November 19, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ለተቋሙ አስተዳደር የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀረቡ


  • ‹‹60 ተማሪዎች ከምግብ ጋራ በተያያዘ የጤና ችግር ገጥሟቸዋል›› ተብሏል፤ 
  • ለኮሌጁ ዲግሪ እና ዲፕሎማ ዕውቅና የማይሰጡ ተቋማት አሉ፤
  • የኮሌጁ ቦርድ እና አስተዳደር ለተማሪዎች መማክርት ም/ቤት መቋቋም ፈቃድ ለመስጠት ተስኖታል፤
  • ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጠቀም “የራሳቸውን ዓላማ ለማስፈጸም የሚሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ” እንደሚገባ ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም) የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከምግብ ጥራት፣ ከጤና እክል እና ከሚያገኙት የሕክምና ደረጃ፣ ከሥርዐተ ትምህርት ተገቢነት እና ከተማሪዎች መማክርት መቋቋም ጋራ በተያያዘ በኮሌጁ አስተዳደር ‹‹በአስቸኳይ ሊስተካከሉ ይገባሉ›› ባሏቸው ችግሮች ዙሪያ ተቃውሞ አንሥተዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ ከኮሌጁ አስተዳደር ጋራ ስብሰባ የተቀመጡት መላው ደቀ መዛሙርት ከሁለት ሳምንት በፊት በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እያሉ በተለያየ መንገድ ያቀረቧቸው እኒህ ጥያቄዎቻቸው አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጣቸው ቢነገራቸውም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው በኮሌጁ ምግብ ቤት መገልገላቸውን በማቆም በውጭ መመገብ መጀመራቸው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የደቀ መዛሙርቱን አካዳሚያዊ እና የተገቢ አገልግሎት ጥያቄ በመጠቀም በተቋሙ አስተዳደር ላይ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር፣ በዚህም “ድብቅ የኑፋቄ እና የጥቅም ዓላማቸውን ለማሳካት የሚሹ ወገኖች” በተማሪው ጥያቄ ተሸሸገው ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ደቀ መዛሙርቱ አሳስበዋል፡፡ ዝርዝሩን በቆይታ እንመለስበታለን፡፡

8 comments:

Anonymous said...

ይህን ነብር ጅራት አልባ ሊያስቀሩት ነው > የተባለው ተረት እኛ ላይ ልታደርሱት ነው መሰለኝ አሁንስ....ያንንም መናፍቅ ያንንም መናፍቅ..ወይ ጣጣ ማነው አማኙ..ደሞ ኮሌጁ ዉስጥ መናፍቃኑ ገቡ ማለት ነው ? ቤተክርስቲያኒቱስ ከሙዳየ ምጽዋት በተስበስበ ገንዘብ የምታስተምረው መናፍቃን ለማድረግ ነው ማለት ነው ? ሁኖ ከሆነ በጣም ያሳዝናል..አደጋም ነው ።

Anonymous said...

አሰግድና አሸናፊ ገብረ ማርያምን አካሄዴ ማን ሰው በቀላሉ የሚገነዘበው አይመስለኝም ለምን ቢባል ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን እያገኙ ተግባራዊ የሚያደርጉት ከነስዩም ያሚና ግርማ በቀለ ነው ስለዚህ በማህበረ ቅዱሳንና በኮሌጁ መካከል ያለውን መልካም ቅርርብ ብሎም አብሮ የመስራት መንፈስ ለማበላሸት ወደኮሌጁ ገቡ እነዚህ ሰዎች የትምህርትቨ ችሎታቸው በእጅጉ የወረደ አንድ ሴንቴስ የማይጽፉ ናቸው ገን በስውር አላምን ለማስፈጸም የበረቱ መሆናቸውን ልንረዳ ይጋበል በተለይም አቡነ ጢሞቲዎስ የተበላሸውን የቤተ ክህነት አስተዳደር ስለሚቃወሙ እርሳቸውን ከመስመር ለማስወጣት የተደረገ ሴራ ነው በቅንብሩ ደጎሞ የብዙሰዎች እጅ አለ

Anonymous said...

ዋናው በቤተክርሲቲያን ኮሌጅ ስም መነገድ የሚፈልጉ
አሉ። አንዳንዴም ሀገረ ስብከታቸውን በመናፍቅነት እየበጠበጡ
ሲያስቸግሩ እስቲ ወደ ሊቃውንቱ ተጠግተው ሲራቸው ይጋለጥ በማለት
ለጊዜው ወደ ቲዎሎጂ የሚላኩ እንዳሉም የማውቀውን ብገልፅ ይጠቅም ይሆን።
አባ ሐይለሚካኤል የሚባሉ በጉርሱም ወረዳ የነበሩ ሰው ሐረር እና አካባቢዋን
አስቸገሩ። ሀገረ ስብከቱ እልፍ ይበሉልኝ ብሎ 4ኪሎ ቅ/ሥ/መ/ኮ በዲግሪ አስገባቸው።
በመቀጠል ተጠያቂ እኔነኝ ማለት ጀመሩ ገና የአደኛ አመት ተማሪ እያሉ ብዙ ውድመት አድርሰው ነበር።
እነ አሰግድና አሸናፊን ሐረር በማምጣት የብዙ ሕፃናትን አእምሮ አበላሹ።
ስለዚህ ገና ሲገቡም እየታወቀ ከእኔ ይራቅልኝ አይነት የሚላኩ አሉ።
ግን አንዲት ቤተክርስቲያን ናትና ለሚደርሰው ጥፋት
ከአንድ ቦታ መሄዳቸው ሳይሆን በዘለቄታ የሚያደርሱትን ጥፋት ማሰብ ይገባል።
አስተያየት ሰጪው እንደገለፅከው አደጋው የከፋ ይሆናል።ስለዚህ ምልመላ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቓል፡፡
እውነተኛ የኮሌጁ ተማሪዎች ግን ቤተክርስቲያንን በምንም ምክንያት አሳልፈው እንደማይሰጣት አምናለሁ።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቀልን!!!!!!!!!!!!!!!!
ሙላቱ
ሐረር

Anonymous said...

The problem is not from the students or from the instructors it is from the adiministration of the college and the synod or the patriarc. The students has been asking this quastion almost every year
1. About the instructors,all Ethiopian instructors are really respect their church doctrin and tradtion even though they need more capacity building. But i have still a quastion on outsiders becuse the Indian man, who teaches ethiopian dogma is also teaching in Catholic institute in ethiopia and no evidence that he is an orthodox
2. The students of the college are selected from differnt dioceses by their respectd bishops. Most of them have a very good background of the church tradtion and we hope that they will serve the church in many ways.
3.The cause of any problems in the college is the weak administration in the college as well as the synod or the patriarc. The have many opportuninities to improve the quality of the college but their is no change at all for many tears.

Anonymous said...

bla bla bla that is all u know

Anonymous said...

ጥያቄ አነሱ ሲባል እኔስ በቤ/ክ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው በደል ይቁም ብለው መስሎኝ ነበር። ስለሆዳቸው እና ስለሚከፈላቸው ደሞዝ አብዝተው የሚጮሁ ክርስትናቸውን በመኖር የሚገልጡ ሳይሆን ሴቶችን በማማለል የሚታወቁ ብዙዎች በኮሌጁ አሉ፡፤ ተመርቀው ከወጡት ውስጥ ጥቂት የማይባሉትም በቤ/ክ ውስጥ እየደረሰው ላለው መከፋፈል፤ሙስና እና የሥርዓት ጥሰት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ናቸው።

Anonymous said...

wadaje hoy k mibela neger belay min ale bilw new.mechem bihon deqamazamurtu kasamay mena ayitabiqu tayiqo kmagignet baelay. bizu sew kahager ytesededewko lteshal nuro bicha sayhone linjeram new. binjerw tiyaqe wiste gin min endale mawaqu tagabi new. bejerbaw 10 negeroch abrw aluna 'hulu neger silamaynegerko ne'

Amrach from Dilla said...

Is the problem only from student?
Why don't you look what the patriarch is behaving.... and some Selfish pope like in Awassa. So, if the fathers behave this way; I do not blame the students. of course the student should have learned from good fathers from those who are devoted fathers for the church Rule. But... may God bring the good for our church

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)