(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 31/2010፤ ጥቅምት 21/2003 ዓ.ም):- አስተያየት የሰጣችሁ ብዙ አንባብያን ከሰጣችሁት በመነሣት ይህንን አጭር ሐሳብ እናቀርባለን። አሁን ከገባንበት ንዴት፣ ሐዘን፣ ቁጭት እና አንዳንዴም ቀቢጸ ተስፋ አንጻር ብዙ ነገር ልንናገር እንችላለን። ምናልባትም “ዳን” የተባሉ ደጀ ሰላማዊ እንዳሉት “ስማቸውን አንስማ፣ ፎቷቸውን አንይ” ልንል እንችላለን። ያ ግን መልስ አይደለም። አንድ አንባቢ “ብፁዕ ወቅዱስ አትበሏቸው” ብለዋል። በዚሁ አጋጣሚ ስለዚህም መናገር ይገባናል።
October 31, 2010
ይድረስ ለቅዱስነትዎ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ (ተባባሪ ፕሮፌሰር)፦ ከዓመታት በፊት በአውሮፓ አንድ የኦርቶዶክሶች ኔትወርክ አባል ሆኜ የሁለት ቀናት “በጎ አመራር” ላይ ያተኮረ ውይይት ለማድረግ ተሰባስበን ነበር። የቡድን ውይይት ወቅት ሁለት ሁለት ሆነን ተመደብንና የምንወያይበት ርዕስ ተሰጠን። አቀማመጣችን ጀርባ ለጀርባ ተነካክተን መቀመጥ ሲሆን። “ለጥፈው” (Post-It) ከብዕር ጋር ተሰጥቶናል። በሕይወታችን የምንኮራበትና አርአያ የምናደርገው በጎ መሪ (በመንፈሳዊው ዓለምም ሆነ ከዛም ውጪ) ከተቀመጥንበት ሆነን በየግላችን ማሰብ እና የተሰጠን “ለጥፈው” ላይ ስሙን መጻፍ። ከዛ ስሙን ለይተን እንደጻፍን መጨረሳችንን ከተናገርን በኋላ ፊት ለፊት እየተያየን እያንዳንዳችን የመረጥነው በጎ መሪ ማንነትና ምንነት እና ለምን በጎ ብለን እንደመረጥነው መወያያት። ከዛም ሁለታችን የተወያየንበትን የበጎ መሪ መገለጫዎች ለቤቱ በየተራ ማቅረብ። አንዱ የመረጠውን ከነመገለጫው የሚያቀርበው አብሮት የተመደበው ተወያይ ነበር።
ርእሰ አንቀጽ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “በቃ” ሊባሉ ይገባል፤
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- "ተዘልፎ ልቡን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፤ ፈውስም የለውም" (ምሳሌ 29፡1)
አቡነ ጳውሎስ አልፈርምም ብለዋል፤ የሚከተለው ነገር ምንድን ነው?
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ከወልደ መንክር)፦ በዛሬው እለት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መጠናቀቅን አስመልክቶ በፓትርያርኩ የተሰጠው መግለጫ ብዙዎቻችን ከምንጠብቀው ውጭ በመሆኑ መገረምና ሀዘን የፈጥሮብናል። አቡነ ጳውሎስ ምን አይነት ሰው እንደሆኑ በቅርበት ለሚያውቃቸው ግን አሁን ያደረጉት የሚጠበቅ ነገር ነው። የሲኖዶሱ አባላት ፈርመው ፓትርያርኩ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም ሲሉ እንደ አካሔድ ታስቦ የነበረው ባይፈርሙም የተጻፈውን ካነበቡት እንደተስማሙበት ማስረጃ ይሆናል የሚል ስልት ነበር። ነገር ግን ፓትርያርኩ ባላቸው ልምድ የሲኖዶሱን አባላት አስቀምጠው አበው የማይስማሙበትን ያውም አጠቃላይና ግልጽነት በጎደለው መግለጫ ሰጥተዋል።
October 30, 2010
ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በጋራ ካዘጋጀው የተለየ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠታቸው ሳቢያ ጉባኤው በመካረር መንፈስ ተለያየ
ማውጫ፦
ሐተታ,
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- አቡነ ገሪማ ከአቡነ ናትናኤል ጋር ያዘጋጁትን ዋናውን የቅ/ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ አልሰጡም፤
- ፓትርያርኩ “አትፈርሙ” የሚለውን የእጅጋየሁን ምክር በተግባር አውለዋል፤
- ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በቃለ ጉባኤው ላይ ፈረመዋል፤ ብፁዕ አቡነ ይሥሐቅ ዘግይተውም ቢሆን እንደሚፈርሙ ይጠበቃል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):- ከተጀመረ ስምንተኛ ቀኑን የያዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጠርቶት በነበረው ጋዜጣዊ ጉባኤ ፓትርያርኩ፣ እርሳቸውም ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉባኤው በመረጣቸው ብፁዕ አባት በንባብ የሚሰማ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ይሁንና ጋዜጠኞች መግለጫው በሚሰጥበት አዳራሽ ከተገኙ በኋላ ፓትርያርኩ በአቡነ ገሪማ እንደተዘጋጀ የሚነገርለትን በድብቅ መክረውበታል የተባለውን የተድበሰበሰ መግለጫ በንባብ አሰምተዋል፡፡ ሁኔታው በሌሎች ብፁዓን አባቶች ላይ መገረምን እንዳሳደረ መግለጫው በንባብ በሚሰማበት ወቅት ያሳዩዋቸው በነበሩ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የራሳቸውን መግለጫ በንባብ አሰምተው እንደፈጸሙ የሲኖዶሱን መግለጫውን በንባብ እንዲያዘጋጁ በትናንትናው ዕለት በጉባኤው ከተሠየሙት አንዱ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በተሰጣቸው ሐላፊነት መሠረት በንባብ የተሰማው የተዘጋጀው መግለጫ አለመሆኑን መግለጽ ሲጀምሩ አቡነ ጳውሎስ ‹የቀረች ትንሽ ሥራ ስላለች› በሚል ብፁዕነታቸውን አቋርጠዋቸው ጋዜጠኞች እንዲወጡ ይጠይቃሉ፡፡
ቅ/ፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የቀነጨበ መግለጫ አነበቡ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):- ተጠናቀቀ በተባለው የቅ/ሲኖዶስ መግለጫ ፍጻሜ ቅ/ፓትርያርኩ የጉባዔውን አቋም የቀነጨ እና የተለመደ ዘይቤ የተከተለ መግለጫቸውን አንብበዋል። የሐውልቱ ጉዳይ አልተጠቀሰም። በጥራት ለማነደበብ እንድትችሉ ወደ ኮምፒውተራችሁ “ዳውን ሎድ” በማድረግ እና መጠኑን ከፍ ማድረግ አትርሱ።
ሰበር ዜና:- አቡነ ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):-
አቡነ ጳውሎስ ሐውልቱ እንዲፈርስ የታዘዘበትን እና የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ስምምነት የተገለጸበትን ውሳኔ በያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹አልፈርምም›› በማለት እና ሲጠየቁም ዝምታን በመምረጥ ቀድሞ ሲገለጽ በቆየው እምቢታቸው ጸንተዋል፡፡
አቡነ ጳውሎስ ሐውልቱ እንዲፈርስ የታዘዘበትን እና የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ስምምነት የተገለጸበትን ውሳኔ በያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹አልፈርምም›› በማለት እና ሲጠየቁም ዝምታን በመምረጥ ቀድሞ ሲገለጽ በቆየው እምቢታቸው ጸንተዋል፡፡
![]() |
አቡነ ይሥሐቅ |
![]() |
አቡነ ጎርጎርዮስ |
- ከፓትርያሪኩ ጋራ ሌሎች አራት ሊቃነ ጳጳሳትም በተለያየ ምክንያት የሐውልቱ መፍረስ የተገለጸበትን ቃለ ጉባኤ አልፈረሙም፡፡ ሲኖዶሱ ከ43 ያላነሱ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ጳጳሳት እና ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት ይገኙበታል፡፡
- የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የሐውልቱን ማስፈረስ ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ በስማቸው ተለይቶ በመግለጫው ላይ መስፈሩን በመቃወም ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ብፁዕነታቸው ‹‹ከእኔ ስም ይልቅ ቢሮው ነው መጠቀስ ያለበት›› የሚል አቋም እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
የምስጋና መልእክት ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
Posted by
DejeS ZeTewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ቀን፦ ጥቅምት 19/2003 ዓ.ም
የምስጋና መልእክት ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
እኛ በዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፤ ሰባክያነ ወንጌል፤ የሰንበት ትምህርት ቤትና የምዕመናን ተወካዮች በጥቅምት 17/ 2003 ዓ.ም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት የብፁዕ አቡነ አብርሃም የዝውውር ሀሳብ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መቅረቡ አግባብና ወቅታዊ አለመሆኑን አስመልክተን
October 29, 2010
የቅ/ሲኖዱስ ምልአተ ጉባኤ ጠንካራ ውይይት በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዙሪያ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
የዛሬ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ተጨማሪ አርእስተ ዜና
- ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ ለነገ መፍትሔ የሚያቀርብ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቋመ
- በጋሻው ደሳለኝ፣ ሌሎች ሕገ ወጥ ሰባክያን እና ዘማርያን የሚፈጥራቸው ችግሮች ዋነኛው ርእሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡
- ብፁዓን አባቶች ፓትርያሪኩን እና ለበጋሻው ደሳለኝ የጥፋት ተግባር ተባባሪ ሆነዋል ያሏቸውን ወገኖች ወቅሰዋል በድርጊታቸውም መማረራቸውን ገልጸዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊነትና ሊገጥሙት የሚችሉት ፈተናዎች
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ከወልደ መንክር):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በርካታ አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል ። ይህ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 19 ወይም ነገ ጥቅምት 20 2003 ዓ. ም ሊጠናቀቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። በቦሌ የተተከለውን የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉ በተለያየ ቦታ የሚገኙ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ዘንድ ከፍተኛ ደስታ ፈጥሯል ። የቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ አካሄድ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ አንጻር ሰፊ ትንታኔ ሊሰጥበት ቢችልም ለአሁኑ ግን "የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆነው እንዴት ነው፣ ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ አንጻር ምን ልንጠብቅ ይገባናል፣ የምእመናንና የካህናትስ ሱታፌ በዚህ ወሳኝ ወቅት ምን መሆን አለበት?" የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው።
ቅ/ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ የደረሰበትን ውሳኔ አጸና
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
አርእስተ ዜና!!!!
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 29/2010፤ ጥቅምት 19/2003 ዓ.ም):-
- ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ የሚገልጽ ማመልከቻ ጠዋት ለሲኖዶሱ ያቀረቡ ቢሆንም እስከ ግንቦቱ የርክበ ካህናት ሲኖዶስ ድረስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ለመቆየት ተስማምተዋል፤ የቀድሞውን ሀገረ ስብከታቸውን (የሰሜን ምዕራብ ሸዋ - ሰላሌ) ደርበው ያስተዳድራሉ፡፡
October 28, 2010
የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ" በ20 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ “አዲስ አበባን አልፈልግም” እያሉ ነው
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- አቡነ ጳውሎስ በውሳኔው ላይ ላለመፈረም እያንገራገሩ ነው፤
- አቡነ ቀውስጦስ ሐላፊነቱን ለመቀበል መቸገራቸው እየተነገረ ነው፤
- "ካልሆነ አቡነ ሳሙኤል ወደ ቦታቸው ይመለሱ" (ሌሎች ብፁዓን አባቶች)
ሰበር ዜና፦ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 28/2010፤ ጥቅምት 18/2003 ዓ.ም):- ቅ/ሲኖዶስ በዛሬ ከሰዓት ስብሰባው ለብዙ ጊዜ ሲያጨቃጭቅ በነበረው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ ላይ በድምጽ ብልጫ ውሳኔ አስተላልፏል። ለቦታው ታጭተው ከነበሩት ሦስት አባቶች መካከል ማለትም ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ከብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መካከል ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን በ22 ድምጽ መርጧል።የቤተ ክርስቲያን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን።
ዝርዝሩን እንደፈፀምን እንመለስበታለን።
ቅዱስ ሲኖዶስ በጳጳሳት ምደባ እና ዝውውር ጉዳይ በፓትርያርኩ በቀረበው ሐሳብ ላይ ውሳኔዎችን ሰጠ
ማውጫ፦
ሐተታ,
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- በውጭ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ የቀረበው የዝውውር ሐሳብ፤
- ‹‹ቅንነት የጎደለው እና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚያናጋ›› በሚል ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ ባሉበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል፤
- ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ‹‹ብጠራቸው አልመጡም›› በማለት ስሞታ አቅርበውባቸዋል፤
- ‹‹ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ስል የእናንተን የአባቶቼን ሐሳብ እቀበላለሁ›› (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፤
- ‹‹ከእርሳቸው ጋራ አብሬ መሥራት አልችልም›› (አቡነ ጳውሎስ)፤
- ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት በዕጩነት ይቀርባሉ፤
- አቡነ ፋኑኤል የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ማሠልጠኛ ኮሌጅ የበላይ ሐላፊ ሆነው ተመድበዋል፤
- በጋሻው ደሳለኝ፣ ያሬድ አደመ እና ቲፎዞዎቻቸው ከአቡነ ፋኑኤል ውጭ የሚደረገውን አዲስ ምደባ በመቃወም ብጥብጥ ለማስነሣት ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 28/2010፤ ጥቅምት 18/2003 ዓ.ም):- በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው እና የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 10 ቀን 1991 ዓ.ም ባጸደቀው እና በሥራ ላይ በሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ሰባት ንዑስ አንቀጽ 13 መሠረት፣ ሊቃነ ጳጳሳትን እና ኤጲስ ቆጶሳትን በየሀገረ ስብከቱ እና በተለያዩ የሥራ ክፍሎች የመመደብ እና በበቂ ምክንያት የማዘዋወር ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቷል፤ የሚሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ እና በሌሎች ሕጎች እና አሠራሮች ሊሻር፣ ሊለወጥ የማይችል ነው፡፡
ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤ ስለ ብፁዕ አቡነ አብርሃም 2 መግለጫዎች
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
የሚከተሉት ሁለት ጽሑፎች በዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፤ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት እና የምዕመናን ተወካዮች፤ እንዲሁም አንድ ፍቅሩ አበበ የተባሉ ሌላ ምእመን በግላቸው የጻፏቸው ናቸው። እንደታነቡ እንጋብዛለን። በጽሑፎቹ የተገለጹት ሐሳቦች በሙሉ የፀሐፊዎቹ እንጂ የደጀ ሰላም አቋም ሆነ አስተያየት አይደሉም። ደጀ ሰላም ቀደም ባለው “ርእሰ አንቀጿ” መልእክቷን ማስተላለፏ ይታወሳል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።
ደጀ ሰላም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የጸሎታችሁ በረከት ትድረሰን እኛ በዲሲና አካባቢው የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፤ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮችና የምዕመናን ተወካዮች ረቡዕ ጥቅምት 17 ቀን ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ ለብፁዓን አባቶቻችን የሚከተለውን ተማጽኖ ስናቀርብ በታላቅ ትህትና ነው፡፡
ርእሰ አንቀጽ፦ የሀ/ስብከት ምደባ አጀንዳ አባቶች የምትለያዩበት/ የምትከፋፈሉበት “የመሪባ ውሃ” እንዳይሆን (ዘጸ. 17)
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ዘዴው “በጎሽ ቆዳ ተደብቆ ጎሽን መውጋት” የሚለው ያረጀ ዘዴ፤ አባቶችን "በሀ/ስብከት ምደባ ሰበብ" መከፋፈልና እርስበርሳቸው ማጋጨት ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2010፤ ጥቅምት 17/2003 ዓ.ም):- የሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አባቶች የወሰዱት አቋምና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰኑ ውሳኔዎች የምእመናኑን ልብ በተስፋ የሞላ፣ አንገቱን ቀና እንዲያደርግና በአባቶች ላይ ያሳደረውን ቅሬታ እንዲያነሳ በር የከፈተ ነው። ቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎቹ ላይ በሕቡር ልብ እና በሕቡር ቃል አንድ ሆኖ እየተወያየ መጥቶ ስብሰባውን ለማጠናቀቅ ትንሽ አጀንዳ ፈሪ፣ ምናልባትም የአንድ ቀን ስብሰባ ብቻ ነው የቀረው። ይሁን እንጂ ዛሬ ረቡዕ በነበረው “የጳጳሳት ምደባና ዝውውር” አጀንዳ ውይይት ወቅት የአባቶች አንድነት እንዲፈታ ጥሩ መንገድ የተገኘ ይመስላል። በስብሰባው ወቅት “በአርምሞ” የቆየው አካል በተግባሩ ወቅት “ከንዋመ አርምሞ”ው ነቅቶ በተግባር ውሳኔዎቹን እንዳይቀለብሳቸው እያስፈራን ነው። አበው እንደሚሉት “ዓይጥ ወልዳ ወልዳ …” እንዳይሆን አስግቶናል። ለዚህም የሚከተሉትን ነጥቦች ለማቅረብ ወደድን።
October 27, 2010
በጳጳሳት ዝውውር እና ምደባ ጉዳይ በፓትርያርኩ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከፍተኛ ክርክር አስነሣ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2010፤ ጥቅምት 17/2003 ዓ.ም):- ከተጀመረ አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጳጳሳት ምደባ እና ዝውውርን አስመልክቶ በቋሚ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ውይይት የተደረገበት ነው በተባለው እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለውሳኔ በቀረበው ሐሳብ ላይ ተወያየ፤ ውይይቱ ከፍተኛ ክርክር የተካሄደበት በመሆኑ ሳይቋጭ ለነገ እንዲያድር ተደርጓል፡፡
ቅ/ሲኖዶስ በሕንጻዎች እና ቤቶች አስተዳደር እና በልማት ኮሚሽን ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ አሠራሮች እና ምዝበራዎችን በመመርመር ውሳኔዎችን አስተላለፈ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- የሕንጻዎች እና ቤቶች አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው ተነሡ፤
- የአስተዳደር ቦርዱ ከቅዱስ ሲኖዶሱ በጽሑፍ ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ሐሰተኛ እና ከጥያቄው ጋራ የማይገናኝ በመሆኑ ቀደም ሲል የተወረሱ ቤቶች አስመላሽ በመሆን የሠሩት መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም በድንገት እንዲጠሩ ተደርጓል፡፡
- "አጥፍተናል፤ እናስተካክላን" (የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፤
- የተወረሱ ቤቶች እና ሕንጻዎች አስመላሽ ሆነው የሠሩት መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም "ቤቶቹን እና ሕንጻዎቹን በማስመለሴ ተቆጭቻለሁ፤ አስተዳደሩ ሕግ እና የአሠራር ደንብ የለውም፤ ለሙስና የተጋለጠ ነው፤ ቤቶቹን ለመከራየት በጨረታ ተወዳድረው ካሸነፉት ይልቅ ከበላይ አካል በሚወርደው ትእዛዝ ለዘመድ አዝማድ ከዋጋቸው በታች እና በነጻ የሚከራዩት ይበዛሉ፤ እውነት እንድናገር የሚፈለግ ከሆነ ለሥራዬ ዋስትና ይሰጠኝ" በማለት ለሲኖዶሱ በማስረዳት ተማፅነዋል፡፡
የድምጽ አስተያየት
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ውድ ምእመናን እና ምእመናት ደጀ ሰላማውያን/ያት!!!!
የተሰማችሁን ስሜት እና ደስታችሁን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በድምጽ አስቀምጡ። ለመደወል ከላይ ያለውን የስልክ ምልክት ይጫኑ። ወይም በስልክ ቁጥር (Area Code +1 or 001)703 776-9824 በመደወል የድምጽ መልእክት አስቀምጡ። ሌሎች ደጀ ሰላማውያን ደግሞ ያንን በሲዲ እያባዙ ለአባቶቻችን ሊያደርሱ ይችላሉ። "በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ፤ እግዚአብሔርን ሥራህ ግሩም/ድንቅ ነው በሉት"!!!!!
“ሐውልቱ” ምን ይሁን?
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2010፤ ጥቅምት 17/2003 ዓ.ም):- ቅዱስ ሲኖዶስ በማያሻማ መልኩ ከትምህርተ ተዋሕዶም ሆነ ከ ሥርዓተ አበው ውጪ የሆነው “ሐውልተ ስምዕ” እንዲነሣ ከወሰነ ጀምሮ የተለያዩ ደጀ ሰላማውያን እንዴት እንደሚፈርስ በቀልድ እያዋዛችሁ አስተያየታችሁን ሰጥታችኋል።
እንግዲህ መፍረሱማ ከሆነ እንዴትና ምን መሆን እንዳለበት ከታሪካችን መጠነኛ አስተያት በመጨመር አጭር ሐሳብ ለማካፈል ወደድን። ሐውልቱ በደህና ቦታ፣ ለምሳሌ ቤተ ክህነቱ ባሠራው ሙዚየም ወይም በሌላ ተገቢ ቦታ አልያም በዚያው በቦሌ መድኃኔ ዓለም “ሙዚየም” (ካላቸው) መቀመጥ አለበት።
እንግዲህ መፍረሱማ ከሆነ እንዴትና ምን መሆን እንዳለበት ከታሪካችን መጠነኛ አስተያት በመጨመር አጭር ሐሳብ ለማካፈል ወደድን። ሐውልቱ በደህና ቦታ፣ ለምሳሌ ቤተ ክህነቱ ባሠራው ሙዚየም ወይም በሌላ ተገቢ ቦታ አልያም በዚያው በቦሌ መድኃኔ ዓለም “ሙዚየም” (ካላቸው) መቀመጥ አለበት።
አባቶቻችን፤ እናመሰግናለን። ውሳኔው ይተገበር ዘንድ እንጠብቃለን
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 26/2010፤ ጥቅምት 16/2003 ዓ.ም):- በሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ብፁዓን አባቶቻችን ያሳያችሁት መንፈሳዊ አርበኝነት እና ለጉባዔያችሁ የሚገባ እና የሚስማማ ውይይት ብዙ ደጀ ሰላማውያን እንዳሉት “እንድንኮራባችሁ፣ ከቀቢፀ ተስፋ እንድንወጣ” አድርጎናል። አሁን አንድ ትልቅ እርምጃ ተራምዳችኋል። ቀጥሎ የምንጠብቀው ነገር ውሳኔያችሁ በተግባር እንዲተረጎም ማድረጉ ላይ ነው። ለዘወትሩ እንደተለመደው “ቤተ ክህነት የአጀንዳ እና የውሳኔ ችግር” የለባትም። ችግሯ የውሳኔ እና የውሳኔ አፈጻጸም ነው። አሁን በምልዓተ ጉባዔችሁ “ያረመሙ” ሁሉ ቆይተው እናንተ ወደየሀገረ ስብከታችሁ ከተመለሳችሁ በኋላ ካጎነበሱበት ቀና ቀና ብለው “ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ” እንደሚሉት ሕጻናት እንዳያደርጉት ጥንቃቄ ይፈልጋል። ከስብሰባው መበተን በፊት የውሳኔያችሁን አፈጻጸም የሚከታተል ክፍል ማቆማችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ሁላችንም በጉጉት እየጠበቅናችሁ ነው። በርቱልን። ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን
October 26, 2010
የቅ/ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ ዝርዝር ሪፖርታዥ
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 26/2010፤ ጥቅምት 16/2003 ዓ.ም):- ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ውሎው ከቅዱስ ፓትርያርኩ “ሐውልተ ስምዕ” መፍረስና ሌሎች ተጨማሪ ወሳኝ እርማጃዎች በተጨማሪም ከጥቅምት አንድ 2003 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ሰገድ ግርማ፣ የአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ሐላፊ አቶ ደሳለኝ መኮንን እንዲሁም የሒሳብ እና በጀት መምሪያ ሐላፊ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ዓለሙ የቅጥር ሁኔታ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን መዋቅር እና የአስተዳደር ደረጃ የመወሰን ሥልጣን የሚጋፋ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ስለዚህም የሐላፊዎቹ የፈረሙት ኮንትራክት ካለ የኮንትራክት ጊዜያቸው ሲያበቃ እንዲሰናበቱ፣ የፈረሙት ኮንትራክት ከሌለ ግን በአስቸኳይ እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡
ሰበር ዜና፦ ቅዱስ ሲኖዶስ የአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› እንዲፈርስ ወሰነ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ዝርዝር ዜናው እንደደረሰልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉን!!!!!
- በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ የተሰቀለው የአቡነ ጳውሎስ ፖስተርም እንዲነሣ ተወስኗል፤
- በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅሮች የተሾሙት ሐላፊዎች የቅጥር ሁኔታ ተመርምሮ በሚቀጥልበት እና በሚቋረጥበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ የሚሰጥበትን አግባብ አስቀምጧል፤
- ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወደ ቅጽረ መንበረ ፓትርያርኩ እንዳይገቡ ታግደዋል!!
- አቡነ ጳውሎስ በሐውልቱ ሥራ ላይ ‹‹አልተሳሳትኩም››፤ ‹‹እኔ አላውቅም›› የሚሉ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ እና ግራ የሚያጋቡ አቋሞችን አንጸባርቀዋል፤ በሌሎቹም ውሳኔዎች ላይ አርምሞን መርጠዋል፡፡ ብዙዎች ሁኔታውን ‹የውዥንብር እና የጸጥታ ዲፕሎማሲ› ብለውታል፡፡
- ‹‹ውሳኔው የቅዱስ ሲኖዶሱን ግብራዊ ህልውና የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔዎቹ ተፈጻሚ መሆናቸውን ስብሰባው ሳይፈጸም ማረጋገጥ አልያም ከጽ/ቤቱ ጋራ በመሆን ውሳኔውን የሚያስፈጽም አካል መሠየም አለበት፡፡›› (የምእመናን አስተያየት)
የቅ/ሲኖዶስ የዛሬ ከሰዓት ውሎ፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በሐውልቱ፣ በፖስተሩ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሹም ሽር ጉዳዮች ፓትርያርኩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ብርቱ ተቃውሞ እና ጥያቄ አቀረበ
ማውጫ፦
ሐተታ,
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአንድ ሊቀ ጳጳስ እና በአንድ ሥራ አስኪያጅ ብቻ እንዲመራ ተወሰነ
- ፓትርያርኩ ለሀ/ስብከቱ የመረጡትን ጳጳስ ለመሾም ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎባቸዋል
- ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሲኖዶሱ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል
- ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የፈጸሟቸውን በደሎች በዝርዝር አጥንቶ በሕግ እንዲጠየቁ የሚያደርግ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወስኗል
- ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አቡነ ሳሙኤልን ‹‹በመፈንቅለ ፓትርያርክ›› ለመክሰስ ሞክረዋል
- ‹‹ለራስ ሐውልት ከማቆም በላይ ምን ውርደት አለ? ዐፄ ኀይለ ሥላሴም ለሞተች ውሻቸው ሐውልት አቁመዋል ይባላል፤ በእርስዎ ዘመን አፍረናል፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ኄኖክ)
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2010፤ ጥቅምት 15/2003 ዓ.ም):- ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ከሰዓት በኋላ ቆይታው ቀደም ሲል በተያዙት አራት አጀንዳዎች ላይ ተነጋግሯል፤ በብዙዎቹም ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
October 25, 2010
ቅ/ሲኖዶስ 3ኛ ቀን ከሰዓት በፊት፦ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን ከሥራ አስኪያጅነት ኃላፊነታቸው አነሣ
ማውጫ፦
ሐተታ,
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2010፤ ጥቅምት 15/2003 ዓ.ም):- ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም የተጀመረውና ዛሬም ቀጥሎ የዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በዛሬው የከሰዓት በፊት ውሎው አወዛጋቢውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን ከኃላፊነታቸው አስወግዷል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን አስመልክቶ አራት አባላት ባሉት አጣሪ ኮሚቴ ቅዳሜ ዕለት ቀርቦ ባዳመጠው እና የጋለ ውይይት ተካሂዶበታል በተባለው ሪፖርት መነሻነት ነው ሥራ አስኪያጁ ከሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ ይዘውት ከቆዩት ኃላፊነታቸው እንዲነሡ የወሰነው፡፡
የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን በደል በማስረጃ አቀረቡ፤ አጣሪው ተልዕኮውን ፈጽሞ ተመልሷል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2010፤ ጥቅምት 15/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን በደልና ጥፋት የሚያሳይ ባለ 73 ገጽ የጽሑፍ ማስረጃ እና 6 የድምጽ እና የምስል (Audio and Video) ችግሩን ለማጣራት ወደ ቦታው ላቀናው ልዑክ አቀረቡ። አቤቱታ አቅራቢዎቹ ያቀረቡት ማስረጃ በደምሳሳው ሲታይ በሀ/ስብከቱ እና በልዩ ልዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተፈጽሟል የሚሉትን የገንዘብ ምዝበራ የሚያሳይ፣ በየዐውደ ምሕረቱ ስለተፈፀሙ አባቶችን የማዋረድና የማንኳሰስ ተግባራት፤ ስለተፈፀሙ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰቶች ወዘተ የሚያትት ነው።
የቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎች
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- “በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ድንጋጌ መሠረት ከጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ” በመካሔድ ላይ የሚገኘው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ መንበርነትና በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ፀሐፊነት የተወከለው 9 አባላት ያሉት ኮሚቴ አጀንዳዎች ማዘጋጀቱን፣ በዚያም ላይ ሌሎች አጀንዳዎች እንደተጨመሩበት መዘገባችን ይታወሳል። ለመረዳት እንዲያስችለን አጀንዳዎቹን እንደሚከተለው እናቀርባለን።
ሰበር ዜና፦ አባ ሰረቀ ብርሃን ደጀ ሰላምን እና ማ/ቅዱሳንን ሊከሱ ነው
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ኃላፊ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል “ደጀ ሰላም የተሰኘው ‘ድህረ ገጽ’ (ድረ ገጽ ለማለት መሆኑ ነው) … በማንነቴና በሃይማኖቴ ላይ ከባድ የግድያ ወንጀል” ስለፈፀመ “የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት በመጠቀም ወደ ፍርድ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ” መሆኑን ሰሞኑን በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።
October 24, 2010
አጣሪ ኮሚቴው በሐዋሳ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳውን ችግር ለመፍታት ቃል በተገባው መሠረት አጣሪ ኮሚቴው ሐዋሳ ከተማ ከገባ በኋላ ምእመናኑን ማነጋገሩን ትናንት ቅዳሜ ጀምሯል። የሊቀ ጳጳሱ ደጋፊዎች እና አቤቱታ አቅራቢዎች የየበኩላቸውን አቤቱታ ለአጣሪው ለማሰማት ሲሞክሩ መጯጯሆች ይሰሙ ነበር። ሁለቱም ቡድን በቅርብ ርቀት የየበኩሉን ደጋፊ አደራጅቶ የበለጠ ለመሰማትም ለመታየትም ሞክሯል። ሁለቱም አካላት ባሉበት በሐዋሳው በቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ መታየት ሲጀምር ቅዱስ ፓትርያርኩ በአጣሪ ኮሚቴ አባላቱ በኩል ለአዋሳ ምዕመናን የጻፉት ደብዳቤ ተነብቧል።
የቅ/ሲኖዶስ ሁለተኛ ቀን ውሎ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- አቡነ ሳሙኤልን ከአ.አበባ ለማስነሣት የአ.አ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች ፈረሙት ተብሎ ለአጀንዳነት የቀረበው ደብዳቤ ውድቅ ተደርጓል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- ቅ/ሲኖዶስ ትናንት ቅዳሜ ሁለተኛ ቀን ጉባዔውን ቀጥሎ ዘጠኝ አባላት ባሉት አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበለት የአጀንዳ ዝርዝር ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴው ያቀረባቸው አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ከመጽደቃቸውም በላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው ሌሎች ሁለት አጀንዳዎችም በተጨማሪ ተይዘዋል። በውይይቱ ወቅት “አዳዲስ ጳጳሳትን ስለመሾም” ቀርቦ የነበረው ሐሳብ ውድቅ የተደረገ ሲሆን አሁን የሚደረገው ሹመት አስፈላጊ አለመሆኑን ምልዓተ ጉባዔው ተስማምቶበታል።
October 23, 2010
አጣሪ ኮሚቴው ወደ ሐዋሳ ተጉዟል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳውን ችግር ለመፍታት ቃል በተገባው መሠረት አጣሪ ኮሚቴው ዛሬ ሐዋሳ ከተማ ገብቷል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው ቁጥሩ ከ700 በላይ የሚሆን የሐዋሳ እና አካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን በብዙ ደጅ ጥናት መልስ ሊያገኝበት ያልቻለውን የአቡነ ፋኑኤልን ጉዳይ ለአንዴም ለመጨረሻውም ለማከናወን ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።
October 22, 2010
የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዛሬ ውሎው አጀንዳዎችን በመቅረጽ እና ዋና ዋና መነጋገሪያ ነጥቦች ሲያወጣ ውሏል። በቅዱስ ፓትርያርኩ በጽሑፍ በተዘጋጀ ንግግር የተጀመረው ይህ ጉባኤ ቅዱስነታቸው በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው እና በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ ያላቸውን ቅሬታ ያካተቱበትን ጽሑፍ አድምጧል። ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጽሑፍ በመቃወም እንደገሰጿቸው ታውቋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ስለምን ጉዳይ ይነጋገራል?
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- በውጪ ሀገር በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋር የተጀመረው ድርድር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ይወያያል፤
- በአምናው ጉባዔ ላይ ወሳኝ መነጋገሪያ የነበረው የ“ሕገ ቤተ ክርስቲያን” ጉዳይ፤
- ስለ “ቀኖና ቤተ ክርስቲያን” ማለትም ከቦሌው ሐውልት ጀምሮ በየጊዜው ስለሚጣሱ ቀኖናዎች ጉዳይ፤
የሀገር ሽማግሌዎች አባቶችን ለማስማማት ሲሞክሩ ቆይተዋል
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ዛሬ ሲጀመር አበው በፍቅር እና በሰላም ተወያይተው መልካም ውሳኔ ለመወሰን እንዲችሉ የሚያግባባ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን ጥረት ሲያካሂድ መቆየቱ ታውቋል።
የቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎተ ምሕላ እና የብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ትናንት በጸሎተ ምሕላ ተጀምሯል። ቁጥራቸው ከ38 የማያንስ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዚሁ የመክፈቻ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ትምህርት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ስለ ቅ/ሲኖዶስ የማይገሰስ መንፈሳዊ ሥልጣን በሰፊው አስተምረዋል። “ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ሐዋርያት በኢየሩሳሌም የመሠረቱት ጉባዔ ነው። ቅዱስ (ልዩ) የተባለበት ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ስለሚመራው ነው፤
የሐዋሳ ምእመናን ለ4ኛ ጊዜ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ መጡ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ትናንት ሐሙስ በጸሎተ ምሕላ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከአዋሳ የመጡ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከትሞ ውሏል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው የሐዋሳው ሕዝበ ክርስቲያን በብዙ ደጅ ጥናት መልስ ሊያገኝበት ያልቻለውን የአቡነ ፋኑኤልን ጉዳይ ለአንዴም ለመጨረሻውም ለማከናወን ነበር ዓላማው።
የሰበካ ጉባዔ ስብሰባ ተጠናቀቀ፤ ቅ/ሲኖዶስ ተጀመረ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 21/2010፤ ጥቅምት 11/2003 ዓ.ም):- በአዲስ አበባ ከጥቅምት 6-11/2003 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ የሰነበተው ዓመታዊው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ሲጠናቀቅ ነገ አርብ የሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ አሐዱ ተብሏል።
ዝርዝሩ እንደደረሰልን እናቀርባለን።
ዝርዝሩ እንደደረሰልን እናቀርባለን።
October 19, 2010
Ethio-Dejeselamaweyan Leading USA-Dejeselamaweyan this week
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
Since the first launching of Deje Selam blogging service in November 2006, most of the visitors were from USA. It was seconded by different countries of Europe and later Canada. But after the blog was acquainted with the Ethiopian readers, the trailed their USA readers by some margin. However, this week, readers from Ethiopia came top of the table by beating USA Deje Selamaweyan in some thousand margin. Good Job D.Selamaweyan from all corners of Ethiopia.
Cher Were Yaseman,
DS
29ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ማውጫ፦
ሐተታ,
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 18/2010፤ ጥቅምት 8/2003 ዓ.ም):- ከጥቅምት 6-11/2003 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቀው ዓመታዊው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስለዚሁ ዓመታዊ ጉባዔ ሪፖርተሮቻችን ያጠናቀሩትን ዘገባ እና ሒሳዊ ሪፖርታዥ እንደሚከተለው እናቀርባለን።
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
-
▼
2010
(305)
-
▼
October
(63)
- “ሰውየውን” ታዲያ ማን እንበላቸው?
- ይድረስ ለቅዱስነትዎ
- ርእሰ አንቀጽ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “በቃ” ሊባሉ ይገባል፤
- አቡነ ጳውሎስ አልፈርምም ብለዋል፤ የሚከተለው ነገር ምንድን ነው?
- ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በጋራ ካዘጋጀው የተለየ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠታቸው ሳ...
- ቅ/ፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የቀነጨበ መግለጫ አነበቡ
- ሰበር ዜና:- አቡነ ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ
- የምስጋና መልእክት ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
- የቅ/ሲኖዱስ ምልአተ ጉባኤ ጠንካራ ውይይት በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዙሪያ
- የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊነትና ሊገጥሙት የሚችሉት ፈተናዎች
- ቅ/ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ የደ...
- ምእመኑ ምን ይላል? (ክፍል 3)
- የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ" በ20 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ትእዛዝ ተሰጥቷል...
- ሰበር ዜና፦ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
- ቅዱስ ሲኖዶስ በጳጳሳት ምደባ እና ዝውውር ጉዳይ በፓትርያርኩ በቀረበው ሐሳብ ...
- ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤ ስለ ብፁዕ አቡነ አብርሃም 2 መግለጫዎች
- ርእሰ አንቀጽ፦ የሀ/ስብከት ምደባ አጀንዳ አባቶች የምትለያዩበት/ የምትከፋፈሉበ...
- በጳጳሳት ዝውውር እና ምደባ ጉዳይ በፓትርያርኩ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከፍተኛ ...
- ምእመኑ ምን ይላል? (ክፍል 2)
- ቅ/ሲኖዶስ በሕንጻዎች እና ቤቶች አስተዳደር እና በልማት ኮሚሽን ውስጥ የሚፈጸሙ...
- ምእመኑ ምን ይላል? (ክፍል 1)
- የድምጽ አስተያየት
- “ሐውልቱ” ምን ይሁን?
- አባቶቻችን፤ እናመሰግናለን። ውሳኔው ይተገበር ዘንድ እንጠብቃለን
- የቅ/ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ ዝርዝር ሪፖርታዥ
- ሰበር ዜና፦ ቅዱስ ሲኖዶስ የአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› እንዲፈርስ ወሰነ...
- የቅ/ሲኖዶስ የዛሬ ከሰዓት ውሎ፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በሐውልቱ፣ በፖስተሩ እና በጠቅላ...
- ቅ/ሲኖዶስ 3ኛ ቀን ከሰዓት በፊት፦ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን ከሥራ አስኪያ...
- የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን በደል በማስረጃ አቀረቡ፤ አጣሪው ተልዕኮውን ፈጽሞ ...
- የቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎች
- ሰበር ዜና፦ አባ ሰረቀ ብርሃን ደጀ ሰላምን እና ማ/ቅዱሳንን ሊከሱ ነው
- አጣሪ ኮሚቴው በሐዋሳ
- የቅ/ሲኖዶስ ሁለተኛ ቀን ውሎ
- አጣሪ ኮሚቴው ወደ ሐዋሳ ተጉዟል
- የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ
- ቅዱስ ሲኖዶስ ስለምን ጉዳይ ይነጋገራል?
- የሀገር ሽማግሌዎች አባቶችን ለማስማማት ሲሞክሩ ቆይተዋል
- የቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎተ ምሕላ እና የብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት
- የሐዋሳ ምእመናን ለ4ኛ ጊዜ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ መጡ
- የሰበካ ጉባዔ ስብሰባ ተጠናቀቀ፤ ቅ/ሲኖዶስ ተጀመረ
- Ethio-Dejeselamaweyan Leading USA-Dejeselamaweyan ...
- 29ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
- "የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች" ደራሲ፣ ዘሪሁን ሙላቱ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ...
- አቡነ ፋኑኤል እና ሥራ አስኪያጁ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ የተቀጣጠለው ተቃውሞ ...
- ለአይ.ቲ ባለሙያዎች የአገልግሎት ጥሪ
- መንግሥትን “አበጀህ፣ ጎበዝ” እንበለው ወይስ ገና ነው?
- በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር እና ፋይናንስ መዋቅሮች የሐላፊዎች ሹ...
- ክርስትናን በኦርቶዶክስ ዐውደ ምሕረት ስንማረው ነገር ግን በፕሮቴስታንት መንገድ...
- ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአስተዳደራዊና መዋቅራዊ ማሻሻያ ዋዜማ?
- አቡነ ፋኑኤል እና ሥራ አስኪያጁ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ የሚጠይቀው የሐዋሳ ምእ...
- በዘሪሁን ሙላቱ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሐሙስ ተቀጠረ፤ የቅጣት ማቅለያ እ...
- «የአበባ ወር» ወርኀ ጽጌ
- Is the Deje Selam Reporting Good Or Bad?
- ዘሪሁን ሙላቱ የመከላከያ ማስረጃዎቹን አቀረበ፤ ብይኑ ለፊታችን ዓርብ ተቀጠረ
- በሙስናና ኑፋቄ የሚከሰሱት የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው ...
- ሰበር ዜና፦ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዳይመለሱ የ...
- ቤተ ክርስቲያኒቱ አገራዊ ተደማጭነቷ አደጋ ተጋርጦበታል
- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተፈጸመ ስላለው ጥፋት የምንጽፍበት ምክንያት
- ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የ1.8 ሚልዮን ብር መኪና ተሸለሙ
- መንግሥት የብዙኀን መገናኛዎች በእምነት ተቋማት ውስጥ የተበራከተውን ‹ኪራይ ሰብ...
- የመስቀለኛው ተራራ መስቀላዊ ተልእኮ
- በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው
-
▼
October
(63)

Must Read Documents
"1/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት/ የመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት አስተዳዳራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች የዳሰሰ ምልከታ"
አዘጋጅ፡- ልዑልሰገድ ግርማ የጠ/ቤ/ክ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
Click HERE to read.
2/ የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት 2004 ዓ.ም አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም ተያያዥ ዶኩመንቶች:: Click HERE to read and scroll down to (Page 5-20).
አዘጋጅ፡- ልዑልሰገድ ግርማ የጠ/ቤ/ክ/ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ
Click HERE to read.
2/ የቅ/ሲኖዶስ የጥቅምት 2004 ዓ.ም አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች፤ እንዲሁም ተያያዥ ዶኩመንቶች:: Click HERE to read and scroll down to (Page 5-20).
