December 29, 2010

የአባቶች ዕርቀ ሰላም ንግግር በጥር ሊጀመር ይችላል


  • በንግግሩ ቅድመ ሁኔታዎች ስምምነት ላይ ከተደረሰ በሁለቱም ወገኖች የተላለፈው ቃለ ውግዘት ይነሣል
  • የዕርቀ ሰላም ንግግሩን የሚያስተናብሩ ሽማግሌዎች ተመርጠዋል
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 29/2010 ታኅሣሥ 20/2003 .)በምዕራቡ ዓለም በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የሚደረገው የዕርቀ ሰላም ንግግር በመጪው ጥር ወር 2003 ዓ.ም አንድ የመገናኛ መድረክ በማመቻቸት እንደሚጀመር የቅዱስ ሲኖዶስ ምንጮች አመለከቱ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ታኅሣሥ 13 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ‹‹በባሕር ማዶ በሚገኙት አባቶችም ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፤ የዕርቀ ሰላም ንግግሩን በገለልተኝነት ያስተናብራሉ›› ብሎ ያመነባቸውን ሦስት ሽማግሌዎችንም መርጧል፡፡

December 24, 2010

በአባቶች ዕርቀ ሰላም ጉዳይ የተነጋገረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠናቀቀ

  • በስደት በሚገኙት አባቶች የተሾሙትን ጳጳሳት ለመቀበል ስምምነት ላይ ተደርሷል
  • ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የሚነጋገሩት የሰላም ልኡካን ተመርጠዋል
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 23/2010 ኅሣሥ 14/2003 .) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተጀመረውን የዕርቀ ሰላም ንግግር እና ድርድር ጉዳይ ለማስቀጠል በቀረበው ምክረ ሐሳብ (መርሐ ድርጊት) ላይ በመነጋገር ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በመንበረ ፓትርያርኩ ባካሄደው የአንድ ቀን አስቸኳይ ስብሰባ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተመረጡት እና ሰባት ብፁዓን አባቶችን ባቀፈው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሐሳብ ላይ ጠንካራ ውይይት በማካሄድ አጽድቆታል፡፡ በኮሚቴው ከቀረቡት የምክረ ሐሳቡ ክፍሎች መካከል በምዕራቡ ዓለም በስደት በሚገኙት አባቶች የተሾሙትን 13 ጳጳሳት ስለመቀበል እና ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል በዕርቀ ሰላሙ ላይ ስለሚነጋገሩት ተደራዳሪ ልኡካን የተነሣው ሐሳብ የጋለ ክርክር እንደተካሄደበት ተዘግቧል፡፡

December 22, 2010

ጎንደር ጥምቀትን በካርኒቫል ደረጃ ልታከብር ነው

በሔኖክ ያሬድ
 (ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Wednesday, 22 December 2010 11:14) ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ለመጀመርያ ጊዜ በጎንደር በካርኒቫል ደረጃ ለአምስት ቀናት እንደሚከበር የጎንደር ባህልና ቱሪዝም መምርያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌታሁን ሥዩም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን ለሦስት ቀናት ይከበር የነበረው የከተራ ጥምቀት በዓል በሁለገብ ዝግጅቶች ለአምስት ቀናት በብሔራዊ ካርኒቫል ደረጃ ይከበራል፡፡

December 19, 2010

የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት ከገና በፊት ሊፈቱ ይችላሉ

(በታምሩ ጽጌና በዘካሪያስ ስንታየሁ ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Sunday, 19 December 2010 12:31 ):-
በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞት፣ በእድሜ ልክና በዓመታት እስር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለገና ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በወቅቱ የፈጸሙትን የተለያዩ ወንጀሎችን በማመን እግዚአብሔርን፣ ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ እንዲጠይቁ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ላሉት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች እንዲለምኑላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፤ የሃይማኖት መሪዎቹ መንግሥትን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ይሁንታ በማግኘታቸው ሳይፈቱ እንደማይቀሩ ምንጮቹ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን ወክለው ይቅርታ አቀረቡ

(መ/ር መንግስተአብ አበጋዝ፤ ማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ):- የአራት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን የይቅርታ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አቀረቡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች ቅዳሜ ታኅሳስ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተገኝተው በሰጡት የጋራ መግለጫ ይህን የታሪክ ጠባሳ በአገራዊ ይቅርታና ዕርቅ መጨረስ ከሁሉ በላይ ታላቅ መንፈሳዊ አንድምታ ይኖረዋል ብለዋል።

December 16, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን የማዳከሙ አዲሱ ሴራና ተንኮል

(አዲሱ ተስፋዬ፤ ለደጀ ሰላም)፦ ባለፈው ወራት በቤተ ክርስቲያን ዙርያ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መንፈሳዊ ጥያቄና  የበጋሻው ክስ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን ደጀ ሰላምም ላይ ይሁን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ጦማሮች ላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከመግለጥ ውጭ የችግሮቹን ሥረ-መሰረት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ጥቂት ነበር። የኛዎቹ ሚዲያዎች ቢተውትም ሌሎች ሚዲያዎች ግን በጉዳዩ ላይ አስገራሚ ምስጢሮችን አስነብበዋል።

Atlanta Abo, Blogging

In the Name of the Father, the Son and the Holy Sprit, one GOD Amen!
Dear Dejeselamawians,
I have seen your recent post regarding the blog sites by Kesis Yared and Kesis Dejene and comments posted to it. I just want to point  to you that Mekane Hiwot Abune Gebre Menfes Kidus EOTC in Atlanta has been operating its own blog site since Sept 11/ 2010 (may be a first for an EOT Church). 

December 9, 2010

የመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው አዲስ የጡመራ መድረክ

መልአከ ሰላም ደጀኔ ከልጃቸው ከዲ/ን አትናቴዎስ ጋር
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ በግሩም ስብከታቸው እና በጠንካራ ጽሑፎቻቸው ለረዥም ዘመን ምእመናንን በማስተማራቸው የሚታወቁት መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ከመስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም (ኦክቶበር 5/2010) ጀምሮ አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። 


መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው የሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች በተለይም አሁን አሁን ከብዙ ሰባክያን አንደበት እና ከስብከት አደባባይ (ዐውደ ምሕረቶች) እየራቀ የመጣው የነገረ ሃይማኖት በተለይም የነገረ ቅዱሳን ጉዳይ በመሆኑ ደጀ ሰላማውያን በሙሉ እንዳያመልጣቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።

የ"ፀረ-ሙስና" ቀን Anti-Corruption Day

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ ኅዳር 30 (December 9) ቀን በዓለም ደረጃ የሙስና አስከፊነት የሚዘከርበት ("ፀረ-ሙስና") ዓመታዊ ቀን ነው። የችግሩ አስከፊነት በተለይም በታዳጊ አገሮች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈጥር ከመሆኑ አንጻር ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተገቢ ነው። "ደጀ ሰላም" ማንሣት የፈለገችው ግን በጠቅላላው በኢትዮጵያ ስላለው ሙስና እና የንብረት ብክነት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችንን ጠፍንጎ ስለያዛት ዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ነው። ከላይ እስከ ታች በተዘረጋ የጉቦ፣ የሙስና እና የሀብት ዝርፊያ ዘመቻ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ መውደቋን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችንን በማስታወስ መፍትሔው ግን አሁንም ሩቅ መሆኑን አበክረን እናስታውሳለን።

December 8, 2010

ከፍተኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማቱ ትኩረትና ድጋፍ ይሻሉ


(ለደጀ ሰላም፤ ከቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አንዱ)፦ ፕሮቴስታንቲዝም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አጥፍቶ ሀገሪቱን ለመረከብ ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ የዘለቀ ጥረት አድርጓል፡፡ በዚህ ጥረቱ ከተከተላቸው እና እየተከተላቸው ካሉ ስልቶች አንዱ የቤተክርስቲያንን የክህነትና የስብከተ ወንጌል አገልገሎት እንዲሁም አስተደደር ለመቆጣጠር መሞከር ነው፡፡ በዚህ ስልት መሠረት የአብነት ትምህርት ቤቶቻችንን እና መንፈሳዊ ኮሌጆቻችንን ለመቆጣጠር በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ባለፉት ወራት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን እናንሣ::

ገዳማትን እና አድባራትን ለመታደግ በለንደን የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ተካሄደ

(ለደጀ ሰላም ታምሩ ገዳ - ለንደን):- በኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚገኙ  ገዳማት አድባራት እና የአብነት/ቤቶችን  (የቆሎ /ቤቶችንውድመት ለመታደግ የታቀደ  የገንዘብ  ማሰባስብ ፕሮግራም  ለንደን ውስጥ  ተካሄደ ፡፡ የፕሮግራሙ  ዋንኛ ተዋንያኖች ሆኑት የማኅበረ  ቅዱሳን  አባላት  ከዚህ ቀደም ያበረከቱት  እና አሁንም  እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ  ለበርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት  ተከታዮች ከፍተኛ አርአያ መሆኑ ተገለጸ፡፡

December 4, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አንድ ተማሪውን ከትምህርት አገደ

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 4/2010 ኅዳር 25/2003 .) የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር ጉባኤ ለአዲስ ተመዝጋቢ ደቀ መዛሙርት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ‹‹ከተቋሙ የቅበላ መስፈርቶች አንዱ የሆነውን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወይም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የተፈረመበት የድጋፍ ደብዳቤ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ አላቀረበም፤ በድጋፍ ደብዳቤ ስም ያቀረበውም ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው ነው፤ ከአንድ ወር በላይ በትምህርት ገበታው ላይ አልተገኘም››፣  ከሬጅስትራሩ፣ ከአካዳሚክ ዲኑ እና ከበላይ ሐላፊው ዕውቅና ውጭ ወደ ኮሌጁ በሕገ ወጥ መንገድ በመግባት ትምህርት ጀምሯል ያለውን አሰግድ ሣህለ የተባለ ተማሪ አገደ፡፡

December 3, 2010

ፍርድ ቤቱ በጋሻው ደሳለኝን በነጻ አሰናበተ

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 2/2010፤ ኅዳር 23/2003 ዓ.ም)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት በጋሻው ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በነጻ ተሰናበተ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠው ተከሳሹ በጋሻው ደሳለኝ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ “አንድ ማኅበር አለ - ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል፡፡ ደም አፍሳሽ ማኅበር፣ የወንድሞችን ደም በጣሳ እየተቀበሉ ለመጠጣት የተዘጋጁ. . .” በማለት ያሰማው ንግግር “አያስከስስም” በሚል ነው፡፡ ውሳኔው ጉዳዩን በሚከታተሉ ሌሎች የፍትሕ አካላት እና የሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ከፈጠረው መደናገር የተነሣ በጥንቃቄ እየተጤነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)