(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 31/2010፤ ነሐሴ 25/2002 ዓ.ም)፦ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ወቅታዊ ሁናቴ የሚያውቁባቸው አዳዲስ የጡመራ መድረኮች በየጊዜ እየተመለከትን ነው። ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላለፉት አራት ወራት ግሩም ግሩም ጽሑፎችን እና የመወያያ ነጥቦችን እያነሣ ሲሆን ሌላው ሰባኬ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅንም በበኩላቸው የራሳቸውን መጦመሪያ (የጡመራ መድረክ http://www.kesisyaredgebremedhin.com/) ፈጥረዋል። ደስ የሚያሰኝ ነው። ባወጡት መርሐ ግብር እንዲዘልቁም እንመኝላቸዋለን። ማስታወቂያቸው እንደሚከተለው ይነበባል።
-----------------------------------------------------------------
August 31, 2010
August 30, 2010
"Anyuak Media" against our Church???
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(Deje Selam; August 29/2010):- In our website browsing, we encountered a concerning report by a certain "Anyuak Media", which labels the Ethiopian Church as "Abyssinizer". We quote the report in length as follows.
ፍርድ ቤቱ በ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ደራሲ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
August 26, 2010
አቤቱ እንድናስተውል እርዳን
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(Kiduse wwek)ከጊዜ ወደ ጊዜ የቤተክርስቲያን ፈተና እያየለ መምጣቱ ግልፅ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር ከእኛ የሚጠበቀውንና መፍትሔ ይሆናሉ ያልኳቸውን ጽፌላችኋለሁ፡፡ ጠቃሚ ነው ካላችሁ የጠመመውን አቅንታችሁ የተሳሳተውን አርማችሁ ለንባብ አብቋት ፡፡1ኛ. ወንጀል ሲፈጸም እያዩ ዝም ማለት እንኳን በፈጣሪ ዘንድ በምድራዊ መንግስትም ዘንድ ስለሚያስጠይቅ በሰበካ ጉባኤ ፣በህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ፣በሰ/ት/ቤት በማኅበራት ውስጥ የምናገለግል ሁሉ የነቃ ተሳትፎ ማድረግና ለሙስናና ለፈተና የማያጋልጥ አሰራር መስራት አለብን፡፡ ከዚህ ባለፈ የሚሰሩትን ወንጀሎች ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብ ማጋለጥ ይጠበቅብናል፡፡
August 25, 2010
ENOUGH IS ENOUGH!
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(By Tewahedo)
These wolves in sheep-clothing should be removed from our church ones for all. They have understood the psychology of the fathers (including that of the politically-minded patriarch) and thus are playing a game for their own advantage. As the saying goes:YE'ASA GIMATU KANATU - since the patriarch himself is void of spirituality, Begashaw, Zerihun and their allies have become confident that no one will confront them for their disturbingly immoral deeds. They know that they can buy the hand of the patriarch and use him for their own advantages as we saw in the statue shameful drama. Hence, let me propose a few points to clean the mess in our mother Church:
These wolves in sheep-clothing should be removed from our church ones for all. They have understood the psychology of the fathers (including that of the politically-minded patriarch) and thus are playing a game for their own advantage. As the saying goes:YE'ASA GIMATU KANATU - since the patriarch himself is void of spirituality, Begashaw, Zerihun and their allies have become confident that no one will confront them for their disturbingly immoral deeds. They know that they can buy the hand of the patriarch and use him for their own advantages as we saw in the statue shameful drama. Hence, let me propose a few points to clean the mess in our mother Church:
August 24, 2010
ዘሪሁን ሙላቱ እና በጋሻው ደሳለኝ እንዲወገዙ እና እንዲከሰሱ ሰባክያነ ወንጌል ጠየቁ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 24/2010፤ ነሐሴ 18/2002 ዓ.ም):- በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩ በሀገረ ስብከቱ ገዳማት እና አድባራት ተመድበው የሚያገለግሉ ሰባክያነ ወንጌል፣ ‹‹ለወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ችግር እና ለአባቶች ክብር መደፈር መንሥኤ ነው›› ያሉት በጋሻው ደሳለኝ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት ጉባኤ እንዲወገዝ እና ክስ እንዲመሠረትበት፣ ‹ሊቀ ትጉሃን› ዘሪቱ ሙላቱ ደግሞ እንዲወገዝ ጥያቄ የሚያቀርብ የአቋም መገለጫ አወጡ፡፡ ስብሰባው ‹‹በሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› መጽሐፍ የተነሣ ክፉኛ ለተረበሹት ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመወገን፣ ሰባኪውን በፀረ ዘሪሁን አቋም ዙሪያ አስተባብሮ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲወገዝ ለመጠየቅ እና መጽሐፉን በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የተባሉትን ሰባክያነ ወንጌል ለማስጠንቀቅ ታስቦ የተጠራ ነበር፡፡
August 22, 2010
‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ፍ/ቤት ቀረበ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 21/2010፤ ነሐሴ 15/2002 ዓ.ም):- ትናንት አርብ ተሲዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛው መኖርያ ቤት ሳለ የተያዘው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በዛሬው ዕለት ጠዋት አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኝ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መቅረቡ ታውቋል፡፡ እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ‹‹በስም ማጥፋት›› ወንጀል ክስ የመሠረቱበት ይኸው ጸሐፊ ለኀሙስ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2002 ዓ.ም (ኦገስት 26/2010) ዳግመኛ እንዲቀርብ ከተወሰነ በኋላ በፖሊስ ተይዞ የተወሰደ ሲሆን ከሳሾችም በርግጥም ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ እርሱ መሆኑን የሚያረጋግጡላቸውን አስረጅ ምስክሮች በዕለቱ እንዲያቀርቡ ታዝዘዋል፡፡ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት ያልደረሰበት ፀሐፊው ሊያዝ የበቃው የቅርብ በሚላቸው ጓደኞቹ ጠቋሚነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡
August 21, 2010
August 20, 2010
እጅጋየሁ እና ፋንታሁን ከፓትርያርኩ ጋራ መከሩ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ታግዶ የቆየውን የእነ በጋሻው የአሰበ ተፈሪ ጉባኤ አስፈቀዱ፤
‹‹የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ዘሪሁን ሙላቱ ተያዘ፤ ለሥራ አስኪያጅ ፋንታሁን ሊደረግ የታሰበው ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ታገደ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 20/2010፤ ነሐሴ 14/2002 ዓ.ም):- ሰሞኑን በእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ከፍተኛ ክትትል ሲደረግበት የቆየው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ በተለምዶ ኮልፌ - 18 ማዞርያ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው በርከት ባሉ ሲቪል የለበሱ የደኅንነት ኀይሎች እና ዘግየት ብለው ወደ አካባቢው በደረሱ ሁለት ፖሊሶች ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን›› በሚል ተይዞ መወሰዱን የዐይን እማኖች ገለጹ:: ስውሩ ጸሐፊ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ተይዞ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ስፍራ የተወሰደው ዳንኤል ከሚባል ጓደኛው መኖርያ ቤት መሆኑን የዐይን ምስክሮቹ ተናግረው በጸሐፊው እና በጸጥታ ኀይሎቹ መካከል ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንደ ነበር ትዕይንቱን በርቀት ሲከታተሉ የነበሩት እኒሁ የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል፡፡
August 19, 2010
አለቃ አያሌው ታምሩ እና ትምህርታቸው፦ ፫ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ
Posted by
DejeS ZeTewahedo

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 19/2010)፦ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት እንደ ሰማይ ኮከብ፣ እንደ ምድር አሸዋ የሚበዙ ሊቃውንት አፍርታለች። ከነዚህ ሊቃውንት መካከል ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አለቃ አያሌው ታምሩ አንዱ ናቸው። ስለ ሕይወት ታሪካቸው፣ ሥራዎቻቸውና ተያያዥ ጉዳዮች በስማቸው የተሰየመውን ድረ ገጽ እንድትመለከቱ እየጋበዝን ስለ ትምህርታቸው የሚናገረውን ክፍል ቀንጭበን ለማቅረብ ወደድን።
“የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች”ን ማንበብ ከፈለጉ ...
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010)፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer) ዘሪሁን ሙላቱ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ማውጣቱን፤ እነ በጋሻው ደሳለኝና ኤልዛቤል የምትባለው ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደተጠቀሱበት፤ ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም የደረበው Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ ጊዜውን በቶሎ በማጥናት እና የፓትርያርኩ ሐውልት ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ሲመለከት፣ የሐውልቱ ተቃዋሚዎች ያሉትን በመሰብሰብና መጽሐፍ አድርጎ በማሳተም ሲያሳዝነው የሰነበተውን ምእመን አሁን ደግሞ ገንዘቡን ሊበላው ይህንን ፓምፍሌት (መጽሐፍ ለማለት ይከብዳል) ማሳተሙን በተከታታይ መዘገባችን ይታወሳል። መጽሐፉን ማንበብ ለፍርድ ይመቻልና እነሆ እንዲህ አዘጋጅተነዋል። ለማንበብ ይህንን (አስነብበኝ) ይጫኑ።
August 18, 2010
ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊበረክትላቸው ነው
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010፤ ነሐሴ 12/2002 ዓ.ም):- በቁጥር ከስድሳ የማያንሱ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች እና አንዳንድ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ለአወዛጋቢው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊያበረክቱ ማቀዳቸው ተሰማ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ‹‹የማጽናኛውን መዋጮ›› ለማስፈጸም በዋናነት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ጸሐፊዎች እና አንዳንድ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ማጽናኛው የሚከናወነው ጸሐፊዎቹ ባሰባሰቡት የገንዘብ አስተዋፅኦ ነው፡፡
August 15, 2010
እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ የ “ሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች ”መጽሐፍ ደራሲን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ ናቸው
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ወጣባቸው፤
August 14, 2010
በርግጥ መጋቤ ብሉይ የተናገሩት የእርቁ እንቅፋት ሊሆን ይገባ ነበር?
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ገብር ሔር ዘመ/መንግሥት እንደጻፈው፤ ኦገስት 14/2010፤ ነሐሴ 8/2002 ዓ.ም)፦ በአንድ ወቅት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በሰሜን አሜሪካ ለሚሰራጨው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ የሰጡት መግለጫ ሰሜን አሜሪካንን ለአስራ ስምንት ዓመታት ላላነሰ ግዜ መኖሪያ ባደረጉት “ስደተኛ አባቶች” ዘንድ አቡዋራ ማስነሳቱን በተባራሪ ወሬ ሰምቼው ነበር። ሳይጀመር ለተጠናቀቀው የሰላምና ዕርቅ መሰናክል የሆነውም ይኸው መግለጫ እነደሆነ ይፋ ሲሆን ሊቁ የተናገሩትን ወይም የሰጡትን መግለጫ ለመስማት ልቡናዬ ተጋ። ግን ከየት አግኝቼ ማድመጥ እችላለሁ? እያልኩ ሳሰላስል የመረጃ ጎተራ የሆነችው ደጀ ሰላም በግራም በቀኝም፤ በድጋፍም በጥላቻም ለተሰለፈው ሁሉ ዕርቀ ሰላሙ ሳይጀመር እንዲያልቅ ምክንያት ሆነ የተባለውን የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴን ቃለ መጠይቅ እነሆ ብላ የመረጃ መረብ ሰሌዳዋ ላይ አወጣችውና የመረጃ ፍላጎት ጥማቴን አስታገሰችልኝ፡፡ በዚሁ እግረ መንገዴን ትጉሁን የደጀ ሰላም (የእርሱን አባባል ልጋራና) ጦማሪ (በልቶ ጠጥቶ ጠግቦ ረክቶ ሳያመሰግን ሹልክ ብሎ እንደሚሄድ ሰው እንዳይመስልብኝ) እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ እላለሁ፡፡
August 13, 2010
የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ቃለ ምልልስ “ስለ ፓትርያርክ ከሥልጣን መውረድ እና መሻር”
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ለአባቶች ድርድር መሰናከል ምክንያት ሆኗል የተባለው የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ቃለ ምልልስ “ስለ ፓትርያርክ ከሥልጣን መውረድ እና መሻር”
M.B Seife Silassie Yohannes about Patriarch Change in Ethiopian Orthodox Church from Deje Selam on Vimeo.
M.B Seife Silassie Yohannes about Patriarch Change in Ethiopian Orthodox Church from Deje Selam on Vimeo.
August 10, 2010
የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሪፖርታዥ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ‹‹ማወቅ ትርጉም ያገኘው በመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ነው፤ ከካባቸው በላይ ሊቅነታቸው ጎልቶ ይታይ ነበር፤ ሊቅነት ብቻ ሳይኾን ይህ ጎደለህ የማይባል መልካም ጠባይዕ ነበራቸው፤ ለእርሳቸው እንዲህ ያለ አቋራጭ ጊዜ ይመጣል ብለን አልጠበቅንም፤ ሰላምን ለማምጣት በመፋጠን ላይ እንዳሉ ከረጅም መንገድ መጥተው ወደ ረጅም መንገድ ሄዱ - የሰላም መልእክተኛ ኾነው ሁሉንም በፍቅር እና በትዕግሥት እያዩ ነው የሄዱት፤ ይኼ ራሱ ትልቅ ምስክርነት ነው እኮ!!›› (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ)
- ‹‹በቅንነት እና በታማኝነት ያገለገሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል፡፡›› (የኀዘን መግለጫው)
August 9, 2010
የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች:- የስውሩ ፀሐፊ “ስም አጥፊ” አዲስ መጽሐፍ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ድሮም ዘንድሮም ወደፊትም ያው ናቸው፡፡ ነገሮች ሁሉ ባልተለወጡበት እና ባሉበት ኹኔታ እየቀጠሉ በጋሻውን የለወጠው ኹኔታ ስታሰብ የጥቅሙን ስፍራ ከማዘዋወር በቀር የሚገባን ነገር የለም፡፡››
- ወ/ሮ እጅጋየሁ ‹‹የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር አየር ባየር ትመራለች፡፡››
- ‹‹የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት መቶ ሺሕ ብር አውጥቶ ያስገነባው በጋሻው ስርየት የሌለው ጥፋት ውስጥ የገባ የራሱን ጥቅም ማዕከል በማድረግ ነው፡፡››
- ስለ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒን ምንም አለመናገሩ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡
August 8, 2010
የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሰኞ ይፈጸማል
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2010)፦ በትላንት ዕለት በድንገተኛ ሕመም ሕይወታቸው ያለፈው የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሰኞ፣ ነሐሴ ሦስት ቀን 2002 ዓ.ም በስምንት ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡
በትላንትናው ዕለት ረፋድ ላይ ለእርቅ እና ድርድር ጉባኤ የሄዱበትን የአሜሪካ ተልእኮ አጠናቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ እንደ ደረሱ ራሳቸውን የማቃጠል እና ልባቸውን የመውጋት ስሜት እንደተሰማቸው አብረዋቸው ለተጓዙት የልኡካን ቡድኑ አባላት የተናገሩት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ አስቸኳይ ሕክምና ሊያገኙ ይችሉ ከነበረበት ስፍራ ርቆ እና ከጊዜው ዘግይቶ አራት ኪሎ አካባቢ ቀድሞ ‹‹ጉድሸፐርድ›› አሁን ‹‹አዲስ የሕፃናት እና እናቶች ሆስፒታል›› በሚባለው የሕክምና ተቋም ውስጥ የመጀመርያ ደረጃ ምርመራ እየተደረገላቸው ሳለ ነበር ሕይወታቸው ያለፈው፡፡ ወዲያኑ አስከሬናቸው በቅዱስ ገብርኤል እና በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ምርመራ ከተካሄደለት በኋላ ዛሬ ቀትር ላይ ሰበካቸው በሚገኝበት እና በአገልግሎት ብዙ በደከሙበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡
August 7, 2010
ሰበር ዜና፦ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ አረፉ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 7/2010)፦ ሰሞኑን ለአባቶች ድርድር አሜሪካ የሰነበቱትና አርብ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተነሥተው ቅዳሜ ጠዋት አዲስ አበባ የደረሱት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ ቤታቸው እንኳን ሳይደርሱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በዚህ ጊዜ አሉ ከሚባሉት ሊቃውንት መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ በአንደበት ርቱዕነታቸው፣ በቅኔ አዋቂነታቸው፣ በሰባኪነታቸው የተመሰገኑና የተከበሩ ነበሩ።
መግለጫዎቹ መግጫ፣ መገጫ፣ መገጫጫ ባይሆኑ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 6/2010):- እነሆ አባቶችን ለማስታረቅ የተደረገው ሙከራ የተፈለገውን ያህል ሳይራመድ መቅረቱን ስንዘግብ ቆይተናል፤ አሁን ደግሞ አሸማጋዩ ክፍል “መግለጫ”ውን አውጥቶ የሄደበትን ሒደት እና የደረሰበትን፣ እንዲሁም ድርድሩ የፈረሰበትን ምክንያት ነግሮናል። ከዚህኛው ጋር በድምሩ ሦስት መግለጫ አንብበናል ማለት ነው። ነገ ደግሞ ሌላ መግለጫ ሊመጣ፣ ለዚያ መልስ የሚሰጥ ሌላ መግለጫ እንዳይወጣ፣ ያንን የሚያስተባብል ሌላ መግለጫ እንዳይከተል እና መግለጫዎቹ መግለጫነታቸው ተረስቶ “መግጫ፣ መገጫ እና መገጫጫ” እንዳይሆኑ ከወዲሁ ለመጠቆም ወደድን።
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባዔ” መግለጫውን አወጣ፤ ድርድሩ በሦስት/አራት ወራት ውስጥ ይቀጥላል
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 6/2010):- በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ያለውን መለያየት ለማስወገድ የማሸማገል ተግባር ሲፈጽም የነበረው የሰላምና የአንድነት ጉባዔ መግለጫውን አውጥቷል፤ ድርድሩ ከሦስት እስከ አራት ወራት ውስጥ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን (PRESS RELEASE) ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣አሜን
August 5, 2010
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላምና አንድነት ከተላከው ልዑክ የተሰጠ መግለጫ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ የተጀመረው ድርድር ሁለቱን ተደራዳሪ ወገኖች ፊት ለፊት ለማገናኘት እንኳን ሳይችል መክኖ መቅረቱን ተከትሎ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ ለመደራደር ከአዲስ አበባ የመጣው ልዑክ መግለጫውን ዛሬ አውጥቷል። ልዑኩ ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ (http://www.eotcdc.org/) ይጫኑ። በተያያዘ ዜና የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ ላይ በትናንትናው ዕለት ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል። የአሜሪካውን ወገን መግለጫ ለማንበብ እዚህ (መግለጫ) ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

እርቅ በማያውቁ አባቶች እና በ“ሰላም ድርድራቸው” ዙሪያ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ሰላምን ልትሰብክ በተመሠረተች፣ ስትሰብክም በምትኖር ቤተ ክርስቲያን ላይ በተሾሙ አባቶች መካከል ሰላም ከራቀ፤ ከደካማ ሥጋችን በእውነት የተዋሐደውን አምላክ እየሰበከች «ተዋሕዶ» የምትባልን ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ በተሾሙ አባቶች መካከል በእውነት መዋሐድ ከጠፋ ይኸውና አንድ ሕጻን ተወልዶ ለዐቅመ አዳም ደረሰ፡፡ በእነሱ ሳይኾን በፈጠሩት ችግር ዕድሜ መጠን ሲያስቡ ቆይተው ይመስላል፤ ይኸውና ችግሩ 19 ዓመት ሞልቶት ለአካለ መጠን ሲደርስ ሰላምን በመካከላቸው ለማውረድ ለውይይት መቀመጣቸውን ሰምተን፣ በዚህም በእጅጉ ደስ ብሎን ነበር። ምክንያቱም በደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ይጠብቁ፣ መንጋውንም ይሰበስቡ ዘንድ የተቀመጡትን አባቶች መለያየት እያየን፤ ያንንም ተገን አድርጎ በየደረጃው ባለው የቤተ ክርስቲያን ምልአት የሚፈጠሩ የጥፋት ሆያ ሆዬዎችን እያየን ስናዝን ኖረናልና፡፡
የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና በድንጋይ ተደበደበ፤ በሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ከአገልግሎት በመመለስ ላይ በነበሩት በጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና ላይ በተሰነዘረ የድንጋይ ውርወራ የመኪናቸው መስተዋት ሲረግፍ በእርሳቸውም ሆነ መኪናው ውስጥ በነበሩት በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ።
አደጋው የደረሰው ብፁዕነታቸው ሰኞ (26/11/2002) ከቀኑ 10፡00 ላይ ጦላይ ኪዳነ ምሕረት በነበረ ጉባኤ ላይ ቡራኬ ሰጥተው ወደ ጅማ ሲመለሱ መሆኑን እማኞች ገልፀዋል።
አደጋው የደረሰው ብፁዕነታቸው ሰኞ (26/11/2002) ከቀኑ 10፡00 ላይ ጦላይ ኪዳነ ምሕረት በነበረ ጉባኤ ላይ ቡራኬ ሰጥተው ወደ ጅማ ሲመለሱ መሆኑን እማኞች ገልፀዋል።
August 4, 2010
ሰበር ዜና፦ እርቀ ሰላሙ ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ሳይታሰር ተበተነ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ልዑካኑም ሳይወያዩ ተበተኑ።
ከትናንት በስቲያ ሰኞ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ “የሰላምና የእርቅ ጉባዔ” በተሸማጋዬቹ መካከል ማድረግ የፈለገውን ውይይት ማድረግ ሳይችል፣ ሁለቱን ልዑካን ፊት ለፊት ማገናኘት ሳይችል፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ ብቻ ሲደራደር ቆይቶ እንዲሁ ተበትኗል። ይኸው ውይይት ውጤት እንደማያመጣ በታወቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ ላይ አውጥቶታል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
August 2, 2010
በሐዋሳ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት እና የሀገረ ስብከቱ ‹ልኡካን› ውዝግብ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ‹‹ከእኛ ወገን አልያም ከዐመፀኛ ኀይሎች ጋራ ለመኾናችሁ ሚናችኹን ለዩ! በእንጀራችኹ ፍረዱ!! ፓትርያሪኩም ቢኾኑ አያድኗችኹም!!›› (አቡነ ፋኑኤል)
- ‹‹በእንጀራችሁ ፍረዱ!›› (ሥራ አስኪያጁ)
የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች ከፓትርያርኩ ጋራ ተወያዩ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ፤
- ችግሩን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወሰነ፤
- ‹‹ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ኀበ ሐዋሳ ንሐውር፤. . . የሐዋሳን ሕዝብ ከመውደዴ የተነሣ እኔ ራሴን የአጣሪ ኮሚቴው አባል ባደርግ ደስ ይለኝ ነበር፤›› (አቡነ ጳውሎስ)
- ‹‹ምእመኑ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ከመመለስ ውጭ የሚያገባው ጉዳይ የለም፤ የቅዱስ ሲኖዶሱን ሕገጋት የማወጣም ኾነ የምሽር እኔ ነኝ፤›› (አቡነ ፋኑኤል)
ውይይቱና ሽምግልናው በምን ዙሪያ?
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 1/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ኦገስት 2/2010 (ሐምሌ 26/2002 ዓ.ም) ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሁለቱም በኩል ያሉ ተወካይ “የሰላም ልዑካን” ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ተሰባስበዋል። እንደተለመደው ውይይቱ እንደሚደረግ በደፈናው ከመታወቁ ውጪ በምን ዙሪያ፣ እንዴት የሚለው ጉዳይ “በምስጢር” ስለተያዘ ብዙም ለማለት አያስደፍርም። ቤተ ክህነቱን የብልሹ አሠራር ምንጭ ያደረገውና ለዚህ ሁሉ ውድቀት ያበቃን ዋነኛው ምክንያት ነገሮችን ከሚመለከተው አካልና ምእመን ደብቆ የመሥራት አባዜ ስለሆነ ይህ ብልሹ አመለካከት ይሰበር ዘንድ ዝምታው ይሰበር፣ መጋረጃው ይቀደድ እንላለን፤ ስለዚህም እንጽፋለን።
August 1, 2010
ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሲዘከሩ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(በሔኖክ ያሬድ):- ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ሐሙስ በአዲስ አበባ በ"ባሕር" አቅጣጫ (በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ) ጉለሌ አካባቢ ካንድ ዐውደ ጥናት ተገኝቼ በ10 ሰዓት አካባቢ ወደ ፒያሳ ሳመራ ቀልቤን የገዛ ክስተት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ፣ የአሁኑን የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ፋኩልቲ እንዳለፍኩ፣ በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡበት ትዕይንት እየተካሄደ መሆኑን አስተዋልኩ፡፡
የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት የከበቡትን ሰዎች መካከል ልብሰ ጵጵስና የለበሱ ከመሐል ኾነው በርቀት ሲናገሩ ይታየኛል፤ የሚኒባስ ታክሲ ሹፌሩን እንዲያወርደኝ አድርጌ ታዳሚውን ተቀላቀልኩ፡፡
የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት የከበቡትን ሰዎች መካከል ልብሰ ጵጵስና የለበሱ ከመሐል ኾነው በርቀት ሲናገሩ ይታየኛል፤ የሚኒባስ ታክሲ ሹፌሩን እንዲያወርደኝ አድርጌ ታዳሚውን ተቀላቀልኩ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
-
▼
2010
(305)
-
▼
August
(31)
- አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን
- "Anyuak Media" against our Church???
- ፍርድ ቤቱ በ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ደራሲ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈ...
- አቤቱ እንድናስተውል እርዳን
- ENOUGH IS ENOUGH!
- ዘሪሁን ሙላቱ እና በጋሻው ደሳለኝ እንዲወገዙ እና እንዲከሰሱ ሰባክያነ ወንጌል ...
- ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ፍ/ቤት ቀረበ
- የቪኦኤ ሪፖርታዥ- ስለ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ
- እጅጋየሁ እና ፋንታሁን ከፓትርያርኩ ጋራ መከሩ
- ‹‹የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ዘሪሁን ሙላቱ ተያዘ፤ ለሥራ አስኪያጅ ፋን...
- አለቃ አያሌው ታምሩ እና ትምህርታቸው፦ ፫ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ
- “የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች”ን ማንበብ ከፈለጉ ...
- ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊበረክትላቸው ነው
- እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ የ “ሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች ”መጽሐፍ ደራሲን ለመክሰስ በዝ...
- በርግጥ መጋቤ ብሉይ የተናገሩት የእርቁ እንቅፋት ሊሆን ይገባ ነበር?
- የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዘገባ ስለ አባቶች የሰላም ድርድር
- የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ቃለ ምልልስ “ስለ ፓትርያርክ ከሥልጣን መውረድ እና ...
- የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሪፖርታዥ
- የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች:- የስውሩ ፀሐፊ “ስም አጥፊ” አዲስ መጽሐፍ
- የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሰኞ ይፈጸማል
- ሰበር ዜና፦ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ አረፉ
- መግለጫዎቹ መግጫ፣ መገጫ፣ መገጫጫ ባይሆኑ
- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባዔ” መግለ...
- ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላምና አንድነ...
- እርቅ በማያውቁ አባቶች እና በ“ሰላም ድርድራቸው” ዙሪያ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦ...
- የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና በድንጋይ ተደበደበ፤ በሰዎች ላይ ምንም አደጋ አ...
- ሰበር ዜና፦ እርቀ ሰላሙ ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ሳይታሰር ተበተነ
- በሐዋሳ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት እና የሀገረ ስብከቱ ‹ልኡካን› ውዝግብ
- የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች ከፓትርያርኩ ጋራ ተወያዩ
- ውይይቱና ሽምግልናው በምን ዙሪያ?
- ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሲዘከሩ
-
▼
August
(31)











