January 20, 2011

አንድ አፍታ ወጣቶችን እናመስግናቸው

Video: Courtesy of "Jerusalem 159"
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 19/2011፤ ጥር 11/2003 ዓ.ም)፦ የፀጋው ሀብት እና ጥልቀት የማይመረመር አምላክ የአባቶችን ልብ ወደ ወጣቶች መልሶ፣ “ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም” የሚለውን ተረት ሽሮ እሳታዊ እና ነፋሳዊ ባሕርይ ያልተስማማላቸውን ወጣቶች በመንፈሳዊ ምስጢር አርግቶ ዕፁብ ዕፁብ፣ ድንቅ ድንቅ የሚያሰኝ የወጣቶች መነሣሣት ፈጥሯል። እናም ይህንን ያደረገ አምላክ ምስጋና ይገባዋል።

ነቢዩ “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ (3626) ሲል እንደተናገረው ትልቅ የልቡናና የአስተሳሰብ መለወጥ ተፈጥሯል።  የዚህ ወጣት፣ “የወጣት ወጣት”፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቅረብ ለቤተ ክርስቲያኒቱም፣ ለአገሪቱም ትልቅ ጥቅም አለው። “የወጣት ወጣት” ያልነው አብዛኞቹ በአሥራዎቹ መጨረሻ እና በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ፣ ከእነርሱ ከፍ ካሉ ከሌሎች ወጣቶች (በ20ዎቹ መጨረሻ እና በ30ዎቹ) ከሚገኙት በዕድሜ የሚያንሱ ስለሆኑ ነው። 

በነዚህ ተከታታይ ዓመታት የሠሩት እና ያሳዩት ነገር ድንቅ የእግዚአብሔር አሠራር ስለሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱም መንግሥትም በጥንቃቄ ሊይዙት ይገባቸዋል። ወጣቶቹም በበኩላቸው ይህ ሁሉ የተደረገው በእግዚአብሔር ቸርነት መሆኑን አውቀው እስካሁን እንዳደረጉት በብስለት እና በመንፈሳዊ አስተዋይነት ሊመላለሱ ይገባቸዋል። ስለሁሉም ግን በብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች መካከል እንዲህ ዓይነቱን የተስፋ ብልጭታ ማየት ትልቅ ተስፋ መሆኑን በማስተወስ ባላቸው ነገር ሁሉ ለዚህ በዓል መሳካት ደፋ ቀና ያሉ የመላ ኢትዮጵያ ወጣቶችን እናሰግናቸዋለን።ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

36 comments:

ዘክርስቶስ said...

ዕጹብ ድንቅ ነው! እኛ ሰዎች ሚዛን የሌለው ሀሴት ሲሰማብን እግዚአብሔርና ወላዲተ አምላክስ ምንኛ ተደስተዋል!!!
ዘወትር ውስጤን የሚያቆስለኝ፣ ለምን አንድ ልብና አንድ አእምሮ ሆነን ወጣቶቻችን ሰብስበን አሁኑ እንዳደረጋችሁት ቤተ ክርስቲያናችን እንድትጠቀምባቸው አናደርግም ነው።

የጎደለብን ጥበብ ቢኖር የውስጥም ይሁን የውጭ ጠላት እርስ በርሳችንን አበላልቶ ከጎድን ወጣቶቻችን አፍሶ ሲወስዳቸው ባዶ ዐውደ ምሕረት ይዘን መቅረታችን ነው። አሁንም የዛሬዋ ሥራ ከዐባይ የተጨለፈች መቅድም ነች እንጂ ሁለት እግር ያላት ሙሉ አካል አይደለችም ።ልብ እናብቅል፤ መነቃቀፍ ትተን መቻቻል አንግሰን በየእንግዳው አዳራሽ የገባውም ፍጥረተ ክርስቶስ ሳይቀር ወደ ቀደመ እውነተኛ ቤተ መቅደስ መሰብሰብ የሥራ ልምዳችን ይሁን።
ዕጹብ ድንቅ ነው! እኛ ሰዎች ሚዛን የሌለው ሀሴት ሲሰማብን እግዚአብሔርና ወላዲተ አምላክስ ምንኛ ተደስተዋል!!!
ዘወትር ውስጤን የሚያቆስለኝ፣ ለምን አንድ ልብና አንድ አእምሮ ሆነን ወጣቶቻችን ሰብስበን አሁኑ እንዳደረጋችሁት ቤተ ክርስቲያናችን እንድትጠቀምባቸው አናደርግም ነው።
የጎደለብን ጥበብ ቢኖር የውስጥም ይሁን የውጭ ጠላት እርስ በርሳችንን አበላልቶ ከጎድን ወጣቶቻችን አፍሶ ሲወስዳቸው ባዶ ዐውደ ምሕረት ይዘን መቅረታችን ነው። አሁንም የዛሬዋ ሥራ ከዐባይ የተጨለፈች መቅድም ነች እንጂ ሁለት እግር ያላት ሙሉ አካል አይደለችም ።ልብ እናብቅል፤ መነቃቀፍ ትተን መቻቻል አንግሰን በየእንግዳው አዳራሽ የገባውም ፍጥረተ ክርስቶስ ሳይቀር ወደ ቀደመ እውነተኛ ቤተ መቅደስ መሰብሰብ የሥራ ልምዳችን ይሁን።

በርቱ ገባርያነ ሠናይ

Unknown said...

እግዚአብሔር አምላክ ስራው ድንቅ የማይመረመር ነው፡፡ ክብር ምስጋና ለአምላካችን ይሁን እስከ ፍፃሜው ድረስ ሁላችንንም ያፅናን ለወጣቱም እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡

Anonymous said...

They deserve. We were happy in seeing such Blessed Ethiopian Epiphany.But it needs care to handle them.they should learn the gospel with customs and traditions of EOTC in details. specially in good behaving any ways Thanks to GOd for all things.

Axumawit said...

Egziabher Yimesgen! Ejig betam kenahubachew. Eza hogne kenesu ga yihen bereket lemesatef bebekahu biye temegnehu. Egziabher Yibarkachu wud wetatoch!!!

Unknown said...

EGZIABHER ESKEMECHERESHAW YATSINACHIHU!

Anonymous said...

Bewnet mesgana yegebachewal teru jmer newena amlak segawen yabezalachew fesamiyachewn yasamrew.Enam yedereshachenen bemeweta wetatochu lebitekerestiyanachew yebelet yemiyageleglubeten menged lenasayachew yegebal.CHER YASEMAN

ወለተ ስላሴ said...

እግዚአብሄር ይባርካችሁ አገልግሎታችሁን ይባርክላችሁ ሌላ ምን ይባላል በአገልግሎታችሁ ያጽናችሁ

Anonymous said...

በዉነቱ በጣም ረክተናል ተአምር አንጂ ሌላ አልለውም
እነ “ዘክርስቶስ” ግን ለወጣቶቹ ብዙ ምስጋና ከማቅረብ ፈንታ አባይ በጭልፋ ነው ብሎ ቆልምሞ ማለፉ ገርሞኛል።

michalay

mebrud said...

አምና አንድ አፍታ አመስግነን ስለነበር ዘንድሮ ሁለት አፍታ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ምስጋና መልካም ነው።በመተቻቸት እንጂ በመመሰጋገን ትጉ እንዳልነበርን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር፣ይሁንልን።
አሜን

ይህን ካልኩ በኃላ።

ስለስሙ ይህን ያደረገ አምላካችን ምስጋና ይግባው።

"ሁሉ ከእርሱ፣በእርሱ፣ለእርሱ ሆነ"

እነዚህ ወጣቶች እንዲህ እንዲሆኖ ያደረጉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

በዚያ በገዳም ያሉ አባቶች ጸሎት ይሆንን?

የሆኖ ሆኖ ብዙዎች ከምስጋናቸው ጎን ስጋት ሸጎጥ ያደርጋሉ እንደ ሽጉጥ።

ወጣቶቹ በእርግጥ ዕድልም ስጋትም ናቸው፡፡

ሰንበት ት/ቤትም እኮ ዕድልም ስጋትም ናቸው።

ማኅበራትም ዕድልም ስጋትም ናቸው፡፡

ውሃም እድልም ስጋትም ነው፡፡

ስለዚህ
መስኖ ይበጅለትና ማሳውን ሁሉ ያጠጣው።

Anonymous said...

አንዳንዶቻችሁ እኔ በምሰጠው አስተያየት በምን መንፈስ እያያችሁት እንደሆነ አልተረዳኝም ረብሾኛልም። ዝምብዬ አንባቢ ብቻ ልሁን?
ግራ እንደተጋባሁ ሌሎች ወንድሞችም ግራ እንዳይጋቡ መልስ ልስጥና ዕንቅፋት ከምሆን ብተወው ይሻላል።
ወንድሜ “michalay”? አንድ ሐሳብ በድርብ መውጣቱ ትክክል ባይሆንም ለመረዳት የሚያስቸግር አይመስለኝም። ከይቅርታ ጋር፣ ነጠላ ዐረፍተ ነገርን በመያዝ መጽሐፍ ቅዱሳችን በተሳሳተ መንገድ እየተረጎሙ እንዳስቸገሩን ሳይሆን የጻፍኩትን ከመግቢያው እስከ መደምደምያው አያይዘህ ደግመህ ብታነብልኝ ግልጽ ይሆንልሃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።አንድም ላይ ላዩ ሳይሆን ውስጥ ውስጡን እያየሁ ነው ስስታም የሆንኩ፤ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ትናንት ምን ነበረች ዛሬስ! ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ዕለት ዕለት ዓርብና እሁድ ወደ ‘እንግዳው አዳራሽ’ ያልኩት የሚጎርፈው ለጋ ወጣት ታየዋለህ? ካየኸውስ ከማን ብብት ተሞልቅቆ እየሔደ መሆኑንስ ተገንዝበሐል? ዐባይ በጭልፋ ሳይሆን ዐባይ በሙሉ ነው ትናንትና አዲስ አበባ ጥምቀትን ሲያከብር የዋለው ብዬ ዋሽቼ ብነግርህ ስም ጠርቼ መናገር እምብዛም ደስ ባይለኝም አንተን ለማስረዳት ስል፦ ማሕበረ ቅዱሳን በእያንዳንዱ ግቢ ጉባኤ ከማን አፍ ለቅሞ ነው የሚያስተምራቸው ያለ? ከነ ፓ/ዳዊት ሞላልኝና መሰሎቹ የተረፉ አይደሉም?
ይህ ተወውና ለናሙና ያህል፣ አዲስ አበባ በነ ‘ዕገሌ’ በዓላት ሲሆን ምን መስላ ትታያሃለች? እስኪ ለአንድ አፍታ ያህል ዓይንህን ጨፍነህ አስብ! የሀገርህን ‘ስከለተን’ በማን ሥጋና እምነት ተመርጋ እየተነፈሰች መሆኗ ተመልከታት? በእንዲሁ ካስቀጠልናት ነገስ ምን ይዞ ጉዞ?

ብዙ ሐተታ መደርደር በራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ስላለው በዚህ ላሳጥረውና ለኔ ከኪሎግራም ወደ ሚሊግራም ሚዛን ወርደናል ብዬ ስለማስብ ለሰጠሁት አስተያየት ዓባይ በጭልፋና መቅድም ነው ማለቴ ስሕተት ከሆነ ሌላ የሚለው ነገር የለኝም አመሰግናለሁ።

የሆነ ሆኖ የተጀመረውን ውጥን “ሬስቶሬሽን” ከግቡ ለማድረስ በያለንበት ሆነን ቀንና ሌሊት እንስራ፤ አምላከ ኢትዮጵያ ይረዳናል።

ዘክርስቶስ

fkre said...

እንደዚህ አይነት ስራ የሚሰሩ ወጣቶችን ማንም ያምጣቸው ማንም እግዚአብሔር ይህንን ሰራ እንበል ሌላው እነሱንም የማያውቁ አድረገን ተሸርት ነጋደዎች አይጨወትባቸው እናስረዳቸው በውነት ከአንድ ተሸርት 10 ብር እያተረፍ ለምን ይነገድባቸዋል እነሱም እኳ ያውቃሉ ደግሞም የሚጻፍት ጥቅሶች ቃለ እግዚአብሔር ከሆኑ ስህተት ባይኖራቸው ቤተ ክህነት ቢያሳዩ መልካም ነው .....

TEMESGEN said...

@fikre, kewetatochu 10 ena 5 birr t-shirt atrfo megzat yiliq bezih agelglot temarkewu wede betachew wede betekrstiyan memelesachewu ejig liyasdesten yigebal.

Yihn Dinq Te'amir lasayen Le Amlakachin Misgana Yihun!

ድሉ የእግዚአብሔር ነው said...

የወጣቶቹ አገልግሎት በጣም ጥሩ ነው እግዚአብሔር ከያዙት መንገድ እንዳይወጡ በጸጋው ይምራቸው። ተፈስሂ ወተሐሰይ ኢትዮጵያ !''ሀየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ!''።
ጎንደር ላይ ስለተደረገው አከባበር ለምን ኣልዘገባችሁንልም? በተለይ በውጭ አገር ለምንኖረው ያካባቢው ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ሁኔታው እንዴት እንደነበር ብታሳውቁን ጥሩ ነው፡ ዘጋቢ ካላችሁ ማለቴ ነው። ከቤተሰብ ደውለን እንደተረዳነው፥ እንዲሁም ከጀርመን ድምጽ ራድዮ እንዳዳመጥነው ከባህል አንጻር ሲታይ በጣም ጥሩ እንደነበር ነው። ግን መንፈሳዊ ባህርዩ እንዴት እንደነበር ከናንተ ብንሰማው መልካም ነው።

ዘሶልያና said...

በዚህ በዓል ላይ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለምን ታቦት ለማጀብ ከተደራጁት ወጣቶች መካከል ነኝ፡፡ በበዓሉ ዝግጅት ላይ በአስተባባሪነት ተሳትፌ ስለ ነበር በእኛም ሆነ በሌላው የአዲስ አበባ ክፍል ይደረጉ ስለነበሩ ዝግጅቶች መረጃው አለኝ፡፡

1. ወጣቱ ይህን ሥራ የሠራው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቀስቃሽነት ነው ለዚህም ማስረጃው ምንጣፍ ለመግዛ ባደረግነው የገንዘብ ማሰባሰብ እኔ ካለሁበት አካባቢ እንኳን ሰላሳ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ ከዚህ በላይ የሚገርመው ግን ምንም ሥራ የሌላቸው ከዚህም ከዚያም ከሚያገኙት ገንዘብ ለዚህ ተግባር ያዋጡት የገንዘብ መጠን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉ ወንድሞች ያለ ምንም ስስት ለዚህ ሥራ ሲያዋጡ ማየት ያስደስታልም ያስገርማልም (ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያን ለተባሉ ለሰው ልጆች የምንቆረቆር ሁላችን እነዚህ ወንድሞች ዛሬ ከንዘባቸውን እንዳዋጡ ሁሉ ነገ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያዋጡ ትልቅ ሥራ ይጠብቀናል)፡፡
2. ሌላው ሁሉም በተሰጠው ጸጋ በፍቅር ለአገልግሎት ሲሳተፍ ማየት ልብን የሚነካ ተግባር ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የመዝሙር ጥናት ሲያደርጉ የቆዩ ወጣቶች (ልብ አድርጉ የሰንበት ተማሪዎች አይደሉም እንደእኔ ያሉ “መንገደኞች” ናቸው) ከራሳቸው አስተናባሪያቸውን፤ መዝሙር የሚመራቸውን፤ ሰልፍ የሚያሲዛቸውን መርጠው ለአገልግሎት ሲሰለፉ፡፡ በመዝሙር ጥናት ያልተሳተፉ ደግሞ ሥነ ሥርዓት በማስከበር፣ ምንጣፍ በማንጠፍ እና የማስተባበር ሥራ በመሥራት ያከናወኑት ተግባር ልዩ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ወጣቶቹ እርስ በርሳቸው የነበራቸው መተሳሰብ እና መረዳዳት እጅግ ይደንቃል፡፡ አድካሚ የሆነውን ታቦቱ ያለፈበትን ምንጣፍ ጠቅልሎ ተሸክሞ ወስዶ በድጋሚ ከፊት በማንጠፍ በፊታቸው ምንም ድካም ሳይታይባቸው በደስታና በፍቅር ይህን ሲያደርጉ ብዙዎች እነሱን አይተው ሲመርቁ እና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ማየት እጅግ ደስ ያሰኛል “ሥራችሁን አይተው የሰማይ አባታችሁን ያመሰግኑ ዘንድ . . . ” የተባለው ይሄ መሰለኝ፡፡
3. ሌላው በእኛ አካባቢ የነበረው ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ የሚከተለው ነው በጨለማ (በእስልምና) የነበረች አንዲት እህት ወደ ክርስትና መጥታ፤ ቀኖናዋን ፈጽማ፤ ተጠምቃ ከእኛ ጋር በትጋት መዝሙር አጥንታ፣ የሐበሻ ቀሚሷን ለብሳ

የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ . . .

ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኒዓለም . . .

እያለች ስትዘምር መመልከት ከኅሊና በላይ የሆነ ደስታን ያጎናጽፋል፡፡ እግዚአብሔር ቢረዳን በሚመጣው ዓመት እሷን የመሰሉ ሁለት ወንድሞች ከእኛ ጋር አብረው ለመዝሙር፤ ለምስጋና ይሰለፋሉ እስኪ ሁላችሁም ስለዚህ ነገር ጸልዩ፡፡

4. በመዝሙር ጥናት ወቅት የመዝሙር ግጥሞቸን በጽሑፍ በማዘጋጀት ለወጣቶቹ በማደል እና መዝሙር በማስጠናት በየአጥቢያው ያሉ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች መዝሙር ስታስጠኑን የከረማችሁትን ወጣቶች ትምሕርተ ሐይማኖት በማስተማር የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ንብረቶች ብታደርጉንስ (በዓላትን ከማክበር በተጨማሪ በሌሎች በጎ ሥራዎቸን እንድንሳተፍ)?

በመጨረሻ የጥምቀትን በዓል አክብረን ታቦተ መድኃኒዓለምን አስገብተን እንዳበቃን ሁላችንም ወደየ ቤታችን ከመሄዳችን በፊት አንድ በአይን ብቻ አውቀው የነበረና በዚህ በዓል ላይ ግን በደንብ ወደተግባባሁት በበዓሉም ላይ በፍጹም መንፈሳዊ ስሜትና መታዘዝ ምንጣፍ በማንጠፍ ሲያገለግ ወደ ዋለ ወንድም ጠጋ አልኩኝና “ . . . በተለይ እናንተ ምንጣፍ በማንጠፍ ያገለገላችሁ እጅግ ደክማችሁአልና እረፍት ያስፈልጋችሁአል አልኩት” ሳቅ አለና “የቅዱስ ሚካኤል ታቦት እኮ ነገ ነው የሚገባው . . .” አለኝ፡፡

በአጠቃላይ በእኛ አካባቢም ሆነ በሌሎች የነበረውን ቅደመ ዝግጅት በአልባሳት፣ በጽዳት፣ በጸጥታ፣ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ይደረጉ ስለ ነበሩ ውይይቶች ወዘተ እንዳልጽፍ አንድም የኔ ቃላትን ከቃላት አገናኝቶ፤ ዐረፍተ ነገርን አሳክቶ የመጻፍ ችሎታ ማነስ አንድም አንባቢን ማሰልቸት እንዳይሆን በመስጋት ሐሳቤን በዚሁ ልቋጭ፡፡

ሁሉን ያዘጋጀ እኛን የማንጠቅም ባሪያዎች ለአገልግሎት ያሰለፈ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
በረድኤቷ በበረከቷ ያልተለየችን ወላዲተ አምላክ ምሥጋና ይድረሳት፡፡
እግዚአብሔር በረድኤቱ አይለየን፡፡

ዘሶልያና
ከቀጨኔ አዲስ አበባ

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

የወጣቶቹን ተሳትፎ በደንብ ያስተዋልኩት አሁን ነው።ስለ እውነት ለመናገር ስራቸው በሰው አነሳሽነት ሳይሆን በእግዝአብሔር እንደሆነ የሳያል። ለምን ቢባል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረና እያማረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። ወገኖቼ ከዚህ በፊት ለወጣቶቹ የነበረኝ ግምት በጣም የተሳሰተ ነበር። እሱም ገንዘብ የሚሰበስቡት ከደባል ሱሳቸው ከሚተርፈው ባንዲራ ለመስቀልና ጨፌ ለመጎዝጎዝ ነው የሚል ነበር። ነገር ግን ይህን ግምቴን ለማዳበር በሔድኩበት በትኩረት ስከታተላቸው ለጥቅማቸው ሳይሆን ለሐይማኖታቸው እጅግ ያደሉ እንደሆኑ አስተውያለሁ። ወጣቶቹ ላባቸውን ጠፍ አድርገው ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ አስር ሰው የማያነሳውን ቀይ ምንጣፍ በቅልጥፍና ለታቦታቱ መረማመጃ ጠቅልሎ በመሸከም ሲዘረጉ ላየና ሌላውንም ድካማቸውን ላስተዋለ ከልባቸው እንደሆነ ማመን አይከብድም። የደስታም ሲቃ ይተናነቃል። ወጣቱ ቀርጦ ከተነሳ ምንም ነገር እንደማያግደውና የማይቻለው እንደሚቻለው አስመስክረውበታል። ወደፊትም ከዚህ በተለየ በእግዝአብሔር ቸርነት ተአምር ይሠራሉ። በተጨማሪ ወጣቶቹን ባመት አንዴ ብቻ ከምናመሰግን ቤተ-ክርስቲያን በመሐበር አቅፋቸው የዘወትር ተመስጋኝ እንዲሆኑ በማለት የዘክርስቶስን ሐሳብ እጋራለሁ።


የእግዝአብሔር ፀጋና ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን!!
መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

Let's hope all these young people are really in to faith not just emotionally driven by anyone except the holly spirit.

Anonymous said...

ጎንደር ላይ የጥምቀት በዓል አከባበር ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው ግን ደግሞ “ኢትዮጵያን በጎንደር” በሚል የካርኒቫል ሥርዓት አገር አቀፍ ትኩረት ተሰጥቶት ነው የተከበረው፡፡ መንግሥት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ከሚጠቀምባቸው መሠረታዊ ስልቶች አንዱ የታሪክና የቅርስ ባለቤት የሆነችውን ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በዓላት በመንተራስ አከባበሮችን ማዳመቅ ነው፡፡
ለዚህም ይመስላል ከላይ በተገለጸው መሪ ቃል ዝግጅቱ እንዲካሄድ የተደረገው፡፡ በዚህ ካርኒቫል ከ60ሺህ የሚበልጡ በውጭ እና በአገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ቱሪስት እንግዶች የበዓሉ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የታቀደ ሲሆን ይህንኑ ዝግጅት የተዋጣለት ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የካርኒቫል አስተባባሪ ኰሚቴ በማቋቋም ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በቤተ ክርስቲያን በኩል ከዚህ ቀደም ከሚደረገው ሥርዓት የተለየ ነገር ባይኖርም መንፈሳውያን ወጣቶች ከዛሬ ዓመት ካሳዩት ትጋት በላቀ በቁጥር ጨምረው፣በአልባሳት ደምቀው፣በአገልግሎት ተግተው የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የሆነውን ታቦተ ሕግ በመከብከብ በደማቅ ሃይማኖታዊ የምስጋና መዝሙርና ሽብሻቦ የጌታችንን በዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ መጠመቅ በማስታወስ እንዲከበር አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክን የሚዘክር ዐውደ ርእይ የቀረበ ሲሆን የአገሪቱም ርዕሰ ብሔር በቦታው ተገኝተው የበዓሉ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Anonymous said...

ለሶልያና ዘቀጨኔ...

በአንተ ትህትና ራሴን ዞሬ ስመለከት ባዶነት ተሰማኝ፡፡
በመጀመሪያ ለወጣቶቹ ካለን የቅርብ ርቀት አንፃር ስለነበራቸው ቅድመ ዝግጅትና መሰል ጉዳዮች አንተ እንዳልከው በሚሰለች ሳይሆን በሚያምር ተዋህዷዊ ለዛ ስላቀረብክልን ቃለ ህይወትን ያሰማህ፡፡ በእውነት አስተያየትህን ሳነብ ከመረጃው በላይ በትህትናህ ተማርኬያለሁ፡፡ ለነገሩ እንደገለጽከው ከመንገድ የመጣህ ሳይሆን በእውነተኛ አባቶች ትምህርት ታሽተህ በእግረ ሥጋ ሳይሆን በእግረ ልቡና ተመላልሰህ ያገኘህው ፀጋ ይመስላልና ሳትታበይ እስከመጨረሻው ጽና፡፡

ከጽሑፍህ እንደተረዳሁት ወጣቶቹ ራሳቸው ወደቤቱ ከመምጣትም በላይ ሌሎችንም በወሬ ሳይሆን በምግባር እየሳቡ ነውና እነሱንም እንዲያፀናቸው እንፀልያለን።

እንግዲህ ምን እንላለን ዘወትር ለስድብ ብቻ ይህን ብሎግ የምንከፍት ሰዎችንም እግዚአብሔር ያንተን ፀጋ ያድለን።

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን! የነገውንም እርሱ ያውቃል:: ዘሶሊያና ዘገባህ/ሽ እጅግ ማራኪ ነው:: የሁላችሁም አስተያየት እሰይ የሚያስብል ነው:: ቤተክርስቲያንን ለምድራዊ ጥቅም ሳይሆን ለስማያዊ ከተጠጋን እንዲህ ዋጋ ያለው ስራ እንሰራለን:: ሁሌም ከዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ጋር ነኝ:: ወጣቶቹን ስራችሁ ብርሃን ነበረ በሉልኝ (ብርሃናችሁ በዓለም ሁሉ አብርቷል):: ማድረግ የምችለውንም ለማድረግ ዝግጁ ነኝ:: dagimhunde@rocketmail.com
ቤተክርስቲያን አትታደስም የሰው ልጅ የአዕምሮ ውጤት ሳትሆን ሰማያዊ ናትና:: ያደሱትን ኑና እዩዋቸው::
ሰላም!

ፍጥረተ ክርስቶስ said...

ደጀ ሰላማውያን please see this video

http://www.youtube.com/watch?v=i2LejufXAZs
"አንድ አፍታ ወጣቶችን እናመስግናቸው"

Anonymous said...

ሰላም
ለደጀ ሰላማዊያን በሙሉ

Anonymous said...

በቤተክርስቲያናችን ሥም የሚሰሩትን ጠንካራም ሆነ ደካማ ጎን
በደጀ ሰላም ብሎግ ሐሳቦችን በነፃነት የማንሸርሸር መብታችን
ሆኖ እያለ፡ አንዳንድ እስተያየት ሰጭዎች ግን መስማት የሚፈልጉትን
ነገር ብቻ እንዲፃፍ ስለሚፈልጉ፡ ለደጀ ሰላም ብሎግ አቅራቢዮች
ቀጭን ትእዛዝ ሲያስተላልፉ እናያለን፡፡

ነገር ግን ከስህተቱ ለመታረምና ከክርስቲያኖች ጋር ተግባብቶ በፍቅር
ለመኖር የማይፈልግ ክርስቲያን ሽብረኛ እንጂ ክርስቲያን አይባልም።
እኔ እንከን የለብኝም ፣ ደካማ ጎኔንም መሥማት አልፈልግም፣
እንዲነገረኝም አልፈልግም በማለት ከመታረም ይልቅ የስድብና
የርግማን መልሶች የምንሰጥ ህዝቦች ሆነናል። እንከን የለሽ አምላካችን
ብቻ ነው። ይልቁንስ በማስተዋልና በጥሞና ቆም ብሎ በማሰብ ከስህተቶች
በመታረም መዳንም ማዳንም በእግዚአብሔር ይቻላል። ሁልጊዜ የሚገርመኝ
ጥፋታችን ሲነገረን ለምን ተነካሁ ለምን ተደፈርኩ ብሎ እንደ ስይጣን በትእቢት
ተወጥሮ ከመታረም ይልቅ የስምና የስድብ ጥላሸት መከላከያ እንደምናቀርብ ነው።
ይሕንንም የምናየው የማህበረ ቅዱሳን አባል ነን ባዮች ላይ ነው።

ወደ ቀደመው ነገራችን ልመለስና በቤተክርስቲያናችን ሥም የሚደረጉት ኢ-
ክርስቲያናዊ የሆኑ ወሬዎችና ድርጊቶች ለአሃቲ ቤተ ክርስቲያን የማይጠቅም
ብመሆኑ ለአሉባልታው ተባባሪዎች አንሆንም። እኛ የአንዲት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት
ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባል ክርስቲያኖች ነን እንጂ በስሙ ከሚነግዱት ማህበር
አይደለንም። ቤተክርስቲያናችንን ለማገልገልም ሆነ በክርስትና ህይወት ለመጉዝ
የማንም ድርጅት አባል መሆን የለብንም። ይህን ያልኩበት ምክንያት በዘመናችን
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንሰማውና የምናየው ነገር ሁሉ አንድ ክርስቲያን በተለይም
በኛ ቤተክርስቲያን የማህበረ ቅዱሳን አባል ሳይሆን በቤተክርስቲያን አገልግሎትና
በመንፈሳዊ ህይወቱ በርትቶ ካዩት የሚሰጠው የተለያየ የሃሰት ስም ደካማውን
ለጋውን ክርስቲያን ከቤተክርስቲያኑና ካለው የክርስትና እምነቱ እንዲርቅ ያደርጉታል።
ነገር ግን የእውነትን መንገድ ለተከተለና ክርስትና በደንብ ለገባው ግን ሚስማር ሲመቱት
እንደሚጠብቀው ሁሉ ቢመታም ያጠብቀዋል እንጂ አይሰነጠቅም። ስለዚህ ወገኖቼ እናስተውል።

ደጀ ሰላም ወደፊት በየጊዜው የሚመጡትን አስተያየቶች ወገናዊነት ሳይኖር ካወጣችሁት
መማማር ይቻላል የሚል ጠንካራ እምነት አለኝና እባካችሁ እንዳትሰለቹን።
በተረፈ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና እውነቱን ከመናገር አንቆጠብም።

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን
የድንግል ማርያም አማላጂነት አይለየን። አሜን።

Anonymous said...

I am speechless...... I remember their older brothers were grow up in a mentality of being shameful to mention the name of out almighty God..... But God work in his miracle way to lift the spirit of the new generation of Ethiopia in the time of where their is not a father figure for our country of Ethiopia and our Orthodox Tewahido Church of Ethiopia. I am almost in tears when I saw this beautiful pictures.

God bless you all and Ethiopia, Israel, America.

Assefa Gedefa said...

ስሜቴን ሙሉ በሙሉ በቃላት ለመግለፅ ብቸገርም ይህን የመሰለ ድንቅና ያማረ ትዕይንት ተመልክቸ ዝም ማለት ግን አልተቻለኝም፡፡ እናም የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ፡፡ በእውነቱ ወጣቶቻችን ከተባበሩ ማድረግ የሚሳናቸው ነገር ይኖራልን? በበኩሌ እኒህ ወጣቶች በዚህ ዓይነት አካሄድ ከተራመዱ ማድረግ የማችሉት ነገር ይኖራል ብዬ ለመናገር እጠራጠራለሁ፡፡ለእነዚህ ወጣቶች እግዚብሔር ፀጋውን አብዝቶ ይስጣቸው፡፡መንግስተ ሰማያትንም ያውርሳቸው፡፡አሜን፡፡

Anonymous said...

በቅድሚያ ወጣቶቹን ለተቀደሰው ዓላማ ያስተባበራችሁ በመቀጠልም በዓሉን ስታከብሩ የዋላችሁ ወንድሞቻን ወጣቶች የላቀ ምስጋናዬን አቀርብላችሗለሁ። እግዚአብሔር ለሀገራችሁና ለቤተ ክርስቲያናችሁ የማይፈነቀል ምሰሶ ያድርጋችሁ!

“ሕልም ተፈርቶ...” ያልክ ቤተሰብ የምጋራህ ሐሳብ ቢኖረኝም ግን ለምንድነው በማሕበረ ቅዱሳን እጅህን ልትሰነዝር የቻልኸው? ማለቴ በዚህ ብሎግ አትንኩኝ፣ወድሱኝ የሚል አካል ማህበረ ቅዱሳን መሆናቸው አለመሆናቸው መረጃ ኑሮህ ነው ወይስ በደጅ የገጠመህን ከዚህ ጋር እንደ ደሲማል በማጠጋጋት...? እኔ የማሕበሩ አባል አይደለሁም ;መንፈሳዊ ሥራን እየሰሩ ካየሗቸው በርቱ፣”ሕየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ” ፣ይበል!ብዬ አመሰግናቸዋለሁ፤ እንዲሁ በስመ ማሕበሩ ሱቅ በደረቴ ከፍቶ ንዋያተ ቅዱሳትን እየሸረሸረ የሚውል ሰው ሳይ ደግሞ ፊት ለፊት በሐሳብ ዕራቆቱን እስከማውጣት ድረስ የልኩን እሰጠዋለሁ። ዝምብለን በግለሰዎች ሰበብ ወይም የግላችን ጣጣን ማእከል በማድረግ የማሕበሩ መልካም ሥራን በአተላ ማጥመቃችን ነውርም ሐጢአትም ነው።
ብታምንም ባታምን፦ የማሕበር ጥማትና አለመብሰል የተጠናወተባቸው በጣት አሐዱ ክልኤቱ ወሰለስቱ ብለህ የምትቈጥራቸው የማሕበሩ አማራር አካላት ከኔ ጋር ፈጽመው የማይስማሙ አሉ። ነገርግን በነርሱ መጥፎ ስራ “ማሕበረ ቅዱሳን” የመሰለ የቤተ ክርስቲያኒቱ አንጋፋ ድርጅት አልነቅፍም። ለነጋዴዎቹና ለአጭበርባሪዎቹ ግን አሁንም ትግላችን ይቀጥላል።

Anonymous said...

ከዚህ በላይ ያለህ ባለረዥም ጽሑፍ...

አንደበቱ ለርግማንና ለሃሜት የተሳለ ተሳዳቢ በስመ ሥላሴ ፃዕ ሲባል፣ እንደነ ሶልያና ዘቀጨኔ አይነት በትህትናው ሰውን የሚያስተምር ክርስቲያን ደግሞ ሲመሰገንና በርታ ሲባል የሚከፋው አንድ አካል ብቻ ነው - ዲያብሎስና የግብር ልጆቹ።

Anonymous said...

ወንጌልን በተግባር አስተምረውኛል፡፡ እግዚአብሔር የህይወትን ቃል ያሰማልን፡፡

Anonymous said...

በጣም ደስ ይላል!! ትልቅ መነሳሳት!! እምነትና ሀገር አንድ ናችው መደፈር የለባቸውም!! ለሚገባው ትልቅ ትምህርት ነው!! አትንኩን ከነካችሁን ቀናዊ ነንና ቀፎው እንደተነካ ንብ ለዕምነታችን ሁሉን እንሆናለን ነው!! ትልቅ ነገር ! ታዲያ ይህ መነሳሳት ሁሌም ይሁን ለጥምቀት ብቻ ሳይሆን! ለትልልቅ በዓላት ብቻ ሳይሆን ሁሌም ንቁ ሆነን በምግባርና ዕምነታችን ጸንተን ለመንግስቱ አስክንበቃ!! ከዕምነት ባሻገር ለሃገራችን ኢትዮጵያም እንደዚሁ በተሰማራንበት መስክ ሁሉ ለሰላሟና ለዕድገቷ እንትጋ!! ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያችንን ይባርክልን!!

Sami said...

ማሕበረ ቅዱሳን ደካማ ጎናቸውን ስትነግራቸው የሚቀድማቸው ማኩረፍና እንደ ስድብ አድርገህ የመቁጠር ባህል ነው። ለምሳሌ ከላይ አንድ አስተያየት ሰጪ ያለው፣ በግለ ሰዎች ተነሳስታችሁ ማሕበረ ቅዱሳን ድርጅትን አትንቀፉ፤በማሕበሩ ስም የሚነግዱና የሚያጭበረብሩ ደግሞ ፊት ለፊት እንዋጋቸዋለን ሲል ነቅ-የማይ ሐቅ ነው የተናገረው፡አንዱ ከበታች ያለው ደግሞ ከላይ ባለ ረዥም ፅሑፍ ተሳዳቢ ዲያብሎስ ብሎ ሙልጭ አድርጎ ሲሰድበው ተመልክተናል። ታዲያ ይህን ካልተቀበላችሁ ምንድነው ፍላጎታችሁን? ወይም አቋማችሁን በግልጽ አሳውቁንና ደጀ ሰላም በናንተ በኩል የሚፈጸሙ ስሕተቶች ሒስ እንዳንሰጥባቸው ይከልክለን።
ወጡ!ጅብ የማይበላው’ኮ ነው ይህች ሀገርና ቤተ ክርስቲያን የገጠማት

Anonymous said...

ብዙ ጊዜ ከታዘብኩት :
አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋዬ ነው የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት አባልም አይደለሁም ነገር ግን ይህ ብሎግ መከታተል ከጀመርኩበት ጥቂት ወራት ጀምሮ ይህ ድርጅት ርዕሱ በማይመሳሰል ጉዳዮች ሁሉ መወያያ ርዕስ ሆኖ አገኘዋለሁ:: እኔ በሀገር ቤት ሆኜ ለስራ በተዘዋወርኩባቸው ቦታዎች ሁሉ በመልካም ስራቸው ነው የሚጠቀሱት ባይሆን ደግሞ በዚህ ሁሉ ዓመት ከባድ ጥፋት ያደርሱ እንደነበር መገመት አያስቸግርም:: ብዙ ጊዜ በትዝብት አልፌ አሁን አስደሳች የሆነውን የወጣቶቹን ስራ እያደነቅን እያመሰግንን ከታች የተሰጠው አስተያየት ግን ሌላ ሆኖ አገኘሁት፡ ይህም የተሰጡትን አስተያየቶች በትክክል ያለማንበብ ነው አለበለዚያ በፍጹም ኦርቶዶክሳዊ አይደለም: በተለይ SAMI የተሰጠውን አስተያየት ሁሉንም ደግመህ አንብብ: በተረፈ ይህ ድርጅት ችግር ካለበት አባቶች ባሉበት መነጋገሩ መለካም ይመስለኛል በስድብ የከበረ በመጽሓፍም በታሪክም ያለ አይመስለኝም:: ከነዚህ ወጣቶችም መማር ያስፈልጋል

Anonymous said...

ዘዘኆኅት
ለሶልያና ዘቀጨኔ፡- በጣም ደስ የሚል አስተያየት ነው፡፡ እኔም የዘንድሮን የጥምቀት በዓል ያከበርኩት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ነበር፡፡ በዘንድሮ የጥምቀት በዓል አከባበር የቀጨኔ የጥምቀት በዓል አከባበር ልዩ ነው ቢባል ማጋነን የሚሆንብኝ አይመስለኝም ምክንያቱም፡-
. 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአካባቢው ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ በደብሩ ተወልደው ያደጉ የዲያቆናት ማኅበርም ሳይቀር ባንድ ላይ በመሆን 28ሺህ ብር በሚሆን ገንዘብ ምንጣፍ መግዛታቸው ምንጣፉም በጣም ረዥም መሆኑና ምንጣፉ በተነጠፈ ቊጥር ወጣቶቹ በመጥረጊያ መጥረጋቸው፤ እንዲያውም የመድኃኔዓለም የቅ/ጊዮርጊስና የቅ/ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ታቦተ ሕግ አንድ ላይ ሆነው በሚጓዙበት ጊዜ 3ቱም ደብር ምንጣፍ ስላላቸውና ሕዝቡ ስለበዛ ለማንጠፍ አስኪቸገሩ ድረስ ለሃይማኖታቸው መልካም ስራ መስራታቸው፡፡ይህም አበረታች ስራ በጠረፍ ላሉትና ስብከተ ወንጌልን ለተጠሙት ወገኖቻችን ወጣቶችን ብናስተባብር ጥሩ ስራ ሊሰራ እንደሚችል አበረታች ሁኔታ ነው፡፡
. የቀጨኔ ደብረ ሰላም የተመሠረተበትን መቶኛ(፻ኛ)ዓመት የሚያከብረው የፊታችን ከጥር 27-የካቲት6 መሆኑና ፻ኛ ዓመቱና አስመልክቶ የተዘጋጀውን ቲሸርት፣ኮፍያና ባጅ ወጣቶቹ ለብሰው ሲዘምሩ፤ሲያስተናብሩ፤ምንጣፍ ሲያነጥፉና ቄጤማ ሲጐዘጕዙ በጣም ደስ ይሉ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በደብሩ ተወልደው ያደጉ ከ፶ በላይ የሚሆኑ ዲያቆናትና የአብነት ተማሪዎች (መደበኛ አገልጋዮችን ሳይጨምር) ጥንግ ድርብና ጥምጣም በመልበስ ከታቦታቱ ፊት በመሆን ያሬዳዊ የወረብ መዝሙር ማቅረባቸውና ስለ ደብሩ ፻ኛ ዓመትም ደብሩን የሚመለከቱ ያሬዳዊ ዝማሬ ሲዘምሩ ላያቸው ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኝ ነበር፡፡
. ወጣቶቹ የከተራንና የጥምቀትን በዓል በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካከበሩ በኋላ የቅ/ሚካኤልን በዓል የዋዜማ ምሽት ደግሞ ባቅራቢያቸው ወደሚገኙት መንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅ/ሚካኤል እና መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ በመሄድ ምሽቱን አስፋልቱን በመጥረግና በአስፋልቱ ዳርና ዳር ሻማ (በወረቀት በመክበብ) በማብራት ልዩና የሚማርክ፤ ምድር ላይ መሆናችንን እስክንረሳ ድረስ በዓሉን ልዩ ውበት ሰጥተውት ነበር፡፡፡
ለደጀ ሰላም፡-
የጥምቀት በዓል በመላው ሃገሪቱ በሳላም ተጠናቅቋል፡፡ ነገር ግን የቅዱስ ሩፋኤል ቤ/ክ በዓለ ጥምቀት አከባበር ላይ ትንሽ ችግር ተፈጥሯል ይህንን አልዘገባችሁልንም፡፡ለምን?

አበበ said...

በዚህ ብሎግ ደህና አስተያየት ይሰጣሉ ብዬ የማምናቸው የሁሉንም በነቂስ አነባቸዋለሁ፣ ሐሳባቸው ደግሞ ትችት ከሆነ በግልጽ ያቀርባሉ ምስጋና ከሆነም ለሚደግፉት በግልጽ ይሰጣሉ። ነገርግን እስካሁን ድረስ የ ዘ-ክርስቶስ ድርሰት ብቻ ነው ልረዳው ያልቻልኩት። ሰውዬው በሌሎች ብሎጎችም ተጠቃሚ መሆኑን አግኝቸዋለሁ በሁሉም ቦታዎች የፃፋቸው በትክክል ተረድተነው ከሆነ በሕይወትና ሕይወት መካከል ሞትን ሰንቅሮ፣ በቅኔ ሸፍኖ ማንንም እንደሚደግፍ ማወቅ የተቸገርኩበት ነው።
ለምንድነው ግን ራስህን እማትገልጠው? አንተ አንተ ነህ እንዳንልሕ መልእክቶችህን ቁልፍልፍ አድርገህ ነው የምታቀርባቸው። አላዋቂ ነህ እንዳንልህም የቀለም ሰው መሆንህን ፍንጮችን ያመለክታሉ። እስኪ ትክክለኛ የኦርቶዶክስ ልጅ ከሆንክ አንድም ይሁን ሁለት እርሾዎችህን አስወግደህ እንደ መረጥከው ስም ትውልድን የሚያንጽ ብቻ ፃፍ?
ባጭሩ ልለው የፈለግሁት ከማን ጎራ መሆንህን በቀና መንፈስ ብትገልጥን ያለ ስጋት የድርሰትህን ተጠቃሚ እንሆናለን።

Anonymous said...

ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ወጣቶች ሆይ! ለሰራችሁት ልዩ የጥምቀት በዓል አከባበር የምገልጽበት ቃላት ባይኖረኝም ከደስታ የተነሳ የእውነት እንባዬን ለማፍሰስ ተገድጃለሁ።

የእግዚአብሔር ጣቶች ያረፉባትንና ዘወትር እጆቿን ወደ እግዚአብሔር እየዘረጋች ከምትኖር ሀገራችን ኢትዮጵያ መወለዳችሁ በሥራ በመግለጻችሁ በዓለምና በእግዚአብሔር ፊት ክብረሞገስ እንድጎናጸፍ አድርጋችሁናል።

ያሳያችሁትን ተጋድሎ በሌሎች መንፈሳዊ ሥራዎችና ሀገራዊ ልማት ቀጣይነት እንዲኖረው የድንግል ማርያም ረድኤት ከሁላችን ጋር እንዲሆን እመኛለሁ።

ቴዎሎጂያን-ከስደት ሀገር

Anonymous said...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሰረቷ እግዚአብሄርን የምታምንበት ዶግማዋ ነው እስከዛሬ ያፀናትም ለዘላለም የሚያኖራትም ይኸው እምነቷ ነው እንደምታውቁት በአምስቱ አእማደ ምሥጢራት ትምህርት ይገኛል በተለይም ምሥጢረ ስላሴንና ምሥጢረ ስጋዌን ጠንቅቆ ያወቀና የመናፍቃኑን ''የሁለት ባህሪና የጌታ ያማልዳል የተሳሳተ ኢመፅሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ያየ'' ክብር ምስጋና ይግባውና እርሱ አያማልድም ይፈርዳል እንጂ: ምን ያህል ተዋህዶ በፀና መሰረት ላይ የተተከለች መሆኑወዋን ይገነዘባል:: ባይሆን ኖሮ ከካቶሊኩ ከፕሮቴስታንቱ ከተሀድሶው ከሙስሊሙ...የሚዘንበው ውርጅብኝ በሀገራችን ሌላ ታሪክ በፈጠረ ነበረ። ይልቁን ወንድሞቼ እኔ የምመክረው በተለይ የቤተክርስቲያኗን ዶግማ ጠንቅቃችሁ ለምታውቁት ያ ቤተክርስቲያኔን በዚህች አለት ላይ ''በአንተ እምነት መሰረትነት ላይ በአለት በተመሰለ እምነትህ ላይ ይኸውም የህያው እግዚአብሔር ልጅ ማለቱ'' እመሰርታታለሁ.... ማቴ. 16፣16-20 የተነገረ ያ የጌታ ቃልና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ሰጥቼሀለው ብሎ ያለው እርሱ ሊቀ ካህናት ሲሆን እነእርሱን ካህናት ያደረገበት ያቺ ስልጠነ ክህነት የተዋህዶን ትምህርት ብቻ ተከትላ ስለምትወርድ በውይይት መግባባት ስለሚደረግባቸው አስተሳሰቦች ብላችሁ መሰረታችሁን አትልቀቁ ከዚህ የክህነት ተዋረድ አትውጡ። ቤተክርስቲያኗ ምታደርገውን ሁሉ የምታደርገው እቤቷ ውስጥ በራሷ አባቶች በራሷ ሊቃውንት በጊዜው ብቻ ነውና የገሀነም ደጆች አይችሉአትም ተብሏል እና ከውጭም ከውስጥም ሆኖ ለማጥፋት መተናነቅ ጊዜ ማባከን ነው መስሏቸው ወጥተው ጊዜ ሰጥቶአቸው እያለቀሱ የተመለሱ አታውቁም እኔ ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ስም አልጠቅስም እንጂ በወቅቱ ዲያቆን የነበረ አሁን ካህን ናቸው ነገረ መለኮቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ መምህር በወቅቱ በነበረው ማእበል ተወስደው እርሳቸው እንዳሉት ለብዙዎች ጥፋት ምክንያትም ከሆኑ ከ9 ረጅም አመታት በሁዋሏ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባውና ልቡን ማስተዋሉን አግኝተው ወደ ቤተክርስቲያናቸው ተመልሰው እንደውም የፕሮቴስታንቱ አለም እየተንደረደረ እየወረደበት ያለውን ቁልቁለት የሚያሳይ ልዩ አይነት መፅሀፍ ለመፃፍም በቁ። እናም ወንድሞቼ በጠላት እምነትና ሀሳብ ቤተክርስቲያኗን ለማደስ ማሰብ አይሳካም ተዉት አንዳንድ ሰዎች ሉተር የተወለደበትን የ 16ኛውን መቶ ክ/ዘመን የካቶሊኮችን ታሪክ እኛ ጋር እንደሚደገም ያልማል ያ ደግሞ እኛ ቤት አይሰራም ካቶሊክ ሁለት ባህሪ ብላ መሰረቷን ለቃ ነበረና ''እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው''ሮሜ 1፣28 ያለው ተፈጽሞባቸው ነው ተዋህዶ ግን መሰረቷን ያልለቀቀች ፅኑ እምነት ነች እምነቷ ስርአቷ ትምህርቷ ያው አንዴ ከቤተልሄም እስከቀራንዮ ጎልጎታ የሆነውን እግዚአብሔር የተናገረውን፣ ነብያት የተነበዩትን፣ ጌታ የገለጠውን፣ ሐዋርያት ያስተማሩትን ይዞ ነውና ቤተክርስቲያኗን ማደስ ምናምን ሀሳብ የትም አያደርስም ይልቁን ወደ ቤታችሁ ግቡና ዘላለማዊውን አምላክ አገልግሉ የልባችንን የሚያውቅ አምላክ ከልብ ስለቤተክርኢስቲያን ምንፀልይ ከሆነ እንኳን ቤተክርስቲያኑን የእኛንም ህይወት ያስተካክል የለ: ጌታ በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ተገኝቶ ሸቃጮችን ገርፎ ሲያስወጣ በእነማን አብዮተኝነት ማን አስታውሶት ነው ቤተክርስቲያኗ መሰረቷ ትክክል ነው ብሎ ያመነ ሰው ጨርሶ ከሀዲ ካልሆነ በስተቀር ባለበት ሆኖ እያገለገለ እየፀለየ አእየተመካከረ ተአምር ይሰራል ከዛውጭ ያለው ትችት ተዋህዶን ፕሮቴስታንት የማድረግ ትንቅንቅ ነው። ከፕሮቴስታንቱ ጋር ያለው ልዩነት ዋናው ጌታ ያማልዳል ማለታቸው ስለስላሴ ያላቸው የተዛባ እምነት ሲሆን አውቀው ነው ስለታምረ ማርያም ስለሌሎች መፃህፍት እያነሱ ምእመኑን ግራ ሊያ ጋቡ የሚሞክሩት የጌታን ፈራጅ እንጂ አማላጅ አለመሆን ያመነ አውቶማተቲካሊ የቅድስት ድንግል ማርያምን የቅዱሳን መላእክትን የቅዱሳን የፃድቃን የሰማእታትን አማላጅነትና ተራዳኢነት ይቀበላልና ጩኸታቸው ለማደናገር ብቻ ነው ’’እግዚአብሔር ሲጣላ ልምጭ ቆርጦ አይቀጣም ያደርገናል እንጂ ንግግር እንዳይጥም'' የሚለው አባባል እንዳይደርስብን አምላክ ይጠብቀን ። የተዋህዶ ልጅ ነኝ ሰላም

Anonymous said...

Dejeselamoch wake up wake up!!! it's already late. How long are you gona sleep. We need some more wore/news/.Get some thing what the hell.

Anonymous said...

ደጀሰላሞች በመጀመሪያ ይሄንን ክብር እንድናይ ለፈቀደልን ቸርነቱ የማያልቅበትን አምላካችን እግዚአብሄር አናመሰግነው!

በጥምቀት በዕል አከባበር ወቅት በእኛ አጥቢያ በሚገኘው የቅዱስ እሩፋኤል ቤተክርስቲያን ወጣቱላይ ስለተፈፀመው ህሊና ቢስ ስራ የተሰማኝን ትንሽ ልበል ታቦተ ህጉ የከተራ ዕለት ወጣቱ ከተለመደው በተለየ መልኩ እጅግ ልብን በሚመስጥ ዜማ እና ወረብ ታቦተ ህጉን አጅበው ወደማደሪያው ሸኙት የበዓሉ ዕለት ታቦተ ህጉ ይመለስበታል ተብሎ በሚጠበቅበት ህዝቡና ወጣቱ እንደተላመደው ምንጣፋቸውን እያነጠፉ ሲሄዱ ታቦተ ህጉ ከተለመደው በተለየ ፍጥነት መስመሩን ቀይሮ ሄደ ያ ለምን አንደሆነ እስካሁን ግልፅ ባይሆንም በጣም የሚያሳዝነው ወጣቱን ድጋሚ ማግኘት አለመቻላችን ነው ያም ማለት ወጣቱ እንባውን እያፈሰሰ ታቦተ ህጉም ያለምንም ክብር 7.40 ሰአት ላይ ተሩዋሩጦ ወደ በአቱ ሲገባ ወጣቱ ለክብረ በአሉ ያሳይ የነበረው ተነሳሽነት እና ትብብር ምንም ያህል ግምት ውስጥ ባለማስገባት በተለይም ቢተክርስቲያናችን ወጣቶችን በጣም በምትፈልግበት እና በፍቅር ወንጌልን አስተምራ ተተኪ ሀዋርያትን መያዝ ባለባት ወቅት ወጣቱ ተከፍቶ በአሉን ሳያከብር ያለፈበት ሆኖ አሌፎአል ደገሰላሞች ይህንን ምን ትሉታላችሁ?

የደገሰላም ተከታታይ.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)