March 9, 2011

ርዕሰ አንቀጽ፡ በጅማ ፕሮቴስታንቶች ላይ የተፈፀመውን የአክራሪዎች ጥቃት ልንቃወም የሚገባበት ምክንያት …

(ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2011)፦ በጅማ አካባቢ ባሉ ሥፍራዎች “በጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች” የተፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡትን ዘገባ እኛም በድጋሚ ትኩረት ሰጥተን ማስተናገዳችን ይታወቃል። እናውቃለን ፕሮቴስታንቶቹ የእኛኑ አማኞች ከርትዕት እምነታቸው ለማፈናቀል እንደሚጥሩ። እናውቃለን አብዛኞቹ ዛሬ “ፕሮቴስታንት ነን” ያሉት ወገኖች በእኛው ቤተ ክርስቲያን በ40 እና በ80 ቀናቸው የተጠመቁ እንደነበሩ። እናውቃለን ቤተ ክርስቲያናችንን በመናቅ እንደሚናገሩ። እናውቃለን ከዚህ በፊት በኦርቶዶክሳውያን ክርስቶያኖች ላይ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲፈፀም ድምጻቸውን እንዳላሰሙ። ነገር ግን አሁን የጥቃቱ ዒላማ እነርሱ ስለሆኑ ልንደሰት፣ ዝም ልንል፣ “ይበላቸው” ልንል አንችልም። ክርስትናችን አይፈቅድልንም። ይህ አደጋ የደረሰው በክርስቲያኖችም ላይ ሆነ በሌሎች እምነት ተከታዮች ላይ ድርጊቱን እናወግዝ ዘንድ እምነታችን ግድ ሊለን ይገባል። ይህንን የፈፀሙት ፕሮቴስታንቶቹ፣ ተጎጂዎቹ ሙስሊሞቹ ቢሆኑ ኖሮ ተጎጂዎቹን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ደግፈን ወንጀሉን የፈፀሙትን እንቃወማቸው ነበር። ጥያቄው “ማን ነው የተጎዳው?” ሳይሆን “ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ይጎዳል?” ነው። አመክንዮዋችንን በሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ እናጠቃለው።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት፣ በናዚዝም ከናወዘው የጀርመን ሕዝብ መካከል አቅሉን ያልሳተ “ማርቲን ኒሚውለር” (1892–1984) የሚባል አንድ ሰው እንዲህ አለ። ርእሱ “በመጀመሪያ ሲመጡ …” ይላል።

“በመጀመሪያ ወደ (ናዚዎቹ) ኮሚኒስቶቹ መጡ (ለመያዝ ለመግደል)፣ ኮሚዩኒስት ስላልሆንኩ ምንም ሳልናገር ዝም አልኩ፤
ቀጥሎ ወደ ንግዱ ማኅበረሰብ አባላት መጡ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባል ስላልሆንኩ ምንም ሳልናገር ዝም አልኩ፤
ቀጥሎ ወደ አይሁዶቹ መጡ (ለመያዝ፣ ለመግደል)፣ ይሁዲ ስላልሆንኩ ምንም ሳልናገር ዝም አልኩ፣
ቀጥሎ (ሊይዙኝ ሊገድሉኝ) ወደ እኔ መጡ፣ ለእኔ ሊናገርልኝ የሚችል ማንም የተረፈ ሰው አልነበረም/ አልተገኘም።”

“First they came...”
(By Martin Niemoller)
“First they came for the communists, and I didn't speak out because I wasn't a communist.
Then they came for the trade unionists, and I didn't speak out because I wasn't a trade unionist.
Then they came for the Jews, and I didn't speak out because I wasn't a Jew.
Then they came for me, and there was no one left to speak out for me.”

“ወዳጅህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ” ይላል ያገራችን ሰው።
http://www.voanews.com/english/news/africa/east/Police-Make-Arrests-in-Ethiopia-Church-Burnings-117589944.html

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

15 comments:

Anonymous said...

ክርስትና /ኦርቶዶክስ/ የፍቅር ና የሰላም ሃይማኖት ናት፡፡ ጌታችን መስራቹ እራሱ እንኳን ሰውን ሁሉ ሲያድን እነድ ጊዜም ቢሆን ሳያስፈቅድ የድህነት ስራውን አልፈፀመም( እፁብ ድንቅ ነገር አምላክ ሆኖ ሳለ የሚበጀንን እና የሚጎዳንን አያወቀ ግን ያስፈቅድ ነበር ዛሬም እንዲሁ… የነፃነት አምላክ ነውና)፡፡ ታዲያ እንኳን እያጠፏቸው ለመልካምም ቢሆን እንኳ በኃይል የመጣን ነገር አስካልታመነበት ድረስ መቃወም ይገባል፡፡ ለነገሩ ተግባሩ ወደ እኛው ለመምጣት እንደመለማመጃ ሜዳ እየተጠቀሙበት እንደሚሆን ለማወቅ ነቢይ መሆን አይጠብቅም፡፡
አምላካችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡
ኃይለ ሚካኤል ከባሕርዳር

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ።አሜን!!

እነዚህ ፕሮቴስታንቶች በትንኮሳቸው በእርግጥ ለእኛም ለኦርቶዶክሳውያንም አላረፉም። በስመ ክርስቲያንም ብዙ ጊዜ በሚተነኩስት ትንኮሳ ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር ሊያጋጩን እንደሚሞክሩ እናውቃለን። ጉዳዩ ግን የወዳጅነትና የጠላትነት ሳይሆን አላስፈላጊ የሆነ ጥቃት ለምን ይፈፀማል? ድርጊቱ የሚመለከታቸው በተለይ የክልሉ መንግስትና ሌሎች ክፍሎች ለምን እንደቀላል ነገር በማየት ችላ አሉት? ነው ጥያቄው። ደጀ-ሰላምም በርዕሰ አንቀጿ እንዳስቀመጠችው በሙስሊም ወገኖቻችንም ላይ ቢሆን የዚህን አይነትና ሌላም አላስፈላጊ ጥቃት ቢደርስ እንደ ዜጋና እንደ ወገን መቆርቆራችን አይቀርምና መጠቃቃትና መጎዳዳቱ ቀርቶ እግዝአብሔር እንደሚወደው በፍቅርና በመተሳሰብ ብንኖር መልካም ነው።

ቸሩ ፈጣሪያችን በፍቅርና በመተሳሰብ እንድንኖር ይርዳን። አሜን!!
መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

ክርስቲያን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ)መጀመሪያ ስለሀይማኖቱ መቆጨት አለበት፡፡ መቆጨት ብቻም አይበቃም መቁረጥም አለበት፡፡..... አሁን እኮ የጠፋዉ ቆራጥ ክርስቲያን ነዉ፤ አሁን ያለነዉ (ከእኔ ጀምሮ )ለዘብተኞች ሆነናል... 1)አብዛኞቻችን የሚጠበቅብንን አናዉቅም፤
2)የምናዉቅም አንተገብርም፤...
3)የምንተገብርም በግብዝተኝነት ነዉ ...ይህም ግብዝተኝነታችን ደጄ ሰላም ላይ ከምንጽፈዉ ሃሳብ ይጀምራል፡፡
ደ/ን ዳንኤል ክብረት "ጥቅም ቀርቶበት የሚሳደብ እና እጠቀማለሁ ብሎ የሚያወድስ አንድ ናቸው፡፡ የሁለቱም መሠረት አመክንዮ ሳይሆን ስሜት ነውና፡፡ "

tad said...

A Nazy survivor reflected on his shorcomings of not stopping Hitler at his early stage,
" First he came after union leaders and I didn't do any thing because I wasn't union leader and he came after communist party and I didn't do any thing because I wasn't a communist and then he came after Jews and I kept quite because I wasn't a Jew and finally he came after me and no one came to help me because everybody was gone.
EOC members unless we are guided by injustice to a person is injustice to the nation we can't get out of thr vicious circle our nation is facing.
Thank you DS for you courage.

Gebre z Cape said...

ይህንን የፈፀሙት ፕሮቴስታንቶቹ፣ ተጎጂዎቹ ሙስሊሞቹ ቢሆኑ ኖሮ ተጎጂዎቹን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ደግፈን ወንጀሉን የፈፀሙትን እንቃወማቸው ነበር። ጥያቄው “ማን ነው የተጎዳው?” ሳይሆን “ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ይጎዳል?” ነው።

This explains everything. This is why Dejeselam wrote this article as to me. Guys let us not waste our time on something not worthy. Muslims are against everyone. This world is in a mess because of "Fundamentalist Muslims". So what can we do to stop this kind of events not to happen again and again. We did not forget what happen around 2007 in Jimma zone. Kahinat alitaredum, other members also died and suffered. Some time in the past also, kahinat were thrown in to a valley in Asab Gedame (Hararge region I guess).

Let's create a discussion how to work on this issues. As we always do in difficult situation we should keep praying to GOD.

GOD bless Ethiopia.

Anonymous said...

i agree with the deje selam article. it doesnt matter if a person is bad or good, we should stand on good justice.eventhough the protestant against us, we don't see them hurt by unjuistice. and they have to know that we are not a revange people.

Anonymous said...

Dear Deje-Selamawian:
I have always liked and mesmerized by your editorials. This one is no different, which i thought to be very short, but precise, powerful and to the point.

By taking this editorial stance, you have demonstrated the depth & maturity of your thoughts, the strength of your Tewahidoawi faith, and most importantly the moral superiority of our Selamawit church, EOTC, that you represent and defend.

I am so proud of you, and May the Almighty Ye Ethiopia Amlak, MedhaniAlem, protect you and bless you with more of his mystical wisdom.

Teteratariw Teketay,

Anonymous said...

I just want to share what happened when muslim killed our church fathers and killed our churches. My cousin, who is protestant came to my house and i was so saddened by what happened to our church and told her how ruthless they were, and she kind of loughed and told me that she doesn't feel sorry for them because Orthodox people loved the muslims more than they do protestants. I was shocked and knew how happy protestants would be all around ethiopia by what happened to their mother church. It didn't take long before it happens to them. May God accept the soul of those who have lost their lives. AMEN!!!

Anonymous said...

ተገቢ ነው፡፡ ማንም ይሁን ማን የሰውል ልጅ በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረ ክቡር ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን የሚጠብቀን ሰላመንነው ብቻ አይደለም፡፡ እንሳሳት እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ በፈቃዱ፣ በከኃሊነቱ ነው የሚጠብቀን፡፡ ስለሆነም ለፍጥረቱ የማያዳላን አምላክ የምናመልክ ነንና፤ ኢሰብአዊ፣ አረመኔያዊ ጥፋት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ እንዳይደስ መትጋት አለብን፣ ሲደርስም መሟገት፣ ጠበቃ መሆን፣ መደገፍ ይገባል፡፡

በጣም ጥሩ የሆነ አቋም፡፡ በርቱ የቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በተግባር የሚገለጥበት መልካም ሥራ፡፡

Anonymous said...

“ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።”
ማቴ 5፤44-45

እኔ እንደሚታየኝ ይህ ችግር በየጊዜው ተደጋሞ የሚመጣው መንግስት ችግሮች በሚፈጠሩበት ጊዜ ችግሩን ከስር መሰረቱ አጥንቶ እና አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ነው፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ አንድ ጊዜ ፓርላማ ላይ …. ፂም ማሳደግ ይቻላል ነገር ግን ያደገው ፂም ቅጫም ካቀጨመ ከእነ አገጩ ነው የምንቆርጠው ….. ብለውን ነበር : ግን ያሉትን መሬት ላይ አውርደው ሲተገብሩት ለመመልከት አልታደልንም፡፡
አሁን ያጠፉ ሰዎችን ይዞ ፍርድ ቤት አቅርቦ ውሳኔ ማሰጠት ችግሩን መፍቻ መንገድ መስሎ አይታየኝም ፡፡ ይህን የመሰለ አካሔድ አሁንም መንግስት የሚጠቀም ከሆነ እሳቱን ሳያጠፉ አዳፍኖ ለወራት ወይም ለዓመታት ማቆየት ይመስለኛል ፡፡ ነገ ከዚህ በፊት እኛው ላይ ያደረጉትን ተግባር እንደማይደግሙብን ምን ማረጋገጫ ይኖረናል? ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ያነገቡትን አላማ መንግስት ሊገባው ይገባል ፤ ምን አስበው እንዲህ አይነት ነግባር እንደሚያከናውኑ ሊያውቅ ግድ ይለዋል ፤ ከተግባራቸው በፊት ያለውን አመለካከታቸውን አውቆ ለተግባራቸው ብቻ ሳይሆን የተቀበረውን አመለካከታቸው ላይ ስራ መስራት ያስፈልጋል ፡፡
ተግባርን ማረም ስለ ተግባር ቅጣት መስጠት ሁለተኛ ነገር ነው ፡፡ ለተግባሩ ቅጣቱን ከመስጠት በፊት አመለካከቱን ማወቅ ግድ ይላል፡፡
እግዚሐብሔር የአባቶቻችንን ጊዜ ይመልስልን …. ቸር ወሬ ያሰማን….ቤተክርስትያናችንን ክፉ ከሚያስቡባት ፤ ጉድጓድ ከሚምሱላት ፤ ግለሰቦች እና ተቋማት አምላክ በቸርነቱ ይጠብቅልን ፡፡ እኛም ያለንበትን ሁኔታ ጠንቅቀን በማወቅ ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር ሰርተን ለልጆቻችን አንዲቷን ቤተክርስትያናችንን እንድናስረክባቸው እግዚሐብሔር ይርዳን፡፡


ላሜዳ ..ከአ.አ

Anonymous said...

Dejeselam,
Please be compassion for your real brothers and sisters FIRST and then you will show us how you really compassionate for others. No one really believes you unless someone who is blind!!!

Anonymous said...

በጣም የሚገርም እኮ ነው! ከዚህ በፊት ያለተጨባጭ ማስረጃ ቁርዓን በዩኒቨርሲቲ ሽንት ቤት ውጥ ተገኘ ብለው በዩዩኒቨርሲቲው ሲያውኩ ከረሙ! አሁን ደግሞ ቁራን ተቀዶ ሽንት ቤት ውስጥ አግኝተናል በሚል ቡራ ከረዩ መንፋት ምንድን ነው!? ምንስ የሚሉት ነው?ሽንት ቤት ውስጥ ለመጣሉና ለመቀደዱስ ምንድን ነው ማስረጃው? ሕግና ደንብ አለበት በሚባለበትስ ሃገር ይህ ችግር የተከሰተ ከሆነ ከሁሉም በላይ ወደሆነው ወደ ሕግ ያመራሉ እንጂ እንዳሻቸው ሊያደርጉ ይገባል ወይ? ቢገኝም እንኳን የጣለው ግለሰብ በሕግ ይቀጣል እንጂ እንዳሻቸው ሊያደርጉ አይገባም! ዛሬ ቤቶችን(አዳራሾችን) ያፈረሱ ነገ እንደለመዱት ሕንጻ እግዚአብሔር የሆነውን የሰውን ሕይወት ለማጥፋት አይተኙም፡፡ ማስተዋልና ልቦናን ይስጣቸው፤ ሃይማኖት በኃይል አይሆንምና ፡፡ ፍቅር ቢኖራቸው ኖሮ ቀደዱ ያሏቸውን ወገኖች በኃይል ሳይሆን በፍቅር ባስተማሩና በመለሷቸውም ነበር፡፡

Anonymous said...

ሁላችንም እናስተውል!!!

ይህ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ላይ የደረሰው ጥቃት መሰረታዊ መነሻውም ሆነ መድረሻው መንግስትና የኮለኮላቸው ካድሬዎቹ ናቸው፡፡ኢትዮጵያዊ ሙስሊምም ሆነ እንዲህ ዓይነት የጭካኔ ተግባርን ቸይፈጽሙም፡፡ እንደሰሜን አፍሪካ መንግስት ተቃውሞ የሚነሳበት ከሆነ ወደፊት ምን ሊያደርግ እንደሚችል ካቀዳቸው ተግባራት አንዱ ማሳያ ነው እና ሁላችንም ጥንቃቄ እናድርግ፡፡እንንቃ!!

Anonymous said...

እባካችሁ የጅማ ከብቶች ይታሰሩልን የማይታሰሩ ከሆነ ግን ነብር ይበላቸዋል

Mizan said...

I never believe in what so ever religion whose stand is "killing lives and destroy properties"

And I strongly believe, Sheol is prepared for the killers and destroyers of properties.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)