January 5, 2011

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ፋካልቲ ተማሪዎች የልደት በዓል ዋዜማን በግቢው እንዳያከብሩ መታገዳቸውን ተቃወሙ


   አርእስተ ዜና፡-
  •   በአገር ዓቀፍ ደረጃ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የማንኛውም  እምነት ተከታዮች በቅጽር ግቢዎች በመዘመር እና በካፊቴሪያዎች ውስጥ ልዩ የዐበይት  በዓላት መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት የሚያከብሩበት ልምድ ‹‹እንዲታገድ ተወስኗል›› ተብሏል፡፡
  •   ይህን ውሳኔ መሠረት በማድረግ የካፊቴሪያው አስተዳደር ከአንድ ቀን በኋላ  የሚውለውን የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተማሪዎች እንደተለመደው ከእኩለ ሌሊቱ የሥርዐተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኋላ   ተመልሰው በካፊቴሪያው በሚያካሂዱት ልዩ መርሐ ግብር ማክበር እንደማይችሉ  ያሳውቃል፡፡
  • ውሳኔውን የተቃወሙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ፋኩልቲ(አራት ኪሎ ካምፓስ) የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ተወካዮቻቸውን መርጠው በግቢው የአክብሮ በዓል ልምዱ ቀደም ሲል ጀምሮ የነበረ፣ አንዳችም ችግር ያልተፈጠረበት፣ በተያዘው የትምህርት ዘመንም በዓላቸውን ያከበሩ  የሌላ እምነት ተከታዮች እንዳሉ በመግለጽ ‹‹ለምን ዛሬ?››  
  • ‹‹ለምን በእኛ ጊዜ@›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ 
  • ክብረ በዓሉ የቀረውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግም አስተዳደሩ ምላሹን እስከ ዛሬ ቀን ዐሥር ሰዓት ድረስ እንዲያሳውቃቸው ያመለክታሉ፡፡ ይሁንና እስከተባለው  ሰዓት ድረስ ምንም ምላሽ ባለማግኘታቸው የተበሳጩ ተማሪዎች የካፊቴሪያው፣ የቢሮዎች እና የዶርሚተሪ ሕንፃ መስተዋቶች በድንጋይ እሩምታ በመሰባበር ጉዳት ርምጃ ይወስዳሉ፡፡
  • በዚህ ሳቢያ ወደ ግቢው የተጠራው የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኀይል ከአምስት ኪሎ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ እስከ አራት ኪሎ የነጻነት ሐውልት ድረስ ያለውን መንገድ  ከተሽከርካሪ እና በመለስተኛ ሁኔታ ከእግረኛ ዝግ በማድረግ አካባቢውን እስከ ምሽት ድረስ  በመቆጣጠር፣ የአራት ኪሎ ካማፓስን በር ዘግቶ ከተማሪዎች እና ተወካዮቻቸው ጋራ በተፈ ጠረው አለመግባባት ዙሪያ ተወያይቷል፡፡ በውይይቱ ላይ ችግሩን ለፖሊስ ያስረዱት ተማሪዎቹ አስከ ነገ አምስት ድረስ ለጥያቄዎቻቸው ቁርጥ ምላሽ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡  

20 comments:

tad said...

Schools and government offices must be free of any religious practices. Religius practices must be allowed only in churches and mosques.
But the sad thing in Ethiopia is churches and mosques are open for politics.

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

አይዞአችሁ፡ወገኖቼ፡ቦታውን፡ጠላታችን፡ቢያስከለክላችሁእንኳን፡በዓሉን፡መከልከል፡ስለማይችል፡ተፅናኑ፡ጊዜው፡የፈተና፡ነውና፡፡ቸሩ፡አምላክ፡ጥሩ፡መልስ፡ያሰማችሁ፡፡መልካም፡የልደት፡በዓል፡እመኝላችሗለሁ!!!

Anonymous said...

It is umfair dicission. The University mgt should revise its decission.

Now a days, we know that in Ethiopia there is a very biased decissions here and there against EOTC.

I wish Melkam Lidet for all students in Ethiopia Universities.

Unknown said...

The university officials and the students' union should give serious attentions b/c there are so many peoples who doing this kind illegal and unfair discussion to fulfill there hidden goals by initiating students for violence. therefore our Christian students should polite and forward there question together with there representative and pray to GOD. GOD IS ALWAYS GOD

Anonymous said...

አለመግባባት እስካልተፈጠረ ድረስ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎች በዓላትን እንደ እምነታቸው ቢያከብሩ ምን ችግር አለው? መንግስት ትናንት ይዞት የመጣውን አመለካከት በተማሪዎች ለማስረጽ በልዩ ልዩ መርሃ ግብር ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያከብር የለ? አሁን በተለያዩ ጉዳዮች የተወጠረ መንግስት ምን አልባት የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየሪያ እንዳይሆን? ለዚህም ተማሪዎች ግራ ቀኙን ማየት አለባቸው ደም የለመደ መንግስት የሳት ራት እንዳያደርጋቸው። ለማኝኛውም እግዚአብሔር ይህን ተንኮል ለጠነሰሱት ሰዎች ልቦና ይስጣቸው።

Anonymous said...

It is not fair to ban the celebration.
But

"ይሁንና እስከተባለው ሰዓት ድረስ ምንም ምላሽ ባለማግኘታቸው የተበሳጩ ተማሪዎች የካፊቴሪያው፣ የቢሮዎች እና የዶርሚተሪ ሕንፃ መስተዋቶች በድንጋይ እሩምታ በመሰባበር ጉዳት ርምጃ ይወስዳሉ፡፡"
this is an outright non-Christian act.
our reaction is always fascinatingly different than would otherwise be expected....

ዘክርስቶስ said...

መንግስት የትምህርት ተቋማቶቻችን የጥናትና ምርምር ከማድረግ ፈንታ የሃይማኖት ማስፋፊያ ማእከላትን አድርጓቸው ነበረ። ምናልባት አድልዎ የሌለው ከሆነ አሁን የነቃ ይመስላል።
ወንድሞቼ ተረጋጉ! ሕግ ጥሩ ነው፤ የሕግ ባለቤት እኛው ነን “ዘእንበለ ሕግ ሐጢአት ምውት ይእቲ፤ ሕግ ይወጽእ እም ጽዮን” ሕጉ ለምን በኦርቶዶክስ አማኞች ተጀመረ ብለን ማኩረፍ የለብንም፤ ነገ’ኮ ለራሷ ስትል ትነጋለች፡ የሞስሊሙና የፕሮቴስታንቱ...በዓል ይመጣል። በአንቀጽ 11 ላይ የተደነገገውን መንግስትና ሐይማኖት ጣልቃ አይገባቡም የሚለው በዛው እናየዋለን።
ድሮውስ መቼ ቤተ ክርስቲያን ኣጣን? እባካችሁ የ6 ኪሎ ወገኖቻችን በአጠገባችሁ ባሉት ምስካየ ሕዙናን በመድሐኔ ዓለምና በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን በዓሉን አክብሩት፤ የአራት ኪሎ ተማሪዎች ደግሞ በቅድስት ማርያም መንበረ ፓትርያርክና በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሂዳችሁ አክብሩት።
እኛ ኦርቶዶክስዊያን ተከልክለን ነገ ሌላው ሲጨፍር ስናይ አቋማችን በግልጽ የምንገልጽበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን የምንሰራውንም እናሳውቃለን።
“ትዕግስት መራር ናት ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ናት”
መልካም ቅዱስ በዓል ያድርግልን!
እውነትን ባልናገር ወዮልኝ!

Anonymous said...

በጣም ግን ይገርማል። በትምህርት ቤቶችና በመስሪያ ቤቶች ያለተደራጁ የእምነት ድርጅቶች እንደፈለጉ ከ2-6 ሰው በማቀናጀት በ cell ደረጃ ስለፈልጉት ጉዳይ ያስተምራሉ ይቀስቅሳሉ፤ ማንም ግን ሃይ አይላቸውም። በተቃራኒው ግን ስለምን እንደተሰበሰቡ በይፋ የሚታወቁት ግን ይከለከላሉ።

ለከልካዮቹን ልብ ይስጣቸው።

Anonymous said...

Ebakachiu wondimina ehitochachine leigna selame belo begrigem betehwoldew kiristos belachiu tetsnanu meneme negar behone bealune betigst lemasalf mokiru dingle mariam begrgem ketehwoledw legowa gare cher wore tasemachiu betslot bertu

Dillu said...

ዘክርስቶስ በሰጡት ሀሳብ እስማማለሁ። የምናመልከው አምላክ በሁሉም ቦታ ስለሚገኝ ሥጋውያን ባንድ ቦታ የማምለክ ነጻነታቸውን ቢገፉት በሌላ ቦታ ማምለክ አለባቸው። ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም በባለሥልጣኖች እጅ መሞትና መሰቃየት የሚገባቸው ክርስቶስን ማምለክ አትችሉም ሲባሉ ብቻ ነው። <> ማቴ.፲፡፳፫

Anonymous said...

በመጀመሪያ ለጌታችን ልደት ስላደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
መንግስት አና ሐይማኖት የተለያዩ ናችዉ በሚል መንግስት በሐይማኖቶች ላይ የሚያደርገዉን ጣልቃ ገብነት አስፍቶ ምናልባትም ከዘመነ ደርግ የሚብስበትን ሁኔታ እያሳየ ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ ለጊዜዉ የተወሰነ አደጋ ቢኖረዉም ዞሮ ዞሮ ችግሩ የእራሱ እንደሚሆን እገልጻለሁ፡፡ ለዚህ እንደ ማስረገጃ የምገልፀዉ በኮሚኒስት ዘመን የነበሩ ባለስልጣናት የደረሰባቸዉን ወድቀት እና አሁን የሚያሳዩትን የመሳሳት እና የልብ መሰበር መንፈስን ነዉ፡፡ ምናልባት የአሁኖቹ ባለስልጣናት ተብዬዎች የዚህን ዓይነት ዕድል የሚያገኙ ከሆነ መልካም ነዉ፡፡
ይህ ወቅት የተለያዩ ነገሮችን ሊያስተምረን ይገባል
1. ለክርስትናችን መጠናከሪያ እና ከእምነቱ ራሳቸዉን ራቅ ላደረጉ መንቂያ ይሆና
2. ይህ ህግ እና አፈና በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች ላይ ብቻ እንደማያበቃ
3. አሁን በግቢዉ ዉስጥ ይህንን በዓል አታከብሩም ብቻ ሳይሆን ወደፊት የጾም ምግብ አይዘጋጅላችሁም የሚል ነገር ሊመጣ እንደሚችል
4. የቤተክርስቲያን መሪዎች (ሊቃነ-ጳጳሳት) ዝምታ ከምንታገሰዉ በላይ እየሆነ እንደመጣ እና ለዚህ ምዕመኑ በማስተዋል ዕልባት ሊያበጅለት እንደሚገባ፡፡ ለምሳሌ፡ በአጥቢያዉ ሰበካ ጉባኤ በመሳተፍ ተፅእኖ ማሳደር
5. ለሆዳቸዉ ያደሩ እና በተማሪዎች መካከል ተሰግስገዉ ተማሪዎችን ለከፋ ጉዳት አሳልፈዉ የሚሰጡ ወገኖች ነግ በኔ ማለት እንደሚገባቸዉ… እና ብዙ ነገሮችን ሊያስተምረን ይገባል፡፡
ከዚህ በተረፈ ምዕመኑ በሙሉ በፀሎት ይህንን ዘመን በቸርነቱ እንደ ሌሎች ክፉ ዘመኖች እንዲያሳልፍልን ቸሩ ፈጣሪያችንን ተግተን ልንለምን ይገባናል፡፡
በስተመጨረሻም አምላካችን ክርስቶስ እራሱ የተወለደዉ ዉጪ በግርግም ስለሆነ ይህንን አጋጣሚ አምላካችን እንዴት በችገር እንዳሳለፈ እንድንረዳበት ያደረገዉ ነዉ ብለን ለችግሩም አምላካችንን እያመሰገንን በዓሉን በሰላም እንድናሳልፈዉ እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ፡፡

lemma k. said...

"At present,there is no right for christians to do any thing even for worship freely!however this will pass one day by God!!!PHil 4:12

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል የዴሞክራሲ ጭንብል ያጠለቀው መንግስታችን
ኦርቶዶክስን ብቻ ለማጥፋት እየታገለ ነው

Anonymous said...

ውድ የተዋህዶ ልጆች ሆይ፤ ዛሬ የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በለመዳችሁት ስርዓት ለማክበር በመከልከላችሁ ቅር አይበላችሁ፡፡ ክርስትና የመስቀል (የፈተና፣ የስቃይ፣ የመከራ) ህይወት መሆኑ ይግባችሁ፡፡ በዓል ማክበር አይደለም በአገራቸው እግዚአብሄርን ማምለክ ያልቻሉባቸው ዘመናት እንደነበሩ አስታውሱ፡፡ ታሪካችሁን እወቁ፡፡ አባቶቻችን ይህችን ለጠላቶቿ የብረት ቆሎ የሆነች ሃይማኖት እንደ ምን በእሳት እንደተፈተነ ወርቅ እየተፈተኑ ከነስርዓቷ እዚህ እንዳደረሱ ተረዱ፡፡ በአይሁድ፣በካቶሊክ እና በእስልምና ዘመናቸውን በሙሉ በዱርና በገደል እየተንከራተቱ፣በስለት እየተሰየፉ፣በደብርና በዓታቸው በእሳት እየነደዱ እምነታችንን ከነመስቀሏ(ከነመከራዋ) አስረክበውናል፡፡ አሁን ባለንበትም ዘመን ቢሆን የእነርሱ እንግዴ ልጆች በጥንት ጠላታችን ዲያብሎስ አዝማችነት፣ በገሃነም ደጆች (ታሪካዊ ጠላቶቻችን) አቀነባባሪነትና የአብራካችን ክፋይ በሆኑት ልጆቻችን ፈጻሚነት እየሆነ ያለው የታሪኩ ቀጣይ አካል ነው፡፡ ዛሬ እኛም ልጆቻቸው ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም የበግ ለምድ በለበሱ ተኩላዎች ታውከናል፡፡ እረኛ እንደሌላቸው በጎችም ለአውሬ ተሰጥተናል፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና ምንም እንግዳ ነገር በማየት እርሱ ባለቤቱ እንዳለው ልባችሁ አይሸበር ነገር ግን በእግዚአብሄር እመኑ፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለምና፡፡ ከዚህ የበለጠ ብዙ በጣም ብዙ ገና ይጠበቅብናልና፡፡ ዛሬ ተዋህዶ ከኛ ከልጆቿ የምትጠብቀው መስዋእትነት እጅግ ብዙ ቢሆንም ቀደም ሲል አባቶቻችን ከከፈሉት መስዋእትነት ጋር ሲተያይ የበለጠ አይደለምና እራሳችንን ለበለጠ መንፈሳዊ ተልዕኮ በማዘጋጀት እንዲሁ በለሆሳስ ሁሉም ለበጎ ነው፤በአንተ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን በማለት እና ለሆነው ሁሉ ባለቤቱን በማመስገን በጸሎት ትጉ፡፡

መልካም የልደት በዓል ይሁንልን፡፡

Anonymous said...

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን

ዘ ክርስቶስ በሰጠኸው አስተያየት ለመሆኑ በዓሉን የት ሃደው እንደሚያከብሩ ያጡት ይመስልሃል?ሁላችንም የዚህ በዓል ተሳታፊዎች ነበርን ሌሊት በዓሉን አንተ ባልካቸው ቤተ ክርስቲያናት ማለትም በ ቅድስት ማርያም፧ በቅዱስ ማርቆስ፧ በጊቢ ገብርኤ ፤ቀደስት ሥላሴ በዓታ ለማርያም ፤ባለ ወልድ ቤተክርስቲያናት ከአከበሩ በኋላ ሰው ሁሉ ወደቤቱ ሄዶ ሲያከብር የካምፓስ ተማሪዎችም አንድ ቤተሰብ ስለሆኑ ተሰብስበው የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆት የሚረሱበት የዕለቱን በዓል የሚያጣጥሙበት ሰዓት ስለሆነ ነው።
ይሄን መከልከል ማለት ወደ ፊትም ቤተሰብም ዘመድ ከአዝማዱ ተሰብስቦ መብላት መጠጣቱም ሕግ ሊወጣለት ነው ማለት ነው።

ነገር ግን ፈታና ስለሆነ በርትቶ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን አጥብቀን ልንጸልይ ያስፈልጋል ።

Anonymous said...

ውድ ወንድሞቻችን ይህ የመናፍቃን ስውር ደባ መሆኑን አውቃችሁ እግዚአብሔር ቁጣውን በምህረት እስኪመልስታገሱ እሱ ምህረቱን ከአርያም ይላክ

Anonymous said...

Celebrating religeous holydays (both Christians & Muslim )in campus is not new in ethiopian university contexts. and there has not been any problems as result of this. There for the responsible stakrholders should reconsider to allow students to celebrate holly days who are far away ffrom their families. Both Christian and Muslim followers shold strugle for this freedom.

Anonymous said...

Thank God to here this. Universities are supposed to be for research not for incubation of Mahibere Irkusans. Hope it will continue to other educational institutes and curb these criminals from spoiling the productive society.
God Bless Ethiopia

Anonymous said...

The intention was not a formal law. There is no such a law till now, but only a draft. Some people used this to try it on us. "What are you going to do about it? We will capture you from the streets if you demonstrate...This is government time and I can't discuss with you anymore!"(but he is the student dean) This and similar answers were the ones we recived from the student Dean at 6 kilo. ....
It was intentional and they want us to get aggressive!...However, despite what has happened God has turned it for good. And, we have celebrated it together!!...If they say it is a law:
1. We should have a say in it before action.
2. It is an individual's right to religion(fasting,etc)so that we have a right to use the CAFE at 9:00 in nights.
3. Those who aggravated the situation by telling us at last moments and pushed us to violence by denying flexibility of situation should be asked.(Ato Shimelese of 6 kilo-Student Dean).
4. Tell to Ato Shimelese and the likes from 6 kilo "We are students and we have rights to ask what ever we want & he is there to answer our questions!!"
5. We want to know why they want to try this silly thing on us(Orthodox Christians) by telling us at the last 2-3 days and by denying us options!

God Be With Us ALL!!

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ዘአዲስ said...

ስንት የቤተክርስቲያናችን ነገር ዳሩ ስደፈር መሃሉ ዳር ይሆናል እንደምባል እየሆነ ሁላችንም ሆዳችን እየባሰ በዉይይት አንድ አቅጣጫ የሚጠቁም ጠፍቶ ዝምታ መርጠናል

ይዞታዎቿ አለአግባብ ሲነጠቁ፡አፅራረ ቤተክርስቲያን ሕግ ባለበት ሀገር ባልተገራ አንደበታቸው ስሳደቡ ወዘተርፈ ባለቤት ካልጮሄ .......እነንደሚሉት ሆነናል መሰለኝ

የአቡነ አኖርዮስ ገዳም ሶፍ ኡመር ሲባል ፡ያልነበረ የአሕዛብ ንጉሥ ከነስሙ ተፈጠጥሮ ታሪክ ስበረዝ ፡ በ1980ዎቹ ዓ.ም በባሌ ክ/ሀ ከወደሙት አቢያተ ክርስቲያናት actual jihad-ism እስከ ለምን ግቢ ገብርኤል፡መስቀል አደባባይ ወዘተርፈ ይባላል እስከሚለዉ intellectual jihad-ism ሲካሄድብን ፡በአንፃሩ 1 የአረበኛ ፅሑፍ ስለተቀደደ ከዳር እስከዳር ስታመስ፡ቀደደ የተባለዉ ተማሪ ያለፍርድ ከትምህርት ገበታዉ ስታገድ፡ፕሮቴስታንቱ ሕግ ባለበት ሀገር በአባቶቻችን ስም ፊልም እየሰራ ስሳለቅብን ፡ሃይማኖታችንን በግልፅ በማን አለብኝነት እየተሳደበ ስደነፋ፡በቻለበት እንዲሁ ምዕመናንን ስጨቁን ዝም አልን ! በቃ በሁሉም ዝም አልን!ስንሰደብ ዝም፡ስንጎተት ዝም ፡ስንወጋ ዝም!በሁሉም ዝም!ለመሆኑ አለን
ታዲያ እነዚህ ሞተዋል ብሎ ለመቅበር ባይመጣ ነዉ የሚገርመዉ፡፡
እስኪ ሞተዋል ብለው ለመቅበር ከመምጣታቸዉ በፊት እስኪ እንዳልሞትን እናሳዉቅ፡፡ አፈር ከተመለሰ ያስቸግራልና፡፡

ስለዚህ ቢያንስ ባለበት እንዲቆም አንድ ብባል መልካም ነው

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)