January 10, 2011

የ ቤን (EthiopiaFirst ) ዓይነት ብዕሮች ይታረሙ!! ይማሩ

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 10/2011፤ ጥር 2/2003 ዓ.ም)፦በገና በዓል አከባበር ዙሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች እና በአስተዳደሩ መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ተያያዥ ጉዳዮችን ስንዘግብ መቆታችን ይታወሳል። ይህንን ዜና “ሪፖርተር ጋዜጣ” እና “ኢትዮጵያ ትቅደምEthiopiaFirst” የተሰኘው ድረ ገጽ ጽፈውበታል። በዚህ ጉዳይ ያለንን አስተያየት ማቅረባችንን በቀጠሮ ይዘን “ኢትዮጵያ ትቅደም፤ EthiopiaFirst” ድረ ገጽ የሰጠውን አስተያየት ለመጠየቅ ወደድን።

ድረ ገጹ ገና ከመጀመሪያው የመረጠው ርዕስ “Threatening the secular face of our country” (ከሃይማኖት ወገንተኝነት የፀዳው አገራችን ገጽታ ለአደጋ ሲጋለጥ)  የሚል ሲሆን ነገሩን በጥሙና ለማይከታተል ማንኛውም ወገን አስደንጋጭ እና አስበርጋጊ ነው። በአንድ ግቢ ውስጥ የተደረገን የአዳራሽ ፈቃድ ጥያቄ በመላው አገሪቱ እንደመጣ መኣት አድርጎ ማቅረቡ ድረ ገፁ በጋዜጠኝነት ሥራ ካሳለፈው ጊዜ አንጻር ፍፁም አንድነት ኖሮት አላገኘነውም።

አቶ ቤን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስላለው የወጣቶች ሃይማኖታዊ ማንነት ተገቢው መረጃ እንደሌላቸው ከጽሑፋቸው የሚያስታውቅ ሲሆን እርሳቸው በኖሩበት በምዕራቡም ዓለም ቢሆን ዩኒቨርሲቲዎች አዳራሾችን ለተለያዩ ሃይማኖቶች አገልግሎቶች መጠቀም አዲስ አይደለም። ይህም ከተማሪዎቹ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች እንደ አንዱ እንጂ “አገሪቱን አደጋ ላይ እንደሚጥል መዓት” የሚቆጥረው የለም።

በርግጥ አንድ እውነታ መኖሩ አይካድም። ኢትዮጵያን በመሳሰሉት ባላደጉ አገሮች ያለው የመቻቻል መንፈስ በጣም ዝቅ ያለ ነው። ወይም ዝቅ እያለ እየመጣ ነው። ይህ አጠቃላይ የአገሪቱ ችግር በተማሪዎቹ ላይ መንጸባረቁ አይቀር ይሆናል። ይህንን ለማስከን ግን ተማሪውን በዘመነ ወታደራዊ አስተዳደር ወደነበረው ዓይነት “ሃይማኖት የለሽነት” ለማውረድ “ግቢዎቹን ከሃይማኖት ነጻ እናድርጋቸው” የሚል አካሄድ አዋጪ አይሆንም። ሁሉ ነገር በሥርዓቱ እንዲደረግ ማድረጉ ላይ አስተዳደሩ የቤት ሥራውን መሥራት አለበት። በደፈናው “እምቢ” ማለት መልስ አይደለም። አቶ ቤን “ዩኒቨርሲቲው በሕጉ መሠረት ነው የከለከለው” ብለው ሲጽፉ የትኛው ሕግ መሆኑን እንኳን ለመጥቀስ ለእኛ ለአንባብያን ክብር አልሰጡንም። ጭፍን “ካድሬነት” አሳዩ እንጂ ጋዜጠኝነት የለበትም።

በጠቅላላው፦ ሰሞኑን በግቢዎቹ የተፈጠረው ችግር “መአት” አይደለም። ተማሪዎቹ እና አስተዳደሩ ሊፈቱት የሚችሉት ትንሽ “አጋጣሚ” (Incident) ነው። የአገራችንንም መልካም ገጽታ የሚያበላሽ ተብሎ “ማስፈራሪያ” መሆን የለበትም። ሃይማኖት የሌለው ተማሪ ለማፍራት መሞከር ዋጋ አይኖረውም። በመከባበር፣ ሁሉም የየግሉን እምነት በማራመድ መኖር እንችላለን፤ ችለናልም። አስተዳደሩ ጥያቄዎቹን መፍታት እንጂ የአንዱን ስለ መብቱ መናገሩ የሌላውን እምነት ከመጥላት እንደመነጨ አድርጎ ማቅረብ ስህተትም ወንጀልም ነው። “አንዱን በአንዱ ላይ መነሣሣትስ” ማለት ከዚህ በላይ ምን አለ?

EthiopiaFirst ቤን ዓይነት ብዕሮች ይታረሙ!! ይማሩ
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)