January 6, 2011

ልደትን በግቢያቸው እንዳያከብሩ በመታገዳቸው የተቃወሙ ተማሪዎች በፖሊስ ታግተዋል

  • ትናንት ሌሊቱን ከአ.አ.ዩ አራት ኪሎ ካምፓስ ከተወሰዱ ተማሪዎች 21ዱ አልተመለሱም፤
  •  በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ እግድ ተላልፏል፤
  •  ከተማሪው ተወካዮች ጋራ የተወያዩት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሐላፊዎች የዩኒቨርሲቲውን  አስተዳደር አነጋግረዋል፤
  • ‹‹እግዱ በሃይማኖታዊ ማንነታችን እየደረሰብን ላለው መድልዎ አስከፊ መገለጫ ነው፡፡››  (ተማሪዎች)                
  • ‹‹ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚ ተቋም እንጂ ቤተ ክርስቲያን አይደለም፡፡›› (አስተዳደሩ)
 (ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 6/2010 ታኅሣሥ 28/2003 .)ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል ልደተ እግዚእ እና ትንሣኤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድ በድምቀት ሲከበሩ ቆይተዋል፡፡ ከበዓላቱ አስቀድሞ ያሉትን መዋዕለ አጽዋማት ሲከታተሉ የሚቆዩት ተማሪዎቹ በዋዜማው እኩለ ሌሊት ላይ ከሚከናወነው ሥርዓተ ቅዳሴ አስቀድሞ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በሚገኙ አዳራሾች በዓላቱን የተመለከቱ የሥነ ጽሑፍ፣ ቃለ ስብከት እና መዝሙራት ዝግቶጅችን በማቅረብ ማክበር ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላም በየካምፓሶቻቸው የመመገቢያ አዳራሾች በአንድነት በመታደም የተዘጋጀውን ማዕድ ይሳተፋሉ፤ ከዚሁም ጋራ በዓላቱን የተመለከቱ ሥነ ትርኢቶችን በማቅረብ ይማማራሉ፤ መልእክቶችን እና ልምዳቸውን ይለዋወጣሉ፡፡ በአንዳንድ ግቢዎችም ልዩ መርሐ ግብሮቹ በበዓላቱ ቀን በሚኖረው የምሳ ሰዓት ቀጥለው የሚውሉበት ተሞክሮም የዳበረ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ዝግጅቶች የተቋማቱ አስተዳደር ይሁንታ ያለባቸው፣ በብዙዎቹም ላይ የዩኒቨርሲቲው ባለሥልጣናት የተማሪዎቻቸው የክብር እንግዳ ሆነው የሚታደሙባቸው፣ የዛሬውን ትውልድ ከ‹‹ያ ትውልድ›› ጠባይ ጋራ በማነጻጸር ዝንባሌውን የሚያደንቁባቸው በመጨረሻም ከተማሪዎቹ ጋራ ተመራርቀው የሚሸኛኙባቸው፣ ከወላጆቹ ርቆ ለሚገኘው ተማሪም መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ መድረኮች እንደሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡
ይሁንና ሰሞኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ግቢ ፋካልቲዎች ጨምሮ በአንዳንድ የክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየሆነ ያለው ነገር ግን ይህን በጎ ልምድ የሚሰርዝ ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 የተደነገገውን ‹‹የመንግሥት እና ሃይማኖት መለያየት›› እንዲሁም ‹‹ዩኒቨርሲቲዎች አካዳሚያዊ እንጂ የእምነት ማራማጃ ተቋማት አለመሆናቸው›› መሠረት ማድረጉ የተነገረለት ይኸው የእግድ ውሳኔ ለልደት በዓል ጥቂት ቀናት በቀሩበት ሁኔታ እንደተሰማ የሁለቱ ፋካልቲዎች ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ለተማሪዎች ዲን አቅርበዋል፡፡ ቀደም ሲል በተያዘው ልምድ የልደት በዓል ከሌሊቱ ቅዳሴ አስቀድሞ በስድስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ እና አምስት ኪሎ ካምፓሶች የሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት በተገኙበት በአምስት ኪሎ ቴክኖሎጂ ፋካልቲ አዳራሽ በጋራ መርሐ ግብሮች ይከበራል፡፡ ከጸሎተ ቅዳሴው በኋላ ደግሞ ተማሪዎቹ በየግቢያቸው የመመገቢያ አዳራሽ በመታደም የተዘጋጀውን ማዕድ ይሳተፋሉ፡፡ በዘንድሮውም ዓመት ይሁንታው ተገኝቶ መሰናዶ እየተደረገ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ይህ ሁኔታ ከዚህ በኋላ እንደማይቀጥል በመጥቀስ ለተማሪዎቹ ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ልምዱ ቀደም ብሎ የነበረና በዚሁ ዓመት በዓላቸውን ላከበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች መርሐ ግብሩ እንዳልተከለከለ በመጥቀስ የተቃወሙት ተማሪዎቹ ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ለበዓሉ የቀረውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ አስተዳደሩ ውሳኔውን እንዲያጤነው ትላንት እስከ 10፡00 ገደማ ምላሽ ሲጠባበቁ ይቆያሉ፡፡ ወዲያውም ደግሞ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አምርተው ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በማግኘት ቤተ ክህነቱ እነርሱን ወክሎ የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር እንዲያነጋግርላቸው ይጠይቃሉ፡፡
ተማሪዎቹ እስከተባለው ሰዓት ድረስ አንዳችም ምላሽ ባይሰጣቸውም በካፊቴሪያው ከመመገብ ተከልክለው፣ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ቀጥለው መፍትሔ ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ቢውሉም እነርሱን ሊወክሉ የማይችሉ እና ጥረታቸውን ለማኮላሸት ‹‹ድብቅ ዓላማ›› ያነገቡ ጥቂት ተማሪዎች ድንጋይ በሕንፃ መስተዋቶች ላይ በመወርወራቸው እና በመጮኻቸው የፖሊስ ኀይል ወደ ግቢው መዝለቁን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም አስረጅ አድርገው የሚጠቅሱት ማምሻውን ምግብ ሳይመገቡ እና ጥያቄያቸው ሳይመለስላቸው በዋሉት ኦርቶዶክሳውያን ላይ አንዳንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ሊዘብቱ በመሞከራቸው በተነሣው ውዝግብ በግቢው የነበረው የፖሊስ ኀይል ተማሪዎችን በየሕንፃው ከፋፍሎ በማስገባት ተቃውሞው እንዲህ ያለ ብጥብጥ ለማስነሣት የታቀደ መሆኑን፣ ከዚህ በኋላ በእንቅስቃሴው ሲሳተፍ የሚገኘውን ተማሪ በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ቅጽ ሲያስፈርም ቆይቶ እኩለ ሌሊት አካባቢ ከሦስት እስከ አምስት በሚደርሱ መኪኖች ቁጥራቸው ከአንድ መቶ የማያንሱ ተማሪዎች በጃንሜዳ፣ አራት ኪሎ እና ጊዮርጊስ አቅራቢያ ወደሚገኙ የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያዎች ተጭነው መወሰዳቸውን ነው፡፡
ዛሬ ጠዋት ሌሊት የተወሰዱት ወንድሞቻች እንዲፈቱ ለመጠየቅ የተቀሩት ተማሪዎች ‹‹በሰልፍ ከግቢው ለመውጣት ሞክረዋል›› በሚል የመግቢያ በሮችን በመዝጋት በግቢው ውስጥ ያሉት ወደ ውጭ እንዳይወጡ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ውጭ የተወጡት ደግሞ ተመልሰው እንዳይገቡ ተከልክለው ማርፈዳቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ከትናንት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ጋራ የተነጋገሩት የተማሪ ተወካዮች በአድራሻ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር በግልባጭ ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትን ጨምሮ ለዘጠኝ አካላት ችግሩን የሚያስረዳ እና መፍትሔው የሚጠይቅ ደብዳቤ አሰራጭተዋል፡፡
የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የዋና ሥራ አስኪያጁ ቢሮ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ውሳኔውን አጢኖ ተማሪዎቹ በተለመደው አኳኋን በዓሉን በግቢያቸው እንዲያከብሩ ይፈቅድ ዘንድ መጠየቁ የተዘገበ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር ሐላፊነቱን ዩኒቨርሲቲው እንደሚወስድ አሳስቧል ተብሏል፡፡ የሦስቱ ካምፓሶች ተወካዮች በበኩላቸው ጥያቄያቸው ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ በአቋማቸው እንደሚቀጥሉና ምናልባትም በዓሉን በተለመደው አኳኋን እንዳያከብሩ የተላለፈው እግድ ከጸና የዋዜማውን ዝግጅት እና ከቅዳሴም በኋላ የሚኖረውን መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ማካሄድ የሚችሉበትን ፈቃድ ከዋና ሥራ አስኪያጁ ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለበዓሉ የሚኖረው የምግብ ዝግጅት እንዳልተከለከለ የተነገረ ቢሆንም ለአከባበሩ የሚደረጉ የልዩ መርሐ ግብር ዝግጅቶች ግን መታገዳቸው ታውቋል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች በተመሳሳይ ሰዓት ለሚያደርጉት ዝግጅት ቀደም ብሎ የአዳራሽ ፈቃድ በመጠየቃቸው ነው›› ተብሏል፡፡ ‹‹በሦስት የክርስትና እምነቶች የአዳራሽ ጥያቄ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ›› የተገለጸው የዩኒቨርሲቲው (ኢንጂነሪንግ ፋካልቲ) አስተዳደር  ተቋሙ ‹‹ሃይማኖትን፣ ፖሊቲካን እና ብሔርን ማእከል በማድረግ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ነጻ መሆን እንዳለበት›› በመግለጽ ቅድምና የነበረውን የኦርቶዶክሳውያን በዓል አከባበር ልምድ አግዷል፡፡ በወላይታ ሶዶ እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዎችም ይህን መሰል ርምጃዎች ስለመወሰዳቸው ዘግይተው የደረሱን ጥቆማዎች ያስረዳሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ የችግሩን ሁነኛ መንሥኤ እና አስተያየታቸውን የተጠየቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንዳንድ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት የትንሣኤ በዓል አከባበር ወቅት በስድስት ኪሎ ካምፓስ ልደት አዳራሽ በግድግዳ ላይ ተለጥፈው የነበሩ ጥቅሶች ከተጻፉባቸው ቋንቋዎች ጋራ በተያያዘ ተነሥቶ የነበረው ውዝግብ ለውሳኔው መነሻ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ መንግሥት ከሚያስቀምጣቸው ስጋቶቹ አኳያ ከእምነት ጋራ ተያይዘው የሚፈጠሩ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልም ሌላው አስተያየት ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ አዎንታዊነታቸው ጉልሕ ሆኖ የሚታዩ ልምዶችን ማበረታታት ሲገባ መድልዎ በተሞላባቸው አካሄዶች ማኅበራዊ መስተጋብሮችን የሚያሻክሩ፣ አንዳችም ጠቀሜታ የሌላቸውን እግዶችን መውሰድ የውሳኔዎችን ቀናነት ጥያቄ ላይ እንደሚጥል እና ከፍተኛ ቀውስ እንደሚፈጥር አስተያየት ሰጭዎቹ አሳስበዋል፡፡ ከኅቡእነት ወደ ግልጽነት፣ ከግለሰብነት ወደ መዋቅራዊነት በመሸጋገር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ግልጽ አደጋን የጋረጠው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እርሾም ቤተ ክርስቲያኒቱን በሁለንተናዋ ለማዳከም በተያያዘው መንገድ በዚህ ዐይነቱ ውዝግብ ውስጥ እጁ ላለመኖሩ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም፡፡

12 comments:

Anonymous said...

ትናንት በሰጠሁት አስተያየቴን እጸናለሁ። ነገርግን ጉዳዩ ገና በጧቱ ያለምነው ስለሆነ ምንም ባያስገርምም ከባዶ ተነስቶ ልጆቻችንን ያሰረ አካል በአስቸኳይ ብቻ ይፍታልንna ከዛ በሗላ ምን እንደምንሰራ እንመካከራለን።

Then after, never and ever will have negotation with the Govn't by our Orthodox Faith!

zekristos

Anonymous said...

The government should see deeply each and every point befor giving the final dicision,with out convincing and reasonabl justification the student should not prohibited to celebret as usuall the national festival.

GOD bless Ethiopia

Anonymous said...

Thank God for giving this temptation. I believe after the dark there is light, as Christian after this kind of thing we will see better life. So our brothers and sisters be patient. I wish you happy Christmas.

Anonymous said...

ወገኖቼ ፤
መጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ፤

ብልህ እንሁን፤
ሰሞኑን መንግስት አንድ የጀመረው ነገር ያለ ይመስለኛል። የደርግ ባለሥልጣናት ይቅርታ፤ አሁን ደግሞ የልደት በአል በካምፓሶች በተመለከተ። በተለይ የመጀመሪያው ጉዳይ ስንት ችግር ባለባት ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ፕራዮሪቲ መሆን አልነበረበትም።

አሁን ቅዱስ ፓትሪያርኩና የቤተክህነት ሃላፊዎች፤ በጉዳዩ ይገባሉ። ችግር ፈችዎችም መስለው ይታያሉ። ይህ የነርሱን ሥም ለማደስ የተደረገ፤ አሜሪካኖች፤ ፕ፤አር የሚሉት፤ የህዝብ ግኑኝነት ሥራ ነው።

ስለዚህ ሁሉን ነገር ሥሜታዊ መልስ ከመስጠት፤ አጥንተን መመለስ አለብን። ያለዚያማ፤ አንዳንድ ነገር እየፈጠሩ፤ ጉልበታችን አሟጠው ሊያዳክሙን ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን። እመ ብርሃን ትታደገን።

tad said...

Religion shouldn't control every aspect of our life.Churches for prayer and Universities for research and reasoning.Please don't over react.We better concentrate on resolving the difference b/n orthodox leaders.
Secterian cells here and there are not good for our common good.

Anonymous said...

This is a very good start. It should continue and for once and for all shall cut links of the mafias under various religion curtains.
These students have forgotten their purpose to perform debteraisim they shouldn't have been there. Washera would be the best option and i think is still open. I would like to advise these so called students to leave the space for those who wanted to learn and change the current track of the country which is leading to the worest poverty.
Debteraizm has held ethiopia hostage for years and shall be stopped and here is the start.

God save Ethiopia from debteras.

Anonymous said...

ወገኖቼ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ፤በጣም ግን ይገርማል። በትምህርት ቤቶችና በመስሪያ ቤቶች ያለተደራጁ የእምነት ድርጅቶች እንደፈለጉ ከ2-6 ሰው በማቀናጀት በ cell ደረጃ ስለፈልጉት ጉዳይ ያስተምራሉ ይቀስቅሳሉ፤ ማንም ግን ሃይ አይላቸውም።

በተቃራኒው ግን ስለምን እንደተሰበሰቡ በይፋ የሚታወቁት ግን ይከለከላሉ።

Jesus IS Lords of Lord Kings of King. He is the Master of Our Church.

With Love

Anonymous said...

ማህበረ ቅዱሳን ዝምታው ምንድን ነው?

Anonymous said...

Well Melkam be'al for all of us.I am surprised to see some body considering this 'debteraism'. What is 'debteraism'? It is better to know what a word means and whether it is fit for a certain context or not before we use it.If the anonymous person who commented is saying that students should be atheists to be of any value to Ethiopia, that is a different story. And in all cases they should choose themselves to be atheist, protestant, Orthodox etc...It should not be forced upon them by a system.These students used their right to follow the religion they follow and they must have complete right to celebrate the major holiday of their religion in the place they live.
Egzeabher yetaserutin yasfetalin. Amen!

Anonymous said...

EFRET KERA MALET NEW BE AGERACHEW BEAL ENDAYAKEBIRU MEBTACHEWIN YETEGEFEFUT KETAYU GUZO MIN LIHON NEW CHEKAGNOCH EMNETE BISOCH NACHU AMERAROCH BEMULU

Anonymous said...

ማኅበረ ቅዱሳን ምን ይበል ? ይህ የመናፍቃን ስውር ደባ ነው ። ወገኔ ምህረት የእግዚአብሔር ነው ፣ ይህ አይነቱም ጋኒን ያለፆምና ፀሎት አይወጣምና ሁላችንም በአንድ ልብ ሁነን ወደቸሩ እግዚአብሔር እንጩሁ ስራውን እሱ ይሰራል።”እኛ ባሮቹ ተነስተን……………የሰማይ አምላክ ያከናውናል”

Anonymous said...

The government is looking every thing from only one direction. I think that is not right and will not be right always.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)