November 8, 2010

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ትናንት በተከሰተ ብጥብጥ ጉዳት ደረሰ፤ አዋኪዎቹ በፖሊስ ተይዘዋል

  •  ሁከቱ ሊቀ ጳጳሱ ወደተመደቡበት ሀገረ ስብከት እንዳይመጡ ለማሣቀቅ እና አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ችግር መፍታት እንደተሳናቸው ለማሳየት ጀምበር በጠለቀችባቸው በእነ ያሬድ   አደመ የታለመ ነው፤
  • ‹‹በሁከቱ ስለት፣ ዱላ እና ድንጋይ የተጠቀሙት ወሮበሎቹ ባደረሱት ድብደባ ከአምስት ያላነሱ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ፖሊሶች ተጎድተዋል፤ አንዱ ወጣት ጆሮው የተቆረጠ  ሲሆን በጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሌላው ወጣት ደግሞ ራሱን ስቶ በጉሉኮስ እየተረዳ ይገኛል፡፡›› (የሆስፒታል ምንጮች)
  • ፖሊስ ከያሬድ እና ዓለምነህ ሽጉጤ በተጨማሪ በሁከቱ የተሳተፉ ሰባት ቀንደኛ ግለሰቦችን  በቁጥጥር ሥር አውሏል፤
  • ፓትርያሪኩ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና በጋሻው ደሳለኝ ሁከተኞቹን ለማስለቀቅ ጥረት  እያደረጉ ነው፤
  • የሐዋሳ የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል
  •  በመጪው ቅዳሜ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ወደ ሐዋሳ እንደሚመጡ በአዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሲነገራቸው ያጉረመረሙት ‹‹የተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› አባላት የሊቀ ጳጳሱ ወደ ሀገረ ስብከቱ  መምጣት እንደሚያስከፋቸው በአዎንታ አረጋግጠዋል
  • ‹‹እነያሬድ አደመ ተከልክለው ማንም አራት ጎማ ያመጣው ሁሉ በዚህ መድረክ ላይ አያዝበትም፡፡››
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 8/2010፤ ጥቅምት 29/ 2003 ዓ.ም) - ትናንት እሑድ ሰንበት ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸቱ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለማነጋገር የጠሩት ስብሰባ ዓለምነህ ሽጉጤ በሚባለው ግለሰብ በሚመራው ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማኅበር›› እየተባለ በሚጠራው አካል በታቀፉ እና በእነ ያሬድ አደመ በተደራጁ ወሮበሎች ከፍተኛ ሁከት ተቀስቅሶበት ውሏል፤ በሁከቱ ወደ ገዳሙ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ እንዳይገቡ በወሮበሎቹ የተከለከሉት እና በቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከታገዱት ሕጋዊዎቹ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት መካከል ከአምስት ባላነሱት ላይ በስለት፣ በበትር እና በድንጋይ በደረሰባቸው ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አንዱ ወጣት ጆሮው የተቆረጠ ሲሆን ሚስማር በተሰካበት ብትር ጭንቅላቱን የተመታው ሌላው ወጣት ደግሞ ራሱን ስቶ በሆስፒታል በጉሉኮስ እየተረዳ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡ የገዳሙን ዙሪያ በመክበብ እና ወደ ቅጽሩ በመግባት ብጥብጡን ያበረደው የፌዴራል ፖሊስ ሁከቱን ለመቀስቀስ ቅዳሜ ምሽት የጠብ ምክር ሲያቅዱ አድረው ረፋድ ላይ በመከሩት መሠረት ብጥብጡን ከለኮሱ በኋላ ኮንትራት በተነጋገረው ሚኒባስ ታክሲ ከሐዋሳ ከተማ ወጥቶ ለመሸሽ የሞከረውን ያሬድ አደመን እንዲሁም ዓለምነህ ሽጉጤን ከሌሎች ሰባት ግብረ አበሮቻቸው ጋራ በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከሁለት ሰባክያነ ወንጌል እና ከሁለት ዘማርያን ጋራ ወደ ሐዋሳ በማምራት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እና የትውውቅ መርሐ ግብር ያካሄዱት ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸቱ ሁከተኞቹን ጨምሮ ከሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአድባራት አስተዳዳሪዎች እና ከቀድሞው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሰበካ ጉባኤ አባላት እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ እየተወያዩ ከመለስተኛ ዕንከኖች በቀር ሁኔታውን በትዕግሥት እና በትሑት ሰብእና ይዘው በመግባባት መንፈስ ለመዝለቅ ችለው ነበር፡፡ የትውውቁ መርሐ ግብር እና የስብከተ ወንጌሉ አገልግሎት ከሥራ አስኪያጁ ጋራ በመጡት ሰባክያን እና ዘማርያን በጥሩ ሁኔታ መያዙ፣ ስምሪቱም በሀገረ ስብከቱ ማእከላዊ ቁጥጥር መደረጉ ያልተመቻቸው ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤም ቅዳሜ ማታ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዳራሽ ተከታዮቻቸውን ይዘው በማግሥቱ እሑድ የጠብ መንሥኤ የሚፈጥሩበትን ስልት ሲቀይሱ አመሹ፤ እሑድ ከቀትር በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ግን ሥራ አስኪያጁ ለብቻቸው እንዲያነጋግሯቸው በጠየቁት መሠረት ለማድረግ ታቅዶ ለነበረው ውይይት አምስት ተወካዮቻቸውን ይዘው እንዲመጡ ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር፡፡

በውይይቱ ላይ አዲሱን ሥራ አስኪያጅ ከቃለ ዓዋዲው ውጭ ‹የተመረጡቱ› ሕገ ወጡ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር እና የገዳሙ ሰበካ ጉባኤ አባላት በሐላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ለመጠየቅ ካልሆነም አካላዊ ጥቃት በማድረስ ጭምር ለማስገደድ ወስነው ነበር፡፡ ከቀትር በፊት ጠዋት ደግሞ ተኣምረ ማርያም የሚያነቡትን ካህን እና ከሥራ አስኪያጁ የልኡካን ቡድን አባላት አንዱ የሆነውን ዘማሪ ምንዳዬ ብርሃኑን ከመድረኩ ጎትቶ ለማውረድ አቅደው ነበር - ‹‹እነያሬድ አደመ ተከልክለው እነርሱ ባቀኑት አገር ማንም በአራት ጎማ የመጣ ሁሉ በዚህች መድረክ ላይ አያዝባትም!›› የሚል ማስጠንቀቂያ ከማፊያው ቡድን አባላት በአንዱ ተነግሮት ነበር - ዘማሪ ምንዳዬ፡፡

እሑድ ጠዋት ድርገት እንደ ወረዱ የዐዋኪው ቡድን አባላት የሆኑ ዘማሪ ነን ባዮች ዩኒፎርም ለብሰው መዘመር ይጀምራሉ፡፡ ሁኔታውን በትዕግሥት ያሳለፉት ሥራ አስኪያጁ የዕለቱ ተኣምር እንዲነበብ እና ስብከተ ወንጌሉ እንዲሰጥ ያደርጋሉ፡፡ በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የፊታችን ቅዳሜ እንደሚመጡ በመናገር ላይ እንዳሉ የቡድኑ አባላት ጉርምርታ ድምፅ ያሰማሉ፤ ሥራ አስኪያጁም የጉርምርምታው ምክንያት የመከፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ሲጠይቁ የአዎንታ መልስ ይሰጣቸዋል፤ አለ የሚባለውን ችግር በዚያኑ ዕለት ከሰዓት በኋላ ከአምስት ተወካዮቻቸው ጋራ በሚደረገው ውይይት በመነጋገር ለመፍታት መታቀዱን ያሳውቃሉ፡፡ አያይዘውም የቡድኑ አባላት ቅዳሴ ሳያልቅ እና ተኣምረ ማርያሙ ሳይነበብ መዝሙር መዘመራቸው አግባብ እንዳልሆነ ያስረዳሉ፤ በዚህ ወቅት ከቡድኑ አባላት አንዱ መነጋገሪያውን በማንሣት፣ ‹‹ምእመናን ሁላችሁም ወደ አዳራሽ ግቡ›› በማለት ያዝዛል፡፡ ሥራ አስኪያጁም ጸሎተ ቅዳሴው የተጠናቀቀ በመሆኑ ምእመናን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ እና የሰንበት ት/ቤት አባላት የሆኑ ወጣቶች ብቻ ወደ አዳራሽ እንዲገቡ ያሳስባሉ፡፡

ሥራ አስኪያጁ በሰጡት ማሳሰቢያ መሠረት ቀደም ሲል በነበሩት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና በሐዋሳ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አላግባብ በተሾሙት አስተዳዳሪ ውሳኔ የታገዱት ሕጋዊዎቹ የሰንበት ት/ቤት አባላትም ወደ አዳራሹ ለመግባት ሲሞክሩ እንዳልተፈቀደላቸው በማፊያ ቡድኑ ይነገራቸዋል፡፡ በዚህ መካከል በተፈጠረው ዐምባጓሮ በምክር ያደሩት እና ያሬድ አደመ በሞባይል ስልክ የሚመራቸው ወሮበሎች ሚስማር በተመታበት ብትር እና በድንጋይ እሩምታ ሽሽት የመረጡትን ወጣቶች መአት ያወርዱባቸው ጀምር፡፡ በድንጋዩ ውርጅብኝ መፈንከት ያልቀረላቸው እና ክሥተታቸው እንደ ተራዳኢ መልአክ የታየው የፌዴራል ፖሊስ አባላትም ሁኔታውን በቅርበት ይከታተሉት ኖሮ ድብደባውን በአስቸኳይ ባይቆጣጠሩት ጉዳቱ ሊባባስ ይችል እንደ ነበር የተነገረ ሲሆን የጉዳተኞችን መጠን አስመልክቶ የተለያየ አኀዝ ተዘግቧል፡፡ ለደጀ ሰላም በደረሰው ጥቆማ ከአምስት ያላነሱ ወጣቶች እና ፖሊሶች ጭምር መጎዳታቸው የተነገረ ሲሆን አንድ ወጣት እስከ አሁን ራሱን እንደ ሳተ በሆስፒታል ሕክምና ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

ትናንት ማምሻው ድረስ እና ዛሬ ጠዋት በጋሻው እና ወ/ሮ እጅጋየሁ በተለይም ያሬድ አደመን ለማስለቀቅ ጥረት ማድረጋቸው የተሰማ ቢሆንም ከመንግሥት ምንጮች እንደተሰማው ፖሊስ በቀጣይ ሁከቱን በማስተባበር እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩትን በጋሻውን እና ወ/ሮ እጅጋየሁን በቁጥጥር ሥር ሊያውላቸው ይችላል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው ሁከተኞቹን እንዲያስፈቱ ጫና እያደረጉባቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡                             

የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ ሲሉ ሀገረ ስብከቱን በአስነዋሪ ድርጊቶቻቸው እና የማያባራ በሚመስለው የእርስ በርስ መከፋፈል አዙሪት ውስጥ ባሰነበቱት በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በቀጠለው ምርመራ ለሁከት የሚያሰማሯቸው ኀይሎች ከያሉበት እየታደኑ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በሁኔታው ሲማረሩ የቆዩት የከተማው ምእመናን የጸጥታ ኀይሉ ከጥንተ ታሪካቸው ጀምሮ የሁከት መዝገብ እና የመለያየት አበጋዝ ሆነው የኖሩት ግለሰቦች በሚያሳዩት እስስታዊ ጠባይዕ ሳይዘናጋ ለአዲሱ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር እና ለከተማው አጠቃላይ ሰላም ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥ ጥብቅ እና ፍትሐዊ ርምጃ እንዲወስድባቸው ተማፅነዋል፡፡

39 comments:

Unknown said...

ምን ጉድ መጣብን ወገኖቼ እግዚዮ በሉ ክርስቲያኖች!!!!
ከሀዋሳ

Unknown said...

ምን ጉድ ነዉ? ወገኖቼ ምን መአት ነዉ? እግዚዮ በሉ ክርሰቲያኖች!!
ከሀዋሳ

Hailemaryam said...

ወይ ጉዳችን እኔ ግን ወገኖቼ ማመን ከበደኝ፤ ግን ይሄ ሁሉ በዉኑ ተፈጽሟል? አቤቱ አምላከ ሰላም ክርስቶስ ሆይ ሰላምህን ላክልን!!! አሜን።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሆይ የሚታገሉሽ ይወድቃሉና ጽኚ፤ የክርስቶስ መሆንሽን ታዲያ በምን ይታወቃል ወርቅ በእሳት እንዲሉ ተፈትነሽ ካላለፍሽ።
ዉድ የክርስቶስ ወገኖች ሆይ እንጽና፤ ልቡናችን አይዉደቅ። ባለቤቱን ያላፈረች አለም ዉስጥ እየኖርን የክርስቶስ ለመሆን ይህችን ጥቃቅን ፈተና ካልታገስን ታዲያ በምን የክርስቶስ መሆናችንን ይታወቃል።
እነቅዱስ ጊዮርጊስስ መላ ሰዉነታቸዉን ተቆራረጡ፣ እነ ተክለሐይማኖት ደግሞ መላ ሕይወታቸዉን ለጌታ መባ አስረከቡ፣ ሌሎቹም እንዲሁ...ከፍጥረት ሁሉ የከበረች እመቤታችንም ሳትቀር ሁሉም የጌታ የሆነ ሁሉ ደምቷል፣ ተሰዷል፣ ተንቋል፣ ታግሷል፣ በመጨረሻም አሸንፏል። በመንግስተ ክርስቶስ ግን ያልተፈተነና ያለሸነፈ ይገኛል? ከንጉሱ ጀምሮ እናቱ በሙሉ ቅዱሳኖቹ...ያልደማ የለምና እንታገስ።

bitweded zehawasa said...

one muslim told me that they were disturbed due to the rebelion which was held in the saint gabriel church
please govvernment officials punish this evil men once again because this men are giving a negative picture for ethiopian orthodox church and ethiopia as well
the muslim woman told me that when i see orthodox christians i see the bright culture of ethiopia
the clear image of ethiopia
please orthodoxians pray pray pray
WHEN GOD SEEMS SILENT HE IS FOUND IN THE FASTEST SPEED

yemelaku bariya said...

ይገርማል:: የአባ ጳውሎስ ጥረት ይደንቃል:: ሁልጊዜ የጥፋት ተባባሪ መሆን አለመታደል ነው:: ገንዘብ የዘረፈን ፍትህ እንዳያገኝ ወደውጭ ማስኮብለል፣ የደበደበን ማስፈታት:: መቼ ነው የተደበደቡትን የሚጠይቁት የተዘረፉትን የሚያያናግሩት መቼ ነው ለተበዳዮች ቁመው የምናያቸው:: የቀረቻቸው ትንሽ እድሜ ለለውጥ የምታበቃ አይመስልም ምክንያቱም ከዚህ ባህሪያቸው ለመላቀቅ ብዙ እና እልህ አስጨራሽ ትግል ይጠይቃልና ነው:: እንዳው እንዲህ እንደሆኑ አንድም በጎ ነገር ሳይኖራቸው መሄዳቸው ያሳዝናል:: እኔ የምፈራው ሲሞቱም ከቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውጭ በተሰራው ሐውልት ሥር እንዳይቀብሯቸው ነው የምፈራው በሞታቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይጠጉ የሚያደርጉ ዘመዶቻቸው ናቸው ከሕዝብም ጭምር የሚለዩአቸው:: ቢያውቁበት ሐውልቱን ቢያፈርሱ ይሻላቸው ነበር በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዳይጣሉ:: እጅጋየሁ በዚሁ መግቢያዋን ታገኛለች :: የሰው ልጅ በሚስማር አስተርትሮ በሰላም መኖር የለም መንግሥትም የአመጹን አስተባባሪዎች ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው ጥርጥር የለንም::

1x said...

በጋሻው ትልቅ ወንድማችን:መመኪያችን:ኩራታችን እና ዘውዳችን በመሆኑ ጳጳስ ሆኖ እንዲሾም እንፈልጋለን..ለዚህም እንቅስቃሴ ጀምረናል..ጳጳሰ እንዲሆንልን ወደ ብጹእ አባታችን ደብዳቤ በትናንትናው እለት አስገብተናል...ለዚህም የተቀደሰ ስራ የ ደጀሰላም ማህበረሰብ ድጋፉ እንዲሰጠን እንማጸናለን::sep

tekelewolde the sodo said...

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሆይ የሚታገሉሽ ይወድቃሉና ጽኚ

Unknown said...

I am really surprised by these guys. They should go to jail. There should not be any excuse for people who are creating anarchy in the church.

Ledet said...

O memenan yehe yehonew lemen yehone? sewochuse yegna nachew? mekneyatume fereyachew mereregn!! keyetese agegnute ? kemans temarute?

Yeabatachenes ye'alem yeselam ambasodernet yehenew maletnew?

Tseleyu.....Tseleyu.....Tseleyu

Anonymous said...

Who ever recommended Begashw to be a bishop, according to the book you need to be a celibate to acquire that title which Begashaw is not as far as I know.

Sam Ze Nairobi said...

Sam Ze Nairobi,
The true Christians of Awassa, Be strong. Now God will fight for you. Your blood and Patience will bring solution.

You Know many of your fathers, mothers, brothers and sisters around the world pray for you.

Axumawit said...

አይ አባ ጳውሎስ ለየሎት ማለት ነው? ግድ የለም እሩቅ አይደለም በህይወት እያሉ የስራዎትን ያገኛሉ ግብራበሮችዎ እጅጋየሁ-አቶ በጋሻው ደሳለኝ-አቶ ያሬድ አደመ-አባ ፋኑኤል ሳይቀሩ ከመንግንግስት በኩል ተገቢዉ ቅጣት ካልተሰጣችሁ በሌላ በኩል የጃችሁን ታገኛላችሁ የሰዉ ደም አፍስሶ በሰላም መኖር የለም ::

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ። እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል አለው። መሳ 6፥13

አዎ እግዚአብሔር ይህችን ቤተክርስቲያን ለወንበዴዎች አሳልፎ ስጥቷታል ከላይ ጀምሮ ያሉት መሪዎች በውንብድና የሚኖሩ ስለሆነ ቤተክርስቲያን ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ብዙ ፈተና ይጠብቃታል ,,ሳይቃጠል በቅጠል እንደተባለው ,, ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ አለ ያገሬ ሰው ,, እነ አለቃ አያሌው ታምሩ የተናገሩት ነገር እየተፈጸመ ነው ሲኖዶስ የሚወስነውን ውሳኔ አልቀበልም ካሉ አቡነ ጳውሎስ ማነው አለቃቸው ? መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ አያገባኝም በሚል ሰበብ እንደፈለጉ ቤተክርስቲያኒቱን ሲመዘብሯት ዝም ብሎ ያያል ህዝቡ ተቃውሞ ሲያነሳ ፌደራል ፖሊስ ያሰማራል አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ በሰበሰቡት ዶላር ብቻ ለጵጵስና እንደበቁ እየታወቀ አለችሎታቸው የማይመጥኑት ቦታ ብዙ ክርስቲያኖች ስለሃይማኖታቸው የሚዋደቁበት ቦታ አዋሳ መመደባቸው ለህዝቡ ታስቦ ሳይሆን ለእሳቸው የተደላደለ ኑሮ ለማመቻቸት ነበር እንደለመዱት መንፈሳዊ አገልግሎቱን ወደ ኋላ በመተው ከነበጋሻውና ያሬድ አደመ ጋራ ጓደኝነት ያዙ እኔ ሳስበው ጳጳስ መሆናቸውንም የዘነጉ ይመስለኛል ከዱርየዎች ጋራ ጓደኝነት ከሚመሰርቱ ለምን ከሊቃውንቱ ጋራ ውለው የማያውቋቸውን ብዙ የቤተክርስቲያን እውቀቶች አይቀስሙም ነበር ? ለመሆኑ በጋሻው ማነው ? ያሬድ አደመስ ማነው ? በደንብም ያወቋቸው አልመሰለኝም ለማንኛውም የሰሞኑ የነ ወ/ሮ እጅጋየሁ ስለ አቡነ ጳውሎስ ሃውልት መፍረስ እያቀረቡት ያለውን መከራከሪያ ልንገራችሁ 1ኛ, ሲኖዶሱ ገዘብም ሆነ ማንኛውንም አስተዋጽኦ ሳያደርግ ለተሰራው ኃውልት አያገባውም ይፍረስም ሆነ ይሰራ የማለት መብት የለውም 2ኛ,ኃውልቱ የተሰራው የቤተክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ ስላይደለ ከሚመለከተው ክፍል የቦታ ፈቃድ አግኝተን ስለሆነ ያሰራነው ሲኖዶሱ አያገባውም
3ኛ, አቡነ ጳውሎስ ሲኖዶሱን የመበተን ስልጣን ስላላቸው ከፈለጉ አሁን ያለውን ሲኖዶስ በትነው እንደገና ማዋቀር ይችላሉ ,,ወ ዘ ተ እያለች ወ/ሮ እጅጋየሁ በአንደበቷ ለአንድ ደጀሰላማዊ ተናግራለች ስትናገርም በልበ ሙሉነት ነው በተያያዘም በአሜሪካን የሚገኝ ልጇ እባክሽን ከዚህ ችግር ውስጥ እራስሽን አውጭ ብሎ እየመከራት ሲሆን እሷ ግን በፍጹም በኃሳቧ እንደጸናች ነች ,,,,,,,,,

ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ራዕ 2፥20

ኤልዛቤልን ከነርኩሰቷ እና አገልጋዮቿ የሚያስወግድ ,, ኢዩን ይላክልን

123... said...

Unless the necessary action taken the same might have happned in Bole Medhane Alem.HAWLTU BE GIZE MEFRES ALEBET.

Anonymous said...

I hope the government will take a fair decision as soon as possible. This is not a matter of only the orthodox religion, it is more than that. They are moving against the constitution and the right to worship.

To Government bodies:- we expect a fair decision as soon as possible.

Otherwise, it will be equivalent to supporting the hooligans to repeat the same crime for the third time. They did it first in 2009 against our Papasat.

Long live to Tewahedo!

Anonymous said...

Egziabhere lewnet endemiferd atiterateru!

Anonymous said...

ወገኖቼ እግዚአብሔር ይማራችሁ ያበርታችሁ ይህ ሰማእትነት ነው ዋጋችሁ ሰማያዊ ነውና አትፍሩ ጽኑ አምላከ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት ሃዋርያት ነብያት ከጎናችሁ ቆሞ ፍርዱን አይንሳችሁ ሌላማ በማ የምትተዳደረው ቤ/ክ ትቆምላችኋለች? ሌላው ቢቀር ቤቴ የፍቅር የሰላም እንጂ የፀብ የክርክር አይደለም ነገር ግን እየሆነ ነውና ወደ ፈጣሪ እንጩህ ተብሎ እንኴን ጾም ፀሎት እንዲደረግ አይታዘዝም ጥፋቱ የማንም ቢሆን ድርጊቱ የተፈጸመው በቅጥረ ቤ/ክ ውስጥ ነውና ድምጿን ልታሰማ ክብሯን ልታስጠብቅ ይገባ ነበር አዬ ወገኖቼ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው በየዋሻው ዘግተው የሚማጸኑት ሰለነሱ ብሎ ይታረቀን ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን
AD

aragaw ewnetu said...

The act is not surprise. Because the laity of Hawass play a great role in exposing those tehadsoes. There fore,tehadsoes begin to distruct the lovely EOTC by using physical force which is one of thier alternative act to distruct. This is the beginning. So all the followers of the church have to wake up to threat tehadso. May God save His church from tehadso.

ብዕሩ ዘአትላንታ said...

አባ ጳዉሎስ ዘመድ ማጣታቸዉ ያሳዝናል። ሃይ የሚላቸዉ ዘመድ ቢኖራቸዉ ኖሮ የጸረ ቤተ ክርስቲያን ቡድኖች ደቀ መዝሙር ባልሆኑ ነበር። የሊቃዉንቱን ምክር ለመስማት የልቻሉት ዕዝነ ሕሊናቸዉ ተደፍኖ ካልሆነ በቀር ከአንድ ታላቅ አባት የማይጠበቅ ግብር ተባባሪ ባልሆኑ። አሁን አሁን ስለሳቸዉ ስሰማ ከማዘን በቀር ሌላ የምለዉ እያጣሁ ነዉ። አርጅና ተጭኗቸዉ ጃጅተዉ አሊያም ደግሞ የማይፋቅ በደል ሠርተዉ ማለት መንፈስ ቅዱስን ሰድበዉ ተስፋ ቆርጠዉ ይሆናል እንጂ ከሊቃዉንት ጉባኤ ርቀዉ የወ/ሮ እጅጋየሁና የበጋሻዉ መጫወቻ አሻንጉሊት ባልሆኑ። የወገን ያለህ ለህዝብህና ለቤተ ክርስቲያንህ ሰላም ጸልይ። ስለ ህዝቡ እንባ አቤልን የጎበኘ አምላክ ስለ ቃየን አባ ቃዉሎስ ጊዜ አለዉ። ብዕሩ ዘአትላንታ

Asrate the dilla said...

keserachew Tawkachualachew... Yehew new sirachew 'Embe kale Be senselet Girefew' Yene begashaw memeria Dilla lay degemo Mahibere KIdusan Lejoch Betekirestian gibe Gebtew Endaytseleyu debdabe tetsefual birowema ketezega huletegna ametu new.. Ay Fiseha lemma Yemeseretew yasefafaw tehadeso group Yared Ademe Egzeabehere Yiyeleh ...

ወልደ ዮሐንስ said...

ውድ ምዕመናን ዛሬም አምላካችን ከእኛ ጋር ነው ትላንት የመሐመድ ጭፍራዎች በቤተ መቅደሳችን ጂማና ኢሉባቡር ላይ በስለት አረዱን ዛሬ የሉተር ውጥረኞች ከውስጥም ከውጭም መሽገው በአባታቸው ዲያቢሎስ ምክር እየተመሩ ቤ/ክርስቲያንን ፈተኗት ያውም መቀነቷን እየሰረሰሩ፡፡

ለዚህ ሁሉ አሳልፈው የሰጡን ታዲያ እረኞቻችን ስለተኙ እኛም ምዕመናን የቤ/ክን አሳብ የማይገደን ስለሆንን ነው፡፡ ተግተው ባይጠብቁን ለእረኞቻችን ይቀርባቸዋል እንጂ፤ የኋላ ኋላ እነርሱን የሾማቸው የማያንቀላፋው ትጉኅ እረኛችን አምላክነ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወንም፡፡ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች እናንተ ታላቅ ሰማዕትነት ከፍላችኋል፡፡

ዛሬም እንደትናንቱ የ‹‹ተሐድሶ›› መናፍቃንን እጅ ለእጅ ተያይዘን እሰከመጨረሻው እንታገላቸዋለን የታጠቁትንም ዝናር ይጨርሳሉ እንጂ ቤ/ክንን እኛ ከተጋን አያጠፏትም፡፡
እኔ ሌሎችን ከመውቀሴ በፊት ራሴ ምን እየሠራሁ ነው? ልበል፤ አሁን የተጀመረውን ለውጥ ለቅድስት ቤ/ክን አንድነትና ለመልካም አስተዳደር መምጣት ተስፋ ስለጫረብኝ ከሚሠሩት ጋር ለመቆም ሁሌም ዝግጁ ነኝ… እስከሞት!፡፡ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው ለራሳችን ዘይት እንያዝ እንጸልይ እናልቅስ አምላካችን ይሰማናል፡፡

(አንድ አስተዋይ መምህር እንዳሉት ማኅሌት የማይቆሙ መክፈልተኞችን) ‹‹ይበቃችኋል እስኪ ደግሞ ሌላ ቢዝነስ ስሩ›› እንበላቸው፡፡

ውሻኮ በሩ እስኪዘጋበት ድረስ ከሥጋ ቤት አይርቅም! የቤታችንን በር እስከመቼ ክፍት እንተወዋለን? እባካችሁ ከአሁኑ ጀምረን ተግባራዊ ምላሽ እንስጥ የብሎግ ጀግናዎች ብቻ አንሁን ፤ በቤ/ክን ባሉ አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ እናድርግ… ሰ/ት/ቤት እንግባ አንድም ባዶ ወንበር አይኑር፡፡ ተሐድሶዎች የተደራጁ አንዳንድ የጽዋ ማኅበርተኞችን ይሄ የእናንተኮ አይደለም ብለን እነቀበላቸው፡፡ ይሄ የሚሆነው ከዳር ቆመን አይደለም፡፡ እንዲህ ካደረግን ይህ ጊዜ አልፎ ወርቃማ ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ አለኝ፡፡

እባክሽ እመ አምላክ ስደትሽን ራብሽን ለልጂሽ አስቢልን

(አንድ አስተዋይ መምህር እንዳሉት ማኅሌት የማይቆሙ መክፈልተኞችን) ‹‹ይበቃችኋል እስኪ ደግሞ ሌላ ቢዝነስ ስሩ›› እንበላቸው፡፡ ውሻኮ በሩ እስኪዘጋበት ድረስ ከሥጋ ቤት አይርቅም! የቤታችንን በር እስከመቼ ክፍት እንተወዋለን? እባካችሁ ከአሁኑ ጀምረን ተግባራዊ ምላሽ እንስጥ የብሎግ ጀግናዎች ብቻ አንሁን ፤ በቤ/ክን ባሉ አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ እናድርግ… ሰ/ት/ቤት እንግባ አንድም ባዶ ወንበር አይኑር፡፡ ተሐድሶዎች የተደራጁ አንዳንድ የጽዋ ማኅበርተኞችን ይሄ የእናንተኮ አይደለም ብለን እነቀበላቸው፡፡ ይሄ የሚሆነው ከዳር ቆመን አይደለም፡፡ እንዲህ ካደረግን ይህ ጊዜ አልፎ ወርቃማ ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ አለኝ፡፡

bebotaw tegegnche kistetune bemayete betame azegnalehu.....

Anonymous said...

እባካችሁ አስተያየት ሰጪዎች በሐዋሳው ብጠጥብጥ ላይ የሐዋሳ ምእመናን እንዲህ ብለዋል አትበሉ ምክንያቱም አማጽያኑ የሐዋሳን ሕዝብ አይወክሉም የሐዋሳ ምእመናን እያሉ ባለሀብቶችና ማኅበረ ቅዱሳን/ማህበረ ሰይጣን የሚያካሂዱት አመጽነው እየበጠበጠ/ቤተ ክርስቲያንን ሰላም እየነሳ የሚገኘው ስለዚህ የአዋሳ ምህመናን ተብሎ መገለጽ የለበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በባለ ሀብትና በማህበረ ቅዱሳን አትመራም፡፡ ምክንያቱም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን የብብት ውስጥ እሳት ነው፡፡

ከሐዋሳ

ወልደ |ዮሐንስ said...

ውድ ምዕመናን ዛሬም አምላካችን ከእኛ ጋር ነው ትላንት የመሐመድ ጭፍራዎች በቤተ መቅደሳችን ጂማና ኢሉባቡር ላይ በስለት አረዱን ዛሬ የሉተር ቅጥረኞች ከውስጥም ከውጭም መሽገው በአባታቸው ዲያቢሎስ ምክር እየተመሩ ቤ/ክርስቲያንን ፈተኗት ያውም መቀነቷን እየሰረሰሩ፡፡
ለዚህ ሁሉ አሳልፈው የሰጡን ታዲያ እረኞቻችን ስለተኙ እኛም ምዕመናን የቤ/ክን አሳብ የማይገደን ስለሆንን ነው፡፡ ተግተው ባይጠብቁን ለእረኞቻችን ይቀርባቸዋል እንጂ፤ የኋላ ኋላ እነርሱን የሾማቸው የማያንቀላፋው ትጉኅ እረኛችን አምላክነ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወንም፡፡ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች እናንተ ታላቅ ሰማዕትነት ከፍላችኋል፡፡
ዛሬም እንደትናንቱ የ‹‹ተሐድሶ›› መናፍቃንን እጅ ለእጅ ተያይዘን እሰከመጨረሻው እንታገላቸዋለን የታጠቁትንም ዝናር ይጨርሳሉ እንጂ ቤ/ክንን እኛ ከተጋን አያጠፏትም፡፡
እኔ ሌሎችን ከመውቀሴ በፊት ራሴ ምን እየሠራሁ ነው? ልበል፤ አሁን የተጀመረውን ለውጥ ለቅድስት ቤ/ክን አንድነትና ለመልካም አስተዳደር መምጣት ተስፋ ስለጫረብኝ ከሚሠሩት ጋር ለመቆም ሁሌም ዝግጁ ነኝ… እስከሞት!፡፡ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው ለራሳችን ዘይት እንያዝ እንጸልይ እናልቅስ አምላካችን ይሰማናል፡፡
(አንድ አስተዋይ መምህር እንዳሉት ማኅሌት የማይቆሙ መክፈልተኞችን) ‹‹ይበቃችኋል እስኪ ደግሞ ሌላ ቢዝነስ ስሩ›› እንበላቸው፡፡ ውሻኮ በሩ እስኪዘጋበት ድረስ ከሥጋ ቤት አይርቁም! የቤታችንን በር እስከመቼ ክፍት እንተወዋለን? እባካችሁ ከአሁኑ ጀምረን ተግባራዊ ምላሽ እንስጥ የብሎግ ጀግናዎች ብቻ አንሁን ፤ በቤ/ክን ባሉ አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ እናድርግ… ሰ/ት/ቤት እንግባ አንድም ባዶ ወንበር አይኑር፡፡ በተሐድሶዎች የተደራጁ አንዳንድ የጽዋ ማኅበርተኞችን ‹ይሄ የእናንተኮ አይደለም› ብለን ጽዋውን እንቀበላቸው፡፡ ይሄን ማድረግ የምንችለው ከዳር ቆመን አይደለም፡፡ እንዲህ ካደረግን ይህ ጊዜ አልፎ ወርቃማ ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ አለኝ፡፡
እባክሽ እመ አምላክ ስደትሽን ራብሽን ለልጂሽ አስቢልን

cvv said...

fdvdfvdfvdvdf

Tamiru Z hawassa said...

እውነቱ ይህ ሆኖ እያለ
ነገር ግን የነዚህ ወሮበሎች ጥቂት ደጋፊዎች “ማ/ቅ እና የዩነቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው በድንጋይ ያባረሩን” ሲሉ አዳምጠናል፡፡
እባካችሁ እነ (አቶ በጋሻው፤ እቺግፍአየሁ(ኤልዛቤል)፤ አቶ ያሬድ) ቤተክርስቲያን መጉዳት አቁሙ ይበቃል! የግፍም እኮ ልክ አለው፡፡
ከዝቡ የታገሰው እናንተ እንደምታስቡት ቤተክርስቲያንን በጉልበት ማፅዳት አቅቶት አይደለም 10 የማትሞሉ አረሞች መንቀል አቅቶትም አይደለም፡፡
1ኛ ጥቂት የማየባሉ ባለማወቅ የተከተሏቹ የዋሃን እንዳይጎዱ ተብሎነው፡፡
እነሱም ቢሆን በሂደት ግብራችሁ የጥንት ጠላታችን የዳቢሎስ መሆኑን ሲረዱ(አሁንም እየገባቸው ነው) ፍፃሜያችሁ ይሆናል፡፡
2ኛ ህዝቡ ፈሪሃ እግዚአበሔር ስላለው እንደ እናንተ ደፋር ስላልሆነ( እግዚአበሔር ሲታገሳቹ ያልገባቹ) ቤቱን እግዚአበሔር ያፅዳ ብሎ በፀሎት ስለሚጠይቅ ነው፡፡

Anonymous said...

Lets stand for the better of our Mother Church!!!
people who are facing challenges around Awassa are a pioneers to say "NO!!!" for these arrogant peoples.
lets help them!!!
New day will come and we will c who they are very soon!!!

Anonymous said...

ወይ በጋሻው እና መሰሎችህ በቃ የተባለው ሁሉ እውነት ሆነ ያንን ያህል ስንወድህ ለካ እንደ እባብ ድርብ ቆዳ ለብሰህ ኖሮአል አሁን ደግሞ ጭራሽ ቤተክርስቲያንን ማመስ ጀመርክ? ምንስ የበደለክ ቢሆን ተሳድቤአለው አሁንም እቀጥላለው ካንተ ይጠበቃል? እግዚአብሔር ልቦናህን ያብራልህ!!!

Get said...

I am very depressed after I read the situation in Hawasa. It is the result of the poor administration in the church and ofcourse the mision of those tehadisos'. I think what we shall do is let's tell to the government that the money minded guys are trying to disturb the country and approprite measurs could be taken on those mafiya groups b/c the government is responsible to handle such acts. What surprises me is that should we be illegal to get our diginity? I think if we try to mobilize people the government will come saying that " Yedehininet guday". Please those security guys do what you shoul do otherwise the sielent people will never retair once they start fighting. Our Holy Fathers please be strong even still death and make us strong. Amilake Kidusan Yaberitachihu, Yabertan Amen.

DEREJE THE AWASSA said...

Dear Dejeselams
I am reading what you posted about the incidence at awassa. we People from Awassa new everything. your post is perfect. Everybody reading this site should trust Dejeselam, atleast on this issue. moreover we should acknowledge the Regional goverment and Police department for its action. but my worry is Begashaw and its followers who never worry about this Church. Begashaw is at Dilla today(Tuesday 09/11/2010) for organizing similar strike atDilla and Awassa. The government and The people of Awassa should Know this. He should be stopped. May God stopped him.
Lonlive Tewahido

mebrud said...

ወልደ ዮሐንስ ወንድማችን ግሩም ብለሃል፡፡
ቁጭት ብቻውን ምንዋጋ አለው?
እኔስ እንዲህ ብል ይሻለኛል፡፡
የምናደርገውን አናውቅምና አቤቱ ይቅር በለን፡፡
"አኮ በከመ ኀጢአትነ ዘገብረ ለነ
ወኢፈደየነ በከመ አበሳነ"
መዝሙረ ዳዊት
103፥10
እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

Dillu Ayqerim said...

የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩ ምንድን ነው ? ከቤተክርቲያኒቱ መሪዎች እስከ ተከታዮቹ (እኛ)የክርስትና እምነታችን ደካማ መሆኑ ኣይደለንም ? የመለያየት ምንጩ ፍቅር ማጣት ነው። የፍቅር ማጣት ምንጩ ደግሞ የእምነት ሕጸጽ ነው። <> እንላለን እንጅ እምነታችን በተግባር ሲፈተን ግን ባዶ ነው። <> (3ኛይቱ የዮሐንስ መልዕክት 1፡11)ታድያ ዛሬ ማን ነው በክፉው ፋንታ በጎውን የሚያደርገው? የቤተክርስቲያን መሪዎች ? ወይስ ተክታዮች እኛ? ተከታዮች እኛ ምዕመናን ከማን እንማር ? ተክታይ እኮ መሪውን ነው የሚከተለው። አይደለም እንዴ ? ባይሆንማ ኑሮ መሪና ተመሪ የሚባል ነገር አስፈላጊ ሁኖ አይሰራም ነበር። ዛሬ በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ፍቅር አለ ? ትህትና አለ ? በካህናትስ መካከልስ ፍቅር አለ?<< ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነብሰ ገዳይ ነው ። >> (1 ዮሐ. 3፡15)ታድያ ዛሬ ማን ነው ወንድሙን የሚወድ ?እንዲያው ብቻ በከመ ምሕረትከ ወአኮ በከመ አበሳነ እያልን ማለፉ ይሻላል እንጅ በስራችንስ ሁላችንም ወድቀናል።

Anonymous said...

የደጀ ሰላም ብሎግ ተሳታፊ ምዕመናን ሁላችሁ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡
በአዋሳ የተፈጠረው ግጭት በጣም እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎት እኛ ኦርቶዶክሳዊያንን ከአክራሪ ሰይፍ ሲጠብቀን የራሳችን ጥጋብ በፆምና በፀሎት ያልቀጣው ሥጋዊ ስሜታችን እየነዳን እርስ በእርስ ደማችንን ለመሰፋሰስ አበቃን ጉድ እኮ ነው!!
ደግሞ የገረመኝ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዛሬም ጭፍን አስተያየት መስጠታቸው ነው፡፡ ውይ ዛሬም በገአዱ ዘመን ሁሉም የሥራው ፍሬ ቁልጭ ብሎ በሚታይበት ዘመን ዛሬም ያልነቁ፣ ያልባነናችሁ ብርሃንን ከጨለማ ክርስቶስን ከቤልሆር መለየት የተሳናችሁ፡፡ ዛሬም ማኅበረ ቅዱሳንን የምታወግዙ የዋኅን ምእመናን እባካችሁ ቆም ብላችሁ ሁሉንም ነገር በጥሞና በአስተዋይ ልቦና ሁኑና ነገሩን ሁሉ ከምንጩ አጣሩ ከዚያም በደረሳችሁበት መረጃ በመነሳት አስተያየት ስጡ፡፡ አይሻልም የጅብ ችኩል እንዳይሆንባችሁ

በስመ ስላሴ አሜን
ብጹዕ አባታችን አቡነ ገብርኤል
በጣም በጣም እንወድዎ ነበረ ፡፡ ገና ከጅምሩ የማይገባ ስም ሰጥተዋቸው በቤተክርስቲያኒቱ ፈላጭ ቆራጭ አድርገውብን ብዙ ወንድሞቻችን የመናፍቃን አዳራሽን እንዲያደምቁ አድርገዋቸዋል፡፡ያኔ የነበረውን ሳንረሳ ዛሬ ተሳስቸቼ ነው በሚል ሌሎቻችንንም በማያስበረግግ እንደመቅረብ እነሱ ያነገቡትን የወንጌል ጠላትነት መፈክር በመድገምዎ እጅግ አዝነናል፡፡ መቼም ብቻዎትን ቤተክርስቲኒቱን ለመምራት አይመጡም፡፡ ከህዝብ ጋር ነው፡፡ ከሆነ ያለ ማዳላት የእነዚህን የጸረ ወንጌል ፈሪሳዊያንን መፈክር አንደማያዋጣዎት አውቀውት ወደ ጎን ትተው ሁላችንን በአንድ አይን ለማየት ልቦናዎን አዘጋጅተው ቢመጡ መልካም ነው፡፡ አለያ መካረሩ እየባሰ እንዳይሄድ ስጋቴን በገለልተኛነት ልነግርዎ እሻለሁ፡፡ መቼም ተወልደን ካደግንበት ሀገር ውጡ የሚለን አይኖርም፡፡ከኦርቶዶክሳዊያኑ አንዱ ነኝ፡፡ ከአዋሳ አረብ ሰፈር

ተክለስላሴ said...

ከሃዋሳ ነኝ ብለህ የጻፍከው ወንድም አስተውል እንጂ እኔም አንተም ያለነው ሃዋሳ ነው፡፡ ዝም ብለህ ረባሾቹ ባለሃብቶችና ማህበረቅዱሳን ናቸው ህዝቡን አይወክሉም ስትል ትንሽ እንኳን አትፈራም እንዴ? አንባቢዎቹ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ግን ከጥቂት ቤተክርስቲያንን እየመዘበሩ ካደጉና አሁንም እያራቆቱ ካሉት ከነ ያሬድ ወገኖች ውጭ የሁሉም የአዋሳ ህዝበ ክርስቲያን ጥያቄ መሆኑን ነው፡፡
አረ ለመሆኑአቶ ያሬድ በየካራቴ ቤቱ፡ በየ ወሹ ስልጠና ቤቱና የከተማ ወመኔዎቹን ሰብስቦ ህዝቡን ለማስደብደብ የመዘምራን ልብስ አልብሶ አውደ ምህረት ላይ ማቆም ከጀመረ መከራረሙንስ እኔና አንተ አናውቅም እንዴ?
በርግጥ አንተ ምናልባት የያሬድ አብሮ አደግ ወይም ደግሞ እውነቱን ያላወቅክ ልትሆን ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ህዝብ እየተደበደበና እየደማ እያየህና ይህንን ሳይት ምን ያህል ሰው ሊጎበኘው ይችላል? የአዋሳ ህዝቡስ አይታዘበኝም ወይ? ወዘተ፡ ሳትል ይህንን በመፃፍህ በጣም እናዝናለን፡፡ "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም" እንደሚባለው እንዳይሆንብህ በዚሁ ሳይት ላይ መልሰህ የኣዋሳን ህዝብ ይቅርታ በለው እልሃለሁ፡፡
ለሁላችንም አስተዋይ ህሊና ይስጠን፡፡
ከኣዋሳ ነኝ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)