January 5, 2011

“ከሰማይ የሚወርዱ ጥቃቅን የእሳት ፍንጣሪ መሰል ነገሮች” የሣር ክዳን ቤቶችን እና የተለያዩ ስፍራዎችን አቃጠሉ

እሳት ወይስ እሳተ እሳት

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 5/2010 ታኅሣሥ 27/2003.)በፊቱ የቀረበለትን ሁሉ የሚያቃጥል - ከሰል፣ ዐመድ፣ ዕመት የሚያደርግ - የሚፋጅ፣ የሚልጥ፣ የሚለመጥጥ ነው ባሕርይው - የዚህ ዓለም እሳት፡፡ እሳቱን የሚያስቆጡት እና የሚያገኑት ነዳድያት እሳታውያንን ሲያገኝ ደግሞ ላንቃው፣ ልሳኑ፣ ወላፈኑ በዝቶ ነበልባለ እሳት(ነደ እሳት) ይሆናል፤‹‹እሳት በላዒ ለዐማፅያን›› እንዲሉ፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ግራዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ታቱ ጀነታ እየተባለ በሚታወቀው ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የታየው ግን ከዚህ የእሳት ባሕርይ በመጠኑ የተለየ ነበር፡፡

ከኅዳር 27 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ አምስት ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ልዩ ተልእኮ ያለው የሚመስል ‹‹ከሰማይ የሚወርዱ ጥቃቅን የእሳት ፍንጣሪ መሰል ነገሮች›› የተመረጡ የሣር ክዳን መኖርያ ቤቶችን እና ሰባት የተለያዩ ስፍራዎችን እያቃጠለ ዐመድ ሲያደርግ ሰንብቷል፡፡ በስፍራው ለእሳቱ መስፋፋት ምቹ የሆኑ ደረቅ ቁጥቋጦዎች እና የአየር ሁኔታ ያለ ቢሆንም በአንዱ ጎጆ/ስፍራ ላይ የሚከሠተው እሳት በሰው ኀይል ከመጥፋት ይልቅ የሚበላውን ከበላ በኋላ በራሱ ጊዜ እንደሚከስም ለደጀ ሰላም የደረሰው የዐይን እማኞች ቃል ያስረዳል፡፡ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት በዚህ መልኩ በቀጠለው እንግዳ ክሥተት 25 የሣር ክዳን መኖርያ ቤቶች እና አንድ መስጊድ ሙሉ በሙሉ 14ቱ ደግሞ ግማሽ በግማሽ በመቃጠላቸው የተፈናቀሉት 125 ነዋሪዎቹ በጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡ ስምንት ኩንታል በቆሎ፣ ማሽላ፣ ሰሊጥ እና በርበሬ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች እንዲሁም ስድስት ሺሕ ጥሬ ብር በእሳቱ ተቃጥለው ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ገልጧል፡፡ ይኸው የእሳት ፍንጣሪ በአንድ የዐሥር ዓመት ልጅ ራስ ላይ አርፎ ፀጉሩ ሳይቃጠል መታየቱንም የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡  


ከወረዳ ከተማዋ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የገጠር ቀበሌ የታየውን እንግዳ ነገር አስመልክቶ ሞያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁ የሐረምያ ዩኒቨርስቲ ምሁራን በምንነቱ ላይ ሳይንሳዊ ገለጻ ለመስጠት አዳጋች በመሆኑ ‹‹ወደፊት ቀጣይነት ያለው ጥናት እና ምርምር ተደርጎ መንሥኤው እንደሚገለጽ›› መናገራቸው ተገልጧል፡፡ ሌሊቱን ከቤታቸው ይልቅ በውጭ በማደር እንደሚያሳልፉ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ‹‹ይህ የአላህ ቁጣ ነው፤ መዐቱን እንዲያርቅልን ልመና እያደረግን ነው፤ በእኛ ዘመን ያጠፋነው ነገር ባይኖርም ቀደም ሲል ግን በአካባቢያችን የተፈጸመ ስሕተት አለ፤›› በማለት ከወረዳ ከተማዋ 18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ዶጉ መድኃኔዓለም አጥቢያ እንዲሁም በበደኖ ቀበሌዎች በ1983/84 ዓ.ም በታጣቂዎች በግፍ ተጨፍጭፈው በጅምላ የተቀበሩትን ክርስቲያኖች እና የተቃጠሉትን አብያተ ክርስቲያን ያስታውሳሉ፡፡ በስፍራው በሚገኝ አንድ ዋሻ ውስጥ 14 ታቦታት ተሰውረው የሚገኙ ሲሆን በዋሻው ላይ የሚያልፉ ከብቶችም እንደሚሞቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩል መስከረም 10 ቀን 2003 ዓ.ም በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሂርና ወረዳ የጋራ ንጉሥ መድኃኔዓለም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት በአክራሪዎች ሙሉ በሙሉ መዘረፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዘራፊዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ሲጠየቁ ንዋያተ ቅድሳቱን እንዳቃጠሉት ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን በፈጣን ችሎት የተመለከተው ፍርድ ቤት በዘራፊዎቹ ላይ የ14 ዓመት እስራት የፈረደባቸው ቢሆንም በቅጣት ውሳኔው ላይ ይግባኝ ባልተጠየቀበት ሁኔታ ወደ የቀደመው የፈጣን ችሎቱ ውሳኔ በሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እንደተቀነሰላቸው ተገልጧል፡፡ እሳተ እሳት የሰማይ እሳት መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ የግራዋው(ታቱ ጀነታ) የእሳት ዝናም መውረድ እና መቀጣጠል የጀመረው ኅዳር 27 ቀን አንስቶ እንደነበር ልብ ይሏል!!

23 comments:

ዘክርስቶስ said...

ጥያቄ አለኝ
1)እሳቱ በሳርና በቆርቆሮ የተሰሩ ቤቶች ነው እያቃጠለ የሚገኘው?

2)እሳቱ ከሰማይ ብቻ ነው የሚዘንበው?
ለሁለቱም ጥያቄዎቼን መልሳችሁ አዎ ከሆነ፡ በሰው ሥጋዊ ጉልበት ለማጥፋት መሞከር እያወቀ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም።
“አኮ በሥጋ አላ ዳዕሙ በጾም ወበጸሎት ትድህን ነፍስ”

እውነቱን ባልናገር ወዮልን!

ጭምት said...

አግዚአብሔር አኛ አንሰማ ሰንል የማቱን ዝናብ ያዘንባል::
ለአነርሱም ትምህርት ነው:: አግዚአብሔር ልቦናቸውን ይመልስ::
የአግዚአብሔር ሥራ ሁሌም ድንቅ ነው::

Anonymous said...

meteor ሚትዮር ይባላል

በተለያዩ አገሮች ይውድቃል በቅርቡም አሜሪካን አገር በ MA, MD, VA, NY, DC, PA በብዙ አገሮች ወድቅዋል

መዐት በኛ ላይ መጣ እያላችሁ ሕዝቡን አታውኩ

Anonymous said...

Betechristian Bechrstos Demm TemesrtalechNa Christos Ytebkatal Enji, Enantenma Be Meskerem(sep) 10 yetekatelew ahunu neew yemtastelalfut, yet neberachihut/ nebern/ Ahuns, manew Eyeteketatele yalew, Mesariachn Tsome tselot Yhun

YeKidusan Amlak Ykir blo kegna ga Yhun

Anonymous said...

በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ እግዚአብሔርን ሥራህ ግሩም ነው በሉት ይህን አይቶ አለመማር ልብን እልከኛ ማድረግ ነው:: የአካባቢው የእስልምና እምነት ተከታዮች ማስተዋል አደንቃለሁ:: እግዚአብሔር ልብ ይስጠን

Anonymous said...

I am surprised by the meteor comment.
Can u give me the probability of having meteor's in such frequency in one region? Most importantly, the possibility of the meteor's falling on the house's at that frequency?

I am more respective of those who suggested future study than yours. I also respect those who said yealah quta (even if they have no proof too). Because evenif it is proven to be meteor, can u disprove that God is not behind it?

Btw, I am not beating a drum to declare this is as a miracle or something else too.

ዘ ድንግል said...

ኣንተ ባለ ሜትርዮ ሃሳብ ሰጪ በየትኛው ካውንቲ ነው ይህንን የተመለከትከው ግንዛቤው ከሌለህ ዝም ብሎ መስማትም ብልህነት ነው። ኑሮዬ በቨርጅንያ ነው።ያልከውን አሳት በየትኛውም ሚድያ ስላልሰማሁ ነው ወይስ ላንተ ለብቻህ ሹክ የሚልህ ኣለ?

ሚሞ said...

ምናልባት በአሜሪካን የተባለው መብረቅ ሊሆን ይችላል እሱም በአንዴ አንድ ቦታ ላይ ይወርዳል እንጂ አይፈነጣጠርም ይሄ ግን ለየት ያለ ነው …….. ምን ይሉዋል
ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ያውጣን

Anonymous said...

ባለ ሜትዮር ... ደፋር! ችኩልነትህ "meteor ሚትዮር ይባላል" ከሚለው አጀማመርህ አንድ ይላል፡፡

ቅዱስ ዳዊት "ትውልድ እኪት ትውልድ ሉት እንተ ኢያርትአት ልባ ወኢተአመነት መንፈሳ በእግዚአብሔር" ያለው ለአንተና ለመሰሎችህ መሆኑን ልብ ብለህ ይሆን? ደርሰህ ተመራማሪ ወዲያው ደግሞ ራስህ አረጋጋጭ ሆነህ ከመቅረብ ሁኔታውን ለማጣራት አደብ መግዛት ምን ይጎዳል? በኢትዮጵያዊነትህ አፈርኩ፡፡

ለነገሩ የኖህ ዘመን ሰዎችስ በፍል ውኃ እስኪቀቀሉ እንኳ በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ አላመኑም፡፡

ይሁበነ እግዚአብሔር ልሳነ ጥበብ
ሄኖክ

Anonymous said...

እግዚአብሒር ሆይ እንደ ቸርነትህ አእነንጀጂ እንደበደላችን አይሁን!!መልካም ልቦና ያድላቸው

Anonymous said...

ዘ ድንግል said...

ኣንተ ባለ ሜትርዮ ሃሳብ ሰጪ በየትኛው ካውንቲ ነው ይህንን የተመለከትከው ግንዛቤው ከሌለህ ዝም ብሎ መስማትም ብልህነት ነው። ኑሮዬ በቨርጅንያ ነው።ያልከውን አሳት በየትኛውም ሚድያ ስላልሰማሁ ነው ወይስ ላንተ ለብቻህ ሹክ የሚልህ ኣለ?

January 05, 2011

አንብብ/ቢ
በሳይንስ ተቅዋማት የሚታተሙ የጥናት ምርምሮችን ማንበብ እውቀቱ ካለህ/ሽ

በየትኛውም ሚድያ ስላልሰማሁ ላልከው/ ላልሺው ቨርጅንያ ስለኖርክ/ሽ በቨርጅንያ ስለደረሰው ሁሉ በቲቪና ሬዲዮ ብቻ ወይም ለብቻህ/ሽ "ሹክ የሚል" አታገኝም

በዛሬው ጊዜ እውቀት ኢንፎርሜሽን ከብዙ ቦታ ይገኛል --ከሚድያ ከቲቪ ሬድዮ ብቻ አይደለም


"ዘድንግል" ብሎ ራስን ሰይሞ የዘለፋ ትችት ራስን ማስገመት ነው -

Anonymous said...

ሄኖክ
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለህ
"ይሁበነ እግዚአብሔር ልሳነ ጥበብ" በል

ሌሎች በእውቀት መጥቀው
የተራበ እንዲበላ
የታመመ መድሃኒት እንዲያገኝ
በስልጣኔ መጥቀው ሰማያትን እየዳሰሱ ጨረቃን ረግጠው አልፈው
የእግዚአብሔርን ስራዎች እየተመራመሩ እያደነቁ ነው

"በኢትዮጵያዊነትህ አፈርኩ"፡ብለሃል እስቲ ያንተን የሚያኮራ ስራ ንገረን

yared said...

እጅግ አስደንጋጭ ተዓምር ነው ፡፡ እባካችሁን አስተያየት ሰጪዎች በዚህ አስጨናቂ የእግዚአብሔር ቁጣ ላይ የምትሰጡት አስተያየት በጥንቃቄና እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ይሁን ፡፡ በኃጢዓታችን ብዛት የተነሳ 25 የሳር ቤቶችንና 1 መስጊድ ሙሉ በሙሉ 14ቱን በግማሽ ያቃጠለው ይህ ከሰማይ የሚወርደው የእሳት ፍንጣሪ በ10 ዓመቱ ሕፃን አናት ላይ ወርዶ ያላቃጠለው ልዑል እግዚአብሔር ንፁሁንና ደጉን ሰው እንዴት እንደሚያድነው ሲያስተምረን እኮ ነው ፡፡ ይህንን የእግዚአብሔር ቁጣ በአሜሪካ እና በሌሎች አገሮች የተደረገ የተፈጥሮ ገፅታ ነው ብሎ አስተያየት መስጠት ፍፁም ድንቁርና ነው ፡፡
“ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ የጥበበኞችን ምክር አጠፋለሁ የመካሪዎችንም ምክር እንቃለሁ እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው ? ጸሓፊስ ማን ነው ይህንን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን ? 1ኛ ቆሮ 1፡19-20 ” ስለዚ ይህንን የሰማህ ወገኔ ክርስቲያን ከመጀመሪያው ዝናም የኋለኛው ይበረታል እንዲሉ አበው የባሰው የእሳት ዝናም እንዳይመጣ ስለ ኃጢዓታችን በፅኑዕ ኃዘን ላይ ስላለችው ቅድስት ተዋህዶ ሃይማኖታችን በዘረኝነት እና በንዋይ ፍቅር መከፋፈል ይህንን ሁሉ መቅሰፍት ላመጣነው ከዲያቆን እስከ ፓትርያርኩ ላለንው የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ምዕመናን ዕንባችሁን እያፈሰሳችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ ፡፡ ማንንም በአደባባይ በሰልፍ አትዋጉ ማንም ወደማይከለክላችሁ እውነተኛ ፍርድ ወደሚገኝባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ገብታችሁ ከእንባ ጋር በጾም በጸሎት በምህላ ተዋጉ ፡፡ የህንን ካደረጋችሁ የኢትዮጵያንና እና የተዋህዶን ትንሳኤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ታያላችሁ ፡፡ልዑል እግዚአብሔር ይማረን ይቅርም ይበልን ፡፡አሜን አሜን አሜን

ከሰው ሁሉ ኃጢዓት እጅግ ኃጢዓቴ የበዛብኝን እኔን ገብረ ኪዳንን በጸሎታችሁ አስቡኝ ፡፡

yared said...

እጅግ አስደንጋጭ ተዓምር ነው ፡፡ እባካችሁን አስተያየት ሰጪዎች በዚህ አስጨናቂ የእግዚአብሔር ቁጣ ላይ የምትሰጡት አስተያየት በጥንቃቄና እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ይሁን ፡፡ በኃጢዓታችን ብዛት የተነሳ 25 የሳር ቤቶችንና 1 መስጊድ ሙሉ በሙሉ 14ቱን በግማሽ ያቃጠለው ይህ ከሰማይ የሚወርደው የእሳት ፍንጣሪ በ10 ዓመቱ ሕፃን አናት ላይ ወርዶ ያላቃጠለው ልዑል እግዚአብሔር ንፁሁንና ደጉን ሰው እንዴት እንደሚያድነው ሲያስተምረን እኮ ነው ፡፡ ይህንን የእግዚአብሔር ቁጣ በአሜሪካ እና በሌሎች አገሮች የተደረገ የተፈጥሮ ገፅታ ነው ብሎ አስተያየት መስጠት ፍፁም ድንቁርና ነው ፡፡
“ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ የጥበበኞችን ምክር አጠፋለሁ የመካሪዎችንም ምክር እንቃለሁ እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው ? ጸሓፊስ ማን ነው ይህንን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን ? 1ኛ ቆሮ 1፡19-20 ” ስለዚ ይህንን የሰማህ ወገኔ ክርስቲያን ከመጀመሪያው ዝናም የኋለኛው ይበረታል እንዲሉ አበው የባሰው የእሳት ዝናም እንዳይመጣ ስለ ኃጢዓታችን በፅኑዕ ኃዘን ላይ ስላለችው ቅድስት ተዋህዶ ሃይማኖታችን በዘረኝነት እና በንዋይ ፍቅር መከፋፈል ይህንን ሁሉ መቅሰፍት ላመጣነው ከዲያቆን እስከ ፓትርያርኩ ላለንው የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ምዕመናን ዕንባችሁን እያፈሰሳችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ ፡፡ ማንንም በአደባባይ በሰልፍ አትዋጉ ማንም ወደማይከለክላችሁ እውነተኛ ፍርድ ወደሚገኝባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ገብታችሁ ከእንባ ጋር በጾም በጸሎት በምህላ ተዋጉ ፡፡ የህንን ካደረጋችሁ የኢትዮጵያንና እና የተዋህዶን ትንሳኤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ታያላችሁ ፡፡ልዑል እግዚአብሔር ይማረን ይቅርም ይበልን ፡፡አሜን አሜን አሜን

ከሰው ሁሉ ኃጢዓት እጅግ ኃጢዓቴ የበዛብኝን እኔን ገብረ ኪዳንን በጸሎታችሁ አስቡኝ ፡፡

Anonymous said...

meteor ሚትዮር ይባላል:: የሆነ ነገር ይመትርህ። የኛ ፈላስፋ ቁጭ ብለህ ትፈላሰፍልናለህ። አሜሪካስ ቢሆን እሳት ከሰማይ ከመጣና ካቃጠለ ቁጣ ነው እንጂ ምሕረት ነው ያለህ ማነው? ሚትዮርም በለው ሜትሮ እሳት ከሰማይ መጥቷልና እግዚአብሔር ቁጣውን ይመልስ ማለት ነው። አንተ በነሙሴ ዘመን ብትኖር ኖሮ መቅሰፍቱን ከእግዚአብሔር ነው ሳትል እንዲሁ አንድ ስም ሰጥተኸው ትቀመጥ ነበር። የእግዚአብሔር እጅ ነው ብለው ብዙዎች ሲያምኑ የአንተ መቃወም እንደ ፈርዖን ድንዳኔ ነውና ወደ ልብህ ተመለስ። እ ው ነ ት የ ራ ቀ ህ ፈ ላ ስ ፋ። አንዳች ይመትርህ። ክፉ አናገርከን።

Anonymous said...

"የቀደመውን በደላችንን አታስብብን:ምህረትህ በቶሎ ታግኘን: እጅግ ተቸግረናልና::...

አህዘዛብ አምላካቸው ወዴት ነው?እንዳይሉ :የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በአይኖቻችን ፊት አህዛብ ይወቁ::"
መዝሙር 78: 8

ABYSSINIA said...

እግዚአብሄር መልካሙን ያምጣልን!ምህረቱንም ከእኛ እንዳያርቅ ተግተን ልንፀልይ ይገባል::

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች! ኸይ እኮ ታላቅ ተአምር ነው፡፡ በሚዲያ እንዲተላለፍ ብታደርጉት ጥሩ ነው፡፡ ሁላችንም ሊገባል የሚችል ነገር ሊኖረው ይችላል፡፡

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች! ኸይ እኮ ታላቅ ተአምር ነው፡፡ በሚዲያ እንዲተላለፍ ብታደርጉት ጥሩ ነው፡፡ ሁላችንም ሊገባል የሚችል ነገር ሊኖረው ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ስለእናቱ ስለድንግል ማርያም ብሎ ከታቀደ መቅሰፍት ያድነን . . .እግዚአብሔር ስለእናቱ ስለድንግል ማርያም ብሎ ከታቀደ መቅሰፍት ያድነን . . .

Anonymous said...

እግዚአብሔር ስለእናቱ ስለድንግል ማርያም ብሎ ከታቀደ መቅሰፍት ያድነን . . .

Anonymous said...

Hi Deje Selamoch << Yemigerim newe>> Teamir Newe!! . . .

Anonymous said...

The so called 'meteor' can you explain why it let only a limited area to be burnt or why a fire was seen on the head of a 10 years old child with out hurting him? could your poor logic of meteor explain this? I know what you will say at
this time" this is probably false "
And we will say to you " you are amongst the menafkan because you took one information leaving the many others and continue your usual wicked game.

sahlie said...

ወገኖቼ እባካችሁ የምንናገረውን ለይተን እንወቅ መጻሕፍትን እንመርምር በመጀመሪያ ስይንሳዊ ፍልስፍናን ከሃይማኖት ጋር አናገናኛቸው; ጥበብን የፈጠረው ልዑል እግዚአብሔር ነው ሁሉም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ለኛ ለሰው ልጆች ከአዕምሮ በላይ ስለሆነ ተአምራትን ከሳይንሳዊ መላምት ጋር አናጠጋጋው:: አንደበታችን ስድብን ሳይሆን በጎ ነገርን ያውጣ::
ሳህሌ ከለንደን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)