March 13, 2011

በጅማ በተከሰተው ግጭት ከ130 በላይ ሰዎች ታሰሩ

- የተቃጠሉት ቤተ ክርስቲያኖች 59 ደርሰዋል

(በዘካሪያስ ስንታየሁ ለሪፖርተር ጋዜጣ):- በጅማ የካቲት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ከ130 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ቀን አንስቶ 59 ቤተ ክርስቲያኖች የተቃጠሉ ሲሆን፣ የአንድ ግለሰብ ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ንጉሴ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ለፍርድ እየቀረቡ ነው፡፡ የተቃጠሉት ቤተ ክርስቲያኖች ቁጥር ወደፊት ተጣርቶ እንደሚቀርብም ገልጸው፤ ይህንንም ያደረጉት ግለሰቦች ለፍርድ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡ ሆኖም አንድም ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ስህተት ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

እንደ ምንጮች ገለጻ፣ 38 የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያኖች የተቃጠሉ ሲሆን፣ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅና ሁለት የቤተ ክርስቲያኒቱ ቢሮዎችም ተቃጥለዋል፡፡ በተጨማሪም 12 የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኖች፣ ሁለት የሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያኖች፣ ስድስት የአድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያኖችና አንድ የሐዋርያት (ኦንሊይ ጂሰስ) ቤተ ክርስቲያን ተቃጥለዋል፡፡

የካቲት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. በአሰንዳቦ በሚገኝ የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁራን ተቀዶ ሽንት ቤት ውስጥ አግኝተናል በሚል ግጭቱ መቀስቀሱ ይታወሳል፡፡ አቶ አብርሃምም የግጭቱ መነሻ ሃይማኖታዊ ቢሆንም፣ ከበስተጀርባው ያለው አጀንዳ በምርመራ ላይ ነው ብለዋል፡፡

በጅማ በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ሲቃጠሉ፣ ከ4000 በላይ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ሲሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ አብርሃም በበኩላቸው ግጭቱ በቁጥጥር ሥር ውሏል ብለዋል፡፡ ግጭቱን ለመቆጣጠር ከሳምንት በላይ ለምን እንደፈጀም ሲያስረዱ፣ ቤተ ክርስቲያኖቹ የሚገኙት ተራርቀው በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የኦሮሚያ ፖሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

16 comments:

Kolo Temari said...

The so called cause is babyish reason.

If they are really muslim who believe in Allah's word, though the Quran is teared, the word of Allah is not teared; rather it will tear them to those who teared it.

If we count our Orthodox books, holy photos etc, numberless are burnt by protestants and muslims but we didn't put any accusations before because we believe in God and in His words not in papers-materials.

However, I don't mean giving respection to the holy books and materials has no value but if inconvenient conditions are happened over them we should not take it as serious issue.

tamagn said...

Unless the government imprisoned the akraians throught their full life time,the rest akrarians cannot learn to save their hands from doing bad things.

Anonymous said...

To me any thing which damages any resource is evil, but Ato Abriham is trying to take it as political problem; yes it is! how ever it has the potent messege for the religion. So the religious leaders should wake up now and give response before thing became worst.

Enbaqom said...

Our country Ethiopia is one of the ancient nations which lead their people with rules and regulations. Why don't these people be punished under the law of the government?

Yes spiritually, their act is exactly to the opposite of Christianity which declares LOVE for ones enemies. But, as citizens, people should have respected the current law of the country. By the way We can not change Muslim dogma which preaches hatred against the human race.
And i am sure now, if they could hear me saying this, they could kill me instead of giving the so-called their "jenet" to me.
So i am calling to the government not to Muslim for peaceful leadership and give justice to the persecuted brothers.

Kidus Ephrem MS said...

ራስህን ቆሎ ተማሪ ብለህ የጠራኸው የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ

እንዴት አድርገህ ነው ኦርቶዶክስን የተረዳኸው? የእግዚአብሔር ቃል ያለበትን ወረቀት እንደተራ የሚቆጥር እምነትማ የለንም፡፡ አንኳን ቃሉና ስዕሎቹ ያሉበት አንድ ቃል እንኳን ስትነጥብ ቅዱሳን ያነባሉ /ድርሳነ ሚካኤልን ተመልከት/፡፡ በእርግጥ በልባችን ውስጥ ያለውን እምነት ማንም ሊቀማን አይችልም፡፡ ሙስሊሙም ፕሮቴስታንቱም ፓጋኑም አላውያን ነገስታቱም ቢዘምቱብን ፈጣሪያችንን ከማምለክ ወደኋላ አንልም፡፡ ግን ማቴሪያል ነገሮች ሲሪየስ ኢሹ አይደሉም ያልከው ከቤተክርስቲያኗ አስተምህሮና እምነት ጋር የሚጋጭ ነው፡፡

ካልሆነ ግን አንተ የቆሎ ተማሪ ሳትሆን የኬክ ተማሪ ነህ፡፡

አክራሪ ሙስሊሞች የሐጢአታችን ውጤቶች ይመስሉኛል መቃወም ብቻ ሳይሆን ‹አቤቱ በድለናል› ብለን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፡፡ በተለይ የእግዚአብሔርን ገንዘብ እየዘረፍን የሰባን አገልጋዮች እግዚአብሔር የማይፈርድ እንዳይመስለን ለእርድ እየተዘጋጀን መሆኑን እንዳንዘነጋ፡፡ የሚጀመረውም ከቤቱ ነው፡፡ት.ሕዝ. ም. 34 በማስተዋል እናንብብ፡፡

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ፡፡›› ይላል ሉቃ.13፥5

እግዚአብሔር አምላክ የኢትዮጵያን ትንሳኤ የተዋህዶን ልዕልና ያሳየን፡፡ አሜን፡፡

Anonymous said...

if we condemin the act we should also cry when some christians dem,olish more than 8 mesjid in gurage & addis ababa
befare.any act to destroy mesjid or church is terrorist act.so if besjid burn you keep quite but for the church you cry..is it fare?

Anonymous said...

ይህ ሁሉ ስለ ሀጥያታችን ነው መፀለይ ነው ሌላ ምን ይባላል? አቤቱ የሆነብንን አስብ ብሎ መፀለይ ያዋጣል
ከዚህ ባሻገር ግን መንግስት ለሌላው ነገር ፈጥኖ መልስ እንደሚሰጥ ሁሉ ይህንንም ጉዳይ በአፋጣኝ አንድ ሊለው ግድ ይላል:: እንግዲህ ከሀገራችን ወዴት ሄደን ማምለክ ይቻላል? የባለፈው የጅማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰማእታት ወገኖቻችን ቸል ሲባል ነው እዚህ የደረስነው ! ! !
የድንግል ማርያም ምልጃ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቃት

Anonymous said...

መን ዋጋ አለው
በሻሻ ገ/መ/ቅዱስ ቤ/ክ ና በኢሉባቦር ለደረሱት ህዝብን አስተማሪ የሆነ እርምጃ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ነገሮች ባልተደጋገሙ ነበር፡፡
ሌላው ይቅርና በደጀሰላም ላይ የወጡትን ዜናዎች ብቻ አይቶ በጅማና በኢሉባቦር መንግስት እንዳልነበረ በደንብ ያስገነዝበናል ምክንያቱም አጥፊውን የሚያበረታታ እንጂ የህግን የበላይነት የተንጸባረቀበት አልነበረም፡፡
እጅግ ከሚገርመው ነገር ግን እያንዳ ጥፋት ጀርባ በመንግስት የተወከሉ ባለስልጣናት ሚናቸው በፊትለፊት ጥፋት ከሚያደርሱት የበለጠ ነው፡፡ መንግስት ግን የቆመው ለህዝብ ወይስ ለግለሰቦች?

Anonymous said...

ቅዱስ ኤፍሬም አንዳለ ያልከው
አንድ ጥያቄ ልተይቅህ ፣ አንድ ሰው መፀሐፍ ቅዱስ አየቀደደ ብታገኘው ትገለዋለህ ዎይስ ማድረግ አንደሌለበት ታስተምረዋለህ? ሰው አንደጥፋቱ ከሆነ ፍርዱ አንተ ማን ነህ አና ሰው የምትገለው ጌታ አንኩአን አሄን አያደርገዉም።ሰው መግደል ይሻላል ወይስ ማስተማር። አረ ለመሆኑ መላአክት ሰው ሲገደል አያዝኑም ያለህ ማነው? አንተ ወንድምህ ቢገደል ደም ታነባ ነበር። አግዚአብሔር በኛ በደል ያመጣው መዓት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ንስሐ መግባት አለብን ያሰኛል አንጂ ገዳዮች ትክክል ናቸው አያሰኛቸዉም። በአግዚአብሔር የሚአምን ቢቀድ ይገርማል ነገር ግን የማያምን ቢቀድ አይገርምም አያምንም አና። ደግሞ የቀደደው የማያዉቅ ሕፃን ልጅ ቢሆንስ? በመጀመሪያ ደረጃ የተቀደደበት ምክንያት ሁሉ መታየት ነበረበት። ስለተቀደደ ብቻ ከሆነ መጋደሉ አራሱ አማኝ የሆነው መገደል ሊኖርበት ሁሉ ይችላል። አስቲ ስንቶቻቸን ነን ከቤታቸን የተቀደደ አና የተጣለ ዉዳሴ ማሪያም የሌለን? ቤት ይፍጀው። በዚህ አይነት ሁሉም መገደል ነበረበት ባንተ አባባል። አኔ ለማንኛዉም የቤተክርስቲአን መፅሐፍ ክብር መሰጠት የለበትም አያልኩ አደለም ግን የተከሰተበት ሁኔታ ማጤን አና መረዳት ያስፈልጋል ከዛም አልፎ ከመግደል በሌላ መልኩ ሰወቸን ማስተማር አና መለወጥ ያስፈልጋል አንጂ ሽብር መፍጠር ያለብን አይመስለኝም። አመሰግናለሁ ።።

Unknown said...

Yes of course, the problem is serious and that should be prohibited and every human being should be protected from such attack and we should talk until fair judgement is coming. However, we should use proper terms at every of our speech. Christians are those true followers of Christ, not those who call themselves 'Christians'. Protestants are not the true followers of Christ, but the protesters against the true and the old path, TEWAHEDO. Dejeselamawian, please teach us the correct teaching of our fathers: One Religion (TEWAHEDO), one God and one Church. The rest are Faith related Organizations.

habtshei said...

should this be the way to express passion??? is that what we learnt from Quran and the Bible, as the case may be????O,Ethiopians, where is our country heading to?May the almighty God keep Ethiopia from enemies. i love all of you as my Savior Jesus loved me.

Unknown said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
አንደነሱ (አንደ በጋሻው) ሃሳብ ቢሆን ኑሮ ሁላቸንም ሃይማኖታቸንን ቀይረን ነበር። አሁንም ጌታችን ፣አምላካቸን፣ መዳኒታችን አየሱስ ክርስቶስ ከኛ ጋር ነው መቸም ወደአናንተ አንመጣም። አረ ስንቴ ልቤን አቁስላችሁታል አራሴን አስክጠራተር ድረስ። ኧረ ለመሆኑ የየሐገራቱ ጳጳሳት ለምን ይሆን በተደጋጋሚ ሲቸፍሩበን ዝም ብለው የሚያዩት? አንዴዉም አኮ አነሱ ናቸው ፈቃድ የሚሰጧቸው።አዉነት አነሱ አዉነቱን አና ዉሸቱን መመርመር አቅቶአቸው ነው ወይስ አነሱም ተሃድሶ ሆነው ነው? መንጋዉን መጠበቅ የማን ሥራ ሆነ አና ነው አንደዚህ ችላ የሚሉት? ምናለበት ለአዉነት ስትሞቱ ብናያችሁ። አግዚአብሔር ልብ ይስጠን። የምህረት አምላክ ቤተክርስቲአንን ይጠብቅልን።የአግዚአብሔር ሰላም የቅድስተ ቅዱሳን አረዴት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

መርከቤ ንጉሴ /ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ።አሜን!!

እነዚህ አመለካከታቸው የተዛባ ጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች እኮ ቁራን ተቀደደ ብለው ችግር ሲፈጥሩ የመጀመሪያቸው አይደለም በአንድ ወቅት በአ.አ.ዩ. ሳይንስ ግቢም አንድ ተማሪ የተቀደደ ቁራን በእጁ ላይ ተገኘ ብለው ቀላል የማይባል ረብሻ ፈጥረው እንደነበር እስታውሳለሁ። ሆኖም የማንኛውም እምነት ተከታይ መፅሐፍ መቀደድ እንደሌለበት እኔም የምጋራው ሐሳብ ሲሆን ቁራን ተቀደደ ብሎ እንደዚህ የከፋና የዘቀጠ ድርጊት ውስጥ መግባት ለጠብ-አጫሪነት ምክነያት መፈለግ ይመስለኛል። እውነት ለመናገር እኛ ኦርቶዶክሳውያን መፅሐፍ ቅዱስ ተቀዶ ብናገኝ ምናልባት ይህን መፅሐፍ ቅዱስ ማን ቀደደው? ለምን ተቀደደ? ብለን እንጠይቅ እንደሆነ እንጂ እንደዚህ አይነት የአረመኔ ተግባር በመፈፀም ጠብ-አጫሪ እንሆናለን ብዬ አልገምትም። ይህ ደግሞ የእግዝአብሔርን ቃል የመናቅና ሐይማኖትን ያለማክበር ጉዳይ አይመስለኝም። ለምን ተቀደደ ብለን ባንጠይቅም እኮ በድፍረት ቅዱስ ቃሉን የቀደደው ግለሰብ በፈጣሪ ዘንድ መጠየቁ አይቀርም። ፕሮቴስታንቶቹም ይህን አያደርጉም ለማለት ባልደፍርም እዚህ ደረጃ ግን ሊያዳርስ አይገባም።ደግሞም ቅዱስ ቁራንም ሆነ መፅሐፍ ቅዱስ በተለያየ ሁኔታና አጋጣሚ ሊቀደድ ይችላል። KOLO TEMARI የተባሉት ግለሰብም ካልተሳሳትኩ ጉዳዩን እንደ አንገብጋቢ ጉዳይ አናየውም ማለታቸው ከዚህ አንፃር ይመስለኛል።

ቸሩ ፈጣሪያችን ለሁላችም ማስተዋሉን የድለን። አሜን!!
መርከቤ ንጉሴ /ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

Ethiopia ejochuan wede Egziabher tizeregalech

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)