December 9, 2010

የመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው አዲስ የጡመራ መድረክ

መልአከ ሰላም ደጀኔ ከልጃቸው ከዲ/ን አትናቴዎስ ጋር
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ በግሩም ስብከታቸው እና በጠንካራ ጽሑፎቻቸው ለረዥም ዘመን ምእመናንን በማስተማራቸው የሚታወቁት መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ከመስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም (ኦክቶበር 5/2010) ጀምሮ አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። 


መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው የሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች በተለይም አሁን አሁን ከብዙ ሰባክያን አንደበት እና ከስብከት አደባባይ (ዐውደ ምሕረቶች) እየራቀ የመጣው የነገረ ሃይማኖት በተለይም የነገረ ቅዱሳን ጉዳይ በመሆኑ ደጀ ሰላማውያን በሙሉ እንዳያመልጣቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።

http://betedejene.blogspot.com/


ደጀ ሰላም የአማርኛውን የጡመራ መድረክ ፈር ከቀደደች ወዲህ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ዙሪያ ጽሑፎችን የሚያስነብቡ መጦመሪያዎች የተከፈቱ ሲሆን ከነዚህ መካከል የዲ/ን ዳንኤል ክብረት "የዳንኤል እይታዎች" እና የመልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድህን መጦመሪያዎች በሰፊው አንባቢ በማግኘት ላይ ናቸው። መልአከ ሰላም ደጀኔም የአንባብያንን ምርጫ በአንድ ቁጥር ከፍ ስላደረጉት ደስ ብሎናል። ይበርቱልን!!!!!

የመልአከ ሰላም ደጀኔን ትምህርቶች ለማዳመጥ፦
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን 

26 comments:

ledet Z awasa said...

Great NEWS

Senetebekew yeneber

Aragaw Ewnetu said...

We are so lucky.

Anonymous said...

God Bless You!

Anonymous said...

yedelhu yemeyasebel new erjim edemena tena yisetelen Melake selam Abatachen Ejeg Betam Emakeberachehew Hiwot Lewach Temheretachew Egziabeher Kekifu Negr Hulu Yitebekelen Melake Selam Qsis Dejene Shefraw Amen:: Des Yemilew Neger Sewn Gera Yagabaw Ye Dejeselam Yemanat Neger Ahun Eyetgelete Metewal Amelakachen Min Yisanewal Mahebre Kidusanoch Atefru Nfesn Liyatefa Yemechelewen Amelak Firu Yegna New Belu Atferu Bimeta Eko Mot New sele Emenetachehu Atefru Eskemeche Tedebeko Atefru Dani Lelochem Yibekagn Egziabehr Ke Enanete Gar Yihun

Anonymous said...

በጣም ደስ የሚል ዜና ነው። የመላክ ሰላምን የአገልግሎት ዘመን ያርዝምልን። ደጀ ሰላሞችም ይህንን ዜና ስላቀረባችሁልን እናመሰግናለን።

ቤተ ክርስቲያኖቻችንም ይህንን አርአያ ቢከተሉና የጡመራ መድረክ ወይም ድረ ገጽ ቢኖራቸው በዚሁም ህይወትን የሚያንጽ ትምህርት ቢያስተላልፉበት ጥሩ ነው እላለሁ።

Kiduse wwek MS said...

ደጀ ሰላሞች ቸር ወሬ ያሰማችሁ፡፡

እግዚአብሔር ይመስገን እጅግ በጣም በጣም ተደስተናል፡፡

Anonymous said...

ኧረ ቤተ ደጀኔን ለማግኘት በጣም ቸኩለናል፡፡

ቤተ ደጀኔ የሚለውን ስንከፍት ምንም ማግኘት
አልቻልንም ፡፡ ትክክለኛውን የዌብ ሳይት አድራሻ በፍጥነት አውጡልን፡፡ አደራ፡፡

Unknown said...

http://betedejene.blogspot.com/

lewtayehu said...

በእውነት ታላቅ የምሥራች ነው። ክብርና ምሥጋና ለእመቤታችንን ይሁንና ስሟን ለመጥራት የተራራ ያህል የከበደባቸው ፣ የቅዱሳን አባቶቻችንን ገድልና ተአምራት አልዋጥላቸው ያላቸው ፤ ከእኛው መንጋ የነበሩ ነገር ግን ያልሆኑ እንግዲህ ምን ይውጣቸው ይሆን? አባታችን ጅማሪዎን እግዚአብሔር ያስፈጽምዎ። ደጀ ሰላማውያንም አባቶቻችንን እንዲህ አበረታቱልን።
ዲያቆን ዳንኤል - - - - - መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ - - - - - - መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው _ _ _ _ _ _ ቀጣዩስ የእመቤቴ ወዳጅ ማን ይሆን? በቅርብ እንጠብቃለን። እግዚአብሔር የአገልግሎታችሁን ዘመን ለእኛ ለደካሞቹ ሲል ያርዝምልን።

Anonymous said...

there is also an address www.kesisdejeneshiferaw.com from Google and the address you gave us is a different one. plz clarify which is kesis's.

Anonymous said...

The Blog Bete Dejene is not working
give us the exact site address

Unknown said...

Sometimes Blogs at blogspot.com, like that of Kessis Dejene could be difficult to access. We reccomend Melake Selam Dejene to change the venue to a .com or .org address. Otherwise, it is working for those who are out of Ethiopia.

Wudasse wwek MS said...

እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

በጣም ከመደሰቴ የተነሳ ፎቷቸውን ፕሪንት አድርጌ ሳም አደረኩት፡፡

ቀሲስ ዌብ ሳይቱ ኢትዮጵያ የማይሰራ ከሆነ ግን ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታችን ነው፡፡

ጥለውን ሄዱ ደግሞ ዌብ ሳይቱንም ለአሜሪካ ብቻ ሊያደርጉት ነው ?

አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጡን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡

Anonymous said...

This so great job indeed! But the bog doesn't work in ethiopia.however it functions with moblile phone. I don't know why. Please dear father try to correct your blog in appropriate form so that all can view it and benefit from it.

ይሁና said...

ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ይሏል ይህ ነው። ማነው ባለ ሳምንት? ከብጹዓን አባቶቻችን አንዱ? ቀሲስ መምህር ብርሃኑ ገበና(የማዕረግ ስማቸውን ስላላወኩ ነው)? ዲ/ን ኤፍሬም?

Anonymous said...

ይህ አገልግሎት የወንዶች ድርሻ ብቻ አይደለም። እህቶቻችንም እየተሳተፉበት ነው። ለምሳሌ፡
http://www.mahletzesolomon.com/

ዲበኩሉ said...

ሰላም ለደጀ ሰላማውያን በሙሉ! አኔ ትንሹ ወንድማችሁ በዚህ ብሎግ እጅጉን ከተጠቀሙት ሰዎች አንዱ ነኝ!በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎችናና ሰዎች የሰጡዋቸውን አስተያየቶች በሙሉ አነባቸዋለው አንዲሁም ለሌሎች አካፍላለሁ ረድቶኛል አባካችሁ መቼም በነዚህ ሁሉ መረጃዎች እንደኔ የሚደሰቱ ብዙ ቢሆኑም እውነቱ የማይዋጥላቸው ጥቂቶች ( ከ በ/ክያን ውጭ ወይም ውስጥ ያሉ) አፍራሽ አስተያየቶችን ሊጽፉ ቢችሉም ስለ ብዙዎች ምስኪን የእናንተን መረጃ ስለሚጠብቁ ብላችሁ እና ከሁሉም በላይ ብርታት ስለሚሆን እግዚአብሔር ብላችሁ በርቱ ተበራቱ ወላዲት እምላክ ክእናንተ ጋር ትሁን

ዲበኩሉ ክጎንደር

Anonymous said...

To all readers and DS,
Don't blame me when I post my suggestion.
Firstly, I appreciate kesis Dejene and other persons who are trying to serve people through blogs. However, I am strongly afraid of that we people may reject going to our holy church to get blessings, looking holy Icons, listening hymn, attending the Mass, attending Sunday school & preaching in the church.... Besides, spending time in the environment of the church has greatest positive influence in our spiritual likelihood.
When I say so, I don't mean I am against them but we have to look things critically rather than saying "good, good, and good!"
It may not have a problem for those once impaired physically and the aged persons. Even for us, we can be beneficiary from blogs during our rest hours but the problem is, as the saying of the forefathers, " Hatiat sidegagem ende tsedk yikoteral: when sin is adapted, it is regarded as righteousness"; accordingly, we may be associated only with blog contributions. I also mean while we always stay with using internet, we will miss going to the church. Then, nothing will separate us from Protestants...
Orthodoxia-Theologian

Girma Kassa said...

Selam to All of You in the Name of our Lord Jesus Christ the Savior!
I have different view from most of you. I don’t think it is that much important to open many orthodox blogs here and there. It is enough if we have three to five well known and matured blogs that are active. People usually start blogs (even I was having a blog writing for some time but could not continue) but will not continue due to different cases. It is good if people can consistently update their blogs like dejeselam which has run for four years.
As to me if we want to help the orthodox society, we need to have focused and organized blogs. Let me describe some important issues that we have to raise and focus.
1. Dogmatic and canonical issues
2. Frequently asked questions / I tried to blog on this issue but could not continue/ anyone having time and energy to do can continue. I can give the password.
3. Spirituality and Christian life related issues
4. Christian social life issues
5. Church history and monastery related issues
So instead of opening many blogs let us have organized websites and blogs that can give full information about the church and answers the questions raised by Christians.
www.Ethiopianorthodox.org and www.tewahedo.org provide good information and hope they have many followers.

Anonymous said...

Deje Selamoch,

I think it would be much much better if they have done this as a web site/blog site of the church they are serving.

We need to work on capacity building of our churches. That is one of teh problems we are facing in our institiutions: Strong personalities and weak insitutions.

Anonymous said...

I agreed with Girma's point.Too many blogs=???no good

Abrha said...

Abrha
ቃለ እግዚአብሔርን ከምንጩ ሲጠጡት እንዴት ይጣፍጣል! ቀሲስ ደስ ብሎናል፡፡

ከላይ በደጀ ሰላም አድረሻ በመምረጥ በኩል የተሰጠዎት አስተያየት ጠቃሚ ነው፡፡

ሌሎች ወንድሞች በተከታታይ የሰጡት አስተያየትም በቅንነት ሊታይና ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡

Anonymous said...

it is not working in ethiopia please try to adjust it.

Anonymous said...

The bog is changed to www.betedejene.org and it is functioning in Ethiopia too.

Unknown said...

Le kiristina mageligen melkam new. neger gin internet lay ketetekelin gin wede betu heden dejun lemesalem gize enatalen. silezih bebetu tegegnto begara mezemer masqedes kidan madiresunina leloch negerochinim alemerisat new. Egziabher amilkak haymanotachinin yitebikilin.

Amen

Anonymous said...

ጁላይ 7/12/2011
ሰላም የደጀሰላም አዘጋጆች:
ደጀሰላሞች ባላችሁ የቅድስት የቤተ ክርሲቲያን ቀናይነት እና የቤተ ክርስቲያን ልጅነት እና ውሸትሳይሆን ሚዛናዊ የሆነ ዜና ማሰማታችሁ በጅጉ የሚያኮራ ነው::ከዚህ በተረፈ ግን የኔ ጥያቄ ለአባ ጳውሎስ ነው;; አባ ጥያቄ ልሰነዝርልዎት እፈልጋልሁ መለስ ግን እንደማይሰጡን አምናለሁ ግን የተሰማኝን መሰንዘር ግዴታ ሰላለብኝ ነው:: አባ ልጠይቅዎ ለመሆኑ አባ እርስዎ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነወት? አይመስሉኝም ለምን ቢሉኝ ቀደም ሲል አሜሪካ ላይ የራስዎትን ሐይማኖት ከወርቶዶክስ እምነት በተለየ ያራምዱ እንደነበር ሁሉም ያውቃል እርስዎም ያውቃሉ:: ታዲያ በዚህ ስህተትዎት ሳይጸጸቱ እንዲያው በቅዱስ ማርቆስ ውንበር ለመቀመጥ በቂ ነኝ ብለው መቀመጥዎት ያሳዝናል ምንዎትም አይበቃም በዘር ወይም በወያኔነት ከሆነ በጣም ብቁ ነዎት በሁቁ ግን ብቁ አይደሉም ደግሞ አባ ለመሆኑ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እጅግ ብዙ ሊቃውንት ያላት መሆኑን እርስዎም ያውቁታል::ታዲያ ይህ ሆኖ እያል እርስዎ ምነው የሴት አማካሪና ጓድኛ አብጅተው ሊቅውንቱን ግራ ሲያጋቡ አያፍሩም ውይ አባ?የእውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ቢሆኑ ኑሮ እስኪ የመልክቱት ቢያንሴ ከጎን አስቀምጦ ሊቃውንቱን ቅኔ ተቀኙ ዜማ ደርድሩ በማለት ጥላ አስይዞ አውደምህረቱን ማስደፈር ይገባል ውይ?አባ! አባ ማለቴ ይቅርታ ለምን ቢሉ እርስዎ በጠበንጃ እንጅ በትክክል ተፈልገው የመጡ ወይም ሀይማኖትውት ብቁ ባለመሆንዎት ነው:: አገባብዎ የነፍጥ በመሆኑ ነው::
ወደ ህሊናዎት ይመለሱ እላለሁ አባ
ትርሲት ነኝ::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)