January 29, 2011

በሐዋሳ ገብርኤል ትናንት አለመግባባት ነበር

 • ፖሊስ ሁከተኞቹን ያሬድ አደመን እና ትዝታው ሳሙኤልን ጨምሮ 12 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ
 • ምእመናን የክልሉ መንግሥት ሐላፊዎች ችግሩን ለመፍታት ባላቸው ሐቀኝነት ላይ የተፈጠረባቸው ጥርጣሬ እየተጠናከረ ነው
 • ‹‹ፓትርያኩ ውሸታም ናቸው፤ ጉባኤያችንን ከመስቀል አደባባይ ወደ ገብርኤል አመጡብን፤ የማንፈልጋቸውን መምህራን አስመደቡብን፤ የጳጳሱን ግቢ በር እናሽጋለን፤ መኪና ወደ ገዳሙ እንዳይገባ እናግዳለን፤ የተላኩብንን መምህራን እስክንመለስ እና የታሰሩብንን እስክናስፈታ ድረስ ጸልዩልን፡፡›› (ዛሬ ጠዋት የእነ ያሬድ አደመ መናጆዎች በደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም ያሰሙት ክስ እና ፉከራ)
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 29/2011፤ ጥር 21/2003 ዓ.ም)፦ ንት ማምሻውን በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ ገቢ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ የሀገረ ስብከቱን ፈቃድ ጥሶ ዐውደ ምሕረቱን በኀይል ለመቆጣጠር በተደረገ ሙከራ ሳቢያ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ ምእመናን በድንጋይ የተፈነከቱ ሲሆን ለብጥብጡ መንሥኤ ናቸው የተባሉት የሐዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ናትናኤል፣ ያሬድ አደመን፣ ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤልን ጨምሮ 12 ሁከት ፈጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የጥምቀት በዓል በጎንደር፦ የደጀ ሰላም ሪፖርታዥ

 • በ17 ማኅበራት የተደራጁ ከ2000 በላይ ወጣቶች ተሳትፈውበታል
 • ካርኒቫል እና ጥምቀት ‹‹አልተገናኝቶ›› ሆኗል
 • ‹‹የጥንቷ ጎንደር ክብር ተመልሷል›› (ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ)
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 29/2011፤ ጥር 21/2003 ዓ.ም)፦ የጥምቀት በዓል በደመቀ ሁኔታ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበር ቢሆንም በዓይን ገብነታቸው እና በቱሪስት መስሕብነታቸው ከሚታወቁት መካከል ግን የአዲስ አበባውን የጃንሜዳን እና የጎንደሩን የሚስተካከል የለም። በተለይም በዘንድሮው የ2003 ዓ.ም (2011) የጎንደር ጥምቀት በዓል አከባበር ዋዜማ የከተማው አስተዳደር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር “ካርኒቫል” የሚል ሐሳብ ማንሣቱ የመወያያ ነጥብ ሆኖ ሰንብቷል። ደጀ ሰላምም የአንባብያንን አስተያየት ስታስተናግድ ቆይታለች። አከባበሩ እንዴት አለፈ? ምን ተከሰተ? ምን ሆነ? ዝርዝሩ ቀጥሎ ይቀርባል።

January 27, 2011

“ነጻው ሚዲያ” ስለ ቤተ ክርስቲያን ባለው አመለካከት “ነጻ” መሆኑን ያሳይ

 • ኦርቶዶክሳዊ ፀሐፊዎች እየመሰሉ፣ በመግቢያቸው “ወያኔ ይውደም” የሚል ማባበያ ቃል እየጨመሩ ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን ትውደም” የሚለውን ግብ ያነገቡ ጽሑፎች በየዕለቱ ማንበብ ይዘናል።
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 26/2011፤ ጥር 18/2003 ዓ.ም)፦በተለምዶ “ነጻ ሚዲያ” እየተባለ የሚጠራው ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆነውና በተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚንቀሳቀሰው ሚዲያ ነው። “ሚዲያ” ያልነውን ራሱን ከለተመለከትነው ደግሞ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ጋዜጣና መጽሔቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ማለትም ሬዲዮና ቴሌቪዥኑን፣ እንዲሁም ድረ ገጾችን ሁሉ ያጠቃልላል። እነዚህን ሁሉ ጠቅልሎ በማጥናት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያስተላልፉትን ለመመልከት ብዙ ጊዜ እና የሰው ኃይል እንዲሁም ገንዘብ የሚጠይቅ ቢሆንም በመጠነኛ የወፍ በረር (Birds Eye-view) ቅኝት ያገኘነውን ሐሳብ መነሻ አድርገን ትዝብታችንን ለመጠቆም እንደማይከለክለን እንረዳለን።

January 20, 2011

አንድ አፍታ ወጣቶችን እናመስግናቸው

Video: Courtesy of "Jerusalem 159"
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 19/2011፤ ጥር 11/2003 ዓ.ም)፦ የፀጋው ሀብት እና ጥልቀት የማይመረመር አምላክ የአባቶችን ልብ ወደ ወጣቶች መልሶ፣ “ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም” የሚለውን ተረት ሽሮ እሳታዊ እና ነፋሳዊ ባሕርይ ያልተስማማላቸውን ወጣቶች በመንፈሳዊ ምስጢር አርግቶ ዕፁብ ዕፁብ፣ ድንቅ ድንቅ የሚያሰኝ የወጣቶች መነሣሣት ፈጥሯል። እናም ይህንን ያደረገ አምላክ ምስጋና ይገባዋል።

January 18, 2011

የከተራ - ጥምቀት በዓል ዝግጅት

 • በመዲናይቱ አዲስ አበባ በ62 ማኅበራት የተደራጁ ከ25‚000 በላይ  ወጣቶች በቅድመ ግጅቱ ታቦተ እግዚአብሔር የሚያልፋባቸውን  ጎዳናዎች በማጽዳት እና በመደልደል፣ መንገዶችን እና አደባባዮችን በሰንደቅ ዓላማ በማሸብረቅ ግንባር ቀደም ተሳትፎ እያደረጉ ነው
 •  የማኅበራቱ አደረጃጀት እና ባለቤትነት በጠቅ/ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መካከል ውዝግብ ያስነሣ ሲሆን በቀጣይ ወጣቶቹን ‹‹የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያው በትምህርተ ወንጌል አንጾ ለአገልግሎት በማዘጋጀት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር እንዲዋቀሩ ስምምነት ተደርሷል፤›› ተብሏል፡፡ ማኅበራቱን ከክፍለ ከተሞች የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ አመራሮች እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ለማጋጨት የታቀደውን ተንኮል እንደደረሱበት የገለጹት የማኅበራቱ ተወካዮች በበኩላቸው ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ተሰጥቶናል በሚሉት ፈቃድ መሠረት በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሥር መቆየትን እንደሚመርጡ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

January 15, 2011

ፍርድ ቤት ተማሪዎቹ በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ

 • "ይህ የክርስትናችን ፍሬ ነው፤ እግዚአብሔር ለበጎ አድርጎልናል፡፡"(ተማሪዎቹ) 
 • "እግዚአብሔር ባወቀ ወደ እስር ቤት ወስዶ አስተምሮኛል፤ ወደ ቀደመ ሃይማኖቴ ተመልሻለሁ፡፡"
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 15/2011፤ ጥር 7/2003 ዓ.ም)፦ በልደተ ክርስቶስ የበዓል ዋዜማ አከባበር ጋራ በተያያዘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ‹‹ሁከት ቀስቅሳችኋል፤ በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርጋችኋል›› በሚል ቀደም ሲል ለእስር የተዳረጉት 18 ተማሪዎች በብር 400፣ ትላንት ከዩኒቨርሲቲው በፖሊስ ተወስደው የተጨመሩት አራት ተማሪዎች ደግሞ የብር 500 ዋስ አቅርበው ከእስር እንዲወጡ እና ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ፡፡

January 13, 2011

ዩኒቨርሲቲው ለመንበረ ፓትርያርኩ ማሳሰቢያ ምላሽ ሰጠ

 • ማሳሰቢያው ‹‹የጣልቃ ገብነት እና የዛቻ ቃል ከመሆን አልፎ ዐመፅን የሚያበረታታ እና የሚያባብስ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡››  (የአ.አ.ዩ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት)
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 13/2011 ጥር 5/2003 .)የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከልደተ ክርስቶስ የበዓል ዋዜማ አከባበር ጋራ በተያያዘ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው አመራር ያቀረቡትን አቤቱታ የመስማት፣ ክትትል እና ማጣራት የማድረግ ሥልጣንም ሆነ ሐላፊነት እንዳለው ‹‹የሚያውቀው ነገር እንደሌለ››፣ ከዚህም አኳያ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ታኅሣሥ 28 ቀን 2003 ዓ.ም በቁጥር 1780/8513/2003 ‹‹የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለመሥሪያ ቤታችን ስላቀረቡት አቤቱታ›› በሚል ለዩኒቨርሲቲው የጻፈው ደብዳቤ ‹‹በተቋሙ አሠራር ውስጥ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ሆኖ እንዳገኘው›› በሰጠው ምላሽ አሳወቀ፡፡

ፍርድ ቤቱ ተማሪዎቹ የይቅርታ ጥያቄቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ወይም ‹ጥፋታቸውን› አምነው እንዲከራከሩ ምርጫ ሰጠ

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 13/2011፤ ጥር 5/2003 ዓ.ም)፦ በልደተ ክርስቶስ የበዓል ዋዜማ አከባበር ጋራ በተያያዘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ‹‹ሁከት ቀስቅሳችኋል›› በሚል ለእስር የተዳረጉ 18 ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡

January 11, 2011

“ሁከት አነሣሥታችኋል” በሚል የታሰሩት ተማሪዎች አልተለቀቁም

 •  ተማሪዎቹ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የይቅርታ ደብዳቤ ጽፈዋል
 •  የመንፈ ዓመት ፈተና ተጀምሯል
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 11/2011፤ ጥር 3/2003 ዓ.ም)፦ ታኅሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ በፖሊስ ተይዘው ከተወሰዱት ከ200 በላይ ተማሪዎች 18ቱ እስከ አሁን አልተለቀቁም፡፡ በዓመቱ የትምህርት ሰሌዳ መሠረት መሠረት በስድስት ኪሎ እና አምስት ኪሎ ካምፓሶች የተጀመረው የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ፈተና መርሐ ግብር ከነገ ጀምሮ በአራት ኪሎው የተፈጥሮ ሳይንስ ፋካልቲ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

ሁለት አዳዲስ የጡመራ መድረኮች

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 11/2011 ጥር 3/2003 .) በዚህ ሰሞን አዳዲስ የጡመራ መድረኮች ወደ ንባብ ብቅ ብለዋል። አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በመክፈት አገልግሎት መስጠት የጀመሩት “አደባባይ” (የዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ) እና “ግእዝ በመስመር ላይ፤ GeezOnline ይሰኛሉ። 


መልካም ንባብ።

January 10, 2011

የ ቤን (EthiopiaFirst ) ዓይነት ብዕሮች ይታረሙ!! ይማሩ

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 10/2011፤ ጥር 2/2003 ዓ.ም)፦በገና በዓል አከባበር ዙሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች እና በአስተዳደሩ መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ተያያዥ ጉዳዮችን ስንዘግብ መቆታችን ይታወሳል። ይህንን ዜና “ሪፖርተር ጋዜጣ” እና “ኢትዮጵያ ትቅደምEthiopiaFirst” የተሰኘው ድረ ገጽ ጽፈውበታል። በዚህ ጉዳይ ያለንን አስተያየት ማቅረባችንን በቀጠሮ ይዘን “ኢትዮጵያ ትቅደም፤ EthiopiaFirst” ድረ ገጽ የሰጠውን አስተያየት ለመጠየቅ ወደድን።

January 7, 2011

የተማሪዎቹ የልደት በዓል ዋዜማ መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ተካሄደ

 •  ‹‹ማንኛውንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ሥርዐት በዩኒቨርስቲው ግቢዎች ውስጥ ማካሄድ እጅግ በጣም የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ዐይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡›› (የአ.አ.ዩ ፕሬዝዳንት)
 • ‹‹የወጣው መግለጫ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡››(ተማሪዎች)                                
 • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ልጆች የለመዱትን በዓል ለማክበር ቢከለከሉ በሚመጣው ችግር  ዩኒቨርስቲው እንዳይጠየቅበት ቢያስብበት መልካም መሆኑን እንገልጻለን፡፡›› (ጠቅላይ ቤተ ክህነት)
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 6/2010፤ ታኅሣሥ 28/2003 ዓ.ም)፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር የልደት በዓል በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች እንዳይከበር ባስተላለፈው እግድ ሳቢያ የዋዜማው መርሐ ግብር ማምሻውን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

January 6, 2011

ልደትን በግቢያቸው እንዳያከብሩ በመታገዳቸው የተቃወሙ ተማሪዎች በፖሊስ ታግተዋል

 • ትናንት ሌሊቱን ከአ.አ.ዩ አራት ኪሎ ካምፓስ ከተወሰዱ ተማሪዎች 21ዱ አልተመለሱም፤
 •  በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ እግድ ተላልፏል፤
 •  ከተማሪው ተወካዮች ጋራ የተወያዩት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሐላፊዎች የዩኒቨርሲቲውን  አስተዳደር አነጋግረዋል፤
 • ‹‹እግዱ በሃይማኖታዊ ማንነታችን እየደረሰብን ላለው መድልዎ አስከፊ መገለጫ ነው፡፡››  (ተማሪዎች)                
 • ‹‹ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚ ተቋም እንጂ ቤተ ክርስቲያን አይደለም፡፡›› (አስተዳደሩ)
 (ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 6/2010 ታኅሣሥ 28/2003 .)ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል ልደተ እግዚእ እና ትንሣኤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድ በድምቀት ሲከበሩ ቆይተዋል፡፡ ከበዓላቱ አስቀድሞ ያሉትን መዋዕለ አጽዋማት ሲከታተሉ የሚቆዩት ተማሪዎቹ በዋዜማው እኩለ ሌሊት ላይ ከሚከናወነው ሥርዓተ ቅዳሴ አስቀድሞ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በሚገኙ አዳራሾች በዓላቱን የተመለከቱ የሥነ ጽሑፍ፣ ቃለ ስብከት እና መዝሙራት ዝግቶጅችን በማቅረብ ማክበር ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

January 5, 2011

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ፋካልቲ ተማሪዎች የልደት በዓል ዋዜማን በግቢው እንዳያከብሩ መታገዳቸውን ተቃወሙ


   አርእስተ ዜና፡-
 •   በአገር ዓቀፍ ደረጃ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የማንኛውም  እምነት ተከታዮች በቅጽር ግቢዎች በመዘመር እና በካፊቴሪያዎች ውስጥ ልዩ የዐበይት  በዓላት መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት የሚያከብሩበት ልምድ ‹‹እንዲታገድ ተወስኗል›› ተብሏል፡፡

“ከሰማይ የሚወርዱ ጥቃቅን የእሳት ፍንጣሪ መሰል ነገሮች” የሣር ክዳን ቤቶችን እና የተለያዩ ስፍራዎችን አቃጠሉ

እሳት ወይስ እሳተ እሳት

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 5/2010 ታኅሣሥ 27/2003.)በፊቱ የቀረበለትን ሁሉ የሚያቃጥል - ከሰል፣ ዐመድ፣ ዕመት የሚያደርግ - የሚፋጅ፣ የሚልጥ፣ የሚለመጥጥ ነው ባሕርይው - የዚህ ዓለም እሳት፡፡ እሳቱን የሚያስቆጡት እና የሚያገኑት ነዳድያት እሳታውያንን ሲያገኝ ደግሞ ላንቃው፣ ልሳኑ፣ ወላፈኑ በዝቶ ነበልባለ እሳት(ነደ እሳት) ይሆናል፤‹‹እሳት በላዒ ለዐማፅያን›› እንዲሉ፡፡ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ግራዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ታቱ ጀነታ እየተባለ በሚታወቀው ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የታየው ግን ከዚህ የእሳት ባሕርይ በመጠኑ የተለየ ነበር፡፡

በቤተ ክርስቲያን የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ


 • የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች እና የቅርስ አጠባበቅ ዐዋጆች መሻሻል ያስፈልጋቸዋል
 • ‹‹በኢትዮጵያ የእምነት ተቋማትን መስተጋብር የሚገዛ ሕግ ያስፈልጋል፡፡››
 • ‹‹በሕጎች ማርቀቅ እና ማጽደቅ ሂደት ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትደምጠባቸውን መድረኮች ማጠናከር ይገባል፡፡››
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 5/2010 ታኅሣሥ 27/2003.)በሥራ ላይ የሚገኙት የቅርስ፣ የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ዐዋጆች የቤተ ክርስቲያንን ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ሀብቶች በአግባቡ ከማስጠበቅ አኳያ ውስንነት ያለባቸው፣ ለአስፈጻሚ አካላት በቂ ሥልጣን የማይሰጡ እና በፈጻሚ ወገኖች ላይ ግዴታዎችን የማይጥሉ በመሆናቸው መሻሻል የሚያስፈልጋቸው አልያም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ሀብቶች ባሕርይ አኳያ ተገናዝበው በወጥነት መዘጋጀት እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡

January 3, 2011

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች "ለደርግ ባለሥልጣናት" ይቅርታ እንደማያደርጉ አስታወቁ

(በዘካሪያስ ስንታየሁ/ 02 January 2011; ሪፖርተር ጋዜጣ):- በደርግ ባለሥልጣናት የተገደሉት ስድሳዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች፣ ለደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት ይቅርታ እንደማያደርጉ ባለፈው ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ለአቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ የስድሳዎቹን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦችን በደርግ ባለሥልጣናት የይቅርታ ጉዳይ ላይ ሊያነጋግሯቸው በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ረቡዕ የቀጠሯቸው ቢሆንም፣ አቡኑ ከቁልቢ ገብርኤል ለቀጠሮው መድረስ ባለመቻላቸው፣ የቀጠሮው ቀን ወደ ሐሙስ ሊተላለፍ ችሏል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)