December 16, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን የማዳከሙ አዲሱ ሴራና ተንኮል

(አዲሱ ተስፋዬ፤ ለደጀ ሰላም)፦ ባለፈው ወራት በቤተ ክርስቲያን ዙርያ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መንፈሳዊ ጥያቄና  የበጋሻው ክስ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን ደጀ ሰላምም ላይ ይሁን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ጦማሮች ላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከመግለጥ ውጭ የችግሮቹን ሥረ-መሰረት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ጥቂት ነበር። የኛዎቹ ሚዲያዎች ቢተውትም ሌሎች ሚዲያዎች ግን በጉዳዩ ላይ አስገራሚ ምስጢሮችን አስነብበዋል።

አሜሪካዊው ፓስተር ዊሊያም ብላክ (William Black) ለዚህ ተጠቃሸ ነው። ይሔ ሰው በትውልድና በዜግነት አሜሪካዊ ሲሆን ባሜሪካ የተለዩ ግዛቶች ውስጥ የፕሮትስታንት ሰባኪና ፓስተር ሆኖ ከማገልገሉም ባሻገር በኢትዮጵያም 6 አመታትን የፈጀ ቆይታ አድርጎአል:: አሁን በኬንያ የፕሮቴስታንት ድህረ ምረቃ ቲዎሎጂ ኮሌጅ መምህር ነው። ኦኔሲሞስ (Onesimus) በሚባለው የጡመራ መድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ማፈራረስ እንደሚቻልና ባሁኑ ወቅትም የሱና መሰል ድርጅቶች ቤተ ክርስቲያናን እንዴት እተዋጉ እንደሆነ “struggle for the soul of the Ethiopian Orthodox Church “በተሰኘው ጽሑፉ ላይ በሰፊው ገልጧል።

መንፈሳዊ ኮሌጆችን የመበከል ሴራ
ዊሊያም በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተዋሕዶና በተሐድሶ መካከል ከፍተኛ ውስጣዊ ጦርነት እንዳለ ከገለጠ በኋላ፤  አዲሱ ስልት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  መንፈሳውያን ኮሌጆችን መጠጋትና ኑፋቄ መዝራት መሆኑንና በዚህም በእጅጉም እንደተሳካላቸው እንዲህ ሲል ገልጦታል:-
“…One group of American missionaries has insinuated themselves under misleading premises (claiming to be business people when in fact they are missionaries from a Western group) into the area near one of the Orthodox reformists theological colleges. By drawing into their circle some of the reformist leaders and students, they have had some success in persuading some to the Protestant perspective on salvation and the Baptist perspective on baptism.” 1

“አንድ ያሜሪካውያን የሚሲዮን ቡድን ራሱን በመደበቅ (ከምዕራቡ ዓለም የመጡ የሃይማኖት ስዎች ቢሆኑም  የንግድ ሰዎች ነን በማለትና በማታለል) ወደ ኦርቶዶክስ  ሥነ መለኮት ኮሌጆች ገብተዋል።ከኦርቶዶክስ  መሪዎችንና ተማሪዎችን ዘልቆ በመግባትም የፕሮቴስታንት ነገረ ድኅነትንና የነገረ ጥምቀትን አስተምህሮ ለማሳመን ተችሏል።
ይህንንም ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያብራራ፦
The intention of these missionaries is to remove these leaders from the Orthodox Church and from the reformist movement and to set up (of course) their own baptist church. Deception, even in the name of Christ, is still deception. These sorts of tactics are being reproduced elsewhere in Ethiopia.” 2
“የሚሲዎኖቹ ዓላማም እነዚህን መሪዎች ከተዋሕዶም ሆነ ከተሀድሶ በማስወጣት የራሳቸውን የባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰርቱ ማድረግ ነው። ማታልል በክርስቶስ ስምም ቢሆን ማታለል ነው። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ታክቲክ በመላው ኢትየጵያ እየተስፋፋ ነው።”
ሲም (Serving in Mission/ http://www.simeth.org/) የተባለው የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅት የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ አንዱ በሆነው በቅዱስ ፍሬምናጦስ  መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ለማስተማር የመምህር ምልመላውን ባደባባይ ጀምሮአል። ፍሬምናጦስ መንፈሳዊ ኮሌጅ  ብሎ ጎግል ላይ ለፈለገ ሰው እስኪገርመው ድረስ የሚያነበው ነገር ቢኖር በዚሁ ተዋሕዶ ኮሌጅ እንዲአስተምሩ ለመናፍቃን መምህራን የውጣን የስራ ማስታወቂያ ነው ለምሳሌ Serving in Mission ( SIM) የተባለው መናፍቃን ድርጅት ያወጣው ማስታወቂያ እንዲህ ይላል:-

This is an unprecedented opportunity to teach and work within an ancient church with direct apostolic roots. If you are interested in learning about different cultures and teaching in a college with an Orthodox Christian perspective, this should greatly interest you. You will be teaching students from around the country, mainly deacons, priests, and monks who have been chosen by the Ethiopian Orthodox Church to attend this new theological college.” 3

ፕሮቴስታንት ተዋሕዶ ኮልጅ ገብቶ እንዴት እንዲአስተምር ተፈቀደለት? የሚያስተምረውስ ምን ዓይነት ትምህርት ነው? የተዋሕዶ ሊቃውንትስ ጠፍተው ነው የመናፍቃን መምህራን እንዲያስተምሩ ያስፈለገው? ምስጢሩ ምን ይሆን? Serving in Mission (SIM) የተባለውን ድርጅትና ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየሠራ ያለውን ሴራ በተመለከተ ዊሊያም ለተከታዮቹ እንዲህ ሲል አብራርቶታል።
 “Even in my own mission (SIM) there is a small group of missionaries working in partnership with Orthodox leaders to strengthen the educational efforts of the reformist movement.” 4
የዊሊያም ገለጣ በግልጥ እንደሚያስረዳው ሲም (Serving in Mission) ቤተ ክርስቲያንን የቀረበበት ዋና ዓላማ የኦርቶዶክስ ተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማበረታታትና ለመደገፍ ነው:: የሚመደቡትን መምህራን የጀርባ ታሪክ ማጥናት ለዚህ ዋና ምስክር ነው።
ለምሳሌ ዶክተር ቲም ቱሲንክን ብንወስድ የፕሮቴስታንት መምህርና አቀንቃኝ ናቸው። የፕሮቴስታንት ድህረ ምረቃ ኮሌጅ ሰባኪ የሆኑት እኚህ ሰው በኛም መንፈሳዊ ኮሌጆች (ቅድስት ሥላሴና ፍሬምናጦስ) አስተምረዋል። ያስተማሩት ነገረ ሃይማኖት ግን ምን ይሆን? ኑፋቄ ወይስ ርቱዕ እምነት?
“Dr. Tim Teusink  … serving with SIM (Serving in Mission) in Ethiopia,….  His primary focus is theological education, particularly a biblical perspective on sexuality and marriage.  He works with the Ethiopian Kale Heywet (Word of Life) Church, the largest Protestant denomination in the country with 7 million members and The Ethiopian Orthodox Church with 35 million members.  He teaches at the Evangelical Theological College of Addis Ababa (ETC), the Ethiopian Graduate School of Theology (EGST), The Ethiopian Orthodox Church’s Holy Trinity Theological College in Addis Ababa and St. Frumentius Theological College in Mekele (Northern Ethiopia) and other Bible Schools. 5
           
“አድሐሪው እና ተቃዋሚው ቡድን”፡- ማኅበረ ቅዱሳን

ዊሊያም ለዓላማቸው መሳካት እንቅፋት የሆነባቸው አንዱ ቡድን ማኅበረ  ቅዱሳን መሆኑን በምሬት እንዲህ ሲል ገልጧል።
Working against both the ongoing creep of Western values and the attempts by the Reformists to restore the church, a reactionary movement called Mehaber Kidusan and led by members of the hierarchy and priests and others, are seeking to fend off any changes and to preserve aspects of the Church which they feel are crucial to their identity and Ethiopia’s place in the world. Central to this conservative agenda is the preservation of the Virgin Mary’s role in their understanding of the Church’s theology.” 

Ethiopian Orthodox have always been fervently devoted to the Virgin Mary. Members of Mehaber Kidusan intentionally play on this intense loyalty to Mary as a means of inflaming passions against any attempts to change the Church, regardless of whether that change comes at the hands of Protestants, Muslims or Reformists. The more biblical and ecumenical nature of Orthodox tradition promoted by these Reformists is thus a direct challenge to the more parochial and nationalistic aspects of the understanding of Orthodoxy promoted by Mehaber Kidusan and its allies. 6

“እየተንሰራፋ ያለውን የምዕራባውያንን እሴት እና ኦርቶዶክስ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚቃወም ማኅበረ  ቅዱሳን የሚባል አድሐሪ ማኅበር አለ።….የዚህም ማኅበር ዋና ዓላማው ቤተ ክርስቲያንን ከተሀድሶ ለመከላከልና ለሀገሪቱ ማንነት ወሳኝ ነው ብሎ የሚያምነውን የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት መጠበቅ ነው። የዚሁ አክራሪ ማኅበር (ማኅበረ  ቅዱሳን) ማዕከላዊ አጀንዳ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥነ መለኮት ጉዳይ ውስጥ የድንግል ማርያምን ሚና መጠበቅ ነው።”

ይህንንም “አድሐሪ”  ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንን ካላስወገዱ እንደፈለጉ መራመድ አለመቻላቸውን መናፍቃኑ ገልጠዋል። ለዚያም ይረዳ ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማዳከምና ለመምታት በርካታ ሴራዎችን አከናውነዋል። ዘመቻው በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ተጧጡፎ ቀጥሏል። ባለፈው ዓመት ብቻ በርካታ ዓለም አቀፍ እና በበርካታ ሚሊዮን ዶላር በጀት የሚንቀሳቀሱ ክርስቲያን ነን ተብዬ ድርጅቶች የማኅበሩን ስም በየድረ ገጾቻቸው ሲያወግዙ ከርመዋል።7
“Christian sources said a group within the EOC called “Mahibere Kidusan” (“Fellowship of Saints”) had incited members to attack the two evangelists as they were proclaiming Christ. The increasingly powerful group’s purpose is to counter all reform movements within the EOC and shield the denomination from outside threats.In some cases, the sources said, EOC priests have urged attacks against Christians, and government authorities influenced by Mahibere Kidusan have infringed on Christians’ rights.”

የዚህ ዕቅድ ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳንን በውስጥ ሰዎች የማጥላላት ዘመቻ እንዲካሄድበት የውስጥ አርበኞቻቸውን ማነሳሳት ነው። “ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን?” የሚል ተራ ድርሰት መሰራጨቱ Thetruthfighter.net የሚል ማኅበረ ቅዱሳንን ለማጥላላት የተከፈተ ድረ ገጽም መኖሩ የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው። ጥላሁን መኮንንም ድረ ገጽ ከፍቶ ቤተ ክርስቲያንንና ማኅበሩን ለማድከም ብዙ ደክሞ ነበር።

ሙስሊሞችም ጋር ማኅበሩን ለማላተም በረቀቀ ሴራ የተከፈተና ማኅበረ  ቅዱሳንን ሙስሊም የሆነ ሰው በሙሉ እንዲያወግዘው የሚያነሣሣ አስገራሚ ድረ ገጽ ተከፍቶ ነበረ።9 ከውስጥም እነ አባ ሰረቀ ብርሃን “ይሄን ማኅበር!!!!” ብለው አካኪ ዘራፍ ማለት ጀምረው ነበር። ደጀ ሰላም ምስጋና ይግባትና በስውር የተላላኩትን የተሐድሶያዊ ዜማ የያዘ ደብዳቤ ካስነበበችን በኋላ፤ ለብዙዎቻችን የአባ ሰረቀ ነገር ግልጥ ሆኖልናል።10 ሰሞኑን ደግሞ “ይሔ ደም አፍሳሽ ማኅበር”  እያለ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን የመሳደብ ስብከት ጀምሮልናል11። የሱም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሮኬት ሳይንቲስት መሆን አያሻም።

የኛስ ሚና ምን ይሆን? የተሳዳቢውን አንደበት ለማሰታገስ የድሬደዋ ንዑስ ማዕከል ያደረገው  እንቅስቃሴና የቅድስት ሥላሴ ዲን አቡነ ጢሞቴዎስ ኮሌጁን ከመናፍቃን ክህደት ለመጠበቅ ያደረጉት ቁርጥ ርምጃ የሚመሰገን ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችንን ለማዳን ከፍተኛ ርብርብ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን።

ማጣቀሻ
  1. http://onesimusonline.blogspot.com/2010/08/struggle-for-soul-of-ethiopian-orthodox.html
  2. ibid
  3. http://webtest.sim.org/frontend_dev.php/opportunity/8346ibid
  4. http://www.firstpresyakima.com/MC_Teusink.cfm?m=f
  5. http://onesimusonline.blogspot.com/2010/08/struggle-for-soul-of-ethiopian-orthodox.html
  6. http://www.bosnewslife.com/9573-ethiopia-court-releases-jailed-evangelists
  1. http://tehadiso.blogspot.com/
  2. http://tehadiso.blogspot.com/
  3. Deje Selam
  4. http://www.dejeselam.org/2010/12/blog-post.html
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)