November 14, 2010

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ሄዱ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ዛሬ ኅዳር 4/ 2003 .ም በዲሲና አካባቢው አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰዓት (9:00 AM) ዋሽንግተን ዲሲ  መግባታቸው ታወቀ:: ዳላስ ለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደብረ ምረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ጥቂት ምእመናን በቦታው በመገኘት አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: የብፁዕነታቸው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መሄድ ሀገረ ስብከቱ እውቅና ይኑረው አይኑረው ለጊዜው ባይታወቅም፤ በአቀባበል ሥነ ርዓ ላይ ግን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብሃም አልነበሩም::
ብፁዕነታቸው ወደ አካባቢው ሲደርሱ በቦታው የነበሩት የደብረ ምረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ሌሎች  የደብሩ አገልጋዮች እንዲሁም ጥቂት ምእመናን በስተቀር፤ ከሌላ አጥቢያ አያተ ክርስቲያናት ሆነ ከሀገረ ስብከቱ ተወካይ አልነበረም::  

ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲሲና አካባቢው ከሚገኙት በቁጥር 20 ከሚሆኑት አጥቢያ አያተ ክርስቲያናት መከል “ገለልተኛ” አስተዳደር ሥር ነን ከሚባሉት መከል አንዱ ነው። ደብሩ የዛሬ አምስት ዓመት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጵጵስና ሲሾሙ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ “የዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰርቼ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለሁ” በማለት በመናገራቸው በደማቅ ሁኔታ የተጨበጨበለትና መንበረ ጵጵስና እንደሚሆን ቃል ተገብቶለት ነበረ ቤተ ክርስቲያን ነው። አጥቢያ ቤተ ክርስቲያ በባለቤትነት ከተመዘገቡት ሦሥት ግለሰዎች መከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንደሆኑ ይነገራል:: ብፁዕነታቸው ወደ ዲሲ አካባቢ የሄዱበት ዓላማ ምክንያት ምን እንደሆነ ለጊዜው አልታወቀም:: 

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ1991 ዓ.ም በወጣው ገ ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ተግባር እና ሥልጣንን በሚደነግግበት አንቀጽ ላይ አንድ ጳጳስ ከተመደበት ሀገረ ስብከት ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ሲሄድ የሚሄድበትን ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፈቃድ መጠየቅ እንደሚያስፈልገው እንደተደነገገ አባቶች ይናገራሉ:: 
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)