March 8, 2011

የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ በግለሰቦች መተዳደር ቅሬታ አሥነሳ


/አዲስ አድማስ፣ ዘኤልያስ ወልደ ሚካኤል፣ ቅዳሜ፣ የካቲት 26 ቀን 2003 ዓ.ም/፤ የኮተቤ ደብረ አራራት ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን እና አገልጋዮች ቤተ ክርስቲያኑ በግል ይዞታ ሥር መሆኑን ተቃውመው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አቤቱታ አቀረቡ፡፡


በጠበል ማጥመቂያ ቦታነት ተጀምሮ በ1991 ዓ.ም የታነፀው ደብረ አራራት ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13 ዓመታት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ውጭ አባ ኀይለ ሚካኤል እና ወ/ሪት ክብነሽ በተባሉ ሰዎች እየተዳደረ እንደሚገኝ ወደ 50 የሚጠጉ አገልጋዮች እና ምእመናን ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ተናግረዋል፡፡ እነዚሁ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደሚሉት ቤተ ክርስቲያኑ ላለፉት 13 ዓመታት ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤት፣ የገቢ እና ወጪ መቆጣጠሪያ ሞዴሎች የሉትም፡፡ በ1993 ዓ.ም አራት ዲያቆናት ችግሩን ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አመልክተው በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ከተባረሩ በኋላ እኛም እንባረራለን በሚል ፍራቻ መሰል ጥያቄ ተነሥቶ እንደማያውቅ ተናግረዋል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ አቤቱታቸውን ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያቀረቡት የአካባቢው አገልጋዮች እና ምእመናን ‹‹ሰበካ ጉባኤ ይቋቋምልን፤ ወጪ እና ገቢው የሚመዘገብበት እና ንብረት ለመቆጣጠር የሚያገለግሉ ሞዴሎች በቤተ ክርስቲያኑ ስለሌሉ እንዲስተካከልልን፣ ሰንበት ት/ቤትም ይመሥረትልን፤›› የሚሉ ጥያቄዎችን አንሥተዋል፡፡ ‹‹ቤተ ክርስቲያኑ ወጥ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር የለውም፤ ለጠበልተኞች ከሚከራዩ ቤቶች የሚገኘው ከፍተኛ ገቢ የት እንደሚገባ አይታወቅም፤›› የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ‹‹የሰበካ ጉባኤ እና የሰንበት ት/ቤት አለመኖር ቤተ ክርስቲያኑን ግለሰቦች እንደፈለጉ እንዲያዙበት፣ ወጪ እና ገቢ ላይ ቁጥጥር እንዳይኖር አድርጓል፤›› ይላሉ፡፡ እንደ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ገለጻ በቤተ ክርስቲያኑ ቅዳሴ የሚቀደሰውም ሆነ ክርስትና የሚነሣው እሑድ እሑድ ብቻ ነው፤ ይህም ሆኖ ሕጋዊ ካህናት እና አገልጋዮች የሉበትም፤ ያሉትም ቢሆኑ ለአስተዳዳሪዎቹ ታዛዥ ከሆኑ ብቻ ይቀመጣሉ፣ አለበለዚያ ይባረራሉ፤›› በማለት አቤቱታቸውን አሰምተዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ኀይለ ሚካኤልን አነጋግረናል ያሉት ሥራ አስኪያጁ አስተዳዳሪው በግል ይዞታቸው ሥር የነበረውን ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ማስረከባቸውን ገልጸው፣ በቀን ከ500 ሰው በላይ እንደሚያጠምቁ፣ አገልግሎቱንም ያለምንም ክፍያ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው ለአቤቱታ አቅራቢዎቹ አስታውቀዋል፡፡ በቅሬታ አቅራቢዎቹ ለተነሡት ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ሥራ አስኪያጁ ጉዳዩን በኮሚቴ እንደተነጋገሩበት እና እንዲሁ ክፍት እንዳልተውት ተናግረው ሁሉንም ነገር ሀገረ ስብከቱ ሥርዐት እስኪያሲዘው ድረስ ትንሽ መጠበቅ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ አሉ ለሚባሉ ችግሮችም መፍትሔ እንደሚሰጡ ቃለ የገቡ ሲሆን ሁሉንም ነገር በሂደት ከአስተዳዳሪው ጋራ በመነጋገር እና በመወያየት በቦታው ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ እና እያገለገሉ የነበሩ(ያሉ) ካህናት እና አገልጋዮችም ቢሆኑ መብታቸው ተጠብቆ የሚያገለግሉበትን ሕጋዊ መንገድ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል፡፡

11 comments:

Anonymous said...

like this there are many churches whihc fill the hunger of private pockets. especially the churches which have holy water are vaccancies for the church suckers like aba haile michael.

after they become rich, they will be against the church, fathers, and laities. or they will be either traders or politicians.

Anonymous said...

የሰሜን አሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት በሽታ ወደ ኢትዮጵያም ተገባ ማለት ነው!

Anonymous said...

what are you doing the people(EOTC Christians)Living there? and the leaders of the church(diocese)

Anonymous said...

ERE yhe meat endaymtaben!!!egzabher bcherneto ytbken

Anonymous said...

Yes you are right, no. 1 anonymous.
Here in Libanos also the same condition but we have to illegitmate them officially. These are busness men in the name of our holy church.

All readers please assess your environment if there are merchants arround holy water places and post to Deje Selam.

Anonymous said...

በፍፁም መሆን መሆን የሌለበት ይህ ለብዙ ነገር መንገድ የሚከፍት ነው

Anonymous said...

እረ ምንድነው ጆሯችን የሚሰማው እግዚኦ…..
ይህው በአውሮፓ እና በአሜሪካ ብዙ የፕሮቴስታንት አብያተክርስትኖች በግለሰቦች እጅ እንደሚተዳደሩ ስሰማ በጣም ነበር የገረመኝ ከፊሎቹ ምዕመን ሲጠፋባቸው የተሸጡ በአሁኑ ጊዜ ሙስሊሞቹ ገዝተዋቸው መስቀሉን አውርደው ጨረቃ እና ኮከባቸውን እንደሰቀሉባቸው የተቀሩት ደሞ የገበያ አዳራሽ ፤ መጠጥ ቤት እንደሆኑ የተቀረፀ ቪዲዮ ተመልክቻለሁ ይህ ሁሉ ችግር የተከሰተው እነዚያ ሰዎች የቤተክርስትያኗ ራስ ሆነው ስላስተዳደሯት ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራው ምንድነው..? ይህ እኮ የሚያሳየው እነዚህ ሰዎች እግዚሐብሔር መርቷቸው አቤተታ ማሰማት ቻሉ እንጂ ብዙ ሌሎች ላለመኖራቸው ምን ማረጋገጫ አለን ? አሁንም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅሩን መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል፤ በስሩ የሚያስተዳድራቸውን አብያተክርስትያኖችን ፤ ገዳማትን ማን ምን አይነት ሃላፊነት እንደተሰጠው ምንስ መስራት እንዳለበት ማወቅ አለበት ፡፡ ወዴት እየተኬደ እንደሆነ መድረሻውም የት እንደሆነ ለማወቅ ብዙም የማያዳግት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ እባካችሁ ስለዚች ቤተ-ክርስትያን እንፀልይ እግዚሐብሔር ይሰማናል፡፡
እግዚኦ….አምላክ ሆይ መቼ ይሆን ቤቱን የሚያፀዳው ?

Anonymous said...

Some 'priests' in Europe were and are controlling the church by their own. Like their own property, stole all the money, doesn't care about teaching of the church and life of the sheep. Please let's make assessments in abroad too. We can share our experience of some churches in Europe.

Anonymous said...

yes as u all say there so many place doing such things.i agree what it says.but when i come to debreararat amanueal monastery ,it is beyond this.i know this monastery since the beginning of the establishment of the church.i know this father komos aba hailemichael too.in fact,as the writer of this issue mentioned, there no Sunday school,what we call it "sebeka gubae", and other.but what i observe from the place is ,every activity is purely spiritual.there are so many people living in the compound for holy water.but no one paying for the holy water.the monastery revenue is the people.even what i surprise from there is, they didn't ask money from people.( as most of them make it exaggerate begging).he(aba) has one say " balebetu yawukal" .the aba hailemichael leadrsip of the church also has it own quality. for example, they develop bio gas system in the compound for their consumption.and also every spiritual activities are well going as far as i know. so what i suggest is please those writer ,when u raise issue like this , please try to see in all direction , especially u dejeselam don't use copy paste. make internalize the issue first, then come with the detail.

Man yazewal said...

ምነው ጃል አዲስ ሆንክብኝ በሰሜን አሜሪካስ ያሉ አንዳንድ መነኮሳትና ካሕናት ጮሌ ከሆኑ ምዕመናን ጋር ቤተ ክርስቲያን
ን በግል ቁጥጥራቸው ሥር አውለው ሥለምርጫ ሲነሳባቸው ሥለ
አሰራራቸው ግልጥ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁ ይህ ቀበሌ አይደለም መውጣት ትችላለህ ብለው በድፍረት በቤተ ክርስቲያን
መድረክ ላይ የሚናገሩትን በየስቴቱ ምን ያህል የበዙ ናቸው።
በተለይም በመነኮሳቱ በኩል ቀደም ሲል የሃገር ቤቱን አስተዳደር
ሲኮንኑና ሲያብጠለጥሉ ቆይተው ይህን የዋህ ህዝብ በፓለቲካ ጥላቻ ከሰበኩት በኃላ እራሳቸውና ሸሪኮቻቸው ይህ አልባቃ ሲላቸው አገር ቤት እጅ መንሻ ይዞ በመሄድ ጳጳስ ሆነው የመጡትን በማየት እንርሱም ሄደው ጰጵሰው ለመምጣት ሲያስቡ የጵጵስናውም መስፈርት እነ ዋልድባ እነ ማህበረ ስላሴ እነዝቋላ ገዳማት ያሉ አባቶች ያሉበት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ አሜሪካና አውሮፓ ሲሆን እዚስ ምን ሠራ ተብሎ ሳይታይ የሚሾም በመሆኑ የቤ/ክ ፈተና ከጊዜ ወደ ጊዜ እነሆ እየጨመረ መጥቶ። ምናልባትም በኮተቤ የተፈጸመው በኢት ላሉት አስደንጋጭ ነው።
በአሜሪካን ግን ተብሎ ተብሎ አሁን በመጠኑ ሕዝብ እየነቃ የግለሰቦችን ኪስ አናደልብም እያለ ነው።አይ አንቺ ቤተ ክርስቲያን ስንቱ በስምሽ መነገዱና ያቆማል።

Anonymous said...

ወንድማችን ማንያዘዋል ጥሩ ብሏል፤

አሜሪካን የሚገኙ አብያተክርስቲያናችን ሁነታ ተመሳሳይ ነው። ቀሳውስቱ ለምን አሜሪካ እንደመጡ ገና ከሃገር ቤት ሳይነሱ ያውቁታል። አሜሪካ እሄዳለሁ፤ ጥቅት የዋህ ምህመናንን እሰበስባለሁ፤ ጥሩ አባት በመመሰል በንብረታቸውና ጉልበታቸው ቢተክርስቲያን እመሰርታለሁ፤ ቢተክርስቲያኒቱ ገቢ ማስገኘት ከጀመረችና ራሴን ከቻልኩኝ፤ መስራች ምህመናን ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ፤ የተላያየ ስሞችን በመስጠት አናቁራቸዋልሁ፤ ከዚያ በቃ፤ አዲሳባ ላይ ፎቅ መስራት ነው።

ብልህ እንሁን።

እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ እንሁን። ቤተክርስቲያናችንን ከ ጮለ ካህናት እናድን። ህብረታችንን እንጠብቅ። ዝም ብለን እንደበግ አንነዳ።

በአሁን ሰዓት ወንድማችን ማንያዘዋል እንዳለው ምህመናን እየነቁ ነው። በግዘር ፈቃድ ይህ ቤተክርስቲያንችንን ለመታገድ አንዱ መንገድ ነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)