December 9, 2010

የ"ፀረ-ሙስና" ቀን Anti-Corruption Day

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ ኅዳር 30 (December 9) ቀን በዓለም ደረጃ የሙስና አስከፊነት የሚዘከርበት ("ፀረ-ሙስና") ዓመታዊ ቀን ነው። የችግሩ አስከፊነት በተለይም በታዳጊ አገሮች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈጥር ከመሆኑ አንጻር ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተገቢ ነው። "ደጀ ሰላም" ማንሣት የፈለገችው ግን በጠቅላላው በኢትዮጵያ ስላለው ሙስና እና የንብረት ብክነት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችንን ጠፍንጎ ስለያዛት ዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ነው። ከላይ እስከ ታች በተዘረጋ የጉቦ፣ የሙስና እና የሀብት ዝርፊያ ዘመቻ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ መውደቋን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችንን በማስታወስ መፍትሔው ግን አሁንም ሩቅ መሆኑን አበክረን እናስታውሳለን።

የሀብት ብክነት እና ዝርፊያ በእኛ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የተጀመረ፣ በእኛም የሚቆም አይደለም። ቤተ ክህነቱ ከዚህ በፊትም እንዲህ ዓይነቱ ችግር ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን አሁን ያለው የቤተ ክህነቱ ንቅዘት ከላይ የጀመረ እና በዝርፊያው ውስጥ ያሉት ሰዎች ሳያፍሩ እና ሳይፈሩ እንዲፈጽሙት በር ከፍቶላቸዋል። በአጭር አነጋገር እሽቅድምድም ላይ ናቸው ሰዎች። ሩጫው "የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ" በሚለው ነው። ሙስናውን ለመረዳት የሰዎቹን የገቢ ደረጃ እና ያላቸውን ንብረት መመልከቱ በቂ ነው። 


በእጅ መንሻ ወይም በጉቦ አንድ የሥራ ቦታ ማግኘት፣ ጥሩ ገንዘብ በመስጠት ወደተሻለ ቦታ ዝውውር ማግኘት፣ ተጠያቂነት በሌለው መልክ ከአብያተ ክርስቲያናት ገቢዎች ላይ መውሰድ፣ በቤተ ክርስቲያን በሚሰሩ አንዳንድ ግንባታዎች እና ሌሎች ፕሮጄክቶች ወቅት ማጭበርበር ወዘተ በጣም ሰልጥኗል። መንግሥት እና የመንግሥት የሕግ ተቋማት የዝሆን ጆሮ ይስጠን፣ አላየንም አልሰማንም ብለው በተቀመጡበት ሁኔታ ጉዳዩ መስመር እየሳተ ነው። ችግሩ ዛሬ ለአንዳንዶቻችን አዲስ ሆኖ ሊያስደነግጥ ቢችልም ወደ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመጠኑ ጠጋ ላለ ለማንኛውም ሰው ግን ነገሩ የአደባባይ ምሥጢር ነው። 


ሁላችንም በየደረጃችን ሃላፊነት አለብን። በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ የተሰማራን ካህናትም ሆንን ምእመናን ሆንን በሰበካ ጉባዔዎቻችን ተመርጠን የምናገለግል፣ ባንመረጥም የተመረጡትን አገልግሎት የምንመለከት ምዕመናን በሙሉም  ቤተ ክርስቲያናችን ለቆመችለት ዓላማ የማይስማማ ለዚህ አስጸያፊ የሙስና ጥፋት መቆም የበኩላችንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።

Anti-corruption Day 2010: Talking about corruption is talking about our lives!

6 comments:

Asrat the Dilla said...

Awo yasfelgal gin endet? MENGEDU AKAHEDUNE ENENGAGERBET LEMAN ABET YIBALAL! MANES YISEMANAL? MANES YASFETSEMENLAL? eNDET ENA MINES ENADEREG YE MEFTHE HASAB KALE AKAFLUN.
ASRAT THE DILLA

ማን ያዘዋል said...

በዚህ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ያሚገኙ አንዳንድ መነኮሳት በተለያየ ጉዳይ የፓለቲካ ጥገኝነት ሳይቀር ጠይቀው ሲትዘን ከሆኑ በኃላ ተመለሰው አገር ቤት ይሄዳና ቤተ ክህነቱን ደጅ ይጠናሉ። እነዚህ መነኮሳት በዚህ እያሉ የአገሪቱን መንግስትና የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በአውድ ምህረት ሲያብጠለጥሉና እነርሱ ግን እውነተኛ መስለው ነው ለሕዝብ የሚታዩ ት። ሲሄዱም ባዶ እጃቸውን ሳይሆን በገለልተኝነት ስም ቤተ ክርስቲያኑን ከከፈቱት ጋር የድርሻቸውን ተካፍለው ይሄዳሉ። ኢትዮጵያ ደግሞ ይሄዱና ደጅ ይጠናሉ ለጊዜው ለካቴድራሎቹ አለቆች ለመሆን በኋላ ደግሞ ጳጳስ ለመሆን ነው። ከዚያ ምን ችግር አለ ዜግነታቸው የውጭ ነው በፈለጉ ጊዜ እየመጡ የድርሻቸውን እየመጡ ይወስዳሉ። ቤተ ክርስቲያን ለእንርሱ እንደ ካምፓኒ ናት። በፓለቲከኛቹ የማይታይ ቆብ በደፉ ደፋሮች ይህ ይታያል። አገሩን የከዳ ባለስልጣን ተመልሶ አገሩ ላይ ባለሥለጣን ሲሆን ወይምበየኤምባሲው ሲሾም አናይም። በኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ቤተ ክርስቲያኒቱን አገሪቱን የከዱ መነኮሳት ጳጳሳት እስከመሆን ሲደርሱና ለመሆን ሲያስቡ የሚደንቅ ነው። ለጵጵስና በሕይወታቸው ንጽሕናም ሆነ በእውቀታቸው ይህ ቀረህ የማይባሉ ከኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት አባቶች ጠፍተው ነው። ከአሜሪካና ከአውሮፓ መነኮሳት ራሳቸውን ለማወዳደር እጅ መንሻ ይዘው አራት ኪሎ የሚሰለፉት። እነዚህስ የቤተ ክርስቲያን የተባሉ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያኒቱን የመከራና የችግር ጊዜያቶች እንዲራዘም የሚያደርጉ አይሆንምን? ስለዚህ በመንግስት በበኩል ጸረ ሙስና ኮሚሽን ሲያቆቁም ለቤተ ክርስቲያንስ ማነው ጸረ ሙስናውን የሚያቋቁመው ቢሉ።
1 ቅዱስ ሲኖዶስ
2 እውነተኛ ካሕናት
3 ምዕመናን መረጃ
በመስጠት ለሚመለከተው ክፍል በመስጠት ቤተ ክርስቲያናችንን ከተደቀነባት አደጋ ማዳን ይቻላል። ጉቦ ሰጥቶ ለከፍተኛ ማዕረግ የሚደርስ አንድ አባት የቤተ ክርስቲያን ችግር እንደሚሆን ሳይታለም የሚፈታ ነው። በየቦታው ያሉትን ሕገ ወጥ መነኮሳት እንቅስቃሴን በመረጃ መያዝና ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚደርስበትን ሁኒታ ማመቻቸታ ያስፈልጋል።

መብሩድ said...

"ቤተ ክርስቲያናችን ለቆመችለት ዓላማ የማይስማማ ለዚህ አስጸያፊ የሙስና ጥፋት መቆም የበኩላችንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።"

ደጀ-ሰላም ፍሬ ሐሳቡን ብረዳውም፡፡
ቃላቶቹ የተሰደሩበትን ሁኔታ ግራ ያጋባል፡፡

'የሙስና ጥፋት መቆም'
ሙስና መቆም
ሙስና ለማጥፋትን መቆም
ሙስና እንዳይጠፋ መቆም
ሙስና ራሱ ጥፋት አይደል ደጃችን
ቢሆንም ወድጄዋለሁ ቢስተካከልም ሸጋዳ
ሰው ካልሰራ አይሳሳትም እንዲሉ አበው

Anonymous said...

To Manyazewal:
I don't know where you are stationed,but I tell you this. Lying about the immigration case or making money from preaching or around church is not an isolated act by the monks or bishops. It is worest by the deacons or married priest be it MK members or individuals.Some even have copied the western teleevangelism here in the states.
So, don't be consumed by some you might have conflict with.
If you are talking about corruption in EOC, get out of the box and think broadly. Otherwise you do'n get anywhere.
Thanks

Anonymous said...

Yekalkidanun tabot meziref yejemere kahin, le egiziabher mekedesha yetewatan genzeb yerasun misil yekome papas, be silet genzeb tejun yemiyankorekur yedebir astedadari ketefelefelebin eko betam koye. Yihenini gud badebabay balechin yewere akim enkuwan endanawegiz "AGAR DIRIJITOCH" zeb komew...Ahunis eyanidandachin behatiyat koshishen sigana demun eyekeledinibet bemengist masabebu yibika. Meftihew kelib niseha gebito kedemu nitsuh mehon bicha new. Gizew sideris balebetu erasu lenibiretu tsere-musina hono yiferidal.

sis

Anonymous said...

Re:ManYazewal
Do you know that this web site is viewed by all people around the world including by the non-believers/protestants???? One thing which I dont get these days especially those who are living overseas like us is that...we tend to put the iniquities/delinquencies of others on the media without knowing or realizing in what path of life we are in. Since we are called christian through our Lord Christ, we are obliged by the Love of Him to live and follow His pattern. Eventhough it is true that the dispute,grief,anguish or tribulation of our church are known to all, as a christian ,we have the approach that will take us to the solution. The verbal violence that we are taking right now or took before ,cannot be the solution. We need to condemn ourselves first and pick the spiritual weapons. Our verbal violence will inflame the situation and we dont find it in any kind of christian life and even not acceptable by the rationalists/pegans.

Verbal violence includes: withholding, defaming, criticizing, characterizing, trivializing, harassing, interrogating, accusing, blaming, blocking, countering, diverting, lying, berating, ordering, taunting, putting down, discounting, threatening, name-calling, and raging.

If a verbally violent person/group or web or blog, by means of lies, threats or propaganda, attempts to enlist you to bond with him/them against someone or some group, the group/person may appear to be on your side. But, in the end, they meant to exert power over you-power that will ultimately serve his or her purposes, not yours or the church.

So,Let us all curb from this kind of practice and abide by the guidelines of the Holy Bible rather than following our secular knowledge.

Bigeban

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)