February 27, 2011

ከ400 በላይ የጉምዝ ብሔረሰብ አባላት ተጠመቁ።


(ማኅበረ ቅዱሳን):- በምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ወንበርማ ወረዳ የሚገኙ ከ400 በላይ የሚሆኑ የጉምዝ ብሔረሰብ አባላት በጎመር ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ቤተ ክርስቲያን እሑድ  የካቲት 13 ቀን 2003 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ በርናባስ የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በሀገረ ስብከቱ ቆሞሳትና ካህናት መጠመቃቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ባህር ዳር ማዕከል ገለጸ፡፡
ብፁዕ አቡነ በርናባስ የካቲት 12ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ በ10፡40 ሰዓት ወንበርማ ሲደርሱ  የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች ሠራተኞች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማዕከል፣ የሻንዳ ወረዳ ማዕከል አባላት፣ የአካባቢው ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ ምእመናን እና የጉምዝ ብሔረሰብ አባላት፣ በመዝሙርና በእልልታ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም በዕለቱ የማኅበረ ቅዱሳን ሸንዳ ወረዳ ማዕከል አባላት፣ የኮሊ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መዘምራን፣ የሸንዲ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መዘምራን፣ ጎመር ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መዝሙርና ሥነ ጽሑፍ በኦሮምኛ በአማርኛ ቋንቋ ለምእመናን አቅርበዋል፡፡
 

ሥርዓተ ጥምቀቱ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን የተጠመቁት ምእመናን በሥርዓተ ቅዳሴው ተሳትፈው ሥጋ ወደሙ ከተቀበሉ በኋላ በሊቀ ማዕምራን ሀዲስ ጤናው የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ እና በመጋቤ ምሥጢር ኃይለማርያም ታዬ ትምህርት ተሰጥቶ ሀገረ ስብከቱ ለተጠማቂያን የብሔረሰቡ አባላት 600 የአንገት መስቀል አበርክቷል፡፡

ተጠማቂ  ምእመናኑ አባይ በረሃን ከሚያዋስኑ ከወንበርማ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች የመጡ ሲሆኑ በአካባቢው ከአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በፊት ጀምሮ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት አልፎ አልፎ ያሉና የተጠመቁ የብሔረሰቡ ምእመናን ቢኖሩም ለዚህ በርካታ  የብሔረሰቡ አባላት መጠመቅ ምክንያት የሆኑት አቶ አያና የተባሉ የቻግኒ ወረዳ ማዕከል አባል ወደ ቦታው ለሥራ በመጡና አሁን የተዛወሩት ግለሰብ እና መምህርት መድኃኒት ሞላ የሸንዲ ወረዳ ማዕከል አባል አማካኝነት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የሸንዲ ወረዳ ማዕከል በ1994 ዓ.ም 2 ህፃናትን ከአካባቢው በመውሰድና የአብነት ትምህርት ቤት ለማስገባት የጀመረው ሙከራ ልጆቹ ሊለምዱ ስላልቻሉ ቢቋረጥም ለዚህ እንቅስቃሴ መጠናከር በምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ወንበርማ ወረዳ ቤተክህነት እና ከአካባቢው ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር በመሆን 2000 ዓ.ም ግንቦት 16 ቀን ወደ የማቤል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በወረዳ ማዕከሉ አስተባባሪነት የተደረገ የእግር ጉዞና ከአካባቢው የጎሳ አካላት ጋር የተደረገው ትምህርትና ውይይት ትልቅ በር እንደከፈተና ከዚያም በኋላ በወረዳ ቤተክህነቱ እና ወረዳ ማዕከሉ የሚደረጉ ትምህርተ ወንጌል ይበልጥ ግንኙነታቸውን እንዳጠናከረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የባህርዳር ማዕከል እና ሸንዲ ወረዳ ማዕከል በሸንዳ ከተማ የእራት ግብዣ በማዘጋጀትና ከበጎ አድራጊዎች 4.000 ብር አስባስቦ ቆርቆሮ እና እንጨት ገዝቶ በማጓጓዣ፤ ግንቦት 2002 ዓ.ም ጉባኤ በማካሄድና ከ460 በላይ የብሔረሰቡ አባላት ጋር ውይይት አድርጎ በቀበሌው ባሉት በመምህርት መድኃኒት ሞላና አንድ ሌላ መምህር አስተባባሪነት ተጨማሪ እንጨት እንዲያዋጡ በማድረግ ቤተክርስቲያን በጎመር ቀበሌ ሊሠራ ችሏል፡፡

ብፁዕ አቡነ በርናባስ ከአሁን በፊት የተጠመቁትንና አዲስ ተጠማቂያንን እንዲበረቱ መክረው በበዓሉ ለተገኙ ምዕመናን እንዳሉት “የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ወገኖቻችን ወደዚህች ሃይማኖት ሊመጡ ችለዋል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በደስታ ልንቀበላቸው፣ ልንከባከባቸውና ልንደግፋቸው ይገባል”፡፡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የብሔረሰቡ አባላት በበኩላቸው ከ 2፡00-4፡00 ሰዓት የሚፈጅ የእግር ጉዞ ተጉዘው  እንደተጠመቁ በመግለጽ ለሰሩት ቤተክርስቲያን ጽላት እንዲገባላቸው፣ በቅርብ ቦታ ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት እንደሰሩላቸውና ካህናት እንዲመደቡላቸው ጠይቀዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ በርናባስም ከወረዳ ቤተክህነት ጋር በመሆን የተቻላቸውን እንደሚፈጽሙና ምዕመናን ከጎናቸው በመሆን ለቤተክርስቲያን ሥራ እንዲተጉ ጠይቀዋል፡፡ በመጨረሻም በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

 ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። 


(በሪሁን ተፈራ ከባህር ዳር ማዕከል)

http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=499&Itemid=18

22 comments:

Anonymous said...

It is good but:
1) Be ready to give Basic christian education to the new christians.
2) Tell to the Tehadsowaians to go there and baptize the rest if they really have mission of Christ.
3)No value if all we persecute the batised ones and go to the unbaptised persons and also after a time persecute them and then also become empty.

Orthodoxawi said...

Egziabher Yimesgen!!!

Kititil madreg gin yiteyiqal!!!

Egziabher Amlak yetetemekutin bebetu yitebikilin!

Long Live Tewahedo!

yalew Tefera said...

meheru bizu serategnoch tikit nachew

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

መቼም፡በጣም፡የሚያስደስት፡ዜና፡ነው፡እግዚአብሔር፡ክብር፡ምስጋና፡ይግባው፡፡ወደፊትም፡እንድንበዛ፡ያድርገን!!!
እመቤታችን፡በረድኤቷ፡ሁሉንም፡ትጠብቅልን!
የመላእክት፡እርዳታ፡አይለያቸው!!!
የጻድቃን፡የሰማዕታት፡ጸሎት፡ይጠብቃቸው!

orthodoxawi said...

Egziabher yemesegen yehanene nebere leregem zemene yatanew Emebata Mareyam tekebere temesegen betame newe dese yalene .From UK DA .

Anonymous said...

እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረስን

የሚያስደስት፡ዜና፡ነው

Anonymous said...

Prise One God, The Father, The Son,and The Holy Sprite.

God Bless You Brothers who did the great job.

Anonymous said...

እግዚሀብሔር ገና ያበዛና
ይህን ትልቅ ስራ ለሰራችሁ ሰዎች እግዚሐብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ
የእግዚሀብሔር አብ ፀጋ የእግዚሐብሔር ወልድ ፍቅር የእግዚሐብሄር መንፈስ ቅዱስ አንድነት የጻድቃንና የሰማዕታት ተራዳይነት የእናታችን የቅድስት ድግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን
አሜን

Anonymous said...

በጣም፡የሚያስደስት፡ዜና፡ነው፡እግዚአብሔር፡ክብር፡ምስጋና፡ይግባው፡፡ወደፊትም፡እንድንበዛ፡ያድርገን!!!
እመቤታችን፡በረድኤቷ፡ሁሉንም፡ትጠብቅልን!
የመላእክት፡እርዳታ፡አይለያቸው!!!
የጻድቃን፡የሰማዕታት፡ጸሎት፡ይጠብቃቸው!

sara said...

በጣም፡የሚያስደስት፡ዜና፡ነው፡እግዚአብሔር፡ክብር፡ምስጋና፡ይግባው፡፡ወደፊትም፡እንድንበዛ፡ያድርገን!!!
እመቤታችን፡በረድኤቷ፡ሁሉንም፡ትጠብቅልን!
የመላእክት፡እርዳታ፡አይለያቸው!!!
የጻድቃን፡የሰማዕታት፡ጸሎት፡ይጠብቃቸው!

ቢኒያም ዘአዲስ አበባ said...

እናንተ ማህበረ ቅዱሳን አይዞአችሁ በርቱ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አለኝታ መሆናችሁን እያስመሰከራችሁ ነው፡፡ ዕውነት እውነት ነውና ምንም እነኩዋን አድር ባዩና ተሀድሶው …….ቢበዛም የትም አይደርስም

yonas said...

በጣም ደስ የሚል መንፈሳዊ ዜና ነው ለዚህ ስራ መሳካት የተፋጠናችሁ ዋጋ ከፋይ የሆነው የድንግል ልጅ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ሰማያዊውን ዋጋ ይክፈላችሁ እያልኩ በቀጣይ ደግሞ መሰረታዊውን የቤ/ክ ት/ት እንዲያገኙ ቢመቻች እላለሁ ለዚሁም እግዚሐብሄር ይርዳን እላለሁ

elsa said...

በጣም ደሰ የሚል ዜና ነው የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ!!!ለመላው የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለታላቁ ፆማችን አደረሳችሁ ፤፤

Anonymous said...

Temesgen!!! SILASE

Anonymous said...

ክርስትና ያኔም በዘመነ ሐዋሪያት የበዛችዉ በአምላክ ቸርነትና በሐዋሪያቱ ተጋድሎ ነዉ፡፡ እኒህን ወገኖቻችንን ነፍሳቸዉን እንደፈዋሳችሁላቸዉ በሁለት እግር የሚቆሙበትን ወንጌልም አስታጥቋቸዉ፡፡ ማህበረ ቅዱሳኖች ይህ በየጥጋጥጉ የምትሰሩት ስራ ለሰማያዊ መንግስቱ እንድትበቁ ያድርጋችሁ፡፡ የበለጠ ለመስራትና ስራዉም የተበራከ እንዲሆን ግን ወቅቱን ተጠቀሙበት (ልጅ ለእናቷ … እንዳይሆንብኝ)

Melkamu said...

ተመስገን አምላካችን!

ወንድሞቻችንን፡ እህቶቻችንን ማን ነው ኢትዮጵያዊነታቸውን ሊነጥቃቸው የሚችለው? ማንስ ነው መንፈሥ ቅዱስን የመዋጋት አቅምስ ያለው?

እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሰን፡ ወገኖች እንበርታ፡ በቋንቋችን በአማርኛ ፊደል መጻፉን እንቀጥልበት

Anonymous said...

በመጀመሪያ መልካም ዜና እላለው!

ጥሪ
ጥሪ
ጥሪ

ለውድ ደጀ-ሰላሞች፤
እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ግዛት ለምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተከታዮች በሙሉ፤

እስኪ በያዝነው የአብይ ጾም መጨረሻ አልያም በዳግማዊ-ትንሳኤ እለት/ ሰሞን አላማው ለክርስትና ማስፋፊያ (በዘገባው እንዳነበብነው አይነት) ና ለአብነት ት/ቤትና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል በስልክና በኢንተርኔት የገንዝብ ማሰባስብ ስራ ብንጀምርስ? ደጀ-ሰላሞችም ብታስተባብሩን?

ኤልያስ/ ዳላስ ቴክሳስ

Anonymous said...

It is a great news, but it may be considered meaningless for the following reasons
(1) the church has lost the tradition of Apostolic bible teaching. Thousands of other animists and muslims have been baptized at this church, but could gorw in faith because of lack of teaching and follow up.
(2) while millions of EOTC followers in rural Ethiopia have converted to supersitious life due to lack of teaching, it does not again mean much to add new believers. You don't have to believe my statement about the supersition, just visit rural Amhara or Oromo areas - you will see it with your own eyes. Tsadkane Mariam in Sela-Dengay of North Shoa is considered to be one of the prominent spiritual places in Ethiopia, but the pepole around it are fully engaged in TINKOLA, instead of worshiping God. This is clearly due to lack of teaching and spiritual nourishment. The people are only told that St Mary will save them regardless and the people believe that and continue in their evil lives. Don't get me wrong, St, Mary is my Love, Mother and Intercessor.

Therefore, th curch preaches the true word of God very strongly, those baptized now will be like the other people in rural Ethiopia. With some effort, supersition has been minimized in urban Ethiopia. Unfortunately. 85% of Ethiopians live in rural areas.

Anyway, it is a good direction as far as it is supported with continous bible teaching. FYI, Pente and other religions would have had the opportunity to grow to such a level if the church had firmly preached the bible acorss the country early on. I think it is not too late for the church to rise up from the squabbles and focus on disseminating the word of God.

Anonymous said...

My previous posting was riddled with errors and typos. Please replace it with this corrected version. I don't want to irritate your readers.

"It is a great news, but it may be considered meaningless for the following reasons:

(1) The church has lost the tradition of Apostolic bible teaching. Thousands of other animists and muslims have been baptized at this church, but could not grow in faith because of lack of teaching and follow up.
(2) while millions of EOTC followers in rural Ethiopia have converted to superstitious life due to lack of teaching, it does not again mean much to add new believers. You don't have to believe my statement about the superstition, just visit rural Amhara or Oromo areas - you will see it with your own eyes. Tsadkane Mariam in Sela-Dengay of North Shoa is considered to be one of the prominent spiritual places in Ethiopia, but the pepole around it are fully engaged in TINKOLA, instead of worshiping God. This is clearly due to lack of teaching and spiritual nourishment. The people are only told that St Mary will save them regardless which they believe and continue in their evil lives. Don't get me wrong, St. Mary is my Love, Mother and Intercessor.

Therefore, unless the curch preaches the true word of God very strongly, those baptized now will be like the other people in rural Ethiopia. With some effort, superstition has been minimized in urban Ethiopia. Unfortunately, 85% of Ethiopians live in rural areas.

Anyway, it is a good direction as far as it is supported with continuous bible teaching. FYI, Pente and other religions would not have the opportunity to grow to such a level if the church firmly preached the bible across the country early on. I think it is not too late for the church to rise up from the squabbles and focus on disseminating the word of God."

Anonymous said...

It is a good news. Thanks to God!
Bertu Egziabiher yirdachihu.

dembet said...

egziabher yabertachu

Kidus Ephrem MS said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ፅሑፉን በሚገባ አንብቤዋለሁ፡፡ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

በእርግጥም እግዚኦ እግዚኦ የሚያሰኝ ነው፡፡

እኔ በጣም ችግር አለ ብዬ የምገምተው ምእመኑ ጋር ይመስለኛል፡፡ ችግሩም መፍትሔውም በምዕመኑ እጅ ነው፡፡ ለምን ጳጳሳት ፣መነኮሳት፣ካህናት፣ዲያቆናትና መምህራን ሆነው እንዲህ አደረጉ ማለት አንችልም፡፡ ይኼ እኮ ገና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን በኋላም በሐዋርያትና በሊቃውንተ ቤ/ክ በተለይም በእነ አባ እንጦስና በእነ አባ መቃርስ በደንብ የተገለጸ ነው፡፡ በመጨረሻው ዘመን የሚነሱ መነኮሳትና ካህናት በንዋይና በስልጣን እንደሚፈተኑ በዚህም ከጥቂት የነፍስ አዳሪዎች በስተቀር ብዙዎቹ እንደሚወድቁበት የተነገረ ነው፡፡

ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ለጊዜው ልተወውና እስኪ አንዳንድ ጥያቄዎች ላንሳ
1. በ1986 ዓ.ም. እነ አባ ወልደ ትንሳኤ /አባ ማለት ይከብደኛል/ በቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ ‹በፒያኖ መዝሙር እንዘምራለን ምንም ችግር የለም ለጌታ ክብር እንዘምራለን በሚቀጥለው ሳምንት ዘማሪ እጋብዛለሁ ፒያኖ ይዞ ይመጣል › ብለው ሲናገሩ የተቃወማቸው ማነው? ለሃይማኖቱ ቀናዊ የሆነው ምዕመን አልነበረምን? እሳቸውም በወቅቱ ማንም እንደማይቀበላቸው ሲረዱ እድሜያቸውን ለማርዘም ይቅርታ ጠይቀው ኑፋቄያቸውን በሌላ መልኩ ሲዘሩ ቆይተዋል፡፡ አሜሪካ ሲገቡ የዘፈን መንፈስ ያለቀቃቸውና ውስጣቸው ተኩላ የሆኑ መናፍቃን በማግኘታቸው ይቅርታ የጠየቁበትን ፒያኖ እያዘፈኑበት ይገኛሉ፡፡
ታዲያ በዚያን ጊዜ ሲቃወም የነበረ የእምነት ጀግና ምዕመን አሁን ኑፋቄ ሲዘራ ለመቃወም የት ደረሰ ?

2. በ1988 እና 1989 ዓ.ም እነ ዲያቆን ግርማ እና እነ በወቅቱ አባ ዮናስ /አሁን አቶና ባለትዳር/ ክብረ ቅዱሳንን ሲያቃልሉ የእነ ዮሐንስ አፈወርቅና የእነ ቅዱስ አትናትዮስ መድረክ አይረክስም ብለው በቅዱስ እስጢፋኖስ በቅዱስ ያሬድ በቅዱስ ዮሴፍና በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተቃወመው የእምነት አርበኞች ወዴት አሉ ?

3. ቦንኬ ሲመጣ መስቀል አደባባያችን አይደፈርም ብለው የተደበደቡና የታሰሩ ሰማዕታት ምዕመናን የት ደረሱ? እንዲያውም እኮ ቦንኬ በግልጥ ፕሮቴስታንት መሆኑን ገልጾ በመምጣቱ ከውስጥ መሰሪዎች የተሻለ ነበር፡፡


4. በልደታ ለማርያም በቅድስት ስላሴ በቅድስት ማርያም በምስካየ ኅዙናን በቅዱስ ዑራኤልና በሌሎችም ሰ/ት/ቤት ኑፋቄን የተቃወሙ ተቃውመውም ያስወገዱ የ118ቱ ሊቃውንተ ቤ/ክ ልጆች ወዴት ተዋጡ ?

መልሱን ለሚመለከተው ልተወውና የእኔን ግምት ልሰንዝር

1. አብዛኛው ምዕመን የቤተክርስቲያንን ልዕልና ፈጣሪ እስከሚያሳየው በማልቀስ በፆም በጸሎት የእግዚአብሔርን ፍርድ ይጠብቃል
2. የተወሰነው ክፍል ደግሞ ሳያውቀው የኑፋቄ አራማጅ ደጋፊ ሆኖ ለጊዜው ዝም ያለውንና እድሜ ለንስሃ የቸረውን አምላክ ቤተ መቅደስ ድንጋይ በማንሳት ሲዳፈር ይታያል፡፡ ጠንካራ ሰ/ት/ቤቶች የተባሉት እንኳን እነ እንትናን አስጨፋሪዎች ሆነው በምን አለበት መዘዝ ተጠምደዋል
3. ሌላው ደግሞ ሁሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ ዘንግቶ እንደፈለጋቸው እኔን አይመለከተኝም ብሎ የተቀመጠ ነው


4. በዛ የሚለው ደግሞ አድናቂ ብቻ ሆኖ ቃሉ ምን ይላል እከሌ ምን አስተማረ ምን ብሎ ዘመረ ሳይሆን ‹አቤት ድምጹ › ‹አቤት ዜማው› በማለት ብቻ ባዶውን የሚመላለስ ነው፡፡አንዱ እንዲያውም ‹ጎርነን ያለ ድምፅ ስሰማ የቅዱስ ጳውሎስ ስብከት ይመስለኛል› ብሎ አርፎታል አሉ፡፡
ለእሱ እንግዲህ ስርዓተ ቤ/ክ ይፋለስም ኑፋቄም ይዘራ አባቶችም ይሰደቡ ብቻ ድምጹ ብቻ ይጩህለት፡፡
ለእሱ ውዴም ትበለው ፍቅረኛዬ ወንድሜም ይበለው ጓደኛዬ ለእርሱ ብቻ ድምጻቸው ይመርለት፡፡ በድፍረት ‹ በአምባላይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁት › ትበል ‹ ከእኔ በላይ ያነፃኸው የለም › ይበል ለእርሱ ምንም ግድ አይሰጠው ብቻ ቅላጼው ይመር፡፡ ምኑንም ሳያዳምጡ ብቻ እየሰሙ አብሮ ማንጎራጎርና ከንፈር መምጠት፡፡
ይኼ መዝሙር የቤተክርስቲያኗን ዶግማና ስርዓት የሳተነው ሲባል ከምን አንፃር እንዴት ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ስድብና ዱላ ይቀናዋል፡፡
5. ህሊናው እያወቀው በተሳሳተ መንገድ እንደሚጓዙ እየተረዳ በግጥምና በዜማ ስጦታ ተሸብቦ ለጊዜያዊ ጥቅምና ለ‹ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ› ተረት ራሱንና ህሊናውን ሸጦ የእግዚአብሔር መንፈስ እየወቀሰው በ30 ብር ጌታውን እንደሸጠው እንደ ይሁዳ ከእውነት ጋር እየተሟገተ ካለፈልኝ በኋላ ንስሃ እገባለሁ እያለ ፈጣሪውን የሚሸነግለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡

ለማንኛውም ከሁሉ በላይ ምዕመናን የነቃ ተሳትፎ ይጠበቅባቸዋል ባይ ነኝ፡፡ ቢያንስ ራስን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጸሎት መትጋት ወደ እውነት እንደሚመራ ጥርጥር የለውም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ እኮ እነዚህ የተሐድሶ አራማጆች ገና ሳይተነፍሱ ጠረናቸው ያስታውቃል እኮ ፡፡ይህ ለሚጾም ለሚፀልይ ግልጽ ነው፡፡ የኑፋቄያቸው ጠረን ከሩቅ ይከረፋል፡፡

ትዕቢት እኮ እንኳን በቤ/ክ አደባባይ ለምንቆም ለነጋዳፊም አልበጀ፡፡

በእውነት ደግሞ አትሰሙም እንጂ በወንድምነት የምመክራችሁ የቤተክርስቲያንን በተለይም ምዕመናን በኑሮ ውድነት ሳይሳቀቁ ከልጆቻቸው ዳቦ ላይ ቀንሰው የመጸወቱትን ሙዳይ ምጽዋት ለግል ጥቅም ማዋል አንድም በበሽታ በደዌ እንመታበታለን ፤ አንበላውም አንድም ጥለነው የምንሄደው ነው፡፡
ዘማሪ ተብዬዎቹ መዝሙር እንኳን አወጣን ሲሉ ቆይ አሁን በሲዲ እናውጣና ከዓመት በኋላ በቪሲዲ እናወጣለን እያሉ በምዕመናን ላይ ቁማር መጫወት ያምራቸዋል፡፡ በእርግጥ ሰዉ በየዋህነትና በእምነት ስለሚያደርገው አይጎዳም ግን የዘማሪዎቻችን ኪራይ ሰብሳቢነት በፈጣሪ እንደሚያስቀጣ ልብ ይሏል፡፡

ምዕመናን አጥብቀን እንጸልይ !እንጸልይ !እንጸልይ!
በተለይ በዚህ አብይ ጾም አጋንንት በክርስቲያኖች ጾም ጸሎት ስለሚቀጠቀጡ በተለይም በምድረ ኢትዮጵያ በሰዓታቱ ፣በኪዳኑ ፣ዳዊት በማስተዛዘሉ ፣በተዓምረ ማርያሙ ፣በቅዳሴው ፣በሰርክ ጸሎቱ ፣በስግደቱ ፣ በምጽዋቱ በሌሎችም ትሩፋቶች ድል ስለሚመቱ ፈተናቸውን ያከብዳሉ ፤ውጊያቸውን ያጠነክራሉ ፡፡ ስለዚህ ምንም ቤ/ክ ብትፈተን ምንም አጋንንት ያገበራቸው ርኩሰት ቢፈጽሙ አንባቢው ያስተውል ፡፡

እኛ ግን ከእምነታችን አንናወጽም ፡፡
እግዚአብሔር አባታችን
ተዋህዶ እናታችን
እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ፤አስታራቂያችን
ቅዱሳን አማላጆቻችን

እንቢ ለተዋህዶ !
እንቢ ለቤተክርስቲያን !
እንቢ ለክራችን !

አባቶቻችንን ያጸና በቸርነቱ እኛንም ያጽናን፡፡ አሜን ፡፡

ደጀ ሰላሞች ከእኔ በብዙ ታውቃላችሁና ጠቃሚና የሚያንጽ ነው ብላችሁ ካመናችሁ አርማችሁም ቢሆን ለንባብ አብቋት፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)