሞራል) ትምህርት የተማራችሁ እጃችሁን አውጡ›› በማለት ጠየቁ፡፡ ከአንድ ሁለት ሰው የዘለለ ያወጣ ስላልነበረ፣ ‹‹መልሱ ይኸ ነው›› አሉ፡፡

በእርሳቸው አነጋገር፣ አንዳንድ ሐኪሞችን ስጠይቃቸው ዓድዋ የት ነው? ስላቸው የሚቸገሩ አሉ፡፡ ዓድዋ በኢትዮጵያ ስለመሆኑ እናውቃለን፡፡ ዓድዋ የት ነው ሲባል ግን ሞያሌ፣ አሥመራ፣ ጎጃም ወዘተ. በማለት የሚቸገሩ አሉ፡፡ ምክንያቱም አልተማርነውምና፡፡

አሁን እኛ ከ115 ዓመት በፊት የተደረገ ነገር እምን ድረስ ይሰማናል ብለው ጠይቀውም እዚያው መለሱ፡፡ ‹‹አይሰማንም፤ ምክንያቱም የታሪክ መምህራንና ተማሪዎቹ ያውቁ እንደሆነ ነው እንጂ፣ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ታሪክን መማር አቁመናል፡፡ ከጓደኛዬና ከታሪክ መምህራን ስለቀሰምኩ ነው እንጂ ብዙ ነገር አላውቅም፡፡ የግብረ ገብ ትምህርት በምማርበት ጊዜ ያኔ የተማርኩትን ነው ይዤ የቆየሁት፡፡››

ሌላው አስተያየት ሰጪም፣ በዓድዋው ፍልሚያ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ሚና ያወሱበት መንገድም አለ፡፡

‹‹ከብዙ መንግሥታት ጋር አያይዘው ሲከሱ ወይም ሲወነጅሏት የማያዩዋቸው ወይም ሊያይዋቸው የማይፈልጓቸው ብዙ ነገሮችን እናስታውሳለን፡፡ በዚህች አገር ውስጥ በሁለመናዋ ነገር ጠላት በመጣ ቁጥር የምትከፍለውን ዋጋ፣ ወይም የከፈለችውን ዋጋ፣ የምታጣውን ቅርስ ወይም የሚፈርሱባትን አብያተ ክርስቲያናት ወይም ደግሞ የሊቃውንቱ መታረድ መሞት የሚያስታውስ ብዙ የለም፡፡ ያም ብቻ አይደለም፡፡ የምንጽፍም፣ የምናነብም ማየት የሚገባን ነገር አለ፡፡››

ከዓድዋ ድል ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማስቀመጥ እፈልጋለሁ ያሉት ተናጋሪ አንደኛው በወቅቱም ሆነ በረዥም ዘመናት ስለሀገሪቱ ብሔርተኝነት ብሔራዊ ስሜትን ከማሳደግ ረገድ ከአስተምህሮዋ ጋር አያይዛ ያደረገቻቸው ነገሮች መኖራቸውንም አመልክተዋል፡፡

ሁለተኛው አስተዋጽዖዋ ያሉትም በወቅቱ ለሠራዊቱም ሆነ በአጠቃላይ ለዘማቹ የነበረው የድርጊትና የሞራል ማዕከል ቅቡልነቷን ያመላከተ ነበረ፡፡

በእርሳቸው አነጋገር፣ ከሚታወቀው ሃይማኖታዊ እሴት ባሻገር ለዚህች አገር ብሞትላት፣ ብታገልላት መስዋዕትነት ብከፍልላት አምላክ በሰማይ ላይ ዋጋዬን ይከፍልልኛል ብሎ እንዲያስብ የሚያደርጉ አላባዎች (ኢለመንቶች) ነበሩበት፡፡
‹‹ደህና ሁኚ ድጓ፣
ደህና ሁኚ ቅኔ፣
ጀግኖች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፤›› እያሉ ካህናቱ በውጊያው ዐውድ እየተከታተሉ ንሥሐና ቀኖና ይሰጡ ስለነበር ሠራዊቱ ከሃይማኖታዊ ዋጋ ባሻገር ሰማዕትነትን የመቀዳጀት ፍላጎቱ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ ‹‹እኔ ሰማዕት ነኝ›› የሚል አንድምታም ነበረው፡፡

ሰዎች በየትኛውም መልኩ አሸናፊ የሚሆኑት የሞራል ልዕልናን ገንዘብ ሲያደርጉ ነው፡፡ የታቦታቱ፣ የሥዕሉ፣ የመስቀሉ፣ የድባቡ ደግሞ በባሕርያቸው የሞራል ልዕልና የሚጨምሩና ሠራዊቱን ወደፊት የሚገፉ ነበሩ፡፡

በአስተያየት ሰጪው ትርጓሜ፣ እነዚህ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦች እንደ አስተዋጽዖ እንወስዳቸዋለን፡፡ የእነዚህ አስተዋጽዖ ድምር ውጤት ሁለት መሠረታዊ ጥቅሞችን እንድናገኝ አድርጎናል፡፡ አንደኛው እንደ አገር፣ የኢትዮጵያውያኑ አስተዋጽዖ መሠረትነት ሠራዊቱ ድሉን ተቀዳጅቶ፣ ጠላቶቹ ተሸንፈው አገሪቱም የጥቁር ሕዝቦች የነፃነቱ እንቅስቃሴ የድርጊትና የሞራል መሠረት አስይዟል፡፡

እንደ አገር ለጥቁር አፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት በመሆን ነፃነታቸው ከገዢዎቻቸው ነፃ እንዲወጡ ወኔ በመስጠትና በማስታጠቅ፤ እንደ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የጥቁር ሕዝቦች የማንነት ተምሳሌት በመሆን እንድትሣል አድርጓል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ወራሪዎች ብዙውን ጊዜ ይኼን መነሻ ያደርጋሉ›› የሚሉት ተናጋሪ፣ ምክንያቱንም ያብራራሉ፡፡ ‹‹አንድ ሰው ሊገዛ የሚችለው ማንነቱን ሲያጣ ነው፡፡ ማንነቱን የማያውቅ ትውልድ ምን ጊዜም ለሚሆነውና ለሆነው ነገር ጉዳዩ ስለማይሆን፣ ተገዢ ይሆናል፡፡ ከዓድዋ በኋላ የተደረጉ ወረራዎች የሚነግሩን በርካታ ቁም ነገሮች አሉና፡፡››

የባዕዳኑ እንቅስቃሴ የመጀመርያው ተግባርና ግባቸው የኢትዮጵያን ለጥቁር ሕዝቦች የነፃነትም ሆነ የማንነት ተምሳሌትነት ማደብዘዝ ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ተናጋሪው፣ ‹‹ኢትዮጵያ የምንላትን አገር ከለወጥናት ከቀየርናት ሌላውን አፍሪካ በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ እንችላለን፤›› የሚል አስተሳሰብ አላቸው፡፡

‹‹የዓድዋው ድላችን ለማንነታችን፣ ለታሪካችን ለተለያዩ ነገሮቻችን አንዱና ዋናው እሴታችን በመሆኑ በዚህ ደረጃ አስፍቶ ማየትና ተሻግሮ ማሰብ ካልተቻለ ታሪክን በታሪክነቱ ብቻ ማስቀመጥ አይበቃም፡፡›› በማለትም ያክላሉ፡፡

‹‹ዓድዋ ለኔ ሰባኪ ነው፤ ምናልባት እኛ በሲዲ ከምናስተምረው በላይ ሰባኪ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ ውስጥ፣ ዓለማቀፍ ስብከት የሰበከው ኢትዮጵያ ማን ነች? ቤተ ክርስቲያኗስ ማን ነች? የሚለው ተሰበከና አፍሪካዊነትም ለጠቀ›› በማለት የተናገሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ መምህር አቶ ደሴ ቀለብ ናቸው፡፡ መምህር ደሴ አያይዘውም፣ ‹‹አሁን እኮ በዓድዋ የተሰበከውን እያጠፋነው ነው፡፡ በሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ስም የምናስተምረው ትምህርት፣ የምንናገረውና የምንዘምረው ሁሉ ነገር ዓድዋ የሰበከውን እያጠፋነው ነው፡፡

አሁን ተመሳሳይ ነገር ቢመጣ መግቢያችን አይታወቅም'ኮ፣ ስለባህሉ በምልዐት የሚያውቅ አለ? አፄ ምኒልክ አሁንም፣ ‹‹ማርያምን አልምርህም›› እንዲሉን ነው? ራሳችን ባህላችንን እስካላወቅን ድረስ ማሸነፍ አንችልም፤›› ብለዋል፡፡

6 comments:

Desalew said...

really interesting!!!!

Correction to all said...

As a pilot research "EOTC's role in Adwa Battle" can presented but the reality is the under.

Especially, since 4th century-era of Ezana & Saizana to the time of Haile Selassie 1974, history tells us Ethiopian History is Ethiopian Orthodox Church History.

Even in the regime of Dergue, Mengistu & HH Abune Merqorios were leading the country that is why HH flight to America after the denouncement of Dergue.

Today, why everybody calls "Patriarch Paulos weyane?"

Historian,

Dillu Ayqerim said...

Who reversed the victory of Adwa and ruling Ethiopia now as a foreign agent that our forefathers defeated ? Who is now teaching Ethiopian children that Ethiopian history is 100 years' history instead 3000 +? Who gave up Eritrea by making Ethiopia landlocked? Who has violated our church's canon law by removing the legal patriarch and installed an illegal one? Can our history teachers say some thing about all this? The enemies which our forefathers defeated at Adwa and many other places are now using our own leaders, who look like us and act like them, to rule us on behalf them by ridiculing our victory and the leaders of that heroic victory.As long as our country and church current rulers remained foreign in their mind set, it would be very difficult to preserve and maintain our own history and culture as well as our religious faith in there originality.

yetsyon said...

I’m immensely delighted to have to read such prolific writings radiating from college quarters in AA. The earlier article, the marvelous feat of MK to organize the Adowa symposium, and now this article by the erudite of the western order is refreshing to the list. Adowa isn’t just a war won over an enemy, but an overwhelming tide that enveloped the proud west to show it a)- that God is in command and b)- that He is the God of his chosen flock that is Ethiopia. The Pope in Rome swallowed this message from God with too great disturbance on March 3, 1986, a vexation that forced him to abandon his coronation anniversary banquet. Vexed Europe then assembled new tricks to subjugate the black race by first erasing Ethiopia’s faith and history. The rest, as they say, is history.

To the writer above…The synod of Aba Merkorios is a Synod of the protestant. The so called exiled synod has broken ranks with the Tewahdo faith by reason of its tehadso (protestant) sermons. So please spare us of this “legal patriarch” mantra and succumb to the true teachings of Tewahdo if you will. Ethiopia does not have a “legal patriarch” who is head of a protestant synod.

yetsyon said...

I’m immensely delighted to have to read such prolific writings radiating from college quarters in AA. The earlier article, the marvelous feat of MK to organize the Adowa symposium, and now this article by the erudite of the western order is refreshing to say the least. Adowa isn’t just a war won over an enemy, but an overwhelming tide that enveloped the proud west to show it a)- that God is in command and b)- that He is the God of his chosen flock that is Ethiopia. The Pope in Rome swallowed this message from God with too great disturbance on March 3, 1886, a vexation that forced him to abandon his coronation anniversary banquet. Vexed Europe then assembled new tricks to subjugate the black race by first erasing Ethiopia’s faith and history. The rest, as they say, is history.

To the writer above…The synod of Aba Merkorios is a Synod of the protestant. The so called exiled synod has broken ranks with the Tewahdo faith by reason of its tehadso (protestant) sermons. So please spare us of this “legal patriarch” mantra and succumb to the true teachings of Tewahdo if you will. Ethiopia does not have a “legal patriarch” who is head of a protestant synod.

Anonymous said...

addis ababa uni people get focused on important issues.we know this.these days there is little difference between a layman and uni professor.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)