በትንሣኤ 25ኛ ቀን በዋለው ርክበ ካህናት የተጀመረው ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት፤ ከአገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተሳታፊነት የሚካሔድ ሲሆን፤ በጉባኤው የቤተ ክርስቲያኗ የልማት ተግባሮች የሚተረጐሙበትና የተከናወኑትም የሚገመገሙበት እንደሚሆን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ዕለት ዘግቦ ነበር፡፡
April 30, 2010
ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፀሐፊውን መረጠ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
April 29, 2010
በሦስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ “ዘመናዊ አማርኛ ቋንቋ ለልጆች ማስተማሪያ ዲቪዲ" በለንደን ሊመረቅ ነው
Posted by
DejeS ZeTewahedo
በተለያየ ዓለም ለተወለዱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመኑ በሚመጥን መልኩ ይህን ፊደል እና ቋንቋ ለመማር በቂ መርጃ እንደሚሆን የተነገረለት ይህ ዝግጅት በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውለደ ኢትዮጵያውያን የአማርኛ ቋንቋ እና የኢትዮጵያውያን ልዩ ታሪክ ለማስተማር እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
April 26, 2010
የቤተ ክርስቲያን ቅን መሪ ቅዱስነታቸው አባ ሽኖዳ ስለምን አለቀሱ?
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 26/2010)፦ ቅዱስነታቸው ፖፕ ሽኖዳ 3ኛ 117ኛው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው። እንደተለመደው ከምእመናን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚመልሱበት የተለያየ ዝግጅት አላቸው። ከዝግጅቶቻቸው መካከል በየሳምንቱ በካይሮ በመንበረ ማርቆስ የሚያደርጉት አንዱ ነው። እነዚህን የምእመናን ጥያቄዎች So Many Years With The Problems Of People” በሚል ርዕስ እየታተሙ ለንባብ በቅተዋል። ጥያቄዎቹ ዶግማን፣ ሥርዓትን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የተመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። በእጄ ገብተው ያነበብኳቸው እነዚህ መጻሕፍት ላይ እንደተመለከትኩት ከሆነ መልሶቻቸው የማያወላዱ፣ በአጭር አባባል ብዙ መልስ የሚሰጡ ናቸው። በቅርቡ ለተጠየቁት አንድ ጥያቄ ግን በቃላት መልስ ከመስጠት ይልቅ በእንባና በዝምታ መመለስን መርጠዋል። ከንግግራቸው በአጭሩ እንመልከት።
April 23, 2010
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕክምና ላይ ናቸው፣ ታይላንድ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 23/2010)፦ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ታመው ባንኮክ ታይላንድ ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው። የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣው የሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶች መካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል።
ያንን ወንጀል የፈፀሙት ሰዎች ማንነት ሳይጣራ እስካሁን ቆይቶ እነሆ ሐምሌ 2002 ዓ.ም ሲመጣ ዓመት ይሞላዋል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም ማዕከሏ የሆነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተደፈረና ሕገ ወጦች በሯን ከፍተው ሊቃነ ጳጳሳቷ ላይ አደጋ ከቃጡ ዓመት ሞላ ማለት ነው።
ያንን ወንጀል የፈፀሙት ሰዎች ማንነት ሳይጣራ እስካሁን ቆይቶ እነሆ ሐምሌ 2002 ዓ.ም ሲመጣ ዓመት ይሞላዋል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም ማዕከሏ የሆነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተደፈረና ሕገ ወጦች በሯን ከፍተው ሊቃነ ጳጳሳቷ ላይ አደጋ ከቃጡ ዓመት ሞላ ማለት ነው።
April 19, 2010
“የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” (Orthodox Photo Bank Service):- ማስታወቂያ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 19/2010)፦ “ደጀ ሰላም” የጀመረችውን የድረ ገጽ ጡመራ እና የመረጃ ልውውጥ የበለጠ በማጠናከር ለመቀጠል እንድትችል አንባብያንን የሚከተሉትን ነገሮች ይልኩላት ዘንድ በትህትና ትጋብዛለች። በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎች የምናገኝበት ጠንካራ ድረ ገጽ ስለሌለን በዚህ ቴክኖሎጂ ዘመን ከሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሲነጻጸር ወደ ሁዋላ ቀርተናል ማለት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት እንዲቻል “ደጀ ሰላም” “የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” ((Orthodox Photo Bank Service) ትጀምራለች። “ፎቶ ባንክ” ያልነው ፎቶዎችና ቅዱሳት ሥዕላት የሚጠራቀሙበት “ግምጃ ቤት” ለማለት ነው።
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር “በበጋሻው ሥራዎች ላይ ጥናት እያደረኩ ነው” አሉ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 18/2010)፦ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም “አርማጌዶን” የሚለው የስብከት ሲዲን ተከትሎ በተነሣው የዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ ሃይማኖታዊ “ሥራዎች” ዙሪያ ጥናት እንደሚያደርጉ መገለፁን “ያኔት” መጽሔት በሚያዚያ 2002 ዓ.ም እትሙ ዘግቧል። ይህ የተገለጸው ዲ/ን በጋሻው ከቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከብፁዓን አባቶች ፊት በቀረበበት ወቅት ነው።
April 13, 2010
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለሕክምና ግሪክ ናቸው
Posted by
DejeS ZeTewahedo
አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርባቸውና በእግራቸው ላይ የሚሰማቸውን ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ግሪክ ያቀኑ ሲሆን በመከታተል ላይ ያሉት ሕክምና ከረዳቸው እንደ ጥንቱ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ለማገልገል ይቻላቸዋል ማለት ነው።
April 12, 2010
“የሲዲ ስብከት በነጻ”
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ሰላም ደጀ ሰላሞች፤
አንዲት መልዕክት ነበረችኝ። ትናንት በዳግማዊ ትንሣዔው ወደ ዋሺንግተን የዲሲዋ የቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሄዱ ሰዎች ቅዳሴውን ጨርሰው ሲወጡ አንድ “ገጸ በረከት” ሲታደላቸው ነበር። ሥጦታው “የትምህርት ሲዲ” ሲሆን “ከኢትዮጵያ ዲ/ን በጋሻው ነው የላከላችሁ” እየተባለ በነጻ ይታደል ነበር። ጉዳዩን የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ይወቀው አይወቀው ግልጽ አይደለም። ከዐውደ ምሕረቱም ስለ ሲዲው የተባለ ነገር አልነበረም። ይኸው “ደህና” የሚለው የዲ/ን በጋሻው ስብከት ከአዲስ አበባ አቋርጦ በዲሲ ጎዳና በነጻ የሚሠራጭበት መንገድ ትንሽ ግር አሰኝቶኛል።
April 11, 2010
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(Mahibere Kidusan) ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ምእመናን በሦስት ነጥብ ስድስት /3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ራንድ/ ተገዝቶ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚያመች መልኩ የተሠራው የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤተ ተከበረ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ፕሪቶሪያ የሚገኘው ይኸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ጥር 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት
ጥንታዊው የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በአደጋ ላይ ነው
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(Mahibere Kidusan)
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ደገም ወረዳ የሚገኘውና በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሠሩት የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በእርጅና ምክንያት በመፈራረስ ላይ ይገኛል፡፡ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፉት ሲዘዋወሩ ካሠሩአቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መሆኑን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ደገም ወረዳ የሚገኘውና በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሠሩት የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በእርጅና ምክንያት በመፈራረስ ላይ ይገኛል፡፡ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፉት ሲዘዋወሩ ካሠሩአቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መሆኑን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(Mahibere Kidusan) በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የምትገኘውን የፍርኩታ ጽርሐ አርያም መንበረ መንግሥት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጥንታዊት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ፡፡ ገዳሟን ለማደስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የላከው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ገዳሟ ከተመሠረተችበት 1450 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ትተዳደረበት የነበረ የራሷ መሬት ነበራት፡፡
April 9, 2010
እንኳን ለ“ዳግማዊ ትንሣኤ”ው ዋዜማ በደህና አደረሳችሁ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 9/2010)፦ ውድ ደጀ ሰላማውያን፤ እንኳን ለዳግማዊ ትንሣኤው ዋዜማ በደህና አደረሳችሁ። ትንሣኤ በተለይም በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ በታላቅ ሁኔታ ነው የሚከበረው። ምዕራባውያን ግን ወደ ልደት (Christmas) ያደላሉ። የምሥራቅ ክርስቲያኖች (እኛ ኦሪየንታሎቹም ሆን ግሪኮቹ) ወደ ትንሣኤው አከባበር የበለጠ እናደላለን። ምክንያት? የክርስትና እምነት ከሌላው የምትለየው ሞትንና በመቃብር መበስበስን (ሙስና መቃብር) ደምስሶ በተነሣው ወልደ አብ ወልደ ማርያም የተመሰረተች ስለሆነች ነው። በበረት የተወለደው፣ በባሕረ ዮርዳኖስ የተጠመቀው፣ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጸው ጌታ እኩዮች አይሁድ እንደሰቀሉት ሞቶ ቢቀር ኖሮ የክርስትና ሃይማኖት ስም አጠራሩ በጠፋ ነበር። April 4, 2010
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን/ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ/ Khristós Anésti! Alithós
Posted by
DejeS ZeTewahedo
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ... በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን ....................... አግዓዞ ለአዳም
ሰላም........................................... እምይእዜሰ
ኮነ ..................................... ፍስሐ ወሰላም::
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ........ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
ሰይጣንን አሰረው ................ አዳምን ነጻ አወጣው
ሰላም ................................... ከእንግዲህ
ሆነ ........................................ ደስታና ሰላም
አሠሮ ለሰይጣን ....................... አግዓዞ ለአዳም
ሰላም........................................... እምይእዜሰ
ኮነ ..................................... ፍስሐ ወሰላም::
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ........ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
ሰይጣንን አሰረው ................ አዳምን ነጻ አወጣው
ሰላም ................................... ከእንግዲህ
ሆነ ........................................ ደስታና ሰላም
April 1, 2010
በሊቢያ በኩል ጣሊያን ስለሚገቡ ኦርቶዶክሳውያን ስደተኞች እውነተኛ ታሪክ (ክፍል 2)
Posted by
DejeS ZeTewahedo
... ከፕሮግራም በኋላ በባህር የመጡትን ወንድሞችና እህቶች ማነጋገር ፈልጌ አንዲት እህትን ጠየኳት። እሷም በባህር ከመጡ ልጆች ጋር አገናኘችኝ። በርግጥ ብዙ ቢሆኑም ከብዙ 4 ብቻ ለማቅረብ ወደድሁኝ። አንብቡት፡- የመጀመሪያዋን እህት እነሆ::
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
-
▼
2010
(305)
-
▼
April
(14)
- ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፀሐፊውን መረጠ
- በሦስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ “ዘመናዊ አማርኛ ቋንቋ ለልጆች ማስተማሪያ ዲቪዲ" በ...
- የቤተ ክርስቲያን ቅን መሪ ቅዱስነታቸው አባ ሽኖዳ ስለምን አለቀሱ?
- ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕክምና ላይ ናቸው፣ ታይላንድ
- “የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” (Orthodox Photo Bank Servi...
- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር “በበጋሻው ሥራዎች ላይ ጥናት እያደረኩ ...
- ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለሕክምና ግሪክ ናቸው
- “የሲዲ ስብከት በነጻ”
- በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
- ጥንታዊው የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በአደጋ ላይ ነው
- የፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ
- እንኳን ለ“ዳግማዊ ትንሣኤ”ው ዋዜማ በደህና አደረሳችሁ
- ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን/ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ/ Khristós Ané...
- በሊቢያ በኩል ጣሊያን ስለሚገቡ ኦርቶዶክሳውያን ስደተኞች እውነተኛ ታሪክ (ክፍል...
-
▼
April
(14)




