December 28, 2011

የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መዝባሪዎች እጃቸውን ከደብሩ እና ከሀገረ ስብከቱ ላይ እንዲያነሡ ተጠየቀ


 • የደብሩ አስተዳዳሪ የአጥቢያውን ልማት የመምራት አቅም የላቸውም::
 • ፖሊስ ሁለት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችንና አንድ ምእመን ይዞ አስሯል::
 • ተዋንያኑ ፋንቱ ማንዶዬ እና ችሮታው ከልካይ በቁሉቢ ለአኵስም ጽዮን ሙዚዬም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ያካሂዳሉ::
 (ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 18/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 28/2011. READ IN PDF)፦ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የስምንት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እናምእመናን በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የተፈጸመው ሙስና ተጣርቶ በሙሰኞቹ ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ፣የደብሩን አስተዳደር በመምራት ረገድ የከፋ የአቅም ማነስታይቶባቸዋል፤በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተተለሙ የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ዕንቅፋት ፈጥረዋልየተባሉት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ቸኮል ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ በተቃውሞ ትዕይንት ጠየቁ፡፡

December 27, 2011

የእነ መ/ር ዘመድኩን የፍርድ ቤት ውሎ


 • READ IN PDF.
 • “የስብከተ ወንጌል ሓላፊ ነኝ” ያሉት የበጋሻው ምስክር ስለ ሕገ ወጥ ሰባክያን የወጣውን መመሪያ “አላውቀውም፤ አልደረሰኝም” አሉ፤
 • በጋሻው በ”አርማጌዶን” ቪሲዲ “አሮጊቷ ሣራ” በሚለው ንግግር “በኑፋቄያቸው ተወግዘው ከወጡት ጋራ መነጻጸሬ አግባብ አይደለም” ቢልም ምስክሩ ታሪኩ አበራ ደግሞ “አነጋገሩ ቤተ ክርስቲያንን የማክበር እንጂ የማዋረድ አይደለም” ሲል መስክሯል፤
 • “አጉራ ዘለል ሰባክያን” ማለት “ፈቃድ የሌላቸውና ሳይማሩ የሚያስተምሩ ግለሰቦች” ማለት እንደ ሆነ ያስረዳው ታሪኩ አጉራ ዘለልነት በጋሻውን እንደማይመለከትና “መጋቤ ሐዲስ መባሉም ትክክለኛ ነው” ብሏል፤
 • ዲ/ን ደስታ ጌታሁን ያቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሹ ያሳተሙት “የሰባኪው ሕጸጽ” መጽሐፍ “ሳይማሩ ተምረናል ሳይላኩ ተልከናል በማለት ያለፈቃድ እንሰብካለን እናስተምራለን የሚሉ ሕገ ወጥ ግለሰቦችን መቆጣጠር” በሚለው የቃለ ዐዋዲው መመሪያ መሠረት መጻፉን መስክረዋል፤
 •  “ባልማርም በአደባባይ የሐዲስ ኪዳን መጋቢ ተብዬአለሁ”/በጋሻው ደሳለኝ/፤

December 22, 2011

የጽላተ ጽዮን ነገር - የደጀ ሰላም ሪፖርታዥ


አቡነ ጳውሎስ ከጽላተ ጽዮን ማደሪያ እድሳት ይልቅ ለሙዚዬሙ ግንባታ ትኩረት ሰጥተዋል
 (ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 12/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 22/2011. READ IN PDF)
 •  የርእሰ ገዳማት ወአድባራት አኵስም ጽዮን ማርያም ሰበካ ጉባኤ 1.8 ሚሊዮን  ብር ወጪ የጽላተ ጽዮን ማደሪያ እድሳት ያካሂዳል፤ በሰበካ ጉባኤው ሥር የሚካሄደው እድሳት አቡነ ጳውሎስ “በተለየ ጥረትና አመራር ሰጭነት” ከሚቆጣጠሩት ሙዚዬም ግንባታ ፕሮጀክት ጋራ የሚያገናኘው ነገር የለም
 • የጽላተ ጽዮንን ማደሪያ በገንዘባቸው በማደስ ስማቸውን ለማስጠራት የመጡ ባለሀብቶች ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም፤ ይልቁንስ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠባቂ እና መድኃኒት ለሆነችው ጽሌ-ኦሪት-ጽዮን ማደሪያ እድሳት እያንዳንዱ ምእመን የአቅሙን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ተደርጓል
 •  ለተቸገሩ አብያተ ክርስቲያን የሚሰበሰበውን ርዳታ ጨምሮ የመንበረ ፓትርያርኩ የገንዘብ ምንጮች/አቅሞች በሕዳሴው ግድብ አምሳል ቅስቅሳ ወደሚደረግለት የሙዚዬም ግንባታ ፕሮጀክት እንዲዘዋወሩ ጫና በመደረጉ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኞች ኑሮ እያቃወሰው ነው፤ በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳደርና በካህናቱ መካከልም ፍጥጫ ፈጥሯል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ


(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 11/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2011/ READ IN PDF)፦ ቀደም ብሎ ለኒውዮርክ ቀጥሎም ለዋሺንግተን እና አካባቢው ሀ/ስብከት በሊቀ ጳጳስነት ተመድበው ሲያገለግሉ ቆዩትና በጥቅምቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ወደ መዕራብ ሐረርጌ እና ጅጅጋ አህጉረ ስብከት የተዘዋወሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ።
 ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 7/2004 ዓ.ም (12/17/2011) በቨርጂኒያ ግዛት በተደረገላቸው የመሸኛ ዝግጅት ላይ ስንብት የተደረገላቸው ብፁዕነታቸው በምድረ አሜሪካ ቆይታቸው ስለነበረው ሁኔታ ማብራሪያ ከመስጠታቸውም በተጨማሪ በእርሳቸው መሔድ የተጀመረው አገልግሎት እንዳይቀዛቀዝ አባታዊ አደራ ሰጥተዋል።

December 17, 2011

በስልጢ ወረዳ የቆቶ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መቃኞ ጉልላት እና ጣሪያ በወረዳው ፖሊስ ተነቅሎ ከተወሰደ በኋላ የግድግዳው ዕንጨት በሙስሊም ተማሪዎች ተቃጥሎ ተቀበረREAD IN PDF.
  • 200 የወረዳው ምእመናን ተወካዮች ወደ ሐዋሳ በማምራት ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር ረዳት ጽ/ቤት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፤ በሁኔታው ያነቡት የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ምእመናንን አጽናንተዋል፤ በጉዳዩ ላይም ከወረዳ አስተዳደር እና ፖሊስ እንዲሁም ከክልሉ የፍትሕ እና ጸጥታ ዘርፍ ሓላፊዎች ጋራ እየመከሩበት ነው
  • መቃኞው የተሠራበት ቦታ የቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥምቀት ይዞታ ስለ መሆኑ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣ በክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሀብትና የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ፣ የስልጢ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና የወረዳው ፍ/ቤት እንዲሁም የቆቶ ባሎሶ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት በየደረጃው በሰጧቸው ውሳኔዎች አረጋግጠው ነበር
  • በውድቅት ሌሊት የተወሰደው የወረዳው ፖሊስ አፍራሽ ግብረ ኀይል ሕገ ወጥ ርምጃ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር በፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ በጠየቀበትና የአፈጻጸም መመሪያ ባልተሰጠበት የተፈጸመ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ግድግዳውን በማፈራረስ ያቃጠሉት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ በወረዳው ክርስቲያኖች ላይ ጅሃድ ባወጀው ጀማል ሽኩሪ በተባለ ጽንፈኛ የተቀሰቀሱ ናቸው

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አወዛጋቢ ስብሰባ ጠርተዋል፤ ለአቡነ አብርሃም ሽኝት ተዘጋጅቷል

(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF)፦ ባለፈው ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለዲሰና አካባቢው እንዲሁም ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ሀ/ስብከት ስም የጠሩት ስብሰባ ነገ ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

December 16, 2011

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚካሄዱ ግንባታዎች ከፍተኛ የሙስና ምንጭ እየሆኑ ነውአርእስተ ነጥቦችዶኩመንቶች
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF.)፦

 • ለድሬዳዋ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ከጅምሩ አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ምእመናን ከተሰበሰበው ብር 11.3 ሚሊዮን ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት መገኘቱን በምእመናን ምርጫ የተዋቀረው “የባለሞያዎች ተሟጋች ቡድን” እና የሰበካ ጉባኤው አባላት እየተናገሩ ነው

December 14, 2011

በጋሻው በመ/ር ዘመድኩን ላይ የመሠረተው ክስ የፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶውን ጥምረት እያጠናከረው ነው


 • “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ኅብረት”፣ ኦርቶዶክሳውያን ፖሊሶች እና የችሎት ተከታታዮች ለመ/ር ዘመድኩን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል::
 • በድብደባ ሙከራ ወንጀል ክስ እንዲመሠረትበት የተወሰነበት መናፍቁ አሰግድ ሣህሉ መ/ር ዘመድኩን ከሕገ ወጡ ቡድን ጋራ ዕርቅ እንዲያወርድ ተማፀነ::
 • በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጥያቄ የተቋረጠው የክስ መዝገብ እንዲቀጥል ተደርጓል::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 4/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 14/2011/ READ IN PDF)፦ በጋሻው ደሳለኝ በመ/ር ዘመድኩን በቀለ እና ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ላይ በስም ማጥፋት ወንጀል መሥርቶት የነበረውና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጥያቄ ተቋርጦ የነበረው የክስ መዝገብ ዳግመኛ ተከፍቶ እንዲንቀሳቀስ በፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ መመሪያ ከተሰጠ በኋላ ሁለቱ ተከሳሾች ዛሬ፣ ታኅሣሥ አት ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

በአርማጌዶን ቪሲዲ በጋሻው መ/ር ዘመድኩንን ከሰሰ


 • በጋሻው በጠ/ቤ/ክህነቱ ጥያቄ የተዘጋውን መዝገብ ለማንቀሳቀስ እየጣረ ነው::
 • “የተሻረው ደብዳቤ” - ወንጀለኛነት መያዣ የሆነበት የበጋሻው ድራማ::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 4/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 14/2011/ READ IN PDF)፦:- መ/ር ዘመድኩን በቀለ አርማጌዶን ቁጥር አንድ ቪሲዲ ጋራ በተያያዘ በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀረበበት፡፡ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ ታይቶ መ/ር ዘመድኩን የዋስትና መብት ተነፍጎት ክሱን በማረፊያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ጠይቆ ነበር፡፡ የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው፣ በቪሲዲው ውስጥ የተዘረዘሩት ነገሮች በይዘታቸው ሃይማኖታዊ በመሆናቸውና ቪሲዲው ከፍ ላለ ሃይማኖታዊ ፋይዳ የተሠራ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለውና በስም ማጥፋት ወንጀል ሊያስከስስ እንደማይችል በማስረዳት በክሱ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል፤ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን መከራከሪያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠትና ክሱ የሚቀጥል ከሆነ የምስክሮችን ቃል ለማዳመጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

December 13, 2011

16ኛው የ(ICASA) ጉባኤ ሪፖርታዥ


 • READ IN PDF.   
 • የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሰዶማውያን ማኅበራዊ ድጋፍ የሚያገኙበትን አጀንዳ ለማበረታታትና ለማስፋፋት የአቶ መለስ ዜናዊን የመሪነት እገዛ ጠይቀዋል፤
 • የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና “ገሞራውያን” የሚላቸው ሰዶማውያን እና ሰዶማውያት ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ፣ የመጸጸታቸው እና የቀና ኅሊናቸው ንጽሕና እስኪታወቅ ድረስም ንስሓቸው የዕድሜ ልክ እንደሚሆን ደንግጓል - “ገሞራውያን ይንበሩ በኵሉ ሕይወቶሙ ምስለ መስተብቋዕያን” /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 48÷17-56/፤
 •  በ16ው የ(ICASA) ጉባኤ የምሥራቅ አፍሪቃ መንግሥታት በብሔራዊ የጤና ፖሊሲ ክለሳዎቻቸው፣ በጤና ሁኔታዎች አመልካቾቻቸው፣ በጤና መርሐ ግብር ዝግጅቶቻቸውና ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን ተሳትፎ እንዲያረጋግጡ የሚጠይቅ የቅስቀሳ ውይይት(Oral Poster Discussion) ተካሂዷል፤

December 4, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ታስረው ተለቀቁ

 • ወጣቶቹ ከካዛንቺስ እና አካባቢው የተሰባሰቡ ናቸው ተብሏል
 • ተቃዋሚዎቹ በመፈክር መልክ ከያዟቸው ኀይለ ቃሎች መካከል “ግብረ ሰዶም ኀጢአት ነው!”፤ “ግብረ ሰዶም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!”፤ “ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በግብረ ሰዶማውያን አትረክስም!”፤ “[የወንጀል ሕጉ] አንቀጽ 629 ይከበር!” የሚሉ ይገኙበታል
 • ግብረ ሰዶማዊነት ለረጅም ጊዜ ከአእምሮ በሽታ ዝርዝር ተደምሮ የቆየ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 23/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 3/2011):- የዓለም ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች ላይ አተኩሮ ከሚካሄደውና ኢትዮጵያ ከነገ ኅዳር 24 - 28 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ከምታስታናግደው 16ው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ቀደም ብሎ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም የተካሄደውን የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ወጣቶች ለአንድ ሰዓት ያህል ታስረው መለቀቃቸው ተሰማ፡፡

December 3, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው

READ IN PDF.
 • ከ40 - 45 የሚደርሱ ግብረ ሰዶማውያን ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ናቸው፤ ያረፉበት ቦታ በምሥጢር ተይዟል::
 • የጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴሎች አስተዳደር የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በሆቴሉ እንደሚካሄድ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ደንበኞቹ እና አጠቃላይ ሕዝቡ እንዲገነዘቡለት አስታውቋል::
 • የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሠራተኞች በኢትዮጵያ ሕግ ወንጀል በሆነው ግብረ ሰዶማዊነት ላይ ለሚሰበሰቡ ግለሰቦች ፈቃድ መሰጠቱ ግራ እንዳጋባቸው ገልጸዋል፤ ሚኒስቴር መሥ/ቤቱ ምን እየሠራ እንደ ሆነ በቁጣ ላቀረቡት ጥያቄ ‹‹መፍትሔ መስጠት የሚችሉት የበላይ የመንግሥት አካላት ብቻ እንደሆኑ›› ተገልጦላቸዋል::
 •  መንግሥት በ‹ዝምታ ዲፕሎማሲ› የግብረ ሰዶማውያኑን የቅድመ (ICASA) ስብሰባ ከመከላከል ሲቆጠብ የስብሰባው የኮሚዩኒኬሽን ሓላፊዎች በበኩላቸው በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ስለሚገኘው ‹ሥልጠና› እና ልምድ ልውውጥ የተካተተበት የግብረ ሰዶማውያኑ ቅድመ ጉባኤ የማነቃቂያ ስብሰባ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር እያደናገሩ ይገኛሉ::

November 29, 2011

የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ያቀዱትን ስብሰባ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ” ተቃወመ!! • የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ የ(ICASA)ን ኮንፈረንስ አሉታዊ ትርጉም እንዳያሰጠው ተሰግቷል
 • “Claim, Scale-up and Sustain”(የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት) የግብረ ሰዶማውያኑ ውይይት መሪ ቃል ሲሆን አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና መሆኗን በመጠቀም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፤
 • እስከ አሁን ደቡብ አፍሪካ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊ ያደረገች ሲሆን በተቃራኒው የናይጄሪያ ፓርላማ ግብረ ሰዶማዊነትን ሕገ ወጥ ያደረገ ሲሆን በኬንያ እና በዑጋንዳ የግብረ ሰዶማውያን መብት በሚል ለፓርላማዎቻቸው ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ አድርገውታል።
 • ዝምባቡዌ ግብረ ሰዶማውያን “ውሾች ናቸው” በሚል ከሀገር ታባርራለች
 (ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 19/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 29/2011 PDF):- የውጭ አገር ዜጎች፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ ውጭ አገር ለንግድ አብዝተው የሚመላለሱ ኢትዮጵያውያን ግብረ ሰዶማዊነትን እንደ ዘመናዊነት/ሥልጣኔ ቆጥሮ በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በአብዛኛው የሚጠራሩበት ስም “ዜጋ” የሚል ነው፤ አንዳንዴ ይኸው ስያሜ “ኦፔራ፣ ወገን፣ ጅራሬ፣ ብርታሉ (ቁምጬ)፣ ጀሲካ ሞናሊዛ፣ ቆሚታ፣ መክተብ” በሚባሉ ስያሜዎች እንደሚተካ ተገልጧል፡፡

November 25, 2011

ከደሴ ደብረ ቤቴል ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምረቃ የቀሩት አቡነ ጳውሎስ የጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መረቁ


 •  መኖሪያ ቤቱ ብር 1.5 ሚልዮን ያህል እንደወጣበት ተነግሯል 
 •  አቡነ ጳውሎስ ያለጥንቃቄ ባደረጉት ጉዞ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል
 •  “አይ ቅዱስነትዎ፣ ተዋረዱ!! አሁን ይህ ለእርስዎ ክብር ነውን? የመቂ ሕዝብ እርሱን [ጌታቸው ዶኒን] ከእኛ የተሻለ ጠንቅቆ ነው የሚያውቀው፤ እንግዲህ የጌታቸው ዶኒ ጓደኛ ነው የሚልዎ!” /አቡነ ጎርጎርዮስ በድርጊቱ ማዘናቸውን ለአቡነ ጳውሎስ የገለጹበት መንገድ/
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 15/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 25/2011/ PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቂ ከተማ ተገኝተው የሊቀ ካህናትጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መርቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ 98 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ከድልድይ በላይ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በ400 ሜትር ካሬ ስፋት ያረፈውና በ‹ሀ› ቅርጽ የተገነባው የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቪላ 1.5 ሚዮን ብር ማውጣቱን ግለሰቡ በምረቃው ዕለት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባቀረበው አጭር ሪፖርት ገልጧል፡፡ በምረቃው ላይ በግለሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው 200 ያህል እንግዶች የታደሙ ሲሆን ድግሱም ሞቅ ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

November 19, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ አቀባበል አደረገ


 • READ IN PDF.
 •  “የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የበለጠ ለመደራጀት፣ ብዙ ሥራ ለመሥራት ይፈልጋሉ፤ ርኵስ መንፈስ ግን እያሰነፈ ሥራዎች እንዲቋረጡ እያደረገ ነው፤ የመናገር ሀብት የመሥራት ስንፍና አለብን፤ አድምጡኝ ብቻ ሳይሆን የማድመጥ፣ የመደማመጥ ነገር መኖር አለበት፡፡ እኛ ስንለያይ ንፋስ እየገባ ቤቱን ያውከዋል፤ ለክፉ ነገር ዝግ፣ ለበጎ ነገር ክፍት መሆን አለብን፤ የሚለዋወጥ ኅሊና ጥቅም የለውም፤ . . . ነገ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ ሐቅና እውነት እንዳልዎት [መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይን] ዐውቃለሁ፤ እግዚአብሔር የሥራ ጊዜዎን፣ አእምሮዎን ይባርክልዎ:: (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ)
 • “ለሁሉም መንገዱ አንድ ከሆነ፣ ለሁሉም ፍቅር ካለው ከራስ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ሥራ መሥራት ይቻላል፤ የምንኖረው፣ የምንተዋወቀው፣ የምንሠራው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ነው (መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ)
 • [የማደራጃ] መምሪያውን በማንኛውም ነገር እናግዛለን፤ በበጎ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያናችንን በሞያችን፣ በዕውቀታችን፣ በገንዘባችን ከማገልገል በቀር ሌላ ዓላማ የለንም፤ አባታዊ መመሪያዎንና ምክርዎን እንሻለን” /የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ/::
 • “Who is he, after all? እርሱ መንግሥት ነው እንዴ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀመጠው፤ የተመደበበት ቦታ ቢሠራ ይሻለዋል፤ ከአቅሜ በላይ ነው ብያለሁ፤” (አቡነ ጳውሎስ ለአባ ሰረቀ ሎቢስቶች የተናገሩት)::

November 15, 2011

በጋሻው ደሳለኝ በመ/ር ዘመድኩን በቀለ እና ዲ.ን ደስታ ጌታሁን ላይ የመሠረተው ክስ ተቋርጦ መዝገቡ ተዘጋ

 •  አሰግድ ሣህሉ በድብደባ ወንጀል ክስ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ ነው
 • መ/ር ዘመድኩን በቀለ ለሰዓታት በእስር ቆይቶ ተለቀቀ
 • አሰግድ ሣህሉ ቅዱስ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ - ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጣጣለው
 • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአሰግድ ሣህሉ እና ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ሊመሠርት ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 5/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 15/2011/ READ IN PDF)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ባለችበት አዳክሞ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ አልያም ከውስጥ በማተራመስ ለመከፋፈል የሚካሄደውን ሤራ በድልድይነት በማስተሳሰር(ኔትወርኪንግ) እና ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን የሚጎርፈውን ከፍተኛ ፈንድ በማሠራጨት እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት አሰግድ ሣህሉ በድብደባ ሙከራ ወንጀል ክስ ተመሥርቶበት፣ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት የመናፍቁ አሰግድ ሣህሉ የድብደባ ሙከራ ወንጀል የተፈጸመው ዛሬ፣ ኅዳር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ላይ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ቅጽር ውስጥ ነው፡፡

የመ/ር ዘመድኩን በቀለ መዝሙር ቤት እና መኖሪያ ቤት ብርበራ ተካሄደበት


 • ዛሬ የመከላከያ መልሱንና ክርክሩን ያቀርባል
 • ጠቅ/ቤተ ክህነት ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ እንዲመለስ ፍትሕ ሚ/ርን ጠይቋል
 • እነበጋሻው መ/ር ዘመድኩንን በተጨማሪ ክስ ለማስቀጣት፣ “እኛን አጥፍቶ እርሱ አይቀመጥም” በሚልም ከሀገር እንዲወጣ የተለያዩ የማሸማቀቂያ ዘመቻዎችን እያካሄዱ ነው
 • “የምትለውን ሕግ አብረን እናየዋለን፤ መቃብርህን ቆፍረሃል፤ 12 ሆነን ንብታችንን ሸጠንም ቢሆን አንተን ጉድጓድ እንከታሃለን፤ ከምትገባበት ጉድጓድ ማን እንደሚያወጣህ እናያለን፤”  (የፊደል ሬስቶራንት ባለቤት መ/ር ዘመድኩንን ያስፈራሩበት የዛቻ ቃል ድምፅ)፤
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 5/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 15/2011/ READ IN PDF)፦ ከአርማጌዶን ቪሲዲ ጋር በተያያዘ “እኛን አጥፍቶ እርሱ አይቀመጥም” እያሉ በመ/ር ዘመድኩን በቀለ ላይ በመፎከር ላይ ከሚገኙት ጥራዝ ነጠቅ የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞች አንዱ የሆነው ታሪኩ አበራ እና ተባባሪዎቹ ሊመሥርቱ ካሰቡት ተጨማሪ ክስ ጋር በተያያዘ የመ/ር ዘመድኩን ጌልጌላ መዝሙር ቤት እና መኖሪያ ቤት ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም ቀትር ላይ በፖሊስ ብርበራ እንደተካሄደበት ተገለጸ፡፡

November 14, 2011

ፓትርያርኩ የጠቅ/ቤ/ክ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የሦስት ከፍተኛ ሓላፊዎች የሥራ ውል እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ተሰማ

 • READ THIS NEWS IN PDF.
 • ሰበቡ ለጋሾች በልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኩል ለሐላፊዎቹ ደመወዝ የሚመድቡትን በጀት ባለመስጠታቸው ነው ተብሏል
 • ትእዛዙን የጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ አልተቀበሉትም
 •  “ጠቃሚ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቀንድ ቀንዳቸውን እየተባሉ ይወጣሉ፤ ሰዎቹ ከጠ/ቤተ ክህነት ፈሰስ ተደርጎም ቢሆን ሥራቸውን ይቀጥላሉደ (ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ)፤
 • “ቤተ ክርስቲያንንና መንግሥትን በግልጽ እንዲለያዩ ያደረገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት 16 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ሲታይ 50 ሚልዮን የሚሆነውን የምእመን ብዛትና ከፍተኛ የሚባል የገንዘብና ካፒታል መጠን ይዘን ብዙም አልተራመድንም፡፡. . .ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በስትራቴጂክ ፕላን እንዲመራ በማድረግ የዕቅዱን አፈጻጸም በየጊዜው መገምገም ሲገባው ወይም እየገመገመ የሚያቀርብለት የባለሞያዎች ቡድን መሠየም ሲገባው እስከ ዛሬም ባለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን የልማት አቅጣጫ፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ የበጀት አያያዝና አፈጻጸም የማያመረቃ ሆኖ ቆይቷል፡፡” /አቶ ልዑል ሰገድ የቤተ ክህነቱን አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች ከዳሰሱበት የዳሰሳ ምልከታ ጽሑፍ የተወሰደ 
 • (THIS DOCUMENT ATTACHED IN PDF)

November 13, 2011

አባ ሰረቀ የተፈጸመባቸው “ከፍተኛ የስም ማጥፋት ውንጀላ” በሥራቸው ለመቀጠል እንደማያስችላቸው ገለጹ


 • READ IN PDF. UPDATED!!!!
 • የመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በፓትርያኩ በመሾማቸው ተቃውሞ ያቀረቡት አካላት፣ “እንከን የሌለበትን ንጹሕ እምነታቸውን ጥላሸት የቀቡ ከሳሾቻቸው” ማንነት እና የክሱ ዝርዝር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል
 • ‹ውንጀላው› እስከሚጣራ ድረስ “እጅግ መራራ ተጋድሎ በከፈሉበትና ውጤት ባሳዩበት” የቀድሞ ቦታቸው እንዲቆዩ አልያም የዕረፍት ጊዜ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል
 • “እውነትንና ፍትሕን” ከቤተ ክርስቲያን እንደሚሹ “እውነትና ፍትሕ” ከቤተ ክርስቲያን ከጠፋ ግን “ሕገ መንግሥቱን ተጠቅመው” መብታቸውን በማስከበር ከሳሾቻቸውን ለመበቀል ዝተዋል
 • ከአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ጋራ ዛሬ ርክክብ ያደርጋሉ

November 9, 2011

ጠ/ቤተ ክህነቱ በሹመትና በሽረት እየታመሰ ነው፤ አባ ሰረቀ ም/ሥራ አስኪያጅነቱን አጥተዋል


 • READ IN PDF.
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ የሹመትና ዝውውር ውዝግብ በሽምግልና ተይዞ ቀጥሏል
 • ንቡረ ድ ኤልያስ ኣብርሃ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅነትን ቀድሞ ከነበሩበት የጠ/ቤ/ክህነቱ የመንፈሳዊ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ጋራ ደርበው እንዲይዙ፤
 • ንቡረ ድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴየገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ፤
 • አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊእንዲሆኑ ሐሳብ ቀርቧል
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ዋና ሓላፊ የሆኑትን ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን ከትንት በስቲያ አባ ሰረቀን በሕገ ወጥ መንገድ ለሾሙበትየመንፈሳዊ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን መርጠዋቸው የነበረ ቢሆንም የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን ስምምነት አላገኙም
 • ቤተ ክህነቱ ሙስና የሚያፍርበት ሳይሆን የሚያሾምበት ይነተኛ ተቋም ሆኗል

November 7, 2011

አቡነ ጳውሎስ አባ ሰረቀን የጠ/ቤ/ክ/ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ


 • ሹመቱን የተቃወሙት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከሓላፊነታቸው እንደሚለቁ አሳውቀዋል:: 
 • የሹመቱ ደብዳቤ ፓትርያኩ በሚቆጣጠሩት ጽ/ቤት በኩል የወጣ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 27/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 7/2011/ PDF)፦ ባለባቸው ከፍተኛ የአቅም ማነስ እና በተጠረጠሩበት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ሤራ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ተወግደው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት የሊቃውንት ጉባኤ ምርመራ እንዲካሄድባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተወሰነባቸው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ዛሬ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በፓትርያሪኩ ማኅተም እና ፓትርያሪኩ በብቸኝነት በሚቆጣጠሩት ልዩ ጽ/ቤት በኩል ደርሷቸዋል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሹመቱን በአድራሻ ለ‹አባ› ሰረቀ በደረሳቸው ደብዳቤ ግልባጭ እንዲያውቁት መደረጉ ተዘግቧል፡፡

November 5, 2011

አባ ሰረቀ ከሹመት ታግደው ይቆያሉ፤ ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ እየተነገረ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 25/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 5/2011/ PDF)፦ አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ከተጠረጠሩበት የሃይማኖት ሕጸጽ ነጻ መሆናቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በማንኛውም ቦታ በሓላፊነት እንዳይመደቡ ዛሬ የተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንደወሰነ ዘግይተው የደረሱን የመረጃ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ ደብዳቤ ደርሷቸው የነበሩት ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ መወሰኑን እነዚሁ ምንጮች ጨምረው አመልክተዋል፡፡ ርግጡን ቆይተን እናየዋለን፡፡

ሁለት ሱባኤ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ‹በሹም ሽር ውዝግብ› መካከል ተጠናቀቀ


 (ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 25/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 5/2011/ READ IN PDF)፦
 • ፓትርያርኩ ትናንት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመተላለፍ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና የፈጸሙት የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሹም ሽር ላይ የምልአተ ጉባኤው አባላት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፤ በመምሪያ ደረጃ በተደረገው ዝውውር የተሾሙት ሓላፊዎችም ለተመደቡበት ቦታ አይመጥኑም” የምልአተ ጉባኤው አባላት ቅሬታቸውን ገልጸዋል - ፓትርያርኩ እና የጠ/ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እርስ በርስ አሻግረው እየተያዩ ለተቃውሞው እና ለቅሬታው የአርምሞ ምላሽ ሰጥተዋል
 • ፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሊያቀርቡት ነበር የተባለው መልቀቂያ ስኬታማውን ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገ/ሥላሴን ከሥራ አስኪያጅነታቸው ለማስነሣት በፓትርያርኩ እና በሀ/ስብከቱ ውስጥ የጥቅም ኔትወርክ በፈጠሩ ግለሰቦች የተዘየደ መላ እንደነበር የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው - “አይ፣ እርስዎ አይለቁም፤ መልቀቅ ያለበት ሰውዬው ነው፤ እንደሚያስቸግርዎት ዐውቃለሁ” (አቡነ ጳውሎስ ለአቡነ ቀውስጦስ ከተናገሩት)
 • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመዘዋወራቸው ደብዳቤ ፈጥኖ የደረሳቸው ሲሆን የሌሎቹ እንዲዘገይ መደረጉ ተነግሯል፤ ሹመቱ እና ዝውውሩ ከገጠመው ተቃውሞ እና ከቀረበበት ቅሬታ አኳያ ማሻሻያ ሳይደረግበት እንደማይቀር ተመልክቷል
 • የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከፓትርያርኩ ጋራ ካላቸው ጥብቅ ግንኙነት አኳያ የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ካነሡት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋራ ተግባብተው የመሥራታቸው ሁኔታ አጠራጣሪ እንደሆነ ተዘግቧል፤ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የንቡረ እድ ኤልያስ መሾም በኅብረቱ ቀጣይነት ላይ ስጋት እንደሚፈጥር አባላቱ በመግለጽ ላይ ናቸው

ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የሚጻረሩ ዝውውሮች እና ሹመቶች እያካሄዱ ነው

 • ከሓላፊነታቸው በተነሡት በአባ ሰቀረ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመልሰው የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አባ ኅሩይ መሸሻ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተመልክቷል፤ አባ ኅሩይ በፓትርያርኩ ከቀረቡት የጵጵስና ሹመት ተስፈኞች ዝርዝር ውስጥ እንደነበሩበት ምንጮች እየገለጹ ነው።
 • ውጤታማው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ያለሲኖዶሱ ዕውቅና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆናቸው ተገልጧል፤
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳውያን ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ያለሲኖዶሱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው ተነሥተው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 24/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 4/2011, READ IN PDF)፦ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 15 መሠረት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ እየመረጠ የመሾም ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን ሥልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ክፍል (አንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 9) ደግሞ የምክትል ሥራ አስኪያጁን አቀራረብ ሲያስረዳ “ሥልጣነ ክህነት፣ በቂ የትምህርት ደረጃና ችሎታ ያላቸውን ሦስት ሰዎች ለም/ሥራ አስኪያጅነት በእጩነት ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ ያስመርጣል፤ በምርጫውም ቅዱስ ሲኖዶስ ሲስማማበት የተመረጠው ሰው በፓትርያርኩ ይሾማል፤ የሚጻፍለት ደብዳቤም በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚፈረም ሆኖ በፓትርያርኩ ፈቃድ እንደተሾመ ይገለጻል” ይላል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)