December 19, 2010

የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት ከገና በፊት ሊፈቱ ይችላሉ

(በታምሩ ጽጌና በዘካሪያስ ስንታየሁ ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Sunday, 19 December 2010 12:31 ):-
በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞት፣ በእድሜ ልክና በዓመታት እስር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለገና ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በወቅቱ የፈጸሙትን የተለያዩ ወንጀሎችን በማመን እግዚአብሔርን፣ ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ እንዲጠይቁ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ላሉት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች እንዲለምኑላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፤ የሃይማኖት መሪዎቹ መንግሥትን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ይሁንታ በማግኘታቸው ሳይፈቱ እንደማይቀሩ ምንጮቹ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል፡፡

አራቱ የሃይማኖት መሪዎች በትናንትናው ዕለት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በደርግ ዘመን የተፈጸመውን በደልና ጥፋት፤ በአገራዊ ይቅርታና እርቅ ለመጨረስ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርቁና የይቅርታው ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የእርቅና የሰላም ሥራ የአገሪቱ ተሀድሶ አንዱ አካል በመሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አካላት እንዲያውቁት መደረጉን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹ፤ በዘመኑ የተፈጸመው በደል ፈጣሪንም፣ ሰውንም ያሳዘነ እንደነበር በመግለጽ ምሕረትንና ይቅርታን መጠየቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከአራቱም የሃይማኖት ተቋማት የተውጣጣ አብይ ኮሚቴ አቋቁመው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሠሩ መቆየታቸውን የገለጹት መሪዎቹ፤ በዘመኑ ጥፋት ሰለባ ከነበሩ ማኅበራት ጋር በመመካከር መግባባት ላይ መደረሱንና በተለይ ከስቃይ ሰለባ ማኅበር መሪዎች ጋር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ተግባራትን ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከሰማዕታት ሐውልት ግንባታ ማኅበር መሪዎች ጋርም ሲሠሩ መቆየታቸውን አልደበቁም፡፡

በወቅቱ የደረሰው በደልና ጥፋት ሰፊና መላ አገሪቱን ያዳረሰ በመሆኑ በሁሉም ክልሎች የሰላም ልዑካንን መላካቸውን፤ በሁሉም ከተማ የሚገኙትን ተጎጂዎች የሚወከሉ ሁለት ሁለት ሰዎች ተመርጠው በጠቅላላው 500 የሚሆኑ የስቃዩ ሰለባ አባላት በተወከሉበት አዲስ አበባ ውስጥ ታህሳስ 21 ቀን 2003 ዓ.ም. የይሁንታ ቀን እንደሚሆን መሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ታህሳስ 21 ቀን 2003 ዓ.ም. የሚቀርበውን የይሁንታ ቀን ለመንግሥት እንደሚያቀርቡና መንግሥት እንደተቀበለውም በታህሳስ ወር መጨረሻ የደርግ ዘመን በደልና ጥፋት በብሔራዊ ደረጃ በይቅርታና በእርቅ ተካቶ የዕርቅ በዓል እንደሚደረግና የኢትዮጵያ ዳግም ሕዳሴ እንደሚበሰር መሪዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

የሃይማኖት መሪዎቹ ጨምረው እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች የጋራ ሥራ ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ የሆነ ታላቅ የሰላምና ‹‹የእርቀ ሰላም ማዕከል›› ለመመስረት እንቅስቃሴ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

በደርግ ዘመን በደረሰው በደልና ጥፋት በርካታ ወገኖች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን፣ አካላቸው መጎዳቱን፣ የአእምሮ ሕመምተኛ መሆናቸውን፣ ያለጧሪና ቀባሪ መቅረታቸውን፣ የተበተኑና የተሰደዱ መኖራቸውን በመግለጽ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያስባቸው መሪዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተቻለው አቅም እጁን እንዲዘረጋላቸው ጠይቀዋል፡፡

‹‹ይቅርታና እርቁ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ጨምሮ በውጭ የተሰደዱ የወቅቱ ባለሥልጣናትንና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የተፈጸመውንም ጭምር ያጠቃልላል?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እንደ ሃይማኖት መሪነታችን ማንም ይቅርታ ሲፈልግ መጥቶ ጠይቁልን ካለ እንጠይቃለን፤ ለአሁኑ ግን በሕግ ማለቅ ያለበት ሒደት ተጠናቆና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆነው ይቅርታው እንዲቀርብላቸው የጠየቁትን ብቻ የሚመለከት ነው፤›› ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የስቃዩ ሰለባዎች ማኅበር ኃላፊዎችና አባላት የሃይማኖት መሪዎች ያቀረቡት የይቅርታ ጥያቄ እንደማይመለከታቸው እየገለጹ ነው፡፡ የማኅበሩ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ተረፈ ኃይሌ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አራቱም የሃይማኖት መሪዎች በጋራ ሆነው ታሳሪዎችን ለመጠየቅ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ነበር፡፡

የደርግ ባለሥልጣናትን ሲያነጋግሯቸው፣ ‹‹ሕዝብንና አገርን በድለናል፡፡ የበደልነውን ሕዝብ፣ በተለይ ለሕዝባዊ ሥርዓት ሲታገሉ የነበሩትን ያለ ሕግ እንዲገደሉ አድርገናል፡፡ ከማንም በላይ የተጎጂ ቤተሰቦችን በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን፤›› ማለታቸውን እንደነገሯቸው ነው፡፡

‹‹እኛ በታሰርን ጊዜ ጀርባችን በኤሌክትሪክና በዘይት ሲጠበስ፣ ያለ ሕግና ያለ ፍርድ ወገኖቻችን በአደባባይ ሲገደሉ፣ ክተት ዘመቻ እየተባለ በጄት ሕፃናት ሳይቀሩ ሲደበደቡ፣ አንዳችሁም ምንም ያላችሁን ነገር የለም፤ በታሰርንበትም ጊዜም ቢሆን በብርጭቆ ውኃ አላቀበላችሁንም፤ ላለፉት 19 ዓመታትም ቢሆን የእነዚያ ተጎጂዎችና የስቃይ ሰለባ ቤተሰቦች የት እንዳሉ አልጠየቃችሁም፡፡ ዛሬ ግን ለእነዚህ የደርግ ባለሥልጣናት ይቅርታ ለመጠየቅ መምጣታችሁ ትክክል አይደለም፤›› የሚል ምላሽ ለሃይማኖት መሪዎቹ መስጠታቸውን ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

በባለሥልጣናቱ ላይ ክስ ሲመሰረት የተጎጂ ቤተሰቦችን የሚመለከት የካሳ ጥያቄ ጎን ለጎን መሄድ እንደሚገባው ጥያቄ አንስተው እንደነበር የሚናገሩት አቶ ተረፈ፤ እስካሁን ምንም አለማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌሎች አገሮች በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከሰሱ ሰዎች ሲኖሩ፣ ለተጎጂ ወገኖች የካሳ ክፍያ እንደሚከፈልና ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የተጎጂ ቤተሰቦች መኖርያ ቤታቸውን ተነጥቀውና በየሜዳው ወድቀው፣ ጉዳት አድራሾች የሚከፍሉት ወይም ንብረታቸው ተሸጦ የሚከፈል የካሣ ክፍያ ባይኖርም፤ የሃይማኖት መሪዎች ሕዝቡንም ሆነ መንግሥትን አነጋግረው የሚረዱበትን መንገድ ሳያመቻቹና ምንም ሳያደርጉ፤ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ ወደ እነሱ መሄዳቸው አሳፋሪ መሆኑን ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት መሪዎች የስቃይ ሰለባ ማኅበር ኃላፊዎችን ለማነጋገር በመጡበት ወቅት የማኅበሩ ኃላፊዎች ምንም መወሰን እንደማይችሉና ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት ውሳኔውን እንደሚያሳውቋቸው በመግለጽ እንደሸኟቸው የገለጹት ምክትል ሊቀመንበሩ፣ ‹‹ጉዳታችን ከአእምሯችን ሳይወጣ፤ ለጉዳታችንና ለጠፋው ንብረት ተመጣጣኝ ካሳ ባላገኘነበት ሁኔታ፣ ይኼ ጥያቄ መቅረቡ አሳዛኝ ነው፤›› የሚል መልስ ከጠቅላላ ጉባኤው መተላለፉን እንደነገሯቸው አሳውቀዋል፡፡

‹‹የሃይማኖት አባቶች በመሆናቸው ልናከብራቸው ስለሚገባ ውይይቱ መጀመሩ ይቅርታ ማለት አይደለም፤›› በማለት የሃይማኖት መሪዎቹ ከወከሏቸው አብይ ኮሚቴዎች ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን አቶ ተረፈ ገልጸዋል፡፡

ጉዳዩ የሕዝብ ጉዳይ በመሆኑ በኢትዮጵያ ክልል ያሉና ከአገር ውጭ ያሉ ተጎጂዎች መካተት እንዳለባቸው ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረው፤ እንቅስቃሴውም ሆነ ይቅርታ አጠያየቁ በአዲስ አበባ ብቻ መሆኑ የታሪክ ተጠያቂ ስለሚያደርግ፤ ስለ ይቅርታ መነጋገር ያለባቸው የአገር ሽማግሌዎች ወይም የሃይማኖት መሪዎች ሳይሆኑ፣ የግፉና የስቃዩ ገፈት ቀማሽ ወገኖች ብቻ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ማኅበራቸውም ተጎጂውን ከየክልሉ ለማምጣት እንደሚተባበር እንጂ ስለይቅርታው እንደማያገባው ከመሪዎቹ ጋር መተማመናቸውን አሳውቀዋል፡፡

የስቃይ ሰለባዎች ማኅበር ተወቃሽ መሆን ስለማይፈልግ፤ በየክልሉ ያሉ ተጎጂዎች ተወካዮችን አዲስ አበባ መጥተው ከሃይማኖት መሪዎቹ ጋር እንዲነጋገሩ የማድረግ ሥራ መሥራቱን የገለጹት አቶ ተረፈ፤ ልጆቻቸው፣ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የሞቱባቸው፣ አካላቸው የጎደለ፣ ንብረታቸው የተዘረፈባቸውና አስታዋሽ አጥተው በየጎዳናው የሚኖሩ ወገኖች ባልተካሱበት ሁኔታ ስለእርቅ ማውራት ተጎጂውን የበለጠ መጉዳትና የታሪክ ተጠያቂም እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

መስቀል አደባባይ ላይ የሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ያስገነቡትን የቀይ ሽብር ቤተሰቦችና ወዳጆች ማኅበር ኃላፊዎች በይቅርታ ልመናው ላይ ያላቸውን አስተያየት ጠይቀን ማኅበሩን ወክሎ መናገር የሚፈልግ አልተገኘም፡፡

‹‹ይኼ የግሌ አቋም ነው›› በሚል አስተያየታቸውን የሰጡን የማኅበሩ የቦርድ አባል አቶ ሰይፈ እሸቴ ሲሆኑ፤ የሃይማኖት መሪዎች ባነሱት ሐሳብ ላይ በግል መነጋገራቸውን እንጂ ማኅበሩን የሚወክል አቋም አለመውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

በመሠረተ ሐሳቡ ማኅበሩ ቂም በቀልን የማይደግፍ መሆኑን፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚና ማኅበረሰብ እንዲኖር የሚፈልጉ መሆኑንና እርቅና ሰላም ጥሩ ነገር በመሆኑ ሐሳቡን በግላቸው እንደሚደግፉ አቶ ሰይፈ ገልጸዋል፡፡

ከ500 ሺሕ በላይ ሕዝብ የሞተበት ጉዳይ መሆኑንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወላጅ፣ ልጅና የልጅ ልጅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በመሆናቸው፣ ሁሉንም በአካል ማነጋገር እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ሰይፈ፤ ዋናው ነገር ‹‹ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም?›› የሚለውን ማየት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቀይ ሽብር ቤተሰቦችና ወዳጆች ማኅበር የቦርድ አባል የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ እንደገለጹልን፤ ባለሥልጣናቱ በመጀመሪያ ጊዜ ክስ ሲመሰረትባቸው ‹‹ነፃ ነን›› በማለት ተከራክረዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሁሉም ነገር ካለቀ በኋላ ይቅርታ መጠየቅ ማሾፍ ነው፡፡

‹‹የማናውቃቸው ሴራዎችና ወንጀሎች አሉ፡፡ እሱን በግል ይናገሩ፤›› በሚል የሃይማኖት መሪዎቹን ሲጠይቋቸው፣ ‹‹በግል ሳይሆን በጅምላ ጥፋታቸውን ይመኑ›› የሚል ምላሽ መስጠታቸውን የገለጹት የቦርድ አባሉ፤ ‹‹ከቅንጅት በኋላ ጅምላ አይሠራም አልናቸው፤›› ብለዋል፡፡ ክሱ ሲጀመር ነፃ መሆናቸውን በመግለጽ ወደ ክርክር ሳይገቡ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ ቢጠይቁ ኖሮ ምንም ማለት እንዳልነበር ተናግረው፤ ‹‹አንዳንዶቹ የሃይማኖት መሪዎች የግፉ ተካፋይ ስለነበሩ ከፈለጉ እነሱ ይቅር ይበሏቸው፤›› ብለዋል፡፡

20 comments:

Ameha said...

እግዚአብሔር አምላክ እኛን ይቅር እንዲለን እኛም የበደሉንን አካሎች ከልብ ይቅር ልንል ይገባል።
ይህ የተጀመረው የዕርቅ ሂደት በራሱ ብዙ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አይቀርም።
በቀደመው ሥርዓት የደርግ ባለሥልጣናት ፈጻሚነት/አስፈጻሚነት የቀይ ሽብር ሰለባዎች የሆኑ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ በሥርዓቱ ውስጥ ገብተው በተለይ በከተማ አስተዳደር (ከነማ) ተመራጭ ሆነው ሲሠሩ በማያውቁት ሁኔታ በነጭ ሽብር አራማጆች ህይወታቸውን ያጡ፣ አካለ ጎዶሎ የሆኑ፣ ቤተሰቦቻቸው ለተለያየ አደጋ የተጋለጡ ዜጎች እንዳሉም ግምት ውስጥ በማስገባት ዕርቁ የሁለቱ ሽብር ዓይነቶች ተዋናዮችን ሊያካትት ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ሌላው ዕርቁ፣ ቃሊቲ እሥር ቤት ውስጥ ያሉትን ታሳሪዎች ብቻ ሳይሆን መንግስቱ ኃይለማርያምን ጨምሮ ሀገር ውስጥ ያሉትንም ሆነ በውጭ የሚኖሩትን ወገኖች ሁሉ ማካተት ይኖርበታል።

ይቅርታ እንዲያደርግ የሚለመነው አካል ማነው? በዋናነት የነዚያ ሽብሮች ሰለባ የሆኑ ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው ሲሆኑ፣ በተረፈ ያንን አስከፊ ዘመን ያሳለፈው የሀገራችን ሕዝብ በሙሉ መሆን ይኖርበታል። ይህም ጥያቄ በይፋ ለሕዝቡ ቀርቦ ውይይት ሊደረግበት ይገባል።

ለደረሰው ጉዳት ካሣ ከፋይ ማነው? እውን እነዚህ 18 ዓመት እሥር ቤት የሚማቅቁ ሰዎች ለቀይ ሽብር ሰላባ ለሆኑ ሰዎች ካሣ ሊከፍሉ ቀርቶ ለራሳቸው የወደፊት ሕይወት የሚበቃ ቅሪት ይኖራቸው ይሆን? ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወው።

የዕርቁ ሂደት መከናወኑ እሰየው የሚባልለት ነገር ቢሆንም ጥረቱ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት ወይስ ለእውነተኛ ሠላም ፍለጋ ... እሱን ወደፊት እግዚአብሔር የሚገልጠው ይሆናል፡፡

የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም እንዲሉ የሞቱትን "ነፍስ ይማር" ብለን፣ ያሉትን ደግሞ እግዚአብሔር ይጠብቅልን ብለን ወደ ፈጣሪያችን መለመን ይጠበቅብናል። ይቅር የሚል ልብ ሊኖረን ይገባል። በአንድም ሆነ በሌላ እያንዳንዳችን የዚያ ዘመን ሰለባዎች ነበርን። ይቅር እስካላልን ድረስ እነሱን ባሰብን ቁጥር ጨጓራችን ሲቃጠል፣ ለብቀላ ራሳችንን ስናዘጋጅ፣ ወደ ኃጢአት እንጂ ራሳችንን ለንስሐ ሳናዘጋጅ ሕይወታችን ያልፍና በወድያኛው ዓለም በእግዚአብሔር ዘንድ የምንመልሰው አጥተን ወደ ገሃነመ እሳት እንዳንወርድ ልንጠነቀቅ ይገባል። ስለዚህ "ጽድቅን (እ)ሹ" የሚለውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን!

Zewdu said...

የምንሰማው ነገር እውነት እንዲሆን እግዚአብሔርን እንማጸናለን ፡፡ ለሁሉም ወገኖች ማለት የምፈልገው ነገር ግን አለኝ በሰማይም በምድርም የሚጠቅመን ነገር በደልን ይቅር ማለት ብቻ ነው ፡፡ መጽሐፋችን ይህንን በማድረጋችሁ ከምታገኙት ፍጹም ዋጋ በተጨማሪ በጠላታችሁ ላይ የእሳት ፍም ትጨምራላችሁ ይላል ፡፡ ይህ ማለት ዘወትር የሚያቃጥል የዘላለም ጸጸት ያገኛቸዋል ማለት ነው ፡፡

እውነት ነው የተበደለ ሰው ይቅር ከማለት በላይ ፍቅር የለም ፍጹም ፍቅር ኃጢአትን በደልን አታስብም በሌላ አነጋገር ሰውን ይቅር ብሎ ሰላምን ፍቅርን ማስፈን ከፍጹም ይቅር ባይ የሚጠበቅ ነው ፡፡ ይህ ካልሆነ የተበደለሰው ይቅር ካላለ ምኑን ይቅርታ ሆነ፡፡

እባካችሁ እቺ ሀገር ሁሉ እላት ሁሉ ሞልቷት ተመጽዋች ያጣችው በፍጹም ልባችን በደሉንን ይቅር ብለን የበደልነውን ክሰን ወደ ፈጣሪያችን ባለመመለሳችን ነውና እባካችሁ በምታመልኩት አምላክ ይህ አጋጣም ለዚህ ምስኪን ህዝብ አይለፈው ፡፡

Unknown said...

እውነትም ህዳሴ ድሮ ተበቃዮች ነበርን አሁን ደግሞ ይቅር ባዮች ታዲያ ከ ዚህ በላይ መታደስ ምን አለ በርቱ ፈጣሪያችን ሊታረቀን ነው ሃገሪቱ የሰላም የፍቅር የብልፅግና ሃገር ልትሆን ለማደግ ሁላችንም አንድ መሆን ይጠበቅብናል የ ምንጠላውም ሰው መኖር የለበትም::

123... said...

New generation was pushing to do so.I think the New generation has began to be listned. It is good.Please let it keep it up in all direction. We need to see in our church too.
BUT ABATACHIN ABUNE PAWLOS ALSO MUST BEGAN TO SAY ''YIKIRTA'' TO HOLLY SYNODOS AND ALL ORTHODOX CHRISTIANS.IT COULD BE BEGAN FIRST BY PRACTICING HOLLY SYNOD OCTOBER'S DECISION.

Anonymous said...

How about TPLF? Is it going to appologize the Ethiopian people? How about Tagaye Paulos?

ዘ ሐመረ ኖህ said...

Ameha በሰጡት አስተያየት ላይ ሙሉ ለሙሉ እስማማለሁ የምጨምረው ነገር ቢኖር የሃይማኖት አባቶች እራሳቸው በቅድሚያ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ነገር ግን ለሁላችንም ይቅርታ ማድረግ ለነፍስም ለሥጋም እጅግ ጠቃሚ ነው

Anonymous said...

የዕርቁ ሂደት መከናወኑ እሰየው የሚባልለት ነገር ቢሆንም ጥረቱ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት ወይስ ለእውነተኛ ሠላም ፍለጋ ...

Anonymous said...

Is this part of the 5 years transformation plan? why now? why it took 20 years to preach about forgiveness? Weren't the religious leaders aware of 'Yikerta'? or are they trying to cover TPLF... as usual?

Anonymous said...

ደጀ ሰላም እስካሁን ስታሰነብበን ከነበረው በርካታ ርእሰ ጉዳይ ይህኛው ለምን እንደነዘረኝ ንባቤን ትቼ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ለካሰ ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ (በእርግጥ ይህን ጽሑፍ ባታስተላልፉት ሌላ ጥያቄ ውስጤ ስለመፈጠሩ አልጠራጠርም፡፡)

አጀንዳው የርህሩህነት ይሁን የጭካኔ፣ የይቅር ባይነት ይሁን የፌዝ፣ የወገንተኝነት ይሁን የገለልተኝነት ብቻ ቅጡ አልገባህ ብሎኛል፡፡ በመሠረቱ ስለሰዎቹ መፈታትና አለመፈታት ከመነጋገራችን በፊት ካሁን በፊት ያላነሳናቸው ሌሎ አጀንዳዎች ያሉ ይመስለኛል፡፡ ሰዎቹ ሰው በላ ነፍሰ ገዳዮች ናቸው ወይስ አይደሉም? ምድራዊ ፍርድ ወይም ዳኝነት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ይህ ምድራዊ ፍርድ መከበር አለበት ወይስ የለበትም? ወዘተ. እነዚህን ጥያቄዎች ከመመለሳችን በፊት ስለሌላ አጀንዳ ማውራት ተገቢ አይመስለኝም፡፡ እናም "ነገሩ በሰው ቁስል..." ይመስላል፡፡
በነገራችን ላይ የዚህ አጀንዳ አራጋቢ የሆንን ሰዎች እነዚህ ወንጀለኞች በፈጸሙት አንጀታቸው አልጠገን ያላቸው፣ ፊታቸው ጽልመት ለብሶ የቀረ፣ አሁን ድረስ ማቅ ያላወለቁ፣ ራሳቸውን ስተው በየበራችን የሚለምኑና ጎዳና ላይ የሚያድሩ የሚደጉማቸው አጥተው ከጥጥ ጋር ተጣብቀው የሚኖሩ ሲብስም ሳይበሉ የሚያድሩ ወዘተ. እንዳሉ ገብቶን ያውቃል? አይመስለኝም! መቼም ለመልስ አነሸነፍምና ኢትዮጵያዊ ሆኖ ይህ የማይገባው ማን ይኖራል? የምንል አራጋቢዎች ብዙ እንሆናለን፡፡ እነዚህ በሰቆቃ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ጨርሰው ራሳቸውን ያለማጥፋታቸው ምስጢር ግን ሰው በላዎቹ ማንም ከህግ በላይ እንደማይሆንና የዋጋቸውን ባያገኙም ጥፋተኝነታቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ በአንድ አካባቢ ተወስነው እንዲኖሩ መደረጉ መሆኑን ልባችን ያውቃል፡፡

ይገርማል! ማን ይሆን ከሕዝብ ጎን የሚቆም? ለመሆኑ ማን ይቅር በለኝ ተብሎ ማን ሊተው እንደሆነም አይገባኝም፡፡
ያልታደለ ሕዝብ! አሁን ለዚህች አገር ስንት የሚያሳስብ ሞልቶ በፈጸመው ወንጀል ለተቀጣ አካል ጊዜ ሰጥቶ መብላላት ጀርባው ጉድ እንጅ ምን ሊሆን ይችላል?

ዓላማው ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ያመለጡት "የወቅቱን ጥያቄ ለመመለስ ያደረግነው እንጅ ..." እያሉ እንደሚያፌዙብን የቀሩት ደግሞ ነገ ወጥታው እንዲያቃጥሉን ማድረግ፡፡

እስኪ በሞቴ የእነዚህ አስከፊ ወንጀለኞች መፈታት ለትውልድ ያስተላልፋል የምትሉትን ትምህርት ግለጹልኝ፡፡ የተለመደውን መደለያ "ይቅር መባባልን" በሉኛ፡፡ በአንፃሩ ህግ በደጋፊ ብዛት ሊሻር እንደሚችልስ አያስተምርም ይሆን?

ለመሆኑ ይህ የተበደለ ሕዝብ የእነዚህን ወንጀለኞች ዘር ማንዘር ለማጥፋት አለመጋበዙንና ጉዳዩን ለህግ አሳልፎ መስጠቱን ከይቅር ባይነት አልቆጠርነውምን?

ዛሬ የሃይማኖት መሪ ነን ባዮች ማውራት ከመጀመራቸው በፊት ቀድሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር ብሏቸዋል፡፡ እንደነሱ ወንጀልማ የሞት ፍርድን ወደዕድሜ ልክ እስራት መቀየር ሳይሆን እነሱንም በሠሩት ልክ አሰቃይቶ ማጥፋት ነበር አጸፋው፡፡ ይህ ሕዝብ ግን በቀል የእግዚአብሔር እንደሆ ያውቃልና በሕይወት እንዲኖሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

እባካችሁ ባይከስምም የጠገገ ቁስላችንን አታመርቅዙት!

pleas, Deje Selam post this massage in the name of God and we shall discuss on it.

Henok

EHETE MICHEAL said...

Selam for all.I don't like this kind of topic to read sorry.
Ehete micheal

Anonymous said...

Well, we Ethiopians listen good news that shows Love, Respect to the Highest Value of creature-Human Being. First I can say why it is now? after 20 years. Too late. Second let tell the Abune-patriarch & Woyane to ask forgiveness from the people of Ethiopia. Then after our Lord GOD will praise our country.
amen. Ben from CANADA

Anonymous said...

For me foregiveness is the highest degree of christianism so please there is no benefit from revising the past things so foregive to them to blessed by God.

Anonymous said...

I will tell you our wise pro fathers saying "sal yizo sirkot, kim yizo tselot" what I want to say is we can not get mercy unless the mercy reach out to the nation. So Meles/Woyane have to ask forgiveness form the Ethiopian people & on the other hand the patriarch has to ask forgiveness form the christian (orthodox)nation.
Let me tell you my story I lost most of my familly from derg regime & I was almost loosing my life by Woyane.
At least may I deserve forgivness?

Anonymous said...

ለአቶ ሄኖክ (Mr Anonymus)
በመሠረቱ የሰይጣን እንጂ የእግዚአብሔር አምላኪ እንዳንተ አይነት አስተያየት አይሰጥም፡፡ በተለይ ሁሉም መንፈሳዊ አስተያየት በሚሰጥበት መንፈሳዊ ብሎግ ላይ የጥንተ ጠላታችንን መንፈስ ማንፀባረቅህ ሕይወትህ በቃሉ ያልተገራ የጥፋት ልጅ ሎሌ መሆንህን ያሳያል፡፡
የፈለገ ቢሆን ክርስቲያን ያለ ወንጀሉ የሰቀሉትን ይቅር ያለ የክርስቶስን አርአያ ይከተላል እንጂ እንዳንተ "…እነሱንም በሠሩት ልክ አሰቃይቶ ማጥፋት ነበር አጸፋው፡፡" ብሎ ክፉን በክፉ አይቃወምም፡፡
"…በሕይወት እንዲኖሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡ " ላልከው አንተን ለመሆኑ ማነው እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት በሕይወት እንዲኖር ፈቃጅ ወይም ከልካይ ያደረገህ?
"…ዛሬ የሃይማኖት መሪ ነን ባዮች፡፡ " ይህ አንደበትህም አባቱን በበጎም ሥራዉ የሚሰድብ ወላጅ የሌለው ልጅ መሆንህን ነው ያሳየኝ፡፡
'ዓላማው ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ያመለጡት "የወቅቱን ጥያቄ ለመመለስ ያደረግነው እንጅ ..." እያሉ እንደሚያፌዙብን የቀሩት ደግሞ ነገ ወጥታው እንዲያቃጥሉን ማድረግ፡፡' ብለሃል፡፡ አንተ የተጎጂዎቹን ሰቆቃ እንደገለፅከዉ በማያውቁት ነገር ለእንጀራቸው ብለው በሰሩት "ዘር አጥፍታችኋል" ተብለዉ ተከሰው በሐሰት ተመስክሮባቸው የማቀቁ እንዳሉ ማን በነገረህ? ስለዚህ እያፌዙብህ ሳይሆን እውነተኞቹ እውነት ነው የተናገሩት የዋሹትም የእውነተኞቹ ን ምክንያት ተጠቀሙ፡፡ ለማንኛዉም ክርስቲያን ከሆንክ ዓላማው የእግዚአብሔር ልጅነት ዓላማ ነው፡፡ "የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸዉ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና" እንዲል ቃሉ፡፡
"ይገርማል! ማን ይሆን ከሕዝብ ጎን የሚቆም? …አሁን ለዚህች አገር ስንት የሚያሳስብ ሞልቶ…" ስትል እውን አንተ ለዚህቸ ሀገርና ለህዝቧ ተቆርቋሪ ትመስላለህ' ነገር ግን በሕዝቡ ስም የግላቸውን ስሜት ከሚያንፀባርቁ ትምክህተኞች ወገን አንደሆንክ "ያልታደለ ሕዝብ!…" አባባልህ ያሳብቅብሃል፡፡ መች ይሆን አንተና መሰሎችህ በዚሁ ህዝብ ማሾፍ የምታቆሙት? ልቦና ይስጥህ እንጂ ህዝቡ አንተ እንደምትለው ያልታደለ አይደለም፡፡ ያልታደልክስ አንተ በስመ ክርስቲያን በዲብሎስ ባርነት የምትማቅቅ፡፡ እውነትም ይገርማል!
ለተጎጂዎቹ ተቆርቋሪ መስለህ መቅረብህ አዳምን አስቶ እንደተረገመው የግብር አባትህ ጥሩ አሳቢ መስለህ ለመታየት ያደረግኸው ጥረት ነው፡፡ አልገባህም እንጂ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የጉዳቱ ቀማሽ ነው፡፡ ነገር ግን እያልን ያለነው "ይቅርታ ማድረግ የክርስቲያን መለያ ነውና መልላካም ነው ' ለክርስቲያን ሕዝብ ቅርታ ማድረግ የ20 ዓመት የቤት ሥራ መሆን አልነበረበትም' አባቶቻችን መልካም አድርገዋል' ነገር ግን በነርሱም መካከል ይቅርታ እንዲወርድ እንፈልጋለን' ሕዝቡ ባለውም መንግስት ለደረሰበት በደል ይቅርታ ያስፈልገዋል…" የሚል የክርስቲያን ውይይት ነው፡፡ ነገር ግን አንተ እንደ እርጎ ዝንብ በክርስቲያኖች ንግግር መሃል ጥልቅ ብለህ የአጥፍቶ ጠፊ ሚናህን ለመጫወት ትሞክራለህ፡፡ በመጨረሻ አንድ ነገር ልንገርህ የኢትጵያን አንድነት ልናይ ያልቻልነው አለመታደል ሆኖ እንዳንተ አይነት ልበ ጠማሞች በዘራችን እንደ እንክርዳድ ስለበቀሉብን ነው፡፡
የምሕረት አምላክ ምሕረቱን' ሰላሙንና ይቅርታውን ይላክልህ፡፡
ታዛቢው

Anonymous said...

እኔ በአክሱም መሐል ከተማ ሁለት ወንድሞቼና አንድ አጎቴ በደርግ ጠበንጃ እንደተዘረጉ የሁል ጊዜ ትኩስ ሀዘን እየሆነ ቢያሽቸግረኝም ቅሉ ግን መንግስቱ ሐይለማርምም ቢሆን በአካለ ሥጋ አዲስ አበባ መጥቶ ከመለስ ጉንጭ ለጉንጭ እየተሳሳሙ ቢያሳየኝ ለእግዚአብሔር ያለኝ ምስጋናና ለሀገሬ አስታራቂ አባቶች የሆኑ የሚሰጠው ከፍተኛ አድናቆት የልቤ እውነተኛ ምኞት መሆኑን ማን በነገራችሁ?
ጽዮነይቲ

Anonymous said...

"ታዛቢው..." በዚሁ ብትቀጥል ጥሩ ተሳዳቢ "ክርስቲያን" ይወጣሃል፡፡

Anonymous said...

Yetejemerew jimaro tiru new honom mejemeria abatoch irs bersachew kelib bemeneche tenesashinet yikir tebabablew bihon tilik misalie behonu neber inesu yegorit eyeteyayu lelawun biyastariku sirachew mulu yemihon aymeslegnim. Kezia gin bahunu gize agerituwan yemiyastedadrew mengist iskahun legedelachew, lafenakelachew indihum melawun ye Ethiopian hizb iskahun laderesew bedel yikirta biteyik tikiklegna akahed yihon neber, yih sayhon gin inegnihin akim yelelachew isregnoch yikirta inditeyiku madereguna yikir maletu bicha yemecheresha lihon ayigebawum lela ye poletika fijota yinorewal tebilo kalhone besteker.Lemangnawum anesasto yasjemerachihu EGZABHER behulum aktacha yirdachihu ignanim be Agerituwa kemidersew tifat bezihu beka bilo hulachininim FIKIRina nitsuh lib yisten, AGRERACHININ yitebikilin. AMEN

Anonymous said...

የሃይማኖት መሪዎች የጠየቁት የይቅርታና የእርቅ ጥያቄ ተቃውሞ እየገጠመው ነው
http://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article&id=4466:2010-12-22-07-26-47&catid=98:2009-11-13-13-41-10&Itemid=617
በታምሩ ጽጌ Wednesday, 22 December 2010

በደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉዳት የደረሰበትም ሆነ ድርጊቱን በታሪክ የሚያውቀው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር እንዲልና እርቀ ሰላም እንዲወርድ፣ አራት የሃይማኖት መሪዎች ታህሳስ 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ያቀረቡት ጥያቄ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡ በአካል በመገኘትና በደብዳቤ ተቃውሟቸውን ለሪፖርተር ከገለጹት መካከል ‹‹የቅዱስ ሚካኤል ማኅበርተኞች›› በሚል የተሰባሰቡት የቀደምት ሰማዕታት፣ ማለትም በደርግ የተገደሉት የ60ዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ናቸው፡፡

ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም. በደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በአንድ ላይ ያለፍርድ የተገደሉት እነፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ (ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ)፣ ሌተናል ጀኔራል አብይ አበበ (መከላከያ ሚኒስትር የነበሩ)፣ ልዑል አስራተ ካሳ (የዘውድ ምክር ቤት አባል የነበሩ)፣ ራስ መስፍን ስለሺ (የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ የነበሩ)፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን (በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ)፣ አቶ አበበ ረታ (የዘውድ አማካሪ የነበሩ)፣ አቶ አካለወርቅ ሀብተ ወልድ (የፍርድ ሚኒስትር የነበሩ)፣ ኮሎኔል ታምራት ይገዙ (የዘውድ አማካሪ የነበሩ)፣ ደጃዝማች ክፍሌ እርገቱ (አምባሳደርና አርበኛ የነበሩ)፣ ሌተናል ጄኔራል ኢሳያስ ገብረ ሥላሴ (የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የነበሩ) በአጠቃላይ 60 ባለሥልጣናትና በ1971 ዓ.ም. በገመድ ታንቀው የተገደሉትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ጨምሮ ሌሎች ሲቪል ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ቤተሰቦቹ ቅሬታቸውን የሚጀምሩት፣ ‹‹እኛ የቀደምት ሰማዕታት ቤተሰቦች ለምን አልተጠየቅንም?›› በሚል ሲሆን፤ አይታወቁም እንዳይባል የሃይማኖት መሪዎቹም ሆኑ ከፍተኛ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በቅርብ እንደሚያውቋቸው ያወሳሉ፡፡

ተበደልን ብለው አመልክተው ሳይሆን መንግሥት ራሱ በወቅቱ ተፈጽሞ የነበረውን ግፍና በደል በመመልከት ልዩ ፍርድ ቤት በማቋቋም በእያንዳንዱ ባለሥልጣናት ላይ ክስ በመመስረት፣ በሰነድ ማስረጃና በሰዎች ምስክርነት ወንጀሉን አረጋግጦ ያስተላለፈውን ውሳኔ በምን ሕግና በምን ሁኔታ ይቅር ለማስባል የሃይማኖት መሪዎቹ እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ እንደማያውቁ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል፡፡

‹‹አንዳንዶቻችን ከአንዳንዶቹ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በቀናቶች ልዩነት እንገናኛለን፤ ለምን እኛን ማነጋገር አልፈለጉም?›› የሚሉት ቤተሰቦቹ፤ መንግሥት ሕግና ሥርዓቱን ጠብቆ የተላለፈውን ውሳኔ ይጥሳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ምናልባት ሌሎች አካላትን አነጋግረው ሊሆን እንደሚችል ነገር ግን እነሱን እንደማይወክል ገልጸዋል፡፡

የቀደምት ሰማዕታት ቤተሰቦች በመሰባሰብ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ውስጥ ለባለሥልጣናቱ መታሰቢያ ቤተመዘክርና ሐውልት ማሠራታቸውን፣ በየዓመቱ ሕዳር 14 ቀን እንደሚሰባሰቡና የሃይማኖት መሪዎችም ተገኝተው ፍትሐተ ፀሎትና የተለያዩ የማስታወሻ ሥርዓቶችን እንደሚያደርጉ መንግሥት ጭምር ስለሚያውቅ፣ የሃይማኖት መሪዎቹ በቀላሉ አግኝተው ሊያማክሯቸው ይገባ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

‹‹አትግደሉ›› እና ‹‹ይቅር በሉ›› የሚለውን አምላካዊ ትዕዛዝ ለደርግ ባለሥልጣናት የእስልምናም ሆነ የክርስትና ሃይማኖት መሪዎች ቀደም ሲል ባለማስተማራቸው በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ አድርሰዋል፡፡ ዕድሜያቸውን ሙሉ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ተሰልፈው ሲያገለግሉ የነበሩትን አርበኞችና ባለሥልጣናት ‹‹የመንግሥት ተቀጣሪዎች ናችሁ›› በሚል ሲገድሉ፣ ሲያስሩና እንዲሰደዱ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሥልጣናት፣ የተጎጂዎች ቤተሰቦች በማያወቁትና ባልሰሙበት ሁኔታ ለይቅርታና ለእርቅ መንቀሳቀሱ የማያዋጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በውጭ አገር ተሰደው የሚገኙትም በእነዚሁ ባለሥልጣናት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የልዩ ዓቃቤ ሕግ ባልደረባ የይቅርታውንና እርቁን ጥያቄ በሚመለከት በሰጡት አስተያየት፤ የሃይማኖት መሪዎቹ እየሄዱበት ያለው መንገድ አግባብና ትክክል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት፤ የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሠሩት በደል ተጸጽተው ይቅርታ እንዲደረግላቸውና የሃይማኖት መሪዎቹ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹላቸው ከፈለጉ፤ እነሱ በሄዱበት መንገድ መሆን የለበትም፡፡ የሃይማኖት መሪዎቹ የይቅርታና የእርቅ ጥያቄያቸውን በፍትሕ ሚኒስቴር ለይቅርታ ቦርድ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የይቅርታ ቦርዱ ይቅርታ እንዲደረግለት የተጠየቀውን ወንጀለኛ አንድ በአንድ ተመልክቶና የራሱን አስተያየት ሰጥቶ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያቀርባል፡፡

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞትን ወደ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት የመቀነስ ሥልጣን ስለተሰጠው በዕድሜ ልክ እንዲታሰሩ ሊያደርግ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

አንድ ሰው እድሜ ልክ ተፈርዶበት 20 ዓመታትን በእስር ካሳለፈ አመክሮ በመጠየቅ ሊፈታ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ የገለጹት ባለሙያው፤ ምናልባት የደርግ ባለሥልጣናት ጉዳይ በዚህ መንገድ ከተሄደበት የሚፈቱበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችልና እሱም አስፈላጊ ቢሆን ከሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በኋላ ሊታይ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በስልክና በደብዳቤ ከደረሱን በርካታ አስተያየቶች ለመገንዘብ እንደተቻለው፣ የደርግ ባለሥልጣናት ለፍርድ በቀረቡበት ወቅት ለፈጸሙት ድርጊት ምንም ዓይነት የመጸጸት ስሜት ሳያሳዩ ሊፈረድባቸው ችሏል፡፡ አሁን ለእነዚህ ባለሥልጣናት ይቅርታ ለማሰጠት የሃይማኖት መሪዎች የሚሯሯጡት በምን የተነሳ ነው? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ ባለሥልጣናቱ ይቅርታ ጠየቁ የተባለው ምናልባት ንስሃ ሊገቡበት ይሆናል እንጂ እነሱን በይቅርታ ስም ለማስፈታት መሯሯጡስ የማንን ተልዕኮ ለማሳካት ነው በማለት ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ በወቅቱ ባለሥልጣናቱ ላደረሱት ጭፍጨፋ ተገቢው የቅጣት ውሳኔ ስለተላለፈባቸው ይህንን ውሳኔ ለማስቀልበስ መሯሯጥ አያስፈልግም ሲሉም ይከራከራሉ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)