December 8, 2010

ገዳማትን እና አድባራትን ለመታደግ በለንደን የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ተካሄደ

(ለደጀ ሰላም ታምሩ ገዳ - ለንደን):- በኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚገኙ  ገዳማት አድባራት እና የአብነት/ቤቶችን  (የቆሎ /ቤቶችንውድመት ለመታደግ የታቀደ  የገንዘብ  ማሰባስብ ፕሮግራም  ለንደን ውስጥ  ተካሄደ ፡፡ የፕሮግራሙ  ዋንኛ ተዋንያኖች ሆኑት የማኅበረ  ቅዱሳን  አባላት  ከዚህ ቀደም ያበረከቱት  እና አሁንም  እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ  ለበርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት  ተከታዮች ከፍተኛ አርአያ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ባለፈው ዳር 12 2003 ዓ.ም (ኖቬምበር 22/2010 እ.ኤ.አ)   በለንደን  ከተማ  እና  አካባቢዋ  በሚኖሩ  //// በሰንበት  /ቤቶች  ማደራጃ  መምሪያ  የማኅበረ  ቅዱሳን  አባላት   እና  በመዲናይቱ  ውስጥ  ታዋቂ  ከሆኑት የኢትዮጵያ   ሬስቶራንቶች መካከል  በቀዳሚነት  የሚጠቀሱት ስንቄ እና ቅ/ገብርኤል በተባሉ ሁለት ሬስቶራንት ድጋፍ (ስፖንሰርነት)   የተዘጋጀው  ይሄ  የገንዘብ  ማስባሰብ ፕሮግራም ላይ ለመገኘት  ከምድር አሜሪካ  የመጡት  በኦሃዮ  ኮሎምቤያ   የቅዱስ ገብርኤል  ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ  ያሬድ  /መድ በኢትዮጵያ  ውስጥ የሚገኙ  ገዳማት  እድባራት  እና የአብነት ትምህርት ቤቶች በተለያዩ  ጊዜያት  በተከሰቱ ተፈጥሯዊ  እና ሰው ሰራሽ  ምክንያቶች  የተነሣ  ለውድመት፣ ለዝርፊያ  እና  ለመበታተን  አደጋዎች ተጋልጥው እንደሚገኙ አውስተው  በቅዱስ  መጽሐፍ (መዝሙረ ዳዊት 67: 1) ላይ  “ኢትዮጵያ   እጆቿን ወደ እግዚአብሔር  ትዘረጋለችተብሎ  በተጠቀሰው  መሠረት ኢትዮጵያውያን  ለፈጣሪ ቅርብ በመሆናቸው  በተለያዩ ዘመናት  የተከሰቱ ችግሮች በእግዚአሔር ቸርነት  ቢቀዘቅዙም   እነዚህ  በገንዘብ ሊተመኑ  የማይችሉ  እና መተኪያ  የሌላችው   የሀገር ሀብቶች የአምልኮት  እና  የዕውቀት   መሠረቶች ከፍተኛ የሆኑ  ችግሮች እየተፈራረቁባቸው  እንደሚገኙ” አስታውቀዋል::    

“ከኢኮኖሚያዊ ችግሮች አኳያ በቀን አንዴ እንኳን መብላት የተሳናቸው መነኮሳት፣ መምህራን እና የአብነት ተማሪዎች
 እየተበተኑ  ይገኛሉ፡፡ ከሃምሳ  ዓመታት  በላይ  ያገልገሉ መምህራን ቢታከሙት  በቀላሉ ሊድኑት በሚችሉ  ደዌዎች ተይዘው  በቤት ውስጥ ከአልጋ  ላይ የዋሉበት ብዙ አጋጣሚዎች ሉ፣ የመንፈስ ልጆቻቸውም  ቢሆኑ  መምህራኖቻቸውን ለማሳከም አቅም ቢያጥራቸውም የመንፈስ አባቶቻቸውን  ጥለዋቸው ላለመኮብለል  በመወሰን እዚያው ባሉብት አብርዋቸው መከራን  የተጋፈጡባቸው  በርካታ  አጋጣሜዎች  አሉ”  ሲሉ  ለተሰባሰቡት ምእመናን ገልጸዋል፡፡ 


እነዚህ  በአገር ውስጥ  ሆነ በዓለማቀፍ  ደረጃ  የኢትዮጵያን ስም ያስጠሩ  ታዋቂ  የጥበብ  ሰዎች  መፍለቂያ   የሆኑትን መምህራን እና  የአብነት /ቤቶች  መታደግ  የሁሉም   የእምነቱ  ተከታዮች ሃይማኖታዊ   እና የዜግነት  ግዴታዎች  መሆኑን የጠቀሱት   ቀሲስ  ያሬድ በተጨማሪ  ከዚህ ጸሐፊ ጋር ባደረጉት  አጭር  ቃለምልልስ   በለንደን የሚኖሩ ምእመናን  እነዚህ  አስታዋሽ እና ትኩረት  ተነፍጓቸው የቆዩት  ገዳማት፣  አድባራት እና  የአብነት /ቤቶች እገዛ እንዲያገኙ  ጥረት ማድረጋችው  በጥሩ አርአያነት  ሊጠቀስ  ይገባል ብለዋል፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን  መሠርታዊ እና ዘለቄታ  እገዛ ያስፈልጋቸዋል  ብሎ ሰፊ ጥናት  በማድረግ  እና ጥናቱንም በሚመለከታቸው  ባለሙያዎች በማስገምገም   እና ፕሮጀክቶቹንም  ከአካባቢ እና ከተጠቃሚው ብረሰብ ጋር  ባራዊ  ሁኔታዋች ጋር  በሚስማሙ መልኩ እንዲከናወኑ በማድረግ  እነዚህ በችግር ላይ  የሚገኙ የቤክርስቲያኒቱ  ውድ ሀብቶች ተገቢውን   ትኩረት እና ርዳታ እንዲያገኙ ከበጎ አድራጊ ምእመናን ጋር በማገናኘት  ላይ መሆኑን   ያስረዱት ቀሲስ ያሬድ  በተለያዩ የልማት  ሥራዎች ላይ   የሚውለው  ገንዝብ  እና ማቴሪያል ግልጽነት እና ተጠያቂነት  ባለው  መልኩ የሚተገበር  በመሆኑ  በርካታ ምዕመናን  የጥናቱን ውጤት እንደ ራሳችው  ሥራ አድርገው  በመውስድ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት  ወዘተ እያገዙ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡


በማያያዝም  የምዕምናን እና የአስተባባሪዎቹ  ማኅበረ ቅዱሳን ጥምረት መፍጠር በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ  ችግሮች  እየተፈቱ የሚገኙትን   ገዳማትን  ነገ ቅኔ ማህሌቱን  የሚመሩት ነገ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው የቅ/ሲኖዶስ አባላት  ሆነው ክርስቲያንን የሚመሩ አባቶች የሚወጡባቸው  የአብነት  /ቤቶችን  ከመጥፋት መታደግ  ይገባናል በማለት ተማጽኗቸውን  አሰምተዋል::

በስተመጨረሻምእኛ  በከተማዎች ውስጥ  የምንኖር የተዋሕዶ ልጆች  እየበላን እና  እየጠጣን ስለእኛ ቀን እና ሌሊ  ሲጸልዩ የሚኖሩት   ቅዱሳን አባቶች  በእንደዚህ ፈተና ውስጥ ወድቀው  ማየት  የለብንም።  መሐሉ ሰላም የሚሆነው ዳሩ በጸሎት  ሲታጠር ነው።  አንድ ገዳም ተፈታ ማለት  የእኛም  በገዳሙ ውስጥ ያለን ሕይወት በአጭሩ ተፈታ ወይም ከባድ መከራ ላይ  ወደቅን ማለት  ነው።ስለዚህ  የዚህች  ቤተ ክርስቲያን  ችግሯን  ማየት የማይፈልጉ የቤተክርስቲያን ልጆች  ጊዜ እና  ቦታ ሳይወስናቸው  ሊተባበሩ  እንደሚገባቸው  እና  በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ይሁን ሌሎች በጎ በራት በሚያዘጋጇቸው  ተመሳሳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ክርስቲያኒቱ ያለባትን ችግር ( የገዳማትን እና የአድባራትን ሁኔታ) ተገንዝቦ ለመርዳት  ጥረት ማድረግ ይገባል ብዬ አስባለሁብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ከነበሩ ምዕመናን በከፊል

በለንደን  ከተማ  የቅድስት ላሴ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ዲያቆን ሚሊዮን አጀበ በዚሁ የገንዘብ ርዳታ ፕሮግራም ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ያካሄዳቸው ወይም   እያካሄዳቸው የሚኙትን  የልማት እንቅስቃሴዎች  እና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በቻርት  እና በምስል  የተደገፈ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። ለርዳታ  ከታጩት  ፕሮጀክቶች  መካከል  የአባ ዮርጊስ  ዘጋስጫ ገዳም  (ደቡብ ወሎ ከለላ ወረዳ  የዛሬ 600 ዓመት ገደማ  ከአንድ  ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ክርስቲያን ነውእና   በከፋ /ስብከት  ቦንጋ ከተማ  አቅራቢያ  የሚገኘው ኪያ  ኬላ አቡነ  ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተጠቃሽ ናቸው::

ገለጻውን ተከትሎ ምዕመናን  በግል እና በቡድን ሆነው  አቅማቸው  እንደፈቀደው ርዳታ እንዲያደርጉ በቀረበው ግብዣ  መሠረት   ግምቱ ወደ አምስት ሺ ፓውንድ እና የአንገት ሐብል እና የእጅ ብራስሌት  ርዳታ ተበርክቷል፡፡  ገዳማቱ እና አድባራቱ የተደቀነባቸው ወቅታዊ ችግሮችን ልባቸውን  ከነካው ምዕመናን መካከል  የለንደን ከተማ  ነዋሩ የሆኑ  አቶ ፍስሐ  የተባሉ  በበኩላቸው  በማኅበረ  ቅዱሳን  ሐሳብ አቅራቢነት  ከተመረጡት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱን  በራሳቸው  ወጪ ከፍጻሜ  ለማድረስ በምዕመናን  ፊት ቃል ገብተዋል::
ከግራ ወደ ቀኝ  ቀሲስ ያሬድ ገመድኅን  ብፁዕ አቡነ እንጦንስ  መልአከ ገነት ቀሲስ ከፍያለው አስቻለው
በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የተገኙት  በኢ//// የሰሜን ምእራብ  አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ  እንጦንስ  በማኅበረ ቅዱሳን  እና  በምእመናን  አማካኝነት እየተደረጉ ያሉ ገዳማትን፣ አድባራትን  እና የአብነት  /ቤቶችን  የመታደግ ርብርቦሽ በጣም የሚመሰገን እና ለሌሎችም ወገኖች ጥሩ አርአያ ሊሆን የሚችል  ተግባር  እንደሆነ ተናግረዋል:: ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ  የተመሰገነ ነው የሐዋርያት 20:35 መጽሐፍ ቅዱሳዊ  ጥቅስን ዋቤ  ያደረጉት  ብፁዕነታቸውእግዚአብሔር ሰጪ  እኛ  ተቀባይ ስንሆን  ዛሬ ደግሞ እናንተ ሰጪ እግዚአብሔር በተራው  ተቀባይ መሆኑን በመገንዘብ  ያደረጋችሁትን አስተዋጽዖ ፈጣሪ ይቆጥርላች”  በማለት ምስጋና አቅርበዋል::  

ንግግራቸውን በመቀጠል የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሃይማኖታዊ ተጋድሎን በተመለከተ ሲያብራሩከዚህ ቀደም እያንዳንዳችን ጳጳሳት ከደሞዛችን 15% በማዋጣት  የተጎዱ ገዳማትን አድባራትን  እና የአብነት /ቤቶችን ለማገዝ  እንድናዋጣ  ተደረገ፡፡ በአዲስ አበባ  የሚገኙ አድባራት  በዓመት  ክብረ  በዓላቸው  ከሚሰበሰቡት  የገንዘብ መዋጮ ፈሰስ  እንዲያደርጉ ቢወሰንም ከችግሩ ስፋት  የተነሳ   የተጠበቀውን ያህል ውጤት አልተገኘም”  ያሉት አቡነ እንጦንስ  “እግዚአብሔር  ይመስገን  እና እነዚህ የመንፈስ ልጆቻችን  (በረ ቅዱሳንቅዱስ ሲኖዶስ  ያልደርሰባቸውን  አካባቢዎች እና ችግሮቻቸውን   በግንባር በመገኘት  አኩሪ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ:: እግዚአብሔር በረ ቅዱሳንን በማሥነሣት  ይህንን የመሰለ  ትልቅ  እና አኩሪ  ሥራ እንዲሰራ በማድረጉ ክብር ምስጋና ይገባዋል::  የአብነት መምህራን ከሌሉ ክርስቲያን የለችም።”

በገዳማት  ያሉ አባቶች በቀን አንዴ እንኳን ዳቤ (ዳቦ) ስለሚያስፈልጋቸው  ዛሬ የምታደርጉት ስጦታ (ርዳታለሃይማኖታችሁ፣ ለታሪካችሁ እና ክርስቲያናችሁ  መሆኑን   በመረዳት  ያደረጋችሁት  እገዛ  ያስመስግናችል”  በማለት ለሁሉም ተሳታፊዎች  ያላቸውን   ታላቅ  ድናቆት  እና እክብሮት  ገልጸዋል፡:


የገዳማት  አድባራት  እና የአብነት /ቤቶች  ወቅታዊ ችግሮችን  ለምዕመናን በማሳወቅ  እና ግንዛቤ በማስጨበጥ  በኩል  በለንደን /ላሴ ክርስቲያን  ከወራት በፊት አዘጋጅቶት በነበረው  ዓመታዊ  የስብከተ ወንጌል ፕሮግራም ላይ  ሰፊ ገለጻ አድርገው የነበሩት   አቶ በላቸው  ጨከነ  የተባሉ ምዕመን  ከዚህ ፀሐ  ጋር  ባደረጉት  ቃለ ምልልስ  እንደገለጹት  “ምዕመናኑ  የቤክርስቲያኒቱ  ችግሮችን እንደራሳቸው  ችግር በመቁጥር  ያደረጉት  መዋጮ የሚያስመሰግናቸው ሲሆን ወደፊትም  ቢሆን ተመሳሳይ   የግንዛቤ እና የርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራሞች ቢካሄዱ  የበለጠ  ውጤት እንደሚኖር ያመላክታል”  ብለዋል::


በገንዘብ ማሰባስቡ  ፕሮግራም ላይ የተገኘች ነገር ግን ስሟ  እንዳይገለጽ የጠየቀች አንዲት ምዕምን  በበኩሏየማበረ ቅዱሳን አባላት እያደረጉት  ያለውን  መልካም  ተግባር  ከሃይማኖት  አባቶች  ዘንድ  በእንደዚህ መልኩ  መገለጹ እና ቡራኬ ማግኘቱ  ለአባላቱ  ታላቅ   መንፈሳዊ ክብር  ሲሆን  ለእኛም  ቢሆን    በሩ ምን ያህል ተጠያቂነት  እና ግልጽነት  ባለው መልኩ  ወደፊት  ምን መሥራት  እንዳለብን  መንፈሳዊ ብርታትን  እንድናገኝ ይረዳናልብላለች::

1985 ዓ.ም ጀምሮ መንፈሳዊ  አገልግሎቱን  በስፋት  የጀመረው በረ ቅዱሳን  2003/4 በጀት ዓ.ም  ብዛታቸው 92 የሚደርሱ  በተለያዩ የአገሪቱ  ክልሎች  ለሚገኙ  የአብነት  መምህራን እና ተማሪዎች መጠነኛ  ወርሃዊ ድጎማ ለማድረግ እቅድ ይዟል:: 2002/3 ዓ.ም በጀታቸው  በአማካኝ 68,000 ብር እስከ 255,000  ብር  የሚፈጁ አሥራ ሁለት የልማት  ፕሮጀክቶችን  ተግባራዊ  ለማድረግ በአጠቃላይ  2003 ዓ.ም በማኅበሩ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ  ዕቅድ እንደተያዘ ታውቋል::

ይህን የአብነት ት/ቤቶች እና ገዳማት ለመርዳት ለሚፈልጉ ምዕመናን 
በስልክ +251-11-1553625 +251-11-1553625       251-91-175 15 29
ባንክ: A/C No 0173060464000
        CBE, Arat Kilo Branch

 E-mail Head office :   gedamat-mk@yahoo.com
Europe
Centre:        muya-agelglot@mkeurope.org
America Centre      etcmkusa-service@yahoo.com
web page:         www.eotc-mkidusan.org
 
በኩል
የበኩላቸውን  እገዛ እንዲያደርጉ  አዘጋጆቹ መንፈሳዊ ጥሪያቸውን  አቅርበዋል::

ለግንዛቤዎ
 ቢረዳዎት፦
 ፠ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከሚመጡት ቱሪስቶች መካከል 85% በላይ  አመጣጣቸው የቤክርስቲያን  ሀብትን ለማየት ነው።
፠ ገዳማትና
የአብነት  /ቤቶች እስከ 1908 ዓ.ም ድረስ “የትምህርት ሚኒስቴር” ሆነው አገለግለዋል።
፠ እጅግ ውድ የሆኑ 3064 በላይ  ንዋየ ቅድሳት እና የብራና መጻሕፍት በሥርቆት ተወስደው በውጪ አገር አብያተ መጻህፍትይገኛሉ።
፠ ኢትዮጵያ
  በአፍሪካ የራሷ የሆነ ፌደል እና አሃዝ ያላት ብቸኛ ሃገር ነች።
የኢ//// 400 000 በላይ አገልጋዮች  በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር  አሏት
፠ በኢትዮጵያ
ውስጥ 37 ሺህ በላይ ገዳማት አድባራት እና አብያተ ክርስቲያን አሉ።
፠ የኢ
//// 40ሚሊዮን በላይ ክርስቲያን ምዕመናን በመያዝ በአፍሪካ አንደኛ በዓለም ሁለተኛ ደረጃላይ ትገኛለች።

( ምንጭ : አቶ በላቸው ጨከነ በቅርቡ  ለግንዛቤ ማስጨበጫ  ይረዳ ዘንድ ካሰባሰቧቸው መረጃዎች የተወሰደ )

21 comments:

Unknown said...

Good Job Londons may God Bless You all. Everyone should contribute his own share in order to solve the problem step by step. In addition to contributing money we have to also try to modernize our monasteries like the Copts. I hope MK is having these types of projects. Most monasteries are trying to implement good agricultural project which can be done easily in most places.

lewtayehu said...

ምንም እንኳን በቤተ ክርስቲያኒቷን ተምረው ፣ አፋቸውን ፈትተው ፣ ለቁም ነገር በቅተው ፤ ዛሬ ያን ሁሉ ውለቷዋን ወደ ኋላ ትተው ገዳማቷንና አድባራቷን ሊያፈርሱ ፣ የአብነት መምህራኑን ሊበትኑ እንደ ወዳጃቸው ዲያቢሎስ ሌትና ቀን ያለ እንቅልፍ የሚተጉ ቢኖሩም እግዚአብሔር ደግሞ እንደ ማኅበረ ቅዱሳንና መሰል ማኅበራትን በማስነሣት ሥራውን እየሠራ ይገኛል። እግዚአብሔር ለሁላችንም እንዲህ ያለውን ከልብ ተነሣሽነት ያድለን ።
አባታችን መልአከ ሰላም ያሬድ እንዳሉት እኛ በሰላም የምንኖረው በገዳም ያሉት አባቶቻችን በባህታቸው ጸንተውልን ስለእኛ ሲያልቅሱልን ነውና መልእክቱን በልባችን ጽላት እንጻፈው።

Lewtayehu ከ Denver

Gebre Eyesus said...

+++
ደጀ ሰላሞች እንደምን አላችሁ
ይህን የቤተክርስቲያንን ሕልውና ከሚያጸኑት ሥራዎች ዋነኛ የሆነውን አብነት ትምህርት ቤቶቻችንን የመደገፍ መልካም ዜና ስላሰማችሁን እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ከዚህ ቀደም በአብዛኛው ስማችሁ የሚነሳው መረጃዎችን ፣ ዜናዎችን በአሉታዊ ጎኑ እንደምትዘግቡ ነበር፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በአዎንታዊ መልኩም እየዘገባችሁ እንዳላችሁ የሚታይ ነው፡፡

የዛሬውን ዜና ሳነበው በጣሙን ደስ ነው ያለኝ፡፡ ምክንያቱም የእናንትም አንድነት የተንጸባረቀበት ነውና፡፡
ስለሆነም በዜናችሁ በምትሰጡን መረጃዎችና በመሳሰሉት ሁላችንን የተዋሕዶ ልጆች ወደ መንፈሳዊነት ፣ ራሳችንን እንደ ሦስተኛ ወገን ሳይሆን የቤተክርስቲያናችን አካል አድርገን እንድናይና ፍጹም መንፈሳዊ የሆነ አገልግሎት ፣ መንፈሳዊ ሕይወት ፣ ልማት…እንዲኖር የእናነት ሚና ቀላል እንደማይሆን አስባለሁ፡፡
ልክ እንደ ማኅበረ ቅዱሳንም በቅንነት ፣ በትህትና እንዲሁም በመንፈሳዊነት ፣ የቤተክርስቲያን አባቶችን አክብሮ ፣ መመሪያ ተቀብሎ ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ ፣ ቀኖናና ትውፊት ጠብቆ በታዛዥነት ለገንዘባቸው ፣ ለእውቀታቸው ፣ ለጉልበታቸው… ሳይሳሱ ለቤተክርስቲያናችን የሚሮጡ አባላትን ፣ መንፈሳዊ ማኅበራት ማጠናከር ፣ ማደራጀት ጠቃሚ ስለሚሆን ዘገባችሁ አዎንታዊ ሁናቴዎችን ማንጸባረቁን እንዲቀጥል አስተያየቴን እሰጣለሁ፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን
ገብረ ኢየሱስ
+++

Anonymous said...

ያለአብነት መምህራንና ገዳማውያን ጸሎት ኢትዮጵያ-ኢትዮጵያ አይደለችምና ማህበሩ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ እግዚአብሔር ብርታትን ይስጣችሁ፡፡ ለንደኖችም ፈጣሪ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ፡፡ ሌሎቻችንም የእነሱን ፈለግ ልንከተል ይገባናል፡፡ "ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብርስ ዥጉርጉርነቱን ይተዋልን?" መባል ይሄኔ ነው፡፡

Anonymous said...

40 ሚሊዮን የ ኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን ም እመናን ቁጥር መሆኑን አንዳንድ ሰዎች ሲጠቅሱ ማየተ አሳዝኖኛል:: ምክንያቱም ይሄ የታሪክ አጥፊው መንግስት እኩይ ደባ እንጅ እውነተኛ ቁጥር አይደለም:: አቡነ ጳዉሎስ እንኩዋን 50 ሚሊዮን ብለው ነው የሚናገሩ ዉጭ አገር ሲናገሩ እናንተ ምን ነካችሁ ? እንደ? እውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል አሉ! እያቀነቀናችሁ እኮ የወያነን እውሸት እውነት እያረጋችሁ ነው::
ስለዝህ ለማይታወቅ አሃዝ ባታቀነቅኑ መልካም ነው:: የኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን ም እመናን ቁጥር 40 ሚሊዮን ብቻ አይደለም !!!!!!!!!!!!!!!!!

ወልደ ዮሐንስ said...

Great job! keep working. Be'ente Simwa Le'mariam.
The students must not worry about their food and residential issues; we must rather primary sponsor for all what they need.

Z,yisma nigus said...

ንግግራቸውን በመቀጠል የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሃይማኖታዊ ተጋድሎን በተመለከተ ሲያብራሩ “ከዚህ ቀደም እያንዳንዳችን ጳጳሳት ከደሞዛችን 15% በማዋጣት የተጎዱ ገዳማትን አድባራትን እና የአብነት ት/ቤቶችን ለማገዝ እንድናዋጣ ተደረገ፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ አድባራት በዓመት ክብረ በዓላቸው ከሚሰበሰቡት የገንዘብ መዋጮ ፈሰስ እንዲያደርጉ ቢወሰንም ከችግሩ ስፋት የተነሳ የተጠበቀውን ያህል ውጤት አልተገኘም” ያሉት አቡነ እንጦንስ “እግዚአብሔር ይመስገን እና እነዚህ የመንፈስ ልጆቻችን (ማኅበረ ቅዱሳን) ቅዱስ ሲኖዶስ ያልደርሰባቸውን አካባቢዎች እና ችግሮቻቸውን በግንባር በመገኘት አኩሪ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ:: እግዚአብሔር ማኅበረ ቅዱሳንን በማሥነሣት ይህንን የመሰለ ትልቅ እና አኩሪ ሥራ እንዲሰራ በማድረጉ ክብር ምስጋና ይገባዋል:: የአብነት መምህራን ከሌሉ ቤተ ክርስቲያን የለችም።”

MAY GOD bless the service of ማኅበረ ቅዱሳን.አቶ ፍስሐ may God help u to keep ur promise.
Yitbarek Egziabher amlake abewine!!!!!!!!!!!!!!

mebrud said...

መዝሙረ ዳዊት
119፥126
ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው።

Anonymous said...

Since the work which was done is for the benefit of the church, I am in support of it and any of likewise but I am a bit surprised that the post is after the incident of one congregation which was held in DC last weekend for almost same purpose. I personally know that MK was doing lots of project and will do same in future but please let us not do this out of an envious feelings. And the other thing that I would like to ask DEJESELAM is that :.......
IS THERE A WAY THAT WE COULD KNOW WHO IS IN CHARGE OF THIS SITE??????......The reason why I am asking you guys is that as a chiristian one has to witness the truth without disguising his/her identity or without being anonymous. It might look a smart ideolgy for this earthly lives but it is definetly against the core belief of our faith and we cannot find this anonymity in our Holy Bible. If you guys are talking the truth and witnessing the truth, let us all know your contacts and who is liable for the web site. Otherwise ,in every action a human is doing that seems right and holy at the glance ,there will be a sin behind it. And by letting yourselves known to the fellow christians who are visiting your site ,you will be accountable for your post as a christian and your credibility will be at the top. otherwise this anonymity will put you guys on the side of the politician and protesters(protestants) who are always disgusing themselves in a church as a christian but who are always strife,hostile,jealous,envy towards the servant of God in the church and who always brings controversy or dissension in the church.

Anonymous said...

god bless you

Gebre said...

To the second from the last anonymous:

You being anonymous yourself, why do you ask who in charge of this site is? Don't you think you should start revieling yourself before asking others to reviel their identity? Why do you even bother to know who is doing what? You are being fed all the info about our church and that should be what you ought to care about, not the people maintaining the site. All you have to do is pray so that God will guide their mind and heart to do the right thing. God bless,

Gebre

Unknown said...

If we talk about Abinet Timhirt I want to mention somethings. As most of us know, currently it is very difficult for the church to get good Students that can finish the church teaching according to the current curriculum. The church should revise the content and the methodology of the Abinet Timhirt.

It is taking too long to finish a subject/field. In addition the student should remember each and every word he learnt.

I have some proposals which I prepared after interviewing people who pass through that system. For the church to be benefited from students, there should be some adjustment in the feature.

Anonymous said...

Dear Anony,who asked the contact detail of Dejeselamwian,

The site owners are already known by God, when they do something they will do in fear of God. Which you fear most? God or people, if you are real christain? I hope your answer is God. So why you need to know them...Try to do your share for our beloved Church, the cumlative will be greta...

Anonymous said...

Tewhado

Great job,

Can you take some step further please? You can conatct the responsible person... don not be tireed , go go..

yalewtefera said...

9ኛው አሰተያየት ሰጪ ስለ ደጅ ሰላም ማንነት መታወቅ አስፈላጊነት ጥሩ አስተያት ፅፎ ነበር፡፡ አያይዞም ደጀ ሰላም ተአማኒ እንድትሆንና እንደ ክርስቲያንም በእውነት ላይ ተመስርታ መረጃዎችን የምታቀርብ ከሆነ የሚያንቀሳቅሷት እነማን እደሆኑ እራሳቸውን ግልፅ ማድረግ እንዳለባቸው ፅፎአል፡፡ በጣም የገረመኝ ነገር ለደጀ ሰላም የሰጠውን አስተያት ለራሱ አልተጠቀመበትም፡፡ በቃል ከማሰተማር በምግባር ይሻላል!!! አስተያየት ስጪው የሚያምንበትን ፅፎአል ስሙን ቢገልፅ ጥሩ ነበር፡፡
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን

Anonymous said...

You Guys who are searching to know the owner of the blog, never you expect that you will be told. However, if you understand the advantage of blog, it is only to fill the gaps; then, immerse your hands accordinglly as I'm investing.

*When the Church is restored & rehablitated, everything has to be revealed for all.

Orthodoxia-theologian!

Anonymous said...

Comment on the issue,

Please donot run here there....

Anonymous said...

Go go go Deje Selam! Your service is great.

Anonymous said...

May God bless the work of these Mahibere Kidusan Association. Please let us know how we can help them.

Thank you DS
Zed

mebrud said...

Dear brothers
what a confusion it is.
why to search the moderator/Admin of this blog?
to attack or support?
it has cons and pros.

Let's focus on support of our beloved tewahdo church.
and stand against enemies.

Hopefully,GOD will lead us to the right and help us to know each other.

Searchers,may not find it easliy,if they missed an objective of this site.I suggest them to find the idea and interset.If the want they can.
I am still comfortable although I can see problems( even they are said problems in my level understanding).

Let's see the point from accountability perspective.

offcourse it is difficult to expect accountability from commenter.

mean while, i come to know that commenter are also becoming smarter in providing information.Thanks to GOD.
We better to keep on going with humility and christianity.

but i don't want to hide my consern about legal responsibility.

I think no body can appretiate a preacher to preach with out getting a license from a church.


I don't forget its advantage of anonimity.If we don't understand wrongly there is a point to be clear.

we should not be innocent only.
It may open a door of problem unknowngly.

I remeber one of the commenter/participant has tried to put a solution for anonimity on this blog.

so how can we reconsile the fear of lack of responsibility with the advantage of anonimity.

apart from this issue,
I don't feel comfortable with saying 40,50 milion ppl of followers.I prefer to count the quality.we can learn from coptic church brothers who are small in number but influencial.Don't forget that,only 120 families have reached the world to preach Gospel.

Abekahu.
keep me in your prayer(weldegebreal).

Anonymous said...

hey guys do not confused everyone is runing for his own agenda do not believe MK is runing for the church or for tewahido that is just B.S.Actually if we are talking frankly MK is cancer for the church.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)