December 16, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን የማዳከሙ አዲሱ ሴራና ተንኮል

(አዲሱ ተስፋዬ፤ ለደጀ ሰላም)፦ ባለፈው ወራት በቤተ ክርስቲያን ዙርያ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መንፈሳዊ ጥያቄና  የበጋሻው ክስ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን ደጀ ሰላምም ላይ ይሁን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ጦማሮች ላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከመግለጥ ውጭ የችግሮቹን ሥረ-መሰረት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ጥቂት ነበር። የኛዎቹ ሚዲያዎች ቢተውትም ሌሎች ሚዲያዎች ግን በጉዳዩ ላይ አስገራሚ ምስጢሮችን አስነብበዋል።

አሜሪካዊው ፓስተር ዊሊያም ብላክ (William Black) ለዚህ ተጠቃሸ ነው። ይሔ ሰው በትውልድና በዜግነት አሜሪካዊ ሲሆን ባሜሪካ የተለዩ ግዛቶች ውስጥ የፕሮትስታንት ሰባኪና ፓስተር ሆኖ ከማገልገሉም ባሻገር በኢትዮጵያም 6 አመታትን የፈጀ ቆይታ አድርጎአል:: አሁን በኬንያ የፕሮቴስታንት ድህረ ምረቃ ቲዎሎጂ ኮሌጅ መምህር ነው። ኦኔሲሞስ (Onesimus) በሚባለው የጡመራ መድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ማፈራረስ እንደሚቻልና ባሁኑ ወቅትም የሱና መሰል ድርጅቶች ቤተ ክርስቲያናን እንዴት እተዋጉ እንደሆነ “struggle for the soul of the Ethiopian Orthodox Church “በተሰኘው ጽሑፉ ላይ በሰፊው ገልጧል።

መንፈሳዊ ኮሌጆችን የመበከል ሴራ
ዊሊያም በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተዋሕዶና በተሐድሶ መካከል ከፍተኛ ውስጣዊ ጦርነት እንዳለ ከገለጠ በኋላ፤  አዲሱ ስልት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  መንፈሳውያን ኮሌጆችን መጠጋትና ኑፋቄ መዝራት መሆኑንና በዚህም በእጅጉም እንደተሳካላቸው እንዲህ ሲል ገልጦታል:-
“…One group of American missionaries has insinuated themselves under misleading premises (claiming to be business people when in fact they are missionaries from a Western group) into the area near one of the Orthodox reformists theological colleges. By drawing into their circle some of the reformist leaders and students, they have had some success in persuading some to the Protestant perspective on salvation and the Baptist perspective on baptism.” 1

“አንድ ያሜሪካውያን የሚሲዮን ቡድን ራሱን በመደበቅ (ከምዕራቡ ዓለም የመጡ የሃይማኖት ስዎች ቢሆኑም  የንግድ ሰዎች ነን በማለትና በማታለል) ወደ ኦርቶዶክስ  ሥነ መለኮት ኮሌጆች ገብተዋል።ከኦርቶዶክስ  መሪዎችንና ተማሪዎችን ዘልቆ በመግባትም የፕሮቴስታንት ነገረ ድኅነትንና የነገረ ጥምቀትን አስተምህሮ ለማሳመን ተችሏል።
ይህንንም ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያብራራ፦
The intention of these missionaries is to remove these leaders from the Orthodox Church and from the reformist movement and to set up (of course) their own baptist church. Deception, even in the name of Christ, is still deception. These sorts of tactics are being reproduced elsewhere in Ethiopia.” 2
“የሚሲዎኖቹ ዓላማም እነዚህን መሪዎች ከተዋሕዶም ሆነ ከተሀድሶ በማስወጣት የራሳቸውን የባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰርቱ ማድረግ ነው። ማታልል በክርስቶስ ስምም ቢሆን ማታለል ነው። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ታክቲክ በመላው ኢትየጵያ እየተስፋፋ ነው።”
ሲም (Serving in Mission/ http://www.simeth.org/) የተባለው የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅት የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ አንዱ በሆነው በቅዱስ ፍሬምናጦስ  መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ለማስተማር የመምህር ምልመላውን ባደባባይ ጀምሮአል። ፍሬምናጦስ መንፈሳዊ ኮሌጅ  ብሎ ጎግል ላይ ለፈለገ ሰው እስኪገርመው ድረስ የሚያነበው ነገር ቢኖር በዚሁ ተዋሕዶ ኮሌጅ እንዲአስተምሩ ለመናፍቃን መምህራን የውጣን የስራ ማስታወቂያ ነው ለምሳሌ Serving in Mission ( SIM) የተባለው መናፍቃን ድርጅት ያወጣው ማስታወቂያ እንዲህ ይላል:-

This is an unprecedented opportunity to teach and work within an ancient church with direct apostolic roots. If you are interested in learning about different cultures and teaching in a college with an Orthodox Christian perspective, this should greatly interest you. You will be teaching students from around the country, mainly deacons, priests, and monks who have been chosen by the Ethiopian Orthodox Church to attend this new theological college.” 3

ፕሮቴስታንት ተዋሕዶ ኮልጅ ገብቶ እንዴት እንዲአስተምር ተፈቀደለት? የሚያስተምረውስ ምን ዓይነት ትምህርት ነው? የተዋሕዶ ሊቃውንትስ ጠፍተው ነው የመናፍቃን መምህራን እንዲያስተምሩ ያስፈለገው? ምስጢሩ ምን ይሆን? Serving in Mission (SIM) የተባለውን ድርጅትና ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየሠራ ያለውን ሴራ በተመለከተ ዊሊያም ለተከታዮቹ እንዲህ ሲል አብራርቶታል።
 “Even in my own mission (SIM) there is a small group of missionaries working in partnership with Orthodox leaders to strengthen the educational efforts of the reformist movement.” 4
የዊሊያም ገለጣ በግልጥ እንደሚያስረዳው ሲም (Serving in Mission) ቤተ ክርስቲያንን የቀረበበት ዋና ዓላማ የኦርቶዶክስ ተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማበረታታትና ለመደገፍ ነው:: የሚመደቡትን መምህራን የጀርባ ታሪክ ማጥናት ለዚህ ዋና ምስክር ነው።
ለምሳሌ ዶክተር ቲም ቱሲንክን ብንወስድ የፕሮቴስታንት መምህርና አቀንቃኝ ናቸው። የፕሮቴስታንት ድህረ ምረቃ ኮሌጅ ሰባኪ የሆኑት እኚህ ሰው በኛም መንፈሳዊ ኮሌጆች (ቅድስት ሥላሴና ፍሬምናጦስ) አስተምረዋል። ያስተማሩት ነገረ ሃይማኖት ግን ምን ይሆን? ኑፋቄ ወይስ ርቱዕ እምነት?
“Dr. Tim Teusink  … serving with SIM (Serving in Mission) in Ethiopia,….  His primary focus is theological education, particularly a biblical perspective on sexuality and marriage.  He works with the Ethiopian Kale Heywet (Word of Life) Church, the largest Protestant denomination in the country with 7 million members and The Ethiopian Orthodox Church with 35 million members.  He teaches at the Evangelical Theological College of Addis Ababa (ETC), the Ethiopian Graduate School of Theology (EGST), The Ethiopian Orthodox Church’s Holy Trinity Theological College in Addis Ababa and St. Frumentius Theological College in Mekele (Northern Ethiopia) and other Bible Schools. 5
           
“አድሐሪው እና ተቃዋሚው ቡድን”፡- ማኅበረ ቅዱሳን

ዊሊያም ለዓላማቸው መሳካት እንቅፋት የሆነባቸው አንዱ ቡድን ማኅበረ  ቅዱሳን መሆኑን በምሬት እንዲህ ሲል ገልጧል።
Working against both the ongoing creep of Western values and the attempts by the Reformists to restore the church, a reactionary movement called Mehaber Kidusan and led by members of the hierarchy and priests and others, are seeking to fend off any changes and to preserve aspects of the Church which they feel are crucial to their identity and Ethiopia’s place in the world. Central to this conservative agenda is the preservation of the Virgin Mary’s role in their understanding of the Church’s theology.” 

Ethiopian Orthodox have always been fervently devoted to the Virgin Mary. Members of Mehaber Kidusan intentionally play on this intense loyalty to Mary as a means of inflaming passions against any attempts to change the Church, regardless of whether that change comes at the hands of Protestants, Muslims or Reformists. The more biblical and ecumenical nature of Orthodox tradition promoted by these Reformists is thus a direct challenge to the more parochial and nationalistic aspects of the understanding of Orthodoxy promoted by Mehaber Kidusan and its allies. 6

“እየተንሰራፋ ያለውን የምዕራባውያንን እሴት እና ኦርቶዶክስ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚቃወም ማኅበረ  ቅዱሳን የሚባል አድሐሪ ማኅበር አለ።….የዚህም ማኅበር ዋና ዓላማው ቤተ ክርስቲያንን ከተሀድሶ ለመከላከልና ለሀገሪቱ ማንነት ወሳኝ ነው ብሎ የሚያምነውን የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት መጠበቅ ነው። የዚሁ አክራሪ ማኅበር (ማኅበረ  ቅዱሳን) ማዕከላዊ አጀንዳ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥነ መለኮት ጉዳይ ውስጥ የድንግል ማርያምን ሚና መጠበቅ ነው።”

ይህንንም “አድሐሪ”  ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንን ካላስወገዱ እንደፈለጉ መራመድ አለመቻላቸውን መናፍቃኑ ገልጠዋል። ለዚያም ይረዳ ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማዳከምና ለመምታት በርካታ ሴራዎችን አከናውነዋል። ዘመቻው በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ተጧጡፎ ቀጥሏል። ባለፈው ዓመት ብቻ በርካታ ዓለም አቀፍ እና በበርካታ ሚሊዮን ዶላር በጀት የሚንቀሳቀሱ ክርስቲያን ነን ተብዬ ድርጅቶች የማኅበሩን ስም በየድረ ገጾቻቸው ሲያወግዙ ከርመዋል።7
“Christian sources said a group within the EOC called “Mahibere Kidusan” (“Fellowship of Saints”) had incited members to attack the two evangelists as they were proclaiming Christ. The increasingly powerful group’s purpose is to counter all reform movements within the EOC and shield the denomination from outside threats.In some cases, the sources said, EOC priests have urged attacks against Christians, and government authorities influenced by Mahibere Kidusan have infringed on Christians’ rights.”

የዚህ ዕቅድ ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳንን በውስጥ ሰዎች የማጥላላት ዘመቻ እንዲካሄድበት የውስጥ አርበኞቻቸውን ማነሳሳት ነው። “ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን?” የሚል ተራ ድርሰት መሰራጨቱ Thetruthfighter.net የሚል ማኅበረ ቅዱሳንን ለማጥላላት የተከፈተ ድረ ገጽም መኖሩ የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው። ጥላሁን መኮንንም ድረ ገጽ ከፍቶ ቤተ ክርስቲያንንና ማኅበሩን ለማድከም ብዙ ደክሞ ነበር።

ሙስሊሞችም ጋር ማኅበሩን ለማላተም በረቀቀ ሴራ የተከፈተና ማኅበረ  ቅዱሳንን ሙስሊም የሆነ ሰው በሙሉ እንዲያወግዘው የሚያነሣሣ አስገራሚ ድረ ገጽ ተከፍቶ ነበረ።9 ከውስጥም እነ አባ ሰረቀ ብርሃን “ይሄን ማኅበር!!!!” ብለው አካኪ ዘራፍ ማለት ጀምረው ነበር። ደጀ ሰላም ምስጋና ይግባትና በስውር የተላላኩትን የተሐድሶያዊ ዜማ የያዘ ደብዳቤ ካስነበበችን በኋላ፤ ለብዙዎቻችን የአባ ሰረቀ ነገር ግልጥ ሆኖልናል።10 ሰሞኑን ደግሞ “ይሔ ደም አፍሳሽ ማኅበር”  እያለ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን የመሳደብ ስብከት ጀምሮልናል11። የሱም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሮኬት ሳይንቲስት መሆን አያሻም።

የኛስ ሚና ምን ይሆን? የተሳዳቢውን አንደበት ለማሰታገስ የድሬደዋ ንዑስ ማዕከል ያደረገው  እንቅስቃሴና የቅድስት ሥላሴ ዲን አቡነ ጢሞቴዎስ ኮሌጁን ከመናፍቃን ክህደት ለመጠበቅ ያደረጉት ቁርጥ ርምጃ የሚመሰገን ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ከፍተኛ ርብርብ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን።

ማጣቀሻ
  1. http://onesimusonline.blogspot.com/2010/08/struggle-for-soul-of-ethiopian-orthodox.html
  2. ibid
  3. http://webtest.sim.org/frontend_dev.php/opportunity/8346ibid
  4. http://www.firstpresyakima.com/MC_Teusink.cfm?m=f
  5. http://onesimusonline.blogspot.com/2010/08/struggle-for-soul-of-ethiopian-orthodox.html
  6. http://www.bosnewslife.com/9573-ethiopia-court-releases-jailed-evangelists
  1. http://tehadiso.blogspot.com/
  2. http://tehadiso.blogspot.com/
  3. Deje Selam
  4. http://www.dejeselam.org/2010/12/blog-post.html

102 comments:

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይጠብቅልን ስለጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ ስላሳወቃችሁን እናመሰግናለን። በአባቶቻችን ፀሎትና ልመና የቤተክርስቲያናችን ዶግማዋ፤ ቀኖናዋ፤ ትውፊቷ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ እመብርሃን ትርዳን።

...ትንሣኤሽን ያሳየን... said...

ውድ አዲሱ ለመረጃው እግዚአብሔር ይስጥልን።ፀጋውን ያብዛልህ። እንዲህ በመረጃ የተደገፉ ዳሰሳዊ ጥናቶች ሁሉም አይኑን እንዲገልጥ፤ ዋነኛው ጠላት ማን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳል እና ቀጥልበት።አልዓዛርን ጌታ ከሞት እንደሚያነሳው ብናምንም ድንጋዮን የማንከባለል ድርሻችንን እንወጣ።

Asrat the dilla said...

Bereketun yadeleh addisu lelochachen degmo yihenen mereja Tewahedon lemewedu hula endederse enadreg beteleyem le dilla mimenan yasfelgachewal, engedehe tenkek new wogene min eyetesera endhone eyayen new

Anonymous said...

ጥንት ኢትየጵያ ስትወረር አንዳንድ የኛው ጉዶች የበሉነትን ወጭት ሰባሪዎች ለማያጠግባቸው እንጀራ እየተገዙ አገር ሲያስወርሩ ፣ ቅርስ ሲያዘርፉ እና ቅርስ ወይም ቤተክርስትያን እንዲቃጠል ሲያስደርጉ ኖረው ይሀው ታሪክ ሲወቅሳቸው ይኖራል (ለምሳሌ በግራኝ ወረራ የነበረውን ማንሳት ይበቃል) አሁን ደግሞ አሁን ባለንመት ዘመን ከዚያም በከፋ ዘዴ ሀይማኖት የሚያፋልስ ኑፋቄ የሚያሰፍን ሲመጣ አብሮ ሀይማኖት አፋላሾች እና ኑፋቄ አስፋኞች በፍጥነት ተነስተዋል፡፡
-›ታዲያ ምን እናድሪግ -በተገኘው አጋጣሚ ለምእመኑ ማሳወቅ መመካከር እና ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ መጮህ(መፆም ፣መፀለይ እና ማልቀስ)

Anonymous said...

ውድ አዲሱ የተዋህዶ ልጅ እንዲህ በጥበብ ሲመላለስ ያስደስታል፡፡ እግዚአብሔር ብርታት ሰጥቶ ይህንን ጥረትህን ያግዝ፡፡
ገብቶንም ሳይገባንም በግምት ለዘለፋ የምንቸኮል የራሷ የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ለማንነቷ የቆሙ የቤተክርስቲያን ልጆች የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ትግል በቅንዓትና በመሳሰሉ ተራ አሉባልታዎች ከመፈረጅና የነMISን ሚና ከምንጫወት ይልቅ ከወንድማችን ጽሑፍ ምን ላይ እንዳለን ቆም ብለን እንድናስብና አብረን እንድንሰለፍ ግድ የሚል ይመስለኛል፡፡
ሄኖክ

Anonymous said...

leul
ere ho bilen ininesa gobez!

ዲበኩሉ said...

መረጃውን የሰጠንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን ስለጊዜው ተጨባጭ የሴራ ሁኔታ ስላሳወቃችሁን እናመሰግናለን።
የሚገርመው ከ ቤ/ክርስትያናችን ውጭ ያሉ ሰዎች እኛን ሊውጡን እንደዚህ ሲንሰፈሰፉ እኛ የተደገሰልንን ይፋዊ የጥፋት ድግስ ችላ በማለት ወይም የድግሱ ተባባሪ ሆነን በቤተክርስትያን ውስጥ አለን የምንባል ሰዎች እርስ በእርስ እየተበላላን እና እየተነካከስንን እንገኛለን! ይባስ ብሎ የቤተክርስቲያናችን ዶግማዋ፤ ቀኖናዋ፤ ትውፊቷ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ የበኩላቸውን የሚንቀሳቀሱትን ማህበረ ቅዱሳንና መሰል ማህበራትን አይን ባወጣ መልኩ ስንቃወም እና ለሌሎች አሳለፈን ስንሰጣቸው ኖረናል። አረ እንንቃ ! እስከመቼ ነው ሌሎች እኛው እራሳችን በከፈትንላቸው በር ገብተው የሚፈነጩብን! መመካከር እና ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ መጮህ መፆም ፣መፀለይ እና ማልቀስ ያስፈልገናል። በአባቶቻችን ፀሎትና ልመና የቤተክርስቲያናችን ዶግማዋ፤ ቀኖናዋ፤ ትውፊቷ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ ወላዲተ አምላክ ትርዳን።
ዲበኩሉ ከ ጎንደር

hiwot said...

Dear Adiss may God bless you more.This generation need research based information. So what you did is realy nice keep the good work.Abatochim please try to open your eye & clean our church & college.We meemenan get to pray & cry to the Almighty God

Dn Haile Michael Zeaddis said...

In the name of the Father the Son and the Holy Spirit Amen!
Dear Dejeselamawuyan I am from St Uarael Church of Debre tsige at Addis Ababa(near 22 Mazoria). I always attend the evening preaching and i observed one group related with reformists. This group has held a regular program every Wednesday evening and trying to attract the laity by different cheating. For instance they use Montarbo and tell the laity that they are investing much for the sake of the laity. I know one called Memhir Fithum who was actively participating in the inauguration of the statue of Patriarch Pawlos leading this program.
One monk who is "Megabe biluy at the church of Saint Urael confirmed me that this Memhir Fitsum is really a reformist.
The reformists have already started calling Mahbere Kidusan as "Reformist" and even ask some one whether he is member of mahbere kidusan and if he says "yes" they say "Oh! you are Tehadiso!" and telling the laity so.
please wake up ,every one should be watchful.

ቢኒ said...

ህዳር 23 ቀን 2003 አ/ም በጋሻው ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰብስቦን ነበር ያለን ቢኖር እኔ የሱ ደጋፊ ነኝ ያለውንም እስማማለሁ ማህበረ ቅዱሳን መጥፋት አለበት ልክ ነው ማህበር አቋቁሙ ማህበሩን እናጠፋዋለን እኔ ድላ አጠፍቸዋለሁ እዚህም ማህበር አቋቁሙ ከዛ እኛን ታመጣለችሁ እኛም ስንመጣ አንድላይ እናዋቅራችኋለን አለን ለምን? እነሱ ይመጣሉ ተዋቅራችሁ ስሩ ለምን አላለንም ? እኔን እንዳልስብክ አምላኬ ጠብቀኝ ይላል ግን እራሱን ይሰብካል ለምን ? እኔ ይሄ አካሂያድ አላማረኝም ድጋፍ በመፈለግ ለምን ቤተክርስቲያንን ይበጠብጧታል ? ለኔ ወንጌላዊ ድጋፍ ፈላጊ አይመስለኝም እኛስ ደጋፊዎችስ ለምን ከከሌ ወገን ከከሌ ወገን ከምንል ከቤተ ክርስቲያን ወገን ለምን አንልም የጭፍን ድጋፍ ከየት ሊያደርስ ሁላችንም ልናስብ ይገባል ባይ ነኝ እኔ ያየሁት ቢኖር አይዞችሁ እኔ አለሁ የሚሉን የየራሳቸው አጀንዳ አለቸው እኔ ያስተዋልኩት እሱን ነው ለምሳሌ ቲሸርት ልበሱ የሚሉን ቲሸርት ነጋደ በጥብጡ የሚሉን የሰላም አጀንዳ የሌላቸው ናቸው ለምን መጠቀሚያ ያረጉናል ነጻ ሰው የለም ማለት ነው ? አባት የተባሉትም ብዙዎቹ መሀል ሰፋሪ ናቸው ሰለዚህ እኔ ከአሁን በኋላ ለማንም አልደግፍም ማህበረ ቅዱሳንም የራሱ ድጋፍ አለው እነበጋሻውም እንደዛው ስለዚህ እኔ በቃኝ........

Anonymous said...

ወንድሞቼ
እርስ በርስ ለማጋጨት ወሬ ከማሰራጨት አልፈው ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚሰበክ ሰው ያገኛሉ ብዬ አላምን ለምን ብትሉኝ የታዘብኩት ነገር አለኝ በመቐለ ሐይማኖት ኮሌጅ ለጉብኝትና ለግብረ ገብነት የሚሄዱ ፈረንጆች ትምህረት የደቂቃዎች ትምህርት በሚሰጡበት ጊዜ ሀላፊዎቹ ከተማሪዎቹ ቁጭ ይላሉ ከማህበራዊ ፕሮግራም ወይም ያልሆነ ከተናገሩ መጨረሻ ለተማሪዎቹ በአማሐርኛ ይህ የኛ አይደለም በአእምሮአችሁ እንዳትይዙት፡ እኛ ኮለጃችን ለማሳደግ ልማታዊ ጉዳይ ከረዱን ብለን ብቻ ነው የምንግባባቸው እንጂ ይሉዋቸዋል ግን የታዘብኩት አንድ ፈረንጂ ስለ አንድነት አስተምሮ በውጭ ግና መጽሀፍ ቅዱስ አስተሚሪያለሁ ኦረቶዶክሲ ቀይረያለሁኝ አሁንም ወደ ሰቆጣ ከተማ ኦርቶዶክስን ለመቀየር ነገ እሄዳለሁ ብሎ ሲናገር አግኝቸው በጊዘው ተናድጄ ለ ኮለጁ ሐላፊ አንድ ፈረንጂ ዛሬ በናንተ መጽሀፍ ቁዱስ አሰተምረዋል ብየ ስናገረው በፍጹም እኛ ፈረንጅ ድርጅታችን ለማሳደግ በተለይ አሁን ቤተ መጻሕፍቲ ለመገንባት እቅድ ስለያዝን በተክኖሎጂ በገንዘብና በማህበራዊ ሳየነስ ካገዙን ብለን አንዳንዶች ለጘቡኝት ከሚመጡ እናደርጋለን እንጂ ፈረንጅ ሲመጣ ከነሐጢኣቱ ተሸክሞ መሆኑ እናውቀዋለን; ለዛ ብለንም ያልሆነ መልእክት እንዳያስተላልፉ ከእግራቸው እየተኸተልን አፋቸውን እንጠብቃቸዋለን። ዛሬ ገስት ለክቸር ያደረገው ደግሞ ማህበራዊ አንድነትን በተመለከተ ብቻ ነበረ ሲለኘ ተረጋጋሁና ተኛሁ ግና ሌሊት ሓሳብ መጣልኝ ሸዊዶይ ሊሆን ይችላል ብየ በነጋታው ከተሳተፉ አምስት ሰወች እያፈላለግሁ ስጠይቅ ምንም ልዩነት አላገሁበትም። አንዱ ተምሃሪ ግና ምናለኝ ዋናው የትምህረቱ ሐላፊ ወደ ስብሰባ እገባለሁ ብሎ ለምኸትሉ ከተማሪዎቹ እንዳትለይ ፈረንጁ ኻሊእ ተልእኮ እንዳያስተላልፍ በደምብ ተከታተለው ብሎት ምክትሉና ሌሎች መምሀራን ብቻ ነበሩ ስብሰባው ቃለቀ ግን መጥተዋል ብሎኛል። እና ከዚህ የተረዳሑት ፈረንጆቹ ይዋሻሉ ደግሞ በተለይ በየገጠራችን እየሄዱ ሰው ይዘዋል የሚል ሐይማኖት አለኝ ስለዚ ሁላችን ሳንከፋፈል አንድ ሁነን እንዋጋቸው
ኣብ መቐለ እየ ዝነብር ሐይማኖተይ እውኒ ኦርቶዶክሲ እየ

Anonymous said...

ወዴት መንጫጫት! ከዓጻዌ ሆህት እስከ ፓትርያርኩ ድረስ አንድ ልብ፣ አንድ እምነት፣ አንድ ሐሳብ አንድ ዓላማ ሆነን ካልተነሳን እርስ በርሳችን እያፈረካከሱ እንደሚጥሉት አረጋግጡ። አየ ሰው ለጊዜው ይህንን ሰማን እንጂ በጓዳ የተወተፈ ስንት ጉድ ይኖራል። የመሐመድ ወገን ድብቅ ጉግልስ አይታችሁታል?
አየ አምላከ ኢትዮጵያ ለጠላት ተምበርክካ የማታውቅ ቅድስት ሀገር እርስ በርሳችን በማከፋፈል ጥበብ ተጠቅመው ሊገዙን ተቃረቡ። ነገራችን በጽሑፍ መደርደር ሳይሆን በጸሎትና በጥዋቱ ከዕንቅልፉ ነቅቶ መስራት እንዲሆን አንተ ወገኔ ምእመን፣ ሰንበት ተማሪ፣ ዲያቆናትና ካህናት፣ ማሕበረ ቅዱሳን፣ ቲኦሎጂያን፣ ጳጳሳትና ቅዱስ ፓትርያርክ እባካችሁ ለንጽሕት ሃይማኖታችን ለመታደግ ስንል መከፋፈልና መተቻቸት ትተን አባቶቻችን ዮዲት፣ ግራኝ አሕመድ፤ ድርቡሽና ጣሊያንን እንደመከቱት የአሁኑ አዲስ ነጭላባሽ ቆራርጠን እንጣለው።

Abebe

Anonymous said...

ውድ አልቃይዳ እና ታሊባን መሰል ወገኖች, መረጃ ብላችሁ የምታቀርቡት ነገር መሰርት የለሽ ይመስላል። ሰዎችን ለማሳደድ እና ለመግደል የማይያያዝ ነገር ከየቦታው ትቃርማላችሁ። ጴንጤው የሚለውን እየያዛችሁ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞቻችሁን በከንቱ ታሳድዳላችሁ። ፔንጤዎችም ጅል መሆናችሁን ተረድተው በአእምሮአችሁ ይጫወታሉ። ደጀሰላሞች አሁንማ ማቆች መሆናችሁ ተረጋገጠ። በእውቀትና በክርስቲያናዊ ጥበብ/ፍቅር ሳይሆን በታሊባናዊ አካሄድ የሚንቀሳቀሰውን ድርጅት ከፍ ከፍ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ስታደርጉ ይስተዋላል።

Anonymous said...

Thank you very much Addisu. this is a great job. We all have to open our mind widely so that we will obtain concrete idea about our church. It is well known that MK is protecting our church from evils but not all members of EOTC understood its work.

Anonymous said...

አዲስ እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥህ!!!!!!!!!!!!! አውቅሃልሁ ከዚህ ብላይ ማለት አንድምትችል;; በርታልን:: ስፋ ያለ ጥናት አጥብቃለሁ:: አመ ብርሃን ብርሃን ትሁንህ::

አኛስ ወገኖች ምን ዐይነት ደባ አየተስራ ገባን??? ልቦና ይስጠን

Anonymous said...

In the name of God.
Dearest All, this is real . Even me, myself was the one who was complaining Mahbere Kidusan for their papers(gaeta ena metshetachew) in relation to their comments on mezmur and the likes. but you know what happend, In my parish kidste kidusan mariam gedam ,here in Addis people complain some monks and priests for they are protestants. as a result addis ababa dioces started the invetigation on wednesday. for your surprise two monks ,two mergetas and one priest becomes protestants and jhobawitness. I was in trouble to accept this but fortunately they have already gone. what surprises me is that they give warnings to any clergy in the parish that if they inform any body he will be in jail in the same day.
for this reason the deacons are claiming the dioces for Garanty to inform the detail.

I will confess for my opposition to MK as well. MK please Go well and Let God help you all the time.Let God protects his church.

Unknown said...

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን!
የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን በየዕለቱ ከምናየውና ከምንሰማው ሁኔታ መረዳት ይቻላል:: ይህ ሁኔታ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች አሳሳቢ ሲሆን ከጥንት ጀምሮ ውድቀቷን ለሚሹ ደግሞ የገና ስጦታ የሆነላቸው ይመስል ሲደስቱ ይታያል:: ሁሉ ሊረዳው የሚገባ ግልጽ እውነታ ግን ተዋህዶ አሁን ከምናየው ሁኔታ እጅግ የከፉ ፈተናዎችን አልፋ እዚህ መድረሷን ነው :: ዮዲት/ጉዲት ለአርባ አመታት ያህል በጦር ብትወጋትም ተዋህዶ ለመለመች እንጂ አልጠወለገችም:: ግራኝ አህመድ 15 አመት ቢወጋትም ተዋህዶ ከፍ ከፍ አለች እንጂ አልወደቀችም: : ስጋዊ ጥቅማጥቅም የወለዳቸው መናፍቃን ከ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ቢወጓትም ተዋህዶ አበራች እንጂ አልጠፋችም:: ከጥንት ጀምሮ ከውስጥ እየተነሱ ብዙዎች ቢዘምቱባትም የዘመቱ ባት ጠፉ እንጂ ተዋህዶ አልጠፋችም::
የደጀ ሰላምን አምድ መከታተል የሚችሉ ድረ ገጽ ተጠቃሚ የሆኑ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች በሚነበበው የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተና ልባቸው እየተነካ አይኖቻቸው በዕንባ ሲሞሉ ውስጣቸው በቁጭት ሲነድ ከገጻቸውም ሀዘን ሲነበብ ማየት እየተለመደ መጥቷል:: የድረ ገጹ ተጠቃሚ የተዋህዶ ልጆች ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው ቀረቤታና የእምነት ጽናት አኩል አለመሆኑን ከእያንዳንዱ ዘገባ በኋላ የሚንጸባረቀውን የአንባብያን ስሜት ከደጀ ሰላም የአስተያየት ገጽ በማየት መረዳት ይቻላል:: በአካልም አንዳንዶች ይህ አይነቱ የቤተ ክርስቲያን ችግር ያለ ጸሎት አይፈታም በማለት በእንባ የተዋህዶን አምላክ ሲማጸኑ ሌሎች ምዕመናን ደግሞ በጥላቻ ሲዋጡ ፣ሀይለ ቃል ሲናገሩ፣ ሀይል የተቀላቀለበት መፍትሄም ሲሹ ይስተዋላል ::
ውድ የተዋህዶ ልጆች እናት ቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ውስጥ ስትሆን የበለጠ በመቅረብ በጋራ መንፈሳዊ መፍትሄ መሻት ይገባናል:: ወንድማችን አዲሱ ያስገነዘበን ጉዳይ ይገርማል ብለን የምናልፈው ነገር አይደለም ይልቁኑ በመቀራረብ በፍጥነት ልንዘምትበት ይገባል:: የመጀመሪያው መፍትሄ የችግሩን አሳሳቢነት ለመላው ምዕመናን በስፋት ማስገንዘብና ምን ማድረግ አለብን? የሚለውን በጋራ መወሰን ያሻል:: በቤተክርስቲያናችን ያሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችንም በዚህ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥና ለመፍትሄው ማንቀሳቀስ ወሳኝ ጉዳይ ነው:: የተበረዙ ወይም የተመረዙ መጻህፍት በየገበያው ብቅ እያሉ ነውና የእኛ ያልሆኑትን መጻህፍት ምዕመኑ እንዳይሰናከልባቸው በቶሎ ማሳወቅም ይገባል:: በቤተክርስቲያናችን ጉዳይ በእውነተኛ የዕምነት ፍቅር እያገለገሉ ያሉ አባቶችንም ለመፍትሄ ማሰለፉ ወሳኝ ነው ::በጥቅምና በስጋዊ ጉዳይ ብቻ ቤተ ክርስቲያን ዋን የተጠጉ በሀገርም ከሀገር ውጭም ያሉ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው የስም ካህናትንም በመረባረብ መስመር ማስያዝ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል:: አለበለዚያ በተናጥል የሚደረግ ትግል መፍትሄውን ያርቅብናልና ስለ እመብርሃን አብረን እንስራ::
ሁላችን ልናስተውለው የሚገባው የነገ የቤተ ክርስቲያናችን እድገት ዛሬ እኛ በምንሰራው ስራ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነውና መልካሙን ስራ እንስራ:: የእኛም የወደፊት ህይወት ብሩህነት ከቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን አንዘንጋ:: የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አሁን ታላቅ የስራ ጊዜ ነውና እባካችሁ ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን እንነሳ:: የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ በየጉባዔው እንዲህ ይላሉ “A church without youth is a church without a future.” http://www.copticchurch.net/topics/pope/ ይህ ትልቅ እውነት ነውና እኛም የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ቀጣይ ጉዞ ለማሳካት በጋራ እንስራ መፍትሄ ፍለጋ እንመካከር:: የዚህ ምክክር ጠቀሜታ ለእያንዳንዳችን ቀጣይ ህይወት እና ለቤተክርስቲያናችን ህልውና ወሳኝ ነው:: ታላቁ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ በአንድ ጉባኤ “A church without youth is a church without a future.” ብለው ሲናገሩ በሰንበት ትምህርት ቤት ሲተጋ የነበረ አንድ ጎበዝ ወጣት እንዲህ አላቸው አዎን አባታችን እንዲሁም “ youth without the church are youth without a future.” http://www.copticchurch.net/topics/pope/ ግሩም ነገር ተናገረ !!! ከሁሉ ይልቅ ዕለት ዕለት የሚያሳስበኝ የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ነው ያለውን የሐዋርያው ቃልም ዕለት ዕለት ብናስብበትስ??? ወላዲተ አምላክ ትታደገን : አሜን::

ኃጥዕ ወአባስ

bisotegnaw ze dila said...

Dear addisu, please keep on writing this very very very very... important infos to all cristians including other medias which could be acsed by many christians, kele hiywet yasemalin.. ade please... keep on... we are with you. you can ask us infos..

Unknown said...

Dear Addisu,yetedebeqewun mestir awutiteh betekeresetitanachin layi yanetaterewun wusetawina wuchawi fetena endinreda selareken Egzeabher tsegawun yabezalih, yagelgelot zemenehin yibarekelin. Kegna min yitebeqal? tileq teyaqe newu.

Anonymous said...

addisu tiru new marajawn wadijalu:-

balfw manfaswi kollegu rasu ywichi swoch chigir fataru bilo neberna lmin rasun kwiche sawoch ayataram? EOTC balem lay manim ayimasilatim liyu nech. ywichi sew gaboto liyastamiribat ayichilim. y dogma astemari ywichi sew new sibal samichem batam garmognal. tadiya bar takafitolachw yele.

bzhi abatoch endalelu yakil zim balubet zamn esti hulachin tababiran bago lalsirat enitar.

Anonymous said...

ዉድ ወንድሜ የመቐሌዉ ፈረንጆቹ እኮ የሚያታልሉት የተማረዉንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደንብ የተረዳዉን አይደለም። እነሱ ከፍሬምናጦስ ኰሌጅ ጋር መታየት ብቻ ነዉ የሚፈልጉት፤ ከዚያ በሗላ የዋህ ምዕመናን የኛ ቤተክርስቲያን አማኝ ናቸዉ እያሉ ይታለሉላቸዋል። ምክንያቱም ከኛ ሊቃዉንት ጋር ስምምነት ሲያደርጉ፣ አብረዉ ሲወጡ ሲገቡ ስለሚያዩ ነዋ!!! ለመሆኑ ገንዘብ ሕይወት ይሆናል? ሐይማኖትስ ከገንዘብ አይበልጥም? የከሳቴ ብርሐን አባቶችስ ለኛ ለልጆቻችሁ ምን አይነት ጉድ ነዉ የምታስተምሩን፤
ሐይማኖትሰ ተዐቢ እምኩሉ ብዕል!

Dillu said...

በእውነት ጥረታችሁ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሂዶ ሃይማኖታችንን ከመናፍቃን እምነት ለመጠበቅ ከሆነ እጅግ በጣም የሚደነቅ ተጋድሎ ነው። ማኅበራችሁን የማይደግፈውን እና ተልእኮአችሁን በጥርጣሬ የሚመለከተውን ሁሉ ግን ''መናፍቅ'' እያላችሁ የምትጥሩት ከሆነ ኣደጋ አለው። "በሚበሉና በማይበሉ ፡ በመገረዝና ባለመገረዝ" የክርስትና ሃይማኖትን እየመዘናችሁ በነዚህ ላይ ልዩነት ያለውን ሁሉም "መናፍቅ" ስትሉ እንደነበር ኣስታውሳለሁ። በዚህም ምክንያት ወንጌላዊት የሆነሽውን ቤተክርስቲያናችንን ኦሪታዊት እንደሆነች ኣድርጎ በሚያሳይ ሁኔታ ስእላችኃታል። ሃይማኖትን ከባህል ለይተን ማየት ካልቻልን ነው ለመናፍቃን ጥቃት የበለጠ የምንጋለጠው። ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም ኣምላክ መሆኑን ፤ ኣምላክነቱ ከሰውነቱ ያለፁም መቀላቀል የተዋሐደ ነው ብሎ የሚያምን ሁሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ ነው። በጻድቃን፡ በሰማዕታት ፡ በመላእክት ፡ ከሁሉም በላይ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ኣማላጅነት የሚያምንና ድንግል በህሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ የሚል ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ክርስቲያን ነው። በኣብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ በልዩ ሶስትነት ያላቸውን ኣንድነት የሚያምን እና ኣምኖ የተጠመቀ ሁሉ ክርስቲያን ነው። እነዚህንና ሌሎችንም የዶግማና የቀኖና እምነቶች የሚቀበሉ ሁሉ የቤተክርስቲያናችን ኣባሎች ናቸው።
ስለዚህ "ተሐድሶዎች" የምትሏቸው ከዚህ የተለየ ትምህርት ያስተምራሉ?

Anonymous said...

ውድ ወገኔ እንዲህ ብለህ/ሽ/ፉ የጻፍክ/ሽ/ፉ "ውድ አልቃይዳ እና ታሊባን መሰል ወገኖች, መረጃ ብላችሁ የምታቀርቡት ነገር መሰርት የለሽ ይመስላል" እባክዎትን ወደልብዎ ይመለሱ ምክንያቱም፤ እኔን መዋሸት አይችሉም፤
Long time ago I had been participating the hidden agenda of Tehadsso. When we raised any questions about Tehaddso. The leaders of that mission፣ they used to deny the existence of Tehdisso by saying (ተሃድሶ የሚባል የለም፤ አንዳንዶችህ ዝም ብለው የሚያስወሩት ነው በማለት ይክዱ ነበር).

Jesus Christ Lords of Lord, Kings of King.

ጆሮ ያለው ይስማ said...

I think it is time for well informed Tewahedowian to connect the dots and wake us up like Adisu did.

God bless you Adisu.

ታደሰ said...

ወይጉድ:: እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ::

Anonymous said...

ለአዲሱ አስተያየት አለኝ
እኔ ለመረጃ ብለህ ከታች በዘረዘርካቸው ሊንክስ መሰረት እውነታውን ለመዳሰስ ሞክርያለሁ መከታተልህ የሚያስመሰግን ቢሆንም የአዲስ ተጠማቂ ወሬ አስመስልኸዋል።
የፕሮቴስታንት ወሬ አሁን ብቻ ነው’ዴ የሰማኸው? ለጸሎት ብለው ሲሰባሰቡ የሚያቀርቡት ሪፖርት ከኦርቶዶክስ ይህን ያህል ወጣት ዘርፈናል፣ የድንግሊቷ ብለው የሚያምኗት ስእል ርገጡት፣ የጻድቃኑም ይሁን የገድላቱ፣ መጻሕፍቱም ይቃጠሉ፣በየገዳማቱና አድባራቱ እንዲሁም በከፍተኛ ተቋማቱ ያሉትን ምርጥ ምሁራን አምጥተናቸዋል ለምሳሌ ያህል እግዚአብሔር ይባርከውና ማህበረ ቅዱሳን ባቀረበው ሪኮርድ ፊልም “ ብጹዕ አቡነ ያሬድ “ የሚባል የኦርቶዶክሱ ጳጳስ ዘምተነዋል ብለው ውሸታቸውን ሲቀዱ አልነበሩም?
ወንድሞቼ ሁሉንም ነገር በስሜት ሳይሆን በማስተዋል ይሁን ጉዞአችን፤ የጰንጤዎች አካሄድ እንደ እስስት ናቸው። ቋሚ እምነት፣ ቋሚ ፕላንና ቋሚ ቁምነገር የላቸውም፤ በየቀኑ አዲስ ፍሬአልባ ወሬ ፈጥረው ለአለቃቸው ሪፖረት ከማቅረብ ሌላ እውነተኛ ሃይማኖታዊና ልማታዊ የሚሰሩት የለም። የአሁኑ ያቀረብኸውም ምንአልባት ለመግባት ተመላልሰው መግቢያ በር ሲያጡ አንዱ ዘዴ እርስ በርስ አበጣብጠው ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ ብለው የፈጠሩት እስትራቴጂ ነው።
ነቅተን እንጠብቃቸው
ፈለቀ

Anonymous said...

ብዙዎች የዋሃን እንደምናስበው የProtestantism(የTehadsso) ተልህኮ ስለጌታ እናት፤ ሰለመላእክት ፤ ስለቅዱሳን ወይም ስለ ቤትክርስቲያን ስርኣት ቤትክርስቲያን የምታስተምረውን ማስተው ብቻ አይደለም። ዋነውና ትልቁ ተልህኮ ሃዋሪያት ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ ወንጌልን መስበክ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ማንነትና ስራ ላይ የሚቃረን ትምህርት ምስተማር ነው። ከአባቱ ጋር በክብር እኩል የሆነውን ጌታን ከክብሩ በማሳነስ በዚህ ዘመንም ስለእኛ እንደሚማልድ(እንደሚጸልይ) ማስተማር ታላቅ የስህተት ትምህርት መሆኑ መታወቅ አለበት። ማ/ቅዱሳን አና ሌሎች መምህራን በዚህ የዶግማ/የሃይማኖት መሰረት/ የሆኑ መሰረታዊ ትምህርቶች ላይ ይልቁንም ከቅዱሳን የአማላጅነት እና ስርኣት ቤተክርስቲያን በበለጠ ሰፊ ጊዜና ማብራሪያ ተሰጥቶት ሊሰራጭ ይገባል። ዋነውና ትልቁ ልዩነት በእኔ አመለካከት ከProtestantism(ከTehadsso)ይህ ትምህርት ነው ። ስለእመቤታችን፤ ስለመላእክት፤ሰለቅዱሳን... ቀጥሎ የሚመጣ ነው። ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ፤ እውነተኛው የእግዚሃብሄር ልጅ፤ እርሱ እግዚሃብሄር ሳለ(ዩሓ 1፤1-)፤ ከክብሩ ስፍራ ወደ እኛን ፤ እኛን ሊያድን ሰው እንደወነ(ከድንግል ማርያም) እንደተወለደ ፤ ሰለሃጥያታችን እንደተሰቀለ ሞቶም በክብር እንደተነሳ እንዳረገም፤ አሁን በሙሉ ክብሩ እንዳለ፤ ሊያድንም ሊፈርድም ቻይ እንደወነ የሚያምና የሚያውቅ፡ እውነተኛው እግዚሃብሄር መንፈስ ቅዱስ በማይታወቅ የድምጽ ጋጋታ ልሳን ነው፤የጸጋ ስጦታ ነው ብሎ ቀድሞም ወነ በዚህ ዘመን እንደማይሰራ በሃይማኖት መርምሮ የተርዳ ትወልድ። መጽሓፍ ቅዱስ አንዴ እንደአንድ መጽሓፍ የእንኩ ተምሎ የተሰጠ እንዳልሆነ እና በአንድ(?) ቮልዩም (ጥራዝ) የተዘጋጀው እያንዳንዱ ቅዱሳን መጻህፍት ከተጽፉ ከብዙ ዘመናት በዋላ እንደወነ የሚረዳ ትውልድ ካለን። Protestantism(Tehadsso) የሚያነሱት ማንኛውንም የሃይማኖት ነገር ለምሳሌ ስለቅዱሳን አማላጅነት፤ስለጾም አስፈላግነት... ከመነጋገሩ በፊት መሰረታዊ እና ዋና ከወነው የወንጌል ትምህርት፦ በጌታች እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተለየ ትምህርት ስለምታስተምሩ በትንሹ ልዩነት(መልስ ስለሌለን እንዳልወነ ይታወቅ) ላይ መነጋገር ከእስማኤልዊያን ጋር በእግዚሃብሄር ሶስትነት እና አንድነት ላይ ከመነጋገር ይልቅ በጾም ወቅት ስጋ ስልመብላትና ስላለመብላት እየተነጋገሩ ጊዜን አንድማባከን ነው፤ እያለ ከመከላከል ይልቅ ወደማጥቃት የሚዘምት፤ የመናፍቃንን ምላሽ የሚማር ትውልድ ብቻ ሳይሆን ሃዋርያት ከሰበኩት የተለየ ወንጌል ንጉስም ወይም ከሰማይ መልአክም፥ ቢሰብክ/ልሰብክ ቢሞክር/ እየተከታተለ በእግዚሃብሄር ቃል የሚይፈርስ ትውልድ ቤተ ክርስቲያን ልታፈራ ይገባታል።

Anonymous said...

ወንድሜ አዲሱ፤- እግዚሃብሄር ጸጋውን ያብዛል፡ እንደ "አድስ ተጠማቂ" ሳይዎን ሁሉን እንደተርዳ ያለህን መረጋጃ ስልካፈልከን እናምሰግናልን። የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ነው በካናዳ ወስጥ ካሉት ከተሞች ወስጥ በአንድ የፕሮተስታን ችሀርች እሄድ ነበር። በይፋ በጉባዬአችው ወስጥ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ለሚያራምዱት የበለጠ ብርታት እንዲኖራቸው ጸሎት ሲደርግ ፈንድም ይሰበሰብ ነበር፤ ተሃድሶን ለሚቃወሙ ደግሞ የእርግማን ጸሎት ሲያደርጉ በጉባኤው ውስጥ ነበርኩ።

ዲበኩሉ said...

dillu ለሚባለው አስተያየት ሰጭ ወመድማቸን እንዲህ በማለት የገለጽከው ነገር የሚገርም ነው....ስለዚህ "ተሐድሶዎች" የምትሏቸው ከዚህ የተለየ ትምህርት ያስተምራሉ? ወይ ተሐድሶዎች እስተምህሮት እልገባህም ወይም ከተሐድሶ እራማጆች አንዱ ነህ!!!አንተ ከላይ የዘረዘርካቸውን ነገሮች ሁሉ ቢያደርጉ ለምን ተሐድሶዎች ይባላሉ? ተዋህዶዎች እንጂ! በጣም የሚገርመው አብዛኛዎቹ የማውቃቸው የተሐድሶ አባላት የምሉት ተሃድሶ የሚባል የለም፤ አንዳንዶችህ ዝም ብለው የሚያስወሩት ነው ....በማለት ነው። ለሁሉላችንም እመብርሃን ትርዳን!


ዲበኩሉ ከጎንድር

Anonymous said...

የበግ ለምድ የለበሱ ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለልጆቾቻ እንዲለቁ ሀያሉ እግዝአብሔር እርዳን፡፡ ድንግል እንደዘወትሩ ሁሉ ማልጂን፡፡ አዲሱ እግዝአብሔር ይባርክ!

Anonymous said...

እግዚአብሄር ይስጥህ ሰዎች ዳር ዳር ሲሉ አንተ እውነቱን አወጣህ ይህ ሁሉ በየሀገረ ስብከቱ ግር ግር መፍጠር አላማው ይህ ነው እኔ የምለው እነዚህ በውጭም በውስጥም የሚበጠብጡን ሰዎች ለምን አይተውንም እውነት ጽድቅ ከሆነ አላማቸው በአውሮፐና በአሜሪካ የተዘጉ አዛውንቶች ብቻ የሚጎበኙአቸውን ቸርቾቻቸውን ለምን ለማስከፈት አይሞክሩም ነው ወይንስ እውነተኛ ሀይማኖትን ለማጥፋትና እኛም እንደነርሱ እንድንሆን ነው ይህ ሁሉ ትግል ቤተ ክርስቲየን እንደሆነች በክርስቶስ ደም የተገነባች ነች እንካን እነሱ የሲኦልደ ጆችም አይችላትም ግን ሂህ ነገር የመጣው ለእውነተኛክ ርስቲያኖች ፈተናነውና ፀልዩ ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ ለብቻው በአስር አውታር መወጠር አይችልም ስለዚህ በየሀገረ ስብከቱ ያላችሁ አባቶች ቄሶች ዲያቆናትየ ሰንበት ትበት ተማሪዎች ምእመናን ሁኔታውን በደንብ ተከታተሉትየ b ፊቱን የአባቶችችን አካሄድና አሁን እየመጣ ያለውን በደንብ ተገንዘቡ ያለዚያ እንደ አካአብ እርስታችንን ላለማስነጠቅ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ሞት ሁሉ ይኖራል እግዚአብሄር አአባቶቻችን ያቆይልን

Tsehay said...

Egziabher keteman kaltebeke sew zem belo yelefal betekerestianenem endihu beterefe gen ene yepawlos negh ene yeablos eyalachehu ers bersachu atetalu seletebale ebakachu erse bersachen anebelala letelatem erasacenen asalefen anest getachen eyesus kerestos eko demun yafeseselen segawenem yekoreselen legna feker belo aydelem ende endet egna bersu feker menor yaketenal emebetachen eko enbawan yemetafesew letsadeku aydelem lehateu enji selezih yazene binor yetseleye endetebale tewatena mata abzeten entseleye lelawen leamlakachen enetewew yabate tekel yalhone hulu yekoretal aydele yemilew metsehafu selezih Tewahedo Haymanot bekerestos dem yetemeseretech selehonech atetefam sew zem belo yegziabheren madan biyay melkam new ena ers bersachen anetelala kerestos yeker endalen yeker tebabelen bebetekerstian enenur selame egziabher kehulachenem ger yehun emebetachen Kidist Dengel Maryam beamalagenetwa tastarken hulunem befeker adergut.Dejeselamochem egziabher yatsnachu.

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!
ወገኖቼ እኔን ያልገባኝ ነገር ለምን የተግባር ሰው መሆን ሲገባን የወሬ ሰው እንሆናለን? እኔ የታዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ማህበረ ቅዱሳን ሁል ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እራሱን ሲያደንቅ እንጂ እራሱን ሲወቅስ አልሰማም። ንፅሒት የሆነችውን ሐይማኖታችንን እኮ እንኳን ለቤተ-ክርስቲያናችን ቅርብ የሆነና በስሟ የሚኖር ቀርቶ እኛ እንኳን በሩቅ ያለነው ሰዎች ስለ ሐይማኖታችን በደንብ ይመለከተናል። ደግሞ ምንም አይነት ሐሳብ ይነሳ ዘወትር በተለይ የአንድ ግለሰብ ስም አብሮ ይነሳል። ለምን? እስቲ አዲሱ የተባሉት ያነሱት ጉዳይ በእርግጥ አንገብጋቢ ነው። ማህበረ ቅዱሳን ይህንን ሰራ ከማለታቸው በፊት ግን ለቤተ-ክርስቲያናችን በጣም ቅርብ እንደመሆናቸው መናፍቃኖች በቤታችን እስኪነግሱ ድረስ ምን ይሰሩ ነበር? እኔ ግን ማህበረ ቅዱሳንም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተን ሰዎች ሌላው ለጠላት በሬን አልከፍትም ሲል እኛ እርስ በርስ እየተነካከስን ለገንዘብና ለሚቀር ርካሽ ጥቅም ብለን ሐይማኖታችንን አሳልፈን ባንሰጥና ከወሬ ይልቅ በተግባር መፍትሔ ብናመጣ መልካም ነው። ማህበረ ቅዱሳንም ምንም አየሰራ አይደለም ባንልም ያለውን ድርሻ ያህል እየሰራ አይደለምና ይህንን ሰራው ከማለት መስራት የሚገባውን ያህል ቢሰራ ጥሩ ነው።


እግዝአብሔር ሐይማኖታችንን ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን።አሜን!!

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

new mk generation said...

new Mk is a generation no one can stop or tilt his mission. we the new spirit of Mk(free from socialism or other political agenda ) are working all over the world to challenge the whole enemy's of gospel starting from the patriarchate to parish level. each Sunday school is ready to protect his congregation. Mk is working with all the church fathers.only rent collectors and are blackmailing his work.
now this is the time for all Ethiopians including government officials must shift their altitude towards our church no agenda we will be entertained other than gospel in all diocese of the church.we will never ever give a chance for intruders,rent collectors and atheist for flashing their rubbish doctrine and flesh generated ideas.
don't expect the main office of Mk @ 4 kilo is leading this movement.thanks to real fathers the have done their assignment on software of a generation so that this is the time for revival of our church any one who is ready for journey to Jerusalem in the sky all the doors of the cart are open were your life vest and join us
O death, where is thy sting? ...............

meti said...

oh dege selam it's nice to all orthodox Christians. you knows that what protestant and the so called "tehadiso" currently wanted how they need to attack our church. if all tewahido Cristian knows this all thing he/she protect their belief verily. but how much of our country people has access to computer to visit your site try to publish all in magazines, news papers.... GOD PROTECT OUR COUNTRY!!! bye 4 now

Anonymous said...

መከርቤ እስቲ ማህበረ ቅዱሳንን ለቀቅ አድርገው ስለቤተክርስቲያን ችግርና መፍትሄወቻቻው ያውሩሁሌ ማህበረ ቅዱሳንን መውቀስ መውቀስ መውቀስ ሰውን መተቸት አልወድም ነበር የርሰወ ግን በዛ ተሀድሶዎች ሲነኩ እንጅ የሚያንገበግበዎትሌላ ችግር ምንም አይመስለዎትም አረ ይተዉ መርከቤ እግዚአብሄር አይወደውምውይ ለይቶለዎት ማልያ እኔ እስከምገነዘበው ድረስ ማህበረ ቅዱሳንን የሚጠላ የቤተክርስቲያን ጠላት ብቻ ነው ምነው እነርሱን ባደረገኝና ያለኝን ሁሉ ለቤተክርስትያን በሰጠሁ ጊዘዜው ወኔው ብርታቱ ኑሮኝ ማለት ነው መርከቤ ወሬኞቹስ እኛ ከዳር ሆነን የምናወራው

Unknown said...

Thank you Dejeselam!!

hafhag said...

Half
Hello ቢኔ;
You made a mistake why because you were in motion of Begashaw or some body else. but no one should be beside of any body. we are already beside of Jesus Christ.
But we shouldn't forget respecting of our elders and listing of their preaching is not bad since they could preach according to the churches law and dogma.

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል said...

ዕለቱ ህዳር 22 ቦታዉ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ሰዓት ሰርክ ጉባኤ የቅዱስ ዑራኤል ወርሃዊ በዓል መምህሩ መምህር ታሪኩ አበራ የቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ሃላፊ ፡

በአፅራረ ቤተክርስቲያን መጋለጥ የተቆጩ ይመስላሉ የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም እየኮነኑ አስተማሩ ምዕመናንም እንዲያወግዙ ለማነሳሳት ሰበኩ ይባስ ብሎ በ1980ዎቹ የተወገዙት መናፍቃንና የቤተክርስቲያን የዉስጥ ጠላቶች በግፍ እንደነበረ ተናግረዉ እርፍ
መምህሩ የቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ሃላፊ መሆናቸዉ ትምህርቱን ከጨረሱ በኃላ በመድረኩ መሪ ስነገር ዲያቆን በጋሸዉም ዘዉትር መክሰኞ መደበኛ መርሐ ግብር እነንዳለዉ ስለማዉቅ ነገሩን የአይጥ ምስክር ድንብጥ እንደምሉት ዓይነት ሆኖብኛል
ቅድስት ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ችግር እንዳለባቸዉ አረጋግጣ አልመለስም ሲሉ የለየቻቸዉን በቤተክርስቲያን መድረክ ቆሞ በስህተት በግፍ ነዉ ብሎ ማስተማር ምን ይባላል፡
አንድ
የቤተክርስቲያን አባቶችን ዉሳኔ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና አቅልሎ በምዕመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነዉ
ሁለት
እራሳቸዉ ተወግዘው የተለዩ የአፅራረ ቤተክርስቲያን የግብር አባሮቻቸዉ መሆናቸዉን
እየመሰከሩ ነዉሌላዉ ተሃድሶዎች አሁን የጀመሩት አጉል ብልጣብልጥነት ማንንም በተለይም እዉነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን የማህበረ ቅዱሳን አባል ወይም አገልግሎቱን አይተዉ የሚወዱትን ተሃድሶ ነህ ማለትን ነዉ
ይህንንም አንድ መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ወሊቀመዘምራን የሆኑ የንስሀ አባቴና መምህሬ ከሁለት ሰዎች በተለያየ ጊዜ እንዳጋጠማቸዉ አጨውተዉኛል
በዚህ አጋጣሚ ዘዉትር ረቡዕ በደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን, የሚካሄደዉን የሰርክ ጉባኤ መገኘት የሚትችሉ ይዘቱንና በተለይም በጉባኤዉ መጨረሻ የሚደሰኩሩትን የሀዉልቱ ስራ አቀንቃኞችንና ንግግራቸዉን አይታችሁ እንዲትፈርዱእንግድህ እንንቃ

Anonymous said...

ለዉድ ወንድሜ ድሉ
ተሐድሶዎች እኮ ላይ ላዩን በክርስቶስ አምላክነት አናምንም አይሉም፤ እንደዚያማ ካሉ ሙስሊም ተብለዉ እንደሚወገዙ ያዉቁታል። እነርሱማ ተአምረ ማርያም አያስፈልግም ነዉ የሚሉት። አላማቸዉ ደግሞ የድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት ጥያቄ ዉስጥ ማስገባት ነዉ። ከዚያስ ተርጉመዋ!!! ያለ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት ነገረ ተዋሕዶን እንዴት ማዉራት ይቻላል? ስለዚህ ተሐድሶዎች ቅዳሴ ማርያም፣ ሰአታት፣ ድጓዉ፣ ወዘተ ይቀነስ የሚል አጀንዳ ይዘዉ የሚንቀሳቀሱት ተያያዥነት ስላለዉ መሆኑን አንርሳ። እነዚህ መጻሕፍት በሙሉ የሚተርኩት ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰዉ መሆን፣ ስለ ነገረ ድሕነት፣ ስለ ተዋሕዶ ነዉና።
በተረፈ ለሊበራሎች ጥብቅና የቆምክ ይመስል በመገረዝና ባለመገረዝ ምናምን እያልክ የምትቀላቅለዉን በመረጃ አስደግፈህ ብታቀርበዉ እንወያይበት ነበር። እስኪ በመናከስና በሩቁ ይላሉ አሉ ተብለህ ከ3ኛ ወገን በሰማኸዉ ሳይሆን እስኪ ራስህ ባለህ መረጃ ላይ እንወያይበት እኛም እንማርበት ይሆናል።
Thanks

Anonymous said...

ዉድ መርከቤ ንጉሴ
ምነዉ ለወቀሳ ጊዜ ብቻ ነዉ እንዴ አይንህ የሚገለጠዉ? ምነዉ ማህበረ ቅዱሳን መናፍቃንን በማጋለጡ ያንን ያክል ሲሰደብ፣ በቅርቡም አቶ በጋሻዉ ደመ ጠጭ ብሎ በአውደ ምሕረታችን ላይ ማህበሩን ሲያዋርደዉ የት ነበርክ? እና ማህበሩን እንደ እሾህ አጣብቀዉ የያዙት ዉስጣችን ያሉ አባት የመሰሉ ተሐድሶዎች አይደሉምን፣ እነ አባሰረቀ? ይሄንንስ ስራ ትቶ ያዉቃል? Think all these issues before bashing MK.

yalewtefera said...

እግዚአብሔር ይስጥልን እጅግ ጠቃሚ የቤተክርስቲያን ጉዳይን ነው ያካፈላችሁን እግዚአብሔር ስራችሁን ይባርክ፡፡ በየዋህነትነና መረጃም ካለማግኘት ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ቀና ደፋ የሚሉትን ግለ ሰቦች ስማቸው ሲነሳ ደስ የማይላቸውም አሁ እውነቱን ይረዳሉ ብዬ አምናለሁ፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ስቶን ቤቱን በውጭ ካሉት መናፍቃን እና ውስጥ ካሉት የናት ጡት ነካሾችና የይሁዳ የግብር ልጆች እንድንጠብቅ ይርዳን፡፡
ሁልጊዜ የምትገፋ ነገር ግን መቼም የማትወድቅ ቤተክርስቲያንን ለሚጠብቅ
ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን አሜን!!!

Anonymous said...

Kale hiwot yasemalin
I couldn't stop crying throughout this article. The reason is because if we were a rich country, nobody would have a gut to come and try to destroy this ancient church. And white people always thought they have brought christianity to Africa. Seeing our church, the oldest in the world is too much to handle. Anyway we all need to unite and protect our church from the invasion of devil's army.
Egziabher Ethiopian yibark.

Anonymous said...

Please all concerned Ethiopian, let us post directly to his Blog so that he can know Ethiopia has children . Although we know our country is guarded bye our GOD. For me his article shows the extreme disrespect of the Ethiopian People.

Anonymous said...

Of course, Protestants are enemies of our religion. I always wonder why they target EOTC christians while there are millions who don't believe in Christ in many parts of the world. The answer is whoever tries to takeover or dilute another Church establised by Christ must be from the devil; I am sure the Holy Spirit or Christ would not send them to destroy His own Church.

However, that being said, MK would be making a big mistake if it interpretes the criticism it is getting from various angles (most importantly the ones coming from genuine Tewahedo followers) as an attack becuase of its mission of protecting the church from being adulterated. THAT IS BIG MISTAKE #1. I agree there could be some enemies of the church who may target MK because of their hate against the curhch. Nevertheless, for MK to say that all attacks/criticisms against it are coming from haters of the church or their internal symphatisers is completely wrong. By the way, does MK think it is immune from sins or errors like the Pope of Rome?

Oh com'on, MK needs to genuinely evaluate itself and accept genuine criticisms or even attacks and improve on its weaknesses while building on its strengths. As any association of humanbeings, MK has made mistakes as we all do. What is bad is not making mistakes, but covering it up or accumulating it while some folks point them out or blaming critics for doing that. My advice to MK is to: (1) first understand that you are just one of the groups who stand to defend the church - know that there are many others who do the same thing that you are claiming to be doing; (2) partner with the other groups that care for the church instead of creating animosity and spreading accusation; (3) fight the true enemies of the church together with your other brothers and sisters; (3) avoid any hegemonic tendencies you or your members may have; and (4) work with the leadership of the church to correct the various errors and glaring mistakes in the various writings (gedeloch, and other awalid books)of the church that are against the core teachings of Christ and have inflamed the criticisms against our chirch. You may bluntly say there is no mistake in any of the awalid books or yetselot mesehafs. However, I can give millions of examples, but it is suffice to mention that Copts wrote in the SinkSar that God punished Ethiopians with thunderstorm for asking to have their own bishops. Surprisingly, the church is carrying this writing to this date as a holy word. Another is that there is rampant writings that suggest that one can have salvation through the intercession of the saints even if one denies the Holy Trinity or Christ. Example, the guy you always preach to have gotten salvation through the intercession of the saints despite the fact that he renounced the Holy Trinity. This is a completely bad and worthless teaching and is against the Bible. What kind of message is being transmitted to believers? Do whatever you want and believe in the saints and you have guaranteed salvation. I want you to know that I firmly believe in intercession of the Saints, particulalry that of St. Mary, but I don't believe in any writing of the sort mentioned above. Don't you think it is now time to revisit all the sinksars and awalids and teach the true teachings of the Appostels and St. TekleHaimanot, inluding the other true Tewahedo fathers? I hope you would agree with me. Otherwise, I admire some of the good works that MK has done.
God bless you all!

Anonymous said...

Theologians and mhaberkidusan please work together all over the world
Addisu, what you raised is a great issue of the church in general and the college in particular.
I would like to say few things from my observation in the trinity college concerning mhaberkidusan.
I know that some mahaberkidusan members don’t have a good knowledge how to serve in association with theologians (those assigned by the Holy Synod) but blaming them. The leaders of mhaberkidusan always articulate that this is not their aim and they are ready to correct any fault done by their members in different areas.
Concerning the relationship between mhaberkidusan and the college I observed and came to understood one big problem clearly.
Currently many members of mhaberakidusan are learning in the regular as well as in the extension programs of the college which is good. Some individuals and groups are not content of this proximity. If these energetic youth group starting to work together many changes will come to the church. Many foreigners as Addisu mentioned don’t like this closeness.
One day, in the month of October/2010 I was chatting in front of the college with two of my college friends. Two foreigners came into to the college by no 5 car and no one was asking them. We all were starting to saw them. They in a straight line went to jossi’s home which I came to knew later. Then two students also entered in to the same place. It seems they had an appointment. Finally I asked the reason but we didn’t know at that time. My friends told me on the other day about the condition.
Jossi (an Indian teacher in the college) has a good relationship with these foreigners and they are coming to his home once or twice a week. His duty is identifying the members of mhaberkidusan in the college from all students and workers. For this purpose he chose two students from day and two from extension. These students, always telling the information to jossi and jossi to the protestant foreigners. Many students know that these foreigners are coming always and entering to his home. In addition to this, jossi has information that who is politician, who is from which race…etc. At present, he is a controversial person in the college.
I found that this is unsafe and at the back of this there is anti orthodox movement.
But I propose that both theologians and mhaberkidusan please work together all over the world. Discuss and solve many troubles of the church. This is your time which God gave you and you mightn’t get this time again who knows!

God Bless our church

mebrud said...

New MK Generation.

አባባልህን ወድጄዋለሁ፡፡

.....This is the time for revival of our church any one who is ready for journey to Jerusalem in the sky all the doors of the cart are open were your life vest and join us
O death, where is thy sting? ...............

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ

መላኩ said...

ተባረክ ወንድማችን፡ በደንብ የታዘብከውን በጥሩ መልክ ስላቀረብክልን፡ ልተመሰግን ይገባሃል።

በእኛ ትውልድ አንድ በጣም አሳፋሪ የሆነ ክስተት ቢኖር ወንዱም ሴቱም ለፈረንጅ አጎብዳጅ እየሆነ መምጣቱ ነው። ጥሩ የሆኑ ፈረንጆች መኖራቸውን ብናውቅም፡ ግን ኢትዮጵያን ከመሰሉ አገሮች ጋር በቅርብ ተጠግተው ሊገናኙ የሚፈልጉት ፈረንጆች ጠላቶቻችንና የኛን በጎ ነገር የማይመኙት ናቸው። በተለይ ታሪካችንን፡ ተዋህዶ ኃይማኖታችንን እንዲሁም ባህላችንን ለመለወጥ በከፍተኛ ወኔ ተነሳስተው በውስጣችን ሰርገው የገቡት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። የኛ ኃላፊነት በተለይ ሕጻናትንና ባጠቃላይ የትምህርት ተቋሞችን ነቃ ብለን መቆጣጠሩ ላይ ነው። እነዚህ በኃይማኖት ስም ወዳገራችን በመግባት ላይ የሚገኙት "በጎ አድራጊዎች" አገሮቻቸውን ወደ መንፈሣዊ ምድር በዳነት ለመለወጥ የበቁ መሆናቸውን፡ ወደኛም ብቅ የሚሉት መንፈሣችንን ለመንጠቅ መሆኑን ሳንፈራ ሳናመነታ በግልጽ ልንናገር ይገባናል።

በሌላ በኩል፡ ኢትዮጵያዊ በሆኑ የመገናኛ ማዕከሎች፡ እንደ ደጀ ሰላም ባሉት ብሎጎች እና በመሳሰሉት ሃሳቦቻችንን በራሳችን ቋንቋና ጽሑፍ የማቅረብ ግዴታ ይኖርብናል እና አሁንም ይታሰብበት እላለሁ። ብዙዎች የብሎጉ ተሳታፊዎች በአማርኛ ሲጽፉ በማየቴ ደስ ብሎኛል ቀጥሉበት እላለሁ።

ይቅርታ በችኮላ ላይ ሆኜ ስለጻፍኩ...

ቸሩ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን

Anonymous said...

ወንድሜ ቲኦሎጂያንና ማሕበረ ቅዱሳን አንድ ሁኑ ያልኸው/ያልሽው ቁርጥና ያለና የመጨረሻው አዋጪ ሐሳብ ነው።
እኔ የማሕበሩ አባል ስሆን የማታ ተማሪ ነኝ። ቲኦሎጂያንን ከምተቹ የነበሩ አንዱ ነኝ። በርግጥ አሁንም ከ100% በጣም ጥቂቶች የተማሩትን በተግባር የማያውሉት ሲገቡ ጀምረው ዱርየነታቸውን ሳያላቅቁ የገቡ እንዳሉ ታዝቢያለሁ። ነገርግን ከፍተኛው ችግር በኛ በማሕበሩ ተደራጅተን በምናገልግል ሰዎች ተቆልሎ እንዳለ አውቀዋለሁ።በተለይ አንዳዶቻችን ምንም ሳናውቅ የማሕበሩ አባላት ብቻ በመሆናችን እየተኩራራን አባቶችንና ወንድሞችን በማቃለል ብቻ የምንውል አለን።ይህ የምናደርግ ወገኖች ፈጽመን ተሳስተናል።የማሕበራችን ጥሩ ምስልና ጠንካራ አገልግሎት በኛ ስም መነቀፍ የለበትም። ከፈለጋችሁ በማዶ ሆኖ የመናፍቅ ትምህርት እያልን ከምናጥላላ ገብተን ብንማር የበለጠ ለውጥ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ። ተመርቀው ከአራት ኪሎ በማይወጡ ጥቂቶች ያልኳቸውን ዱሪዬዎችን አንመልከት ከስንዴ እንክርዳድ አይታጣምና። እኔ በአሁን ጊዜ ተመልሼ ራሴን የሚያይበት ሰዓት ውስጥ ነኝ ያለሁት። በቲኦሎጂው ሚዛን ስመዘን እዚህ ግባ የማልባል ሰው ነኝ።
እንዲያም ከተቻለ የተማሩትን በእውቀታቸው ያልተማርንም በገንዘባችንና በጉልበታችን አንድ ሆነን ብናገለግል አንድም ጠላት ከመሐል ገብቶ የሚበጠብጥ አይኖርም፤ ጠላቶች ውስጣችንን ከታዘቡ በሗላ የዘመቻ ፍንጭ ማሳየት ብቻ ሳይሆን በግልጽ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያተለለችን ይበቃታል፤ ጊዜው የኛ ነው፤ ወጊድ እንበላቸው …” ሌሎች በዚህ ብሎግ ለማውጣት ዘግናኝ የሆኑኝ ሓሳቦችን ባልተማረው ምላሱ ሲነቅፍ በዓለም አደባባይ ወጥቶ ማግሳት ጀምረዋል። ከፈለጋችሁት ጎግል ገብታችሁ ፓሰተር ዳዊት ሞላልኝ ብላችሁ ክሊክ አድርጉና ከፓርት ዋን እስከ ፓርት ሰቨን እዩት።
በመጨረሻም እርስበርስ የምንተራረምበት በሁሉም አቅጣጫ መድረኮችን እንፍጠር ከዛ በሗላ ሀገራችን ማጽዳት እንጀምር ባይ ነኝ። ይህ በእግዚአብሔር ሐይል፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ምልጃ፣ በጻድቃንና ሰማእታት ጸሎት፣ በኛ በር ሳንከፍት ያለንን ደካማ ጎን በየጊዜው እየተራረምን አንድ ሆነን ጠላት እንደ ፈርኦን በቀይ ባሕር ማስመጥ እንችላለን።
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ይሁን!

Kiduse wwek MS said...

እባካችሁ በየዋህነት ተሐድሶ የሚባል የለም ፣ ተሐድሶና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም ልዩነት የለውም የምትሉ ሁሉ በቂ መረጃ ለማግኘት

ሐመረ ተዋህዶ ቁጥር 3 ን አንብቡ፡፡ በቂ መረጃ ታገኛላችሁ፡፡

አውቀው የተኙት ግን ቢቀሰቅሷቸውም አይሰሙ፡፡

H/meskel (Dr) said...

'... bizuhan yimets'u besimye.... bizuwoch besime yimetaluna....', this is what our lord told us in the bible,why we then frustrate? it is true that lost are saying we are of crist, we preach crist... all confusing if you see them via your naked eye; please wear the glass of faith to correctly learn who is the real... our lord jesus crist in the has told us that ' ...kefreyachew tawkuachewalachhu...' just see what is thier output.

let me depect it the chain of the output tewahido ___via tehadso will be changed to____ catholic/ then to ______ protestantism will end up with_______ No God _____will finaly say_ Saitanism. so this is the chain that devil has prepared to detach cristians to his kingdom. this is not theeory, you can just see the real world today. please don't be the path for devil. take your hands back.
Deje selam try fighting this path
MK please work day and night to tackle this path
God fathers be awre of what the devil is doing on us

Anonymous said...

tiru hasb ansitachuhal

ebakachu theologian ena mhabrakidusan tababru gena bizu tisaralachu.ygara talatachun ewaqu liki kzim kazam hono ymiyatalu (enda jossi) yalutin masafar albachu!

lzhim amlak yirdan egnam entsalyi

Unknown said...

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእናት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ እየታዩ ያሉትን ስር የሰደዱ ችግሮች እና የችግሮች መገለጫዎችን ከተሀድሶ እንቅስቃሴ ጋር ስናቆራኝ ቆይቶም ከአህዛብ (መሀመዳውያን) መስፋፋት ጋር ስናይይዝ ሰንብተናል፡፡ አሁን ደግሞ ስለመናፍቃን ሴራ እያወራን እንገኛለን፣ ይህ ሴራ ቢኖርም ባይኖርም የቤተክርስቲያናችን መሰረታዊ ችግር ግን ከመናፍቃኑ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ በቅርቡ መምህር ምህረተአብ ‹‹ፕሮቴስታናዊ ጅሀድ. . .›› በሚል ርዕስ ያቀናበረውን የስብከት ምላሽ ተመልክቼ ነበር ፤በሰአቱ የፓስተር ዳዊት ሞላ ዘለፋ አበሳጭቶኝ ነበር፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ሰውየው የተናገረው ዘለፋ ትክክል ባይሆናም ሙሉ ስብከቱን ለመስማት ወሰንኩ፡፡ ሙሉ ስብከቱን ከተመለከት በኋላ ግን ንዴቴ በርዶልኛል፡፡ ምክንያቱም የፓስተር ዳዊት ሞላ ስብከት ለአላማ ተቆራርጦና ፀብን ለማነሳሳት በሚያስችል ርዕስ ታጅቦ መቅረቡን አስተዋልኩ፡፡ ፓስተሩ የተናገረው ተንኳሽ ዘለፋ ትክክል ባይሆንም፣ የመምህር ምህረተአብ ምላሽ ግን የመምህሩን ብሉይና ሐዲስ አዋቂነት ጥያቄውስጥ የሚከት ብሎም ቤተክርስቲያናችን የውጪን ትችት በአግባቡ ሊመክት የሚችል መምህር የላትም እንዴ የሚያሰኝ ነው፡፡ እነ ዲያቆን ዳንእል ክብረት ፣የት ገቡ ያሳስባል፡፡ ብቻ ሁላችሁም የፓስተር ዳዊት ሞላን ስብከት እንድትመለከቱት አደራ እላለሁ ፡፡ ልዑል እግዚአብሄር ብተክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡

lemma kefyalew said...

indet nachihu dejeselam? be bete kristiyanachin lay iyetederege yalew ye mades zemecha le igna bemasawoku zuriya iyaderegachuhu yalew inkisikase betam yasdesital .igna hizbe kristiyanoch degmo bebete kiristiyanachin lay iyetederege yalewun iske machee new zim bilen yeminayew? ibakachihu yeakmachinin inisra!!!

ጆሮ ያለው ይስማ said...

What's Computer Teacher Got to Do With God?

Please go to the following link and see it for yourself. Which Careers they are hiring for and for what purpose.


http://webtest.sim.org/frontend_dev.php/opportunity/countries


Computer Teacher/Coordinator, Mekelle Youth Center

Career: Community Education
Country: Ethiopia
Length of Service: More than 2 years
Priority: Urgent
PRF Number: 7894
Do you have a passion to build relationships with young people and encourage them in their walk with God? Are you a team player with computer skills and experience? Do you love to learn about new cultures and relate to others in a culturally sensitive way? If so, the Mekelle Youth Center is just the place for you!

The Mekelle Youth Center gives impoverished youth hope and opportunity through computer training, sports and recreation opportunites, HIV/AIDS education, English teaching, and many other practical and life-affirming skills in a loving and positive environment.

But most importantly, by God's grace, we are working to develop relationships which impact lives in a most significant and lasting way. Come and see how you can have a dynamic impact on hundreds of youth and be a part of what God is doing here in Mekelle!

Anonymous said...

ዘወር አሉ እንጂ አልሸሹም አሉ....አንተስ አሁን የሚጠቀስ የአብነት መምህር አጥተህ ነው ? ዳንኤልን የጠቀስከው ? አላዋቂ ነው ማለቴ አይደለም ነገር ግን..ጉባኤ ዘርግተው.መናፍቃንን ረትተው..ተዋህዶ ሐይማኖትን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ብዙ አባቶች መምህራን አሉ..ምን ነበረበት ከነዚያ አንዱን ብትጠቅስ.
በርግጥ ላታውቃቸው ትችላለህና አልፈርድብህም

Anonymous said...

እኔ የገረመኝ በዚሁ ብሎግ ወደ 53 የምናህል ሰዎች አስተያየት ሰጥተናል። በጠላታችን (ዊልያም ብላክ) ብሎግ እስካሁን ድረስ 17 አስተያየቶች ተጽፈዋል ከ 17ቱ 13ቱን የኛ ወገን የጻፋቸው ሲሆኑ 4ቱን የኔ ናቸው አንዴ መቀሌ አንዴ ትግራይ ወዘተ እያልኩ (በእርግጥም መቀሌ ነኝ) የተቻለኝን ያህል መዋጋት ጀምሬያለሁ። ለምን ግን ሁላችን ከታቻለ ብዙ ካልተቻለ አንዳንድ የቃላት ጥፊ አናስቀምሰውም? አንዲት ቃል/ልሳን/ አጥንት የምትሰብር መሆኗን’ኮ ቅዱስ መጽሐፋችን ነግሮናል፤ ደግሞ ተከታዮቹን እንኳን እጃችን ሰንዝረንባቸው በድምጻችን ብቻ ምን ያህል እንደሚበረግጉ እናውቃቸዋለን። እሱ በውሸት አልቃይዳ ሲሆንብን እኛ እውነቱን ለመንገር ቢያንስ አንድ ሐዋርያ መሆን ያቅተናል’ንዴ? ወጊድ ወዲያ በል ፈሳም ሉተር እንበለው!
ስለዚህ ወንድሞቼ! የተቻላችሁን ያህል ዮዲት ጉዲት በሆነውን ዊልያም ብላክ መቃብር የስንብት ድንጋይ ለመወርወር ሁላችሁም ቃል ግቡልኝ ይህም የትግል አንዱ መንገድ ነውና።
ዛሬ ጀምሩ!
ትግራዋይ

William Black said...

Dear Ato Deje Selam

It would seem that you have written a provocative post on some aspect of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and the interaction of Western missionaries with it. You have made use of several quotes from my own provocative post, ‘The Struggle for the Soul of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church’. I am glad that you have found my post helpful in making whatever argument you made. However, my Amharic is such that I cannot follow a sustained article. Because I would like to know exactly what you said and how you have made use of my work, would you kindly provide an English translation for me?

Whatever you have said, it has generated a lot of traffic over to my blog, Onesimus Online. I am always glad to have new people read and interact with me over my ideas. However, I must inform you that much of the interaction with people coming from your site has been sadly disappointing. Not that I have a problem with people disagreeing with me on this or that issue. Rather, most of those who have left comments on my blog have been exceedingly unkind in the things they have said to me and about me: name-calling, abusive speech, slander, as well as twisting my words and taking them out of context.

Having lived in Ethiopia and having many Orthodox friends, I know how passionate they can be. I also know how kind, generous and respectful they are as well, especially to outsiders. So I must say I am shocked to be so badly treated by people who don’t even know me. This is so unlike the Ethiopians who were my friends and neighbors for so many years. Which makes me wonder if they, for some reason, have misunderstood what I have said. In the article, I am simply being a reporter, attempting to help interested people understand some of the dynamics that are actually going on, both on the EOTC side and on the Protestant side. It puzzles me why such an attempt would provoke such unkindness; I would have thought either thoughtful questions, or attempts to better instruct me if I am wrong. But most disappointing to me is to be so treated by people who claim to be defending their church. I myself am an Orthodox Christian (I have converted this year). These people don’t seem to realize that I really am their friend.

There is nothing you can do about this. But I thought you would like to know.

Have a blessed Nativity fast.

ዘብሔረ ቡልጋ፤ said...

ደጀ-ሰላምዋያንና ወገኖች በሙሉ የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛላችሁ። አሜን!!
እኛ ዋና ማድረግ የሚገባን ነገር ቢኖር በቤተ ክርስትያናችን ውስጥ ያለብንን ችግር በተሐድሶዎችና በጴንጤዎች ላይ ከምናላክክ
በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ መመርመር ነው። የሄ ሁሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወደሌላ እምነት የሚኮበልለው ሐገሩን ጠልቶ፤ የእናት አባቱን ተጸይፎ ወይንም በባእዳን ተንኮል ተታሎ ሳይሆን፤ በኦርቶዶክስ ውስጥ የሚደረገው መሰረታዊው እምነትና አምልኮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጣም ስለሚጋጭበት ነው። ስለዚህ በድፍረት ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑትን፤ ከራሳችን፤ ከባህላችንም ሆነ ከግብጽና ሶሪያ የመጡትን አፈታሪኮችንና ተረቶችን ነቅሰን ማውጣት ነው። ያን ጊዜ የኮበለለው ሁሉ ይመለሳል። ያለውም በፈተና ሁሉ ይጸናል።
"እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ህዝብ ምስጉን ነው።' መዝ 144;15
እግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ። አሜን!

tewodros said...

Well that is good news. So what is to be done? Do u remember the first puzzles the davel brought to Lord Jesus? Two out of three is related to money. Coming to my point, one with Theology degree, of five years in school, his salary is not greater than 600birr /per month. Can u believe it? This money is nothing in current market of Ethiopia. My salary is more than four thousand still not enough for me. Don't tell people are living by 200 birr per month. This is insult and not acknowledging their problems.
Conclusion
1,The church must use her resourses effectively.
2, The church must pay theologians the salary they deserve. So that they can say no to reformists.

Anonymous said...

Realy,I have observed what D/n H/micheal said. So the church membere should follow and tell us such information what is going on in each Church, please ... Now I tell you Dejeselamaweyan, I have also seen similar things in Gedame Eyesuse in this week dec. 15/2010.

Anonymous said...

ለአቶ/ለወሮ Lula እውነት የቤ/ን ልጅ ቢሆኑ ተሃድሶ እና ፕሮቲስታንት የቤ/ን ዋነኛ ጠላት እንደሆኑ አይጠፋዎትም ነበር።ከመናፍቃን ሴራ ሌላ ስለነማን እንድናወራ ፈልገው ነበር።"ሙሉ ስብከቱን ከተመለከት በኋላ ግን ንዴቴ በርዶልኛል" ቤ/ን ስትሰደብ ንዴቱ የሚበርድለት የቤ/ን ጠላት ሰይጣን ብቻ ነው።ምነው የቤ/ን ልጅ አይደሉም እንዴ!!!!! መምህር ምህረተአብን ከመተቸት ፓስተር ዳዊት ሞላን መገሰፅ አይቀልም ነበር።"የፓስተር ዳዊት ሞላን ስብከት እንድትመለከቱት አደራ እላለሁ" ምነው አደራዎ የመምህር ምህረተአብን ስብከት እንመለከት ቢሆን። ድንቄም የቤ/ን ልጅ እና ተቆርቆሪ።
Brile

H/meskel (Dr.) said...

To the last commentor,

R u really jocking? leavealon 600 birr, had it been 6 birr do you mind that having been tought for 5 years will let people to be enemies of thier religion. what is your opinion about those fathers who studied thier perfect, and onto God education at ye 'abnet t/bet' for morethan 20 to 30 years and are being paid 60 birr? was it to get money that these people get to the College, if so please let them stop it today as they may sell the church for the one who comes to give them a million birr like Juda who sold his creater for 30 birr. please you have basic understanding problem. if peoples are in need of money, they should join Universities and other secular ciolleges; my expectation was the College could harbour more educated spritual peopes but as you said.... really devastating.

Unknown said...

We have talked alot about the tehadisos and protestants and muslims. It is good to talk about all of them because they are in one or other way enemies of the orthodox church.

But let us see on thing also. The weakness of our church.I agree with ዘብሔረ ቡልጋ. As I said repeatedly here in Dejeselam, we have also our problem. It is not dogmatic but there are cultural things that are associated with the church which are wrong. We should avoid them.

For us to defend our church 100% let our church remove some of its problems. If you guys are really working for strong Orthodox Church we have to do the following.

1. Let the Synod be strong and decide by its own.
2. The synod should revise the church's teachings avoid many unorthodoxy /wrong beliefs and practices
3. Let us not interfere the Synods Work.
4. Let us know our church more and read our books rather than forming groups
5. Let us avoid division among us and concentrate on the church's problem.
6. Our enemies are many so let us not split ourselves and be enemies each other.

May God Bless Orthodoxy Forever!

Dillu said...

ሰላም ለኩልክሙ
የኣንዳንዶቻችሁ ኣስተያየት ከክርስትና እምነት ጠባቂዎች ወይም ተቆርቋሪወች ከሚሰጥ የእርማት ትምህርት ይልቅ ከፖለቲካ ተቀናቃኞች የሚሰጥ እሰጥ ኣገባ ያውም የሰለጠነው ዓለም የሚያደርገው ሳይሆን (Ethiopian style debate)ይመስላል። ለዚህም ነው ኣንዳንዶቻችን እውነተኛ ማንነታችሁን ለማውቅ እስካሁን እየተቸገርን ያለነው።
ክርስቶስ ከሞቱ፣ ከትንሣአኤውና እርገቱ በሁዋላ ኣሁንም 'ኣማላጅ ነው' የሚሉ ጴንጤዎች እንጂ የኦርቶዶክስ ኣማኞች የሉም። ካሉም እንዲመለሱ ተመክረው የማይመለሱ ከሆነ ከቤተክርስቲያን ተወግዘው መለየት ኣለባቸው። ምክንያቱም ቃለ ኣብ እግዚኣብሔር ወልድ በመለኮት (በኣገዛዝ)ከኣብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ኣይደለም ማለት ስለሆነ።
ስለዚህ እናንተ ማድረግ ያለባችሁ ተሐድሶዎች የምትሏቸው ሰዎች የሚያስተምሩትን የክህደት ትምህርት ክህደት ወይም የመናፍቃን ትምህርት መሆኑን በመረጃ እያስደገፋችሁ ብታቀርቡ ይሻላል እንጅ እንዲያው እናንተን ባቀራረብ ስልታችሁ ድክመት ምክንያት የሚተቻችሁን ሁሉ መናፍቅ-ተሐድሶ የምትሉት ከሆነ ከግንባታችሁ ኣፍራሽነታችሁ እየጎላ እንዳይመጣ እሰጋለሁ።
ለሁሉም እግዚኣብሔር ለሁላችን ጥበቡን ይግለጽልን፡ ዓሜን።

Anonymous said...

lula---ምንስ ቢሆን ከፓስተር ዳዊት ሞላ ስብከት> የዲያቆን ምህረተ አብ ስብከት.አይሻልም ብለሽ ነው የፓስተሩን ስብከት እንድናዳምጥ የጋበዝሽን ? የኑፋቄውን መጠንና አይነት ለማሳወቅ ብለሽ ከሆነ ቀደም ብለን አዉቀነዋል።ደግሞም ምንጊዜም ከፓስተሩ..እምነትና ጽድቅ ይገኛል ተብሎ አይጠበቅም
ነገር ግን እባካችሁ እርስ በእርሳችን እንመካከር እንጂ አንነካከስ
እንተራረም እንጂ አንነቃቀፍ አንድ እንሁን እንጂ አንሳሳብ የቀደሙት ክርስቲያኖች አንድ ልብ አንዲት ነፍስ ነበራቸው
ሕዝብና አህዛብን አንድ ያደረገ አምላካችን -በሐይማኖት በባህል በቁአንቃ በአንዋዋር አንድ የሆነው እኛ የግላችንን ፍላጎት ለማሳካት እጅግ በጣም ተለያይተናልና በቸርነቱ ሰብስቦ በስጋ ግብር የሚመጣውን የራስ ወዳድነትና የ እኔ አዋቂ ነኝ ባይነት መንፈስ በሃይለ መስቀሉ ደምስሦ አጥፍቶ አንድ ያድርገን

Anonymous said...

Besme Abe Wowold Wmenfes Qedus and amlak amen,
Dear ortodoxawyan acording to mr Willyam words on his blog we understood, that he and his principle followers plans to demolish the faithes of the EOTC by diffrent western faithes and we need our fathers to stop this bad situation to save us all.
Fiker yesten.

Anonymous said...

Adisu betam enamesegnalen kale hiwot yasemalen.hulachinim tebabren enenesa haile new yemiyasifelegew zim sibalu yaltaweke eyemeselachew new

Anonymous said...

ene yemiferaw endezih yemiyadersilinin web site (dejeselamin) endayatefubin esegalehu

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

ወገኖቼ ምነው ዝም አላችሁ? በተለይ ሰው ተገቢ አስተያየት ሲሰጥ ያልተገባ አስተያየት በመስጠት ሰውን የምትተቹ ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉ አስተያየት ሰጪ እኛን መስለው የሰጡትን አስተያየት አላየታችሁትም? ካላያችሁት እንዲህ ይላል “የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወደ ሌላ እምነት የሚኮበልለው በኦርቶዶክስ ውስጥ የሚደረገው መሰረታዊው እምነትና አምልኮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጣም ስለሚጋጭበት ነው።ስለዚህ በድፍረት ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑትን አፈታሪኮችንና ተረቶችን ነቅሰን ማውጣት ነው።” ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉት ጠባብና ጭፍን አስተያየት ሰጪ እንዳሉት ሳይሆን የኛ ሐይማኖት መሠረቷ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ የሆነች፣ተረትና አፈታሪክ የሌለባት፣በየአዳራሹ እንደሚታየው ድራማን እውነት አስመስላ የማታቀርብ፣ በአባቶቻችን ተከብራ የኖረች ጠላት ሁሉ ሊያጠፋት ቢታትር መቼም የማያጠፋትና ዘላለም የምትኖር ውድ እምነታችን ነች። ተዋሕዶ ንጽሒትን ለየት የሚያደርጋት ደግሞ ሐያላን ሀገራት የሰሎሞንን ሚስጥርና ጥበብን ለማወቅ ዘወትር የሚደክሙበትን የግዕእ ቋንቋ ተጠቃሚ መሆኗ ነው። ታዲያ ሌላ ጊዜ መልስ ለመስጠት የምትቸኩሉና አቅም አለን የምትሉ እኛ በመሐይም አቅማችን ስንፍጨረጨር ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉ መናፍቅ መሐላችን ጥልቅ ብለው ሐየማኖታችንን በዚህ ብሎግ ሲያቃልሉ ምነው ተኛችሁ? በዚህ አጋጣሚ Brile /ብርሌ/ የተባሉትን ተሳታፊ ንቃት እጅግ አደንቃለሁ። Lula /ሉላ/ የተባሉ ኦርቶዶክሳዊ መሳይ በብለሐት ሰው መ/ር ምህረተአብን ችላ በማለት ፓስተር ዳዊት ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲከታተል መክረዋል። ይህንን ግልጽ ንፏቄ ከተረዱት ሰዎች አንዱ ታዲያ Brile /ብርሌ/ ስለሆኑና ተገቢ መልስ ስለሰጡ ላደንቃቸውና ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። ሌሎቻችን ደግሞ ሐይማኖታችንን እንወዳለን የምንል ብንኖር መልስ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ዋነኞቹ አጠገባችን ሆነው ሰውን ለማሳትና እኛን ኦርቶዶክሳውያንን መስለው በየብሎጉ የሚፅፉትን መናፍቃን ልንነቃባቸውና አጓጉል ዘለፋ ያልተቀላቀለበት ተገቢውን ምላሽ መስጠት በጣም ይጠበቅብናል።ቸሩ ፈጣሪያችን ሳንነካቸው የሚነኩንን ፈጥኖ ይጣላቸው። አሜን!!
መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

ዘብሄረ ቡልጋ said...

ውድ ደጀሰላማውያን፤ ከሁሉ አስቀድሞ አስተያየቴን ሳትቆነጻጽሉ ለውይይት በማቅረባችሁ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። በጨዋነትና በመረዳዳት መንፈስ ለመወያየት ያላችሁንም የከበረ አቋም ለማወቅ አስችሎኛል።
አዎ፤ በርግጥ እኔ በአሁኑ ጊዜ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አይደለሁም። "ከኦርቶዶክስ እምነት ውጭ ያለሰው በዚህ ጡመራ የበኩሉን አስተያየት ሊሰጥ አይችልም።"የሚል አቋም ካላችሁም፤ እያዘንኩ አስተያየት መስጠቴን አቆማለሁ። እኔ በእናንተ ጡመራ ውስጥ ገብቼ ልበጠብጥ ሳይሆን በእውነት እኔና ብዙ መሰሎቼ ከኦርቶዶክስ እምነት የወጣንበት ምክንያትና ያሉብንን መንፈሳዊ ጥያቄ በአግባቡ የመለሰልን ሰው ባለመገኘቱ መሆኑን አብክሮ ለማሳወቅ ብቻ ነው።(መናፍቅ ብሎ በጅምላ ከመኮነን በስተቀር።)
ነገሩ ተድበስብሶ ወይም በጅምላ እየተወገዘ ብቻ ይቅር ከተባለም ያው አሁን በየቀኑ የምናየው ትእይንት ይቀጥላል። የብዙዎቻችንም የመኮብለል ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊና መሰረታዊ ጥያቄ እንጂ በውጪ ሐገር ሰዎች ተጽእኖ ወይም የናት አባት ጥላቻ፤ የሐገር ንቀትና የመሳሰሉት እየተባለ መቅረቡ መፍትሔ አያመጣም። እኔ አሁን ባለሁበት ቤተእምነትም ውስጥም ምንም እንኳን በመሰረታዊው እምነት ብስማማም፤ በልሳን አጠቃቀም፤ በፈውስ፤ በትንቢት አገልግሎትና በመሳሰሉትም ጥያቄ አለኝ። ጥያቄዎቼንም በግልጽ ከማቅረብ ሌላ የሚሰሩትን ታላላቅ ስህተቶች በጭፍን ሸፋፍኜና አድበስብሼ ለማልፍ አልፈልግም። እውነቱን መመዘኛ የእግዚብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አለልን። እኔ ወገናዊነቴ ለእግዚአብሔር ቃል እንጂ ለሐይማኖት ድርጅት እንዲሆን አልፈልግምና። በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን ከማድበስበስ፤ ጠያቂዎችንንም በጭፍንና በጅምላ "መናፍቅ" እያሉ ከማውገዝ "ለምን?" ብሎ በአንክሮ መጠየቅ ይበጃል።
እኔ በእውነት ያሉብኝ መሰረታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነትና የአምልኮ ጥያቄዎች በአንክሮ ቢመለሱልኝ ወደቀደመው ቤተክርስትያኔ የማልመለስበት ምክንያት የለም። ተወልጄ ያደኩት ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ት/ቤት ውስጥ ሲሆን፤ እቲሳ ተክለሃይማኖትንም በጣም እወደዋለሁ። በየቀኑም ይናፍቀኛል። ሐገሬን፤ ማንነቴን...እጅግ እወዳለሁ። ነገር ግን ክርስትና ከሐገር፤ ከቋንቋ፤ ከትውልድ፤ ከዘርና ከሐይማኖትም በላይ ነው።
በመሆኑም ለእኔ ምንም ነገር ከጌታዬ፤ ከአምላኬና ከንጉሴ ከኢየሱስ ክርስቶስ እንዲበልጥብኝ አልፈልግም።
ለእናንተም በቅንነት የምመኘው ይህንኑ ነው።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ሕዝቧን ይባርክ።
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይባርክ!
አሜን ወአሜን!

Anonymous said...

ወንድሜ ዘብሔረ ቡልጋ ፣ ተጋጩብኝ ያልካቸውን እስኪ በዝርዝር አስቀምጥልን። ለጥያቄዎችህ መልስ ለመስጠት ፍጹም ዝግጁ ነኝ
ትግራይ

Anonymous said...

“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን፤”(ገላትያ1-8)

ብዙዎች የዋሃን እንደሚያስቡት የProtestantism(የTehadsso) ተልህኮ ስለጌታ እናት፤ ሰለመላእክት ፤ ስለቅዱሳን ወይም ስለ ቤተክርስቲያን እውነተኛዊቷ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ማስተው ብቻ ሳይሆን። ዋነውና ትልቁ ተልህኮ ሃዋሪያት ከሰበኩት ወንጌል የሚለይ ወንጌልን መስበክ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ማንነትና ስራ ላይ የሚቃረን ትምህርት ምስተማር ነው። ከአባቱ ጋር በክብር እኩል የሆነውን ጌታን ከክብሩ በማሳነስ በዚህ ዘመንም ስለእኛ እንደሚማልድ(እንደሚጸልይ) ማስተማር ታላቅ የስህተት ትምህርት መሆኑ መታወቅ አለበት። ሃዋርያት እንዳስተማሩን በአካል የማስታረቁን ስራ አንድ ጊዜ መበስቀል ለይ ፈጽሟል። ዕብራውያን 7-27 “እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።”
2ኛ ቆሮ 5-16 “..ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።...እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።
ስለመንፈስ ቅዱስ የሐዋ 2፤4-10 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር... እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ...” እንግዲህ አንዱከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የወነው ልሳን(የሚታወቅ የሰው ልጅ ቋንቋ ነው)፤ Protestant(Tehadsso) መንፈስ የሞላ ብለው የሚያሱን ግን ምን እንደወነ የማይታወቅ የድምጽ ጋጋታ ነው። ይህንንም ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ልሳን አድርጎ ማስተማር መንፈስ ቅዱስን መሳደብ
ወገኔ ዘብሄረ ቡልጋ ፡ ለእኔ ጌታዬን እየሱስን የከፍለልኝ ዋጋ ይበቃዋል፡ አሁን ጌታን በፊት በስጋ ወራት እንደምቀው አይደለም። አሁን እኛ ወደድንም ጠላንም በክብሩ ነው ያለው በእኛም(በቅዱስኑም) የማስታረቅ ቃል አኑሮአልና። ይህ እውነት ስለወነ ነው እንጅ፤- ስለዘር፤ ስለቤተሰብ፤ ወይም ስለአገር አይደለም።
የእግዚሃብሄር ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን።

ጆሮ ያለው ይስማ said...

Deje Selam, considering William Black smart-aleck, I think you shouldn't post his sarcastic remarks on your blog. Here most people whether they are pro or con at least they seems genuine. It is easy to see how he is full of himself. Please see how he is playing dummy just from the start of his phony comment by saying, "Dear Ato Deje Selam".
By the way If it is not for his heart, It would have been a blessing for him to live in our beloved holy land, ETHIOPIA. Leaving his destructive mission aside, in a personal level here is the first golden rule if it means any thing to him.

"Don't do unto others what others you don't want to do unto you"

Anonymous said...

ቡልጋ ለክህደትህ ምክንያት ነው። የምትለውን ነገር ። ብትነግረን መልካም ነው

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

ወንድማችን ዘብሔረ ቡልጋ ማንነትህን አለመካድህ መልካም ነው። ነገር ግን ብትክድም አውቀንሃል ደግሞ የልብን ከተናገሩ በኃላ መለሳለስ አድኖ መግደል ይባላል። በእውነት ወደ ቀድሞ እምነትህ የመመለስ ፍላጎት ቢኖርህ ኖሮና እንዲመለስልህ የምትፈልገው ጥያቄ ቢኖርህ ኖሮ የኦርቶዶክስ እምነት ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል፣ ተረትና አፈ-ታሪክ ነው ብለህ በድፍረት ባላቃለልክ ነበር። አሁንም እኔ በኮልታፋ አንደበቴ ስለ ውድ ሐይማኖታችን የማውቃትን በዚህ ብሎግ ደግሜ ልነግረህ አልፈልግም። ሆኖም ወደ ቀድሞ እምነትህ
የመመለስ ፍላጎት ካለህ ፀጋው የበዛላቸው በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አባቶችና ወንድሞች ስላሉ አእምሮህን ነፃ አድርገህ ለጥያቄህ በቂ ምላሽ ማግኘት ትችላለህ። ከዚህ በተረፈ ይህ ጉዳይ የኛ የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ስለሆነ ጭፍን አስተያየትህንና ጥያቄህን እዚህ ላይ ብትገታው መልካም ነው።

ቸሩ ፈጣሪያችን የተሠወረብንን መልካም ነገር ይግለጥልን።አሜን!!

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

ውድ ደጀ ሰላም
ይሄ መናፍቅ ዊልያልም’ኮ ጠበንጃውን ከተኮሰ በሗላ የኮሜንት መስጫ ቦክሱ ዘግቶታል፤ ከተለያየ አቅጣጫዎች የጎረፉ ኮሜንቶች ደሙን የሚያፈሉት መሆናቸውን ሲረዳ አጥፍቷቸዋል። ታድያ ከልቡ የተጸጸተ ከሆነ የጻፈውን የሐሰት ሪፖረት ለምን አብሮ አያጠፋውም ነበር? እባካችሁ አድሬሱን የምታውቁ ካላችሁ ተባበሩን። እሱንና መሰል ተከታዮቹ ከየትም ቢሆን ቆፍረን ሲኦል እናወርዳቸዋለን። ሌባ! ድሆች ናቸው ብሎ ነው? ደግሞ የትኛውን ክርስቶስ ሊሰብከን ነው ‘ሚቀባጥረው? ኢትዮጵያዊያን ቀድማችሁ ከምንጩ የተማራችሁ ስለሆናችሁ አስተምሩን አይለንም ባጭሩ

Anonymous said...

to ዘብሔረ ቡልጋ:

Please visit http://www.betedejene.org/ for your questions. (if you want to know about EOTC).

Anonymous said...

to "Zebehere Bulga"

I qoute from Priest Dr. Miltiades Efthimiou article

# If you are a Lutheran, your religion was founded by Martin Luther, an ex-monk of the Roman Catholic Church, in the year 1517.

# If you belong to the Church of England, your religion was founded by King Henry VIII in the year 1534 because the Pope would not grant him a divorce with the right to remarry.

# If you are a Presbyterian, your religion was founded by John Knox in Scotland in the year 1560.

# If you are a Congregationalist, your religion was originated by Robert Brown in Holland in 1582.

# If you are a Protestant Episcopalian, your religion was an offshoot of the Church of England, founded by Samuel Seabury, in the American colonies in the 17th century.

# If you are a Baptist, you owe the tenets of religion to John Smyth, who launched it in Amsterdam in 1606.

# If you are of the Dutch Reformed Church, you recognize Michelis Jones as founder because he originated your religion in New York in 1628.

# If you are a Methodist, your religion was founded by John and Charles Wesley in England in 1774.

# If you are a Mormon (Latter Day Saints), Joseph Smith started your religion in Palmyra, New York in 1829.

# If you worship with the Salvation Army, your sect began with William Booth in London in 1865.

# If you are a Christian Scientist, you look to 1879 as the year in which your religion was founded by Mary Baker Eddy.

# If you belong to one of the religious sects known as “Church of the Nazarene”, “Pentecostal Gospel”, “Holiness Church,”, or “Jehovah’s Witnesses,” your religion is one of the hundreds of new sects founded by men within the past hundred years.

# If you are a Roman Catholic, your church shared the same rich apostolic and doctrinal heritage as the Orthodox Church for the first thousand years of its history since during the first millennium they were one and the same Church. Lamentably, in 1054, the Pope of Rome broke way from the other four Apostolic Sees (Patriarchates), by tampering with the original Creed of the Church, and considering himself to be the universal pastor over other Sees and infallible.

# If you are a Uniate Roman Catholic of any Eastern Rites, you had your roots in the Orthodox Church, but were forced into the Roman Catholic Church, either by financial hardship, or regional political/ ecclesiastical unrest (e.g.: Malankara Syrian Catholics), or by western colonialization (e.g.: Syro-Malabar Rite), or by military strength.


# If you are an Orthodox Christian, you religion was founded in the year 33 by Jesus Christ, the Son of God. It has not changed since that time. Our Church is now almost 2000 years old. And it is for this reason, that Orthodoxy, the Church of the Apostles and the Fathers is considered the true “One, Holy, Catholic, and Apostolic Church.”

# This is the greatest legacy we can pass on to the young people of the new millennium

Tig

Anonymous said...

Deje selam,
what you doing? you started talking things related to the college and the discussion is about something else.

T came to knoew your target is to give other name to the college.

mebrud said...

ቸኮልን እንዴ?

ወንድማችን አዲሱ ያቀረበልን ትንታኔ ግሩም ነው፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡ጊዜ ወስደህ የሰራኸው ይመስላል፡፡

ይሁንና በዚሁ አስተያየት መስጫ ላይ
Mr. william Black.የሰጠው አስተያየትና እንዳንድ ነገሮች ግራ አጋብተውኛል፡፡
በጥቂቱ፡-
1ኛ
እውነት ለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም ወደ ኦርቶዶክስ መቀየሩን ይጠቅሳል፡፡
"...I myself am an Orthodox Christian (I have converted this year). These people don’t seem to realize that I really am their friend..."
2ኛ
Tig ስለ ሃይማኖትና መስራቾች ለዘብሔረ ቡልጋ የጻፈችውን ከMr. william Black BLG ላይ በሊንክ ታገኙታልችሁ፡፡
in title:How old is orthodox
http://theorthodoxchurch.info/blog/articles/2010/12/how-old-is-the-orthodox-faith/
3ኛ
ብሎጉን ሳነብ ብዙ አዎንታዎችን ከማግኘቴ በተጨማሪ
EOTC ምዕመናንን ያስቆጣ ቋንቋ መጠቀሙን ጠቅሶ ይቅርታ መጠየቁን ልብ ይሏል፡፡

ስለዚህ

መቆጨት ጥሩ ነው ማስተዋልና ትህትና ሊኖረው ግን ይገባል፡፡
ብቻ የሆነ የቾከለ ነገር እየጻፍን እንዳለ እየተሰማኝ ነው፡፡
እባክችሁ ለመናገር የዘገየን ለመስማትም የፈጠን እንሁን፡፡
በተለይ አሳብ እንደመጣልን ባንጽፍ፡፡
1ኛ፡
ከርዕሱ ጋር መሄድ አለመሄዱን እናስተውል
2ኛ፡
ሌላው ሰው ሲያነበው ይማርበታል ወይስ ያስቆጣዋል እያልን
3ኛ፡
የምጽፈው ነገር ስሜት ነው ወይስ ማስረጃ የተደገፈ እውነት ነው ብለን እናረጋግጥ
4ኛ
አስተያየቱ ከስድብ ነጻ መሆኑን እርግጠኛ እንሁን፡፡
5ኛ
በፍቅር በትህትና በጸሎት Font እናሳምረው፣ ተነባቢ ይሆናላ፡፡

አለዚያ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
ይቅርታ ቸኮልኩ ይሆን እንዴ?
ከችኮላ አድነን እንጂ...አሜን፡፡

ማሰተዋል said...

ሰላመ እግዚአብሔር ለሁላችን ይሁን። አሜን!
መቼም በሰው ልብ ውስጥ ያለውን የሚያውቀው መድሐኔዓለም ብቻ ነው። አንዳንዶች ጥርጥርን ለመዝራት አንዳንዶችም ለክርክር ጥቂቶች ደግሞ በቅን ልቡና ጥያቄ ሊኖራቸው ይችላል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ያለበትን ሁሉ ማውገዝና ማራቅ ማንንም አይጠቅምም። "ዘብሔረ ቡልጋም" ያለባቸውን መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ቢያቀርቡ በአግባቡ መልስ ልንሰጣቸው ይገባል። "ከዚህ በተረፈ ይህ ጉዳይ የኛ የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ስለሆነ ጭፍን አስተያየትህንና ጥያቄህን እዚህ ላይ ብትገታው መልካም ነው።"የሚለውን የእነ አቶ መርክቤ አይነት አስተያየት ምንም ጠቀሜታ ያለው አይመስለኝም። እኔ ጥያቄዎቻቸውን የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ብታመቻቹ መልካም ይመስለኛል:: ከኦርቶዶክስ የኮበለለው ሁሉ ምንፍቅና አምሮት ነው ብለን ልንደመድም አንችልም። በእውነት ብዙ መሰረታዊ ጥያቄ ያላቸው እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ወገኖች መኖራቸውን አምናለሁ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር።

Anonymous said...

Thank you Deje selam,
After your post we had the chance to post our views directly to his blog. I read a lot of amazing comments from my fellow Ethiopians. I thank you in the name of God. This shows how Ethiopia has children with a view much better than those outsiders. After having a lot of pressure, he is forced not to accept any more comment! He tried to make an excuse but that is not enough. He should write the details of all wrong views that he made. Any ways this is your effort. I thank you again.
Tewodros from German

Anonymous said...

አቶ መርከቤ ንጉሴ፦ ይኸውልህ እንዳንተ አይነቱ ነው ቤተ ክርስቲያንን ያቆረቆዘብን። ካነጋገርህ ብዙም የማታነብ ቤተ ክርስቲያንህንም በጥሞና የማታውቃት መሆንህን ያሳይብሃል። ዘብሄረ ቡልጋ መልካም አስተያየት ነበር የሰጡት። አንተ ግን የክርስትና የፍቅር መንፈስ ተትቂቱም እንኩዋን የሸተተህ አትመስልም። ቤተ ክርስቲያናችን በሐዋርያት መሰረት ላይ የታነጸች መጽሀፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያላት ናት። ይህ ማለት ግን ከጊዜ በሁዋላ ባለአዋቂዎች ቀስ በቀስ የገቡ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉ ቤተ ክርስቲያንን የሚያውቁዋት ሁሉ ይረዳሉ። ለምሳሌ የቤተ ክርስቲያናችንን ዚቅ የሚያነቡ ከሆነ በሚያዚያ 25 ገጽ 170 ላይ ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዲህ ይላል <> እና ይሄ ጤነኛ ይመስልሃል? እንዴት የክርስቶስን ነገር ወስዶ ለአንድ ጻድቅ እንደሰጠ አታስተውልም? ይሄ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አይደለም። ታላቅ ክህደትም ነው። በጣም ያሳፍራል። እንደዚህ አይነት ከመጽሀፍ ቅዱስ ሀሳብ ጋር የሚጋጩ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ስህተቶች ሰርገው ገብተው ቤተ ክርስቲያናችንን አበላሽተዋታል። እንዲህ አይነቱን ነገር ነው ቢስተካከል ጥሩ ነው የሚሉት ዘብሄረ ቡልጋ። አስተያየቱም የጠላትነት ሳይሆን የወዳጅነት ነው። ችግሩ ግን እንዳንተ አይነቱ ጭፍን ቤተክርስቲያንን ስለተቆጣጠረ አባቶች እነዚህን ብልሹ የስህተት ትምህርቶች ለማረም አልቻሉም። ቸር ይግጠመን።

Anonymous said...

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን
ለወንድሜ ማስተዋል "ዘብሔረ ቡልጋም ያለባቸውን መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ቢያቀርቡ በአግባቡ መልስ ልንሰጣቸው ይገባል። ያለባቸውን መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ ቢያቀርቡ በአግባቡ መልስ ልንሰጣቸው ይገባል" ያሉት በእውነት ሁላችንም የቤተክርስቲያን ልጆች የምንጋራው ሃሳብ ነው። ነገር ግን ሁሉም ስፖርቶች የየራሳቸው የጨዋታ ሜዳ እዳላቸው የታወቀ ሆኖ ሳለ፤ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉት ወንድማችን ጥያቄያቸውን በትክክለኛው የመጫወቻ ሜዳ ቢያቀርቡት የተሻለ ይሆን ነበር።ያለቦታው የሆነ ጥያቄ ማንሳት ግን የግለሰቡን ማንነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊያስገባ ይችላል።ከዚህ በመነሳት ይመስለኛል መርከቤ ንጉሴ የተባሉ አስተያየት ሰጬ "ከዚህ በተረፈ ይህ ጉዳይ የኛ የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ስለሆነ ጭፍን አስተያየትህንና ጥያቄህን እዚህ ላይ ብትገታው መልካም ነው።" ለማለት ያነሳሳቸው እና ያበቃቸው።ስለሆነም ዘብሔረ ቡልጋ ያለዎትን ጥያቄዎች ሁሉ በሚከተሉት ትክክለኛ ሜዳዎች ላይ አቅርቡ፤ከበቂ በላይ የሆነ መልስ ያገኛሉ። ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳዎ እመብርሀን አይነልቦናዎን ታብራልዎ።
http://www.kesisyaredgebremedhin.com/
http://www.betedejene.org/
Brile (ብርሌ)

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉት ሰው ያልተገባ አስተያየት ከመስጠታቸውም ሌላ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አይደለሁም በማለት እያረጋገጡልን መናፍቃኖች መሐላችን ገብተው መዘባረቅ አለባቸው ቢሰድቡንም በያቃልሉንም ችግር የለውም የምትሉን ማን እንደሆናችሁ አሁንም እናውቃለን። ደግሞ አላዋቂ እንደሆንኩ አውቀዋለሁ። ባለማወቄም አላፍርም አለማወቅ በማወቅ ይለወጣልና። ሌላኛው አሕዛብ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ሐይማኖታችን መቼም ቆርቁዛ አታውቅም። በጭራሽም አትቆረቁዝም። ቤተ-ክርስቲያናችን ብዙ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣የሚጨበጥና የሚሰማ እንዲሁም ከልቡ ለሆነ ኦርቶደዶክስ ተዋሕዶ በማንኛውም መንገድ የሚመኩባት በገንዘብና በጥቅም የማይለውጧት ሐይማኖት ነች። ከዚህ በተረፈ ከመፃፍ ቅዱስ ጋር ተጋጭቶብን ተረትና አፈ-ታሪክ ሆኖብን ሐይማኖታችንን ቀየርን ከምትሉን ለምን ለገንዘብ፣ለስንዴና ለዘይት ለርካሽ ጥቅም እንደቀየራችሁ አልነገራችሁንም? አሁንም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የእነ William Black ሴራ ሳያነሰን ከእኛ ጋር ተመሳስለው ያልተገባ አስተያየት የሚሰጡን አሕዛቦች ያለ ጉዳያቸው ገብተው እንዳያቦኩ እድል ባንሰጣቸው መልካም ነው።

ቸሩ ፈጣሪያችን ሕሊና ላጡት ሕሊና ይስጥልን። አሜን!!

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!

ዘብሔረ ቡልጋ የተባሉት ሰው ያልተገባ አስተያየት ከመስጠታቸውም ሌላ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አይደለሁም በማለት እያረጋገጡልን መናፍቃኖች መሐላችን ገብተው መዘባረቅ አለባቸው ቢሰድቡንም በያቃልሉንም ችግር የለውም የምትሉን ማን እንደሆናችሁ አሁንም እናውቃለን። ደግሞ አላዋቂ እንደሆንኩ አውቀዋለሁ። ባለማወቄም አላፍርም አለማወቅ በማወቅ ይለወጣልና። ሌላኛው አሕዛብ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ሐይማኖታችን መቼም ቆርቁዛ አታውቅም። በጭራሽም አትቆረቁዝም። ቤተ-ክርስቲያናችን ብዙ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣የሚጨበጥና የሚሰማ እንዲሁም ከልቡ ለሆነ ኦርቶደዶክስ ተዋሕዶ በማንኛውም መንገድ የሚመኩባት በገንዘብና በጥቅም የማይለውጧት ሐይማኖት ነች። ከዚህ በተረፈ ከመፃፍ ቅዱስ ጋር ተጋጭቶብን ተረትና አፈ-ታሪክ ሆኖብን ሐይማኖታችንን ቀየርን ከምትሉን ለምን ለገንዘብ፣ለስንዴና ለዘይት ለርካሽ ጥቅም እንደቀየራችሁ አልነገራችሁንም? አሁንም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የእነ William Black ሴራ ሳያነሰን ከእኛ ጋር ተመሳስለው ያልተገባ አስተያየት የሚሰጡን አሕዛቦች ያለ ጉዳያቸው ገብተው እንዳያቦኩ እድል ባንሰጣቸው መልካም ነው።

ቸሩ ፈጣሪያችን ሕሊና ላጡት ሕሊና ይስጥልን። አሜን!!

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

ዘብሔር ቡልጋን የደገፋችሁበት ምክንያት የማን ለማን በምን እንደሆነ አልገባኝም...ዘብሔር ቡልጋ በመጀመሪያው አስተያየቱ ያለው ነገር ቢኖር.ስለ ጽሎት ሥራት ወይም ስለ ዝማሬ አይደለም
ያለው ነገር ዶግማን ነው < የአኦርቶዶክስ ሐይማኖት ማለት አምልኮቱ.ትክክል አዪደለም ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል > ነው ያለው ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ? እንድኔ አረዳድ ከሆነ የ ቀኖና ጉዳይ አይደለም...ዶግማ ነው ዪሄ ደግሞ በድፍረት ሰዎች የሚያስተካክሉት አይደለም።
ስለዚህ አቶ ቡልጋ ከ እዉንት የቅንንት ከሆን ኑፋቄን መዝራት ብቻ ሳይሆን. ያለብዎትን ችግር ተናግረው መልስ ቢሰጠዎ ጥሩ ነበር ። ነገር ግን ለመጠየቅም ለመረዳትም ሳይፈልጉ ነገር ግን ዘም ቢሎ የሰውን ልብ እንዲጠርጠር የማድረግ ስልት ከሆነ መልካም አይደለም ከቅንነትም አይመስለኝም።በዚህ ዌብሳይት እርሰዎ ያመኑበትንና በ ኦርቶዶክስ ያልዎትን ጥያቄ ግልጽ ቢያደርጉ የኦርቶዶክስም መምህራን መልስ ቢስጡ የበለጥ ለሁላችንም ትምህርት ነው ።ሃስብ መደጋገም እንዳይሆንብኝ እንጂ የ እርሰዎ ችግር ብለው ያነሱት በመሰርታዊ እምነት ላይ ነው።ምናልባት ፈቃደኛ ከሆኑ.የሐይማኖት ጽሎት /ጽሎት ሐይማኖት/ የሚል 318 ሊቃዎንት በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የረቀቅውን አጉልተው ምስጢሩን አምልተው ያስቀመጡልን መሰረተ ሐይማኖት አለ ፈልገው በጽሞና ቢያጠኑትና ቢረዱት መልካም ነው ።
ለማንኛውም የእርስዎን መሰረት ሐይማኖት ቢነግሩን አሁንም ለዉይይቱ ትሩ ነበር.ምናልባትም እኮ በትምህርተዎ የሚያምን ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል ።
ጻድቅ እግዚአብሔር እዉነቱን ይግለጽለዎ

Anonymous said...

Lula ተመልከቱ ያልሺውን/ያልከውን የዳዊት ሞላን ሲዲ አይቼዋለሁ ፡፡ ሰውየው ቤተክርስቲያናችንን ሆነብሎ ተመተንኮስ በተናገረው ብስጭቴ ብሶብኛል እንጂ አልበረደልኝም፡፡ መምህር ምህረተአብ ግን የፓስተሩን ምሳሌ ሳይቀር የራሱ አስመስሎ ማቅረቡ አስደንግጦኛል፡፡ መምህራን ተብለው በየአውደ ምህረቱ የሚያስተምሩ መምህራኖቻችንን ጉድ የሚያጋልጥ ሲዲ መናፍቃኑ የለቀቁ ቀን የት ልንገባ ነው፡፡ ሀዚህ ቀደም በጋሻው ከሌላ ፓስተር ከነ ርዕሱ የወሰደውን ሰምተናል፡፡ እነዚህ የቤታችን ጉዶች ኪሳቸስን ለማወፈር በቪሲዲ የሚለቋቸው ስብከቶች በቤተክህነት መገምገም ይኖርበታል፡፡ የምህረተአብ ምላሽ ስህተትን(ኑፋቄን) በስህተት ያረመና አፍቅሮተነዋይን ያገናዘበ ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ያክል ምህረተአብ ስለ ንእማን የሰጠውን ምሳሌ ከፓስተሩ ቃልበቃል የወሰደው ሲሆን እሱ ግን የራሱ አስመስሎ ደረቱን በእቡይነት አሳብጦ ነው የተናገረው ፡፡ በዚህ አይነት እስከ ዛሬ ያደረሱንን ስብከቶች ከመናፍቃኑ ጓሮ የቃረሟቸው ስላለመሆናቸው በምን እንወቅ? ከምንም በላይ የሚገርመው ግን ቃለእንዚአብሄርን ለምላሹ ሲል ማጣመሙ ነው፤ ለምሳሌ ‹‹ፅድቅን የተማሩ ይጠግባሉ…››የሚለውን ፣‹‹ለፅድቅ የሚራቡ… ›› ብሎ አቅርቧል፡፡ አክሎም ‹‹በዘንዶ ላይ ትጫማላችሁ…›› የሚለውን ‹‹ዘንዶን ትጫማላችሁ…›› ብሎ አቅርቧል፡፡ እግዚአብሄር ከቃሉ ላጎደለም ሆነ ለጨመረ የከፋ ቅጣት ይሰጣል፡፡ ‹‹ለቤትህ ብዬ፣ መናፍቃንን ላሸማቅቅ ብዬ፣ወዘተ… ›› ማለት አይቻልም፡፡ ዳዊትም ምህረተአብም ሌላ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል፡፡

Anonymous said...

ይድረስ ለ “ዘብሔረ ቡልጋ...”ና መሰሎቹ
መጀመርያ መልስን ለመስጠት ያመቸን ዘንድ ስምህን ሳትቀያይር ጥያቄዬን የ’ዚቁ’ ጉዳይ ነው ብለህ መምጣት ነበረብህ።
ተግባብተን ከሆነ ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ አነሳህ እንጂ አንተንና መሰሎችህ በድንግዝግ ዓለም እንድትቆረቁዙ ያደረገ ዲያቆን ነኝ ባዩ በጻፈው መጽሐፍ: የቅድስት ድንግል ማርያም፣የጻዲቁ ተክለ ሐይማኖትና የአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ፣ የቅድስት ዕለተ ሰንበትና ሌሎችን የሚያትት ጽሑፍ ለሥጋው ስንቅ ማስገኛ ወደ ገበያ ጣል አድርጓል። ሌሎች ጓዶኞቹ/አባቶቹም ከጥንታዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትርጉም ፈጽሞ በተፋለሰ መልኩ “ገድል ወይስ ገደል” መጽሓፋቸው ሲበትኑ የጥራዝ ነጠቅ አእምሮም እውነት መስሎት እንደ ጠበለ እግዚእ ሀህ ብሎ ጠጥቶታል።
ወንድሜ? ታላቁና እውነተኛው ቅዱስ መጽሐፋችንን ለመተርጎምና ለመረዳት ከፈለግህ በአንደኛውና ቅድመ አንደኛው ክፍለ አዝማን የነበረውን የነበረውን ሁኔታ ማሰስ ይኸውም፦
1. የእስራኤል/ፓለስቴን/ ባህል፣ ሐይማኖት፣ የኣኗኗር ገጽታን፣ የሥነ ጽሑፋቸውን ዕድገትና መልእክት የመሳሉትን ማወቅ ይጠይቃል።
2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና የመጻሕፍቶቿን መልእክትን በትክክል ለመረዳት ከተፈለገ ደግሞ መልሱ በቁጥር አንድ ያስቀመጥሁትና ሌሎች የታሪክ ወጤቶች መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ለምሳሌ
ወንጌላዊው ማርቆስ ወንጌሉን በ42 ዓ/ም፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲጽፈው በጊዜው በነበረው ባህልና የሥነ ጽሑፍ ጥበብን በመጠቀም ነበረ ማለቴም ስድ የእጅ ጽሑፍ (አርእስት፣’ፓራግራፍ’፣ምዕራፍና ቁጥር፣ዳራ የሌለበት) ነበረ። በ2ኛ፣በ3ኛና በ5ኛው መቶ ክፍለ መዋዕል ግን ወንጌሉ በአርእስት፣በምዕራፍና በቁጥር ተለይቶ እንዲጻፍ የተወሰነ ዕድል እያገኘ ከመምጣቱ ባሻገር ከአንድ ቋንቋ ወደ ብዙ ቋንቋዎች የመተርጎም ጊዜም ተቀበለ፤ እንደዛው እያለ ነው ወደ ዛሬው ደረጃ ( ቅዱስ መጽሐፉ በዓቢይ አርእስት፣ይዘት፣ጭብጥ መልእክት፣ዝርዝር አርእስት፣’ፓራግራፍ’፣ምዕራፍና ቁጥር፣ በጽሑፉ መኻከል አንዳንድ ታሪካዊ ስእሎችን ማስገባት፣በሕብረ ቀላማት ተጠቅሞ መጻፍ፣ የግርጌ ማስታወሻ መጠቀም፣ወደ ዜማ መቀየር አንድምታ ማበጀት፣ወዘተ)። ይሔውልህ! ከኛ በዃላ የሚፈጠረው ትውልድ ይህ የሥነ ጽሑፍ ለውጥ ካላስተማርነው በስተቀር እንዳለ ከጥንቱ የወረስነው ነው የሚመስለው፤ መለስ ብሎ እናዳያይ እናደርገዋለን ማለቴ ነው።

አሁንም አስተውል! የቤተ ክርስቲያናችን የሥነ ጽሑፍ ዕድገቷ ሌሎች የዓለም ሀገሮች ከሚጠቀሙት ለየት ያለ መሆኑ አትዘነጋውም በተለይም በቅኔዋና በውስጠ “ዘ”ዋ። ይህ ጥበብ ከ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው እየጎላ የመጣው በነ ዓጼ ገብረመስቀልና በቅዱስ ያሬድ ዘመን።

በአሁን ጊዜ ደግሞ እኛ እንደተወለድን የአባቶቻችን ጥበብ ሳይሆን የተማርነው የቀበሌያችን ቋንቋ ይዘን በሥጋ ዐደግን ቆይተንም ልብ ስናበቀል በዓውደ ምሕረቱ ያለውን የኣባቶቻችን ዘይቤያዊ ጥበብን ትተን በመንደራችን አስተሳሰብና አተረጓጎም ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበብን መተርጎም እንደ ሐይማኖት አድርገን ያዝነው ብሎም በኣቋራጭ “ፓስተር” እገሌ። በንባብ ዲፖሎማ፣ዲግሪ፣2ኛ ዲግሪ፣ዶክትሬት ይገኛል’ንዴ? እኔ የገረመኝ ወገንህ ከሆነ ፓስተር ዳዊት “እኔ’ኮ አንብቤ ነው በዚሁ ደረጃ [ፓስተር] የደረስኩት ብሎ ሲሰብክ ነው ፕሮቴስታንቲዝም ፊክሽን የምታነብበት ሱቅ መሆኑን የተገለጸልኝ።

ያም ሆነ ይሁን በኦርቶዶክስ ሐይማኖታችን ላንተ እንደ ተረትና ነቀፋ ያለበት መስሎ የሚሰማህ ካለ ወደዚህ ልምራህ።በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተለይም በንጉስ ዘርአ ያዕቆብ የሥነ ጽሑፍ(ግእዝ ቋንቋ) ርቀት ያቆጠቆጠበት ጊዜ ስለ ነበረ አብዛኛውን የቅዱሳት መጻሕፍት ድርሶቶቻችን ከዚህ ጊዜ ጀምረው የተለዋጭና የሰዋዊ አነጋገር ፍልስፍና እየተጣበቡበት መጥተዋል። ለምሳሌ ያህል አንተ የጠቀስኸውን “አቡነ መርቆሬዎስ እግዚእነ...”ወይም ፈጣሪነ እንበለውና ድርሰቱን የደረሱ ኣባቶች ጻዲቁ ኣባት ሰው መሆናቸውን ጠፍቷቸው አይደለም የሰሩትን ገድል ለማጉላት ፈልገው እንጂ፤

ቅዱስ አባ ሕርያቆስ “አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ” ያሉበት ምክንያት ሥላሴ ማለት የምናየው ዕሩቅ ፀሐይ ነው ለማለት ፈልገው’ኮ አይደለም ለምስጋናቸው ምሳሌ/መግለጫ ስላጡበት ነው ፤

እያንዳዱ መልክዐ መልክዕ ከጥፍረ እግር እስከ ጸጉረ ርእስ በምስጋና ተሸልመዋል። ሥላሴና መላእክት እንደኛ የሚዳሰስ ግዙፍ አካል ኑሯቸው ሳይሆን ለረቂቅ አካላቸውም በሰው ሰውኛ አነጋገር ምስጋና ያስፈልጋል ከማለት የተነሳ ነው ።

“ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም” የኣለም አዳኝ ክርስቶስ መሆኑ ጠፍቷቸው’ኮ አይደለም ማርያም የዓለም ቤዛ ነሽ ያሏት፤ ከርሷ በተወሰደው ሥጋ ዓለምን የዳነበት መሆኑን ለመግለጽ ወድደው ነው እንጂ።

“ሰንበት ብሒል እግዚአብሔር ውእቱ” እሁድ ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው ብለህ በደረቁ ከተረጎምክ’ማ አርዮስም በዚህ የአተረጓጎም መንገድ ተጉዞ ነው “ትቤ ጥበብ ፈጠረተኒ-ጥበብ ፈጠረችኝ” ብሎ ወደ ገደል ሽው ያለው። እንኳን አንተ ቤተ ጳውሎስ ረግጫለሁ የምትል ቀርቶ ማንም ጀማሪ ሰንበት-ተማሪ ብትጠይቀው ባጭሩ፦ ‘ሰንበት/እሁድ/’ ማለት የመጀመርያው ቀን ወይም ቀዳሚት ዕለት ፤እግዚአብሔር ማለት ደግሞ የዓለም ባለ ቤት ነገርግን በግእዙ ቋንቋ ሰንበት ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው የሚለው አባባል እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ መፍጠር መጀመርያ የሥራው ቀን ያደረጋት፣ ክርስቶስ ሙቶ ከመቃብር የተነሳበት የብርሃን ቀን መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ይመልስልሐል።


አየ አንተ! በውኑ በአካለ ነፍስ በቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ተመላልሰህ አድገህ ከሆንክ በኮሌጁ ቤተ መጻሕፍት ያሉት ጥንታዊያን ቅዱሳት መጻሕፍት ለስሙ አንድ ቀን ገልጠሐቸው ታውቃለህ? ያልገባህስ እዛው ያሉ ሊቃውንቶቻችን ጠይቀኻቸዋል? ሌላው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አድገህ ከሆንክ አባቶቻችን በሙያቸው አስሬ የተመረቁበት ሊቅ ቢሆኑም “እስኪ ባለ ቅኔው ይፍታው ምን ለማለት እንደፈለገ?” ሲሉ ነው የሚያስተምሩት። መልእክቱ ለሁላችን ይመስለኛል ሳንማር እንዳንተረጉም የማስጠንቀቂያ ቀይ መብራት መስጠት። ነገርግን ይህ ሁሉ ቀብረን፣በሙያው የዋሉበት ሊቃውንት የገድሉን፣ የተአምሩንና የመጽሐፍ ቅዱሱን ትክክለኛ ትርጉሙ ምንድንር ነው ብለን ሳንጠይቅ በራሳችን ፈለግ ጉዞ ስንጀምር ጥልቅ ወደ እንግዳው በረት።

Eወንድሜ አደራ ነቀፋ እንዳታበዛብኝ ጥያቄህን በግልጽ ስላላወቅሁት ነው መነሻ/መንደርደርያ ያስቀመጥኩልህ።

Mመቐለ-ቴዎ...

Anonymous said...

አቶ መብሩድ?
ደህና ግድ የለህም! እኔ የዊልያምን ማንነት ለማግኘት ያልቆፈርኩበት ጉድጓድ የለም።ፖስት ያደረግሁትም አጋጣሚ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘሁት ነው።
አንድ ልልህ የሚፈልገው ጋሼ መልአከ ጽልመት መልአከ ብርሃን መስሎ እንደሚመጣ አትርሳ ምክንያቱ ፈረንጆች ኦርቶዶክሳዊያን በጣም ከባዶችና እስካሁን ድረስ ለማንም የውጭ ሃይል ያልተምበረከክን መሆናችን ስለሚያውቁ ሰይጣን በእባብ ትከሻ ታዝሎ አዳምንና ሔዋንን እንዳሳታቸው ሁሉ እነ ዊልያምም በረቂቅ አካሄድ እንዲገቡ ነው ጉዞአቸው። እኔ’ኮ እየተመላለስሁ ፈትኜዋለሁ ለምሳሌ I read in Deje Selam blog you wrote, “I myself am an Orthodox (I have converted this year) if it is yours. Who is the bishop/priest received you including your original name pastor William black? ብዬ ከጠየቅሁት በኻላ በብሎጉ ላይ ፓስተር ዊ.ብ ብሎ ጽፎት የነበረው ፓስተርነቱን ፍቆታል። ይህ ምንን ያሳየናል ለመመሳሰል ብሎ የሚያደርገው የገበያ ለውጥ ነው።
ዙሮ ዙሮ ኦርቶዶክሳዊያን ጠላታችን ያልሆነውን እስከሚቀባጥር ድረስ ያሳያችሁትን ተጋድሎ ይበል የሚያሰኝ ነው በርቱ ለወደፊቱም ዛሬ ጀምሩ ስንላችሁ እንደማታሳፍሩን ተስፋችን ያበበ ነው።
አየ ወይዘሮ ደገ ሰላም ዝናሽ እንደ ሐዋርያት ስብከት ጽንፍ እስከ ጽንፍ ተዳርሷል፤ የኔ ቁርስ፣ የኔ ምሳና እራት! ግን እስከ መቼ ነው የቤተ መቅደስ ሙሽራ ሆነሽ የሚትኖሪው? አምላክ በሥጋ ሲገለጥ ያንቺ ትንቢትስ አልደረሰም?

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን፦ አያችሁ እናንተ እንኩዋ እንዴት እንዳፈራችሁ? በዚቃችን ሚያዚያ 25 ገጽ 170 ላይ ያለውን ምንባብ ጽፌው ነበር ነገር ግን ጥቅሱን አውጥታችሁ ነው መልእክቴን ፖስት ያደረጋችሁት። አዎ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያኔን አፈቅራታለሁ አጅግም አከብራታለሁ ነገር ግን አሁን አለም በጠበበችበት ጊዜ እንዲህ አይነቱን ነገር መደባበሱ ጥሩ አይደለም። ሀሰቱን ሀሰት ብሎ ማረም ለሁሉም ነገር ደግሞ በግልጽ መልስ መስጠት ተገቢ ነው። እንደጠቀስኩት አይነት ጥቅስ እጅግ ብዙ የተበላሹ ነገር ግን ጥንታውያን ኦርቶዶክሳውያን አበው ያላስተማሩዋቸው ነገሮች አሉ። እነዚህ ነገሮች ቤተ ክርስቲያንን ይጎዳሉ እንጂ አይጠቅሙም። ብዙዎች ወገኖቻችን ወደሌላ አዳራሽ የኮበለሉት እነዚህ የስህተት ትምህርቶች የቤተክርስቲያናችን ትምህርቶች አድርገው ስለሚወስዱ ነው። ብዙዎቻችን ቤተ ክርስቲያናችንን ንጽህት ቅድስት እንከን የሌላት መጻህፍቶችዋ በሙሉ እንከን የለሽ አድርገን እንናገራለን። ይህ ራስን ማታለል ነው። መጥራት ያለበት የአባቶቻችን ትምህርት ያይደል ብዙ አሰስ ገሰስ አለ። ቤተ ክርስቲያንን መጥቀም የሚፈልግ ሁሉ እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ተብሎ በግልጽ መነገር እንዳለበት አምናለሁ። እድሜ ማህበረ ቅዱሳንን ለመሳሰሉ አልቃይዳ ቡድኖች እና የከተማ ባህታውያን። አባቶች እንኩዋንና እንደዚህ አይነቱን የአጹዋማትን ቀኖና ለማስተካከል ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቶአል። እሱ ራሱ በቸርነቱ ቤተክርስቲያኑን ይጠብቅ/ይስራ። አሜን

ዘብሔረ ቡልጋ፤ said...

ውድ ደጀ-ሰላማውያንና ወገኖች በሙሉ፤
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። አሜን
ወገኖች በእውነትና በቅንነት ለምን ከኦርቶዶክስ እምነት እንደወጣሁ በዚህ መድረክ ላይ ባጭሩ የገለጽኩት በእናንተ ዘንድ የተለዩ ምላሾችን አስከትሏል። በቅንነት የመሰላችሁልኝን ለመሰላችሁልኝ ከልቤ አምሰግናለሁ። የአንዳንዶቻችሁም መፍትሔ የማያመጣ "ለምን ተጠየቅን" ወይም በጭፍን ሐይማኖታችን ተደፈረ አይነቱን ምላሻችሁንንም በቅሬታ አይቸዋለሁ።
ለማንኛውም በተቻለኝ መጠን አንዳንድ ወገኖቼ የጠየቃችሁኝን አግባብ የመሰለንኝ ጥያቄዎች በአጫጭሩና በቅርቡ በትህትና አቀርብላችኋለሁ። አሁንም ቢሆን ሐይማኖት፤ ሐገር፤ ቋንቋም ሆነ የመሳሰለው በምድር ላይ ቀሪ በመሆኑ ከሁሉም የበለጠ ሊያንገበግበንና ሊያሳስበን የሚገባው የፈጣሪያችን ቅዱስ ትእዛዙና የዘለዓለም እጣ ፋንታችን ነው። ለዚሁም ዋናውና ብቸኛው መለኪያችን ሁል ጊዜ እውነት የሆነው፤ ሙሉ ለሙሉ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ የማይሻረው የማይሻሻለው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በመሆኑም በቅንነት ለእግዚአብሔር ክብርና ለኛም ጥቅም ይሆን ዘንድ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያስወጣኝን፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች ከጸለይኩበት በኋላ ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ለናንተ በቅርቡ አስነብባለሁ።
ከዚህ በተረፈ ነገሩን ለማካበድ ሆነ በሌላ ድብቅ ሐሳብ ለማስተላለፍ በዚህ ጡመራ በሌላ የብእር ስም እንደማልጠቀም በጌታ ስም አረጋግጥላችኋለሁ።
ለሁላችንም እውነትና የእውነት መለኪያ የሆነው ቸሩ ፈጣሪያችን ከእርሱ የሆነውን ይግለጽልን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ሕዝቧን ይባርክ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ፤ ንጉሴና አምላኬም ነው።
በክርስቶስ ፍቅር።
ዘብሔረ ቡልጋ።

Anonymous said...

አይ እንግዲያውስ መተው ነው የሚሻለው መሰለኝ ነገራችሁ እውነቱን ለማወቅ መስሎኝ ትንሽ ፊንጭ/መንደርደርያ የጠቆምኩልህ።
እኔ ፈጣሪ አይደለሁም በልብህ ላለው ጥያቄ ይህን ነው ብዬ ተገቢውን መልስ ሊሰጥህ የምችለው፤ ደግሞ በስመ “እንደነ መርቆሬዎስ የመሳሰሉ” ስትል እኔም ከተደፈነው ርእስህን ተነስቼ ነው ምንአልባት የዘብሔረ ቡልጋ ጥያቄ ከነዚህ ውስጥ ይሆናል ብዬ ነው በጣም ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ማስቀመጥ የሞከርኹት። በእርግጥ የመጽሐፉ ገጽና ቁጥር መስጠት አንዱ የጥቆማ መንገድ መሆኑን አሁን ትዝ ብሎኛል ነገርግን መጽሐፉ የለኝም ።
ደጀ ሰላምም ሰውዬው የሚለው ያለ እውነት ከሆነ ባትቆነጻጽሉት መልካም ነበር ወይም ጥያቄውን ወደ ሚመልስለት ሰው/አድሬስ ማስተላለፍ ነው ያለባችሁ። እኛ’ኮ ጦርነታችን ከዕቅፋችን ውስጥ ያለውን ህዝባችን ለመጠበቅና በስሕተት ወደ ሌላውን በረት የገባ ሰው ቁንጫውን አራግፎ ወደ ትክክለኛው መኖርያው እንዲመለስ ነው።

lovely

Unknown said...

Dear the above anonymous እንዲህ በማለት የገለጽከው ነገር የሚገርም ነው...."እድሜ ማህበረ ቅዱሳንን ለመሳሰሉ አልቃይዳ ቡድኖች እና የከተማ ባህታውያን። አባቶች እንኩዋንና እንደዚህ አይነቱን የአጹዋማትን ቀኖና ለማስተካከል ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቶአል።" It is shame to write such disgusting words. You are really house of Satan. Can you tell us when MK's have tried to do such things. What ever you wrote a number of nauseating words you couldn't deviate EOTC members towards MK. Because their true work explained themselves. Please come to the truth rather than blackmailing the true work.
Let God gives you true heart!

Anonymous said...

እግዚብሄር ፀጋውና በረከቱን ያድልህ ይመቀሌ ቴዎ፡እኔ የዘረዘርካቸው መፃህፍት አንቢብያቸው ማይንድዬ አቁስለው ነበረ፡ለምሳሌ ብለህ የዘረዘርካቸው መልሶች ግን ከዚህ በፊትም አባቶችን ጠይቄ ግልጽ ያልሆነ መልስ ነው የሰጡኝ፡ ያንተ መልስ ግን ሰምቻቸው የማላውቃቸው በጣም የሚነደነቁ አሳማኝ ፡ የአባቶቻችን መልስ ነው የሰጠሀን ለሁላችን፡ ፐሪንቲም አድርጌዋለሁ ለጓዶኞቼም እሰጣቸዋለሁ ፡ ግን ይህን የመሰለ ትምህርት ለምን በዋናው ርእስ አላወጣሀውም ሁሉም ክርስቲያን እንዲማርበት፡

Anonymous said...

አቤት ርእስ ማስቀየር ሲችሉበት እኔ የምፈርደው በነሱ ሳይሆን በደጀሰላም ነው ስብሰባ ላይ እንካን አካሄድ ይባላል ምነው ደጀሰላሞች ሃይማኖታዊ ጥርጥር እኮ የራሱ ቦታና ብሎግ ሊኖረው ይገባል እንጅ ይህ የራሱ ርእስ ያለው ነገር ነው ምነው ምነው ምነው የማንንም....እያቀረባችሁ ባታበግኑን

Anonymous said...

Deje selam,
your great information forced Mr Wiilliam to delete that groundless article. I once again thank you.
Tewodros from German

biniam weldegebrial said...

dear dejeselams am happy that you are trying to aware the people what is going aroung on our church.MAY GOD BE WITH YOU,

Anonymous said...

Alelign
What a shame on you!
Do you blame MK for not involving in "Reducing Canonical Fasting Days"?
You can eat by yourself, whoever wants to fast more, he can do! Written law is only a public guideline, it can't be a private mind dictator! Lead yourself to whatever may seem you better. AND DON'T blame someone fasting the whole day, as hypocrite, because you are not doing it! Menfesawee Qinat is not becoming a Fetena to others, its a Way to catch up the spirituality level to them!!!
If anybody feels he can fast the whole year, why not?

ORTHODOXIA said...

I love you all concerned Ethiopian Orthodox Church followers. We become happy on your effective struggling with the 'menafiq'.

Keep it up on same events for you will be among the 100s reward,"bo ze-miet"

Anonymous said...

Mahibere Kidusan Keep it up
we are ready to defend every negative aspects every where in every sector.
Yegize Guday new enji hulum megalechaw dersual.mahibere kudusanoch bertu beminm neger kgonachu nen.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)