March 29, 2011

አቡነ ጳውሎስ እና ፕሮቴስታንታዊ የተሐድሶ-ኑፋቄን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ እየፈጠሩ ያሉት ጫና (ጥልቅ ሪፖርታዥ)

   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 29/2011)፦ ማክሰኞ፣ የካቲት 14 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀትር በኋላ፤ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ስልክ የተመታላቸው አንድ የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ከፍተኛ ሓላፊ መረጃ የሚቀበሉ የደኅንነት መኰንኖችን በአስቸኳይ እንዲልኩ ይጠየቃሉ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሁለት የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት አባላት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊት ይገኛሉ፡፡ ከጥቂት የመግባቢያ ጭውውት በኋላ ፓትርያርኩ፣ “ለመሆኑ ምን እየሠራችሁ ነው? ሰሞኑን ወጣቶቹ [ማኅበረ ቅዱሳን] ምን እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ታውቃላችሁ? እንዴ፣ የዐረቦቹ ብጥብጥ'ኮ የተነሣው በወጣቱ ነው?” ሲሉ ልብ እና ማስተዋላቸውን ይገዛል ያሉትን አገባብ ተጠቀሙ፡፡

   March 25, 2011

   "Muslim Extremists Torch Protestant Churches": Two Related News

   Ethiopia’s religious divide flares up in violence 
   ASENDABO, Ethiopia (Reuters) - The hollow chants of "Allahu Akbar!" reverberating from a distance seemed innocuous at first for Abera Gutema, who ventured home quietly from his shop just a short distance away. Moments later, a large, angry mob of machete-wielding Muslim youths descended on his family's dwelling and chased him out, before burning and looting his property.

   March 19, 2011

   በጅማ በሃይማኖት ሽፋን ጉዳት ያደረሱ ወገኖች በቁጥጥር ሥር ባለመዋላቸው ቅሬታ እየቀረበ ነው


   • መንግሥት በግጭቱ “የአልሸባብ እጅ አለበት” ይላል:: ነዋሪዎች አልተቀበሉትም
   (ሰንደቅ፣ በጋዜጣው ሪፖርተር፣ መጋቢት 7 ቀን 2003 ዓ.ም)፤ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በሊሙ ኮሳ ወረዳ ከሳምንት በፊት በተከሠተው የሃይማኖት ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ባለመዋላቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ነዋሪዎቹ ገለጹ፡፡ የጅማ ኢሚግሬሽን እና ደኅንነት ጽ/ቤት ያወጣው ደብዳቤ በበኩሉ፣ መንግሥት ባለው መረጃ የድርጊቱ ቀስቃሽ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ሳይሆኑ ከሶማልያ የመጡ የአልሸባብ አባላት መሆናቸውን፣ ስድስት የአልሸባብ አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ሌላ ሃያ ተጠርጣሪ ተጨማሪ የአልሸባብ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

   March 17, 2011

   የበገና ደርዳሪዎች ተመረቁ

   (ሪፖርተር ጋዜጣ):- በማኅበረ ቅዱሳን ሥር የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ የአብነትና የዜማ መሣርያዎች ማሰልጠኛ ተቋም ለስድስት ወራት በበገና አደራደር ትምህርት ያሰለጠናቸው 185 ተማሪዎች ባለፈው ቅዳሜ አስመረቀ፡፡ በኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል መጋቢት 4 ቀን 2003 ዓ.ም. በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ የአገሪቱን ታላቅ ቅርስ የኾነውን

   March 13, 2011

   ማን ለእስራኤል መድኃኒትን ከጽዮን ይሰጣል?

   (በኤርሚያስ ኅሩይ በተለይ "ለደጀ ሰላም"):- ዓለምና በዓለም ያለው ማንኛውም ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ነገር ሁሉ የፍጥረታት በኹር የሆነውን የሰውን ልጅና ደመ-ነፍስ ያላቸውን እንስሳት አራዊት ጨምሮ ከሰው አእምሮ በላይ በሆነ ፍጹምና ረቂቅ አምላካዊ ጥበብ የሚያልፍ መሆኑ ማስረጃ የማይሻ እውነታ ቢሆንም ሰው በዚህች ምድር ላይ ሲኖር እያንዳንዷን የዕድሜውን ሽራፊ ደቂቃ በሚፈልገው ሁኔታና መጠን ተደስቶና ረክቶ ለመኖር ከሚያስችሉት እጅግ አስፈላጊ ነገሮች አንዱና ዋነኛው የሀገር ደህንነት ነው።

   በጅማ በተከሰተው ግጭት ከ130 በላይ ሰዎች ታሰሩ

   - የተቃጠሉት ቤተ ክርስቲያኖች 59 ደርሰዋል

   (በዘካሪያስ ስንታየሁ ለሪፖርተር ጋዜጣ):- በጅማ የካቲት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ከ130 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ቀን አንስቶ 59 ቤተ ክርስቲያኖች የተቃጠሉ ሲሆን፣ የአንድ ግለሰብ ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

   March 11, 2011

   ተሐድሶ - በወሊሶ

   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 11/2011)፦ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-መናፍቃን እምነት አራማጅ ነው የሚባለው “የቅድስት ማርያም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማኅበር” በሚል ራሱን የሚጠራው ቡድን ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በማናለብኝነት በመጣስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በመተላለፍ የሚፈጽመውን ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል የቡድኑ መሪዎች በዐቢይ ጾም በወሊሶ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ከበሮ በመምታት ምእመኑን ሲያውኩ  እና ግራ ሲያጋቡ አምሽተዋል፡፡

   March 10, 2011

   የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ድርሻና ውለታ!

   (አቶ ፍቅር ለይኩን ከደቡብ አፍሪካ በተለይ "ለደጀ ሰላም"):-  የዓድዋ ድልን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን በስንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ በማኅበረ ቅዱሳን የምርምርና የጥናት ማእከል ድሉን አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ የነበራትን ሚና ለማዘከር በአዲስ አበባ በብሔራዊ ሙዚየም የተደረገውን ውይይት ዜና በደጀ ሰላም ማንበቤ በውስጤ አንድ ስሜት አጫረብኝ፤ እናም ስለ ድሉና ቤተ ክርስቲያናችን ስለነበራት ታላቅ ድርሻና ወለታ ጭምር ጥቂት ለመጨመር አስብኩና ብእሬን አነሳሁ።

   የዓድዋው ድል ታሪካዊ ፋይዳ

   ፎቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ
   ‹‹ትልቁ አደጋ የተጋረጠበት የኢትዮጵያ ታሪክ ይመስለኛል›› (አቶ ሽመልስ ቦንሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር)
   (ሔኖክ ያሬድ ለሪፖርተር ጋዜጣ):- ለኢትዮጵያውያን በተለይም ለጥቁሩ ዓለም ፈርጥ የኾነው በኢጣሊያ ላይ የተመዘገበው የዓድዋ ጦርነት ድል በያመቱ የካቲት 23 በመጣ ቁጥር በታላቅ ክብር ይዘከራል፡፡ ዘንድሮም ለ115ኛ ጊዜ ሲከበር ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ፣ ከአፍሪካ እስከ መዲናዋ ኢትዮጵያ ድረስ በልዩ ልዩ መልክ ተከብሯል፡፡ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣም ከ115 ዓመት በፊት የዘገበውን አካትቶ ያቀረበው መሰናዶም ነበር፡፡ በኢትዮጵያም ከተለምዷዊ አከባበር በተለየ መልኩ በዓድዋና በአዲስ አበባ ዐውደ ጥናቶች ተዘጋጅተው ነበር፡፡

   March 9, 2011

   የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዐድዋ ድል የነበራትን ድርሻ የዘከረ ውይይት ተካሄደ


   “ኢትዮጵያዊሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ”...
   Photo 1 © The British Museum - 2007
   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2011)፦ ለጦርነቱ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምህላ ታውጇል፤ ዘማች ታቦታት ተመርጠው የአዝማች ኮሚቴም ተቋቁሟል፤ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘማች ታቦታቱ መሪ ነበር፤ ለመላው ዘማች ሠራዊት ሥነ ልቡናዊ ጥንካሬን (የሰማዕትነት ወኔን) የሰጠ የሰባት ቀናት የቁም ፍትሐት ተደርጓል፤ ሊቃውንቱ ከጦርነቱ በድል እንደምንመለስ በቅኔያቸው ትንቢት ተናግረዋል፤ ዐፄ ምኒልክ የክተት ዐዋጅ ካስነገሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው “አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን ቤተ ክርስቲያን የሣር ክዳኑን ለውጨ ባማረ ሕንጻ አሠራዋለሁ” ብለው ብፅዓት አድርገዋል፡፡

   ርዕሰ አንቀጽ፡ በጅማ ፕሮቴስታንቶች ላይ የተፈፀመውን የአክራሪዎች ጥቃት ልንቃወም የሚገባበት ምክንያት …

   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2011)፦ በጅማ አካባቢ ባሉ ሥፍራዎች “በጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች” የተፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡትን ዘገባ እኛም በድጋሚ ትኩረት ሰጥተን ማስተናገዳችን ይታወቃል። እናውቃለን ፕሮቴስታንቶቹ የእኛኑ አማኞች ከርትዕት እምነታቸው ለማፈናቀል እንደሚጥሩ። እናውቃለን አብዛኞቹ ዛሬ “ፕሮቴስታንት ነን” ያሉት ወገኖች በእኛው ቤተ ክርስቲያን በ40 እና በ80 ቀናቸው የተጠመቁ እንደነበሩ። እናውቃለን ቤተ ክርስቲያናችንን በመናቅ እንደሚናገሩ። እናውቃለን ከዚህ በፊት በኦርቶዶክሳውያን ክርስቶያኖች ላይ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲፈፀም ድምጻቸውን እንዳላሰሙ። ነገር ግን አሁን የጥቃቱ ዒላማ እነርሱ ስለሆኑ ልንደሰት፣ ዝም ልንል፣ “ይበላቸው” ልንል አንችልም። ክርስትናችን አይፈቅድልንም። ይህ አደጋ የደረሰው በክርስቲያኖችም ላይ ሆነ በሌሎች እምነት ተከታዮች ላይ ድርጊቱን እናወግዝ ዘንድ እምነታችን ግድ ሊለን ይገባል። ይህንን የፈፀሙት ፕሮቴስታንቶቹ፣ ተጎጂዎቹ ሙስሊሞቹ ቢሆኑ ኖሮ ተጎጂዎቹን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ደግፈን ወንጀሉን የፈፀሙትን እንቃወማቸው ነበር። ጥያቄው “ማን ነው የተጎዳው?” ሳይሆን “ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ይጎዳል?” ነው። አመክንዮዋችንን በሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ እናጠቃለው።

   ጀርመን ሬዲዮ (DW) & አሜሪካ ድምጽ (VOA) ሪፖርታዥ About "Jimma" Area


   ጀርመን ሬዲዮ (DW) & አሜሪካ ድምጽ (VOA) ሪፖርታዥ About "Jimma":
   http://www.youtube.com/watch?v=VOcGhDjveCw

   ጅማ- የሚመለከታቸው በሚገባ ያልተመለከቱት አካባቢ

   ማስታወሻ፦ ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ በፀሐፊው ፈቃድ ከፌስ ቡክ ላይ ተወስዶ እዚህ የተለጠፈ ነው። መልካም ንባብ።
   ++++
   ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ
   (ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ):- ጅማ ከ፲፱፻፺፱ ዓም ጀምሮ ስሟ በክፉም መነሣት ጀምሯል፤ የአካባቢውን ነዋሪና አስተዳደር ስሜት ለሚረዳ ይህ ጥሩ አይደለም። መረጃዎችን በግንጥሉ ለሚሰማ ደግሞ ጅማ ላይ ብቻ የተከሠተ አድርጎ ያየዋል። ሌሎችም መታየት ያለባቸውንና የሚመለከታቸው ቢያስቡበት መፍትሔው የማያስቸግረውን ጉዳዮች ብናነሣስ? ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በልማቱ ከተዘነጉትና አሁን በመጠኑ በልማቱ ወላፈን ከሚጎበኙት አካባቢዎች አንዱ ነው። ላያቸው ግን ሁሌም የማይረሱና ለመላው ኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም የሚበቃ ሀብት እየታፈሰባቸው ነው፡-

   March 8, 2011

   የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ በግለሰቦች መተዳደር ቅሬታ አሥነሳ


   /አዲስ አድማስ፣ ዘኤልያስ ወልደ ሚካኤል፣ ቅዳሜ፣ የካቲት 26 ቀን 2003 ዓ.ም/፤ የኮተቤ ደብረ አራራት ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን እና አገልጋዮች ቤተ ክርስቲያኑ በግል ይዞታ ሥር መሆኑን ተቃውመው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አቤቱታ አቀረቡ፡፡

   March 6, 2011

   "በጅማ ዘጠኝ {የፕሮቴስታንት} ቤተ ክርስቲያኖች ተቃጠሉ" (ሪፖርተር ጋዜጣ)

   We know this news is about Protestants. ..... But does not this news tell you any message when you read it? This time it is them; what about next time? They are Ethiopians and they have every right to practice their belief. We oppose their "Sheep-stealing" and defend our Church from their heretic teachings, but we don't want them to be massacred, their worship places burned down, their houses ransacked. That is inhuman. Thus, we oppose what the fanatics did.
   Deje Selam.

   (በዘካሪያስ ስንታየሁ/ ሪፖርተር ጋዜጣ):- በሚኒስትር ማዕርግ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ለብሉምበርግ በሰጡት መግለጫ፣ ለአምልኮ መገልገያ የሆኑ ሁለት ቤቶች መቃጠላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹ማንም ሰው አልሞተም፤ ጉዳዩም ያን ያህል የተጋነነ አይደለም›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

   የብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ የቀብር ሥነ ሥርዐተ ተፈጸመ

   • ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ለመሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ነበር
   • ‹‹ብፁዕነታቸው በመንፈሳዊው ትምህርት የተሟላ ሊቅነት ያላቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔርን በዝማሬ መላእክት፣ ሕዝበ ምእመናንን በትምህርት፣ በስብከተ ወንጌል እና በጸሎተ ቡራኬያቸው ያገለገሉ ያሬዳዊ ቅርስ ነበሩ፡፡›› (ዜና ሕይወታቸው)
   • ‹‹ድጓው፣ ጾመ ድጓው፣ ዝማሬ መዋስዕቱ አልሞተም፤ እዚያው ከዋናው ከቅዱስ ያሬድ ጋራ በሰማይ ያመሰግኑበታል፤ የካቲት 24 ቀን የተክለ ሃይማኖት በዓል ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም እንዲቀድሱ ተራ ደርሷቸው ነበር፤ ነገር ግን በወዲያኛው ዓለም ከእነ ቅዱስ ያሬድ እና ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋራ እንዲቀድሱ ተጠሩ፡፡›› (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ)
   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 5/2011)፦ ከትናንት በስቲያ በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በ76 ዓመታቸው ያረፉት የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ሥርዐተ ቀብር ዛሬ፣ የካቲት 26 ቀን 2003 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡ የብፁዕነታቸው አስከሬን ትናንት ዓርብ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት ወደ ካቴድራሉ ተወስዶ ጸሎተ ፍትሐት ሲደረስለት ያደረ ሲሆን በመላው አህጉረ ስብከትም ጸሎተ ፍትሐቱ ተደርጓል፡፡

   March 5, 2011

   የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ይፈጸማል

   ደጀ ሰላም፤ ማርች 4/2011)፦ ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ፣ የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ነገ ቅዳሜ በአዲስ አበባው የመንበረ ፀባዖት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ታውቋል። ዛሬ አርብ አስከሬናቸው ካረፈበት ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ካቴድራሉ የተዘዋወረ ሲሆን ሌሊቱን ጸሎተ ፍትሐት እንደሚደረግላቸው ምንጮቻችን በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል።

   March 4, 2011

   ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ (1927 - 2003 ዓ.ም) ሲታወሱ

   • ‹‹የምናሠለጥናቸው በሌላ ቋንቋ ተናግረው የሌለ ሃይማኖት እንዲያመጡ አይደለም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ በ1991 ዓ.ም ከተናገሩት)
   •  ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል፤
   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 4/2011)፦ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ማረፋቸውን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል። ብፁዕነታቸው በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸው የተሰማው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በመንበረ ፓትርያርኩ ከሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ነው፡፡

   ከአንድ ወር በኋላ ሥልጣኑን የሚረከበው የቀጣዩ ቋሚ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፈትኖ ላቀረባቸው በርካታ ዲያቆናት ከሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋራ የቅስና ማዕርግ ሰጥተዋል፡፡

   March 3, 2011

   ሰበር ዜና፦ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አረፉ

   (ደጀ ሰላም፤ ማርች 3/2011)፦ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ፣ የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣  ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም አረፉ። የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕነታቸው ዛሬ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ማረፋቸው ታውቋል። በቤተ ክርስቲያን የዕለቱን ሥርዓተ ቅዳሴ ተካፍለው በደህና የተመለሱት ብፁዕነታቸው በድንገት ማረፋቸው የታወቀ ሲሆን መንስዔው ከልብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮቻችን ገልጸዋል። ብፁዕነታቸው ያረፉት በአዲስ አበባ ነው። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን።

   Blog Archive

   የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

   ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)