November 19, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የምግብ ቤቱ ሐላፊ እንዲነሡላቸው ጠየቁ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 19/2010፤ ኅዳር 10/2003 ዓ.ም)የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በምግብ አቅርቦት ጥራት፣ በጤና አገልግሎት ሽፋን፣ በሥርዐተ ትምህርት ጫና እና የደቀ መዛሙርት መማክርት መቋቋምን አስመልክቶ ለተቋሙ አስተዳደር ያነሷቸው ጥያቄዎች፣ “ወቅታዊ ምላሽ እና ተገቢ ትኩረት አልተሰጣቸውም” በሚል ከትናንት አንሥቶ በካፊቴሪያው ባለመመገብ እና ትምህርት በማቋረጥ የጀመሩትን ተቃውሞ ቀጥለው ውለዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ዛሬ ጠዋት የበላይ ሐላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እና ሌሎች የኮሌጁ አስተዳደር ሐላፊዎች በተገኙበት በተነሡት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

በውይይቱ ደቀ መዛሙርቱ የምግብ ቤቱ ሐላፊ ተቋሙ ዳግመኛ ከተከፈተበት 1988 ዓ.ም አንሥቶ ይፈጽሙታል ለሚሏቸው በደሎች በቂ ማስረጃ ያላቸው በመሆኑ ከቦታቸው እንዲነሡ እንዲያውም ወደ ኮሌጁ ቅጽር እንዳይገቡ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ከምግብ እህል ግዥ አንሥቶ በአቅርቦቱ ጥራት ላይ የሚታዩት ችግሮች በአስቸኳይ እንደሚስተካከሉ ቃል የገባው የኮሌጁ አስተዳደር፣ የምግብ ቤት ሐላፊውን ከቦታቸው ለማንሣት የራሱ አሠራር ስላለው ደቀ መዛሙርቱ በጠየቁት ፍጥነት ለማንሣት እንደሚቸገር ገልጾ ደቀ መዛሙርቱ አሉን የሚሏቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ እንደሚችሉ ከመግለጹም በላይ በካፊቴሪያው መመገባቸውን እንዲቀጥሉ፣ የከሪኩለም ጫናው ችግር ደግሞ በሒደት እንደሚፈታ እና ከመጪው ሰኞ አንሥቶ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚያስጠነቅቅ ማሳሰቢያ ማውጣቱ ታውቋል፡፡ 

ደቀ መዛሙርቱ በበኩላቸው ምርቱ ከግርዱ ያልተለየ የምግብ እህል ያለጨረታ በጥቅም ትስስር በመግዛት ጥራቱ የተጓደለ ምግብ እንዲቀርብ በማድረግ ለረጅም ጊዜ የጤና ችግሩ እንዲጸና ምክንያት የሆኑት (በአንዳንድ ደቀ መዛሙርት ዘንድ ኅዳርን ጠብቀው በሚያሥነሱት ችግር ‹የኅዳር በሽታ› በመባል ይታወቃሉ) የምግብ ቤቱ ሐላፊ ከቦታቸው ተነሥተው ወደ ቅጽሩ እንዳይገቡ እስካልታገዱ ድረስ በካፊቴሪያው ያቋረጡትን ምግብ መመገባቸውን እንደማይቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የደቀ መዛሙርቱ መማክርት እንዲቋቋም ከአስተዳደሩ ጋራ መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ ከየትምህርት ዓመቱ አንድ አንድ ተወካዮች በአጠቃላይ ስድስት አባላት ያሉት መማክርት መቋቋሙ ታውቋል፡፡ መማክርቱ በኮሌጁ አስተዳደር ዕውቅና ካገኘ በኋላ አሁን በደቀ መዛሙርቱ እና በአስተዳደሩ መካከል የሚታዩትን አለመግባባቶች በወቅቱ ለመፍታት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተስፋ ተደርጓል፡፡ በተቋሙ የቀድሞ ተማሪዎች የተቋቋመው የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር በበኩሉ ችግሩ በአጭር ጊዜ እልባት እንዲሰጠው የማግባባት ጥረት ለመጀመር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡

9 comments:

Sam Ze Nairobi said...

Shame on you "Dekemezamirt". We EOTC followers expecting you to raise question on the completion of the decision made by the holy synod on the last session. We lost hope for your future. It will be a matter of profession you are going to live on not the spiritual value. You are all the same. Amilake kidusan Libona yistachihu.

Unknown said...

"LETEKEMACHI SEMAY KIRBU NEWU" Sam Ze Nairobi. The Dekemazamurtes cannot solve the problems in church. Let them solve the problems that they are facing. I have been hearing this corruption problem in the College for a couple of years.

If we want to solve the problem in the church, we need to focus on solving the problems in Synod. Otherwise we will live crying for all duration of our life.

The dekemezamure are learning only by theory not of practical christianity from their fathers and teachers. If we want the dekemezamurtes to be problem solvers and hope for the church of the tomorrow, let us wipe our problems.

Anonymous said...

"በሥርዐተ ትምህርት ጫና" so funny! This implies as they are not qualified at the first place.All are all crying for their soul, for money, for power.... If these students can't serve the church as they are expected to and couldn't leave the life of their fathers, why the church invest in them? All the unorthodoxy songs, the unorthodoxy preaching is streaming from there. what is really going on there?

Anonymous said...

University students give their life and suffered and suffering for their country.Most of the changes in Eth. came due to students struggle.They are candle for the poor Eth. But our future "papasat and astedadariwoch" are crying for food. We didn't see them protesting against the statue, we didn't hear them preaching about the evil acts of our church.....

Anonymous said...

O Deeje Selamawian?
You are not an attorney of the Church. I know you how much you are running against our church. When we feed you the real information you are throwing to your pocket as the bishops do. You need only stuipd data.

lemehonu, who are you? Catalyst or ventlator?

Anonymous said...

Is Dejeselam the church-wing of the diaspora politics ? They are always into news of doom and gloom !

Anonymous said...

Dear DS, please post this news if you find it relevant.

http://www.dw-world.de/dw/article/0,,6256085,00.html?maca=amh-standard_feed-amh-611-xml

Kiduse wwek MS said...

አይ ደጀ ሰላሞች ደግሞ ለቲኦሎጂ ተማሪ ትጨነቃላችሁ፡፡
እዚህ የላመ የጣመ ለምደው ነው ክፍለ ሃገር ሲመደቡ አንሔድም እያሉ የሚያስቸግሩት፡፡

በእርግጥ ለበሽታ የሚዳርግ መብል ይመገቡ ማለቴ ወይንም የኮሌጁ አስተዳደር ችግር የለበትም ለማለት አይደለም ግን የኮሌጅ ተማሪዎቻችን በአብዛኛው ማለት ይቻላል ድሎት የለመዱና በዘመድም ሆነ በጉቦ ከተማ ተመድበው መንቀዋለል የሚፈልጉ ናቸው፡፡

ስለዚህ ችግርን ቢቀምሱት መልካም ለወደፊት አገልግሎታቸው ጠቃሚ ነው እላለሁ፡፡

Anonymous said...

Dear DS, I know this message won't go with the headline. But I just wanted to share the news with you incase you didn't read it. I don't want it to be posted atleast under this:
Two men arrested after attempting to destroy statute

http://ethioforum.org/archives/2566

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)