March 5, 2011

የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ይፈጸማል

ደጀ ሰላም፤ ማርች 4/2011)፦ ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ፣ የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ነገ ቅዳሜ በአዲስ አበባው የመንበረ ፀባዖት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ታውቋል። ዛሬ አርብ አስከሬናቸው ካረፈበት ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ካቴድራሉ የተዘዋወረ ሲሆን ሌሊቱን ጸሎተ ፍትሐት እንደሚደረግላቸው ምንጮቻችን በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል።


ልደት እና ዕድገት፤

ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ በአድዓ ወረዳ የረር ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ በ1927 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ፊደልን፣ ንባብ እና ዳዊትን ከመሪጌታ ገብረ ሚካኤል በተወለዱበት አጥቢያ አጠኑ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ወደሚገኘው ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በመምጣት ከቀኝ ጌታ ገሪማ ለሦስት ዓመታት ያህል ዜማን ተምረዋል፡፡

ትምህርት እና አገልግሎት፤

በ1941 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ዲቁናን ተቀብለው በ1943 ዓ.ም ሚያዝያ ወር ላይ ከሁለት ባልንጀሮቻቸው ጋራ ወደ ጎጃም ተሻግረው ቡሬ ዳሞት ወረዳ ሐራ ቅዱስ ገብርኤል በሚባለው ደብር ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ እንዲሁም የሑለት ዘመን ድጓ ዘልቀው ወደ ቅኔ ትምህርት ገቡ፡፡ ለሦስት ዓመታት በቅኔ ትምህርት ተሰማርተው እንደቆዩ ወደ ጎንደር ተሻግረው አፋፍ ወገራ በተባለ ቦታ ለአምስት ዓመታት ያህል አቋቋም ተምረው ወንበር ዘርግተው ሲያስተምሩ፣ ‹‹የለም፣ ወደ ሀገርህ መመለስ የምትችለው ድጓ ስታስመሰክር ነውና የአቋቋም ወንበር አትዘርጋ›› ብለው ጓደኛቸው ስለመከራቸው የድጓ ብራና አውጥተው ወደ ጎንደር ዳባት ቅዱስ ሚካኤል አመሩ፡፡

በዳባት ከየኔታ ገብረ ማርያም ድጓ እየተማሩ በትርፍ ጊዜያቸው ይጽፉ ነበር፡፡ ቤተ ልሔም ወርደው ካስመሰከሩ በኋላ ዙርዓምባ ማርያም ገብተው ዝማሬ መዋስዕት ተምረው እና ጽፈው በጎንደር ዙሪያ ወደሚገኝ ቁራ እጅግ ቅዱስ ገብርኤል በሚባል ደብር ወንበር ዘርግተው ድጓ ማስተማር ጀመሩ፡፡ ለሁለት ዓመት በማስተማር ቆይተው በ1964 ዓ.ም ሐምሌ ወር ወደ ትውልድ ቦታቸው ተመለሱ፡፡

ከ1965 - 1972 ዓ.ም ለስምንት ዓመታት ያህል በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም የብሉያት ትርጓሜን ተማሩ፡፡ ዘመናዊውን ትምህርትም እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ተምረው አጠናቀቁ፤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ወርደውም ሥርዐተ ምንኩስናን ፈጸሙ፡፡ ከ1973 - 1976 ዓ.ም ወደ ዝዋይ የካህናት ማሠልጠኛ በማምራት በርእሰ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ የቅስናን ማዕርግ የተቀበሉት በ1977 ዓ.ም በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ነው፡፡

ብፁነታቸው ለአንድ ዓመት ያህል ወደ ጀርመን ተጉዘው ጀርመንኛ ቋንቋ አጥንተዋል፡፡ ከዚያም መልስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የካህናት አስተዳደር መጋቤ ካህናት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ቀጥሎም የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ምክትል ዲን ሆነው ለአራት ዓመታት እንደሠሩ ከ1986 - 1989 ዓ.ም በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በማስተማር ላይ እንዳሉ ኅዳር አራት ቀን 1987 ዓ.ም የኤጲስ ቆጶስነትን ማዕርግ ተቀበሉ፡፡

ከ1987 - 1989 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከጠረፍ ጠረፍ በማስተማራቸው ብዙዎች ያስታውሷቸዋል፡፡ ከዚያም በኋላ ለአንድ ዓመት የምሥራቅ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕነታቸው በኋላ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ዲን ሆነው ሠርተዋል፡፡ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ሲያገለገሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ከ1999 - 2001 ዓ.ም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሠርተዋል፡፡

ዝክረ ነገር፤

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት በ2001 ዓ.ም በተደረገው የግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እና በሐምሌው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ከቤተ ዘመዳዊ አሠራር እና ሙስና አጽድቶ አስተዳደሩን ለማሻሻል በተደረገው ብርቱ ጥረት ከፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋራ አራምደውት በነበረው አወዛጋቢ አቋም ይታወሳሉ - ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተምረው ስለሚያወጧቸው ደቀ መዛሙርት በአጠቃላይ እና በዲንነት ስለመሩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተለይ በአንድ ወቅት የተጠየቁት ብፁዕነታቸው ተከታዩን መልስ ሰጥተው ነበር፡-

‹‹. . . ገጠር መሄድ ከሁሉም በላይ የሚመረጥ ነው፡፡ እኔ ብዙ ነገር ላውቅ የቻልኩት ገጠር ነው፡፡ አንደኛ የተማርኩት በገጠር ዞሬ ነው፡፡ ሁለተኛም ከተማ ቆይቼ ወደ ገጠር በሄድኩበት ጊዜ ብዙ ዕውቀት ነው ያገኘሁት፡፡ ከሕዝቡ ነው ችግሩ የሚታወቀው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚታወቀው ገጠር ሲወጡ ነው፡፡ ህልውናዋ ተዳከመ ወይ; እንዴት ነው; ብሎ ማወቅ የሚቻለው ወደ ገጠሩ ዞረው ሲያዩት ነው፡፡ እዚህማ(አዲስ አበባ) ብዙ ሕዝብ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለሚጎርፍ ሊታወቅ አይችልም፡፡ የተማሪዎቹ ዕውቀት ታፍኖ እየቀረብን ነው፡፡ ተልእኳቸውን የተወጡም ያልተወጡም አሉ፡፡

. . . የተቋማቱ ተመሳሳይነታቸው ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን መሰለፋቸው ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ በሌላ ቋንቋ ተናግረው ሌላ ሃይማኖት እንዲያስተምሩ አይደለም የምናሠለጥናቸው፤ ያለችቱን ቤተ ክርስቲያን ቀጥ አድርገው እንዲይዙ ነው፡፡ የሌላ ቋንቋ ስላወቁ የሌላውን ሃይማኖት እንዲያመጡብን አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዓለም አቀፍ ተልእኮ እንዲያቃኑ ነው፡፡ የእኛ ት/ቤት ግን ብሔራዊውን(ቅኔ፣ ድጓ፣ ዝማሬ መዋስዕት፣ ቅዳሴ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት) በሚገባ ማስያዝ ማስጠበቅ፣ በዚህ ሞያ ብቁ የሆኑትን ማፍራት ነው ዓላማው፡፡››

6 comments:

Kidus WWEK MS said...

በስመ ሥላሴ አሜን፡፡
እኔ በጣም የሚገርመኝ በተለያዩ ቦታዎች ዞረው የእውቀት ምንጭ መሆናቸው ነው፡፡ እንደዚህም ሆነው ተምረው ምንም አናውቅም ነው የሚሉት፡፡ አንድ ጥቅስ ይዘው አስር ቦታ ካልረገጥን የሚሉት ፣እንደ መብረቅ ነጎድጓድ ድምጻቸውን በማጮህ ብቻ መጋቢ ሐዲስ የተባሉት ከእነዚህ አባቶች ምን ይማሩ ይሆን ?
እንዴው ወደፊትስ እንደ እርሳቸው በየገጠሩ ተዘዋውረው ከተለያዩ መምህራን እውቀት የሚቀስሙ አባቶች ይገኙ ይሆን ?
ለአባታችን እረፍተ ነፍስ ይስጥልን፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡ ተተኪ አባት ደግሞ አያሳጣን፡፡ አሜን፡፡

Wudasse Ephrem said...

አንድ ሊቅ አረፈ ማለት አንድ ቤተ መጻህፍት ተቃጠለ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሌላ ቤተ መጻህፍት ይክፈትልና፡፡

Anonymous said...

YEFETARI TIRI YETHDQ ENDEHONE YASTAWQAL,KEAMSALE EYERUSALEM KIDST BETEKRSTIYAN WEDE SEMAYAWITWA EYERUSALEM. BITUABATACH BIZU SINTEBQNA SIYASBU YEQN GODELO HONEBNI. YESIST AYNI BEZABOT YIHON,ALSHENEF BAYNETWON EWNETEGHA EREGHA MEHONHO LETIQAT DAREGHO YIHON,......WEYSI MIN? BITU ABATACHN KEMNM BELAY YEMIYASFELGUN SEAT LAY NEBERU. MINM EKO YERJNA MENFES,TESFAYEMEKURET AZMAMIYA AYTAYBOTM NEBER. BITU ABATACHN KEQDUSAN ATHED HONEW KIDIST HAGER ETHIOPIANNA BETEKRSTIYANINI BETHELOTWO YASBULN. BEKUMACHEW KEMOTUNA MIGBARACHEW SEW YEMIGELUTN YENSHA EDME ENDISETACHEWNA YEFETARIM SIRA ENDIGELETH YITHELYU.HULEM BEREKTWO YIDERBN,TATARINETWONA EWNETEGHA NETWON ENKETELALEN. MANIM YEQOME BIMESLEW ENDAYWEDQ YITENKEK

Wubshet said...

Bereketachewu Yiderben, Nefesachewun Yimarlen.

My other information Dear Deje Selam "have you heard that Muslims in Jimma zone-Assendabo, Dimtu, Serbo towns are Firing protestants Office and home.There are so many federals and Feteno Derash From Zone but doing nothing. They Are simpling Bagging the Muslims not to do that. They have fired more than 10 "tselot bet" and more residential houses ...., what will be next? Please have the information & say something.
The help of God with his mother marry be with US.
Welde Michael from A.A.

wolde hawaryat said...

betam yasazinal hamus liarfu ehud ene yalehubet debir metew agelgilewal egziabher yemiwodachew tilik abat neberu ............egziabher sete egziabher nesa yegziabher sim yetemesegene yihun!!!!!!!!!

wolde hawaryat said...

EGZIABHER SETE EGZIABHER NESA YEIGZIABHER SIM YETEMESEGENE YIHUN!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)