January 13, 2011

ፍርድ ቤቱ ተማሪዎቹ የይቅርታ ጥያቄቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ወይም ‹ጥፋታቸውን› አምነው እንዲከራከሩ ምርጫ ሰጠ

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 13/2011፤ ጥር 5/2003 ዓ.ም)፦ በልደተ ክርስቶስ የበዓል ዋዜማ አከባበር ጋራ በተያያዘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ‹‹ሁከት ቀስቅሳችኋል›› በሚል ለእስር የተዳረጉ 18 ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡

ተማሪዎቹ ታኅሣሥ 30 ቀን 2003 ዓ.ም የይቅርታ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለፍርድ ቤቱ ቢያመለክቱም ‹‹ያልተሟላ›› በሚል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ‹‹የተሰጣችሁን ምክር አልተቀበላችሁም፤ ጥያቄያችሁም ጥፋታችሁን አምናችሁ በግልጽ ይቅርታ የጠየቃችሁበት አይደለም›› ያለው ፍርድ ቤቱ ‹‹ወይ ጥፋታችሁን አምናችሁ የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር ይቅርታ ጠይቁና ጉዳያችሁ በዚሁ ይለቅ አልያም ጥፋተኛ አይደለንም ብላችሁ ተከራከሩ›› በሚሉ ሁለት ምርጫዎች ላይ ተማሪዎቹ ወስነው ለመጪው ዓርብ ጥር ስድስት ቀን 2003 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

በሁለት ምድብ (ዘጠኝ፣ ዘጠኝ) ተከፍለው ከችሎቱ የቀረቡት ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው የሕንፃ መስተዋቶች ላይ በደረሰው ጥፋት አለመሳተፋቸውን፣ በምትኩ ከጥበቃ አባላት እና ከካፊቴሪያው ሠራተኞች ጋራ የማረጋጋት ጥረት ማድረጋቸውን፣ ተፈታኝ እና ተመራቂ በመሆናቸው ከትምህርታቸው ተስተጓጉለው ለሀገር እና ለቤተሰቦቻቸው ሸክም እንዳይሆኑ ጥፋት ቢገኝባቸው እንኳን ዩኒቨርሲቲው በአባታዊ ተግሣጽ (ማስጠንቀቂያ) እንዲያልፋቸውና በፈተናው ለመቀመጥ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

ይሁንና ይህ ‹‹ፖሊስን ሐሰተኛ፣ ዩኒቨርሲቲውን ተጠያቂ የሚያደርግ እና ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ አስመስሎ የሚክድ›› በመሆኑ ተማሪዎች በተሰጧቸው ሁለት ምርጫዎች ላይ ውሳኔያቸውን ይዘው ከነገ በስቲያ እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ እና ከሁከቱ ጋራ በተያያዘ እፈልጋቸዋለሁ ያላቸውን ቀሪ ተጠርጣሪዎች ይዞ ለማቅረብ ተጨማሪ ሰባት ቀናትን የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ሁለት ቀናትን ብቻ ሰጥቶታል፡፡ ለፈተና መቀመጥን በተመለከተ ባሉበት ሁኔታ ለተማሪዎቹ እንደሚያስቸግራቸው ፍርድ ቤቱ ገልጾ ይሁንና ከፖሊስ ጋራ በመነጋገር በጠባቂ ሄደው ፈተናውን ለመውሰድ እንደሚችሉ መፈቀዱ ተገልጧል፡፡

በሌላ በኩል ታኅሣሥ 30 ቀን 2003 ዓ.ም በዚያው በአራት ኪሎ ካምፓስ በድብደባ ጉዳት ካደረሱት አንዱ እና በሁከቱ ስፍራ ስለት ይዞ የተገኘው ሌላው ተማሪ በድብደባ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በዛሬው ችሎት የቀረቡ ሲሆን ጉዳያቸው በተመሳሳይ አኳኋን (በይቅርታው ጥያቄ) እንደሚታይ ከችሎቱ እንደተገለጸላቸው ተዘግቧል፡፡

9 comments:

The Architect said...

ፍትህ አልባዋ ዓለም እጅና እግርን አሥራ በፍርድ ወንበር ፊት ስታቆም እናንተ የመጀመሪያም የመጨረሻም እይደላችሁም፡፡ ነቢያትን እንዲሁ አድርገውባቸው ነበር፡፡

ቤዛ ኣዳም ክርስቶስን እነኳ ሳታፍር እና ሳትፈራ በግፈኞች የፍርድ ወንበር ፊት አቁማዋለች፡፡ ሐዋርያቱስ ቢሆኑ ክስ እና ፍርድ መች ቀረላቸው!

ከምንወርሳት ርስት ንግስተሰማያት ጋር ስትነጻጸር ይህች ኢምንት በሆነች ፈተና በእምነት እነዳትዝሉ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ጽናቱን ያድላችሁ፡፡

"ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።

እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤

ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።" ሐዋ.5:40

Anonymous said...

Dear Brothers;
There is only one way out, do focus on your goal education while u are in university. I advise you to admit your mistakes, as what you have done is never acceptable by any one with right mind and request pardon from the university and go back to your studies before it is too late.

Debras

H/meskel said...

ante degmo min bet neh hidna iza asabk wendmochachinin yememker bikatu yelehim, hidna yemtasferarawun asferara. timhrt ke hiywet behuala mehonun zenegah? indante hodam wendmoch aydelum beka ziga...

Orthodoxawi said...

Ananiya, Azariya ena Misaelin ke esat yadane Amlak, Melaku Kidus Gebrelin yilakilachihu!

Ewnet Tashenfalech!

Ke enante gar yalut ke enersu gar kalut yibeltalu!

God Be With U, dear brothers!

Haylemikael ze5kilo said...

we are always there with U in soul brothers and pray.MAY God be with u!
"YEZEMENU SEMATNET YEHE NEWE",
"CHRESTIAN ENA MISMAR SIMETUT YETEBKAL"

dinbe said...

ምንም እንኳ የቆማችሁላት ቤ/ክን መሪዎች ዝም ቢሉም እግዚአብሔር አሁን ምልክት ባያሳይም ለመታሰራችሁ ማንም የሰባዊ መብት ተሟጋች ባይጮህም ቤተክርስቲያን ግን ስብከተ ወንጌልን ባነሳቸና በዘከረች ቁጥር ታሪካችሁ ሲወሳ ይኖራል በኛም ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላችሁ እውነተኛ ክርስቲያኖችም ይህን አይረሱትም......

Anonymous said...

For us the students are brothers with holly cause but for a legal entity they are just criminals. You see the difference?

Anonymous said...

there is no justice and freed of worship in ethiopia. including ,the headof ethiopian orthodox church doesn't believe by the church adm. and priniciple. i am deeply sorry for folish students. i know God with them everyday , but i don't support them going to "Tekely bete kehenet" one which is corapted with EPDRF or weyane.

Anonymous said...

aye no justice in Ethiopia.we know what is going on in our country just to abolish Cristian.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)