January 3, 2011

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች "ለደርግ ባለሥልጣናት" ይቅርታ እንደማያደርጉ አስታወቁ

(በዘካሪያስ ስንታየሁ/ 02 January 2011; ሪፖርተር ጋዜጣ):- በደርግ ባለሥልጣናት የተገደሉት ስድሳዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች፣ ለደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት ይቅርታ እንደማያደርጉ ባለፈው ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ለአቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ የስድሳዎቹን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦችን በደርግ ባለሥልጣናት የይቅርታ ጉዳይ ላይ ሊያነጋግሯቸው በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ረቡዕ የቀጠሯቸው ቢሆንም፣ አቡኑ ከቁልቢ ገብርኤል ለቀጠሮው መድረስ ባለመቻላቸው፣ የቀጠሮው ቀን ወደ ሐሙስ ሊተላለፍ ችሏል፡፡

የስድሳዎቹ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ግን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በሚገኘው የባለሥልጣናቱ የመታሰቢያ ሐውልት ተገኝተው ከተወያዩ በኋላ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ቤተሰቦቹ የተስማሙበትን የአቋም መግለጫ ለአቡነ ጳውሎስ ሐሙስ ዕለት በፓትሪያርኩ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው አንብበውላቸዋል፡፡ በመግለጫው መሠረት፣ የደርግ ባሥልጣናቱን ይቅርታ በተመለከተ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠ ገደብ ስላለ ቤተሰቦቹ ይቅርታ ማድረግ እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የሕገ መንግሥት ገደብ በመኖሩ የሃይማኖት አባቶቹ እኛን አስማሙም፣ አላስማሙም፣ ገደቡን ማለፍ እስካልተቻለ ድረስ በዚህ ጉዳይ ይቅርታ ልትጠይቁን አትችሉም፤›› ሲሉም በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

‹‹ስለሆነም ለዚህ ጉዳይ ሕጉ ቀዳዳ ስለሌለው ራሱ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ደግሞ ረጅም ጊዜ ከመጠየቁም ባሻገር አስቸጋሪ ነው፤›› ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቤተሰብ አባል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹የሃይማኖት መሪዎቹ የደርግ ባለሥልጣናትን ይቅርታ እንዲደረግላቸው እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን እኛ የሰማነው በጋዜጣ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ተቃውሟችንን በማሰማታችን አቡነ ጳውሎስ ሊያነጋግሩን ችለዋል፤›› ሲሉ ግለሰቡ ገልጸዋል፡፡

የስድሳዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦችም ለደርግ ሥርዓት ይቅርታ እንዲያደርጉና ብሔራዊ እርቅ እንዲሆን ከሆነ ሌላ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፣ የደርግ ባለሥልጣናቱ ወንጀለኛ ተብለው ፍርድ እየተፈጸመባቸው ባለበት ሁኔታ ለእነርሱ ይቅርታ ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም አቡነ ጳውሎስ የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን እኚሁ ግለሰብ ገልጸዋል፡፡

የባለሥልጣናቱ ቤተሰቦቹ ለአቡነ ጳውሎስ ያስተላለፉትን የአቋም መግለጫ አንብበው ከተወያዩ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት ለመወያየት ከጥምቀት በዓል በኋላ ለመገናኘት ተስማምተው ተለያይተዋል፡፡
++++++++++++++

‹‹የሃይማኖት አባቶች በጀመሩት መንገድ ይቅር መባባሉ መቀጠል አለበት›› (አቶ ሞላ ዘገዬ፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ)

19 comments:

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ የፖለቲካ ዘፈን ለመደነስ መድረክ ፈለጋ የሚያደርጉት ውዥምብር ነው

በሳውዝ አፍሪቃ በቺሊ እንዲህ አይነት አገር አቀፍ ይቅርታ ከመደረጉ በፊት ምን አይነት ምርመራ ምስክርነት ተሰማ
ምን ተመዝግቦ ተያዘ ብለው የጉዳዪን ክብደትና ጥልቀት ሳያውቁ

የሊቀ ጳጳስ ዴዝኖንድ ቱቱ ኮሚሽን ምን ሰራ ብለው ሳያጠኑ

መጀመሪያ ----
አባ ጳውሎስ መጀመርያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ላደረሱት በደል ላደረሱት የሃይማኖት ሕጸጽ - የጣዖት ድንጋይ ምስል ማቆም
የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ሲኖዶሱን ማርከስ ስራ አቁመው ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ሳይጠይቁ

አሁን ደግሞ እነ ሊቀ ጳጳስ ዴዝኖንድ ቱቱ ለመምሰል

የይቅርታ ሳይሆን የፖለቲካ ውዥንብር ተያይዘዋልሪፖርተር፡- የሃይማኖት መሪዎቹ የተጐጂ ቤተሰቦችን አነጋግረን ይሁንታ አግኝተናል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከ60ዎቹ ባለሥለጣናት ቤተሰቦችና የስቃይ ሰለባ ነበርን የሚሉ ወገኖች ምንም የሰማነው የለም ነው የሚሉት፡፡ እርስዎ ይህንን ጉዳይ ከየት ሰሙት?

አቶ ተሾመ፡- ከእናንተ ጋዜጣ ነው የሰማሁት፡፡ ስልክ ደውዬ ይህን ወሬ ከየት አመጣችሁት? አልኩ፡፡ አብረን ከታሰርነው መካከል አንዳንዶቹን ስጠይቅም የነገሩኝ ምንም እንደማያውቁ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ በበኩሌ ማንም የጠየቀኝ የለም፡፡

ሪፖርተር፡- በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ወንጀል ፈጸሙ የተባሉት የደርግ ባለሥልጣናት በሕግ ፍርድ ካገኙ በኋላ ይቅርታ ይደረግላቸው ሲባል እርስዎ እንደዜጋ፤ ሌሎች ተጐጂዎችም እንደዚሁ የሚፈጥርባችሁ ስሜት ምን ይመስላል?

አቶ ተሾመ፡- እንደዚህ ተብሎ የሚጠየቅላቸው እነሱ ማናቸው? ምንስ የሞራል ብቃት አላቸው? የእኔ ጌታ እንዴት ነው ነገሩ? ደርግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያንን ሁሉ ድግስ ደግሶ ሲፈጅ፤ በየአደባባዩ ስብሰባ ላይ እየተገኙ ሞገስ የሰጡ የሃይማኖት አባቶች እንደዚሁ ሸንጐ ውስጥ የሶሻሊስት መሐላ እየማሉ ገብተው ከእሱው ጋር ሲዶልቱ የነበሩ ሰዎች፤ ጳጳስን የሚያህል ንጉሥን የሚያህል ህፃን ሳይቀር ሲጨፈጭፉ አሁን ያሉት ሰዎችስ ምነው ቢያስቡበት? ለመሆኑ በየትኛው ውለታቸው የእኔ ጌታ ይቅርታ የሚለመነው? ጣሊያኖች መጥተው የኢትዮጵያን ሕዝብ በሚጨፈጭፉበት ጊዜ ለመዋጋት አንድ ጳጳስ ወጡ፡፡ ተያዙና ለጣሊያን ተገዙ ብለህ ስበክ ይባላሉ፡፡ ሕዝብ በተሰበሰበበት ለጣሊያን የተገዛህ የተኮነንክ ሁን ብለው አወገዙ፡፡ ጣሊያንም ተኩስ ብሎ አዘዘ፤ ጳጳሱም ሞቱ፡፡ እኛ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ይባላሉ፡፡ ሐውልታቸው ይኼው እየታየ ነው፡፡ እኔ የማውቀውና የምወዳቸው የሃይማኖት አባት እኚህ ናቸው፡፡ የሕዝብን ጥቃት የራሱ ጥቃት አድርጐ የሚያይ አባት ማለት እንደሳቸው ነው፡፡ የአሁኑ ታዲያ ምን ማለት ነው?

ሪፖርተር፡- ሰዎቹ እኮ ለጥፋታቸው ተጽጽተናል ብለዋል ነው የሚባለው፡፡
አቶ ተሾመ፡- አላሉም፤ ያሉላቸው እነሱ ናቸው፡፡ እኔን አንድ ቀን እንኳ በዚህ ጉዳይ መጥቶ የጠየቀኝ የለም፡፡ እነዚያ ግን እንደወገን ታይተው ይቅርታ ይጠየቅላቸዋል፡፡ ሕጉ ያስቀመጠውን ጥሰው እንዴት እንደዚህ ይሠራሉ?

Anonymous said...

ይቅር ለእግዚአብሔርም ….. በቦታው፣ በጊዜውና፣ በባለ ጉዳዮች ቢሆን፤ ቤተ/ክርስቲያናችንም ከዚህ ጉዳይ ቢያንስ በዚህ ወቅትና ከዚህ አቀራራብ እራሷን በታርቅ


በጥቅሉ ይቅር መባባል ጥሩ ቢሆንም፤ የጅምላ ይቅርታ ግን አንድም ያለ-ባለጉዳዩ ሌላውም ከበስተጀርባው political advantageous ጠባይ ያለው እንዳይኖር እሰጋለው።
የመቶ ሺ ዎች ወጣቶች ደም እንደ እንስሳ በየጎዳናውና በየጉድጓዱ የፈሰሰበትን ዘመንና ሐዘን እንዲሁ እንደዋዛ / እንደ አንዳንዶቹም ‘ባንሳልቅበትም’ ጥሩ ነው። የደቡብ አፍሪካን፤ የሰርቢያን፤ ወይም የሌላ ሀገርን ተመክሮና ምሁራዊ መፍትሔ በመስጠትም የሚሽርም ባይመስለን የትሻለ ነው። ከሆነም ደግሞ በዘመናችን በቺሌ፤ በኤንዶኔዥያ፤ በቅርቡም በአርጀንቲና የተከሰተውን ማስተዋሉም ደግ ነው። በተለይ፤ በተለይ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመስጥት ለሚፈልጉት ብዙም የምለው ባይኖረንም (ድርጊቱም ፖለቲካል ይዘት ያለው ነውና) ነገር ግን ቤተ/ክርስቲያናችን ከዚህ ጉዳይ ቢያንስ በዚህ ወቅትና አቀራራብ እራሷን ማራቅ አለባት። …. ካልሆነ ግን በብዙ ቤ/ክ በር ላይ (በየክፍለ ሀገሩ)፤ ለምሳሌ በአአ በተ/ሃይማኖት፤ በቅ/ጊዮርጊስ፤ በቅ/ቂርቆስ፤ በቀጨኔ መድሃኔ ዓለም፤ በአማኑኤል፤ … ብጎንደር፣ ብሲዳሞ፣ በጅማ፣ በድሬድዋ፣ በደ/ማርቆስ፣ ወዘተ ቤተ ክርስቲያኖች ደጅ ለጠፋው የሰው ልጅ፤ ያውም የብዙ ሺ ወጣቶች ሕይወት ቤ/ክ/ ቤ/ክህነት ያሳየችው የ- ዝምታ መንፈስ ከማስታረቁ የከበደ ይመስለኛል። ….
….. አልያ ግን፤ በግፍ የተቆረጡ ጡቶች፤ በምስማር የደሞ ጆሮዎች፤ በዘይት የተጠብሱ ሰውነቶች፤ በስለት የጠፉ ጨቅላ ዐይኖች፤ የተተለተሉና የሚያሳሱ ስስ እጆች፤ የለጋ ወጣቶች ህይወት፤ ……
እስከዛሬም የሓዘን ከላቸውን ያላወለቁ በብዙ ሺ የሚቆተሩ እናቶች፤
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አባቶች ልጆቻቸው በህይወት ይኑሩ ወይ ይሙቱ እስከዛሬ ሳያወቁ ከሓዘን ሲቃ ጋር የሚኖሩት፤
በብዙ ሺ የሚቆጠሩትም የወንድሞቻቸውን፤ የእህቶቻቸውንና የጓደኞቻቸውን ሞት ቀስ በቀስና በረጅሙ ለመርሳት እየጣሩ ያሉት፤
በስደትም በመቶ ሺ የሚቆጠሩትና ከዛ ክፉ ዘመን ተርፈው ግና እስካሁንም የሰላምና የእረፍት አዕምሮ ያልታደሉት፤ ….. ይታሰቡ እንጂ

ይቅር ለእግዚአብሔርም ….. በ’ዘመቻ’ አይሁን
የአባቶቻችን ጸሎት አይለየን
የሞቱን ንፍስ ይማርልን

ኤልያስ/ ዳላስ-ቴክሳስ

Anonymous said...

It seems that Deje..couldnt get chruch related news to publish. Now, they started to report on poletical issues by directly copping from the reporter newspaper. What if i give them some 'good' news about a 'SAINT' preacher called ZEMEDKUN...WILL THEY PUBLISH IT ? We will see! Here is a link...http://www.ethiochannel.net.et/278S2News.pdf

ዘክርስቶስ said...

ዕርቁ ከበስተጀርባው የፖለቲካ ረብን ለማስጠበቅ ነው የሚለው የአንዳንዶቻችን ጥቅል አባባል፡ ቢኖረውም መልካም ነው ባይ ነኝ አጀንዳው ለበጎ ተግባር ከሆነ። ነገርግን ለኔ ውስብስብ ያለ ሕልም ሆኖብኝ መፍታት ያልቻልኩት ቢኖር የቅዱስነታቸው ጉዳይ ነው። ለምን? ብትሉኝ በሞት ባይቀጡም ቁጥር አንድ የደርግ የሰባት ዓመት የእስርቤት ሕፃን ሆነው ያደጉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በአሁኑ ወቅት የአስታራቂ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሆነው የሚያገለግሉ ያሉ እርሳቸው ናቸውና እንዴት ለሚለው ጥያቄን ምናልባት የፖለቲካ ደባ የሌለበት ያስመስለዋል? ሚስጢሩ የሰማዩ አባት እስኪገልጥልን ድረስ።
የሆነ ሆኖ አንድ መሠረታዊ ነገር ለማለት የሚፈልገው ግን፦በደርግ ባለሥልጣናት ተጎቷል የምንለው ሕ/ሰብ ጎጂው አካል ከውጭ በመጣው ወራሪ ሀይል ሳይሆን ኢትዮጵያዊ-ወንድም ወንድሙን ነው የበደለው። አንድም በተራው የስልጣን ዕድልን አግኝቶ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ሰው፦ ድሀ፣ ገበሬ እያለ እየረገጠ የጠጅ መጠጫን ያዥ፤እንደ ተናጋሪ ዕቃ አድርጎ በመቁጠር ሰርቶ በላ ሳይሆን ሰርቶ የሚያበላw፣ እንዲያውም አልፎ ተርፎም አኝኮ እንዲያጎርሰው የቤት እመቤት ወፍጮ ቤት ሲያደርገው የታሪክ መጻሕፍትና አዛውንት ይናገራሉ።
ምን ለማለት ፈልጌ ነው “ሳንተዋወቅ አንተናነቅ” ነው ፍቹና ወይም “ላም እሳትን ወለደች እንዳትልሰው እንዳያቃጥላት እንዳትተወው ልጇ ስለሆነባት”ነው የሚባለው? አስተካክሉኝ ወንድሞቼ።
የሞተውንና የቆሰለውን ሁሉ እኛ ኢትዮጵያዊያን በወንድሞቻችን ኢትዮጵያዊያን፣ ብሎም ቂምን ቋጥረን ወደ መቃብር ሳንገባ ለነፍሳችንም ሆነ ለቀሪው ትውልዳችን በሀገሩ፣ በሐይማኖቱ፣በልማቱና በታሪኩ ኮርቶ እንዲኖር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሀገሮችም ትምህርት የሚቀስሙበት አትራኖስ ስለሆነ ፈጣሪያችን ክርስቶስ ፈትኖ የሰጠን ‘ዕርቅ’ ማድረግ በጠባብዋ በር ማለፍ መቻል ማለት ነው።
እውነትን ባልናገር ወዮልኝ!

Anonymous said...

The jury verdict in terms of public opinion is still out there as to whether Derg officials who have already served their terms of imprisonment should, in the final analysis, be forgiven and be released from prison.

What is even more important and is regrettably escaping our attention is the status of the main criminal in the highly tragic episode of the Derg regime and the murders it committed, namely, Dictator Mengistu Hailemariam. When will we Ethiopians and the whole international community ensure that, like other criminal dictators such as Yugoslavia's Milosovich, and Liberia's Taylor, Mengistu is also brought to face justice at the the International Court of Justice in the Hague?

While we are clamouring about criminals who are already in jail, the main perpetrator of injustice and genocide is laughing in a luxurious splendour in Zimbabwe.

How can we avoid the repetition of the same type of a dictatorial leadership in Ethiopia when we allow criminals like Mengistu to go scot free?!!!!

Think about it and act!

tewahido said...

Abun Paulose hoye ergite yaderegute yabatochachen yemeselale yenegna sele hayemanotachew silu angetachewn yesetutu

Gine sewen yekerta adergu yemil erasu bemejemeria yekerta biteyek melekam new !

Menew Yekeduse Sinodose meri Menfese Kiduse New belachihu astemerachihun yelem ende?

Tadiya enante bemenfese kiduse atamenume ende? wusanewun lemen ayefetsemem kalehone lela temehiret asetemerun.

Anonymous said...

አለባብሰው ቢያርሱ
በአረም ይመለሱ

A truth commission or truth and reconciliation commission is a commission tasked with discovering and revealing past wrongdoing by a government, non-state actors, and individuals, in the hope of resolving conflict left over from the past.
The report should also, provide proof against historical revisionism of state terrorism and other crimes and human rights abuses.

One has to be cognizant that the work of Truth Commissions are sometimes criticized for allowing crimes to go unpunished, and creating impunity for serious human rights abusers. Their roles and abilities in this respect depend on their mandates, which vary widely.

Mind you these religious leaders, such as Aba Paulos, have no mandate for this monumental and national task.

The issue, one among the many issues faced here is what should be the relationship between truth commissions and criminal prosecutions.

What do we know how others dealt with similar difficult national issue

What was done by the truth and reconciliation commissions of countries that suffered similar state terrorism and other crimes and human rights abuses?
o Argentina
o Chile
o El Salvador
o Ghana
o South Africa and other countries

This task should not be given to self-selecting groups.

As religious people they can pray for the criminals but they HAVE NO RIGHT and MANDATE for the task.

If left to them we the victims of The Red Terror are going to be victimized AGAIN.

When CAN WE say NEVER AGAIN when we don’t know the full scale of the crime?

What is the lesson for the generation to come.

Dillu said...

አቡነ ጳውሎስ ድሮም እኮ አሜሪካ ውስጥ ሁነው ወገንተኝነታቸው ለ2ቱም ነበር=ለደርግም ለወያኔም። ከወያኔ ለደርግ ከደርግ ለወያኔ መረጃዎችን ያቀብሉ እንደነበር መረጃዎች ኣሉ።
''ወኢያደሉ ለመንግስተ ሥርዓተ ገጽ ' ስለሆኑ አድልዎ አያውቁም ማለቴ ነው።

Anonymous said...

To begin with, is there a level ground for excueses? Are there ethically right persons to do this job?

Anonymous said...

It smells politics and fiction.

The De... said...

Shame on you for not featuring the attack against Egypt christians.

Anonymous said...

እውነተኛ ይቅርታ ለኢትዮጵያ !
በአንድ የደቡብ አፍሪካ የእርቅና የእውነት አፈላላጊ ፍርድ ቤት የተፈጸመ ታሪከ ነው፡፡ችሎቱ የበደል ሳይሆን የጸጋ ድንቅነት የታየበት ነበር፡፡የአፓርታይድ ሰለባዎች በሚበዙበት በዚያ ቀን በዋለው ችሎት ታላቅ ፀጥታ የነገሰበት ጉባኤ ቢሆንም እንደ እኛ ያለውን ኃጥተኛ የተቀበለውን ጌታኝ በማወደስም ፍርዱ ተጠናቋል፡፡ዳኛው በስተቀኛቸው ማዶ ላይ የተቀመጡት...ን የሰባ አመት አሮጊት‹‹በዚህ ሰው ምን ቢወሰንበት ይፈልጋሉ?››ሲሏቸው ሁሉም ለመስማት የጓጉ ይመስላል፡፡
እኚህን አሮጊት የወላድ መሐን ያደረጋቸው ሚስተር ቫንዳር ብሩክ የተባለ ነጭ ፖሊስ ነው፡፡ቫንደር ብሩክ ከአመታት በፊት ወደ እኚህ አሮጊት ቤት በመምጣት የአሮጊቷን ወንድ ልጅ በፊታቸው ከገደለው በኋላ በእሳት በማቃጠል ከግብራበሮቹ ጋር በፈንጠዝያ ይዘላል፡፡እንደገና ከወራት በኋላ በአንድ ምሽት በመምጣት ባለቤታቸውን ወደ አልታወቀ ሥፍራ ያወስዳቸዋል፡፡ለሁለት ዓመታት የባለቤታቸው ድምጽ ጠፋ፡፡ከሁለት አመት በኋላ ግን የዛሬው ተከሳሽ ቫንደር ብሩክ ወደ እኚህ አሮጊት በመምጣት በውል ወደማያውቁት ሥፍራ ይወስዳቸዋል፡፡ቦታው ባለቤታቸው የሚሰቃዩበት ምድራዊ ገሀነም ነው፡፡በዚያ ምሽት ባለቤታቸው በተፈለጠ እንጨት ላይ ተጋድመው ሲያጣጥሩ አዩአቸው፡፡ወሪያው እሳት ሲለኩሱባቸው‹‹አባት ሆይ ይቅር በላቸው›› የሚለው ድምጽ በመደጋገም ወጣ፡፡ሚስተር ቫንደር ብሩክ በዚህ የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን ፊት በደሉን ተናዘዘ፡፡በዚህ ጊዜ ነው ዳኛው ወደ ገረጡትና በድጋፍ ወደመጡት ባልቴት በመዞር ‹‹ምን ቢፈረድበት ይፈልጋሉ››ያላቸው፡፡እሳቸው ግን እርጋታና ሰላም በተሞላበት ድምጽ ‹‹የምፈልጋቸው ሦስት ነገሮች አሉ›› አሉ፡፡
በመጀመሪያ ‹‹ባለቤቴ የተቃጠለበት ቦታ ውሰዱኝና አፈሩን ሰብስቤ በማዕረግ ልቀብረው እፈልጋለሁ፡፡››ከቆይታ በኋላም ‹‹የነበረኝ ቤተሰቤ ባሌና ለጄ ብቻ ነበሩ፣በሁለተኛ ደረጃ የምፈልገው ሚስተር ቫንደር ብሩክ ወንድ ለጄ እንዲሆን ነው፡፡በወር ሁለቴ ወደ ደሃ ጎጆዬ መጥቶ ሙሉ ቀን እየዋለ በሕይወቴ ውስጥ የቀረውን ፍቅር በእርሱ ላይ ለማፍሰስ እፈልጋለሁ››አሉ፡፡‹‹ሦስተኛና የመጨረሻ ፍላጎቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ምህረት ለማድረግ ሕይወቱን በመስጠቱ ምክንያት እኔም ለሚስተር ቫንደር ብሩክ ይቅርታ እንዳደረኩለት እንዲያውቅ እፈልጋለሁ፡፡የባለቤቴም ፍላጎት ይኸው ነበር፡፡ስለዚህ አንዳችሁ ደግፉኝና ሚስተር ቫንደር ብሩክ አጠገብ ውሰዱኝና በእጆቼ አቅፌው ከልቤ ይቅር ማለቴን ልገልጽለት እፈልጋለሁ›› ብለው ጉዞ ሲጀምሩ ሚስተር ቫንደር የሚሰማውን መቋቋም አቅቶት ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡በፍርድ ቤቱ ውስጥ የነበሩት ዘመድ አዝማዶች የዚህ ሰለባዎች በዚህ መንገድ ይቅር ያለንን ጌታ ማመስገን ጀመሩ፡፡ደቡብ አፍሪካ የይቅርታንና የዕርቅን መንገድ ባትመርጥ ኖሮ እስከ ዛሬ በዚህ ልዕልናዋ ባልቆየች ነበር፡፡የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ታጋይ ማንዴላና የእርቅ ኮሚሽኑ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡በቀል ካሳ አይሆንም፡፡ዛሬም በምድራችን እንዲህ ያለ የእርቅ ተቋም ያስፈልገናል በአብያተ ቤተክርስትያናት ጠቦች ሙሉ በሙሉ መቀበር አለባቸው፡፡ግን ይህን ለማድረግ እግዚአብሄር እንዴት እነደወደደን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡አንዲት ቤተ ክርስትያን ወይም ኅብረት የምክር አገልግሎትና የአስታራቂዎች ቡድን በግድ ያስፈልጋታል፣ምእመናኖቻ ገና በፈተና ዓለም ነውና ያሉት፡፡ምእመናኖቿንም የማታሸንፍ ቤተ ክርስትያን ምእመናን የሏትም ማለት ይቻላል፡፡ማንኛውም ክርስትያን ቤተ ክርሰቲያኑ የትዳሩን፣የጥሉን፣የፖለቲካውን፣ ጉዳይ ልትፈታ እንደምትችል እንጂ እነደሚሳናት ቆጥሮ በዓለም ፊት ቢካሰስ ጌታን ያዋርዳል (1ቆሮ 6.1-8)፡፡ከዲያቆን አሸናፊ ከይቅርታ መፀሐፍ የተወሰደ
መታሰቢያነቱ እርቅና ይቅርታ ለሚገባቸው እና ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚህ አገልግሎ ለሚያውሉት በሙሉ ይሁን

Unknown said...

abune pawlos tir 1,1991 stpanos church yesgedelut bahtawi fekadeselasi tersa endie?
mejemerya sewyew feth kale leferd mekreb albachew!
yehiymanot meri mebal waga yelwem lewnet bewnet mekom yasfelegal!
nefse geday shmaglie mhon endit yechlewal?
helinacen ayweksenm endie?
weldeab weldemaryam
east africa

kingdom of GOD said...

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተሰቦች ለደርግ ባለስልጣናት ይቅርታ አናደርግም ቢሉ እንኳ ተጎድተናል ያሉትን ጉዳት ሊያገኙት አይችልም ፡፡ ማንም ይጠየቅ ተብሎ ቢታሰብ ማንም እጁ ከተጠያቂነት የነጻ አይደለም ፡፡ ፍቅና ምህረት የኃጢአትን ብዛት ሸፍናል እንጂ ፡፡ በሁላችንም ቤት ለቅሶ እንዲሆን መፈለጉ ልጆች ላሉት ብሎም ለኢትዮጵያዊነታችን ባህርይ የሚስማማ አይመስለኝም ፡፡
ሌሎችም ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦች ባለፈው ከመጸጸት ወደፊት እንዳይደገም ምህረት ታላቅ ኃይል አለው ፡፤ ዛሬ እነርሱ ቢገደሉልን ነገ የእነርሱ ልጆች …… እባካችሁ ይህን ደም አድርቁ ፡፡

kingdom of GOD said...

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተሰቦች ለደርግ ባለስልጣናት ይቅርታ አናደርግም ቢሉ እንኳ ተጎድተናል ያሉትን ጉዳት ሊያገኙት አይችልም ፡፡ ማንም ይጠየቅ ተብሎ ቢታሰብ ማንም እጁ ከተጠያቂነት የነጻ አይደለም ፡፡ ፍቅና ምህረት የኃጢአትን ብዛት ሸፍናል እንጂ ፡፡ በሁላችንም ቤት ለቅሶ እንዲሆን መፈለጉ ልጆች ላሉት ብሎም ለኢትዮጵያዊነታችን ባህርይ የሚስማማ አይመስለኝም ፡፡
ሌሎችም ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦች ባለፈው ከመጸጸት ወደፊት እንዳይደገም ምህረት ታላቅ ኃይል አለው ፡፤ ዛሬ እነርሱ ቢገደሉልን ነገ የእነርሱ ልጆች …… እባካችሁ ይህን ደም አድርቁ ፡፡

Anonymous said...

በመጀመሪያ ስምህሽ kingdom of GOD ሊሆን አይችልም ውዥንብር ለመፍጠር ስሜ ነው አትበል

Blogger kingdom of GOD said...

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተሰቦች ለደርግ ባለስልጣናት ይቅርታ አናደርግም ቢሉ እንኳ ተጎድተናል ያሉትን ጉዳት ሊያገኙት አይችልም ፡፡ ማንም ይጠየቅ ተብሎ ቢታሰብ ማንም እጁ ከተጠያቂነት የነጻ አይደለም ፡፡ ፍቅና ምህረት የኃጢአትን ብዛት ሸፍናል እንጂ ፡፡ በሁላችንም ቤት ለቅሶ እንዲሆን መፈለጉ ልጆች ላሉት ብሎም ለኢትዮጵያዊነታችን ባህርይ የሚስማማ አይመስለኝም ፡፡
ሌሎችም ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦች ባለፈው ከመጸጸት ወደፊት እንዳይደገም ምህረት ታላቅ ኃይል አለው ፡፤ ዛሬ እነርሱ ቢገደሉልን ነገ የእነርሱ ልጆች እባካችሁ ይህን ደም አድርቁ ፡፡

January 04, 2011

አንተ እንደምታስበው የገደለ እንግደል ብሎ ያለ አልሰማሁም

ሕግ ና ሥርዓት ባለበት ወንጀል ተመዝግቦ በማስረጃ ሲቀርብ ፍርድ ይሰጥበታል
ፍርዱም በየፈርጁ የቅጣት ወይም የይቅርታ ሊሆን ይችላል
የተበደለ ይቅር ቢል ትክክለኛ አስተዳደር መንግስት በደለኛን የመቅጣት ሃላፊነት ግዴታ አለበተ
በደሉ እንዳይደገም - መቀጣጫ እንዲሆን- -- ለዚህ ነው ሕገ መንግሥት የሚያስፈልገው

በሃይማኖትም አንጻር ያልተናዘዘ ንስሣ አያገኝም
ኑዛዜ ማለት በዝርዝር በደልን ተናግሮ ተጸጽቶ በደሌን ይቅር በሉኝ
ንስሃ ስጡኝ - nasa ንስሃ ወይም nasah ከዕብራይስጡና ግዕዝ ነው
በደሌን አንሱልኝ ሲል ነው ይቅርታ የሚያገኘው

ሁለቱን አናደባልቅ

Anonymous said...

የራስዋን አታውቅ ነዳይ
ቅቤ ለመነች አወይ

Anonymous said...

ለራስዋ አታውቅ ነዳይ
ቅቤ ለመነች አወይ.......
አይነት ነገር ነው የሆነብኝ
ምናለበት ቤታችንን ብናስተካክልመጀመሪያ

Anonymous said...

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት በግፍ መገደላቸው እጂግ ያሳዝናል
በተለይ ያለምንም ሕግና ፍርድ መገደላቸው በሰው ልጅ ታሪክ ፍጹም አስከፊ የሚባለው ወንጀል ነው፡፡ ግን እነዚህ ሰዋች ፍጹም ንጹሕ ናቸው ወይ; ይቅርታ አናደርግም ለማለትስ ማናቸው፡፡ ከመነሻው ጃነሆይ መፈንቅለ መንግሥት አድረገው ለሥልጣን ሲበቁ የተሾሙ ናቸው፡፡ አሁን ለሀገር ሰላም ያለፈው እንዳይደገም ብሎ ለወደፊቱ ትውልድ የቂምና የበቀል ታሪክ ከማስቀመጥ የይቅርታና የሰላም ቅርስ ለምን አናስረክብም፡፡ ማን ማንን እንዲበቀል ነው ይቅርታ አናደርግም የሚያስብለው ደርግ ለመሆኑ ያልጎዳው ያልበደለው ልጁን መንገድ ላይ ገድሎ የጥይት ዋጋ አምጣ ያለላው፣ አንዲት ሀገር ያፈራችውን ትውልድ ድራሹን በማጥፋት በሀገር፣ በትውልድ፣ እና በግል ያጠፋ መንግሥት ነው፡፡ ግን በምን መመለስ እንችላለን የኋላየን ትቸ ወደ ፊት እሄዳለኩ እንዳለው ሐዋርያ፣ ደርግን አምላክ ከፍሎታል ታሪኩንም ዝናውንም ግርማውንም አፈር አልብሶታል አሁን እኛ ታሪክ የምንሰራበት ጊዜ ስለሆነ በይቅርታ አርመን አዲስ ትውልድን በአባቶቻችን እውነተኛ የእምነት መሰረት ላይ ልንገነባ ይገባናል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)