April 12, 2011

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተዘረጋባትን የተሐድሶ ወጥመድ ይፋ አድርጓል የተባለ “ሰነድ” ይፋ ሆነ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 5/2011፤ ጥር 29/2003 ዓ.ም)፦ ከ1920ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እና ትውፊት በመለወጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እና መዋቅሮች ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሠሩ የተሐድሶ ኑፋቄ ማኅበራት እና ድርጅቶች በተለዋዋጭ ስልቶች ሲማስኑ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ጥረታቸው ያሰቡትን ያህል ያልተራመደላቸው የተሐድሶ መናፍቃኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ‹‹ከውስጥ እያጠቁ ወደ ውጭ በመገስገስ እና ከውጭ ከበባውን አጠናክሮ ወደ ውስጥ በመግፋት›› ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አልያም ውጥንቅጧን አውጥቶ ለሁለት ለመክፈል ስልት ቀይሰው፣ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማእከል አድርገው በመንቀሳቀስ ላይ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ሰነድ ሰሞኑን ለደጀ ሰላም ደርሷል፡፡በልማት ስም የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋማት በሚያደርጉላቸው ከፍተኛ የገንዘብ፣ የሥልጠና እና የስልት ቅየሳ እየታገዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥ በማተራመስ እና ከውጭ በማስጨነቅ አዳክሞ ፕሮቴስታንታዊ አድርጎ ለመውረስ (Reformed Church) አልያም የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ እና ተያያዥ ችግሮች ሃይማኖታዊ ይዘት በመስጠት ምእመኑን ማነሣሣት፣ ጉዳዩ የተሟላ ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ መልክ ሲይዝም እንደ ሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ለመክፈል የተሐድሶ ኑፋቄ ማኅበራት እና ድርጅቶች በእያንዳንዷ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሸርቡት ሤራ እና የሚያደርሱት ጥፋት ‹‹እጅግ አስፈሪ እና አሳሳቢ›› እየሆነ መምጣቱ በሰነዱ ላይ ተገልጧል፡፡ ሁኔታው እስከ አሁኑ እንደሚታየው እንደ ሌለ ተቆጥሮ ዝም ከተባለና ተገቢው ስልት ተነድፎ ተመጣጣኝ ቅንጅታዊ ሥራ ካልተሠራ የቤተ ክርስቲያን ህልውና ከባድ ጥያቄ ምልክት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተሐድሶ መናፍቃኑ ታላቁ ሤራ ከቀድሞው በተለየ አኳኋን በመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ቅዱስ ፍሬምናጦስ እና በአዲስ አበባው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጆች ጠንካራ አደረጃጀት ፈጥሮ ጥቂት በማይባሉ መምህራን፣ ደቀ መዛሙርት እና ሠራተኞች በመታገዝ እየተካሄደ እንዳለ ሰነዱ ያትታል፡፡ ‹‹የቴዎሎጂ ት/ቤቶችን ማእከል አድርጎ የተሐድሶ ማኅበራትን እና የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶውን ኑፋቄ በበላይነት በመምራት ቤተ ክርስቲያንን በአጭር ጊዜ የመውረስ›› ሕልም ይዞ የተነሣው ይኸው እንቅስቃሴ ዋና ጽ/ቤቱን በአዲስ አበባ ከፍቶ በሰባት ተጨማሪ ክልላዊ ቅርንጫፍ ቢሮዎች እስከ ወረዳ ድረስ የተዋቀረ መሆኑ ተገልጧል፡፡ የማኅበሩ የስልት አፈጻጸም ዐቅድ እንደሚያሳየው የተሐድሶው መነሻ እና ሞተር የቴዎሎጂ ት/ቤቶች መምህራን፣ ደቀ መዛሙርት እና ምሩቃን ሆነው ከእነዚህ በመነሣት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን፣ ከዚያም በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲኒቱን አካላት እስከ ሰበካ ጉባኤ ድረስ በመያዝ በመጨረሻ ምእመኑን ሁሉ መለወጥ ነው - ‹‹መምህራኑን መለወጥ የትምህርቱን ይዘት መለወጥ ነው፡፡ ለዚህም ለመምህራኑ በውጭ አገር(በተለይ እንግሊዝ) ነጻ የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡ የእነርሱን ባህል ተምረው የመጡት መምህራን ኦርቶዶክሳውያኑን መምህራን የማጥላላት ሥራ ይሠራሉ፤ ተማሪዎችም ባልጠረጠሩት መንገድ የቤተ ክርስቲያናቸው ተቃዋሚ እና አፍራሽ ኀይል ሆነው እንዲወጡ ያደርጋሉ፡፡››


የእንቅስቃሴው ዓላማ ተደርገው ከተቀመጡት ውስጥ፣ ‹‹የኢትዮዽያ አብያተ ክርስቲያናት በክርስቶስ ጥላ ስር ተሰብስበው እንዲያመልኩ እና በአንድ እንንዲተባበሩ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ ከስንዴ ጋራ አብረው የገቡትን ትምህርቶች እና መጻሕፍት(አስተምህሮ) ማስወገድ፣ ቤተ ክርስቲያንን ምንም ከማይጠቅም ወግ፣ ልማድ እና በብልሃት ከተፈጠሩ ተረታዊ ትምህርቶች ተለይታ እውነት የሆነው ክርስቶስ እንዲሰበክ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ራሱን የቻለ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ ማኅበር ማቋቋም›› የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡


ሰነዱ እንቅስቃሴውን ለመደገፍ እና ለማበረታታት በግንባር ቀደምነት የሚሠራውን Serving in Mission(SIM) የተባለ የአሜሪካ ሚሲዮናዊ ድርጅት በመጥቀስ እንደሚያስረዳው፣ ከነገረ መለኮት ኮሌጆች ባሻገር የካህናት ማሠልጠኛዎች፣ ገዳማት እና አድባራት፣ የቤተ ክህነት መሥሪያ ቤቶች እና የተለያዩ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት የእንቅስቃሴው ስትራተጂክ ቦታዎች ናቸው፤ የለውጡ መሪዎችም ‹‹በእምነት እና በዕውቀት የታመነባቸው የነገረ መለኮት ተማሪዎች፣ ልዩ ልዩ መምህራን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ቀሳውስት እና ዲያቆናት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ምእመናን እና ልዩ ልዩ ድርጅቶች ናቸው፤›› ይላል፡፡

በአሁኑ ወቅት እንቅስቃሴውን በዋናነት የሚመሩት (ኮሌጆቹ እንደተቋም እና ብዙኀን የተቋማቱ መምህራን፣ ደቀ መዛሙርት እና የአስተዳደር ሠራተኞ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ) መቐሌ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ የነበሩና ያሉ ተማሪዎች እና መምህራን ሲሆኑ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም አስተማማኝ መሠረት እንዳለው ታውቋል። ሤራውን የሚመራው ማኅበር በ2002 ዓ.ም የተለያዩ ስብሰባዎችን እና ውይይቶችን በማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል። በ2002 ዓ.ም መጨረሻ መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገ አንድ የፕሮቴስታንት ድርጅት ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አቅርቦት ስለነበረው የሥልጠና ጥያቄ ሰነዱ እንደሚከተለው ጽፏል፤

በ2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አንድ
የሥልጠና ጥያቄ ቀረበ። ሥልጠናውን ለመስጠት ጥያቄውን ያቀረበው
በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የፕሮቴስታንት ድርጅት ነው፤ የተጠየቀውም ለኮሌጁ
30,000 ብር ለመስጠት እና በዚህም ገንዘብ ለኮሌጁ ተማሪዎች እና ምሩቃን
የአምስት ቀናት ሴሚናር ለመስጠት ነበር። በሴሚናሩ ላይም ከእንግሊዝ
ሀገር የሚመጣ አንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ስለ ሥነ ፍጥረት፣ ስለ አዳም
አወዳደቅ፣ ስለ ነገረ ድኅነት፣ እግዚአብሔር ለዚህ ዓለም ስላለው. . . ዕቅድ
ትምህርት እንዲያስተምር ነበር።


በዚህ ጥያቄ ዙርያ የኮሌጁ መምህራን እና አመራሮች ሁለት የተለያዩ ሐሳቦች
ያዙ። አንዳንዶች ‹‹ሥልጠናው መካሄድ አለበት›› ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ
ተቃወሙ። ከተቃወሙት ውስጥ ‹‹ለሴሚናሩ የመጣውን ገንዘብ ተቀብለን
ትምህርቱ ግን በኢትዮጵያውያን መምህራን ይሰጥ›› የሚል ሐሳብ ቢያቀርቡም
የእንግሊዙ ድርጅት አልተስማማም። ስለዚህም በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ
ቁርጥ ያለ አባታዊ ውሳኔ ለድርጅቱ ገንዘቡ ተመለሰለትና ሥልጠናው
ሳይሰጥ ቀረ።


ድርጅቱ እያደረገ ያለው ‹‹ርዳታ›› እና አጠቃላይ ዓላማው የእንግሊዝ
የፕሮቴስታንት ድርጅት የሕንድን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት
የከፈለበትን ታሪክ በእኛም ቤተ ክርስቲያን ለመድገም ነው። ይህን የጥፋት
ሥራ የተጀመረው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ‹‹ርዳታ›› በማቅረብ ስም ነው። ይህ
ከላይ የተገለጸውን ሥልጠና ለማካሄድ አስቦ የነበረውና ገንዘብ የሰጠው
የእንግሊዝ የፕሮቴታንት ድርጅት የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን
ከሁለት በመክፈል ሰይጣናዊ ልምድ ያካበተ ድርጅት ነው፡፡ አሁንም በሕንድ
ያገኙትን ድል እኛም ላይ ለመድገም እየቋመጡ ይገኛሉ፡፡


እነዚህን እንቅስቃሴዎች በዋነኛነት እያስተባበረ ያለው በመቐሌ ዩኒቨርስቲ
በፊዚክስ ዲፓርትመንት በመምህርነት የሚሠራ ሰው መሆኑ ታውቋል። በዚህ
ሰው እና በሌሎች ሰዎች እንቅሰቃሴ ምክንያት የመቐሌው የከሣቴ ብርሃን
ኮሌጅ በከፍተኛ ደረጃ የፕሮቴስታንት ተጽዕኖ አድሮበታል። የከሣቴ ብርሃን
መንፈሳዊ ኮሌጅ በአሜሪካ ከሚገኘው ‹‹ብርጅ ኦፍ ሆፕ››(Bridge of Hope)
የሚባል ድርጅት ጋራ ጠንካራ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።


የእንቅስቃሴው መሠረታዊ መንሥኤ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ክርስትና በ‹ነበር› እንደቀረባቸው ሌሎች አገሮች በታሪክ ብቻ ለምልክት የምትወሳ አለመሆኗ፣ በምዕራባውያን ሚስዮናውያን አለመመሥረቷ እና በእነርሱ መንገድ አለመቃኘቷ የማያስደስታቸው በአንጻሩ በአፍሪካውያን እና በሌሎችም ዘንድ ያላት ተፈላጊነት የሚያሰጋቸው የጭፍን ግሎባላይዜሽን ኀይሎች ክፋት ነው፤›› - እንደ ሰነዱ ገለጻ፡፡ በዚህ ክፋት ከተቻለ የቤተ ክርስቲያኒቱን ማንነት በማንኛውም ወጪ እና መንገድ(ፖሊቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ. . .) በመለወጥ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ውስጧ ሆነው የሚወጓት እና የሚያደሟት በፕሮቴስታንት ሳምባ የሚተነፍሱ እና ለእነርሱ የቆሙ ጥቅመኛ ደጋፊዎችን እና ተከታዮችን በማፍራት ያላትን ነገር በይገባኛል መካፈል እና አንድነቷን በመክፈል ለማዳከም እና ወደ ዋናው ግብ ለመድረስ አበክረው ይንቀሳቀሳሉ፡፡


ይህ እንቅስቃሴ በአጠቃላይ ፕሮቴስታንታዊ ባልሆኑ የእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በተለይም ደግሞ በኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ላይ(የምሥራቅ ኦርቶዶክስን ጨምሮ) በከፍተኛ ትኩረት፣ የገንዘብ ኀይል፣ ስልት እና ቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተሠራበት ይገኛል፡፡ ይህንንም ጉዳይ ሰነዱ እንደሚከተለው አብራርቶታል፤

‹‹የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ወደ እነርሱ ለመውሰድ ከ19ኛው መቶ ዓመት ጀምሮ ብዙ ስልት ሲቀይሱ እና ሲደክሙ ኖረዋል፡፡ በ20ኛው መቶ ዓመት መጀመሪያ ላይ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ‹እናድሳለን› በሚል ከውስጧ ለመለወጥ እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ግብጽ በቅኝ አገዛዝ ሥር ስለ ነበረችና ሀገሪቱ የነበረችበት አጠቃላይ ሁኔታ የተመሰቃቀለ ስለ ነበር ያን አጋጣሚ በመጠቀም ቤተ ክርስቲያኒቷን ለመውረስ ተዘጋጅተው ነበር፡፡

ሆኖም ግን የእነ ሊቀ ዲያቆን ሀቢብ ጊዮርጊስ መነሣት እና በሰንበት ት/ቤቶች፣ በቴዎሎጂ ኮሌጆች እና በመሳሰሉት ሁለ ገብ ዘርፎች ያደረገው ድካም እና ውጤቱ፣ ወደ ኋላ ላይም የእነ ‹ድሀው› ማቴዎስ መነሣትና በእነርሱ እንቅስቃሴ የአስቄጥስ ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት ተዳክሞ ከነበረበት ሁኔታ እንደ ገና ማበቡ፣ እንዲሁም የእነ አቡነ ሺኖዳ ትውልድ መነሣትና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተጠናከረ የመጣው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያኒቷን ከነበረችበት የተወሳሰበና የደከመ ደረጃ ወደ አዲስ ጥንካሬና ሁለ ገብ ዕድገት አወጣት፡፡ በዚህም ፕሮቴስታንቶች ቤተ ክርስቲያኗን በተሐድሶ ሽፋን ለመለወጥ የነበራቸው ክፉ ምኞት ሳይሳካላቸው ቀረ፡፡
በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ላይም ተመሳሳይ የመውረር ዘመቻ አድርገዋል፡፡ የሕንድ ቅኝ ገዢ የነበረችው እንግሊዝ በመሆኗ የአንግሊካን ፕሮቴስታንቶች በሁለት በኩል ዘመቱባቸው፡፡ ይህም በአንድ በኩል ኦርቶዶክሳውያኑን ወደ እነርሱ ጎራ እንዲቀላቀሉ ከውጭ ሆኖ በመጋበዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከውስጥ ሆኖ ቤተ ክርስቲያኗ ትታደስ በማለት ነበር፡፡ ይህም አካሄድ ተሳክቶላቸው የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መክፈል ችለዋል፡፡ ሁለቱም - ኦርቶዶክሳውያኑም ተሐድሶዎቹም በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ይገባናል ስላሉ መንግሥት በፍርድ ቤት የነበሩትን ሕንፃ አብያተ ክርስቲያናት ከሁለት ማካፈል ግዴታ ሆነበት፡፡ በዚህም በአንግሊካኖቹ ላኪነት ተሐድሶ(ፕሮቴስታንት) የሆኑት ‹ማር ቶማ› የተባለ ቤተ ክርስቲያን አቋቋሙ፡፡ እነዚህ የተገነጠሉትን እምነታቸው ፕሮቴስታንት ስለ ሆነ ‹ኦሬንታል ፕሮቴስታንት - Oriental Protestant› ይሏቸዋል፡፡››

በከፍተኛ ትኩረት፣ የገንዘብ ኀይል፣ ስልት እና ቴክኖሎጂ የሚታገዘውን ይህንኑ ፀረ- ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ እንቅስቃሴ በፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ተጋድሎ ለማምከን የፊት ለፊት ፍልሚያ የሚጀመርበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ሰነዱ ያበሥራል፡፡ የተሐድሶ ማኅበራትን እና ድርጅቶችን በዋናነት የሚመሩ እና የሚያስተባብሩ ከ76 በላይ ቀንደኛ የመንፈቀ ሉተራውያን አዝማቾች በስም ዝርዝር እንደተለዩ ሰነዱ ጨምሮ አጋልጧል፡፡ ብፁዓን አባቶች ጉዳዩን በበለጠ እንደሚረዱት እና እንደሚያሳስባቸው ያመለከተው ሰነዱ፣ ሰባክያነ ወንጌል በስብከት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም በጽሑፍ ምላሽ በመስጠት ምእመኑን እንዲያነቁ፣ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ጀምሮ ያለው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅርም በየደረጃው የተሰገሰጉትን የተሐድሶ ኑፋቄ አስፈጻሚዎች በጥብቅ እየፈተሸ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ርምጃ የሚወሰድበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡

ባለፉት ዐሥር ዓመታት በዋናነት አርክ ክርስቲያን ሰርቪስ፣ የታላቁ ተልእኮ አገልግሎት(ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ)፣ የ‹‹ሙሉ ወንጌል›› ክንፍ፣ የ‹‹መካነ ኢየሱስ›› ክንፍ እና በሌሎችም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ የገንዘብ እና ሁለ ገብ ድጋፍ ሲደረግለት የቆየው የተሐድሶ ኑፋቄ እንቅስቃሴ ከድርጅት ወደ ድርጅቶች፣ ከግለሰብ ወደ ማኅበር፣ ከኅቡእነት ወደ ግልጽነት፣ ከመፍራት ወደ ድፍረት፣ ከአንድ ከተማ ወደ ሀገር አቀፍ፣ ከጓዳ ወደ ሜዳ እንደተሸጋገረ ተገምግሟል፡፡ እንደ ሰነዱ ማብራሪያ በይፋ ታውቀው በስም የተዘረዘሩት፣ በሂደት ላይ ያሉት እና ገና ያልታወቁት የተሐድሶ ማኅበራት በተለያየ ደረጃ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚመሩበት አጠቃላይና ከ1990 ዓ.ም ወዲህ ጎልቶ የታወቀው አዲሱ ስልታቸው ‹‹የጥንቷ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ነበረች - The ancient Orthodox was the right church›› የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያንን ከውጭ ከመቃወም ይልቅ ውስጥ ገብቶ ምእመን መስሎ ከፕሮቴስታንት እምነት እና ባህል ውጭ ያለውን ነገር ሁሉ፣ ‹‹ይህ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አይደለም›› እያሉ ቤተ ክርስቲያኗ ኦርቶዶክሳዊ ዶግማዋ፣ ቀኖናዋ እና ትውፊቷ በሙሉ ጠፍቶ ፍጹም የጠራች የነጣች ድኃ ፕሮቴስታንት እስክትሆን ድረስ መሥራት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በተለያዩ ኅትመቶቻቸው በሚያወጧቸው ጽሑፎቻቸው ‹‹የትግሉን ሜዳ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማድረግ አለብን››፣ ‹‹ከቤተ ክርስቲያን መውጣት ቀረ››፣ ‹‹የወጣህ ተመለስ›› እያሉ በመዛት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

በጥንቃቄ የተነደፉ፣ ከአንዱ ተግባራቸው ወደ ቀጣዩ ለማሸጋገር የሚያስችላቸው እና ተመጋጋቢነት ባለው መንገድ የተቀየሱ የማንሸራተቻ ስልቶች እንዳሏቸውም ሰነዱ ይተነትናል፡፡ በመጀመሪያ ‹‹ቤተ ክርስያኒቱን ፕሮቴስታንት ለማድረግ ወራጁ ውኃ ላይ (ሕዝቡን መውሰድ) ሳይሆን ምንጩ ላይ መሥራት›› የሚል ነው፡፡ ለዚህም የቤተ ክርስቲያኒቱ የወደፊት ምንጭ የሆኑትን መፍለቂያዎች መለየት እና እነርሱን ለመያዝ የሚቻልባቸውን ሥሥ ገላ መፈለግ ነው፡፡ እነዚህ ምንጮችም ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች፣ የነገረ መለኮት ት/ቤቶች ደቀ መዛሙርት እና መምህራን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች እና በውስጣቸው የሚካሄዱ መንፈሳዊ ጉባኤያት፣ የቤተ ክህነት አስተዳደር እና የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት ጽዋ ማኅበራት ናቸው፡፡ እነዚህን ምንጮች ከመለየት ቀጥሎም የእያንዳንዳቸውን ደካማ እና ጠንካራ ጎን በማወቅ ሁሉንም እንዳስፈላጊነቱ ለመጠቀም የሚቻልበትን መንገድ መንደፍ ነው፡፡

ቀጣዩ ምዕራፍ በእነዚህ ምንጮች ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ በመምሰል ሰርጎ መግባት እና ለሥራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡ የአፈጻጸም ስልቶቹም እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ እና የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ እና ተቆርቋሪ መስሎ መታየት፣ ኦርቶዶክሳዊውን ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዐት ለጊዜው አለመንቀፍ፣ በሕይወት እና በአገልግሎት ምሳሌ ሆኖ መታየት፣ ተአማኒነትን ለማግኘት ማንኛውንም መንገድ መጠቀም፣ የአገልግሎት መድረክ መያዝ - ሐላፊነት፣ ሥልጣን መያዝ እና በሕዝብ ልብ ውስጥ ለማደር መሥራት ናቸው፡፡ በዚህ መቆናጠጫ ቦታ ከያዙ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን በአንድ በኩል ዶግማዋን እና ቀኖናዋን እንዳያውቁ ስብከት ላይ ብቻ መጻፍ እና ማስተማር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቷ ትምህርቷ እና እምነቷ ትክክል ስላልሆነ መታደስ አለባት›› በማለት ይለፍፋሉ፡፡

ይኸውም የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ጉባኤያት ይዘት ‹‹ከትምህርት ወደ ስብከት›› መቀየር፣ ‹‹ክርስቶስን አስኳል አድርገን እንሰብካለን›› ማለት፣ ‹‹ኦርቶዶክስ እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፣ ግን በየጊዜው የተጫኑባት ገለባዎች አሉ፤ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል፤ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን መመለስ አለብን››. . . ወዘተ እያሉ ደጋግሞ መስበክ እና ሕዝቡ ሲደጋገም እንዲቀበለው ወይም ተቃውሞውን እንዲያለዝብ ማድረግ፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ ስለ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም እና የተጋድሎ ሕወይት ማለትም ጾም፣ ጸሎት፣ ስግድት ወዘተ አስመልክቶ አለ ማስተማር፣ ማስረሳት፤ በዚህ ዙሪያ ማስተማር ለሕይወት የማይጠቅም ርባና የለሽ እንደ ሆነ ማስወራት፤ ስለ ፕሮቴስታንት፣ ለመናፍቃን ምላሽ. . . ወዘተ አለማስተማር ማለት ነው፡፡ ማኅበራትን በሕዋስ (cell) መልክ በማደራጀት፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ጉባኤያትን ማስለመድ፣ በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ስም ራስን ማደራጀት እና ቀስቶቹ የተነጣጠሩባቸው አካላት የገንዘብ ችግር ስላለባቸው ምንጩ ያልታወቀ ነጻ ርዳታ መስጠት ተቆጣጣሪ የሌላቸው መስመሮች የሚዘረጉባቸው ቀጣይ ስልቶች ናቸው፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ መገለጫ የሆኑትን ነገሮች(Icons) በማስረሳት እና በማስጠላት(ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ሲኖዶስ፣ ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ሰንበት ት/ቤቶች የባህል፣ የአስተምህሮ፣ የቀኖና፣ የዶግማ እና የሥርዐትን ድንበር ማጥፋት፤ ምእመኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር፣ በአባቶች፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በምግባር በመሳሰሉት የተነሣ ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠላ በማድረግ፣ ቤተ ክርስቲያንን ያረጀች ያፈጀች ‹‹አሮጊቷ ሣራ›› አድርጎ በመሣል ቤተ ክርስቲያንን ማስጠላት ሌላው የማንሸራተቻ ስልት ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የሚመጣው ተሐድሶ እንኳን እንደ ሆነ የማያውቅ ግን ተሐድሶ የሆነ ትውልድ መፍጠር እና ሳያውቀው የሚደግፍ ቲፎዞ ማፍራት ነው፤ ስልቶቹም ተቆርቋሪ በመምሰል፣ ገንዘብ እና ርዳታ በመስጠት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማት እና ሕዝቡን መያዝ እና ቲፎዞ እንዲሆን ማድረግ፣ ኦርቶዶክስን የማያውቅ-ፕሮቴስታንት የሆነ-ነገር ግን ተሐድሶ(ፕሮቴስታንት) መሆኑን እንኳ የማያውቅ ምእመን ማፍራት ናቸው፡፡

ከመጀመሪያ ጀምሮ ያሉትን ስልቶች ወደዚህ ውጤት እንዲያደርሱ አድርጎ በሚገባ በመተግበር የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ እና ተያያዥ ችግሮችን ሃይማኖታዊ ይዘት በመስጠት ምእመኑን ማስከተል፣ ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ጠንካራ ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ ይዘት ሲይዝ እንደ ሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት መክፈል አልያም ቤተ ክርስቲያኗን ባለችበት ከእነ ምእመኗ እና ሕንፃዋ ሙሉ በሙሉ ፕሮቴስታንታዊ አድርጎ መውረስ የስልቱ የመጨረሻ ግቦች ናቸው፡፡

‹‹የተለመዱ የተሐድሶ ስትራቴጂዎች ናቸው›› የሚላቸውን ሲያስረዳም፣ ‹‹አባቶችን መከፋፈል እና የአንዱ ደጋፊ የሌላው ነቃፊ መምሰል፣ የጥላቻ ጽሑፎችን በማሰራጨት ምእመናንን ማደናገር፣ ፖለቲካዊ ክሶችን ማቅረብ፣ ከገዳማት እናቶችን ማስኮብለል፣ የነጋዴዎች እና የብፁዓን አበው ደጋፊ መስሎ መቅረብ፣ ብዙ ውስጠ ወይራ የሆኑ የጽዋ ማኅበራትን መመሥረት፣ ጉባኤያትን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዲካሄዱ እገዛ ማድረግ፣ በተቻለ መጠን የውስጥ ለውስጥ(Underground) ሥራዎችን በይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል(ለዚህም ከገድላት የተወሰኑ መቀበል)፣ የፎርጅድ ጽላት ዝግጅት፣ የሙዳየ ምጽዋት ብርበራ፣ የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ እና ንዋየ ቅድሳት ዘረፋ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ በግለሰብ ስም ማዛወር፤ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ አባል በመሆን፣ በከተሞች ታላላቅ ጉባኤያትን በማዘጋጀት በገዳማት እና አድባራት ስም ገንዘብ ማሰባሰብ እና ለግል ጥቅም ማዋል፣ ፎርጅድ ማኅተሞችን በማዘጋጀት በአባቶች ስም ልመና ማካሄድ፣ በባሕታዊነት ስም መነገድ እና አስነዋሪ ድርጊቶችን በአደባባይ እና ሰዉ በሚያይባቸው ቦታዎች በመፈጸም ሕዝቡ ባሕታዊ እና መነኩሴ እንዲጠላ ማድረግ፣ ገዳማት ውስጥ እየገቡ በተለያዩ ሰንካላ ሰበቦች ሁከት መፍጠር እና ጠብ አስነሥቶ የተወሰኑትን አስወጥቶ ይዞ በመጥፋት እነዚያን የመናፍቃን ሰለባ ማድረግ፣ ገዳማትንም መፍታት›› እንደሆኑ በዝርዝር አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ‹‹እናድሳለን›› በሚል ሽፋን ከውጭ ወደ ውስጥ ሠርጎ በመግባት ምእመኑን እስከ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የመረከብን ስልት አንግበው የሚሠሩ 14 የተሐድሶ ማኅበራት እና ድርጅቶች ማንነት እና የትኩረት አካባቢዎች ከዝርዝር ስልቶቻቸው ጋራ በሰነዱ ተብራርቷል፡፡

ለአብነት ያህል፣ የተሐድሶ ድርጅቶች አባት በሆነው ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ የተቋቋመው ‹‹የምሥራች አገልግሎት በኢትዮጵያ›› የተባለው ማኅበር በትግራይ፣ ጎጃም፣ ጎንደር እና ወሎ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ድርጅት ነው - ‹‹ደቡብ ኢትዮጵያን ይዘነዋል፤ የቀጣዩ ዐሥር ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ሰሜን ኢትዮጵያ ነው፤›› የሚል መፈክር ያስተጋባል፡፡ የዚህ ድርጅት ዋነኛ ተልእኮ የተሳሳቱ አዋልድ መጻሕፍትን ወደ ገዳማት እና ሰንበት ት/ቤቶች እያስገቡ መበከል ነው፡፡ ወንዶችን ሴት በማስመሰል ወደ ገዳም ያስገባል፡፡ በገዳማት እና ሰንበት ት/ቤቶች ተመሳስሎ በመግባት ፕሮቴስታንታዊ ትምህርትን ያስፋፋል፡፡ በትግራይ አብነት ተማሪዎች ላይ ጠንክሮ እየሠራ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥር መሠረቷን ነቃቅሎ ለመጣል ይረዳኛል ያለውን መንገድ ለማወቅ ጥናት አስጠንቶ የራሱን ሰዎችም ሆነ ሌሎች ተባባሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ ለማድረግ በመሯሯጥ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አርባ ዙር የሥልጠና ሥራዎችን ሠርቷል፤ የሚያሠለጥነውም የአብነት መምህራንን፣ ተማሪዎችን፣ ካህናትን እና ዲያቆናትን ነው፡፡ ከ500 በላይ ዲያቆናት እና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ይህን ተልእኮ ይሠራሉ፡፡ ከእነዚህ ብዙዎቹ የሚሳተፉት ለቤተ ክርስቲያናቸው እየሠሩ እንደ ሆነ እየተነገራቸው እና እየመሰላቸው ነው፡፡ ከ22,000 መነኮሳት መካከል 3,000ውን እንዴት መውሰድ እንደሚችል የመጀመሪያ ዙር ስልት ቀይሷል፡፡ ዛሬ የአማራን ክልል በሰፊው ለማዳረስ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡ የሥልጠና ቦታው መቐሌ ከተማ ውስጥ ነው፤ የራሱ የሆነ የሚዲያ መንገድም አለው፡፡

‹‹ከሣቴ ብርሃን›› - በአገሪቱ ውስጥ በሰፊው ተሰራጭቶ የሚገኘው ሌላው ዋነኛ የተሐድሶ ድርጅት ነው፡፡ መሥራቾቹ በ1990ዎቹ መጀመሪያ በኑፋቄያቸው ከኮሌጆች የተባረሩ፣ ከተመረቁ በኋላ አበው አውግዘው የለዩአቸው፣ በራሳቸው ጊዜ ኑፋቄውን ይዘው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንቆይም ብለው በፍቅረ ንዋይ ተታልለው የወጡ ‹ወገበ ነጭ› ደባትራን መዘምራን የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ያቋቋማቸው ያው አባታቸው ፕሮቴስታንት ሲሆን አሁን ግን ራሱን ችሎ መሥራት የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አዲስ አበባ ላይ የአብነት ተማሪዎችን የሚያሠለጥንበት አራት የሥልጠና ጣቢያዎች አሉት፡፡ ጎንደር እና ባሕር ዳር ላይ ብዙ ሰዎች የተሳተፉበትን ሥልጠና አካሂዷል፡፡ ጎንደር ላይ ለካህናት እና ለአብነት ተማሪዎች በይፋ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ አስተማሪዎቹ ከተለያዩ አጥቢያዎች በኑፋቄ ችግር የተባረሩ ናቸው፡፡

(ማስታወሻ፦ በዚሁ ስም የሚጠራ እና በተለይም በአሜሪካ ግዛት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ማህበር አለ። ይህ በነመምህር ዘበነ ለማ የተቋቋመው “ከሳቴ ብርሃን” ማህበር እውነተኛ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመሆኑ ከዚህኛው ጋር እንዳይምታታ እናሳስባለን።)

ማኅበሩ በሚያወጣቸው የኅትመት ውጤቶች ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ኅትመቶቹ ግልጽ አድራሻ የላቸውም፡፡ ሆኖም ግን ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጁ›› ይላሉ፡፡ የተለያዩ ኅትመቶች ያሏቸው ሲሆን ዋና ዋና ኅትመቶቻቸው፣ መጥቅዕ፣ ርግብ፣ ትምህርተ ድኂን፣ ገድል ወይስ ገደል፣ የተቀበረ መክሊት፣ ይነጋል . . . ወዘተ ናቸው፡፡ ኅትመቶቻው ሁሉ የሚያቀነቅኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተሐድሶ ስም ተለውጣ ፕሮቴስታንታዊ እንድትሆን ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን ዶግማ፣ ቀኖና ማንኛውንም ነገር ሁሉ ይነቅፋሉ፤ ኢትዮጵያዊ የሆነን ነገር በመንገሽገሽ ይተቻሉ፡፡

በ1984 ዓ.ም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዞ ከቤተ ክርስቲያን ቢባረርም በመንፈሳዊ ኮሌጆች እና በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ደቀ መዛሙርትን እና ምእመናንን በማጥመድ እንዲሁም በሌሎች ተንኮሎች ተመልሶ ለመግባት እና ቤተ ክርስቲያንን የማድማት እና የፕሮቴስታንት ቀለብ የማድረግ ሥራውን ለመቀጠል ጥረት እያደረገ የሚገኘው ‹‹ሃይማኖተ አበው›› ከአዲስ አበባ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የበከላቸው ወጣቶች ጥርቅም የሆነው ‹‹የቅድስት ልደታ ማኅበር›› ሌላው ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊ በመሰለ ውስጡ ግን ፕሮቴስታንታዊ በሆነ አቀራረብ እና ስልት ‹‹የርቀት ትምህርት›› በሚል ስም የሚሰጠው ብዙዎችን እያሳሳተ ይገኛል፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠው በነጻ ነው፡፡ አካሄዱ አደገኛ ነው፡፡ የግእዝ ቃላትን ይጠቀማል፡፡ አሠራሩን በቤት ለቤት እና በሰንበት ት/ቤቶች ውስጥ ሕዋስ መር እና ግለሰባዊ(Cell based and Individual based) በሆነ መልኩ ያካሂዳል፡፡ በየሀገረ ስብከቱ ቅርንጫፍ ከፍቶ በእስር ቤቶች እና ኮሌጆች ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡

‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› - ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት በኑፋቄው በአባቶች ተወግዞ በወጣው ግርማ በቀለ በተባለው ግለሰብ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ ማኅበር ወይም ድርጅት የርቀት ትምህርቶችን ማስተማር፣ በራሪ ጽሑፎችን ማሰራጨት እና ቤተ ክርስቲያናችንን የሚነቅፉ መጻሕፍትን ማሳተም እና ማሰራጨት ላይ በርብርብ እየሠራ ይገኛል፡፡ ለዚሁ ዓላማ መሳካትም ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የሚወጡ አንዳንድ ተማሪዎችን እየወሰደ በማሠልጠን መልሶ በማስገባት ትምህርቶችን መበከል አንዱ ስልቱ ነው፡፡ የትኩረት አቅጣጫው የነገረ መለኮት ምሩቃን እና ተማሪዎች ሲሆን በተናጠልም በቡድንም ትምህርቶችን በየአቅጣጫው ያሰራጫል፡፡ ትልቁ ተልእኳቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ጉባኤያትን እና ዐውደ ምሕረቶችን መቆጣጠር ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሦስት ቢሮ አለው፡፡ በሰሜን ሰቆጣ እና ደሴ ላይ ይሠራል፡፡

‹‹ማኅበረ ኪዳነ ምሕረት›› - የገዳም ኑሮ ሲከብዳቸው የኮበለሉ ሰዎች የመሠረቱት ማኅበር ነው፡፡ ‹‹ብቃት ደረጃ ላይ ደርሰናል›› የሚሉ ሰዎችን በመከተል እና ሴቶችን በመድፈር ነውር ይታወቃሉ፡፡ መሥራቹ ግለሰብ በጽላት ዘረፋ ተይዞ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በማረሚያ ቤት ይገኛል፡፡ በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ፣ ወለጋ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ(ምዕራብ ኢትዮጵያ) ከተሞች ይንቀሳቀሳል፡፡

‹‹የቅድስት ማርያም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማኅበር›› - ይህ ማኅበር በቅርብ ጊዜ የተቋቋመ(እነ በጋሻው ደሳለኝ እና ያሬድ አደመ በዋናነት የሚሳተፉበት) ሲሆን የተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች፡- (1)የትምህርት አሰጣጡን ይዘት ከመሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ይልቅ ግራና ቀኝ ወደማያስለይ እና መሠረታዊ ቁም ነገር ወደማያስጨብጥ ተራ ወግ እና ተረት መለወጥ ነው፤ የዚህ ተግባር ዓላማም ምእመኑ መሠረታዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያኑን አስተምህሮ እንዳያውቅና እንዲህ ከሆነም የሚጫንበትን ኑፋቄ ሳያቅማማ እና ሳይለይ እንዲቀበል ለማድረግ ነው፡፡ (2)የስብከተ ወንጌሉን አቅጣጫ ለቤተ ክርስቲያናችን ወካይ ዓርማ (Icon) የሚባሉትን ነገሮች የሚያጥላላ እና የሚያናንቅ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ሕዝቡ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን አክብሮት እንዲቀንስ እና እንዲጥል ከዚያም በውስጡ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲጠላ ማድረግ ነው፡፡ (3)ሃይማኖታዊ ልዩነቶችን ማጥፋት፤ ይህም ፕሮቴስታንታዊውን አስተምህሮ አሾልኮ በማስገባት ‹‹አንድ ነን፣ እዚህም እዚያም የሚሰበከው ጌታ ነው፤. . . ወዘተ›› በማለት ከውስጥ ሆኖ መለወጥ ነው፡፡ (4)የተለያዩ ማኅበራትን በሕዋስ(Cell) ደረጃ በየጉራንጉሩ መመሥረት እና ማቋቋም፤ እነዚህን ጥቃቅን ማኅበራት አህጉረ ስብከት ስለማያውቋቸው እና የሚቆጣጠሩበትም መንገድ ስለ ሌላቸው እነዚህ የሚያዘጋጇቸው ጉባኤያት፣ የሚጋብዟቸው ሰባክያን እና በዚያም የሚሰጠው ትምህርት ለዓላማቸው የተመቸ ይሆናል፤ እየሆነም ነው፡፡ (5) በስብከቶቻቸው እና በጽሑፎቻቸው የፕሮቴስታንቶችን ምንጮች መጠቀም፣ ለዚህም በቅርብ ጊዜ ያሳተሙት መጥሐፍ ሐሳቡ ብቻ ሳይሆን ርእሱ ሳይቀር የፕሮቴስታንት ፓስተር ከጻፈው መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡

ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት - የተደራጀው ከሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በሃይማኖታዊ ችግሮች በተባረሩ እና በወጡ አካላት ነው፡፡ ከክልሉ በፀረ-ኤች. አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እንቅስቃሴ ስም ፈቃድ በማውጣት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የሚሠራቸው ሥራዎች ከቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ውጭ ጉባኤያትን በማዘጋጀት እና ገንዘብ በማካበት ነው፡፡

ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሚያሳስባቸው የመንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች የተላከልን ይኸው ባለ 50 ገጽ ሰነድ ሁኔታው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በእጅጉ ከሚያሳስብበት ደረጃ ላይ በመድረሱ በሚመለከታቸው አካላት መካከል የተሐድሶ ኑፋቄን ምንነት እና የሚያስከትለውን አደጋ ተረድቶ የጋራ ግንዛቤ ከመያዝ አኳያ እና መወሰድ በሚገባቸው ርምጃዎች ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶች እየተካሄደበት እንደሆነ ተመልክቶበታል፡፡

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት እና ህልውና ላይ ስለጋረጠው ግልጽ አደጋ የተለያዩ መረጃዎችን ስታድርስ የቆየችው ደጀ ሰላም ዘግይቶም ቢሆን ከሚደረገው ከዚህ እንቅስቃሴ ጎን እንደምትቆም እያረጋገጠች ወደፊት የሰነዱን ይዘቶች እንዳመቺነቱ በመከፋፈል ለማስነበብ ጥረት ታደርጋለች፡፡

102 comments:

ዘብሔረ ጉራ said...

እግዚአብሔር ኢትዮዽያን ይጠብቅ!! እመ ብርሃን ትጠብቀናለች። አንድ እንዲረሳ የማልፈልገው ነገር ቢኖር ለማንኛውም መንፈሳዊ ጥቃት መንፈሳዊ መፍትሔን ማስቀደምን አንዘንጋ። ካልሆነ ግን ከምንም ተነስቶ የሚጠራጠር፣ በተጠቂነት መንፍስ ከመጠን በላይ የሚንገበገብና ማንንም የማያምን ትውልድን እንፈጥራለን። መንፈሳዊ ሰው መከራ፣ስለ ዓይማኖት መሰደድ፣መገፋት፣… ክብሩ ነው። መብቱንም ሲያስከብር፣ሲጠነቀቅ፣… መንፈሳዊነቱን ሳያጣ መሆን ይገባዋል።… እኛ መንፈሳዊ ከሆንን በሺህ ተዓድሶ ብንከበብ እንኳን እግዚአብሔር በእኛ ይሰራል። ስለቤተክርስትያን እኛ ራሳችንን ስንሰጥ፣ ፀጋው ይበዛላናል።……………………………………………….
ይህንን በልቡ የያዘ ትውልድ ከ”ተሐድሶ” ሴራ እንዴት ራሱንና ሌሎችን መጠበቅ ይችላል?
1- “ተሐድሶ” ማን ነው/ናት?
2- እነዚህ ሰዎች ማንን እየተጠቀሙ ቤተክርስትያንን ያጠቃሉ?
3- የትኞቹ መንገዶች ራሳችንን/ቤተክርስትያንን(እኛም ማህበረ ምዕመኑም ቤተክርስትያን ነንና!) ከተሐድሶ ጥቃት መከላከል ያስችሉናል?
4- ለመሆኑ ልጆችንና ታዳጊዎችን ስናሳድግ ምንን ገንዘብ እንዲአደርጉ ማድረግ ይገባናል?
5- ……………………..
እነዚህን ነገሮች ማንሳት ያስፈለገኝ በአንድ ነገር ስለማምን ነው። የተሐድሶ እንቅስቃሴ አገሪቱ ባለፉት 40ና50 ዓመታት ያለፈችባቸው ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚአዊ ና ማህበራዊ ቀውሶች ውጤት ነው። ብዙዎቹ የዚህ እንቅስቃሴ አራማጆች የመብት ጥያቄ፣ ፖለቲካዊ እይታና መንፈሳዊ ማንነትን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የተዛባና የወገንተኛነት ጠባይ ያላቸው ናቸው። ስለዚህ የቀደመዉ ትውልድ ቤተክርስትያን ከላይ በጠቀስኳቸው ዘመናት የነበራት ሚና ላይ በግልጥ ይሞግት!!! በነገው ሚናዋም ላይ እንዲው!!!!.................................................
እኛ ልዩነታችንን በመንፈሳዊነትና ቅን በሆነ ውይይት ስናጠብብ፣ መናፍቃንም ሆነ ሌላ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች(የውጭም ሆነ የውስጥ) ፍሬ አልባ ይሆናሉ። ስለዚህ ስለቤተክርስትያን የነገ ማንነት የምትጨነቁ መንፈሳዊያን አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ እህቶቼና ወንወድሞቼ ከአዲሱ ትውልድ ጋር ተነጋገሩ።(ጦምሩሩሩሩሩሩሩሩሩ!!!-በብሎግ፣በፌስቡክ ጻፉ፤ በየቦታዉ ተወያዩ፤ ….እንስማችዉ!!! ካለበለዛ ጥሬ መረጃ መፍትሔውን ትተን ከሌሎች በእምነት ከማይመስሉን ጋር በጥርጣሬ እንድነተያይ ከማድረግ አይዘልም። ይህ ደግሞ ዓይማኖት ሲነሳ የመለያየት ምንጭ ብቻ መሆኑ እንዲታሰብ ያደርጋል።………. ስለዚህ ከሕይወት ልምዳችው ጻፉልን፣ ንገሩን፣…..)

Anonymous said...

ምነው ይህ ሁሉ ጉድ እያለ ማኅበረ ቅዱሳን ዝም አለ። ነው ወይስ እነሱም እንደ ቤተ ክህነት ደረቴ ይቅላ ሆዴ ይሙላ ማለት ጀመሩ።በእርጝጥ በእነሱም ላይ ያለው ፈተና ከውስጥም ከውጭም መሆኑ የተለየ እንደሆነ አውቃለሁ።የተሐድሶ መሰሪዎቹ ለበላይ አሽከሮቻቸው አድሃሪው ማኅበር ብለው መስየማቸው ጥቃቱ ከማኅበረ ቅዱሳን የሚጀምር መሆኑን ሁላችንም የተረዳን ይመስለኛል።
ሆኖም ግን ማኅበረ ቅዱሳን በሚዲያዎቹ ሊያስረዳን፤ ሊቀስቅስን ይገባ ነበር። ምን አልባት የተሓድሶዎች እንቅስቃሴ ለ እናንትም እንደ እኔ እንግዳ ነገር ከሆነባችሁ አገልግሎታችሁን ልትፈትሹ ይገባል። ከዚህ ውጭ ግን ከዚህ በላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተከፈለች በኋላ መንገዱ የህዋ ጉዞ እንዳይሆንብን እሰጋለሁ።
እኛ ምዕመናን፡ ደግሞ ማንነታችን ማወቅ፤ ነገሮችን ማጤን ያለብን ይመስለኛል። እንዲያው ሰሞኑን እንደሚባለው ፌስቡክ ጀነሬሽን ልንሆን አይገባም። ማንነታችንን፤ መለያችንን፤ከዚያም በላይ ህይወታችንን ለጠብቅ ይገባል ባይ ነኝ። ቤተ ሰቦቻችንን፡ የስ/ት/ቤት ወንድምና እህቶቻችንን መዝሙር ማስጠናት ብቻ ሳይሆን የጠላቶቻችንን መስሪ በማሳወቅ ጥበበኛ እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ልናደርጋቸው ይገባል። በጥምቀት በዓል ላይ ባለቤትነታቸውን ያስመስከሩት ወጣት ወንድሞቻችንን ልናሳውቃቸው ይገባል፡፤ ሰባኪያን፤ዘማርያን፤ አባቶቻችንና የደበር አስተዳዳሪዎች በዚህ ሴራ ተባባሪ እንዳይሆኑ ማሳወቅ ይኖርብናል።
የቤተ ክርቲያን ጠላቶችን ያስታግስልን።
እግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

Unknown said...

this strategy must happen and can be succeed partially b/c EOC is on sleep but God will not destroy all Her teaching for whom to be saved yet

Anonymous said...

ደጀ ሰላም አግዚአብሔር ይስጥልን:: በጣም የሚገርም በጉጉት የምጠብቀው መረጃ ነው::

ምን አናድርግ?????!!!!!!!!!!!!! ቶሎ ቶሎ አንበል ወገኖቼ::

Anonymous said...

'' ...ያላቹ እስኪ እንያቹ '' አለ... እኮ ማክሽፊያው አምጡታ ሊቃውንት:: ምን ይደረግ?

Anonymous said...

woy ene begashaw mechereshachehu yehe hone.Egiziabher betekirisitianachenin yitebik

Anonymous said...

Ou..Ou...Ou...Ou....ooooooo

yebetekrstiyan amlak yaleh!!!

'yalesh mesloshal tebeltesh alkeshal' ale yahage sew?

Mimenan hoy ibakachu iyayen betekirstyan litbela new, yezih tifat alama asfetsami yehonachihu abakachu bebandanet inatachun lejib atsitu, temelesu.

Ine Harer bizu gize slinerku yehenin drigit lemefetsenu 100% irgitegna negn awkewalehu.

Begashaw tebye banda benath ke dila geter bedehnet tekoramteh sitnor zare deretih iski kela yemtbelaw belayua lay bametskibat b/kirstyan sim new; yibekahal temeles imbi bleh inde feron libihin katsenal seyf yibelahal. bandanethin akum.

To all EOC believers.
Please forward this message to at least 10 peoples of whom you know via your e-mail.

Imebrhan hoy irjin, irjin imeamlak... betekrstiyanen tebkilin adera adera haylachin anchi bcha iko nesh dingle aderea...adera....

Desalew said...

tanks degeselamawyan!!!!.it is critcal issue.lib yalew lib ybel.wgen neka bel!

ermias said...

እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ.

Anonymous said...

Why are these people(Tehadso and Protestants in Ethiopia) using satanic tactics while claiming to be Christians?

Anonymous said...

በእውነት አሳዛኝ ነው ግን ምን እናርግ የመፍትሄ ሀሳብም ብትጨምሩበት በግል ክምናደርገው እንቅስቃሴና ፀሎት በተጨማሬ
በጋራ ማድረግ የሚገባንን ነገር ደግሞ ሙሉውን መርጃ ማግኝት የምንችልበት መንገድ ቢመቻችልን
አለማየሁ ጤናው ከ ባህር ዳር

Anonymous said...

Guys,

I am an ardent supporter of the EOTC and its CORE faith. However, the true problem of the church is not the outside so-called TEHADSO group, but rather the church leadership and the people around it. Anyone who believes all aspects of the church is based on the true ROCK, means Jesus Christ, would not be afraid of the challenges posed by tehados. Why not the church responds to the legitimate questions on the contradicotry writings in the Awalids and Gedls or correct them? I believe the problem lies in the leadership that is not doing much to guide its followers separate the good from the bad, and cope up with the INFORMATION AGE. It is now very clear that the church is inundated with various anti-Christ teachings infiltrated by some debtras and church enemies. Reform is not bad as far as it cleans up the dirts thrown on our church over the years; however, we cannot tolerate another infiltrators, Pentes, to come and harm the church.

In a nut shell,
1) The core faith of EOTC is good, and cannot be changed as it is based on the true teachings of Christ.

2) However, there are lots of bad debtra writings that need to be either burnt or corrected if the church wants to be intact and win over its enemies. The auxiliary debtera teachings need to be tested by the words of God. I can mention hundreds of them, but that is not necessary now.

3) Reform is inevitable! However, the reform should be led by the true believers of the church, not by external parties or enemies of the church. If genuine reform cannot take place within, then the enemies, the ones you mentioned in the article, will obliterate our church and make it a no man's island. (fyi, i lost close friends to other competing faiths and have broken communication since then. I am saying that i know how those bad debtera teachnigs have trapped people.)

4) If the groups, which claims knowingly or unknowingly that all our books and traditions are clean, continue to dominate the church and harass those genuine reformers, then the church will definitley be hurt and can even split or lose millions to other faiths. As the generation reads more of those bad awalid books, they will start hating the church and abandon it. We need to avoid that by cleaning our house by ourselves, instead of giving to external Tehados elements a reason to undermine our church. Simple bura kereu will not help the church, but will hurt it beyond any magnitude.

If you want wisdom, you may want to consider some of the advices above - not claiming in anyway to be a wise person here. However, I know open-minded smart people can trasform our world for the better while blinded folks can lead us ot hell. I hope you are among the former ones who are transformational.

I know you (moderator) don't have the courage to post my comment, but I won't stop from commenting on such issues as I love my church and want to see it rising, instead of falling. Even if you don't post it, please share it with the writers of the article. They may listen unless their ears are deaf and eyes.....

Anonymous said...

Dear Brothers and Sisters,

The danger our church is faced is not a new phenomenon. Its a continuation of an already started 'operation' to devastate our beloved church.

A brother of us has asked why Mahibere Kidusan has been silent on the case. I am assuming our brother is not attending the association's movement closely. Mahibere Kidusan has been warning of these hidden and dangerous movements as of ten years ago. It has also clealry and quite repeatedly warned of the current "Tehadiso Movement". The recent "Hamere-tewahido" special edition was entirely dedicated towards awaring the church followers of this dangerous movement. It has very deep analysis of the current situation supported with research.

I am also sure this current document released by Dejeselam has been organized by Mahibere Kidusan and presented to the "bete Kihnet".

Now, what shall we do? Mahibere Kidusan has clearly outlined what we need to do. The tasks expected from every emmber of the church has been carefully outlined and presented. Lets all read Hamere Tewahido of September 2010 edition.

The church has full answer and explanation to any question the Tehadiso's raise (for those of you who honestly want that). Go to Mahibere Kidusan's shops and ask for books answering the questions. Surf on Kesis Dejene's blog (betedejene.org) or send your questions to any of the church teachers who are online such as Daniel Kibret, Ephrem Eshete..etc

Gates of the hell will never resist the church!

mebrud said...

እነሆ ይፋ ሆነ!!!!!
ስለ "ሰነዱ" አምላካችንን እናመሰግናለን።
የቤተክርስቲያን ነገር እንቅልፍ ነስቷቸው ችግሩን አጥንተው የሰነዱት ወንድሞችን እናመሰግናለን።
ባናመሰግናቸውም የቤተክርስቲያን አምላክ ዋጋቸውን እንደማያስቀረባቸው እናምናለን።ደጀ ሰላምም ዜናውን ስላደረስሽን ከምስጋናችን ድርሻሽን ውሰጅ።

ከቀረበው ዘገባ እኩሉ ማመን ስላልቻልን ወይም ስላልፈለግን እንጂ በቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሀን(የትኛው መገናኛ ብዙሀን አትበሉኝና) ሲዘገብ መቆየቱን አንዘንጋ።

ትስስሩን(ሊንካቸውን) ዘረዘረው፣፣የአደጋው ደረጃ ስፋቱን ጥልቀቱን አሳወቀን፣ ተጠናቅሮ ቀረበ፣ አካፋ አካፋ ተባለ ነው። እንዲህ በስፋትና በጥልቀት ባይተነትኑትም በእውነት የቤተክርስቲያን ልጆች ምልክቱን፣ስጋቱን ወጥመዱንና፣አደጋውን ቀድመው ያውቁታል።"ሰነዱ" ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ሴራ እንደተሸረበ፡ልጆቿ ግን ማንቀላፋታቸውን ይፋ አደረገው" ተብሎ ሊነበብ ይችላል።

የሆነ ሆኖ "ምን እናድርግ?" ብለን መጠየቃችን ጥሩ ሆኖ ሳለ፤ከኛ የሚፈልቅ መፍትሔ የለም ወይ?ያስባልል።
ለምሳሌ ተኝተን ነበር እንንቃ የነገራችን መጀመሪያ ሊሆንኮ ይገባዋል።ግንዛቤው መፈጠሩ ራሱ ትልቅ የመፍትሔ ደረጃ ነው።

አሁንም መገረምም መሸበርም አያስፈልግም።
በርግጥ የቤተክርስቲያ "አባል" ከሆንን አንጂ ልጆች ከሆንን አይደንቅም።

ካልፈለግንና አምላክም ካልፈቀደ የሚሆን ነገር የለም።
ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ።
እንደሰው የድርሻችንን ለመወጣትና ቤተክርስቲያን የተጠመደባትን ጌዜ ጠበቅ ፈንጂ ለማምከን።በተረጋጋ መንፈስ ማሰብ እንጀምር።

እንደግለሰብ-እንደቤተሰብ-እንደሰ/ት/ቤት-እንደሰበካጉባኤ እንደሲኖዶስ-እንደካህን-እንደምዕመን ምን እናድግ ብለን ጠይቀን።መፍትሔውን መቀመር ነው።እነሱ ለጥፋት ከተባበሩ እኛ ከአምላክ ጋር ለልማት የሚሆን ሰነድ ማፍለቅ ይሳነናል ወገኖቼ?አንጠራጠር።

ከኛ ጋር ያለው ከጠላቶቻችን ይበልጣል። ከኛ የሚፈለገው ፈቃደኝነታች ስለሆነ ወደ ተግባር ተቀይሮ ቤተክርስቲያናችንን ላይ የተሰበቀውን ጦር ለመመከት የሚያስችል ሰነድ እንዲዘጋጅ የጦር ዕቃችሁን አንሱ እርሱም ጸሎት ነው።

...አቤቱ ወደፈተና አታግባን።ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ.....ለዘላለሙ አሜን!

Dn. Tewahido said...

Abewu esti Yegeta kale ende Kiduse petrose teze yebelachehu!

"Begochen Tebeku" belo yazezachihune begune lemetebek beretu yetebekal ena!

Zare eko eyayen yalenew gubaea enkuaen siyazegaju yehen kemesemana kemaye belachehu tetefalachehu ( Example Ende Wolaita Sodow, hawasa Abatoch sera askiyajoche ena Aunoch) ADERA ADERA ADERA ...............

Anonymous said...

We are with you, Brother. The Anonymous no.12, advice and comment
is wonderful and very true. We love our Church and Faith.

God Bless you.

Aragaw said...

Second comentor,please read Hammere Tewahido 4.

Anonymous said...

እመ ብርሃን አደራሽን

Anonymous said...

The one who begins his writng by the word "Guys" tries to seem some wht follower of EOTC but his content indicates who he is. There nothing to be corrected from the EOTC teachings. The books are written by saints driven by holly sprite. Their is no any "debtera" book in EOTC. If you are saying their are debtera books, you dont know EOTC. so better to ask first about the churches books. and if you are an EOTC follower, the church didnt tought you to open your mouth for insult. "Aweraw bekidusan lay afun yekefetal" endetebale k aweraw wegen kalihoonk beker ysideb kal mesenizer baletegebahi niber.

Yekidusan amlak betekristianin yetebik

Anonymous said...

Dear all,

The main reason for all these mess up are:
1. The word of God should come true, it has been written in the Bible that all these will happen
2.Love for money,people badly desire to have a nice living style..and flashy stuffs. They are unknowingly driven by their motive under the cover of God.
3. Innocent people, those who did not ever go to church if they happen to be in others chapel, they start to complain and forward criticism to our lovely church which means they are talking about what they do not really know.

I think Mahiber kidusan has been playing a good and symbolic role as far as I know though I am not the member of them. Therefore this the time that M.Kidusa has to add a momentum to move forward to cut this bad demonic sprite from Ethiopia.

We know the end of the tehadis's teaching is going to be a perfect protestant and finally they will end up with non believers as we see them from different countries experience.

They all say Jesus is for them, however we indeed know how we all believe in Jesus and how we call him during our worship. He is our lord, God and Alpha and Omega, he is our every thing you guys let them know that we believe in Jesus much much greater and respectful than any one else. He is the base for Tewahido's church what is why the church has been their for such long period regardless of a lots of ups and downs. The church will also be there till the doom's day!

Let the grace of his lovely mother saint Marry be with us all.

sertsemedhin said...

ማንነው አዳሹ? ማንነው ታዳሹ? ይልቁንስ ሁሉም ወደእግዚአብሔር ያመልክት ..."መንፈሰ ርቱዐ ኀድስ ውስተ ከርስዬ..."

Orthodoxawi said...

ነገሩ እጅግ አስጨናቂና እንቅልፍ የሚነሳ ነው!
እግዜር ያክብርልን ደጀ ሰላማውያን!

እስኪ የመፍትሔው አካል እንድንሆን ድርሻችንን አሳውቁን::

እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን የጠብቅልን::

እንደቃሉ:- "የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!"

ጸልዩ!
እግዚኦ በሉ!

Anonymous said...

የ“ማኅበረ ቅዱሳን” ጥላቻ ምንጩ፣ መሠረታዊ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ የታወቀበት ዘገባ ነው፡፡ ሠርቶ የማያድር ነግዶ የማይከበር የወጣት (የዜጋ) ሸፋፋ (ልብ በሉልኝ ለለውጥና ራስን ለመቻል የሚፍጨረጨሩትን፣ የሚተጉትንና የተሳካላቸውን ብሎም ለወገናቸው የሥራ መስክ እየከፈቱ ያሉትን አይጨምርም) አቋራጩ መንገድ ፕሮቴስታንታዊውን ፈንድ ያለሃሳብና ያለድካም የሥጋዊ ኑሮአቸው ማድመቂያ ማድረግ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምዕመናን ዶላርም ባይሆን ብር ይሰጣል፣ እርሱ ተቸግሮ ለሰባክያኑ ለዘማርያኑ ከአየር ትኬት እስከ ኮንትራት ኮብራ መኪና፣ ከሆቴል አልጋ እስከ ምግብ፣ ከውሎ አበል እስከ ቦነስ ክፍያ ይሰጣል፡፡ የትኞቹም ሰባክያንና ዘማርያን ለወንጌል አገልግሎት ሲወጡ እነዚህ ነገሮች ጉባኤውን ባዘጋጁት አጥቢያዎች የሚሸፈኑ ወጪዎች ናቸው፡፡ የገንዘብ ምንጩ ደግሞ በዋናነት እግዚአብሔርን ለማገልገል ፍጹም ትኅትና ያላቸውና የገንዘብ አቅማቸው ከዕለት ጉርስ በላይ የሆኑ መልካም ኦርቶዶክሳውያን፣ ካለኝ ላይ ካልሰጠሁማ ምኑን ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብለው ከገቢያቸው ላይ ቀንሰው የሚሰጡና፣ የወንጌል አገልግሎቱን የሚያፋጥኑ ወጣቶች ናቸው፡፡
ለዚህ ሁሉ የጥፋት ድግስ የልብ ልብ የሰጠው ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ልጆቿን፣መንፈሳዊ ተልእኮዋንና አስተዳደራዊ ሰላሟን የሚያስጠብቅላትን ሕግ የሚጻረሩ ተግባራት በገፍ አየተፈጸሙ በዝምታ መታለፉ ነው፡፡ አሁንም አልመሸም፣ መቼም ቢሆን አይመሽምም፡፡ በደመ ክርስቶስ የታነጸች ቤተክርስቲያን የመሸበትን ታነጋለት ይሆናል እንጂ፡፡ ለዚህም ነው ይህ ሁሉ የጥፋት ድግስ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ በእንጨጩ ፀሐይ የሞቀው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በሁሉም የመረጃ ማስተላለፊያ መንገድ ሁሉ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

Anonymous said...

TellTthe Truth:

ሰላም ወገኖች፡

ከ10 ኣመት በፊት በአንድ የሰንበት ትምህርት ቤት በእውኑ ወቅት ከሚያስችግሩት ሰዎች በተሰጠ የክረምት ኮርስ ወስጄ ነበር። እግዚሃብሄር ግን ከስመተህድሶ በድብቅ ግን የፕሮቴስታን መንጋ ከመዎን በጥበቡ አዳነኝ።

የተሃድሶ እንቅስቃሴ የሚባል የለም እያሉ እውቀውም ይሁን ሳያውቁ የሚሟገቱንን በዚህ blog እና dskmariam.org በተለያዩ ጊዚያት ከለምዴ በመነሳት አስተያየቴን ሰጭቻለው። የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመማር የሚመጣውን መስኪኑን ወገን እንዴት ቀስ በቀስ እንዴት እንደሚሰልቡት፤ ከዚያም እንዴት ወደ ሌላ በረት እንደሚከቱት፤ እኔ እንዴት እየተፈተንኩ እንደነበረ፤ እንዴትስ እውነተኛውና የታመነው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከዚያ ከፕሮቴስታንትዊ እንቅሰቃሴ እንዴት እንዳዳነኝ- ለሌላው ትምህርት እንዲሆን አስተያየት ከመስጠት በገንዘብ ከመደገፍ በአለፈ ደረጃ እንዳልሳተፍ(እንዳልመሰክር) ስንፈና ያዘኝ።

Jesus Christ is our God & Saviour, Lords of Lord Kings of King, The Son Of God. He is the Master of Our Church.

Yours brother in Christ from N.America

መላኩ said...

እግዚአብሔር ይስጥልን፡ ደጀሰላም!

ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ወገን ይህን ያህል ጸረ-ኢትዮጵያዊ አቋም ይዞ አባቶቹንና እናቶቹን የሚያንቋሽሽ ድርጊት እየፈጸመ ፈጣሪውን በድፍረት የሚያስቀይም ስልት ሲጠቀም ሳይ እጅግ በጣም ነው የሚያሳዝነኝ። እንዴት ይሆን ይህን ያህል ራሱን የሳተ ደካማ ትውልድ ሊፈራ የበቃው?

"ተሐድሶ" የሚለው ቃል "ተዋሕዶ" ከሚለው የግዕዝ ቃል ጋር ስለሚመሳሰል፡ ዘመቻ ላይ ያሉት ሠራዊቶቹ ከፕሮቴስታንት ወገን መሆናቸውን ብዙዎቻችን ልብ ብለን አናስተውልም።
ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ብለው ከቀረቡን ብቻ የኛዋ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነገር ስለሚመስለን፡ የሚቀርብልንን መረጃ ጽሑፍ ሁሉ አግበስብሰን እንቀበላለን። ይህ የሚያሳየን፡ ሰይጣን፡ዒላማውን ለመምታት፡ ምን ያህል ወሽካታ፡ደካማና አስቀያሚ የሆነ መንገድ እንደሚከተል ነው።

ቸሩ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጠን!

ልሳነ ሳህል ከለንደን said...

ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ ይገባኛል: ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ትልቅ ችግር ላይ ነች በውስጥ የተሃድሶ አቀንቃኞችና በፍቅረ ነዋይ የደነዘዙ ግለሰቦች ከውጪ መናፍቃንና አህዛብ ሲፈታተኑዋት እያየን ነው:: ዘሬ መናፍቃን ስልታቸውን በመቀያየር ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑና በፍቅረ ንዋይ ዐአእምሮዋቸው የደነዘዘ አንዳንድ ካህናትንና በልዩ ልዩ ኮሚቴ የሚሳተፉ አገልጋዮችን በጥቅም በመያዝ ምን አለበት በሚል የደካሞች ፈሊጥ በመጠቀም ሕገ ቤተክርስቲያን እንዲጣስ በማድረግ ላይ ናቸው:: ዛሬ ጾምን የሚቃወሙ : ከጋብቻ ውጪ የወሲብ ግንኙነትን የሚገድፉ:በወር አበባ ወቅት ቤተክርስቲያን መግባትንና ማገልገልም እንዲሚገባ የሚያስተምሩ :አሳማም ይሁን ጅብ ውሻም ይሁን ዝንጀሮ አይጥም ይይሁን ቀብሮ ሥጋ ሥጋ ነው ኦሪት ተሽሮዋል የሚሉ የተሃድሶ አቀንቃኞች ስለበዙ ከወትሮው በበለጠ ተጠናክረን ቤተክርስቲያናችንን እንጠብቅ::

Ameha said...

ይህንን እውነታ እንድናውቅ ያደረገ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው! የተደበቀውን ገላልጠው በቤተ ክርስትያናችን ላይ የተነጣጠረውን ሤራ ለሕዝበ ክርስትያኑ ያሳወቁትን የማህበረ ቅዱሳን አባሎች እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይክፈላቸው። ከዚህ ሪፖርት በመነሳት ሁላችንም በያለንበት ቤተ ክርስትያናችንን እንድንታደጋት በእግዚአብሔር ስም መላውን ምእመናን እጠይቃለሁ። ከምንም በላይ በጾምና በጸሎት ልንተጋ ይገባናል። "ኢትዮፕያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" የተባለው ዘመን አሁን ነው። እግዚአብሔር ኃይማኖታችንን፤ ቤተ ክርስትያናችንን እና ሀገራችንን ይጠብቅልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Anonymous said...

ወገኔ "ዘብሔረ ጉራ" ለጠየካችው ጥያቄዎች ከዚህ በፊት(DEC'2010) በዚህ በመድረክ ካስለፍኩት ህይወት ተነስቼ አንዲህ ከዚህ የተቀራረበ አስፍሬ ነበር፦

ብዙዎች የዋሃን እንደምናስበው የProtestantism(የTehadsso) ተልህኮ ስለጌታ እናት፤ ሰለመላእክት ፤ ስለቅዱሳን ወይም ስለ ቤትክርስቲያን ስርኣት;- ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ቀስ በቀስ ማስተው ብቻ አይደለም። ዋነውና ትልቁ ተልህኮ ሃዋሪያት ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ ወንጌልን መስበክ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ስራ ላይ የሚቃረን ትምህርት ምስተማር ማጸረስ ነው። ከአባቱ ጋር በክብር እኩል የሆነውን ጌታን ከክብሩ በማሳነስ በዚህ ዘመንም ስለእኛ እንደሚማልድ(እንደሚጸልይ)፤ ቅዱሳኑ ግን ይህንን እንደማያደርጉ ቀስ በቀስ እና ወስጥ ለውስጥ ያስተምራሉ። እነዚን ታላቅ የስህተት ትምህርቶችን በዋናነት ለማድከም ማ/ቅዱሳን አና ሌሎች መምህራን እንዲሁም የቤተክርስቲያን ወገኖች በሙሉ የዶግማ/የሃይማኖት መሰረት/ የሆኑ መሰረታዊ ትምህርቶች ላይ ይልቁንም ከቅዱሳን የአማላጅነት እና ስርኣት ቤተክርስቲያን በበለጠ ሰፊ ጊዜና ማብራሪያ ተሰጥቶት ሊሰራጭ ይገባል።

ዋነውና ትልቁ ልዩነት በእኔ አመለካከት ከProtestantism(ከTehadsso)የዶግማ ትምህርት ነው ። ስለእመቤታችን፤ ስለመላእክት፤ሰለቅዱሳን... ቀጥሎ የሚመጣ ነው። እዚህ ጋር ለማለት የፈለኩት ስለነዚህ አንማር ሳይሆን፤ መእመኑን በቤተክርስቲያኗ የዶግማ ትምህርት ላይ ከተተከለ፦ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ፤ እውነተኛው የእግዚሃብሄር ልጅ፤ እርሱ እግዚሃብሄር ሳለ(ዩሓ 1፤1-)፤ ከክብሩ ስፍራ ወደ እኛ ፤ እኛን ሊያድን ሰው እንደወነ(ከድንግል ማርያም) እንደተወለደ ፤ ሰለሃጥያታችን እንደተሰቀለ ሞቶም በክብር እንደተነሳ እንዳረገም፤ አሁን በሙሉ ክብሩ እንዳለ፤ ሊያድንም ሊፈርድም እርሱ ቻይ እንደወነ የሚያምና የሚያውቅ፡፡ እውነተኛው የእግዚሃብሄር መንፈስ ቅዱስ፦ በማይታወቅ የድምጽ ጋጋታ "ልሳን" ፤ የጸጋ ስጦታ የተባለ በውሸት በቀድሞም ወነ በዚህ ዘመን እንደማይሰራ ከቅዱሳት በጻህፍ መርምሮ የተርዳ ፤ መጽሓፍ ቅዱስ አንዴ እንደአንድ መጽሓፍ እንኩ ተብሎ የተሰጠን እንዳልሆነ እና በአንድ(?) ቮልዩም (ጥራዝ) የተዘጋጀው እያንዳንዱ ቅዱሳን መጻህፍት ከተጻፉ ከብዙ ዘመናት በዋላ እንደወነ የሚረዳ ትውልድ ካፈራን። Protestantism(Tehadsso) የሚያነሱት ማንኛውንም የሃይማኖት ነገር ለምሳሌ ስለቅዱሳን አማላጅነት፤ስለጾም አስፈላግነት... ከመነጋገሩ በፊት መሰረታዊ እና ዋና ከወነው የወንጌል ትምህርት፦ በጌታች እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተለየ ትምህርት ስለምታስተምሩ በትንሹ ልዩነት(መልስ ስለሌለን እንዳልወነ ይታወቅ) ላይ መነጋገር ከእስማኤልዊያን ጋር በእግዚሃብሄር ሶስትነት እና አንድነት ላይ ከመነጋገር ይልቅ በጾም ወቅት ስጋ ስልመብላትና ስላለመብላት እየተወያዩ ጊዜን አንድማባከን እንደወነ እያስረ፤ ከመከላከል ይልቅ ወደማጥቃት የሚዘምት፤ የመናፍቃንን ምላሽ የሚማር ትውልድ ብቻ ሳይሆን ሃዋርያት ከሰበኩት የተለየ ወንጌል ንጉስም ወይም ከሰማይ መልአክም፥ ቢሰብክ/ልሰብክ ቢሞክር/ እየተከታተለ በእግዚሃብሄር ቃል የሚይፈርስ ትውልድ ቤተ ክርስቲያን ልታፈራ ይገባታል።

With Love

ዘክርስቶስ said...

ሙሉ ዘገባውን እስከማነብ ድረስ ዝምታን መረጥሁና የታየኝን ስጋት በአጭሩ ሊገልጽላችሁ ደግሞ ተውተረተርሁ።

የደጀ ሰላም ዘገባ መልካምም አስጊም ነው። ይህ ሪፖርት አማናዊ ከሆነ ከተራው ምእመን እስከ ጫፍ አማኝ ነካክቷል። እና ‘መልካም ነው’ ያልኩበት ምክንያት በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ አጥንተው ማቅረባቸው፤ ‘አስጊም ነው’ ያልኩበት ምክንያት ደግሞ የሆነውንና ያልሆነውን ይዘን ለሐይማኖታቸው ሲሉ ቀንና ሌሊት በመትጋት ላይ ያሉ ወገኖቻችን ስማቸው በተሀድሶውን ፋይል ስናስቀምጠው በመሐከላችን የባሰ ክፍፍል እንዳይነግስ ወይም ሌላ ሲኖዶስ እንዳይፈጠር በጣም ሰጋሁ። ይህም ለመናፍቃኑ እስትራቴጂ አፋጣኝ ስራ አስፈጻሚዎች ሆንላቸው ማለት ነው። እነሱ የፈለጉት የመጨረሻው ስልት እርስ በርስ አለያይቶ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት መረከብ ይመስለኛል።
ስለዚህ ወንድሞቼ አካሄዳችን ጥበብ ይኑርበት፤ ጥናቱም እውነትና ቀጣይነት እንዲኖረው እንፈልጋለን፤ ነገርግን ለመፍትሔው ስማቸው በዘገባው ካየናቸው ተቀራርቦ መወያየትና ቤታችን ለመጠበቅ አንድ የሚያደርግ ስልት መቅረጽ ያስፈልጋል ካልሆነ ግን ሥራችን
የተሐድሶዊያን የሕዝብ ብዛት መጨመር ይሆናል ማለት ነው።

ደጀ ሰላም? በአሉታም ይሁን በአዎንታ የግለሰዎች ስም ባታወጡ ይመረጣል

ሁላችን አንድ ሆነን ቤታችን ለመጠበቅ እግዚአብሔር ጥበቡን ይስጠን

Anonymous said...

Yesened megenget minim ayasdeniqengin mikiniyatuum mantehadiso indehonena adash indehone begibrachewu silemitawequ lezih hulu tebasa mefeter ke hayer arkiwu iske mimenuu dires texeyqiwoch nen diroos beyefirkitawu sir yetsiwamahiberat indegibreguundan sibeeza dimokirasinewu tebiloo zim yalewu maaneu? "akasuumaan najelqabe jettemaraatuun jedhani".

Anonymous said...

Few of suggestion givers have looked the negative side of the report but most of us are emotionally jot downing our unscreened comments. I have not even a single belief that solution will come by doing unforeseen futures.

Deje Selamawians and all readers? Read DISCERNMENT before doing everything.

Ke Awasa

Izra Zegondar said...

Dear all believers, don't worry God is always by our side.

Dejeselam, thank you for sharing us this valuable info. We have to focus on their strategies. I know finger-counted tehadisos and their words are always devlish and often similar. Let's focus on this strategies and do what we have to do. Here in Gondar, they are totally unable to control the youth. We know how to deal with these pointless guys....shall I name you? please reckon that you know nothing to be echos of protestantism...

Fighting tehadisos is no more Mahbere kidusan's agenda. I am a sunday school student fully aware of what they are. Sefytan efer!

Unknown said...

እግዚአብሄር ይመስገን ህዝቦቹን ከጥፋት ይጠብቅ!!!ወደፊትም በደንብ አሳዉቁን:: እግዚአብሄር ምስጢሩን ይግለፅላችሁ::

Anonymous said...

This is so awful!! but the salient stuff at this time ought to be looking for the ideal solution to this problem. Religion is a matter of identity. Guys, the so called reformers don't care about us. In Europe it is only 5 to 7% of the population have religion. So if they are that much worried about how to preach Christ, the ideal place is found in Europe. But their ultimate aim is not Jesus but dismantling our true religion and switching the society to paganism like them. Historically,it is believed that the reformation movement in Europe fueled by their Evil father, Martin Luther,is the cause of the current mess they face. In true sense there is no life!! We are a social animal. We need to be gathered and vowed for our God. It is our church which thought as the concept of Unity is strength! As a testimony, taking timiket and meskel is enough!! It is these all we true Christian are!! But Luther gave wrong authority to all individuals to interpret the Bible as they like. This authority empower everybody to stay home and pray for God,no gathering, no mutual respect. This self centered though sprouted the current super ego citizens of Europe. These people who are a victim of egoism can never be our reformers.

as to me it is impossible to think Ethiopia without EOC.Who fought for this country? who kept the historical chronicles of this country? Who inspired the people to say "No" to white colonizers? who make the people calm and cool? Can we be Ethiopian with out EOC? .ALL WE WALK AT THIS TIME BECAUSE of THE SCARIFIES OF THIS CHURCH!! LUTHER DIDN.T STOP COLONIZATION!!!!!UNLIKE LUTHER WHO CENTERED ON EGOISM, OUR CHURCH PREACHES ABOUT UNIFICATION AND MUTUAL RESPECT.

I don’t want to crass any body for the problem we face. We all should be spiritual soldiers and should do away with this problem. We have to cease this wrong expansion. We should safeguard our church!! But there should be some entity which should be in charge of mobilizing the people. We should have our own mechanism of informing who is who in the church. You know all we are in the era of information technology therefore this doc should be distributed to the public using some meanses. Or at least we have to inform the public by sending SMS texts to the public where to get this doc.

Saykatel bektel

What is happening in Hawassa is a good example.they could deceive the people and urge the people to develop wrong perception about the church. This doc shouldn,t be kept as a secret in some isolated place.let us get it and identify our enemies.

God bless this blessed nation!!!!!

Anonymous said...

Here is a suggestion from someone who is a follower of the EOTC and has been reading this kind of writings for sometime. To those protestants who would like to change the orthodox church or followers to the orthodox faith I say this:
What you call reform is a misnomer. What you want is to bring about change such that the orthodox faith is replaced by the protestant faith. This is a fundamental change and is not a reform. The protestants (both Ethipians and non Ethiopians) have been trying to do this for some time now. For them,followers of the Orthodox faith in general (including EOTC,Egyptian Orthodox church, etc) are not true christians. The truth of the matter is they are the ones that are not true christians. They are the ones that do not follow the bible, pick and choose what they want to believe and practice in the bible. But they think that they are the only ones who are truly christians. That is one of the reasons for having hunderds of denominations in the protestant church. Every body translates the bible in the way he or she pleases them and form their own denomination. My advise to these protestants is if you want to bring change, your church is the one that needs change badly. Your church is the one that requires true interprtation of the Bible. Start the change in your home. That is what the bible teaches. Do not try to spread your false teachings to others.
My advise to Othodox christians is study your faith and know your faith, and do not be distrubed by teachings that come from with in and with out that try to disrupt our church. Ignorance is our number one enemy. If you want to our church to stay strong, you will need to be knowledgeable in your faith. That is the only way out church can survive.
To followers of Mahbere Kidusan, my suggestion is : please stop considering yourselves as the ony followers of the EOTC. You are not the only ones that follow the teachings and faith of EOTC. Instead, try to work with others to come up with a common program with others that would make our church stronger. If you think that you are the only followers of the faith, and every body else is "menafikan", that shows that you have a problem. And you would need to change this attitude. It is not good for you (the Bible does not encourage or teach this kind of attitude); and it is not good for the church as it leads to fracturing of its members. Work for peace and love, rather than confrontation and division.

May the Lord keep our church from intruders.
With our prayer, and the prayers of our Mother and all the Saints, our church will endure until the coming of Christ, out Lord.
Geremew Zeberga

Unknown said...

Selam Borthers and Sisters,
I don’t get surprised by the Protestants’ mission on the church. They are always looking for destruction of the church. Though they say we respect the church we have been looking what they have worked for the past 20 years. They major mission center is the church and its people.
We can avoid these if we do the following:
1. Let us have well organized teaching system so that every orthodox Christian knows the orthodox dogma and cannon
2. Let us differentiate the true teachers from the wolves. There are many wolves here and there so let us identify and make clear from whom to hear from.
3. The major thing we need to know is making the people to know the truth about the church. Let us teach the true Gospel of the Jesus to everybody in the church. Let everyone knows his own religion and defend by himself. Fathers cannot see each and every body. But if we have strong teaching about the beliefs of the church and the Gospel of Christ, many people cannot be easily victims of the wolves.
4. Let us make the reformation by our self. This is not a matter. I myself who grew up in church from priest family know some traditional beliefs which are not related to the church’s teaching /Gospel. The reformists and Protestants exaggerated them and try to ashamed the orthodox Christians. So the best solution is if the church fathers are really concerned about the church they have to make the necessary modifications.
5. After all the orthodox dogma is solely on bible but the reformists and Protestants teach and speak everywhere as if our dogma is on awalde metsahefit or tamire mariam or any other books excluding bible. Though those books are respected by the church they are not the sources of our dogma. Our dogma is on bible.
6. All Orthodox Christians should identify dogma, cannon, tradition and other different things in the church. The wolves are constantly making different attempts to dismantle the orthodox belief from the people as most of don’t identify the differences and relations between them.
7. Even we should try to challenge the Protestants. I myself who had been talking with Protestants challenge them and show how Protestants are wrong. So if we know orthodoxy from ground in appropriate way we can show them they in the wrong path.

yalew said...

praise and glory be to God

Anonymous said...

“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን፤”(ገላትያ1-8) በሚል መሪ ቃል ምእመኑን በወንጌል ቃል ምበትከል ለሚጠይቁት ሁሉ የተዘጋጀ ማድረግ ይኖርብናል።

የProtestantism(የTehadsso) ተልህኮ ስለጌታ እናት፤ ሰለመላእክት ፤ ስለቅዱሳን ወይም ስለ ቤተክርስቲያን ስርአት፤ እውነተኛዊቷ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ማስተው ብቻ ሳይሆን፤- ዋነውና ትልቁ ተልህኮ ሃዋሪያት ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ ወንጌል ባለማወቅም ወነ በማወቅ ይዘራሉ። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ማንነትና ስራ ላይ የሚቃረን ትምህርት ያስተምራሉ ።

ከአባቱ ጋር በክብር እኩል የሆነውን ጌታን ከክብሩ በማሳነስ በዚህ ዘመንም ስለእኛ እንደሚማልድ(እንደሚጸልይ) ማስተማር ታላቅ የስህተት ትምህርት መሆኑ የኛ ወገን ብቻ ሳይሆን ከበር ውጭ ያለሁም ሁሉ እንዲያወቅ ማድረግ አለብን። ሃዋርያት እንዳስተማሩን ጌታ በአካል የማስታረቁን ስራ አንድ ጊዜ በመስቀል ለይ ፈጽሟል። ዕብራውያን 7-27 “እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።”
2ኛ ቆሮ 5-16 “..ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።...እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።

ስለመንፈስ ቅዱስ የሐዋ 2፤4-10 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር... እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ...” እንግዲህ አንዱከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የወነው ልሳን(የሚታወቅ የሰው ልጅ ቋንቋ ነው)፤ Protestant(Tehadsso) መንፈስ የሞላ ብለው የሚያሱን ግን ምን እንደወነ የማይታወቅ የድምጽ ጋጋታ ነው። ይህንንም ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ልሳን አድርጎ ማስተማር መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው።


ማስታወሻ በማወቅም ወነ ባለማወቅ የተሃድሶ(የፕሮተስታንት)ተከታዮች ለሆናችው፦ እባካችውን ለእውነተኛውን ጌታ ክብር የምትሮጡ ከመሰላቹ ፤ እርሱስ በሐሰት አይከብረም ከብሮም አያወቅም። የክብርን ጌታ ብታውቁትስ ኖሮ እንዲህ ብላችሁ ወደልባችው ትመለሱ ነበር ፦ ጌታ እየሱስ የከፍለልኝ ዋጋ ይበቃዋል፡ አሁን ጌታን በፊት በስጋ ወራት እንደምናውቀው አይደለም። አሁን እኛ ወደድንም ጠላንም በክብሩ ነው ያለው በቅዱስኑም ላይ የማስታረቅ ቃል አኑሮአልና። ይህ እውነት ነው።

Jesus Christ our God, Lord Of Lord Kings Of King, the Son Of God.

Anonymous said...

ለዘክርስቶስ
ከጥምቀት በዓለ አከባበር ጋር በተገናኘ በሰጠኸው አስተያየት ላይ የአንተ ጉዳይ ሾላ በድፍን ሆኖባቸው ማለት የምትፈለገውን በግልጽ ቋንቋ እንድታስቀምጥ ሲያሳስቡህ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ በእርግጥ እኔም በይሁንታ እያለፍኩት ቢሆንም የእነዚህን አስተያየት ሰጪዎች ትኩረት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ አሁን ለእኔም ግልጽ ሆኖልኛል፡፡
መረጃው የሚለው እኮ ባለ50 ገጽ የጥፋት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ ነው፡፡ ገባህ! ታዲያ ስንዴውን ከአረም ጋር እንዳንነቅለውን ምን አመጣው? ሠነዱ ስለአረም ነው የሚያወራው፤ ያውም አራሙቻዎቹን የት እንዳሉ፣ከማን ጋር እየሠሩ እንደሆነ፣ መቼ እንደተጀመረ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ታዲያ ያንተ ስጋት ከምን የመነጨ ነው? የምንስ ሲኖዶስ ነው የሚፈጠረው? ያለኸው አሜሪካ ነው? ከሆነ እዚያ ውስጥ ደጋጎቹና የእኛ እረኞች አባቶቻችን እንኳን በማያውቁት መንገድ የተሰገሰጉ ተሃድሶአውያን እንዳሉ ልትነግረን ፈልገህ ከሆነ አትድከም፤ እናውቀዋለን፡፡ ስምን አትጥቀሱ ምንን አመጣው? በመሠረቱ አካሄድህ የደፈጣ መሆኑን ያሳየኝ የፈራኸው የስም ዝርዝር በአሉታዊ እንዳይዘረዘር ሚዛናዊ ለመምሰል “ደጀ ሰላም? በአሉታም ይሁን በአዎንታ የግለሰዎች ስም ባታወጡ ይመረጣል” ያልከውን ሳነበው ነው፡፡ በመሠረቱ እገሌ ጥሩ ሠራ ተብሎ በቤተክርስቲያን አይሞገስም በብዙ ምክንያቶች ዋናው ግን ውዳሴ ከንቱ እንዳያሽንፈው፤ ገባህ ታዲያ መሠሪዎቹ እንዳይጋለጡ በስልት ለመናገር ሞከርክ፡፡ ምን አስፈራህ? በራድ ወይም ሞቅ ያልክ ሁን ለብ ማለት ተቀባይነት የለውም፡፡
በመሠረቱ የተሃድሶ ዋነኛ ዓላማው ሁለት ነው፡፡
አንድ አስተያየት ሰጪ ለዘብሔረ ጉራ የሰጡት አስተያየት አንዱ ነው፡፡ እንደሚከተለው ተቀምጧል
“ብዙዎች የዋሃን እንደምናስበው የProtestantism(የTehadsso) ተልህኮ ስለጌታ እናት፤ ሰለመላእክት ፤ ስለቅዱሳን ወይም ስለ ቤትክርስቲያን ስርኣት;- ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ቀስ በቀስ ማስተው ብቻ አይደለም። ዋነውና ትልቁ ተልህኮ ሃዋሪያት ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ ወንጌልን መስበክ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ስራ ላይ የሚቃረን ትምህርት ምስተማር ማጸረስ ነው። ከአባቱ ጋር በክብር እኩል የሆነውን ጌታን ከክብሩ በማሳነስ በዚህ ዘመንም ስለእኛ እንደሚማልድ(እንደሚጸልይ)፤ ቅዱሳኑ ግን ይህንን እንደማያደርጉ ቀስ በቀስ እና ወስጥ ለውስጥ ያስተምራሉ።”
ሁለተኛው በጣም ከባዱ ነው፡፡ ጨርሶ ከእምነት መሠረት መንቀልና ለአውሬው ማዘጋጀት፡፡ አሜሪካም ሆነ አውሮፓ ውስጥ ሃይማኖት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳይ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ ይህን አጭር ጽሑፍ ካነበብኩት ላካፍለህ፤
አሜሪካ ውስጥ ከ1963እ.አ.አ ጀምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት ሥርዓት በይፋ የተከለከለ ሲሆን በአንጻሩ በአሁኑ ጊዜ በሺህዎች የሚቆጠሩ ት/ቤቶች ዲያብሎሳዊ ትምህርቶችንና ሰይጣናዊ አድራጎትን ያስተምራሉ፡፡ ከ200ሺሀ በላይ የጠንቆላና የአዚም ተግባራት የሚፈጽሙ ሰዎች ያሉ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በዚሁ ዘርፍ በትምህርት ስም ተሰልፈው ይገኛሉ፡፡ በአዚምና ጥንቆላ ላይ የሚጻፉ መጽሐፍት ሽያጭም በእጥፍ እያደገ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ U.S. public schools "departed from the faith" when in 1963 the Bible & prayer were officially banned. Now thousands of these same schools are teaching credited courses in "the doctrines of devils"--the occult and Satanism! It is estimated that there are over 200,000 practicing witches in the United States & there are literally millions of Americans who dabble in some form of the occult, psychic phenomena, spiritism, demonology & black magic. Statistics show that occult book sales have doubled in the last four years!
ታዲያ እነዚህ ክርስቶስ አልተሰበከም ብለው መንፈሳዊ መስለው አኛን አክለው የሚነዘንዙን አዳሾች በሚሊዮን የሚቆጠረውን የራሳቸውን ሕዝብ ወደ መንፈሳዊነት ያለማምጣታቸው ምክንያቱ ምን ይሆን? ሌላም ልጨምር፣
አሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ ኢንፎፔት ተብለው በሚጠሩና ለምርምሩ በተመረጡ እንስሳት፤ ቆዳቸው ተበጥቶ ማይክሮቺፕ (microchip) የተገጠመላቸው ሲሆን ምርምሩ እንደሚያሳየውም በዚህ አማካይነት አስከ 4ቢሊዮን የሚቆጠሩ በዓለም ላይ የሚገኙ የድመትና ውሻ ዝርያዎችን በኮምፒውተር አማካይነት በቀላሉ መቆጣጠር እንደሚቻል ተደርሶበታል፡፡ ይህ እንግዲህ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ የሚሆነው በግንባር ወይም በቀኝ እጅ የሚገጠመው ማክሮቺፕ የአውሬው ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ይህም ምርምሩ ውጤታማነቱን በአጥጋቢ ሁኔታ ያስመሰከረ ሲሆን ቀጣዩ በተግባር ማዋሉ ላይ መሆኑ ነው፡፡
በመጨረሻም ሠነዱ ስትራቴጂውን በግልጽ አስነብቦን እንኳን አሁንም አንተ ልትሸውደን እየሞከርክ ነው እኮ፡፡ ሠነዱ የሚተርከው እኮ አንተን ነው፡፡ አንተ ዞሮብህ የዞረብን አታስመስል፡፡ ይኸው ከጽሑፉ የተወሰደው፣
“ቀጣዩ ምዕራፍ በእነዚህ ምንጮች ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ በመምሰል ሰርጎ መግባት እና ለሥራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡ የአፈጻጸም ስልቶቹም እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ እና የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ እና ተቆርቋሪ መስሎ መታየት፣ ኦርቶዶክሳዊውን ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዐት ለጊዜው አለመንቀፍ፣ በሕይወት እና በአገልግሎት ምሳሌ ሆኖ መታየት፣ ተአማኒነትን ለማግኘት ማንኛውንም መንገድ መጠቀም፣ የአገልግሎት መድረክ መያዝ - ሐላፊነት፣ ሥልጣን መያዝ እና በሕዝብ ልብ ውስጥ ለማደር መሥራት ናቸው፡፡ …”

Anonymous said...

Dear brothers and sisters
this is the awakening bell for those (such as me)who are sleeping even though we are witnessing the preaching from TAHADSO. for eg. I'm one the group of little ppl from DC, MD, and VA who are attending at this place (ECDC) which the "prist' officially announcing that "been 'tehadso' is not bad as others says" kind of official preaching. He is well known by other tewahido members as tehadso. even most of his members are known as protestant.The question is there are ppl who are attending this place without knowing him who he is. I went one time and know who he is but did not help others .
what do i've to do?

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን የደረሳችሁን ማስረጃ ስለአሰማቸሁን እግዚአብሔር ይስጥልን
ሰውየው ከሰውጋር ተጣላና ሲረግመው መጥፎ ጎረቤት ይስጥህ ብሎ ቢረግመው ቤቱን ለቅቄ እሔዳለሁ አለው
እንግዲያው መጥፎ ሚስት ይስጥህ ቢለው እፈታታለሁ ቢለው መጥፎ ልጅ ይስጥህ አለው አሁን በየት አገኘኸኘ
አለው ይባላል፡፡ አሁንም መጥፎ ልጆች ተውልደው ታሪክን አጥፊ ዳግማዊ አርዮሶችና ንስጥሮሶች …………..
እባካችሁ የበግ ለምድ ለብሰው የዋሁን ሕዝብ ከሚያመሳቅሉ እንጠንቀቅ ጉልበታችንም ሀይላችንም እግዚአብሔር
ነው ድንግልን ምርኩዝ ይዘን የማንወጣው ዳገት የለምና ይታገሉናል እንጂ ሊጥሉን አይችሉም እንጸልይ እገዚኦ
እንበል እንደ ነነዌ ሕዝብ መአቱን ያነሳልናልና፣እንቅልፍ አናብዛ ጽናት ያስፈልጋል ሁሉም ዘብ ይቁም በቦታው፡፡
እባካችሁ አንድ ተቆርቋሪ እንዳለው ይህን ጽሁፍ ላልደረሳቸው እያባዘን ብንሰጥ ጥሩ ነው፡፡

lemma kefyalew said...

sinodos inezih mahiberat ina sewoch tehadiso mehonachewun kaweke lemin kebete kristiyanachin ayleyachewum?

Anonymous said...

ጽሁፌን ታወጡት ይሆን? ሚዛናዊ ዘገባ ወይስ ወደአንድ ወገን ያደላ? ይሆን አቀባበላችሁ። ተሀድሶን የተመለከተ የተቃውሞና የቁጭት ሃሳብ ተቀብላችሁ፤ የዚያን አጸፋ ትጥሉት ይሆን እያልኩ ጽፌላችኋለሁ። በዚህ ዘመን ላይ ፍጽምት የሆነች ቤተክርስቲያን አትገኝም፤አትኖርምም። ክርስትና ግን በክርስቶስ ፍጽምት ነበረች፤ ነችም። የክርስቲያን ጉባዔ(አክሌሲያ)የተለያዩ ሰዎች ባህል፤ወግ፤ስርዓት፤አስተምህሮ ወዘተ ይዘው የሚገናኙባት በመሆኗ ልዩነቷ ሰፍቶ ፍጽምት የነበረችውን ክርስትና በየራሳቸው ስምና ጎራ ለይተው ይጠሩ ዘንድ ግድ ሆኗል። ኦርቶዶክስ፤ካቶሊክ፤ፕሮቴስታንት፤ሉተራን፤ካልቪኒዝም,,,የሚባለው የጎራ ስም በሰዎች የተፈጠረ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የነዚህ ስሞች አስተምህሮ አይገኝም። አንዲቷ ቤተክርስቲያን የተለያየችበትም ምክንያት ከፍጽምትነት በመለየቷ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ከዚህ ውጪ አይደለችም። የሚመሯት ሰዎች የመንፈስ ቅዱስ ተገዢ እስካልሆኑና እርሱ ባልከበረበት ቦታ እድሜን ለክቶ ክብር ይሰጣል ማለት እንደ እሩቅ ብእሲ መቁጠር በመሆኑ ከዚህ አደጋ ልንጠነቀቅ ይገባል። ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያን በበረሃ ወድቀው የቀሩት መንፈስ ቅዱስን ስላልታዘዙት እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ስላልነበሩ አይደለም። ከባህር የወጣ ሰይጣን ተገረዘ፤ተጠመቀ፤መነኮሰ፤ መንግስተ ሰማያት ገባ፤ የምትል ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራት ብሎ ማሰብ እብደት ነው ወይም የእግዚአብሔር ፈቃድ ለሰዎችና ለሰይጣናት ምን እንደሆነ ገና ስለማታውቅ ቀስቃሽ ያስፈልጋታል ማለት ነው። (ገድለ ተ/ሃይማኖት ምዕ 48)(ራዕይ3፤15) ያለውን ችግር ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ችግሩን ለይቶ እንደእግዚአብሔር ቃል ለማረም መሞከር ብልህነት ነው። የተከደነ የተሰወረ አይኖርም። ሁሉም ይገለጣል። አሁን በቤተክርስቲያን ብዙዎች(ለእሉ ክልዔቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ)የሚለውን ክብር ለሚገባው ክብር መስጠትን ወደጎን ትተው የክብር ሁሉ መገኛ ከሆነው አምላክ ጋር እኩል ማድረግ ፍጡርን ማስተካከል ክህደት መሆኑን ተረድተውታልና ይልቅ ከእውነቱ ታረቁ። ያዘው፣ልቀቀው መፍትሄ አይሆንም።

tad said...

DS;
Look, you might be right guys sometimes, but because you accuse everybody who sings attractive songs and preaches eloquently, like Mirtnesh and Begashaw, I am doubting your posts on those issues."You remind me the foul crying shepered.

Anonymous said...

ሰላም ለሁላችሁ ።
ጥያቄ አለኝ፣ በሥላአሴ ሦስትነት እና አንድነት የምታምን፣ በአንድ ሲኖዶስ፣ቀኖና ሥርዐት ስትመራ የነብርች ኦርቶዶክሳዊት አምነት ስትሆን፣ ለምን የተለየ መሀበር ማቋቋም አስፈልገ? ለምሳሌ ማህበረ ቅዱሳን ተብሎ የሚጠራ ማሕበር አለ፤ የመሀብሩ ተቋዎሚ ወይም ደጋፊም አይደለሁም! ዋናው ሀሳቤ............................
እስኪ አወኩሽ ናኩሽ ይቅር?
በአንድነት ሆኖ መናፍቃንን መዋጋት ሲቻል፤ለምን ክፍፍል መጣ?
እኔ እንደሚመስለኝ የመናፍቃኖች እንደዚህ አፍጥጦ መንነሳት አንድም ነገር በነርሱ ላይ አይፈረድም ባይ ነኝ፣ ምክንያቱም የእራሳችን አንድ ያለመሆን ክፍተት ስለፈጥረ እነርሱን የበለጠ እንዲጠናከሩ፣ እንዲዳፈሩ ፣ ሰርገው በመግባት ክፍፍል ለመፍጠር አንዲያስችላቸው ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽዎ አድርጓል (አያያዜን አይተው ጭብጦዬን ቀሙኝ) እንደተባለው ነው።
አሁንም አልመሸም ስለእግዚአብሔር ብለን፤ እግዚአብሒርን ጋሻ ና ጦር ፤እመቤታችንን መከታ አድርገን በአንድነት ሆ ብለን እንነሳ ፣ አበው አባቶቻች፣ነቢያት፣ሰማዕታት ሕይወታቸውን የሰውላትን ፣የተወገሩላትን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት እና የማምለኪያ ቤታችንን ከተኩላዎች እናስጥል??? እርስ በእርስ መተቻቸቱ ይቅር፣ስለ እግዚአብሔር ፍቅር! የመናፍቃን መሳለቂያና መጫወቻ አንሁን!
በተለይ እናንተ ምሁራንኖች፣ ወንጌሉን ጠንቅቃችሁ የተማራችሁ፣አይናችሁ ለምን ተከደነ??
የወንጌል ገበሬዎች፣ወደኋላ ነው እንዴ እያረሳችሁ ያላችሁት? ማሳው ተበላሸ እኮ!

Anonymous said...

"...መረጃዎችን ስታድርስ የቆየችው ደጀ ሰላም ዘግይቶም ቢሆን ከሚደረገው ከዚህ እንቅስቃሴ ጎን እንደምትቆም እያረጋገጠች ወደፊት የሰነዱን ይዘቶች እንዳመቺነቱ በመከፋፈል ለማስነበብ ጥረት ታደርጋለች፡፡"

ሰነዱን፡እንዳለ፡ሳይውል፡ሳያድር፡በፒዲኤፍ፡ማቅ
ረብ፡እጅጉን፡አስፈላጊና፡ጠቃሚ፡ነው።እያንዳንዱ፡
የተዋሕዶ፡ምዕመን፡ሊያውቀው፡የሚገባ፡ጉዳይ፡ነው
ና፡አላንዳች፡የቀጠሮ፡ማብዛት፡ጽሑፉ፡እንዲነበብ፡
ቢደረግ፡ይበጃል!

የጠላትን፡ፈጣንነት፡እኛም፡ፈጥነን፡እንድንመክ
ት፡መረጃዎችን፡በፍጥነት፡ማቅረብ፡ታላቅ፡አገልግ
ሎት፡ነው።ስለዚህም፡መረጃው፡እንዳለ፡በፒዲኤፍ፡
ተሰርቶ፡በፍጥነት፡እንድናገኘው፡ቢደረግ፡ደጀ፡ሰላ
ምንም፡ያስመሰግናል።

እግዚአብሔር፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ይጠብቅል
ን!የአውሬው፡አገልጋዮች፡ቤተ፡ክርስቲያናችን፡ላ
ይ፡የሚያደርጉትን፡የተቀናጀ፡ወረርሺኝና፡ጥቃት፡
በንቃትና፡በአንድነት፡እንድንመክት፡እመ፡ብርሃ
ን፡ትርዳን!አሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

haile said...

እንደምትሉት ከሆነ ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው 1980ዎቹ ዉሰጥ ነው.
20 ኣመት ሙሉ ባውደምህረታችን ሲያስተምሩ 20 ኣመት ሙሉ ባደባባዩ ሲዘምሩ
እስከ ዛሬ የት ነበራችሁ? እነዚህ ሰዎች እግራቸዉን ኣደላድለው ተቀምጠዋል፡፡ ስፍራዉን ሁሉ ተቆጣጥረውታል፡፡ የምእምኑ ሁሉ ጆሮ የነሱን ድምጽ ከለመደ ቆይቷል፡፡ ኣሁን ከማንም በላይ ቤተኞች እነሱ ናቸው፡፡ ህዝብ ሁሉ እነሱ መጡ ሲባል የ ቤተ ክርስትያን ደጅ ይረግጣል፡፡ እነሱ ሲሄዱ ይሄድና እነሱ ሲመጡ ባመቱ ብቅ ላል፡፡ ይህ ኣዲስ ነገር ከየት መጣ. ህዝብ ለምን በዛላቸው፡፡ምንድነው ሚሰጥሩ
እውነት እነ በጋሻው “ተሃድሶ” ከሆኑ ይሄ ሁላ ህዝብ ታድሶ ነው ማለት ነው?
ስለዚህ የታደሰው ካልታደሰው በቁጥር ይበዛል ማለት ነው፡፡ ኣንድ መካድ የለለብን ትልቅ ሃቅ ኣለ፡፡ በዚህ ግዜ ስብከትናሰባክያን ፡ምዝሙርና ዘማርያን በዘተዋል ፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚው ‹ምእመኑ› በዛ ልክ በዝቷል ማለት ነው፡፡ ይሄ ሁላ ህዝብ በስብከታቸው ተለውጦ በ ዝማሬያቸው ታድሶ ይሄ ሁሉ ኣመት እነሱን ተጣብቆ ኑሮ ኣሁን ተለይ ብትሉት ያምናችኋል? ትንሽ የዘገያችሁ ኣይመስላችሁም? እነዚህ ሰዎች ባንድ ወቅት ህዝቡ ፍጹም ከሚያምናቸው እውነተኛ ኦርቶዶክሳዉያን መምህራን ጋር ምድረክ እየተጋሩ፤ማይክ ኣየተቀባበሉ ህዝቡን ኣስተምረዋል፡፡ ህዝቡ እነዚያን ልጠርጥር ቢል እንኳ ለነእነዚህኞቹ ሲል ያምናቸዋል፡፡ ኣሁን በጋሻውን ተሃድሶ ነው ብትሉት ይሄ ህዝብ ኣያምናችሁም፡፡ ቤተክርስትያንን የረገጠውኮ በሱ ስብከት ነው፡፡ ትዝታው መናፍቅ ነው ብትሉት ኣያምናችሁም፡፡ መዘመር የጀመረው በሱ ካሴት ስለሆነ፡፡ በእርግጠኝነት ሁላቺንም‹ የዚህ ብሎግ ባለቤት ጭምር› ቢሆን እነዚህን ሰዎች መጀመርያ በፍፁም ኣልጠረጠርናቸውም፡፡ ኣንድ ምሳሌ፡፡ ‹ሃይልህ ብዙ ሲሆን…› የሚለዉን ስብከት ሁላችንም ኣድምጠነዋል፡፡ ሰባኪው በ እንባ ጭምር ነው ህዝቡን የሰበከው፡፡ ብዙዎቻችሁ ኣብራችሁት ኣላለቀሳችሁም? ያኔ እንባው የዉሸት ነው ብሎ የጠረጠረው ማን ነው፡፡ ማንም!!!! በ ምስሉ ከሚታዩት ምእመንን ሁሉ ተክዘው ነበር፡፡ እነደዉም ኣንዷ ኣብራው ስታለቅስ ትታያለች፡፡ ያቺ ልጅ ታድሳለች ማለት ነው? ያቺን ልጅ በጋሻው መናፍቅ ነው ብትሏት ምን እምትላችሁ ይመስላችኋል? Never!!!!! u r too late!!!

Anonymous said...

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ለሁሉም፡

"ጽሁፌን ታወጡት ይሆን?" ላልከው ወገኔ ለአንተ በመንፈስ ቅዱስ መመራት ማለት በማይታወቅ የድምጽ ጋጋታ እራስን ማታለል(ወይም በስህተት መንፈስ መታለል)። ይህንን ነው፤ ለአንተ በመንፈስ ቅዱስ መመራት ማለት። የድምጽን ጋጋታ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ልሳን አድርጎ ማስተማር ለእኛ ግን በእውነተኛው ጌታ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለምናምን ፈጽሞ ተቀባይነት የለሁም።

እንዲህ "ከባህር የወጣ ሰይጣን ተገረዘ፤ተጠመቀ፤መነኮሰ፤ መንግስተ ሰማያት ገባ፤ የምትል ቤተክርስቲያን.." ብለህ ጽፍክ እኔ ተራ ምእመን ነኝ አንድ ቀንም እንዲህ ያለ ነገር
ከቤተክርስትያኔ አልሰማሁም(አልተማርኩም) as far as I know I don't know from where you get this. So, could you please let me know? could you please provide evidence for your claims?

አንዲህም "ክብር ሁሉ መገኛ ከሆነው አምላክ ጋር እኩል ማድረግ ፍጡርን ማስተካከል" ይንን ከራስ አውጥተ ጻፍክ። ያልገባው ሰው ይጥይቃል እንጂ ሀሰት አይናገርም። እኛስ በፍጡርና በፈጣሪ፡ በአምላክና በኣምላኪ በመካከል ያለውን ልዩነት ከማወቅ አላፈን እናስተምራለን ልባችውን ክፍት ላደርጉ። እኛ የአነተን ቃል ሳይሆን እንዲ የምለውን የጌታ ቃል እንሰማለን "..በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤.." 2ኛ ቆሮ 5-16። አንተ ወደድክም ጠላህም ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ አምልካችን ነው። የእርሱ ቅዱሳን ደግሞ የማስታረቅን ቃል ከእርሱ ተቀብለዋል። እንተ ይህንን ቃል ብትቃወም ለአንተ የመውጊያ ብረት ይብስብሃል።

Jesus Christ is our God, Lords Of Lord Kings Of King. He is The Son Of God, our Saviour.

Anonymous said...

Dear all,
This point is not new for me. and I hope this may not new idea for those christians who really examine thier surroundings.The problem is lack of awareness of the general public or not comfortable to admit the existence of Tehadiso. It was claimed that the word tehadiso does not exit rather it was pecieved as if it was fabricated by MK which is wrong.I have read from 'Hamere Tewahido No. 4 that every thing was known from the beginning. I advice to try to get this book and read for further detailed information about the anti-orthodox movement.I think expected from us first to get adequate information about the movement and act accordingly.
may God give us strength to carry the cross!

Anonymous said...

ጽሁፌን በሚዛናዊነት ያወጡት ይሆን? የሚለውን ጥርጣሬ ወዲያ ጥላችሁ በማውጣታችሁ በእውነት ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። አነዚህ ካቶሊክ፤ ፕሮቴስታንት፤ጄሆቫ፤ መሰረት፤ቃል ቤዛ፤ብርሃን፤ጥምቀት፤ህይወት...ምንትስ ቤተክርስቲያን የሚባሉት ራሳቸው እንደእግዚአብሔር ቃል የማይኖሩና የሞቱ፤ ይልቁንም ከማንም በፊት መታደስ የሚያስፈልጋቸውና የመናፍስት ማደርያ ሆነው ሳሉ ስለመታደስ ሊናገሩ አይችሉም። ቋንቋ ተገለጸልኝ ፤መንፈስ ቅዱስ ወረደልኝ፤እያለ ግን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ሄዶ የሐመር፤የመዠንገር፤የኑዌር፤የአኙዋክ...ህዝብ በሚሰማው ቋንቋ መናገር የማይችል አላጋጭ ስለመታደስ ለመናገር ቢሞክር መልዕክቱ ከራሱ ሳይሆን በስመ ልሳን ከሚያስዋሸው ከሰይጣን መሆኑን መግለጽ አግባብነት አለው።(የሐዋ2-6)(1ኛ ቆሮ14፤16)ቁ 23 መታደስን የሚጠላ የለም። መታደስን የማይፈልግ ሰይጣን ብቻ ነው።ስብራቱን መጠገን፤ጉድፉን ማስወገድ፤ የጠመመውን ማቃናት፤የተወላገደውን ማስተካከል ያልቻለ በራሱ ፍጹም እንደሆነ ያስባልና መቼም ቢሆን ለተቀናቃኝ የተጋለጠ ነው። ካቶሊክን የበጣጠሳትና ለብዙ ብጥስጣሾች መንገድ የሆነው የሉተር በፐርጋቶሪና ኢንደሊጀንስ ጥያቄዎች በአግባቡ እንደመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ምላሽ መስጠት ባለመቻሏ ነው። ጳውሎስም «የልቡናችሁን እውቀት አድሱ» ኤፌ4፤23 በማለት ከክርስቶስ በተማርነው እንድንኖር መታደስ በሚያስፈልግ ወቅት የግድ መሆኑን ይነግራል። ከተማርከው ውጭ ከሆንክ ጎብጠሃል ወይም ተጣመሃል እና በዕውቀት ልትቃና ይገባል ማለቱ እንጂ ሃይማኖት ቀይር ማለቱ አይደለም። መታደስ የሚለውን ቃል የሚጠሉ ሰዎች መታደስ ለምና እንዴት የሚለውን የማያውቁ ብቻ ሳይሆን ለመስማት የማይፈልጉ ጅሎች ናቸው። ካቶሊክ ለቅስና ማዕረግ ጋብቻን ትከለክላለች፤ ግን ይህንን ከየት አገኘችው? መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ጢሞ3፤1-3 ላይ የአንዲት ሴት ባል ይሁን ይላል። እንግዲህ ከክርስቶስ ያልተገኘ እውቀት ማለት ይህ ነው። መታደስ፤መለወጥ አለባቸው። ባለመሆኑም ነው ህጻናትን ሳይቀር ግብረ ሰዶም እየፈጸሙ የሚኖሩት። ካቶሊክ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳባትን አባል አትቀበለውም ብቻ ሳይሆን ከመግደል አትመለስም። ምክንያቱም ከሷ ወዲያ ፍጹም እንደሌለ ታስባለችና ነው። ፕሮቴስታንት ስለልሳን ብዙ ይላል። እሱ ልሳን የሚናገረው በጉባዔው መንፈስ ቅዱስ ስላለ ነው ይላል። ይሁን እንጂ የፕሮቴስታንት ልሳን የትኛውንም ክርስትና ያልተሰበከውን ህዝብ ቋንቋ በመግለጽ አስተምሮ መለወጥ አይችልም። ጳውሎስም አብደዋል እንደሚባሉና የሚሰማው ካላወቀ እንዴት «አሜን» ይላል? ሲል በልሳን ዙሪያ የተናገረውን ወደጎን በመተው የዕብዶች ጉባዔ ሆነው ቀርተዋል። ሌሎቹም የከበሬታ ወንበር ሲሹና እጅጌያቸውን አስረዝመው ባረኩሽ፤ ቀደስኩሽ ሲሉ ቤተክርስቲያኒቱን አዳከሙ። በላተኞች እንጂ አምራቾች አይደሉም። ቅጥረኞች እንጂ ሰራተኞች አይደሉም። ማንም ምዕመንና ምዕመናት ሳይመርጧቸው እራሳቸው ባቋቋሙት ጉባዔ እየተመራረጡ ቤተክርስቲያኒቱን በየድርሻቸው ተከፋፍለው ይዘዋታል። የጠመመውን አያቃኑም፤የተወላገደውን አያስተካክሉም።የጎበጠውን አያድሱም። ስንት ገመናና ጉድ እያላቸው ብጹዕና ቅዱስ ይባላሉ። መታደስ መለወጥ የሚያስፈልጋቸው ሆነው ሳሉ ከዚህ ጉድ ጀርባ የቤተክርስቲያኒቱን ተግዳሮት ለመፍታት ይቅርና ተግዳሮት ስለመኖሩም አያውቁም፤ ወይም እነሱን እስከሞቃቸው ምን ገዷቸው!! ቤተክርስቲያኒቱ የታመቀ እውቀትና አስተምህሮ እያላት ማን እንደጻፈውና እንዳስገባው የማይታወቅ፤ ከነበራት አስተምህሮና ከወንጌል ቃል በተጻራሪው የሚናገረውን ልፋፈ ጽድቅና መርበብተ ሰሎሞን ዓይነት ገድልና ድርሳን ማረም፤ማስተካከል ማቃናት፤ እንደክህደት ይቆጠራል። የበረከት ሀገር የነበረችው የስደት፤ የድርቅና የረሃብ ሀገር ሆና በዓለም ላይ መጠራቷ እግዚአብሔርን ያሳዘነ የክብርና የውዳሴ ማጋራት አባዜ ስላለን እንጂ እኛ ሀገረ እግዚአብሔር ነን ብለን ራሳችንን ስላሞካሸን አይደለም። ምንም ነገር በሌለበት ምድር እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ወተትና ማር የምታፈሰውን ሀገር እሰጣችኋለሁ ያለው በቃሉ መኖር ለፈለጉትና ሁሉን ማድረግ ስለሚችል ማሳያ ነው። የተክልዬ ተቅማጥ እንደክርስቶስ ስቅለት መቆጠሩን(ገድለ ተ/ሃይማኖት ምዕ54)የምታስተምርና ምትክ፤አቻና ወሰን የሌለውን የክርስቶስን የማዳን ስራ ወደ ምድራዊው የሰው ልጅ ጠባይዓት የምታወርድ ቤተክርስቲያን ባለችበት ሁኔታ ረሃብ፣ጦርነት፤ስደትና ውርደት ይጠፋል ማለት ዘበት ነው። ይህን ቃል ከወንጌል ቃል ውጪ ነው፤ቀደምት አባቶች ያላስተማሩት የክህደት ስርዋጽ ነው ብሎ መናገር ተሃድሶ ያሰኛል ፤ያስወግዛል፤ ከቤተክርስቲያን ያስባርራል። የቆየ ነገር ሁሉ ውሸትም ቢሆን እውነት ይባላል?ውሸትን ሁሉ በመቆየቱ ብቻ እውነት ለማስመሰል የጥቅስ ድጋፍ ፍለጋ ከመባዘን ይልቅ ከወንጌል ቃል የተለየውን ሁሉ ጳውሎስ እንዳለው በዕውቀት መታደስ ይገባዋል፤ (ኤፌ4፤20-21) ያልተጻፈ መነበቡ ይቁም፤ በስመ ትርጉም ክህደት ይቅር ለሚል የሚሰጠው ምላሽ ነገሩን ከመመርመር ይልቅ ስድብና ስደት ነው። እስኪ አንዱን ብቻ ለማሳያ ላቅርብ። በ2000 ዓ/ምቤተክርስቲያኒቱ ካሳተመችው መጽሐፍ ቅዱስ ላስነብብ።(ዮሐ1፤47-49) «ናትናኤልም በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይችላልን?» አለው፤ ፊልጶስም መጥተህ እይ» አለው። ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደእርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ«እነሆ በልቡ ተንኮል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው» አለ ፤የሚል ተጽፎ ይገኛል። እንግዲህ በልቡ ተንኮል የሌለበት ንጹህ እስራኤላዊ መሆኑን የሰማይና የምድር ንጉሥ ክርስቶስ ከመሰከረው ውጭ ኃጢአት የሚስማማው የሰው ልጅ የተለየ ትርጉም ይሰጥ ዘንድ እሱ ለጥፋት የተዘጋጀ መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር ክርስቶስ ያስቀረውን ለመግለጥ ወይም ክርስቶስ ለመናገር ያልፈለገው ኖሮ ሌላው በተሻለ ለመናገር የበለጠ ሆኖ መገኘቱን አያሳይም። ይህንን ከላይ በክርስቶስ ስለ ናትናኤል ንጹህነት የተመሰከረውን ቃል አንድምታ በተባለ ትርጉም ላይ እንዲህ የሚል ተጽፎ ይገኛል። «ከበለስ በታች ሳለህ አይቼሃለሁ ማለቱ፤ ከበለስ በታች የጎልማሳ ሚስት ስትደፍር አይቼሃለሁ ማለቱ ነው፤ አንድም ሰው ገድለህ ከበለስ በታች ስትቀብር አይቼሃለሁ ማለቱ ነው ወዘተ እያለ ይተርካል። ክርስቶስ ኃጢአት የሌለበት ንጹህ እስራኤላዊ ብሎ የተናገረው ከማንም ትርጉም ቃል በላይ በቂ ሁኖ ሳለ በተቃራኒው ኃጢአተኛ ነው ብሎ መናገር እውቀት ሳይሆን እብደት ነው። ክርስቶስን ውሸተኛ ነህ ማለት ነው ወይም ክርስቶስ ያስቀረውን እኔ እገልጠዋለሁ ብሎ መመጻደቅ ነው። የሌለ ነገርን ለማግኘት መቆፈር ምን ይባላል? ለማሳመር ኮስሞቲክ ቃላትን ቢቀባቡ እውነትን አይተካም። በዚህ ሃሳብ ላይ ድርቅ ብሎ መገኘትም የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ሆኖ መታየት የልብ ዕውርነት ነው። ስርዋጽና ሽንቁር ቃላት ተሰግስገው ከገቡበት ቦታ በዕውቀትና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚያርሙ፤ የሚያስተካክሉ መሪዎች በሌሉበት ዘመን ይህ አይጠበቅም። ጊዜው ሲደርስ ሰዎች በፈቃዳቸው ለመስራት ያልፈለጉትን ስራ እግዚአብሔር በአንድም አለያም በሌላ መንገድ ይሰራዋል። ችግሩ ግን እግዚአብሔር ሲሰራው ላልታዘዙበት ሁሉ ቅጣትን ያስከትላልና ይህ ያስፈራል። ከወዲሁ በልባችን መታደስ እንለወጥ። ለውጥ ሂደት ነው። የግድ የሚሆን። መልካም ጊዜ!!!

Anonymous said...

ጽሁፌን በሚዛናዊነት ያወጡት ይሆን?... የሚለዉ ሰዉ የሚጽፈዉ ጽሁፍ ለእኔ አልተስማማኝመም .... ደጄ-ሰላሞች ምን ትላላችህ ???

be

Anonymous said...

በመጀመሪያ ሰላምታዪ ለሁሉም ይድረስ
አጭር መልስ ለመመለስ ብቻ ነው ክበለስ በታች አየሁህ ያለው በትርጉሙ ላይ ጌታ በተወለደበት ዘመን እሱም ህጻን ነበረና በነሱ የትውልድ ዘመን የነበረው ሄሮድስ እንዳይገለው እናቱ ክበለስ በታች ደብቃው ነበረና የባህርይ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ያላወቀው ምስጢሩን ነገረውና ተክታዩ አደረገው ታሪኩ ይሄ ሆኖ አንተ ግን ሌላ አተትክ ስታነብ ሙሉ ነገር በማንበብ ሌሎችን አታሳስት ለማንኛውም ተመለስ

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ። አሜን!!

ወገኖቼ በዚህ አይነት ሁኔታ ማን ይታመናል? አንዳችን ካንዳችን ጋር እኮ በአንድ ቤት በመተማመን ሳይሆን በጥርጣሬ ዓይን መተያየት ሊኖርብን ነው ማለት ነው። ደግሞ እኮ በዋነኛነት ችግሩን ያባባሰው የሚመለከታቸው ሰዎች ቸልተኝነት ነው። ሐተታ ሳላበዛ አንድ ዓመት ያልሞላው ነገር በምሳሌነት ላንሳ፡ እኔ መመላለስ በማዘወትርበት ደብር አንዱ ቄስ ይቀድሳሉ፣ያስተምራሉ፣ ያሳልማሉ፣ በአጠቃላይ ቄስ የሚያከናውነውን ተግባር ያከናውናሉ። ነገር ግን ለካስ እኚ ቄስ ተሐድሶ ነበሩና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ለደብሩ አስተዳዳሪ ጉዳዩን ነግረዋቸው ችላ ብለውት ሦሥት/3/ ወር ያመላልሷቸዋል። ከዚህ በኋላ አንድ ቀን ከቅዳሴ ተከትሎ አስተዳዳሪው ዛሬ ነገ በማለት ጉዳዩን ችላ ሰላሉት መዕመናኑ ማወቅ አለበት ሲባል አስተዳዳሪው በጭራሽ በማለት ሲሟገቱ ቆይተው ጉዳዩ ታወቀ።ከዚያም አሉ ከተባሉት ተጨባጭ ማስረጃወች በተጨማሪ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ በእለቱ ከመዕመናን ይመረጥና ለ15 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶ ሰው ይበተናል። ቀኑ ደረሰና ኮሚቴዎች ብዙ ማስረጃ እንዳገኙ በመግለፅ ሪፖርት ሊያቀርቡ ሲሰናዱ አሁንም አስተዳዳሪውና ፀሐፊው ረብሻ ፈጠሩ። ሆኖም የሰው፣ የድምፅና የፅሑፍ ማስረጃ እንደተገኘ /ዝርዝሩ ቢፃፍ ብዙና የሚገርም ነው ነገር ግን ሰው እንዳላሰለች ላሳጥረው ብዬ ነው።/ ለመዕመናኑ አስረዱ። ኮሚቴዎቹ ማስረጃዎቹን በእጃቸው ላይ ይዘው አሁንም አስተዳዳሪው እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል ይህ ሰው ንፁህ ነው በማለት ወገንተኝነት በማሳየት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ መታገስ ያልቻሉ ሰዎች አስተዳዳሪው ትክክል እንዳልሆኑ ነግረዋቸው ረጋ አሉ። በመጨረሻም ኮሚቴው ባዘጋጀው ሪፖርት ላይ የሚፈርም ጠፍቶ በመዕመናን ትግል እኚህ ሰው ከዚህ ደብር ተነስተው ያለምንም ምክርና ተግሳፅ ሌላ ደብር ተመድበው በመስራት ላይ ይገኛሉ። እኛን ኦርቶዶክሳውያንን በዋናነት እያጠቃንና ሐይማኖታችንን እያስደፈረ ያለው ጉዳይ ገንዘብ ወዳድነታችን ነው። እነዚ ሰይጣኖች በየቦታው እንዳሉ ሁሉ በየብሎጉም እኛን መስለው ሲዘባርቁ አስተውለናል። ለምሳሌ በዚህች ብሎግ እንኳን ዘብሔረ ቡልጋና ሉላ የተባሉትን ስም በመቀያየርና ያለ ስም የሚፅፉትንም መጥቀስ ይቻላል። ሌላው ደጀ ሰላሞች ጉዳዩ ወሬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር እናንተም አጋርነታችሁ እንዲቀጥል ተዋንያኖቹም በግልፅ ታውቀው ትግላችን በፍጥነት መጀመር አለበት። በዚህ ብሎግ ላይ እኛ የምናነበውንና የምናውቀውን የማያውቁ ሰዎች በርካታ ስለሆኑ እያባዛን እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳውያን ስለ ሐይማኖቱ ያለውን ስውር ሴራ እንዲያውቅ ብናደርግ መልካም ነው።

የእመቤታችን አማላጅነት የእግዝአብሔር ቸርነት አይለየን። አሜን!!
መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

The one who write about abune Teklehaymanot

Before you conclude the concept of the "Gedel" as you are saying, it is better if you open your mind and listen from church fathers about its meaning. Do you remember the history written on "yHawariat sera 8:30-40". "ethiopiawiw jandereba" was reading Esayasis part and when philipos came to him, he asked filipos to explain/translate for him. so all the "Gedlat" or "Bible" part requires interpretation by church fathers. It is the same in case of Natnaiel. so u should take time to listen the teachings of the church sitting under the foot of your fathers. Ingeneral the issue of "Tehadeso" is not relevant for our church in any context.
We, christians should go through "Neseha" to get new life and to be forgiven.

May God keep our church

Anonymous said...

የተዋህዶ ልጆች በሙሉ፦ ግድ የለም ነገሮችን ረጋ ብለን በክርስትና ዓይን እንመለከታቸው። እውነት ማሻነፏ አይቀርም። የአንዳንዶቻችን ሁኔታ እኮ ከአንዳንድ አክራሪ ሙስሊሞች የማይሻል እኮ ነው። ቦምብ ወገባችን ላይ ታጥቀን እራሳችንን በሃይማኖት ስም ለማፈንዳት ወደ ሁዋላ የምንልም አይመስልም። እንደምታውቁት ይሄ ክርስትና አይደለም። ነፍሳቸውን ይማርና ታላቁ ሐዋርያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በታሪክ መጽሐፋቸው ላይ ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው ብለዋል። በአፍ ሲናገሩት ቀላይ ይመስላል ግን ይሄ አባባል ክርስትናን በጥልቁ ከመረዳት የመነጨ አባባል ነው። ክርስትና ወንድማችንን ለየት ባለ አመለካከቱ ብቻ ጠላት ማድረግ አይደለም። ይሄ ነገር መጽሐፍ ቅዱሳይ አይመስልም ሊስተካከል ይገባዋል ማለት እንዴት ሆኖ ነው ስቅላት/መለየት/መናፍቅነት/ከሀዲነት የሚያስፈርድበት። ይሄ ክርስትና ነው? እንኳንና ጥቃቅን ነገሮችን ይቅርና አባቶቻችን አርዮስ የተባለውን መናፍቅ በፍቅር/በማስተማር/በመከራከር ለመመለስ እጅግ ጥረው አሻፈረኝ በማለቱ ከቤተክርስቲያን እንደተለየ ታሪክ ይነገረናል። ዛሬ ዛሬ ግን እንኳን አምላክን ፍጡር ነው ማለት ይቅርና ጥያቄ መጠየቅ ሁሉ የሚያስደበድብ/መናፍቅ የሚያደርግ ሆኖአል። አካሄዳችን ሁሉ ያስፈራል። ክርስቲያን መሆናችንንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፤ ፍቋር በውስጣችን አይንጸባርቅምና። የተሐድሶ ወጥመድ፥ ይፋ ሆነ! የጦርነት መልዕክት። ጣሊያን መልሶ አገራችን ውስጥ የገባ አስመሰላችሁት እኮ። ደግሞ በጣም ዘየጋችሁ ራሱን ተገኘ የተባለውን ሰነድ ሳትቀንሱ ሳትጨምሩ አስነብቡን እንጂ። የኔ እናንተ የምትሉትና ሰነዱ የሚያወራው የሰማይና የምድር ያህለ ነው የሚለያየው። ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

Thank you, Dejeselamwiyan for the info. but my only question is? where were maheber kidusan? when all this happen? are they completely forgoten for what they stand for? the gardian of "tewahedo" ? stil not too let. we need to work hard and fight back those devil messangers(Tehadiso). "YEKIDUSAN AMLAK ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDON YITEBIQAT" AMEN.

Anonymous said...

"ጽሁፌን በሚዛናዊነት ያወጡት ይሆን?" lemetelew sew.

Letehadiso ewunetegnanet concrete evidence eyakerebk meseloh kehone tesastehal. Yelekes menorachewun lementerater lende ene aynetu masereja honk. ahun yegna teyakeyachen enante yemetelut ewunet new weys wushet yemil ayedelem.teyakeyachen betekeresteyanachenen lekekulen new. yenanten ewunet tedebekachew west lewest sayhone wechi honachew sateferuna sataferu 'wedegna nu' belun. yane yemeyasamen kehone eneketelachehualen...kezih befet eslamem,pentem endeteketelen malet new. beadebabay tehadeso ayedelenem telalachehu... bedebek gin alen alen telalachehu... leke ahun be 'Anonymous' sem endemetekebetaterew malet new. ewenetegna betehonuma balferachew neber...

Anonymous said...

DEJE SELAMAWEYAN, God bless you for exposing ተሐድሶዎች evil plan. It will be extremely important to expose all the documents without any delay. Already you could see how agitated ተሐድሶዎች are. That is why they are trying to solicit your blog. They know this is the best place to manipulate and defuse this burning issue. I know you are trying to be fare but unintentionally you are giving ተሐድሶዎች an access to promote their evil agenda on your blog. Please keep ተሐድሶዎች out of Deje Selam so they don't get anymore chance to destroy our ENAT TEWAHEDO CHURCH.

Anonymous said...

ዻዸ ሰላማዊያን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ይህንን ማወቅ ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚቀጥለውን ዝግዻት በተስፋ እንቀጥላለን፡፡
የእግዚአብሔር አብ በረከት ፣
የእግዚአብሔር ወልዱ ቸርነት፣
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዳስ አንዱነት፣
የእመቤታችን የቅዱስት ዱንግል ማርያም አማላዻነት፣
የቅዳሳን መላእክት ተራዳኢነት፣
የጻዱቃን የሰማዓታት ፀሎት፣
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡

Anonymous said...

i am very sorry 4 what has been happen in our church...we better pray now and you dejeselam and all cristiand should be stonger than ever

Anonymous said...

amlke yesewren ye tinbit meftsemiya kemhone

judith said...

"እስመ አንተ ተአእምር ድካሞ ለሰብ"
"የሰዉን ድካም አንተ ታውቃለህና"
ጌታ ሆይ እንደኛ ቸልተኝነት አይሁን

Anonymous said...

መረጀጃው እኔ እስከማውቀው ድረስ እውነት ነው፤፤
ማ.ቅዱሳንም በተለያዩ መንገድ በሐመር በስምዐ ጽድቅ ስጽፍ እንደነበር በተከታታይ አንብብያለሁ፤፤
በቅርቡ ደግሞ ውኃ የለሌላቸው ምንጮች የሚል ስብከት አድምጭያለሁ ከጥምቀት ወዲህ፡፡
አሁን ግን ስብከተ ወንጌልን በምንችለው አቅም ከነመረጃው ማስፋፋት ይገባናል ብዬ አምናለሁ፡፡

Anonymous said...

This is unbelievable!

Anonymous said...

posting the teachings of "tehadesos" on this blog is not important. some peoples like me will be confused. for example the comment made by some one withregard to "Gedle teklehaymanot" requires a strong reply from our church. I think you will post some teachings or directions about the issue.
May God keep our church

henon said...

አምላከ ቅዱሳን ሀገራችንን ይጠብቅልን ስለ ሀይማኖቱ የሚያነባ ልብ ይስጠን ። ሁላችን ስለ ማንነታችን ስለ ደበቅነው ሚስጢር አስበን የሚሰሩትን የቤተክርስቲያን ልጆቸ ከ መንቀፍ እንታቀብ ። የቅዱሳን ልጆች በርቱ እንግዲህ አሁን ነው መነሳት ። ጆሮ ያለው ይስማ ! በየጊቢ ጉባኤ ስትመረቁ የተቀበላችሁት መስቀል ለጌጥ አደለም አደራ ነው ። በርቱ ተበራቱ ። አይዞን!

Anonymous said...

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!

እባካችሁ በ PDF ዳውንሎድ እናድርገው አውጡት

አመሰግነናለሁ

Anonymous said...

ጽሁፌን በሚዛናዊነት ያወጡት ይሆን? ላልከው ወንድሜ።

በተወስኑት ነጥቦች ላይ ብስማማም። ብዙ ሃሳቦችህ ግን ከመጻፍ ቅዱስ ጋር አይስማማም።

1) ይህንን ሃሳብ አስፍረሃል“..ስንት ገመናና ጉድ እያላቸው ብጹዕና ቅዱስ ይባላሉ።” ወንድሜ ስለሰዎች “ሃጥያት” የምንፈርድ እኔ እና አንተ ማን ነን? ስለሃጥያት መፍረድን በሃይሉ ችሎት ላለው ብንተወው ይሻላል። በሃዋርያት መካከል ይሁዳ እንደነበር ሁሉ በእውነተኛ እባቶች መሃል ሐሰተኛ ቢኖር ለእኔ አይደንቀኝም። ከሃዋርያት መካከል ከሃዲ ስለነበር ሃዋሪያት ለምን ሃዋርያት ይባላሉ እንድማንል ሁሉ። የቤተክርስቲያን አባቶች ለምን ብጹዕ ይባላሉ አይባልም።

2) እንዲህ ብለሃል “...የበረከት ሀገር የነበረችው የስደት፤ የድርቅና የረሃብ ሀገር ሆና በዓለም ላይ መጠራቷ እግዚአብሔርን ያሳዘነ የክብርና... “ እዚጋ ጥያቄ አለኝ ፤ በአንተ አባባል ‘...የበረከት ሀገር የነበረችው..” መቼ ነው? ከመቼስ ጀምሮ ነው “..የስደት፤ የድርቅና የረሃብ ሀገር ሆና በዓለም ላይ መጠራት..” የጀመረችው? ከስንት እመት ጀምሮ ነው”...እግዚአብሔርን ያሳዘነ የክብርና የውዳሴ ማጋራት አባዜ..” የያዘን? እንዚህን ጥያቅዎች እንድትመልስልኝ እፈልጋለው። ያለበልዚያ ምን እንደወነ ሳትውቅ እንደመጣልህ ብቻ እንደጽፈከው እስደዋለው።


3)” ...ወደ ምድራዊው የሰው ልጅ ጠባይዓት የምታወርድ ቤተክርስቲያን ባለችበት ሁኔታ ረሃብ፣ጦርነት፤ስደትና ውርደት ይጠፋል ማለት ዘበት ነው...” ይንን ሳነብ እራሴን እንዲ ብዬ ጠየቅኩ ለምን በቻይና፤ በሳውዲያረቢያ፤ በተባበሩት አረብ ኢመሬት… የጠቀስካቸው ችግሮች የሉም? እስቲ መልስልኝ ወጌኔ፡ ግን ቤተክርስቲያን በነዚህ አገሮች ስለሌለች እንደማትለኝ ተስፍ አደርጋለው። ወገኔ እኔ የምኖርው በሰሜን አሜርካ ነው በቤተክርስትያኖቻቸውም ወነ በምድሪቷ እግዚአብሔርን “የሚያሳዝን” በጣም በጣም ብዙ ነገር እደረጋል። ለምን ረሃብ፣ጦርነት፤ስደትና ውርደት የለም?፡? የኛን አገር የምቀጣ ለላውን ግን የሚተው ፤ እስቲ ወንድሜ ንግረኝ እርሱ ማን ነው? ? ?

3) “... ክርስቶስ ኃጢአት የሌለበት ንጹህ እስራኤላዊ ብሎ የተናገረው ከማንም ትርጉም ቃል በላይ በቂ ሁኖ ሳለ በተቃራኒው ኃጢአተኛ ነው ብሎ መናገር እውቀት ሳይሆን እብደት ነው..” እዚጋ ትርጓሜው ትክክል ነው አይደለም ለማለት እልፈልግም። ነገር ግን የሃስብህ መነሻ ስህተት ፈላጊነት ላይ ያተኮረ ስለውነ እንድ ለማለት እውዳለው። የዛሬ 13 አመት ገደማ በአንድ ስፍራ የክረምት ኮርስ ስወስድ ጽጌ ስጦታው (የፕሮትስታንት አቀንቃኝ) አንተ ከጻፍከው ሃሳብ ጋር አንድ የወነ ቃል ሰምቻለው። ከርሱ ኮርጀሃል ወይም ሁለታችሁም ከአንድ ቦታ ኮርጃችዋል(ከፕሮቴስታን?)።

እስቲ ልጠይቅህ ውንድሜ ቅዱስ መጽሃፍ እንዲ ይላል፤ ናትናኤልን ኢየሱስም መልሶ። ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ “ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው” ምን ማለት ነው?
ስለ ቅዱስ ዳዊት እግዚሃብሄር ሲመሰክርለትም። እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ። ሓዋ13-22 እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የተባለው ቅዱስ ዳዊት መ የኦርዮን ሚስት ጋር የማይገባ ነገር እንዳደርገ ቅዱስ መጽሃፍ ይነግርናል። ሃጥያት የእግዚያብሔር ፈቃድ አይደለም፤ ለምን ዳዊትን ፈቃዴን ሁሉ የሚያደርግ አለው? ናትናኤል ሰው አይደለም እንዴ ? እንደሰው ወድቆ ቢነሳ ምንድነው የሚያስገርመው? ምሳ 24-16 “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፥ ይነሣማል፤” ይህ ጥቅስ መሬት ላይ ሰለመንከባለል ነው እንደማተለኝ ተስፋ አደርጋለው። p

fikir said...

.. አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን አስፈሪም ጭምር ነው፤ ወዴት ነው እየሄድን ያለነው... ምናለ ስለፍቅር ስለ አንድነት ብትሰብኩን፣ ዘላለማዊው ወንጌል አልቆባችሁ ነው? ወይስ ስለ መስቀሉ ፍቅርና ውለታ መነጋገር በቅቶን ነው? ምናለ ህዝበ ክርስቲያኑን ባታደናግሩት... ሌላው ዓለም የትናየት ጥሎን ሄዷል ግና እኛ ዛሬም ከመወጋገዝ ከመለያየት ድንበር ወጥተን የፍቅርን መንገድ ለህዝባችን ልናሳየው አልቻልንም። ከተጫነን ከባድ የድኅነት ቀንበር በባሰ የፍቅር ርሃብተኞች መሆናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ ነው ... ነጋ ጠባ ጆሮአችንን ተንስ፣ ታጠቅ እነ እከሌና እከሊት የሚባሉ መናፍቃን ሰርገው ገብተዋል፣ በፕሮቴስታንት የእምነት ድ/ት የሚታገዝ እራሱን እከሌና እከሌ ብሎ የሚጠራ ድርጅት በህቡእ በመንቀሳቀስ ላይ ነው ወዘተ...በሚል የዋሃን ሰዎቸን በሚያደናገርና በሚያሸብር የመዓት ወሬ ጆራችን እንደት ይደነቁራል...መሆኑ ይሄ መጦመሪያ መድረክ የመንፈሳዊ እውቀት መገበያያ ነው እንጂ የስለላ ድ/ት የዜና ወኪል ነው እንዴ?! ስማችሁና ግብራችሁ አንድ ይሁና!

የሃገሪቱ ህገ መንግስት የእምነት ነጻነትን በግልጽ ባስቀመጠበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነቱ ዜና ምን ሊባል እንደሚችል ባለ አእምሮ ሰው ሊፈርደው ይችላል። መነጋገር፣ ማወራት፣ ለህዝብ ክርስቲያኑም ማስተማር ካለብን ስለ መስቀሉ ቃል እንጂ ስለ ህቡእ ድርጅቶች አይደለም ...መፍራትና መስጋት ያለብን ኃጢያትን፣ ያለንበትን ጉስቁልና፣ የውርደት ህይወትና መለያየታችን እንጂ የህቡእ ድርጅቶች ጉዳይ አይደለም፤ በመጀመሪያ በእውነት ስለእውነት እንናገር እናስተምር...ያን ጊዜ ቃሉ እንደሚል፡ "እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያውጣችኃል" ይላል የዛን ጊዜ ብህቡእ የሚንቀሳቀስ የሚባለው ድ/ት ይቅርና የገሃነም ደጆች እንኳን ሊያናውጡን አይችሉም።

ደጋግሜ እንደታዘብኩት ያለ ፍቅር በሆነ እውቀት እየተከሄደው ያለው ጉዞ ብዙ የዋሃን ሰዎቸን ወዴት ሊያመራቸው እንደሚችል ቆም ብለን ልናሰብ ይገባናል፤ በተደጋጋሚ እንደታየውም ተሃድሶ፣ ጴንጤ፣ ጸረ ማርያም በሚል ተለጣፊ ስም የስድብና የድንጋይ ውርጅብኝ የወረደባቸው ሰዎች አሁን ባለው ሁኔታ እሾህን በእሾህ በሚል የአጸፋ እርምጃ እንደማይወስዱ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ደጀ ሰላምም ሆነ ሌሎች ብሎጎች ፍቅርን፣ መነጋገርን፣ ልዩነቶቻችንን በጨዋ መንገድ ለመፍታት በሚያስችለን መንገድ የምንነጋገርበትን መድረክ ከማመቻቸት ይልቅ ልዩነቶቻችንን የሚያሰፋ ምክንያቶችን አየፈለጋችሁ መቋጫ ወደ ሌለው ጨለማ መንገድ አትውሰዱን፤ በመንፈሳዊም ሆነ በዘመናዊ ትምህርት ብቁ የሆኑ የተማሩ ሰዎች አሉበት ከሚባል ብሎግ ማንበብም ሆነ መነጋገር የምንፈልገው ስለ ፍቅር፣ ስለ እውነት፣ ስለ ሰላም ... እንጂ ስለመለያየት... ስለጥላቻ መሆን የለበትም።
ሰላም!

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን አሜን፡፡ በርቱ

Anonymous said...

To “fakir”

እባክህን አይናቹን ጨፍኑና ላሞኛቹ አትበለን። እኛን አሳፋሪ እያለከን… ጠበቃ የቆምክላቸው የራሳችን ቤት መጥተው “..ከባህር የወጣ ሰይጣን ተገረዘ፤ተጠመቀ፤መነኮሰ፤ መንግስተ ሰማያት ገባ፤ የምትል ቤተክርስቲያን.." እያሉ፤ ቤተክርስቲያ የማታስተምርውን፤ እያሉ ስሟን በሃሰት ያጠፋሉ። ይህ ለአንተ የእምነት ነጻነትን ነው( for us this is insulting)። ስለእምነት ነጻነት ከመናገርህ በፊት ምን ማለት እንደወነ ልትማር ይስፈልግሃል።

With Love

Anonymous said...

ቃለ ህይወት ያሰማልን።

bemnet said...

God bless you.

Anonymous said...

እጅግ ወቅታዌ የሆነ መረጃ ነው። አምላክ ቤተክርስቲያን
ንና ምእምኑን ይጠብቅ አሜን!

Anonymous said...

EMEBETE MARIYAM LE ETHIOPIAN BETESTESH KAL MESERET EGZIABHER MISTRUN YEGLETSELEN
LEHULUM ETHIOPYAWI YEKER YEBELEN AMEN

Anonymous said...

በእውነቱ ከሆነ ደጀሰላምን ላመስግን እወዳለሁ ምክንያቱም ይህንን ወቅታዊ የቤትክርስቲያን ፈተና ተረድተን እኛን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን እንድንነቃ ስላደረጋችሁን ።ስለዚህ ወገኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ሆይ እየተደርገ ባለው ነገር እና ለማድረግ በታሰበው ነገር ሳንደንግጥ እና ግራ ሳንገባ እያንዳንዳችን ትንሽ የምንላትን ሥራ በመስራት ከእግዚአብህእር ዘንድ ዋጋ የምናገኝበት ሰዓት አሁን መሆኑን ተርድተን መንሳት አለብን ። እንደኔ ሃሳብ እያንዳንዳችን ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች ጥቂቱን ለማለት እፈለጋልሁ ።
፩ኛ እያንዳንድቺን መምህር ንሰሃችን ጋር በመገናኝት ንሰህ በመግባት ፅሎት ማድረግ
፪ኛ ሌላ እካል ይህንን ይሰራዋል ከሚል የጤባቂነት መንፈስ መላቀቅ
፫ኛ በአቅም ሊሰራ የሚችለውን ስራ ለመስራት እራስን ማዘጋጀት ፬ኛ ታማኝ እና ቁርጠኛ የቤት ክርስቲያን ልጅ መሆንን ማሳየት (በተግባር)

solgeta said...

በእውነቱ ከሆነ ደጀሰላምን ላመስግን እወዳለሁ ምክንያቱም ይህንን ወቅታዊ የቤትክርስቲያን ፈተና ተረድተን እኛን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን እንድንነቃ ስላደረጋችሁን ።ስለዚህ ወገኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ሆይ እየተደርገ ባለው ነገር እና ለማድረግ በታሰበው ነገር ሳንደንግጥ እና ግራ ሳንገባ እያንዳንዳችን ትንሽ የምንላትን ሥራ በመስራት ከእግዚአብህእር ዘንድ ዋጋ የምናገኝበት ሰዓት አሁን መሆኑን ተርድተን መንሳት አለብን ።
እንደኔ ሃሳብ እያንዳንዳችን ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች ጥቂቱን ለማለት እፈለጋልሁ ።፩ኛ እያንዳንድቺን መምህር ንሰሃችን ጋር በመገናኝት ንሰህ በመግባት ፅሎት ማድረግ
፪ኛ ሌላ እካል ይህንን ይሰራዋል ከሚል የጤባቂነት መንፈስ መላቀቅ
፫ኛ በአቅም ሊሰራ የሚችለውን ስራ ለመስራት እራስን ማዘጋጀት
፬ኛ ታማኝ እና ቁርጠኛ የቤት ክርስቲያን ልጅ መሆንን ማሳየት (በተግባር

ያለው ተፈራ said...

February 10, 2011 ከተሰጡት አስተያየት የመጨረሻው አስተያየት ሰጪ
መነጋገር፣ ማወራት፣ ለህዝብ ክርስቲያኑም ማስተማር ካለብን ስለ መስቀሉ ቃል እንጂ ስለ ህቡእ ድርጅቶች አይደለም ብሎአል ይህ አሰተያየት ሰጪ በየዋህነት አልያም የተሃድሶ አቀንነቃኝ በመሆን የሰጠው አስተየት መሆን አለበት፡፡
ወንድሜ ህቡእ ድርጅት የሚለው ከዚህ በፊት ነበር፡፡ አሁን ግን በተደራጀና በግልፅ ቤተ ክርስቲያንን እየገዘገዙ ስለሆነ ከአሁን በሁዋላ ህቡእ ድርጅት የሚለውን እነሱና መሰሎቻቸው ቢጠቀሙበት እንጂ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ አይቀበለውም፡፡ ምእመኑን ማደናገር ነው ላልከው እውንቱን ሲነገረው የሚደናገር ካል ምንም ማድገር አይቻልም እውነት ነው ከማለት በስተቀር፡፡
ሌላው ደግሞ የሃገሪቱ ህገ መንግስት የእምነት ነጻነትን በግልጽ ባስቀመጠበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነቱ ዜና ምን ሊባል ብለሃል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የምታመልከው አምላክ የነጻነት አምላክ ስለሆነ እርሱዋም ማንንም የለፈቃዱ እንዲያምን አታደርም፡፡ አሁን እየተከራከርክላቸው ያለኸውም ድርጅቶችና ግለሰቦችም አንተ እነዳልከው የፈለጉትን ማመን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተመሳስሎ ገብቶ በቤቱዋ እየኖሩ ቤቱዋን ማፈረስ አይቻልም ከላይ በጠቀስከው ህግም ወንጀል ነው፡፡ የሚምኑትን በይፋ ይሄንን ነው የማምነው ብለው መለየትና መንነቀሳቀስ አለባቸው፡፡ ወንድሜ ይህንን ሃሳብ የስጠኌ በየዋህነት ከሆነ ጉዳዩን በጥልቅ መርምር፡፡ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንደሚባለው ከሆነም እግዚአብሄር ማሰተዋሉን ይስጥህ ይስጠን!!! አሜን፡፡

The Architect said...

ለከርሞ ምኞቴ
መሠረታዊው ነገር እኮ በወተት (በመጀመሪያ) ስማቸው ተሃድሶዎች የሚባሉትም ሆኑ በማጣርያ (በመጨረሻ) ስማቸው ፕሮቴስታንቶች የሚያምኑበትን እና ልክ ነው የሚሉትን እምነት እና ሃሳብ በፈለጉት እና በሚመቻቸው መንገድ በራሳቸው የእምነት አደባባይ (ካላቸው) ቢያራምዱ መብታቸው ነው፡፡ እግዚአብሔርም ለሰይጣን ሳይቀር የሰጠው ነጻ መብት አላቸው፡፡ ይህንን መንግስትም እኛም ልናከብርላቸው ይገባናል፡፡ ተገቢም ነው፡፡
ስህተቱ የሚጀምረው ግን በሰው ቤተእምነት በግልጽ እና በስውር እየገቡ የምታምኑትን እንተርጉምላችሁ ይሄና ያ ስህተት አለባችሁ እያሉ መዘባረቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ተሳስታችኋልና እናርማችሁ፣ እናድሳችሁ ማለት ኦርቶዶክሳውያንን መናቅና መስደብ ብቻ ሳይሆን ማዋረድም ጭምር ነው፡፡ በነጻነት ሰበብ የሚደረግን ብልጣብልጥ ዝርፊያ እና አዋረጅ ስድብ የምንታገስበት አንዳች ምክንያት የለም፡፡ ትናንት ሁለት ጥቅስ የሰማ ሁሉ ጥንታዊት እና ሐዋርያዊት የሆነች የሚሊዮኖች ድንኳን ቅድሰት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሰውን ሳያፍሩ እግዚአብሔርንም ሳይፈሩ በአደባበይ መዝለፍ ለእኔ ከትዕግስት በላይ ነው፡፡
ደግሞስ መቆርቆራቸው እውነት ለወንጌል መስፋፋት ከሆነ ምነው ስንት ያላመኑ እስማኤላውያን እና ዓለማውያኑ ዙሪያ ገባውን ሞልተው ተርፈው የለምን? ክርስቶስ በወርቀ ደሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን ላይ መዝመት እና መረባረብ ለምን አስፈለገ? ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ቀጥቅጥ መዝራዕቱ ለእኩይ ወለእቡይ” (እኩይ እና እቡይ የሁነውን ክንዱን ቀጥቅጠው) ያለውን ያላነበብን መሰላችሁ?
የመጨረሻ ማስጠንቀቂያችን!!! አልደረስንባችሁም አትድረሱብን! አልተስማማንም፣ አልተመቸንም፣ የምትሉ ካላችሁ ጀሌዎቻችሁን ሰብስባችሁ ውልቅ! ከአሁን በኋላ የምናመልከውን ስለምናውቅ እንነገራችሁ፣ እናርማችሁ፣ እናድሳቸሁ… የምትሉ ውርድ ከራሳችሁ!
ለኦረቶዶክሳውያን ማኅበራት እና አገልጋዮች! የምን መንቦቅቦቅ ነው! ማነው እናንተን በክርስቶስ ደም ተደራዳሪ እና አዛኝ ያደረጋችሁ! ከፈራችሁ እናንተው ተመለሱ፡፡ እኛ ግን ቤታችንን ለመጠበቅ አናንስምና በማይጠቅም ማኅበርተኝነት ትጥቅ አታስፈቱን!

Anonymous said...

How the so called "ዘክርስቶስ" is invisble person! I am surprised on his aresto with little poison.

Tadiewos said...

We should not go according to the strategy of the protestants,ie creating war among us and then subdue the church.

"ይኸው ባለ 50 ገጽ ሰነድ ሁኔታው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በእጅጉ ከሚያሳስብበት ደረጃ ላይ በመድረሱ በሚመለከታቸው አካላት መካከል የተሐድሶ ኑፋቄን ምንነት እና የሚያስከትለውን አደጋ ተረድቶ የጋራ ግንዛቤ ከመያዝ አኳያ እና መወሰድ በሚገባቸው ርምጃዎች ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶች...."

We must patiently formulate better strategy than the protestants.

The tekilay betekihnet has to invite both secular and church scholars for good strategy and implmentation.

We readers and stockholders also find different mechanisms than being emotional comment giver.

Anonymous said...

"The one who begins his writng by the word "Guys" tries to seem some wht follower of EOTC but his content indicates who he is. There nothing to be corrected from the EOTC teachings. The books are written by saints driven by holly sprite. Their is no any "debtera" book in EOTC. If you are saying their are debtera books, you dont know EOTC. so better to ask first about the churches books. and if you are an EOTC follower, the church didnt tought you to open your mouth for insult. "Aweraw bekidusan lay afun yekefetal" endetebale k aweraw wegen kalihoonk beker ysideb kal mesenizer baletegebahi niber."

elsa said...

በጣም ይገርማል ቤ/ክ አሁንም በውስጥ ጠላቶች መጠቃቷ! ደጀሰላሞች በርቱ ለቤ/ክ ይህ ወቅታዊና አስፈላጊ ነገር ነው የዚህ ፁህፍ ተቃዋሚዎች እባካችሁ የትላልቆቹ ተኩላዎቸ ይበቃል!! እስቲ ለቀቅ አድርጓት ምን ታድርጋችሁ የእናት ጡት ነካሽ ባሆኑ ምን አለ !ልብ ይስጠን!!

Anonymous said...

በዉኑ ለእግዚአብሄር የሚሳነዉ ነገር አለን? ለዚህ ስዉር ሴራ የኝን ድርሻ እንወጣ ከፍርድ ለመዳን ይች በቤተ/ክር/ን እንደሆነች በክርስቶስ ደም የተመሰረተቸች በመሆነ ምንም አትሆንም፡፡ በሉ የአባቶቻችን ፀሎት በቤተ ክ/ርስቲየያንን ይጠብቅልን፡፡ አንተነህ ነኝ ከባህር ዳር

Anonymous said...

Hello , Brothers Pls don'n be troubled for God of Israel is watching all over the wold. It is my sincer advise not to externalized your problems.The origin is human sinful nature and our very hypocrite way of living.I wish all side to wake up to live the Truth ...

Yishak said...

Thanks a lot! Although I'm too late I want to send this comment to you and others with you. You should not frustrate by such kinds of people, associations, and the likes. Because you are responsible to shield the people from the calves as God said. And finally you will be winners, too.
God and His Beloved Mother blessed us
Yishak from MekelleThanks

Anonymous said...

የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሰነዱን አስመልክቶ ጥልቅውውይይት ካደረገ በኋላ በብፁዕ አባታችን አቡነ ቀውስጦስና በክቡር ንቡረዕድ መሪነት ስጋቱን ለፓትርያሪኩ ገልጿል፡፡ ይህ አይነትን አርምጃ በየ አህጉረስብከቱ መውሰድካልተቻለ እነ አሰግድ ቤተ ክረስቲያኒቱን አሳልፈውመስጠታቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡

Anonymous said...

ደጀሰላሞች መረጃዉን ይፋ ስላደረጋችሁት ምስጋና ይገባችኃል፡፡ አንድ ጥያቄ ግን አለኝ የመረጃዉ ምንጭ?--- ለምንድነዉ የጠየቅሁት በዚህ አመት መጀመሪያ ታትሞ በወጣዉ የማህበረ ቅዱሳኑ ሐመረ ተዋህዶ መጽሃፍ በግልጽ ተጽፎ ነበር:: በተለይ ስለህንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንና ስለሀገራችን ተሃድሶዎች ማንነትና ብልግና የተሞላባቸዉ መጽሄቶቻቸዉ ይዘት በተለይ “ጮራ መጽሔት” ብዙ ብዙ ተብሎ ነበር፡፡ ከዛ በኃላ ማህበረ ቅዱሳን በጉዳዩ ላይ በሰፊዉ መረጃ ሰብስቦና ጥናት አድርጎበት ለሚመለከተዉ ሁሉ ለማቅረብ ስልጠና ተሰጥቶ በጉዳዩ ላይ የካቲት 6 ቀን 2003 (February 12 2011) አባላትን ሰብስቦ ሙሉ መረጃዉን አቅርቧል፡፡ ዉስጥ ዉስጡን የረጅም ጊዜ ስራ ሲሰራ ከቆየ በግልጥና በይፋ ጸረ ተሃድሶ ዘመቻዉን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቀቀ፡፡ እንደ አበዉ ልማድ ከስራ በፊት ጾም መቅደም ነበረበትና የዘንድሮዉን ጾመ ነነዌ ለ3 ቀን በልዩ ሁኔታ ምህላና ልመና ከደረሰ በኋላ ስራዉ ተጀምሯል፡፡ ለዚያ ነዉ የጠየቅሁት፡፡ ምንጩ ቢያንስ ማህበረ ቅዱሳን ሊሆን እንደሚችል መጥቀስ ነበረባችሁ፡፡ በመረጃ አሰባሰብና ጥራት ላይ መቼም ደጀሰላም አትታማምና ይሄ ተሰዉሮባችሁ ነዉ ለማላት ከበደኝ፡፡ የአዋሳዉ ጉዳይም እኮ የተሓድሶዉ ዘመቻ አካል ለመሆኑ ምን ጥርጥር አላዉ፡፡ ስለ እነ በጋሻዉ፤ ያሬድና ትዝተዉ መቼስ ድሮም ታዉቋልና ምን ማለት ይቻላል? እግዚአብሔር ተዋህዶን ይጠብቅልን፡፡ አንድ አሰተየየት ሰጪ እንዳሉት ለአቢይ ጾም ትልቅ የቤት ስራ ፈጠሩልን፡፡ ተግተን እንጸልይ …ተግተን እንጸልይ …ተግተን እንጸልይ …..

Anonymous said...

ክርስቲያንና ምስማር ሲመቱት ይጠብቃልና ለዚህ አይነቱ የተኩላዎች ፍትጊያ ልንደናገጥ አይገባም፤ ገና ብዙ አይነት መከራ እንደሚመጣም አስቀድሞ እንደተነገረን አንዘንጋ

Mitiku said...

አባቶቻችን እንዳስተማሩንና በታሪክ እንደምናውቀው ቤተክርስቲያናችን ያላሳለፈችው መከራ የለም... ቤተክርስቲያናችን እንደክር ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም። መቼም ይሄ ጽሁፍ/ሰነድ/ ቀድመን እንድናውቀው ‹‹አርማጌዶን›› እና ‹‹የሲኦል ደጆች›› በሚሉ ስብከቶች ተረድተናቸዋል። ግን በምንም መልኩ ቢሆን መቼ ወደ መፍትሄው እንደምንገባ ሳስብ ይጨንቀኛል ምክንያቱም የቤተክህነቱን የአስተዳደር ችግሮችን እያሰብኩ። ይህ ነገር በተናጠል ወይም በማህበር ደረጃ የሚመለስ አይደለም ትልቁን ሚና መጫወት ያለበት ቤተክህነቱ ነው እንዲሁም ሲኖዶሱ ከእንቅልፍ የመምንነቃበት ጊዜ አሁን ነው ይህ ካልሆነ ግን አምላካችን ጅራፉን ያነሳል ..... ወይ ጉድ መቼ ነው እግዚአብሔር የሰጠንን መክሊት የምንጠቀመው?

“የውጭ ጠላቶቻችንንስ ለይተን እናውቃቸዋለን ከውስጥ ጠላቶቻችን እግዚአብሄር እንዲጠብቀን እንፀልይ”
እግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን...

Mitiku said...

አባቶቻችን እንዳስተማሩንና በታሪክ እንደምናውቀው ቤተክርስቲያናችን ያላሳለፈችው መከራ የለም... ቤተክርስቲያናችን እንደክር ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም። መቼም ይሄ ጽሁፍ/ሰነድ/ ቀድመን እንድናውቀው ‹‹አርማጌዶን›› እና ‹‹የሲኦል ደጆች›› በሚሉ ስብከቶች ተረድተናቸዋል። ግን በምንም መልኩ ቢሆን መቼ ወደ መፍትሄው እንደምንገባ ሳስብ ይጨንቀኛል ምክንያቱም የቤተክህነቱን የአስተዳደር ችግሮችን እያሰብኩ። ይህ ነገር በተናጠል ወይም በማህበር ደረጃ የሚመለስ አይደለም ትልቁን ሚና መጫወት ያለበት ቤተክህነቱ ነው እንዲሁም ሲኖዶሱ ከእንቅልፍ የመምንነቃበት ጊዜ አሁን ነው ይህ ካልሆነ ግን አምላካችን ጅራፉን ያነሳል ..... ወይ ጉድ መቼ ነው እግዚአብሔር የሰጠንን መክሊት የምንጠቀመው?

“የውጭ ጠላቶቻችንንስ ለይተን እናውቃቸዋለን ከውስጥ ጠላቶቻችን እግዚአብሄር እንዲጠብቀን እንፀልይ”
እግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን...

chalie Afeowrk said...

Thank you for shrig and keep in touch!!!

Anonymous said...

I just want to remind everyone to forward this valuable document to every one, who is the child of our blessed church.
May God protect our Church,Tewahido!!
Fikiremedhin

nati said...

አሁንስ ምርር ነዉ ያለኝ።መነቃቀፋ አንዱ ከአንዱ በላይ መሆኑን ለማፅደቅ መካሰስ ዉይ ዉይ ዉይ። ህዝቡም የሠማዉን መቀበል ብቻ ። መጀመሪያ መርምሬ ነዉ ማነዉ ትክክል የምለዉ። አንዱን ወገን ሠምቼ አልቀበልም።

ኃ/ማርያም said...

አዲስ ያለሆነ ግን አዲስ…………ሳነብዉ ገረመኝ አዘንሁም……………ሳየዉና ስሰመዉ አብሬዉ እንዳለኖረሁ እንዳዲስ አነበብሁት………አዉ………በየቦታዉ ስረገዉ ከግቡ……….የቤተ ክርስቲያናችን…….ምሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ዘማሪዎች፣አዲራጊ ፍጣሪዎች……..ከሆኑ ቆዩ……..ብዙ ነገሮች ተበላሽተዉብናለ፣ ተፋልሰዉብናል ግን አሁንም ጊዜዉ አልመሸም………ተባብረን ቤተ ክርስቲያናችን ከጥፋት ልንታደጋት ይገባል. በእርግጥ ቤተ ክርስቲያን ትከሳ ይሆናል ግን አትሞትም ሞትን ድል በሚያደርገዉ በክርስቶስ ደም ተመስርታለቺና. ለዚያም እኮ ነዉ ቅዱሳን ያን ሁሉ መከራ አልፈዉ እዚህ ያደረሷት.

የእግዚብሄር ቸርነት የእመቤታቺን አማላጂነት የመላእክት ጥበቃ የክዱሳን ተራዳኢነት አይለየን!!! አሜን

Anonymous said...

In my opinion those protestant and everybody is doing their job,the protestant think our church is oldies or we are wrong so they want to teach us , we orthodox people and the church are still sleeping we are not moving teaching our people other than insulting them or accusing those protestant who are doing something bad on our church , hay people that is their target. we need to move we need to teach our people what our church believe.

Getinet Seifu said...

Please, I invite all of you to read ሐመረ ተዋሕዶ ቁ4

Anonymous said...

ቀንድኛው የተሃድሶ እንቅስቃሴ በእርግጥ ይኖር ይሆን እያልኩ እጠራጠር ነበር ማለቴ በተቀናጀ መልክ ማለቴ ነው። ነገር ግን በእርግጠኝነት እንቅስቃሴው መኖሩ ትናትና ተርድቻለሁ አንድ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቆ የነበረ መነኩሴ በሰሞኑ ባደረገው የካህናት ለተሃድሶ አላማ ሲያሰለጥን መያዙን ሰምቼ የታሰረበት ቦታ ሄጄ አጣራሁ ክእርሱ ውዳጅ ባግኘሁት መረጃ የምስራች እግልግሎት አባል እንደሆነና በግርማ በቀለ መደብ ደግሞ አሰግድሳህሌ አመራር ሰጭነት እንቅስቃሴው እንዳለ የዚሁ የጥፋት ተልእኮ እባል እንድሆነች የምትታውቀው የእሰግድ ሳህሌ እህት ክምንኩሴው ጋር እንድምትስራ እርጋግጫለሁ የመነኩሴዌ ስም እባ ገብረ ሚካኤል ይባላል ይታስርዌም ቶታል ጦር ሃይሎች ነው ማንም ለእምነቱ ተቆርቃሪ የሆን ሁሉ ሄዶ ሊርዳ ይችላል

Atinatious said...

To dears you have to understand their long term plan is as follows;Teaching bible in Orthodox church in the concept of protestant/catholic these are the strategic plan to change our church.

ዘጎርጎርዮስ said...

ዘጎርጎርዮስ
እባክህ ጎርጎርዮስ ሞገዱን ገስጸዉ:: ነገሩ አይኔን ሰዉ አማረዉ ብለህ ነበር::
ደጀሰላም እግዚአብሄር ያበርታችሁ :: PDF ብታደርጉት እና ኢንተርኔተ ለማያገኙ ብናደርስ::
እግዚአብሔር ስለተዋሕዶ አርበኞች ቤታችን ይጠብቅ::

Unknown said...

ሰላም ደጀሰላሞች አንደምን ሰነበታችሁ?በቅድሚያ አያደርጋችሁ ያላችሁትን ተዋህዶን የመታደግ ተግባር አጅግ አደንቃለሁ። አባካችሁ አኔም ተዋህዶን ለመታደግ አንደተማሪነቴ ምን ማድረግ አንዳለብኝ ንገሩኝ የሰማሁት የ''ተሃድሶ'' ንቅስቃሴ አጅግ በጣም አሳዝኖኛል ።በተረፈ ስላሴ በቸርነቱ ወላድተአምላክ በምልጃዋ ተዋህዶን ትታደግልን አሜን።
ሰይፈሚካኤል ነኝ ከአምስትክሎ

Haftom said...

እያንዳንዳችን እግዚአብሄር ይርዳን:: ይህንን ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ደግሞ እግዚአብሄር የተበላሸው ልቡናቸው እግዚአብሄር ያድስላቸው:: እግዚአብሄር ከዘመኑ ፈተና ሁሉ ሁላችንን ይተብቅ:: እመብርሃን መጨረሻችንን ታሳምርልን:: አሜን::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)