December 31, 2010

2011, Happy New Year!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

43 comments:

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

I am your admire for your day today activity for our church. But some times you put some thing with out further thinking. Which new year are saying? As far as I know the country espesially the church has its own calander. Please remove this pic, or add some phrase, which say happy new year for whom using the European calander. Thank you

Anonymous said...

i thought it was Tahisas 22? DS in identity crisis

ዘክርስቶስ said...

ምነው ዘክርስቶስ ወደ ፈረንጆች አዘነበልክሳ እንዳቱልኝ እንጂ የኛም የኢትዮጵያዊያን የአዲስ ዓመት ቀመራችን (ቀን)መጀመርያ መሆን የነበረበት ታሕሳስ 29 ነው። የፈረንጆቹ አቆጣጠር ትክክል ነው ማለቴ ግን አይደለም።
ለማንኛውም በጀመረ ይጀምር ሁሉም የእግዚአብሔር ቀናት እስከ ሆኑ ድረስ ደጀ ሰላምም እንኳን የፈረንጆቹን ቀን ለማክበር በሰላምና በጤና አደረሰሽ!
እውነቱን ባልናገር ወዮልኝ!

Unknown said...

Happy New Year to all who are using the Gregorian Calendar.

Almost all Orthodox Churches use Julian Calendar. Even most orthodox countries change their calendar to the Gregorian Calendar late. The last country to join the Gregorian Calendar is Russia in 1918.
http://en.wikipedia.org/wiki/Julian_calendar

Anonymous said...

Deselam

please Remove this untimely message....

Anonymous said...

"Happy New Year" ? ...i beg your pardon ? ...we are in the fourth month of the year TAHISAS...what is going on with you Deje Selam ?

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

እባካችሁ፡ከራሳችን፡አቆጣጠር፡አንውጣ፡፡ሃይማኖትም፡
ባህልም፡ቀስ፡እያለ፡የሚጠፋው፡በዚህ፡ሁኔታ፡ነው፡፡ የተበላሸውን፡ማደስ፡እንጂ፣ወደ፡ጥንቱ፡ወደ፡ትክክሉ፡ ወደ፡አባቶቻችን፡መንገድ፡መመለስ፡እንጂ፡ወደ፡ሌላ፡ ስህተት፡አንግባ፡፡

Anonymous said...

ዸጀ ሰላሞች ሁሌ መጠጠንቀቅ ጥሩ ነው አስፈላጊ ነው ብላችሁ ካመናችሁ ለፈረንጆቹ አዲስ አመት የሚለውን መጥቀስ አለባችሁ መታወቅ አለመታወቁ አይደለም የምትወክሉት ቤተክርስቲያንን መሆኑ ነው ቁምነገሩ።

ለዘክርስቶስ...ሊቃውንት አባቶቻችን መስከረምን ለምን የመጀመሪያ ወር አደረጉት ብለህ ጠይቅና ስለራስህ እወቅ ያገርህና የቤተክርስቲያንህ ታሪክ የራስህ ነውና

Orthodoxawi said...

አይይይይይ!!!!! ደጀሰላም ምን ነካሽ ብዙ ታዉቂ ነበር እኮ! ቤተክርስቲያናችን (እንዲሁም አገራችን) የራሷ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ አላት:: ስለዚህ እባክሽን ቢያንስ "ለሚያከብሩት ሁሉ" የሚል ጨምሪበት::

ለማንኛዉም እንኳን ለታህሳስ 22 (ብስራተ ገብርኤል) በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

And for those of you who are using the Gregorian Calendar:- Happy New Year!!!

Anonymous said...

Adnakiachihu negn. Sew min yilal bilachihu yesewun simet lemelekat endaderegachihut gebtognal.

ዘክርስቶስ said...

ለውድ ወንድሜ/እህቴ
“ለዘክርስቶስ...ሊቃውንት አባቶቻችን መስከረምን ለምን የመጀመሪያ ወር አደረጉት ብለህ ጠይቅና ስለራስህ እወቅ ያገርህና የቤተክርስቲያንህ ታሪክ የራስህ ነውና” ላልከኝ፦

አብልጬ የምወዳት የሀገሬና የቅድስት ቤተ ክርስቲያኔን ታሪክ የኔ አይደለም ማለቴ’ኮ አይደለም፤ ሊቃውንት አባቶቻችን የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓልን ከየካቲት 23 ወደ ጥር 12፣ የመለወጫ የዓመት መጀመርያ እንደ አይሁድ በሚያዚያ/አቢብ ወር ሳይሆን ከታሕሳስ ወደ መስከረም መሳባቸው ባሕረ ሐሳቡን ዘንግቼው ሳይሆን ጥንተ ነገሩን ለማንሳት( የምንናፍቀው የነበረ መሲሐችን ሥጋና መለኮት አንድ አድርጎ ፣ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሆኖ ለውድ ፍጥረታቱ የታየበት የዓመተ ምሕረት መጀመርያ ቀን ታሕሳስ 29 መሆኑን ለመጠቆም ፈልጌ ነው)። አሁንሳ ቅሬታህ/ሽን ብትፍቅልኝ ምን ይመስልሀ/ሻል?

ስለ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በመቆርቆርህ/ሽ በጣም ሳላመሰግንህ/ሽ አላልፍም
እውነቱን ባልናገር ወዮልኝ!

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

ቃለ፡ሕይወት፡ያሰማልን፡orthodoxawi!
ዘክርስቶስ፡ለሀገርም፡ሆነ፡ለሃይማኖት፡መቆም፡ትልቅና፡ በፈጣሪ፡ፊት፡የሚያስመሰግን፡ነው፡፡በኔ፡አስተያየት፣ ከተሳሳትኩ፡አርሙኝ፣አባቶቻችን፡ቅዱሳን፡ሊቃውንት፡ የጊዜ፡ቀመሩን፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ተመርተው፡ነው፡እንጂ፡ የሰሩልን፡በዚህ፡ዓለም፡በሰው፡ጥበብ፡ተመርተው፡ አይደለም፡፡ስለዚህ፡ለምናስበውም፡ሆነ፡ለምንናገረው፡ነገርበጣም፡ጥንቃቄ፡መውሰድ፡አለብን፡፡
ሊያስተምሩን፡የሚችሉ፡ብዙ፡እውቀቱ፡ያላቸው፡አስተማሪዎች፡ስላሉን፡ጠይቀን፡እንረዳ፡፡
አምላካችን፡ሁላችንንም፡ከስህተት፡ይጠብቀን!!!

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

ስለዚህ፡ለምናስበውም፡ሆነ፡ለምንናገረው፡ነገርበጣም፡ጥንቃቄ፡መውሰድ፡አለብን፡፡ሊያስተምሩን፡የሚችሉ፡ብዙ፡እውቀቱ፡ያላቸው፡አስተማሪዎች፡ስላሉን፡ጠይቀን፡እንረዳ፡፡
አምላካችን፡ሁላችንንም፡ከስህተት፡ይጠብቀን!!!

123... said...

ደጀ ሰላሞች
መልካም ምኞታችሁ አይከፋም።ግን ''ለ አውሮፓውያን አቆጣጠር ለምትጠቀሙ ሁሉ'' ብትሉበት ያምር ነበር። መቸም ቅድስት ቤተክርስትያናችን ''አመ ኩሉ'' ነች አና አንድ ሰው በ አዚህ ዘመን ስላልቆተርክ ገነት አትገባም አይባልም። ግን በተችርስትያናችን ዘመንን የምትቆጥረው ከ ጥንተ ዓለም ፍጥረት ጀምሮ ስለሆነ አና አትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር በ መስከረም ወር ስለሆነ መልካም አዲስ ዓመት ማለታችሁ ለ አኔ ስሜት አልሰጠኝም። ይልቁን'' መልካም የ አውሮፓውያን አዲስ ዓመት'' ብትሉ ያምር ነበር አላለሁ። መቸም ስንት በጎ ሥራ የሰራችሁ ወደፊትም የምትሰሩ ናችሁ አና ዛሬ በ አኔ አይን ስህተት ነው ያልኩትን ሳይ ዓለም የተገለበጠ ያህል አልቾህም። ግን ግን ሃሳቤን ብታዩዋት ደስ ይለኛል።

Anonymous said...

Happy New Year
2011 is better than 2007

Anonymous said...

ደጀ ሰላም በፈረንጆች በዓል ስም አንድ ነገር ለማስተማር ያሰብሽ ይመስለኛል። የሚደገፍ ሐሳብ ነው ቢያንስ ከ ዘክርስቶስ አስተያየት:ቁምነገር በትሕትና አልብሶ እንደዋዛ ጣል ካደረጋት ምን ያህል እንደተማርሁ ልብ ያመስግን።
አበበ ከአዲስ

Dn Haile Michael Zeaddis said...

The same to "123...."'s comment.

Dear Dejeselamawuyan you should have expressed your new year wish explicitly for those it concerns.

Thanks

Anonymous said...

Egypt car bomb kills 21 at Alexandria Coptic church

http://www.bbc.co.uk/news/world-middle-east-12101748

Please let us pray to God for the safety of Christians in the Middle East

yeshi said...

I am supporting most of the member that they said.we Orthodox are unique from others that have our own calendar so this is not new year for me as our previous fathers told us,in our church every activity is supported by evidences.

Anonymous said...

What type of New year? we are Just at the middle of the year.

Anonymous said...

ለዘክርስቶስ፣- ቅሬታ ተሰምቶኝ ሳይሆን ካለማወቅ የመነጨ ከሆነ ብዬ ነው። እንዳልከው ቤተክርስትያናችንን የምትወዳት ከሆነ እንዲህ ጎላ ያለ የብሉይ ኪዳን መሰረት ያለው እግዚአብሔር እራሱ በአልን አድርጉ የደስታ ቀናችሁ ይሁን ብሎ ባዘዘው መሰረት እስራኤልም የዘመን መጀመሪያቸው የማድረጋቸውን ታሪክና የሀገራችንን ወቅቶች በማገናዘብ አባቶች የደነገጉትን ስርአት በሙሉ ልብ ያለመቀበልና ለማስተካከል የመፈለግ መንፈስ ሊኖርህ አይገባህም እኮ። እኛ የእምነትና የስርአት ተረካቢዎች እንጂ ጀማሪዎች አይደለንም የሚባለው ለዚህ አይደል። በነገራችን ላይ የካቶሊኩ ጳጳስ ጎርጎሪዮስ ሰባተኛ ይሄንን መላዋ ቤተክርስቲያን ትቀበለው የነበረውን የዘመን መጀመሪያ ወር አንተ ባልክበት ስሜት ከገና ጋር ላያይዘው ብሎ ቀይሮትም እንኩዋን ሩሲያ፣ግሪክ፣ሩማንያ የመሳሰሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናትም እስካሁን የቤተክርስቲያን አዲስ አመት ይሉታል አሉ። እናም ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያናችን በበቂ ታሪክ፣ ምሳሌና ማስረጃ መስከረምን የዘመን መጀመሪያነቱን ታህሳስም አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ወር መሆኑን መጽሀፍ ገልፃ ታሪክ ጠቅሳ እየሰበከች ትኖራለች። እግዚአብሔር ከእውቀቱ ከፍሎ ያበለፀጋቸው ባህር የሆነው የአባቶቻችን የእውቀት በረከት በሁላችን ላይ ይደር።በነገራችን ላይ 'አንተ' ነኝ። ሰላም።

Anonymous said...

There is 2011 project by MK to increase the number of Mimenan. I think if we do it 2011,Happy new year!!!!!!!!

Anonymous said...

The easiest thing to wish DS is happy new year period.Is it big deal? It has nothing to do with our new year in September unless we want to talk the talk as usual.

ዘብሔረ... said...

አየ ማሕበረ ቅዱሳን መቼ ናችሁ ግሳንግሱን ትታችሁ እውነቱን መናገር የምትችሉ? እኔ የሚመልስልኝ ስላጣሁ ኮሜንትን መስጠት ትቼው ነበር ነገርግን አንዳንዶቻችሁ ሳትማሩ የአዋቂነት ሥጋ ለመልበስ ቀንና ሌሊት በመፍጨርጨር የምትጽፉት ዝባዝንኬና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን እንደ ሕግና ስርዓት አድርጋችሁ ብሎጉን ስታጨናንቁት ያበሳጨኛል። ለምሳሌ “ዘክርስቶስ” እውነቱን በፍርሐት ሸፍኖ ሲያቀርበው ‘አንተ’ ነኝ ባዩ በጭንቅላትህ የተደቀነውን ባህል እውነቱን እንዳትቀበል ሲያፍንህ ከፊሉ እሱ ያለውን ደግመህ በመጥቀስ “እኛ የእምነትና የስርአት ተረካቢዎች እንጂ ጀማሪዎች አይደለንም” ትላለህ። እኔ የሚገርመኝ ያለው የትኛው እምነትና ስርዓት ነው ለትውልዱ የምናወርሰው? ማንም ተራ ሰው በስመ መንፈስ ቅዱስ ገለጸልኝ በማለት የግሉን ድረሰት የደረሰውን ነው የምንቀበለው ወይስ የነቢያት ፣የክርስቶስ፣ የሐዋርያትና ከመጽሐፍ ቅዱሱን ሳያጣርሱ የጻፉት ቅዱሳን አባቶች?

አንዳንዶቻችሁም በአካባቢያችሁ ስለሚፈጸመውን መጥፎ ድርጊት ማየትና መጸለይ የተሳናችሁ በግብጽ፣ በምሥራቅ እንዲህ ሆነ፤ ቦምብ ፈነዳና እንጸልይ እያላችሁ ግብዝነታችሁን የምትቀባጥሩ ለምን ስለ ራሳችሁንና ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ መጀመርያ አትጸልዩም? ወይስ ጸልያችሁ ጨርሳችሁ የወሬ ፕሮግራምን ለመክፈት ፈልጋችሁ ነው? ስለ አፍሪካና ዓለም አንጸልይም ሳይሆን እውነትን መዝለል የለብንም ነው መልእክቱ። ደጀ ሰላም እኮ ብሎጉን በተራ ወሬ ልንለፈድደው አይደለም የፈቀደልን።

ሌሎቻችሁም የየራሳችን የወረስነው የአከባበር ስርዓት/ባህል አለንና እንኳን ለፈረንጅ አዲስ ዓመት አደረሳችሁ በሉት ብላችሁ አስተያየታችሁን በደፈናው የሰጣችሁ ትመሰገናላችሁ።

Anonymous said...

Melkam terefe tsom lehulachin. Tsom kekifu yesiga hasab,mignot ena fekad hulu mekelkel newna beselam yasfetsimen!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

ውድ ዘብሄረ፡ ለዘክርስቶስ በሰጠሁት መልስ ቱግ ቱግ ማለትህ ገርሞኛል። ጥሩው ነገር ያለው እንዳለ ይቀጥላል። ስሙ የተመሰገነ ይሁን። አንተም ተረጋጋ።

ጽዮነይቲ said...

እኔ መጀመርያ ደጀ ሰላም በፈረንጅኛ ቋንቋ መልካም አዲስ ዓመት ያድርግላችሁ ስትለን፦ ዜና አጥታ ነው ይህን የዘገበችልን ብዬ አሳንሼ አይቼው ነበር። ነገሩ ግን ከወዲያ ነው ‘እብን ዘመነንዋ ነደቅት ወኮነት ርእሰ ማእዘንት’። “ዘክርስቶስ” ነው የሁላችንን አእምሮ የሳበው፤ ባለችኝ ትንሽ ዕውቀት ስገመግመው ከመፎክሩም ጀምሮ (እውነቱን ባልናገር ወዮልኝ!) ይበረታታል እንጂ ምንም ሕጸጽ አላገኘሁበትም ።
ኢትዮጵያዊያን በመስከረም 1 የምናከብረው በዓል ተራ አድርገን የዓመት መለወጫ በሚለው ሳይሆን የዓመተ ምሕረት መጀመርያ፣ ከዓመተ ፍዳ ወደ ዓመተ ምሕረት የተሸጋገርንበት ቀን፡ ልክ እስራኤላዊያን በሙሴ አመካኝነት ከገብጽ ቀንበር እንደወጡ ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ከሰይጣን ግዛት ለመውጣት ሰው ሆኖ ብቅ ያለበት ታሕሳስ 29 በመሆኑ ነው። የአባቶቻችን ቀመርም ከወቅቱ ለማያያዝ ብለው ወደ መስከረም ወር እንዲሆን ማድረጋቸው የሚያስነቅፍ አይመስለኝም፤ እግዚአብሔር ታሕሳስ 29 ዘለህ ለምን በመስከረም 1 አከበርኸኝ አይልም ደግሞ በሁለቱም ቀናት እያከበርነው ነን።
አንዳንዶቻችን ግን አስተያየት ስንሰጥ አባቶቻችን ያስተማሩን ሥነማግባር በጠበቀ መልኩ እንደ ዘክርስቶስ ቢሆን ሒስ ከሚቀበል ሰው ይልቅ አስተማሪ እንሆናለን። በማያያዝም እውነትንና ሰውን ለይተን መናገር አለብን ባይ ነኝ ለምሳሌ “አንተ ነኝ” ቁምነገር በካቶሊክ አፍ ስለተነገረ እውነቱን እውነት አልመሰለኸም፤ተናጋሪው ጴንጤ፣ ካቶሊክ፣ ሕጻን ፣ያልተማረ ሰው ወይም ሳይንቲስት... ስለሆነ ሳይሆን እገሌ ያለውን ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብለን ቅድሚያ መጠየቅ አለብን። ደግሞ ከዘብሔረ ክርክር ገጥማችሃል ምን ያድርግላችሗል? ዘብሔርም ምነው እውነቱን ደግፈህ ከማለፍ ምላስህን በስድብ ሞላኸውሳ? ማሕበረ ቅዱሳን በዚህ ምን አገባው በስድብ ያጎናጸፍኸው? የሰጠኸው አስተያየት መሬት ጠብ የማይል ነበረ ግን ምን ያደርጋል ሰውን በመዝለፍ ሆነ’ኮ ሥራህን! እውነት በመናገሩ የሁላችንን ቀልብ የሳበ ዘክርስቶስም እኮ ሲሰደብ በትሕትና መልስ መስጠቱ አንተ እንደ ፍርሐት ቆጠርክለት።
አረ ተው ከስድብ ዓለም እንውጣ!
ጽዮነይቲ

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

ዘብሔረ ምነው እዚህች ሐይማኖት ላይ መልክህን በመቀያየር በረታህ? ከዚህ በፊት ማንነትህን ደብቀህ በመመሳሰል “የአኦርተቶዶክ እምነትት ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል፣ ተረትና አፈ-ታሪክ ነው።” እስከማለት ደርሰህ ነቃንብህና በእርግጥ የሌላ እምነት ተከታይ እንደሆንክ ነገር ግን ከላይ ባነሳኸው ጠባብ ምክነያት ከኦረቶዶክስ እምነት እንደወጣህ በመግለፅ ብዙ ነገር ልትዘባርቅ ስትሞክር ነበር። አሁን እንደገና ያላወቅንህ መስሎህ “ማንም ተራ ሰው በስመ መንፈስ ቅዱስ ገለጸልኝ በማለት የግሉን ድርሰት የደረሰውን ነው የምንቀበለው።” በማለት ውድ እምነታችንንና ቅዱሳኑን በድጋሚ ልታቃልል ሞከርክ። አልገባህም እንጂ እንዳንተ አይነቱ አሕዛብና እንደኔ አይነቱ ሐፂያተኛ እንደበደላችን ሳይሆን በቸርነቱ የምንኖረው እኮ አንተ በምታቃልላቸው ቅዱሳንና መላዕክት እንዲሁም በወላዲተ አምላክ አማላጅነት ነው። በተረፈ እኔ መሐይሙ ሳልሆን የበቁና ፀጋው የበዛላቸው አባቶችና ወንድሞች በቂ ምላሽ ይሰጡሐል የሚል እምነት አለኝ።

ሌላው “አንዳንዶቻችሁ ሳትማሩ የአዋቂነት ሥጋ ለመልበስ ቀንና ሌሊት በመፍጨርጨር የምትጽፉት ዝባዝንኬና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን እንደ ሕግና ስርዓት አድርጋችሁ ብሎጉን ስታጨናንቁት ያበሳጨኛል።” ብለኸናል። ለመሆኑ አንተ በኛ በኦርቶዶክሳውያን ጉዳይ ምን ያበሳጭሐል? ደግሞ አዋቂ መስለህ ሌላውን ለማረምና ለደጀ-ሰላም ብሎግ አሳቢ ሆንክ? እኔ ግን ከመናፍቃኖችም ቢሆን ከእንዳንተ አይነቱ ጭፍን አስተያየት ሰጪ አሕዛብ ያልተሻለ አላየሁም። ስለዚህ ጆሮ የሚሰጥህ ያገኘህ መስሎህ ብሎጉን እያጣበብክ ያለኸው አንተ ነህ። በእርግጥ ሰይጣን ቡዳ ነኝ መስተፋቅር ነኝ መተት ነኝና የመሳሰሉትን እያለ ስሙን በመቀያየር ሰውን እንደሚፈታተነው ሁሉ አንተም ትንሽ ቀዳዳ እየፈለክ እንኳን ቡልጋን ዘብሔረንም ብታጠፋው ስለምናውቅህ በእኛ ጉዳይ ገብተህ ባትዘባርቅ መልካም ነው። ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቼና እህቶቼም እንዳንሳሳት በዚህ ብሎግ የሚሰጡት አስተያየቶች ከፍተኛ ሚና አላቸውና ተገቢ ያልሆኑትን በጥልቀት እንድናስተውላቸውና መልስ እንድንሰጥ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም አሳስባችኋለሁ። ቸሩ ፈጣሪያችን የተሠወረብንን መልካም ነገር ይግለጥልን።አሜን!!

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

Sorry Tsioneiti, I accept your comment and appreciate Zekirstos but I thought the comment is from MK because of
“There is 2011 project by MK to increase the number of Mimenan.” Do you believe MK’s plan to increase the number of believers? It is viceversa. We had excess Orthodox Christians including me and many scholars but they went to other flocks as the result of MK’s bad action or persecution.
And now, they may have a plan to reduce....
I pray the Lord Jesus with EOTC
Zebehere...

Anonymous said...

Dear All,

I am at USA, but I do not feel like my new year Because I am ETHIOPIAN.

IF Dejeselam is for ETHIOPIA, Please remove it but it is passing new year greetings for Westerns I donot know what to say ..

SHAME!!!!!!
Know your readers

Anonymous said...

Dejeselamoch andandie balemastewal yemaninim zibazinkiena yesewun libuna yemishereshiru asteyayetochin batifekidu melkam neber. tekamina tikikilegna tichit yeyazutin bicha bitastenagidu melkam yimesilegnal. endewu mizanawi lememisel bicha ekuy hasab yalachewun banastenagid melkam neber.

መላኩ said...

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትናንትና ግብጽ ውስጥ ስለተፈጸመው ሰይጣናዊ ግድያ የሰጠችው መግለጫ ይኖር ይሆን? ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንስ ለመንፈሣዊ ወንድሞቻቸቸውና እህቶቻቸው የድጋፍ ድምጾቻቸውን እያሰሙ ይሆን? ክርስቲያን በእንደዚህ ዓይነት ወቅት ነው የሚፈተነው...

Anonymous said...

መርከቤ ቃለሕይወት ያሰማሽ እነሱ የሚፈልጉት ሀይለቃል ለማናገር እዩዋቸው ለማስባል መድረኩን ከንቱ መለፋለፊያ ለማድረግ ነውና ንቆ መተው ይሻላል በሚል ነው። እንደዛ ባይሆን እዚህ ጥግ ስር ሽጉጥ ብለው ነገር አያነፈንፉም ነበረ ኦርቶዶክሳውያን እንደሆነ የምንለው ግልፅ ነው እነእርሱ ደግሞ አይመቻቸውም እኛ በተነፈስናት ሁሉ ከሚቃጠሉ ለምን የራሳቸውን መድረክ ከፍተው እዛው አይመቻቸውም ግን አላማቸው የኛን ማደፍረስ ስለሆነ ከዚች አይጠፉም ወገኖቼ አንድ ወንድም ባለፈው እንዲህ ብሎ ነበረ..." ".... እና: ኹለትም ሦስትም ኾነን በያለንበት: ጽድቅን ማድረግ ብቻ ነው ተገቢው:: እንዳይጻፍ ስለሚፈለጉ ነገሮች ብዙ እንጻፍ:: እንዳይሳሉ የሚፈለጉ ነገሮችን እንሳል:: እንዳይረዱ የሚፈለጉ አባቶችን ወይም ሰንበት ትምህርት ቤቶችን እንርዳ: እንዳይወጡ የሚፈለጉ ዓይነት ካሴቶችን እናውጣ:: እንዳይኖሩ የሚፈለጉ ዓይነት ትምህርታዊ ገጾችን እንክፈት:: ጽደቅ ያለው ከዚያ የተነሣ ይጸድቃል:: ተኮነን ያለው ገነትም ቢያገቡት ለመውጣት ግድግዳ ሲጭር ያድራል::"
ነውና እነሱን ናቅ ማድረግ ነው
እነዚህን ብሎጎች ያላየ ካለ እነሆ፦
Betedejene.blogspot.com
www.kesisyaredgebremedhin.com
www.danielkibret.com
ሰላም አንተ ነኝ

Anonymous said...

ደጀ ሰላም..በጣም አዘንኩባችሁ ካንዴም ሁለቴ አስተያየቴን ሳታወጡት ቀራችሁ ለምን ? እኔ እኮ ማህበረ ቅዱሳንን አያስፈልግም አይደለም ነበር ያልኩት" ያለበትን ችግር ነው እንዲስተካከል የጠቆምኩት። ለማንኛውም ቅር ከተሰኛችሁ ይቅርታን ስጠይቃችሁ ከልብ ነው። ይህን ስል አስተያየቴን እንድታወጡልኝ መለማመጥ ሳይሆን ህግንና ጽድቅን ለመፈጸም ነው።
ክዚህ ሃሳብ ስወጣ... ዘክርስቶስ ላመሰግንህ እወዳለሁ
የቀን አቆጣጠራችን ወቅትን የተከተለ ሳይሆን በትክክል የክርስቶስን ልደት ማለትም አመተ ምህረትን መነሻ ቢያደረግ መልካም ነበር የሚል ሃሳብ እኔም አለኝ።ጌታ ተወለደ ከምንልበት ቀን ለምን አዪጀመርም? በርግጥ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይህን የሰሩበትን መንቀፌ አይደለም የራሴን ሃሳብ ነው ይገለጥኩት። ምናልባትም ከታህሣሥ ወደ መስከረም የሄደበትን ምክንያት ባጭሩም ቢሆን የምታውቁ ብትነግሩን መልካም ይመስለኛል።
በመጨረሻም ደጀ ሰላም ሁላችንንም
ከማለት ለፈረንጆቹ የሚል ብትጨምሩበት መልካም ነበር።
ስህተትን ማን ያስተውላታል

Anonymous said...

I am sorry for Merkbe Niguse. If you are a lay man, why don't you give the stage to the knowledgable persons? Simply, you are wasting time and forces.
ooooooffff, head each!

Anonymous said...

እስቲ በዚህ አስቡት
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዓ.ምን የምትቆጥረው ተስዕሎተ መልከ ከሚፈጸምበት ቀን ነው ይህም ጥንስ ስድስት ወር ከሞላው ቀን ጀምሮ ነው፡፡ጌታ በእናቱ ማህጸን ስድስት ወር ያደረገው በየትኛው ወር ነውብንል ከመጋቢት29 ጌታ ከተጸነሰበት ወር ጀምረን ስድስት ወር መቁጠር ነው፡፡መስከረም ስድስተኛ ወር ነው በዚህ ወር የጽንስ እንቅስቃሴ የሚጀምርበት ለመሆኑ እናቶችን ወይም ሀኪሞችን መጠየቅ ነው ስለዚህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ድኅነት የተወጠነውበማሕጸነ ማርያም ነው ስለዚህ የዓመተ ምህረት መጀመሪያ መስከረም ነው ብለን ነው የምናምነው

Anonymous said...

deje seytan,

what is the purpose of your "new year" message? Who are you and what is your mission? Are you pente coste posing as MK to sow divsion in Tewahedo?

Anonymous said...

To ዘብሔረ...,

You are usually criticizing our fathers , I have come to realize that you are not in favor of our books and dersan and others as per your nasty words.
I could see your problems from two point of view.
1. Understanding the books or misinterpreting them that is you are in trouble to read between the lines rather you are reading them like fiction. IF you read the following two sentences, I do not know if you understand them our not.
These are.

Leave him ,not kill him
leave him not, kill him that is just a comma kills persons leave alone a word that you all are currently in trouble.

Therefore I strongly suggest you to read them and understand from the writers point of view not from your point of view if not so I am confident that you will soon change your current thinking as often as possible as long as the meaning of words change with technology.

2. You are not reading those books to know them and reading from the authors point of view but you are looking for some words that presumably against bible but they are not actually.Please be informed that that
The writers know about the holy bible much more that our generation who are reading and interpreting the holy bible by mixing it with technology and philosophy based on non spiritual professors/pastors

IF you are ready to learn from them, please invite others who understand the books,they will tell you about interpretation.But to avoid blindness please get first hand information
But do not be like biblical Professors who do not believe in GoD.

My worry for you is your criticism may not end on the dersan but also go to the bible and finally not to be the mentioned professors.

May God shed his light for you and me too.

Anonymous said...

Dear Dejeselam

I am the first Anony, I tried to comment to change the titel of the good wish. Unfortunately, you did not do any thing. As you see more than 99% of the commenst reavels how much the reader upset by your say. Why you ashamed to say sorry, just we did it in the perspective of this. Do you know how much our heart hurt, even, the anti-ethiopia, weyane, did not do this. If you see the news on 1 Jan on ETV just they reported the celebration in outside world. But suddenly, you said happy new year....for the sake of God, please just say some thing and if you have post some documents about the Gorgorian and Ethiopian Calnder.... any way thank you

Anonymous said...

Since I am angry still I have been searching many books which may tell us the truth of the starting date for ‘Amete Mihret’ but I found all have tendency to what ze-kristos wrote. However, I did not stop my searching and asking church scholars for further comment.
Whatever the truth either yours or else is, I very much thank you Ze-Kristos who enforced me to conduct a deep research on this topic in future.

My heartly grattitude also to deje who serve us day and night.

Dureti said...

ሠላም!
በዚህ ርዕስ ብዙ ሽምቅ ተዋጊዎች ብቅ ያሉበት ነው። ጥያቄ አለኝ
1 ለመሆኑ ፈረንጆቹ ለምን ዴሴምበር 25 ላይ ዘመናቸውን አልቀየሩም?
2 አሁንም እነሱኑ ከማድነቃችሁ በፊት ( በተለይ ድርሰት ያልከው ሰው) ክርስቶስ በዚህ ወርና ቀን ስለመወለዱ መረጃ ከየት አገኛችሁ?
3 የዘመን አቆጣጠር ከአንድ ክርስቲያን የጽድቅ ህይወት ጋር ምን ግንኙነት ኖሮት ነው የቀደሙትን ለመዝለፍ ያበቃን?

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ለሁሉም እንኳን ለብርሐነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
ወለክሙሰ ብጹአት አዕይንቲክሙ እለ ርእያ ወአዕዛኒክሙ እለ ሰምዓ።እንዲል
ፈተና በሌለበት ማሸነፍ የለም
ካላሸነፍን አክሊል የለም።
ሁሉም ልብ ያለው ልብ ይበል
ለመጠቀም የወደደም የት ጥቅም እንዳለ አውቆ ይጠጋ።
አንድ መንገድ ብቻ አለች።ይህችም የአባቶቻችን መንገድ ናት ውዴት እንደሆነች መርምሯት።

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ለሁሉም እንኳን ለብርሐነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
ወለክሙሰ ብጹአት አዕይንቲክሙ እለ ርእያ ወአዕዛኒክሙ እለ ሰምዓ።እንዲል
ፈተና በሌለበት ማሸነፍ የለም
ካላሸነፍን አክሊል የለም።
ሁሉም ልብ ያለው ልብ ይበል
ለመጠቀም የወደደም የት ጥቅም እንዳለ አውቆ ይጠጋ።
አንድ መንገድ ብቻ አለች።ይህችም የአባቶቻችን መንገድ ናት ውዴት እንደሆነች መርምሯት።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)