March 9, 2011

ጅማ- የሚመለከታቸው በሚገባ ያልተመለከቱት አካባቢ

ማስታወሻ፦ ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ በፀሐፊው ፈቃድ ከፌስ ቡክ ላይ ተወስዶ እዚህ የተለጠፈ ነው። መልካም ንባብ።
++++
ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ
(ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ):- ጅማ ከ፲፱፻፺፱ ዓም ጀምሮ ስሟ በክፉም መነሣት ጀምሯል፤ የአካባቢውን ነዋሪና አስተዳደር ስሜት ለሚረዳ ይህ ጥሩ አይደለም። መረጃዎችን በግንጥሉ ለሚሰማ ደግሞ ጅማ ላይ ብቻ የተከሠተ አድርጎ ያየዋል። ሌሎችም መታየት ያለባቸውንና የሚመለከታቸው ቢያስቡበት መፍትሔው የማያስቸግረውን ጉዳዮች ብናነሣስ? ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በልማቱ ከተዘነጉትና አሁን በመጠኑ በልማቱ ወላፈን ከሚጎበኙት አካባቢዎች አንዱ ነው። ላያቸው ግን ሁሌም የማይረሱና ለመላው ኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም የሚበቃ ሀብት እየታፈሰባቸው ነው፡-
 •  2300 ሜጋዋት በላይ እንዲያመነጭ የሚገነባውና በቀጣይም ሌላ ተመሳሳይ መጠን የሚጠበቀው የግቤ ወንዝ ምንጭ ከዚህ ይገኛል፣ 
 •   ለዚህና ለትልልቁ የባሮና አኮቦ ወንዞች እንዲሁም የአየር ንብረቱ ሚዛን ዋስትናዎቹ የጅማ፣ የከፋ፣ የኢሉባቦርና የሸካ ደኖች ያሉበት ክልል ነው፣
 •   በሀገሪቱ ለሚቃጠሉ ከፍተኛ ሙቀት ፈላጊዎች /አብዛኞቹን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጨምሮ/ ምንጩ ከጅማ ዙሪያ የሚወጣው የድንጋይ ከሰል ነው፤
 •  ወደፊት የማዳበሪያ ጥያቄዎችን የሚፈታው ምርት የታቀደው ከበደሌ /ጅማ ድንበርተኛ/ ይሆናል፤
 •  አሁን በጥራትና በብዛት በማቅረብ ደረጃ ቢቀደምም ለዓለም ቡናን ያበረከተውና የኢኮኖሚ ዋልታ የሆነው ከዚህ በመነሣት ነው፤ ከተሳካም የጋምቤላ ነዳጅ ፍለጋም የሚጓጓዘው በዚሁ በጅማ አቋርጦ ነው፤
አሁን ጥያቄው ምን አገናኘው እንዳትሉ፤ ልማት ከሰላም ነው፤ የባቡሩም፣ የትራንስፖርቱም ሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጩ ያለሰላም ተጓጉዞ የትም ሊሄድ አይችልም። የአካባቢውን ሰላም የሚነሣው የሃይማኖት ግጭት ይመስላል። አክራሪ እስልምና ማሠልጠኛው ጭምር እዚሁ አለ ይባላል፤ ቢያንስ ግን መቻቻልን የማያውቁበት የሠለጠኑት በገሃድ አሉ ባለፈው ሳምንት በተጀመረው አዲስ ጥቃት ትኩረታቸው የፕቆቴስታንቱ የሆነው በፈቃዳቸው ሳይሆን ከአዛቾቻቸው ተከልክለው ነው ወይ የእኛው ምላሹ አስግቷቸው የመናፍቃኑን ግብዝነት ተገንዝበው፣ አለያም ሌላ ሰፊ ዕቅድ ይዘው ነው፤ እንጂ የሚያዘናጋ አይደለም። ይህን ለመረዳት ከክረምቱ ጀምሮ የነበረውን ውጥረት ማየት ይቻላል።
 •   የዴዶና ሰርቦ ወረዳዎች በውጥረትና በችግር ነው የከረሙት፤ ዲያቆናትና ካህናት በግልጽ ብቻቸውን መንገድ አይሄዱም፣ ባልሠሩት ይከሰሳሉ፣ ቁልቁል ተዘቅዝቀው ይገረፋሉ፣ ይደበደባሉ፣ እንዳያስተምሩና ክርስቲያኑን እንዳያሰባስቡ ይታዘዛሉ፣፣ 
 •  የቤ/ ጉዳይ በመንግሥት /ቤቶች ዘንድ ተሰሚነት የለውም፤ ለትሕትናው ምላሹ ንቀት የተሞላበት ትርጉም የለሽና ከመንጝሥት የማይጠበቅ መንገላታት ነው፣ በዚህ ዓመት ደመራ በዓል ላይ «ዜጋ ከሆንን እንኑርበት፣ አይደላችሁም ከተባልን ንገሩን» ያሉት ሊቀጳጳሱ ወደው አይመስለኝም፣
 •  እያደር የሚጠራው እውነት ግን አሁን በዞኑ ከ፹ ከመቶ በላይ አለ የሚባለው እስልምና ብዙው መቶ ዓመት ያልሞላው፣ የቀረውም ከ፻፸፭ ዓመት የማይበልጠው ታሪክ በከፊል የውጪ ዜጋ እንደሆኑ በሚነገርላቸው «አቶ» ጅማ አባጅፋር ወላጆች ሥራ እንጂ ታሪኩማ የእናርያው ቅዱሳን፣ የአባ ኢየሱስ ሞአ ደቀመዛሙርት ሀገር ነበረ፤ ለዚህ ጥሩው ማሳያ በ፳፻፩ ዓም በ፲፬ አባወራዎች ተጠይቆ ግንባታው የተጀመረው / ሕንጻ ሲሠራ «ሃይማኖታችን እኮ እዚህ ነበረ» ብለው እንዲቀበሏቸው የለመኑት ፴፩ዱ አባወራዎችና ጉልላቱ ሲተከል አስታውሰው «የእኛ ሃይማኖት ምልክት ይኼ ነበረ» ብለው አጥምቁን ያሉት ፯፻፴ ሽማግሌዎች መመለሳቸው ነው፤
አሁን መታየት ያለበት:-
 1. ለሀገሩ ሁሉ የሚተርፈው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ደን፣ የድንጋይ ከሰልና ማዳበሪያ ያለፍትሐዊ አስተዳደር፣ በውጤቱም በሰላም እጦት ይሳካል ወይ?
 2. የመንበረ ፓትርያርኩ ዝምታና ሊቀጳጳሱን አለመርዳት መጨረሻው ክፉ እንዲሆን ተፈልጎ ካልሆነ አዲሶቹን እንደኔ ከግራኝ ወዲህ ካህን ያጡትን ለማጥመቅ /ለጵጵስና ሹመት እጅ መንሻ ለመቀበል/ ጋምቤላ እንደሚሄዱት ሁሉ የተጠመቁትን ስለማጽናት ፓትርያርክ ጳውሎስና አጃቢዎቻቸው ሲለመኑ ሀገረ ስብከቱን አለማገዛቸው ምን ተፈልጎ ነው?
 3. በጅማ ጎልቶ የታየው አንድም የአክራሪዎቹ ጥፋት ስላየለ፣ አንድም ሊቀጳጳሱ ለመሥዋዕትነት ጭምር ተዘጋጅተው እረኝነታቸውን ስለተወጡ እንጂ በየሀገረስብከቱ በሽፋኑ በግድ እየሰለሙ ያሉና በየጊዜው የሚቃጠሉና የሚመዘበሩ አድባራትስ መፍትሔ አጥተው ወይስ ለሥልጣንና ለገንዘብ ብቻ ዘብ በቆመው የፓትርያርክ ጳውሎስ አስተዳደር ችግር? የሚጠቅማቸውስ ከሆነ ምን ያህል ያዛልቃቸዋል?
እንደ እኔ ለመንግሥትም  በሚገባ ካላየው በጅማ ዙሪያ ሰላም፣ ልማት፣ ለጠ//ክህነትም ክርስትና ብሎ ማሰብ ሳያስቸግር አይቀርም፤ በግድና በተግሣጽ የታገደው ክርስቲያኑ ከመጠን በላይ ሲሆንበት የሀገረስብከቱን መመሪያ ላያከብር እንደሚችል መገመትና ፍትሐዊ አስተዳደር ማስፈን እንደሚያስፈልግ መጠቆምም ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም።

8 comments:

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያንን በመምራት ላይ ያሉ አባቶች ጳጳሳት በአብዛኛው ነገሮችን ከአለም አቀፍ ሁኔታና ከሀገሪቱ የወቅቱ ሁኔታ ጋር ገምግመው ነገሮችን ከመከሰታቸው ወይም ከተከሰቱ በኃላ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት በቤተክርስቲያን መሪነታቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመወሰንና ተፈጻሚነታቸውን ለመከታተል የሚያስችል ልምድ ወይም መዋቅር ያላቸው አይመስለኝም:: ለዚህ ይመስለኛል በነገር ሁሉ ምህመናኑን ከመምራት ይልቅ ምህመናን ችግሮች የሚፈቱበት ሁኔታ በየቦታው ሲሰጡ የሚታየው:: በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲባል አንዳንዶቹም አባቶች ቤተክርስቲያንን በእንደዚህ አይነቱ ችግሮች ላይ ትክክል የመስላቸውን ከማድረግ ይልቅ በስልጣን ላይ ያለውን አካል ላለማስቆጣት ወይም እንዲህ ብንል ስልጣኑ ይነካ ይሆን በሚል መድራዊ ሃሳብ ስለሚያተክሩ ምህመኑ ያለ አቀኛ አባት አስቀርተውታል:: በጎ ዘመን ያምጣልን እንጂ ሌላ ምን ይባላል::

Anonymous said...

Is it in Ethiopia those things happening or in Afganstant? If it is happening, where is the government? Or does the government want Christians to protect themselves?

Anonymous said...

Please people, record it on videos then show the world what is happening by those fundamentalist in Ethiopia and put it on Youtube and send it to various TVs & News Channals.

Saudia Arabia, Yemen, Iraq, Egypt and other Middle Eastern countries used to be a chirstian countries. Who killed those christians? I think all of us know the answer. So are we waiting the same thing in our land.

If the government & the peace loving muslims don't do any thing to stop this evil, we need to defend our right & life.

Anonymous said...

for those who come after a years ago, please taker-off. The gov't should take an action for one and ever other wise the people have to take it own measure

Anonymous said...

KEHADI DIABLOS has no time to serve God and his followers. DIABLOS has only time to entertain BEYONCE and serve killers and looters.

Anonymous said...

ምነዉ እናንተ አክራሪዎች ነቢያችሁ አበሾችን አትንኩ ብሎናል እያሉ የራሳችሁ ወንድሞቻችሁ የሚነግሩኣችሁን ሰምታችሁ በነፍስ በሥጋ ሞታችሁ መግደልን ብተትተው!ኢትዮጵያዊ የሆነ ኑሮአችን እናንተን በዕምነታችሁ እንዳትሄዱ መቼ ከለከላችሁና ነው ጦር የምትመዝዙት ለምን የአፍጋኒስታንን እና ለሌሎች የእስልምና ተከታይ ሀገሮችን መከራ በራሳችሁና በሌሎች ላይ ለማምጣት ትሮጣላችሁ እባካችሁ ረጋ ብላችሁ አስቡ አልተገፋችሁም አልተጨቆናችሁም ሁሉንም በሰላም ለማድረግ መብት አላችሁ እባካችሁ አስኑሩንና አብረን በሀገራችን ላይ ሰርተን እንኑር እናንተም ኑሩ አምላክ ልቦና ይስጣችሁ እላለሁ

Anonymous said...

The Government, it better wake up and smell the coffee.

Anonymous said...

Really nice saying; ጅማ ከ፲፱፻፺፱ ዓም ጀምሮ ስሟ በክፉም መነሣት ጀምሯል፤ የአካባቢውን ነዋሪና አስተዳደር ስሜት ለሚረዳ ይህ ጥሩ አይደለም። መረጃዎችን በግንጥሉ ለሚሰማ ደግሞ ጅማ ላይ ብቻ የተከሠተ አድርጎ ያየዋል። ሌሎችም መታየት ያለባቸውንና የሚመለከታቸው ቢያስቡበት መፍትሔው የማያስቸግረውን ጉዳዮች ብናነሣስ?....ፍትሐዊ አስተዳደር ማስፈን እንደሚያስፈልግ መጠቆምም ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም።
I agree. Thank you blogger.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)